HU Awada student info center @huawada Channel on Telegram

HU Awada student info center

@huawada


This channel provide you basic information about HU awada cumpas

HU Awada student info center (English)

Welcome to HU Awada student info center! Are you a student or looking to study at HU Awada campus? Look no further, as this Telegram channel, @huawada, is your go-to source for basic information about HU Awada campus. Whether you are a current student seeking updates on events, schedules, or important announcements, or a prospective student wanting to learn more about the campus facilities, programs offered, or admission requirements, this channel has got you covered. Stay informed and connected with the HU Awada community through this channel. Join us today and be a part of the HU Awada student info center!

HU Awada student info center

09 Jan, 09:22


ጉብኝቱ በተካሄደባቸው በዋናው ግቢ የመርከብ፣ ሲኒየርና ጁኒየር ካፍቴሪያዎች የተገኙ ተማሪዎች ከፍተኛ አመራሩ ለተማሪዎች የተዘጋጁትን ምግቦች ተገኝተው በመመልከታቸውና አብረው በመካፈላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው የዘንድሮው በዓል ለየት ያለ ድባብ ያለበት መሆኑን ገልጸዋል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

HU Awada student info center

09 Jan, 09:22


የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የበዓል ምሣ ከተማሪዎች ጋር ተጋሩ::
*//****
ታህሳስ 30/2017 ዓም
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊዎች እና የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንት ተማሪ እሰይ ጴጥሮስ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በዓሉን ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ለሚያከብሩ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የተሰናዳውን ምግብ በየምግብ አዳራሾቹ ተዘዋውረው ከተማሪዎች ተጋርተዋል።

ፕሬዚደንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ስለ ጉብኝቱ ሲያብራሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለረጅም አመታት ሲተገበር የነበረው የተማሪዎች የምግብ ሜኑ በበጀት ጫና ምክንያት አቅርቦት ላይ የነበረውን ችግር ለመቅረፍና ለማሻሻል ሌት ተቀን እየሰራን ነው ብለዋል:: የዛሬውን ዓመት በዓል ምክንያት  በማድረግ ዩኒቨርሲቲው በልዩ ሁኔታ ግብዓት ጨምሮ ተማሪዎቻችን የተሻለ እንዲመገቡ አድርገናል ያሉት ዶ/ር ችሮታው ተማሪዎች አብዛኛውን በዓላት ከወላጅ ቤተሰቦቻቸው ርቀው ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር የሚያሳልፉ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ቤተሰባዊ ስሜትን ለመፍጠር ዕለቱን አስመልክቶ ለየት ያለ የምግብ አይነት በማዘጋጀት ማቅረቡን እና እነሱም ከልጆቹ ጋር ምሣ መጋራታቸው ጥሩ የቤተሰብነት ስሜት እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ በበኩላቸው የጉብኝቱ ዋነኛ አላማ በዓሉን ከተማሪዎች ጋር በጋራ የማሳለፍና ቅርርብ የመፍጠር መሆኑን አንስተው ዩኒቨርሲቲው ሁሉም ሀገራዊ በዓላት በሚከበሩበት ወቅት ተመሳሳይ ዝግጅቶችን በማካሄድ በዓሉን የሚያከብሩ ተማሪዎች ባይተዋር እንዳይሆኑ ማድረግ ችሏል ብለዋል።

HU Awada student info center

09 Jan, 05:09


👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

07 Jan, 03:50


ውድ የኮሌጃችን ተማሪዎች፤የኮሌጃችን ማህበረሰብ፣ እና በተለይ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!

መልካም የገና በዓል 🎉🎉🎉

የተማ/መማ/ፕሬዝዳንት
ግሩም ገ/ሚ
👇👇👇👇
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

06 Jan, 18:01


Dear students,
I wish a Merry Christmas to all of you.

May  holiday brings a multidimensional success and peace for all of you in general and exit exam taking (GC of 2017 E.C)  students in particular.
Hopefully, Tomorrow we will have a wonderful Christmas  ceremony together.

Merry Christmas once again

Argaw A .(MA) in development of economics
Dean of the students
Awada college of business and Economics
Hawassa University

👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

04 Jan, 19:11


👉የጥንቃቄ መልዕክት

ከሰሞኑ የአንደኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተናን አስመልክቶ መነሻዉ ከምንና ከየት እነደሆነ ሳይታወቅ ፈተናዉ የሚሰጥበት ቀን መራዘሙን ተሳስተዉ ሌሎችን በሚያሳስቱ ግለሰቦች በስፋት አየተወራ ይገኛል። ይሁንና እስካሁን በኮሌጁ በኩል የፈተና መፈተኛ የጊዜ ሰሌዳዉ ላይ ምንም አይነት ለዉጥ ያልተደረገበትና አስቀድሞ በተገለፀዉ የጊዜ ሰሌዳ ማለትም (ከ ጥር 05 - 16) የሚሰጥ በመሆኑ ዉድ ተማሪዎቻችን ይህን አዉቃችሁ መነሻዉ በማይታወቅ የተሳሳተ መረጃ ተታላችሁ ሳትዘናጉ ለፈተናዉ አስፈላጊዉን ዝግጅት እንድታደርጉ አጥብቀን አናሳስባለን።

