ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia @guzoethiopia Channel on Telegram

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

@guzoethiopia


ጉዞ ኢትዮጵያ በሀገራችን ያሉ ተፈጥሯዊ ፣ ሀይማኖታዊ ፣ታሪካዊ እና ሰው ሰራሽ መስህቦችን የሚያሰጎበኝ ድርጅት ነው።

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia (Amharic)

ጉዞ ኢትዮጵያ በሀገራችን ያሉ ተፈጥሯዊ ፣ ሀይማኖታዊ ፣ታሪካዊ እና ሰው ሰራሽ መስህቦችን የሚያሰጎበኝ ድርጅት ነው። ጉዞ ኢትዮጵያ የታክስ በረሃና ጉባኤዎችን በማገኘት እና የሰላም ነገሮችን በማገኘት እንዲሰጡኝ ያስተምሩና በአንድም ላይ እናገኝትን ማወቅ እንዳለን እንጠቀማለን። ጉዞ ኢትዮጵያ የዚህ ድረ-ገጾችን ስኬሉን በመለዋወጥ አንደኛው ቅኝ ስለጉዞ ኢትዮጵያን ስለሚወዱ እና በሚቀጥለው ስኬል ከቃለመጠይቅ ስለመፍታት እንዲሁም ለሁላችን በመከላከል ባለፈው ጊዜ ሀገር እንዲሁም አንደኛው ሰፈሩን በአገልግ ለመለዋወጥ እንዲሆን የQ&A መልእክታችንን ላኩ።

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

19 Jan, 19:18


የሁሉ አስገኚ ሲሆን በባሪያዉ እንጅ ለመጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ወረደ  የተቀበረ የሞት ደብዳቤአችንን ሻረ ዘላለማዊ ልጆቹ እንሆን  ዘንድ ተጠመቆ አሳየን አብ በደመና የማፈቅረው ልጄ እረሱ ነዉ ብሎ የመሰከረለት መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ እርግብ የወረደለት  የልእልናችን መሰረት የነፍሳችን ቤዛ መድኅን ዓለም ክርስቶስ ለአርአያነት በማዬ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠመቀ ።
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ ።

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

07 Jan, 09:56


አዳም የተመኘዉን አምላክነት ያገኘበት ሰማያዊው የማይመረመረዉ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን የተቆጠረለት እየገፋነዉ የወደደን እየራቅነዉ የቀረበን ለመዳናችን ተስፋ  የልጅነትን ጸጋ የሰጠን  የዘለለም ሕይወት ይሆነን ዘንድ እነሆ መድኃኒት የሆነዉ ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሄም ከቅድስት ድንግል ማርያም ከላይ ሳይጎድል ከታች ሳይይጨመር ተወለደ ። የተናቁት እረኞች ከመላእክት ጋር ዘመሩ ።
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ መልካም በዓል ይሁንልን ።

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

11 Dec, 16:29


ኑ የበረከቱ ተካፋይ እንሁን ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ክበረ በዓለን በጋራ እናክብር ።

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

03 Feb, 13:21


http://m.besiegesniff.top/6e90XgJBRFZISFRIfBRXBSYxNVMnXXEoc09dQAooCwQ8NiIHbAQwHlA1JzwOFy4MRVo5VigxazAcDGATO0cqdCELEAseRR8cTg0p&p=uyiftg&_mi1675430447363

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

13 May, 11:48


የጥንቱ አዲስ አበባ ❤️❤️❤️

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

19 Mar, 19:01


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 10 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

13 Feb, 18:00


ታላቅ መንፈሳዊ የበረከት ጉዞ

#ወደ_እመጓ_ኡራኤል_ገዳም

የጉዞው ዋጋ #500 የምግብና አልጋን ጨምሮ
ወደጉዞው ስንሄድ የምንመለከታቸው ቦታዎች በጥቂቱ

#ደብረብርሀን ስላሴ
#ደብረብርሀን አርሴማ
#አርባ ሀራ መድሀኔ አለም
#ቆጵሮስ ተራራ ፅዋው የተቀመጠበት ቅዱሱ ተራራ
#ክናሊ ተራራ እመቤታችን የፀለየችበት
#ዘብር ገብርኤል

ይህ ቦታ ካሉት ቃልኪዳኖች በጥቂቱ

#ቦታውን የረገጠ 7 ትውልድ ይማርለታል
#ተረከዙላይ በስውር ማህተብ ሲኦልን እንደማያይ ይፃፍለታል
#ከላዮ ላይ በስውር ያሉበት መንፈሶች ይወገድለታል

የዚህ በረከት ተካፋይ መሆን ምትፈልጉ ከስር ባሉት ስልኮች በመደወል አናግሩን
+251910455701
+251913162292


መነሻ ቀን የካቲት 12 አርብ
መመለሻ የካቲት 14 እሁድ
አዘጋጅ ማህበረ ኡራኤል (የእመጓ ኡራኤል ገዳም)

