Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ @healthtipsbydrsarayohannes Channel on Telegram

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

@healthtipsbydrsarayohannes


ይህ የቴሌግራም ገጽ ጤናን የሚመለከቱ ጉዳዮች የሚቀርቡበት ነው። በተጨማሪም በYouTube https://youtube.com/@Sarayohannes_444?si=KLp_A8Mu5sNOzgMW Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

Dr. Sara Yohannes Health Tips (Amharic)

የሰርዝ የጤናና ጥንቃቄዎች በእናንተና በትምህርት እንዲሁም በትምህርት ላይ ለተወቅተው እናት ወንድማችን መምሪያ ሰጡ። በዚህ ቦታ ከቡሌት ባለቤት ሳራ ዮሃንስ ትእዛዞችን እና ቅሬታዎችን በትምህርት ያክልሉ። እናት ወንድማችን በእኛ የሚሰማበት አገልግሎት በማስታወቅ ይመልከቱ። ለተጨማሪም በYouTube በታች ሳራ ዮሃንስ በተጨማሪም ይደውሉ። https://youtube.com/@Sarayohannes_444?si=KLp_A8Mu5sNOzgMW

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

02 Feb, 21:12


https://youtu.be/2ND9yzHCMyQ?si=1G85ldnsUnx7avxL

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

19 Jan, 13:22


📌ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ።

መልካም በአል

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

06 Jan, 22:03


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሠላም አደረሳችሁ፣መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ።

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

05 Jan, 08:01


📌በመሬት መንቀጥቀጥ (earth quake) ጊዜ መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች፦

በአዋሽ ፈንታሌ እና አጎራባች አከባቢዎች ለወራት የቆየ እና የመንቀጥቀጥ ምጣኔው (richter scale) እየጨመረ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ (earth quake) እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል። ንዝረቱም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች እና አከባቢዎች እየተሰማ ይገኛል።

🎯የመሬት መንቀጥቀጥ ጥንቃቄዎች፦

1. በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች፦

🛐በህንፃዎች ውስጥ እያለን በሚያጋጥምበት ጊዜ በመጀመርያ እራስን ማረጋጋት እና ባለንበት መቀመጥ ያስፈልጋል።

🛐ከጠረጴዛ፥ ዴስክ፥ ወይም አግዳሚ ወንበር ስር መደበቅ።

🔕ጭንቅላት ጉልበት ስር በማሳረፍ ጎንበስ ማለት እና አይናችንን በመጨፈን ጆሯችንን መድፈን።

የምንደበቅበት ጠረጴዛ ከሌለ የህንፃ የውስጠኛው ግድግዳ ከውጫዊው ግድግዳ የመደርመስ አደጋው የቀነሰ ስለሆነ ከውስጠኛው ግድግዳ ስር መቀመጥ።

🏢በቀላሉ ሊደረመሱ እና ሊወድቁ ከሚችሉ ከደረጃ፥ ከመደርደርያ፥ ከመስኮት እና ከመሳሰሉ አካባቢዎች አስር ጫማ (10 feet) መራቅ።

🚷ሊፍት እና ደረጃን ተጠቅሞ ለመሸሽ እና ከህንፃ ለመውጣት አለመሞከር። የመሬት መንቀጥቀጡ እስኪቆም (usually seconds) ድረስ አለመሮጥ፥ አለመንቀሳቀስ እና ከመንቀጥቀጥ በኃላ ለሚፈጠር ንዝረት (after shock) መዘጋጀት።

🔥በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ የሚፈጠር የእሳት አደጋ የተለመደ ስለ ሆነ ብሎም የመሬት መንቀጥቀጥ የእሳት አደጋ ማስጠንቀቅያ ደወል እና አሳንሰር እንዳይሰራ ስለሚያደርግ እሳት አደጋ መከሰቱን በንቃት ማስተዋል እና ለመሸሽ ደረጃን መጠቀም ያስፈልጋል።

🔕በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ ውጭ ከሆንን ባዶ ቦታ ላይ በመቀመጥ ከዛፍ፥ ህንፃ፥ የኤሌክትሪክ ፖል እና በመውደቅ እና በመፈናጠር አደጋ ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ።

🚗መኪና ውስጥ ከሆንን ውስጥ መቆየት እና ለመውጣት አለመሞከር።

2. ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ።
ለምሳሌ፦ ቤት ውስጥ ሊወድቁ የሚችሉ እንደ ጠረጴዛ፥ መጽሐፍት መደርደርያ፥ ጠረጴዛ እና የተሰቀሉ እቃዎች በአስተማማኝ ሁኔታ ጠብቀው መቀመጣቸውን ማረጋገጥ።

🏢ከተቻለ ህንፃዎች እና መኖርያ ቤቶች ለመሬት መንቀጥቀጥ መቋቋማቸውን ማረጋገጥ።

🧰የድንገተኛ አደጋዎች የሚያገለግሉ የህክምና ቁሶች (first aid kits), disaster kits, and earth quake specific kits ለምሳሌ፦ የእጅ መብራት፤ ጠንካራ ጫማ (ከስከስ) እና የአደጋ ኮፍያ (helmet) መያዝ ያስፈልጋል።

🚷አደጋ አድራሽ ከሆኑ ህንፃዎች፥ ተራራ እና ድንጋያማ ቦታዎች፥ ትላልቅ ዛፎች፥ የኤሌክትሪክ ፖሎች እና የመንገድ ዳር መብራቶች መራቅ እና ባዶ ሜዳ ቦታ ላይ መቆየት።

Stay still, stay safe!

Source:
Earthquake Precautions
https://www.mcasiwakuni.marines.mil/Emergency-Preparedness/Earthquake-Precautions/

ዶ/ር የማነ ገብረመድህን: የድንገተኛ እና ጽኑ ህሙማን ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

27 Dec, 19:56


https://youtu.be/EzTii-cDMP0?si=_zOpMD6RNO0gmekC

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

24 Dec, 02:06


📌ሺሻ በዉሀ ስለሚጣራ አይጎዳም?

በአንድ ወቅት አንዲት ታካሚዬ በናይት ክለቦች ዉስጥ ሺሻን እንደምታጨስ ምክንያቱም "ሺሻ በውሃ ስለሚጣራ ጎጂ ንጥረ ነገሮችን እንደሚያስወግድም" ነግራኛለች። ነገር ግን ጥናቶች ምን ይናገራሉ ስለ ሺሻ፡-

1. መርዛማ ኬሚካሎች፡- የሺሻ ጭስ እንደ ካርቦን ሞኖክሳይድ፣ ታር እና ካርሲኖጂንስ ያሉ ጎጂ ንጥረ ነገሮችን በውሃ ውስጥ ካለፉ በኋላም በውስጡ ይዟል።

2. ከፍተኛ የካርቦን ሞኖክሳይድ መጠን አለው፡ ተጠቃሚዎች ብዙውን ጊዜ ከሲጋራ አጫሾች የበለጠ ካርቦን ሞኖክሳይድ ወደ ውስጥ ስለሚተነፍሱ የልብና የደም ቧንቧ አደጋን ይጨምራሉ።

3. ሱስ፡- በሺሻ ውስጥ ያለው ኒኮቲን ሱስን ሊያስከትል ይችላል በተለይ ለረጅም ጊዜ በማጨስ።

4. ከፍ ላለ ጭስ መጋለጥ፡ በአንድ ጊዜ ቆይታ ሰዎች ሺሻ ሲነፉ ከ100 ሲጋራዎች ጋር እኩል ለሚሆን ጭስ ሊያጋለጡ ይችላሉ።

5. ሰከንደሪ ስሞከር፡- አንድ የማያጨስ ሰው በአቅራቢያው በሚያጨሱ ሰዎች ምክኒያት ለጎጂ ኬሚካሎችም ይጋለጣል ስለዚህም ሁለተኛ አጫሽ ሊባል ይችላል በእጁ ባይነካም።

6. ኢንፌክሽኖች፡ የሽሻ ማጨሻዎችን መጋራት እንደ ሳንባ ነቀርሳ፣ ኮቪድ እና ሄፓታይተስ ላሉ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል።

ስለዚህ ሺሻ "አይጎዳም አሪፍ ነው" የሚለው ሀሳብ ሙሉ በሙሉ የተሳሳተ ነው። ይህንን የተሳሳተ ግንዛቤ ለመቀየር እና ስለ ጤና ስጋቱ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይህን ሀሳብ እናጋራ።

ዶ/ር ይቅናሸዋ ሰለሞን (የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

13 Dec, 05:45


የጨጓራ መቀደድ

የጨጓራ መቀደድ ብዙ ጊዜ ከቆየ የጨጓራ ህመም የተነሳ የሚመጣ የህመም አይነት ነው

አጋላጭ ሁኔታዎች

🔹 እድሜ ከ60 ዓመት በላይ
🔹 ሲጋራ ማጨስ
🔹 ብዙ ጊዜ የቆየ የጨጓራ ባክቴሪያ
🔹 ለረጅም ጊዜ የህመም ማስታገሻ በተለይም NSAID የሚባሉትን መጠቀም
🔹 ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት
🔹 ከመጠን ያለፈ የአልኮሆል መጠጥ መጠጣት
🔹 የጨረር ህክምናዎች