የሀ.ዩ.አ.ቢ.ኢ. ኮሌጅ የተማ/መማክርት
👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

02 Jan, 19:36


👉ከስምንት ዓመት በኋላ ተመልሷል⚽️

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 17-27/201 ዓ.ም ይካሄዳል።


የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል የዩኒቨርሲቲዎችን ተቋማዊ ግንኙነት ፤የተማሪዎችን ወንድማማችነት እና እህትማማችነት የሚያዳብር እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ተሳታፊ ዩኒቨርሲቲዎች በእግር ኳስ ፤በአትሌቲክስ ፤በአለም አቀፍ ቴኳንዶ ፤በቼዝ ፤ገበጣ እና ቡብ የስፖርት አይነቶች ዝግጅቶቻቸውን እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ አስተናጋጁ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተሳታፊ እንግዶቹን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅቱ እያጠናቀቀ ይገኛል ፡፡
ከስምንት አመት የእረፍት ጊዜ በኋላ እንደገና የጀመረው የስፖርት ፌስቲቫል በተማሪዎች መካከል መነቃቃትን የሚፈጥር እና ስፖርታዊ ተወዳዳሪነትን የሚጨምር እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ለጥቆማ 👉 https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

30 Dec, 05:35


የሃዘን መግለጫ
ታህሳስ 21/2017 ዓም

ሀ.ዩ አዋዳ ቢዝነስ እና ኢኮኖምክስ ኮሌጅ የተማሪዎች ህብረት በትላንትናው ዕለት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቦና ዙሪያ ወረዳ በተከሰተው አስከፊና አሳዛኝ በሆነው በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ስላጡ ወገኖች የተሰማውን መራር ሃዘን እየገለፀ ለተጎዱ ወገኖች ወዳጅ: ዘመድና ለቤተሰቦቻቸው እግዚአብሔር ፍጹም መጽናናትን እንድሰጣቸው ይመኛል!

የሀ.ዩ.አ.ቢ.ኢ ኮሌጅ የተማ/ህብረት

👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

29 Dec, 14:34


👇👇👇

https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

28 Dec, 06:30


ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  ከሰላም ሚኒስቴር የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት::
//
ህሳስ 18 ቀን 2017 ዓም

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኢ.ፌ.ድ.ሪ የሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በ2016 በጀት ዓመት በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በሀገር ግንባታ ስራዎች ላይ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡

የኢ.ፌ.ድ.ሪ የሰላም ሚኒስቴር "ብሄራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር: ሚዛን የጠበቀ ግንኙነት" በሚል ርዕስ ዛሬ በአዳማ ከተማ ባካሄደው የ2016 በጀት ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የክረምት ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም የስልጠናና የስምሪት አፈጻጸም ግምገማ እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ላይ ያተኮረ የባለ ድርሻ አካላት አውደጥናት ያካሄደ ሲሆን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ በዚሁ መድረክ ላይ ተገኝተው ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠውን የምስጋና ሰርተፊኬት ከሚኒስትሩ ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ እጅ ተቀብለዋል::

በመድረኩ የሁሉም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ የሰላም ሚኒስቴር ተጠሪዎች፣ የሁሉም ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን ለማወቅ ተችሏል::

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!
           
በዚህ ይከታተሉን:-
👇👇👇
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

28 Dec, 06:25


🩸ደም ይለግሱ ህይወትን ይታደጉ!!!🩸❤️🩸
:- የደም ልገሳ ፕሮግራም በአዋዳ ካምፓስ ከታህሳስ 21 እስከ 25 በይርጋለም ደም ባንክ አገልግሎት ለተማሪወች የተዘጋጀ አርስዎ ከ45 ኪሎ በላይ ከሆኑ ደምወን በመለገስ ደም አተዉ ለሚሞቱ እናቶች ይድረሱ!
🩸🩸ደም ልገሳ ታላቅ ሰብአዊ አገልግሎት ነዉ ደም ልገሳ የጾታ የዘር የትምህርት የሀይማኖት ልዩነት የማያደርግ የሁሉንም ህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ የሚጠይቅ ታላቅ ሰብአዊ አገልግሎት ነዉ።
ደም ከመለገስ የሚገኙ ጥቅሞች
🩸በሰብአዊ አገልግሎት ተሳታፊ ያደርጋል።
🩸 ታላቅ የህሊና እርካታ ይሰጣል።
🩸 የደም አይነት ያለክፍያ ማወቅ ያስችላል።
🩸 ሰወች በደም እጥረት ምክንያት አይሞቱም
🩸 የጤና ጠቀሜታ እንዳለዉ በአንዳንድ ምርምሮች ተረጋግጧል (ማለትም ደም የሚለግሱ ሰወች ከማይለግሱ ጋር ሲነፃፀር የድንገተኛ የልብ አደጋ Heart Attack) የመጋለጣቸዉ እድል አነስተኛ ነዉ።
ልበ ይበሉ!! ደም መለገስ ከ20-30 ደቂቃ ዉስጥ የሚከናወን ህይወት አድን ስራ በመሆኑ ጊዜ ይወስድብኛል ብለዉ አይጨነቁ!!
:- ይርጋለም ደም ባንክ አገልግሎት ከአዋዳ ካምፖስ ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ ታላቅ ሰብአዊ ተግባር ነዉ እርስወም ደምወን በመለገስ የዜግነት ግዴታወን ይወጡ።

👇👇👇
https://t.me/HUawada

https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

27 Dec, 16:26


ወደ መቶ ብር ከፍ ያለው የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት የተለየ ለውጥ ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም ተባለ

የዩኒቨርሲቲዎች በጀት 100 ብር ሆነ ማለት ድሮ ተማሪዎች ሲመገቡ ከነበረበት የምግብ አይነት የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዩኒቨርስቲዎች የምግብ በጀት በቀን ከ22 ብር ወደ 100 ብር መሻሻሉን ተከትሎ፤ ከሰሞኑ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች የምግብ ተመኑ ሲያድግ በተቃራኒው ግን የሚቀርበው የምግብ አይነትና መጠን ያነሰ በመሆኑ ቅሬታቸውን እያቀረቡ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ አሐዱም ይሄንን የተማሪዎች ቅሬታ በመያዝ ትምህርት ሚኒስቴርን አነጋግሯል።

በዚህም በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሰሎሞን አብርሃ በሰጡት ምላሽ፤ የምግብ በጀቱ 100 ብር ሆነ ማለት የግድ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት እንዳልሆነ ገልፀው፣ "የምግብ አይነቱም ሙሉ ለሙሉ አስደናቂ በሆነ መልኩ ይቀየራል ማለት አይደለም፣ ሊቀየርም አይችልም" ሲሉ ገልጸዋል።

ድሮውንም ተማሪዎች በተመደበላቸው 22 ብር ብቻ ሲመገቡ እንዳልቆዩ የሚገልጹት ዶ/ር ሰሎሞን፤ "ከፌዴራል መንግሥት የሚመደበው 22 ብር አነስተኛ መሆኑ ስለሚታወቅ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው አካሄድ ሲያስተካክሉ ቆይተዋል" ብለዋል።

አሐዱም "የትምህርት ሚኒስቴር ያደረገው ማሻሻያ በቂ ነው ወይ? አሁን ካለው የገበያ ሁኔታ ጋርስ ተመጣጣኝ ነው?" ሲል ዩኒቨርስቲዎችን ጠይቋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ የትምህርት ሚኒስቴር ለተማሪዎች የቀን ምግብ 22 ብር ቢመደብ፤ ከዛ በላይ ወጪ እንደበረው እና ተቋማቱ ለሌላ ሥራ የሚያገኙትን ገንዘብ ለምገባ የሚያውሉበት ሁናቴ መኖሩን ገልጸዋል።

"ዩንቨርስቲዎች በሚመደው 22 ብር ብቻ ተማሪዎቻቸውን አይመግቡም ነበር" ሲሉ ዶ/ር ሰሎሞን ያነሱትን ሃሳብ ተጋርተዋል።

"አሁን የተሻሻለው በጀት በተወሰነ ደረጃ ችግርን ይቀርፋል ተብሎ የሚጠብቅ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የተደረገው ማሻሻያ ቁጥሩ ትልቅ ቢመስልም ቀድሞ ሲወጣ ከነበረው ወጪ አንጻር ሲታይ አሁንም ተጽዕኖ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

በአንጻሩ ሌላው አሐዱ ያነጋገራቸው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ቶሎሶ ዳኒ፤ "አሁን ካለው የዋጋ ንረት አንጻር 22 ብር ተማሪዎችን መመገብ አይችልም ነበር፡፡ በተደረገው ጥናት መሰረት ወደ መቶ ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል" ያሉ ሲሆን፤ የተመደበው በተማሪ 100 ብር በቂ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

በንጽጽር ሲታይ ቀድሞ ከነበረው 22 ብር ወደ መቶ ብር ከፍ መደረጉ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ መሆኑን አንስተዋል።

ዶ/ር ሰሎሞን የዩንቨርስቲዎቹን ፕሬዝዳንቶች ሃሳብ ሲያጠናክሩ፤ ዩኒቨርስቲዎች ከሚመደብላቸው የተለያየ በጀት እያዟዟሩ በቀን ከ80 እስከ 150 ብር በማውጣት ተማሪዎችን ሲመግቡ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ከመሻሻሉ በፊት አንድ እንጀራን እስከ 24 ብር ድረስ የሚገዛ ዩኒቨርስቲ እንደነበረ ጠቅሰው፤ "ድሮ ይመደብ የነበረው በጀት አንድ እንጀራ እንኳን በቅጡ የማይገዛ ነበር" ሲሉ አክለዋል።

በመሆኑም ይህ አካሄድ የዩኒቨርሲቲዎችን እንቅስቃሴ ስላስተጓጎለና የአሰራር ስርዓታቸው ላይም ችግር ስለፈጠረ፣ የምግብ ሜኑ ሲዘጋጅ ጥናት ተጠንቶ ሀገር አቀፍ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ጭምር በአካል በተገኙበት የዩኒቨርሲቲዎች ምግብ ማሻሻያ መደረጉን ለአሐዱ ተናግረዋል።

አክለውም ተማሪዎች አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ማድረግ ያለባቸው የሚመደብላቸው በጀት በአግባቡ ለእነርሱ መድረሱን እና በቀን የመቶ ብሩ በጀት ተሰልቶ በሳምንት 700 ብር ወጪ መደረጉን፣ እንዲሁም ያንን ወጪ ታሳቢ ያደረገ ሜኑ መቅረብና አለመቅረቡን ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ህብረት አደረጃጀትም ሀላፊነት በመውሰድ በአግባቡ መከታተል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።

🎙[ዘገባው የአሀዱ ራዲዮ ነው]

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

HU Awada student info center

27 Dec, 07:52


የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ማኔጅመንት አባላት ሳምንታዊ የስራ ምልከታ አደረጉ።

👇👇👇
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

27 Dec, 07:24


🩸ደም ይለግሱ ህይወትን ይታደጉ!!!🩸❤️🩸
:- የደም ልገሳ ፕሮግራም በአዋዳ ካምፓስ ከታህሳስ 21 እስከ 25 በይርጋለም ደም ባንክ አገልግሎት ለተማሪወች የተዘጋጀ አርስዎ ከ45 ኪሎ በላይ ከሆኑ ደምወን በመለገስ ደም አተዉ ለሚሞቱ እናቶች ይድረሱ!
🩸🩸ደም ልገሳ ታላቅ ሰብአዊ አገልግሎት ነዉ ደም ልገሳ የጾታ የዘር የትምህርት የሀይማኖት ልዩነት የማያደርግ የሁሉንም ህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ የሚጠይቅ ታላቅ ሰብአዊ አገልግሎት ነዉ።
ደም ከመለገስ የሚገኙ ጥቅሞች
🩸በሰብአዊ አገልግሎት ተሳታፊ ያደርጋል።
🩸 ታላቅ የህሊና እርካታ ይሰጣል።
🩸 የደም አይነት ያለክፍያ ማወቅ ያስችላል።
🩸 ሰወች በደም እጥረት ምክንያት አይሞቱም
🩸 የጤና ጠቀሜታ እንዳለዉ በአንዳንድ ምርምሮች ተረጋግጧል (ማለትም ደም የሚለግሱ ሰወች ከማይለግሱ ጋር ሲነፃፀር የድንገተኛ የልብ አደጋ Heart Attack) የመጋለጣቸዉ እድል አነስተኛ ነዉ።
ልበ ይበሉ!! ደም መለገስ ከ20-30 ደቂቃ ዉስጥ የሚከናወን ህይወት አድን ስራ በመሆኑ ጊዜ ይወስድብኛል ብለዉ አይጨነቁ!!
:- ይርጋለም ደም ባንክ አገልግሎት ከአዋዳ ካምፖስ ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ ታላቅ ሰብአዊ ተግባር ነዉ እርስወም ደምወን በመለገስ የዜግነት ግዴታወን ይወጡ።

👇👇👇
https://t.me/HUawada

https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

20 Dec, 18:00


የፍጻሜ ጫወታ ተካሄደ
።።።።።።።።።።።
11/04/2017
አዋዳ ይርጋለም

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተማሪዎች በትምህርት ክፍሎች መካከል ላለፉት ሁለት ተከታታይ ሳምንታት ሲያደርጉት የነበረውን የእግርኳስ ውድድር በዛሬው እለት ፍጻሜውን አግኝቷል።

በዛሬው የፍጻሜ ጫወታ የሎጂስቲክስና ስሳፕላይ ቼንማናጅመንት ትምህርት ክፍል ከማናጅመንት ክፍል ጋር ያገናኘ ሲሆን በሎጂስቲክስና ስሳፕላይ ቼንማናጅመንት ትምህርት ክፍል የበላይነት 2 ለ 1 ተጠናቋል። ይህንንም ተከትሎ የሎጂስቲክስና ሳፕላይ ቼን ት/ት ክፍል ለተከታታይ ሁለት አመት የኮሌጁ ሻንፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።

በዕለቱ የማጠቃለያ መርሀግብር ከኮሌጁ ዲን ዶ/ር ወገኔ ማርቆስ ሻንፒዮኑ የሎጂስቲክ ቡድን የዋንጫ ሸልማቱን ተረክቧል። በተመሳሳይ ሁለተኛ ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁት የማናጅመንት ት/ት ክፍል ቡድን የኮሌጅ ማ/ዳይሬክተር አቶ ዘውዴ መኮንን ሽልማት ስጥተዋል።

HU Awada student info center

12 Dec, 20:06


#Update #MealMenu

ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተመሳሳይ የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ይፋ ተደርጓል‼️

ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ያስተላለፈው የተማሪዎች የምግብ ሜኑ መግለጫ 👇

<በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች የተመደበው ዕለታዊ የምግብ በጀት በየጊዜው እየጨመረ ያለውን የምግብ ዋጋ ንረት ሊሸፍን ባለመቻሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ጥናት በማካሄድ በጀቱ እንዲሻሻል ለመንግስት ጥያቄ በማቅረብ የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ በጀት ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 (መቶ ብር) እንዲሆን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በቁጥር መከ/0-721/1 በቀን 25/03/2017 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን አሳውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በወጥነት እንዲከናወን ሚኒስቴር መስሪ ቤታችን ከምግብ ተመን ማሻሻው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት 3 ገጽ አባሪ በማድረግ የላክን መሆኑን እየገለጽን ይህ የምግብ ሜኑ ዝቅተኛውን መስፈርት መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ተቋማት ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ተማሪ ሳምንታዊ ወጪው ከ700 (ሰባት መቶ) ብር ባልበለጠ መልኩ ስራ ላይ መዋል ያለበት መሆኑን አሳስባለሁ፡፡> (ሚንስትር ዴኤታው)

[የምግብ ሜኑውን ከምስሉ ይመልከቱ]

👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

11 Dec, 11:14


https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeZmvNdhvDD30Xhs3dR8qHcfEFQL7d0UTQD-XA5tYUwpcl7cw/viewform?usp=sf_link

HU Awada student info center

09 Dec, 10:08


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።


ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው።

ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ያደረገ ሲሆን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል። በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን በባለሙያዎች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ወቅታዊ የምግብ ዋጋ ንረትን ግምት ውስጥ በማስገባት የምግብ በጀት ማሰተካከያ መደረጉን ገልጸዋል።

ዶ/ር ሰለሞን አክለውም በሀገራችን ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ያለው የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ጠቁመዋል።

#MoE
👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

08 Dec, 09:54


👇👇👇

https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

07 Dec, 20:01


የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ተደረገ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ለገንዘብ ሚኒስቴር የፃፉት ደብዳቤ 👇

< ከመ/ቤታችሁ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር 1/143/150/17 በተጻፈ ደብዳቤ አሁን በስራ ላይ ያለው የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ከወቅቱ የገበያ ዋጋ አኳያ ተማሪዎችን ለመመገብ በቂ ባለመሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት በማካሄድ የተመን ማሻሻያው እንዲፈቀድ መጠየቃችሁ ይታወሳል:: የቀረበውን የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት ከወቅቱ የገበያ ዋጋና ከመንግሥት የመክፈል አቅም አኳያ በማየት የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን በቀን በአንድ ተማሪ የነፍስ ወከፍ ወጪ 100 ብር (አንድ መቶ ብር ) ሆኖ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተወስኗል።

በዚህም መሰረት የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በወጥነት እና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲከናወን መስሪያ ቤታችሁ ከምግብ በጀት ተመን ማሻሻያው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ዩኒቨርስቲዎች አንዲጠቀሙበት እና በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ክትትል እንድታደርጉ በጥብቅ አስታውቃለሁ፡፡ >


👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

27 Nov, 05:06


#አዋዳ  #ይርጋለም #bertatgeneration #ብርቱ_ትውልድ

" ከጠበቅነው በላይ ብዙ ታዳሚ የነበረበት....በምወደው ከተማ ይርጋለም በተማርኩበት በአዋዳ ካምፓስ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ደረጃ የተዘጋጀ ደማቅ እና ልዩ ፕሮግራም ነበር!

በ2024 የነበረን የመጨረሻው Bertat Genration  ፕሮግራም ነው! በቀጣይ አመት ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ላይ የሚቀጥል ይሆናል.....በአዋዳ ካምፓስ እስከ 2025 መግቢያ ድረስ ዘወትር አርብ በቅንዲል አማካኝነት በሚዘጋጀው መድረክ አጋር ሆነን እንቆያለን።" ሀና ሀይሉ


#Berchiinc #Abriminds

https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

23 Nov, 09:51


"እጅግ በጣም አመሰግናለሁ! #ይርጋለም #አዋዳ " ሀና ሀይሉ

"በትላንትናው እለት እኔን እንዲሁም የስራ አጋሮቼን በልዩ ሁኔታ አቀባበል ካደረጉልን  የቢታኒያ ኮሌጅ አስተዳደር ጋር በቀጣይ አብረን መስራት የሚያስችለንን የጋራ ጉዳይ በመነጋገር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመናል።

ስላደረጋችሁልን አቀባበል ፣ስለምሳ ግብዣው እንዲሁም ስለፍቅራችሁ ከልብ እናመሰግናለን!"

HU Awada student info center

22 Nov, 04:03


በየክላሱ ስንዞር የነበረው ስለ እህታችን ሀይሚ መታከሚያ ከእናንተ ከእህት ወንድሞቿ የተሰበሰበው ብር ጨርሰን ልከንላታል ።ከልብ እናመሰግናለን።

HU Awada student info center

22 Nov, 04:03


በየክላሱ ስንዞር የነበረው ስለ እህታችን ሀይሚ መታከሚያ ከእናንተ ከእህት ወንድሞቿ የተሰበሰበው ብር ጨርሰን ልከንላታል ።ከልብ እናመሰግናለን።

👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

21 Nov, 19:14


https://vm.tiktok.com/ZMh7jsUpX/

HU Awada student info center

20 Nov, 20:51


Exciting Event Invitation for All Students!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

We are thrilled to invite all students to an exciting event that promises to be both fun and enriching!

Join us for an unforgettable experience filled with activities, networking, and opportunities to connect with others.

Details:
Date: 14/03/2017
Time: 2:30 morning
Location: Awada campus

👇👇👇

https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

18 Nov, 20:15


ውድድሩ ተጀምሯል!

ቅዳሜ ህዳር 14

ለቲክቶክ ተጠቃሚዎች  🎊🎉

ስለፕሮግራሙ ማስታወቂያ ወይም ከ21 አመት በታች ያሉ ወጣቶች መጠጥ እንዳይጠጡ የሚናገር content በቪዲዮ ለሚሰሩ ሰዎች እስከ ቅዳሜ ማለዳ ብዙ  view ያላቸውን በማወዳደር ለ3 ሰዎች 2000 - 10,000 ብር ተሸላሚ  ይሆናሉ ።

ውድድሩ ተጀምሯል!

ይሄንን ሀሽ ታግ መጠቀም ግዴታ ነው
#bertatgeneration
#berchiinc #abriminds

👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

18 Nov, 15:09


https://t.me/qindeal

HU Awada student info center

18 Nov, 12:38


አዲስ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች እንኳን ወደ ልህቀት ማዕከሉ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን መልካም የትምህርትና የስኬት ዘመን እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን!

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

HU Awada student info center

18 Nov, 12:37


ዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ።
**//*
ህዳር 9 ቀን 2017 ዓም
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ4,500 በላይ የሚሆኑ የ2017 ዓም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎቹን ከዛሬ ጀምሮ እየተቀበለ ነው::

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት ከተማሪዎች አገልግሎት ዲን ፅ/ቤት እንዲሁም ከካምፓስ ፀጥታና ደህንነት አካላት ጋር በመቀናጀት ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች አቀባበል እያደረጉ ነው::

የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ከጸጥታና ደህንነት እንዲሁም ከምግብና መኝታ አገልግሎት ጋር የተያያዘ ሰፊ ዝግጅት በዩኒቨርሲቲው ሲካሄድ መቆየቱን ገልጸው ተማሪዎቹ በዋናው ግቢና በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እንደተመደቡ ተናግረዋል:: ም/ፕሬዝዳንቱ ልጆቻቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲው ይዘው የመጡ ወላጆችም ሆነ ተማሪዎች ያለምንም ስጋት በአቀባበል ኮሚቴው አባላት የሚሰጣቸውን መመሪያ በመከተል አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ለተማሪዎቹም እንኳን ደህና መጣችሁልን ብለዋል::

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተማሪዎች አገልግሎት ም/ዲን መ/ር ዳሞት ተስፋዬ በበኩላቸው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የብዙ አዳዲስ ተማሪዎች የቅድሚያ ምርጫ ከሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ እንደመሆኑ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን አጠቃላይ የተማሪዎች አገልግሎቱና የካምፓስ ቆይታው የተሻለና ሰላማዊ እንዲሆን በትጋት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ሀሳባቸውን የሰጡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከመምጣታቸው በፊት የቀድሞ ተማሪዎችን መረጃ መጠየቃቸውን ገልጸው ጥሩ ግብረ መልስ በማግኘታቸው ዩኒቨርሲቲውን መርጠው መምጣታቸውን ተናግረዋል:: እስከአሁን ያለው አቀባበልም አስደሳች ሆኖ እንዳገኙት ገልፀዋል።

HU Awada student info center

17 Nov, 10:35


👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

16 Nov, 09:31


የፊታችን ቅዳሜ በሀዋሳ ዪኒቨርስቲ አዋዳ ካምፓስ በሚዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የምትገኙ ተማሪዎች እዚህ ላይ እንድትመዘገቡ በአክብሮት እንጠይቅለን!

መግቢያ ነፃ ሲሆን በዚህ ሊንክ መመዝገብ ግን ግዴታ ነው!
ሊንኩ ላይ ከተመዘገቡ ስሞች መርጠን በእለቱ ለብዙ ሰዎች የሞባየል ካርድ የምንሸልም ይሆናል!

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ!

https://docs.google.com/forms/d/1cySXjy0Qs7GVnyDrciM8l38gDZNtCfmqivE3XcOfJ7Q/edit

👇👇👇

https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

15 Nov, 15:36


Update...
Postponed to Monday and Tuesday

HU Awada student info center

15 Nov, 04:35


ታዋቂ አርቲስቶች ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች በተገኙበት....

📌የፊታችን  ቅዳሜ ህዳር 14 ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ
🤝 አብሪ ማይንድስ ከበርቺ ጋር በመተባበር ልዩ የሆነ ዝግጅት
📍በሀዋሳ ዪኒቨርስቲ አዋዳ ካምፓስ ትልቁ አዳራሽ!

በዚህ ዝግጅት ላይ በመገኘት ብቻ ሽልማቶችን ያገኛሉ።🎁🎁

በእለቱ ጨዋታ ፣ ሽልማት ፣ ሙዚቃ ፣ አነቃቂ ንግግር ፣ ኪነ ጥበብ ፣ ውዝዋዜ ፣ ቴያትር ተዘጋጅቷል!

የዚህ ፕሮግራም ዋና አላማ 🛑 ከ21 አመት በታች ያሉ ወጣቶች መጠጥ እንቢ እንዲሉ እና እንዳይጠቀሙ የሚያበረታታ ነው።


ለቲክቶክ ተጠቃሚዎች  🎊🎉

ከላይ ያለውን ሀሳብ ተጠቅማችሁ ስለፕሮግራሙ ማስታወቂያ ወይም ከ21 አመት በታች ያላችሁ ወጣቶች መጠጥ እንዳይጠጡ የሚናገር content በቪዲዮ ለሚሰሩ ሰዎች እስከ ቅዳሜ ማለዳ ብዙ  view ያላቸውን በማወዳደር ለ3 ሰዎች 2000 - 10,000 ብር ተሸላሚ  ይሆናሉ ።
ውድድሩ ከዛሬ አርብ ይጀምራል
ይሄንን ሀሽ ታግ መጠቀም ግዴታ ነው
#bertatgeneration
#berchiinc #abriminds

👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

12 Nov, 15:55


⚙️LOST ID:

Name :Temesgen Assefa Ayele

Department : Economics (4th)

Id No: 1131/14

👉ያገኛችሁ ተማሪዎች ከታች ባለዉ አድራሻ ትሰጡኝ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ ።🙏

Phone No : 0965980175 📞
:0701003496📞

HU Awada student info center

09 Nov, 16:23


👇👇👇

https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

06 Nov, 12:09


please share for your's friends.

👇👇👇
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

31 Oct, 20:14


የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የአዋዳ ካምፓስን ጎበኙ::
**//**
ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
በተ/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ የተመራው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ቡድን ዛሬ በአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የጉብኝትና ውይይት መርሃግብር አካሂደዋል::

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ወገኔ ማርቆስ አመራሮቹን ሲቀበሉ ስለ ኮሌጁ ታሪካዊ ዳራ: አሁናዊ ቁመናና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ከሌሎች ኮሌጆች ለየት የሚያደርገው ደግሞ ኮሌጁ ሦስት ቦታዎች ላይ ማለትም ሀዋሳ ዋናው ግቢ: አዋዳና አለታወንዶ ላይ የሚሰራ በመሆኑ ለአስተዳደር ትኩረት የማጣት ብሎም ለክትትልና ድጋፍ የማያመች መሆኑን ጠቁመዋል:: እንደ መልካም ዕድል ከተነሱ ነጥቦች መካከል ደግሞ የሚሰጣቸው የትምህርት መስኮች በጣም ተፈላጊ መሆናቸው እና በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተማሪ የሚያስተናግድ መሆኑን አንስተዋል::

የከፍተኛ አመራር ቡድኑ በግቢው ውስጥ ያሉ የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በአካል ከጎበኙ በኃላ ከኮሌጁ አመራሮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከኮሌጁ አመራሮችና መምህራን ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ሦስቱም ምክትል ፕሬዝዳንቶች በየዘርፉ ምላሽ ሰጥተዋል::

በመጨረሻም ተ/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ በኮሌጁ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል ከልብ አመስግነው ኮሌጁ ለዩኒቨርሲቲው የራስገዝነት ጉዞ ትልቅ ድርሻ ከሚወስዱት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው የማጠቃለያ ሃሳብና የስራ መመሪያ ሰጥተዋል::

ዶ/ር ችሮታው መንግስት ለዩኒቨርሲቲዎች በየዓመቱ እጅግ ከፍተኛ በጀት መድቦ ቢያስፋፋም ብቁና ተወዳዳሪ ምሩቃን ከማፍራትና ችግር ፈቺ ምርምሮች ሰርቶ ስር ነቀል ሃገራዊ ለውጥ ከማምጣት አንፃር የሚጠበቀውን ውጤት ሊያመጡ ስላልቻሉ በትክክል እንዲያመጡ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት በተወሰኑ

HU Awada student info center

31 Oct, 20:14


የትኩረት መስኮች ላይ ጥራትን መሰረት ያደረገ ልየታ ማድረጉን አስታውሰው አሁን ግዜውን የዋጀ አሰራር ለመዘርጋት ያሉትን ሁሉ የትምህርት ፕሮግራሞች ይዘን መቀጠል ስለማንችል በአጭር ግዜ ውስጥ በጥናት ላይ የተመረኮዘ የፕሮግራም ክለሳ ይደረጋል ብለዋል:: እንደተባለው ዩኒቨርሲቲ መምሰል: ራሳችንን ለመቻል ከፍተኛ ጥረት ማድረግና ተወዳዳሪ ሆኖ ፈተናውን ለማለፍ እጅ ለእጅ ተያይዘን በጥንቃቄ መስራት አለብን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል::

ስለራስገዝነት ስናስብ ማወቅ ያለብን መንግስት ማንንም ያለአግባብ ሥራ የማሳጣት ዓላማ ኖሮት ሳይሆን ሁሉም ብቁና ተወዳዳሪ ሆኖ በተቀመጠበት የስራ መስክ ውጤታማ መሆን ካልቻለ ከውድድር የሚወጣበት አሰራር መዘርጋት ላይ እያተኮረ ነው ያሉት ተ/ፕሬዝዳንቱ አሁን የአስተዳደር ሰራተኛ ብቻ ሳይሆን በአግባቡ ማስተማር ያልቻለ መምህር: ውጤታማ ያልሆነ ማንኛውም ሰው በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ቦታ አይኖረውምና ሁሉም ኃላፊነቱን አውቆ በየደረጃው በህግ ተጠያቂነት ስሜት ስራውን ካልሰራ ከሲስተም እንዲወጣ እናደርጋለን ብለዋል:: እጁ ንፁህ ሆኖ ሕጋዊ አሰራርን ብቻ ተከትሎ ካልሰራ ማንኛውም ሰው ከተጠያቂነት እንደማይድን አስተዳደሩም ህገወጥነትን እንደማይታገስ ተ/ፕሬዝዳንቱ አስምረውበታል::

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

24 Oct, 19:20


Hello Dear Hawassa university Students .This opportunity is only for GC Students,Hence we have limited places you're expected to register faster.
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdALU8YSyBXCJlDJpS09xpbX3AjAW_F7AE0jT5s6YqdGrVL5Q/viewform

HU Awada student info center

22 Oct, 07:58


Dears, please help others to join HU Career Development Center. Notices will be shared over this channel.