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

05 May, 11:05


ለአርበኞች ቀን እንኳን አደረሳችሁ።

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

20 Jan, 11:27


እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

08 Jan, 12:49


ከላይ ሳይጎድል ከታች ሳይጨመር ከቅድስት ድንግል ማርያም ስለእኛ ተወለደ።
መልካም የልደት በዓል ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች ይሁንልን።

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

25 Dec, 16:38


በጃፓን ኦሎምፒክ ወቅት የጠፋው የአበበ ቢቂላ ቀለበት ከ55 ዓመታት በኋላ ለቤተሰቦቹ ተመለሰ
****************************

እኤአ 1964 በተካሄደው በጃፓን ኦሎምፒክ ወቅት አበባ ቢቂላ የቶኪዮ ማራቶን ውድድርን ባሸነፈበት ውድድር ወቅት የጠፋው ቀለበት ለቤተሰቦቹ ተመለሰ፡፡

የጠፋው የአበበ ቀለበት በወቅቱ በፅዳት ስራ ላይ በነበረች ጃፓናዊት እጅ እንደነበረ እና ከ55 ዓመታት በልጇ አማካኝነት ለአበበ ቤተሰቦች መመለሱ ነው የተገለፀው፡፡

በወቅቱ አበበ ቢቂላ ቀለበቱን በእስታዲዮም መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ረስቶት መውጣቱ ስታዲየሙን በማጽዳት ስራ ላይ የነበሩት ባረክ እናት አግኝተውት ለአበበ ቢቂለ እንዲሰጠው ለልጃቸው እንዳስረከቡት ሚስተር ባረክ ተናግሯል፡፡

በወቅቱ የ19 ዓመት ልጅ የነበረው ሚስትር ባረክ ለግማሽ ክፍለ ዘመን የዘለለ አደራ ይዞ በዕድለኝነት ስሜት የአበበን ቤተሰብ ይቅርታ በመጠየቅ ቀለበቱን አስረክቧል፡፡

የአበበ ቤተሰብም ይቅርታውን በመቀበል ቀለበቱን ተቀብለዋል፡፡
Via Etv

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

24 Dec, 15:08


The 10 wonders of the world, as chosen by team Wanderlust

ታዋቂው የእንግሊዝ የጉዞና ቱሪዝም መጽሔት Wanderlust በትላንትናው ዕለት በዓለም የሚገኙ 10 አስደናቂ ቦታዎችን ዝርዝር ይዞ ወጥቷል፡፡ ከአስሩ የዓለም አስደናቂ ቦታዎች ውስጥ #በኢትዮጵያ የሚገኙት Danakil Depression በ3ኛ ደረጃ ላሊበላ ደግሞ በ9ኛ ደረጃ በዝርዝሩ ተካተዋል፡፡ ላሊበላ ከ8ቱ የዓለም አስደናቂ ቦታዎች ውስጥ አንዱ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

የዓለም አስደናቂ ቦታዎችን ለማየት https://www.wanderlust.co.uk/content/wonders-of-the-world-wanderlust?fbclid=IwAR0a9aPFI3pGTyyDXbefQe8ZfM4j_AmMxheoyjrNcf4uOyW8BLZWFf0JyZU

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

23 Dec, 20:32


ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሳተላይት ምስል ግዢ ጥያቄ ለኢትዮጵያ አቀረቡ!

ኢትዮጵያ "የሳተላይት ምስል" ሽያጩን በራሷ መመሪያ መሠረት ከገዢ ሀገራት ጋር ውል በመፈፀም መሸጥ እንደምትጀምር የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲቲዩት ይፋ አድርጓል። የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት የሰው ሃብትና ቴክሎጂ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት የሳተላይቷን ቁጥጥርና መረጃ አሰባሰብ ተመልክተዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራቸውን በማኖራቸው የኢንስቲትዩቱን ሰራተኞች አመስግነዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ኢትዮጵያን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ባለብዙ ተልዕኮ የሳተላይት መረጃ መቀበያ ተከላ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል። የመቀበያ አንቴናው ሀምሳ ሴንቲ ሜትር የምስል ጥራት እና እስከ አምስት የሚደርሱ የሳተላይቶችን መረጃ በአንድ ጊዜ መቀበል የሚያስችል ነው።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ሰለሞን በላይ ኢትዮጵያ ሳተላይት ባመጠቀች በአራት ቀናት ውስጥ ብቻ ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሳተላይት ምስል ግዢ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ታህሳስ 10 ያመጠቀቻት ሳተላይት የታሰበላትን ቦታ ይዛ ስራዋን በአግባቡ እየሰራች መሆኑ ተገልጿል። ሳተላይቷ በቀን አስራ አራት ጊዜ በተዘጋጀላት ምህዋር እየዞረች መረጃ የምትሰበስብ ሲሆን በቀን አራት ጊዜ ደግሞ የሰበሰበችውን መረጃ የመቀበል ስራ ይሰራል፡፡ በቀጣይ የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ግንባታ እንደሚጀመርና በዘርፉ የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡

(MinT)
via tikvahethiopia

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

20 Dec, 10:29


እንኳን ደስ አለሽ ኢትዮጵያዬ