ምልክቶቹ

🔸 ድንገተኛ የሆነ የላይኛው ሆድ አከባቢ ያለ ህመም። ይህ ህመም ወደ ጀርባ የሚሠራጭና እየባሰ የሚሄድ አይነት እና ቀና ብሎ መሄድ የማያስችል ይሆናል
🔸 የሆድ መነፋት፣ ማስመለሰ፣ ማቅለሽለሽ
🔸 የሰውነት ሙቀት መጨመር፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ማንቀጥቀጥ
🔸 ራስን መሳት፣ ትንፋሽ ማጠር እና ጉልበት ማጣት

🔻 እነኚህ ምልክቶች ካሉብዎት በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የጤና ተቋም በአፋጣኝ በመሄድ ህክምናውን ያግኙ

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል

📍አድራሻ - በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6

ለበለጠ መረጃ ፡ 
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

07 Dec, 13:45


https://youtu.be/ZEAf5LvItlA?si=JY9QeKP_m3HhBMQu

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

03 Dec, 07:36


https://youtu.be/Vj9ZeMiqxrI

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

22 Nov, 17:12


የመድኃኒት ደህንነት ማስጠንቀቂያ

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን RELIEF የሚባል ሕገወጥ መድኃኒት (በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት እንዳለው ይገመታል) በኢትዮጵያ ገበያ እየተዘዋወሩ መሆኑን ተደርሶበታል።

ይህ መድኃኒት በሕጋዊ መንገድ በባለስልጣን መስሪያ ቤታችን ያልተመዘገበ በመሆኑ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ አይታወቅም።በተጨማሪም ፣ የዚህ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ ተቅማጥ ፣ የሆድ ህመም ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ ድካም፤ የእይታ መዛባት፤ መፍዘዝ ፣ ራስ ምታት ፣ የቆዳ ሽፍታ ፣ የጉበት ኢንዛይሞች መጨመርና ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል የኩላሊት ጉዳትን ያጠቃልላል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህንን መድኃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም ከባድ የጉበት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ የመያዝ እድልን ከፍ ሊያደርግ ይችላል።


በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን መድኃኒት ከመጠቀም እንዲቆጠብ እያሳሰብን መድኃኒቱን በአካባቢዎት ካገኙ በነጻ ስልክ ቁጥር 8482 ደውለው ለኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ባለስልጣን ወይም ለክልል ጤና ተቆጣጣሪ አካላት እንዲጠቁሙ በአክብሮት እንጠይቃለን።

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

19 Nov, 21:00


Diaper Dermatitis
የዳይፐር ሽፍታ ከዳይፐር ጋር ቀጥተኛ ንክኪ ያላቸዉ ቦታዎች አካባቢ የሚወጣ ሲሆን

መንስኤዎች
🔹ኢንፌክሽን (እንደ ፈስገስ ፣ ባክቴሪያ)
🔹አለርጂ / የቆዳ መቆጣት
🔹ጥቃቅን መላላጦች

አጋላጭ ሁኔታዎች
🔹የበዛ እርጥበት (ዳይፐር ቶሎ አለመቀየር)
🔹ሰገራ እና ሽንት ዉስጥ ባሉ ንጥረ ነገሮች ምክንያት ሚፈጠር
🔹ከፍተኛ በሆነ ተደጋጋሚ ተቅማጥ ምክንያት ሚፈጠር

❗️ የፎርሙላ ወተት የሚጠጡ ህፃናት ጡት ከሚጠጡ ህፃናት የበለጠ ተጋላጭ ናቸዉ::

መፍትሔ
🟠 ለልጅዎ የተወሰነ ግዜ ከዳይፐር ነፃ የሆነ ግዜ መስጠት
🟠 ሰገራ ካለ ወዲያዉ ዳይፐር መቀየር
🟠 ያልተስማማ ዳይፐር ወይም ዋይፕስ(wipes) ካለ መቀየር
🟠 ለብ ባለ ዉሀ ቀስ ብሎ ማፅዳት
🟠 ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ እንደ በሽታዉ ሁኔታ የተለያዩ ህክምናዎችን ማድረግ፡፡

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል
📍አድራሻ - በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6
ለበለጠ መረጃ ፡ 
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

08 Nov, 13:39


🚨ውድ እህታችን ያሳጣን አደገኛ ህመም ምን ይሆን? 🚨

👉እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው ::ብዙ እናቶች ከወሊድ በኃላ የሳንባ ደምስሮች ውስጥ በሚከሰት የደም መርጋት በህክምና አጠራሩ Pulmonary embolism ምክንያት ሂወታቸውን ያጣሉ :ውድ እህታችንም ያለፈችው በዚህ እጅግ አደገኛ ችግር እንደሚሆን እገምታለሁ ::

👉የዚህ ችግር ምልክቶቹ ምንድናቸው?
🩺ሰላም በነበረ ሰው ላይ በድንገት የሚከሰት የትንፋሽ መፍጠን እና ማፈን ዋነኛው እና በብዛት የሚታየው ምልክት ነው  96%)
🩺የልብ ምት መፍጠን
🩺ሳል እና የደረት ህመም
🩺ትኩሳት :ማላብ
🩺አክታ ያለው ሳል
🩺ራስን በድንገት መሳት
🩺ባት አከባቢ ህመም ያለው እብጠት
🩺ዋነኞቹ ምልክቶች ናቸው :እነዚህ ምልክቶች ከሳንባ ምች

👉የተጠቀሱት ምልክቶች ሙሉ በሙሉ ሊከሰቱ እንደማይችሉ ማስተዋል ይገባል :ስለዚህ በዋነኛነት ድንገተኛ የትንፋሽ መፍጠን ወይም ማፈን ሲከሰት አስቀድሞ ይሄንን ችግር ማሰብ ብልህነት ነው

👉የዚህ ችግር ምልክቶች ከሳንባ ምች ምልክቶች ጋር እጅግ በጣም ስለሚመሳሰሉ: የምልክቶቹን ድንገተኛነት እና የሚያጋልጡ ነገሮችን አስተውሎ ምርመራ ማድረግ እና ውጤቱ ከመምጣቱ በፊት ጀምሮ በፍጥነት ሕክምናው ካልተጀመረ ገዳይ ሊሆን የሚችል ከባድ ህመም ነው ::

👉ለዚህም ችግር የሚያጋልጡ ነገሮችምንድናቸው?
 
🌟አጋላጭ ምክንያቶች በተለይ በሀገራችን የምርመራ ደረጃ ላይታወቁ ይችላሉ ነገር ግን የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው :-

🩺በተለያየ ምክንያት ለቀናት እንቅስቃሴ ሳያደርጉ አልጋ ላይ መተኛት :

🩺ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ የተደረገ ከፍተኛ ቀዶ ጥገና ካደረጉ ወይም የተከሰተ አደጋዎች :በተለይ በእግር እና ዳሌ አጥንት ላይ

🩺ባለፈው ወር ውስጥ አራት ሰዓት እና ከዛ በላይ የፈጀ ጉዞ ተደርጎ እንደሆነ

🩺እርግዝና ወይም ወሊድ

🩺በአፍ የሚዋጡ የወሊድ መከላከያዎች

🩺ካንሰር የልብ በሽታ  በተለይ የልብ ምት መዛባት (Atrial fibrillation ) ስትሮክ እና መሰል ለረጅም ጊዜ ሚቆዩ በሽታዎች (Chronic disease?

🩺ኢንፈክሽኖች

🩺 ደም ትክክለኛ የቅጥነት መጠኑን ጠብቆ እንዲዘዋወር የሚያደርጉ ቅመሞች እጥረት

🩺ከዚህ በፊት በእግር ወይም በሳንባ ውስጥ የደም መርጋት አጋጥሞ ከሆነ

🩺ማጨስ ወዘተ ናቸው

👉👉እንዴት መከላከል ይቻላል?

🩺ወሊድ ወይም ከማንኛውም ቀዶ ጥገና ወይም ህመም በኃላ በፍጥነት እንቅስቃሴ መጀመር!

🩺 አልጋ ላይ የሚያስተኛና እንቅስቃሴን ፈፅም የሚያግድ ህመም ከተከሰተ በሐኪም የሚታዘዙ የደም ማቅጠኛ መድሃኒት (Heparin, Enoxaparin) መውሰድ

🩺 ኮምፕሬሽን ስቶኪንግ ወይም ተለጣች ካልሲ ማድረግ (ግፊት በመፍጠር ደም እንዲዘዋወር እንዳይረጋ ስለሚረዳ)

🩺በቂ ፈሳሽ መጠጣት

🩺ረጅም ጉዞ ላይ በየሰዓቱ እንቅስቃሴ ማድረግ

🩺መኝታ ላይ እግርን ከፍ አድርጎ መስቀል ናቸው

👉ሕክምናው ምንድነው?

🩺እንደተጠቀሰው ምልክቱ እጅግ በጣም አሳሳች በመሆኑ ምልክቶቹን በአንክሮ በማስተዋል ይሄንን ችግር መጠርጠር እጅግ መሰረታዊ ጉዳይ ነው ምክንያቱም ሰዓታት ባለፉ ቁጥር ውጤቱ መጥፎ ይሆናል ስለዚህ በተቻለ መጠን ሐኪሞች እና የምርመራ መሳሪያዎች ወዳሉበት ሆስፒታል መሄድ ወሳኝ ነው

🩺ችግሩ እንደተጠረጠረ በፍጥነት የደም ማቅጠኛ መድሃኒት መስጠት እና እንደታካሚው አካላዊ ሁኔታ እስከ ፅኑ ህሙማን ክትትል ክፍል (ICU ) ድረስ የሚያስፈልግ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ ናቸው

🩺የችግሩ አጋላጭ ምክንያት ከታወቀ ታካሚው ተሽሎት ከሆስፒታል ሲወጣ ከ 3-6 ወር ድረስ የደም ማቅጠኛ መድሃኒቱን መቀጠል ያስፈልጋል :አጋላጭ ምክንያቱ ካልታወቀ ወይም ምክንያቱን ዓክሞ ማዳን የማይቻል ከሆነ ላልተወሰነ ጊዜ ወይም እድሜ ልክ መድሃኒቱ መቀጠል አስፈላጊ ይሆናል ::

በዶ/ር አበራ ኢታና

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

06 Nov, 15:47


#ጥንቃቄ🚨

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት የጨቅላ ህፃናት እንዳይጠቀሙት የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳስቧል፡፡

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት ኖቫርቲስ ፋርማ ሽዌይዝ AG/ Novartis Pharma Schweiz AG በተባለ የገበያ ፍቃድ ባለው የመድኃኒት አምራች ፋብሪካ የሚመረት ነው።

ቴግሬቶል (ካርባማዜፔይን) 100 mg/5ml Oral Suspension (OS) የተሰኘው መድኃኒት አብዛኛውን ጊዜ አጠቃላይ ለሚጥልና ከፊል መንቀጥቀጥ/ management of generalized tonic clonic and partial seizures ለማከም የሚያገለግል ነው።

ይሁን እንጂ የተጠቀሰው መድኃኒት በውስጡ በሚይዘው ፕሮፓይሊን ግላይኮል (propylene glycol) የሚባል ንጥረ-ነገር መጠን ምክንያት ለጨቅላ ሕፃናት ማለትም ከ4 ሳምንታት በታች ለሆኑ ሕፃናት ወይም በሶስት ወራት የመወለድ ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት ሊወስዱት እንደማይመከር ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

ተቋሙ ፥ በዚህ ምርት ውስጥ ከሚገኙት ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነው ፕሮፓይሊን ግላይኮል ለምግብ እና ትንባሆ ምርቶች እንዲሁም ለፋርማሲዩቲካል እና መዋቢያዎች በአጠቃላይ በአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (FDA) ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ይታወቃል ብሏል።

ይሁንና በዚህ ምርት ውስጥ ያለው መጠን በዚህ የማሳወቂያ መልዕከት ላይ ከተጠቀሱት ለጨቅላ ሕፃናት እና ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ ከደህንነት ገደብ በላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ነው ያለው።

ስለሆነም ይህንን መድኃኒት በጨቅላ ሕፃናት ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ መጠቀም ጉዳቱ ከጥቅሙ የሚያመዝን በመሆኑ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች መድኃኒቱን ለተጠቀሱት የእድሜ ክልል ከማዘዝ እና ከማከፋፈል እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ህብረተሰቡም መድኃኒቱን እንዳይጠቀም መልዕክት አስተለልፏል።


#SHARE

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

27 Oct, 09:52


📌የወባ በሽታ/Malaria 📝

👉 አብዛኛውን ጊዜ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የሚታይ በሽታ ሲሆን መንስኤውም ፕላስሞዲየም የሚባል ፕሮቶዞዋ ጀርም ነው።
👉 በሴቷ የወባ ትንኝ (Female Anopheles mosquito) አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል።
👉 በተለያዩ ነገሮች ምክንያት ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ተጋላጭ ናቸው።
👉 ምልክቶቹም ትኩሳት፣መንቀጥቀጥ፣ድካም፣ማላብ፣የራስ ምታትና ራስን መሳት ናቸው።
👉 እነዚህ ምልክቶች ከታዩ በአስቸኳይ የጤና ተቋም ሄዶ መመርመር ያስፈልጋል።
👉 ህጻናትና ነፍሰ ጡር ሴቶች ላይ ህመሙ ስለሚበረታና መዘዞቹም የከፋ ሊሆኑ ስለሚችሉ በአስቸኳይ በሀኪም መታየት ይኖርባቸዋል።

📍 ዝናባማ በሆኑ ወቅቶች ላይ ስለሚከሰት ለወባ ትንኝ መራቢያ የሚሆነውን የታቆረ ውሀ ካለ ማስወገድ ይገባል።

📍የወባ በሽታ ወዳለበት ቦታ ከመጓዝዎ በፊት መከላከያ መድሀኒት ስለሚሰጥ ሀኪምዎን ያማክሩ።

📍በአልጋ ዙሪያ የትንኝ መከላከያ አጎበር መጠቀምና Insect repellant creams መቀባት ከትንኝ ንክኪ ይከላከላል።

መልካም ቀን
ስለጤናዎ ይወቁ
በዶ/ር ሳራ ዮሐንስ

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

18 Oct, 09:36


ወቅታዊ ጉንፋን እና ጉንፋን መሰል የመተፈንሻ አካላት ህመም በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
_______________
የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።
ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ሙከስ መምብሬን” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡
ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።
የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል። ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣ ማስነጠስ፣ አይን ማሳከክ እና መቅላት፣ ማስታወክ፣ ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣ ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።
በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከ2003 ዓ ም ጀምሮ የእንፍሉዌንዛ እና መሰል የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች እየተሰራ ይገኛል። ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል1፡፡ በተጨማሪም የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡
ጉንፋን መሰል በሽታን ከምንከላከልባቸው መንገዶች መካከልም የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) በማድረግና በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት እና የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በ952 እና 8335 ነጻ የስልክ መስመር መደወል የሚቻል መሆኑን እያስታወስን ሕብረተሰቡ ሊከተላቸው የሚያስፈልጉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን አስመልክቶ ዝርዝር መግለጫ እና መረጃዎችን በየጊዜው የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።
ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

06 Oct, 19:07


#ATTENTION🚨

ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ? መደረግ ያለበት ጥንቃቄስ ምንድነው ?

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ምን አሉ ?

" ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ወይ ? የሚባለው ሰሞኑን በሙሉ ይሄን አይነት ንዝረቶች ነበሩ።

መሬት መንቀጥቀጥ መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን መተንበይ አይቻልም።

ስለዚህ ሊከሰት ይችላል ሊመጣ ይችላል። ይሄ ሁል ጊዜ በተለይ አዲስ አበባ የምንኖር ሰዎች ነቅተን የምንጠብቀው ነገር መሆን አለበት።

ስምጥ ሸለቆና የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ነቅተን የምንጠብቀው ነገር ነው መሆን ያለበት።

ለጊዜው መናገር የምችለው ከበድ ያለ ነገር ከመጣ አይመጣም ብለን ነው የምንገምተው ከመጣ ግን ምን መደረግ ስለለበት ጥንቃቄ ነው።

➡️ የቤት ቋሚዎች በተለይ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ ያሉ ሰዎች ኮለኖች አካባቢ መጠጋት ለምን መውረድ ሊከብድ ይችላል ቁልፍ ማክፈትም ሊከብድ ይችላል። ስለዚህ ኮለኖች አካባቢ መጠጋት።

➡️ ከተቻለ ጠረጴዛ ስር መግባት።

➡️ ሊፍት አትጠቀሙ። ማንም ሰው በሊፍት ለመውረድ እንዳይሞክር። ያን እንዳትጠቀሙ።

ይሄን ይሄን ጥንቃቄ ማደርግ ያስፈልጋል። ነገር ግን አሁን ባለው እዚህ ደረጃ የሚያደርስ ከባድ ነገር አለ ብለን አንገምትም። "

#Ethiopia #AddisAbaba

@tikvahethiopia

1,148

subscribers

186

photos

15

videos