HU Awada student info center

18 Oct, 19:18


በዛሬው እለት ሀ/ዩ/አ/ቢ/ኢ/ ኮሌጅ 2ኛ አመት ለሁሉም ድፓርትመንት ተማሪዎች የኮሌጁ ዲን የሆኑት ዶ/ር ወገኔ ማርቆስ፤የተማርዎች አገልግሎት ረዳት ዲን አቶ አርጋዉ አመሎ፤የኮሌጃችን የተለያዩ የስራ ዘርፍ ሀላፊወች እና የተማሪዎች መማክርት በተገኙበት ስለ ኮሌጃችን አጠቃላይ ሁኔታ ውይይትና ገለፃ ተደርጓል።

👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

16 Oct, 09:41


Campaign schedule

HU Awada student info center

16 Oct, 09:41


👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

16 Oct, 09:41


📣 Hey, Hawassa University! 📣

Exciting events in partnership with Dereja!

🗓 Dates & Times:

Thursday, October 17 | 2:00 PM
Friday, October 18 | 2:00 PM
Saturday, October 19 | 2:00 PM
ARE YOU #GC2025? Don’t miss out on the opportunity to elevate your career journey! 🚀

See you there!

HU Awada student info center

15 Oct, 04:49


GC Birthday🎂

እነሆ ጊዜዉ ደርሶ እኛም ባለጊዜ ሆነን የአዋዳ የበኩር ልጅ ልንሆን ዘመን መጣ!!

በብዙ ወጣቶች ልብ ላይ በማይጠፋ ቀለም ተፅፎ ዘላለም በሚኖረዉና የወጣትነት ዘመን ድንቅ ማስታወሻ በሆነዉ የጊቢ Life ላለፉት 3 አመታት በሳቅ እና ለቅሶ፣ በመዉጣትና መዉረድ ብሎም በልዩ ልዩ ፈተና እና ድል ታጅበን ያለፍንበትን፣ ከዶርም ጎደኞቻችን ጋር ሰብሰብ ብለን የሳቅንበትንና፣ ከክላስ ጀለሶች ጋር ያሳለፍናቸዉን አይረሴ ቀናት እና የአዋዳ ድንቅ ትዉስታ በትዝታ እየዘከርን፤ የዘንድሮዉን የታላቅነትና የከፍታ ዘመን በድንቅ መንገድ ልናከብር ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 16 ተቀጣጥረናል። በዚህ ልዩ ዕለት የጨዋታ፣ የመዝናኛ እና የPhoto ኘሮግራሞች ተዘጋጅተዋል። በዕለቱም ወንዶች እንደ ንጉስ ልጅ የምትለብሱት፣ ሴቶች እንደ ልዕልት ደምቃችሁና አጊጣችሁ የምትታዩበት ድንቅ T-Shirt ተዘጋጅቷል። ከእናንተ የሚጠበቀዉ ከዛሬ ጀምሮ በየክላሱ በተመደቡ አስተባባሪዎች በኩል 300 ብር በመክፈል መመዝገብ ብቻ ነዉ።

ሁላችሁም ተሳተፉ ተመዝገቡ, ጥቅምት 16 ዕለተ ቅዳሜ አይቀርምምም!!

(አስተባባሪ ኮሚቴ)

👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

14 Oct, 19:04


በሀዋሳ ዩንቨርስቲ በአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የሎጅስቲክና ሳፕላይ ቼይን ማኔጅመንት የ3ኛና 4ኛ ዓመት ተማሪዎች  አድስ ወደ ድፓርትመንቱ የተመደቡ የ2ኛ ዓመት ተማሪዎችን የካምፓሱ አካዳምክ Dean ,የLSCM Head,የፕሮግራሙ የክብር ስፖንሰር የBitania B&T ኮሌጅ Dean,የLSCM መምህራን ,እንድሁም የተለያዩ ዕንግዶች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

👇👇👇
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

04 Oct, 13:15


BAGA AYYAANA IRREECHAA

መልካም የኢሬቻ በዓል!

#Irreechaa  #Ethiopia  #ኢትዮጵያ  #ኢሬቻ

https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

02 Oct, 12:02


https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

HU Awada student info center

02 Oct, 09:32


ለኮሌጅ ካውንስል አባላት ስልጠና ተሰጠ
።።።።።።።።።።
21/01/2017
አዋዳ

ዕቅድና ሪፓርት አዘገጃጀትን መሰረት በማድረግ አዲሱን የቁልፍ አመላካቾችንና የአፈጻፀም ውል ላይ ለኮሌጁ ካውንስል አባላት ስልጠና ተሰጥቷል።

https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada
https://t.me/HUawada

1,823

subscribers

532

photos

5

videos