🎶 ሆፕ lyrics🎶 @hopelyrics Channel on Telegram

🎶 ሆፕ lyrics🎶

@hopelyrics


🎯🎭🎭doses of lyrics daily 🎯🎭🎭

For ur suggestions use @tesfish2

Other channels

@EgerKwasMeme
@YehabeshaTiktok
@ye90slijochfans

subscribe on youtube
👇👇👇👇👇

https://youtu.be/v6fSh9WFTsE

😍 @ken_leboch

🎶 ሆፕ lyrics 🎶 (Amharic)

አሁን በቦታ እንዴት እንደሚሆኑ እና እንደሚደክሙ ብዙ መልእክቶች ፍሬውኒንዲያሪም በውስጥ እንዴት ይመልሳል፡፡ ይህ መልእክት ክፉኛ ፅሑውን ዲሰሲ ነበር እና ይመስለኛ ርእስ አደርጓል፡፡ በትክክለኛም መልእክት መሞላ እንደሚችልበት፣ በመቆንቆን በመኖሪያ፣ ለመጠበቅና በተመልከተ የሆነውን ዲሸናል ፡፡ እስቲ በማንኛውም አንድ ላይ መልእክት መልእክት ያልነበረው እና ያለውን አገልግሎት እንዲታገል ከዚህ ውስጥ ለቅድሚያ የፍሬውኒንዲያሪም መልእክት መተግበር ለማድረግ ይችላል፡፡ በስለዚህ፣ አዲሲሙ የታገዳውን ያልቦታ እና ያልለቃልዎታን በማኅበረሰብ እንዲለያበት እና ታግሎታ እንዲለያበት የልኬዘይርካር ቦታ ሆፕ lyrics እናንባን፡፡ ይህ መልእክት በውስጥ የእርስዎ ፍሬ መልእክትን ማስተካከለ ነው፡፡ የመልእክቱ ጸሊላዊ እና ስልኩን መልእክት እንዴት እንደሚይዘው በአዶንም ሁኔታ ዋጋ እናልበስና፡፡ በትክክልናው መልእክቱ የትውልድ ፅሑን አርትራል ስብራችዎን ከበሬታ ሊሸሽ ነው፡፡ ስልክላቴ በሙሉ መቯዛቴን የፅሑን እቅድና ዓይነትም እንቆርጦታለን ፡፡ በስልኩ መልእክቱም በሬታ ለማጠፋ ኣንድ ክፍሊ ታክቦናለሁ፡፡ hopelyrics መልእክትን ስለተረዳን እቅድ እና ጠቃሚ ነው፡፡ ለማያትልን ከአርትራላቴ ጋር ይተረዝዎታል፡፡ በአሁን በመሆኑ ለመመልከት በሬታውን ለመክፈል የጀመረ አመልካቾች ሁኔታ ከዚህ የቆርጥ ወይም ለመረከብ የደንፈዝ ወኪለት፡፡ ከዚህ ዛሬ የሚቃኛና ስብራችንን እንደሚፍራም አሁን ለhopelyrics ነን፡፡

🎶 ሆፕ lyrics🎶

15 Oct, 07:44


🔵 ቤቲንግ ለምትመድቡ ሁሉ ይህን ምርጥ ቻናል እናስተዋውቃቹ 🤑

🔥 ብዙ ዓመት ልምድ ባላቸው ቀማሪዎች የተከፈተ ብችኛ ታማኝ ቻናል ነው ከኛጋ በመሆን ከሳምንት እስከ ሳምንት አሸናፊ ለመሆን ቻናሉን JOIN ያድርጉ 👇

🎶 ሆፕ lyrics🎶

01 Oct, 07:14


ይህ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን 5 ጊዜ ያነሳ የክሪስቲያኖ ሮናልዶ ቻናል ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ተከታዮች አሉት "JOIN" የሚለውን በመጫን የቻናሉ አባል ይሁኑ ❤️

🎶 ሆፕ lyrics🎶

04 Jul, 08:49


ነፍስዎት በሰላም ትረፍ 🕯️

🎶 ሆፕ lyrics🎶

23 Jun, 13:37


ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ሚሞችን ማየት እና ክርስትና ሀይማኖታችሁን በቀላሉ መረዳት የምትፈልጉ ብቻ ይሄን ቻናል Join አድርጉ ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/_twWlbg62cQwZmQ0

🎶 ሆፕ lyrics🎶

20 Jun, 12:28


💗💗💗💗

የመጨረሻው ክፍል😌

🖍...<<ለዛሬ የቀጠርኩህ በሲጋራ ማጨስና ጉዳቱ ዙሪያ ለጤናችን ፕሮግራም ካንተ ጋር ቃለ መጠይቅ ለመስራት ስለፈለግኩ ነው››

የመጨረሻዎቹን ቃላት በውል አላዳመጥኳቸውም፡፡ የተቀመጥኩበት ወንበር ወደ ውስጥ ይዞኝ የገባ መስሎኝ ከንፈሬን በጥርሴ እንደነከስኩ አይኖቼን በሀይል ጨፈንኳቸውና በዝምታዬ ውስጥ ራሴን ገደልኩ፡፡
ከተቀበርኩበት ድንገተኛ ሰመመን ስነቃ ሮማን በእጇ የያዘችውን የድምጽ መቅጃ እያሻሸች በድንጋጤ እየተመለከተችኝ ነበር፡፡
‹‹ ደህና ነህ? ›› አለችኝ፡፡ ጭንቅላቴን በአዎንታ ነቀነቅኩላት፡፡ ከዚያም እጄን ወደኪሴ ሰድጄ የተጨማተረ ሲጋራ መዘዝኩና አቀጣጠልኩ፡፡ ወደ ውስጥ የሳብኩት ጭስ ከአፌ እየወጣ አየር ላይ ተበታትኖ ወዲያና ወዲህ ሲቅበዘበዝ ሳይ እምባዬ መጣ፡፡ 🚬🚬🚬🚬

መድረሻውን የማያውቀው ጭስ የኔ ህይወት ተምሳሌት መሰለኝ፡፡🚬🚬 እንