ህዳር 11/2017 ዓ.ም (ት.ሎ.ሚ)ኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2024 አለም አቀፍ ዓውደ ርዕይ እና ሲምፖዚየም እና የአፍሪካ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (PIDA WEEK) መርሃ ግብር አፈጻጸም ላይ በመርሃ-ግብሮቹ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት እንደ ተገለፀው ከህዳር 13- 20/2017 ዓ.ም የሚካሄደው ኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2024 ዓውደ ርዕይ እና ሲምፖዚየም በሁዋጃን ቀላል ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚካሄድ ሲሆን የአፍሪካ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (PIDA WEEK) መርሃ ግብር ከ ህዳር 16-20/2017 /November 25-29 / በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
ኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2024 የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አስካለ ተክሌ ሁነቱ አረንጓዴ ትራንስፖርት አረንጓዴ ኢነርጂ, ፣ አረንጓዴ ኢኮኖሚ!/ Green transport Green energy, and Green economy/ በሚል መሪ ቃል የሚከበር መሆኑን ገልጸዉ ይህም ኢትዮጵያ እንደሀገር በአረንጓዴ ልማት ላይ እያደረገች ያለዉን ተግባር የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለማበረታታት በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የተደረጉ የታክስ ማበረታቻዎች አስታዉሰዋል፡፡
ሙሉ ዜናው👇
https://www.facebook.com/100068876633464/posts/pfbid02vXm3QFveDcjWGRJbBiugoiRnUwbs3aSQsh2kJr5xTaDiSMFMfZfs4GaFbwnp3Qx8l/?app=fbl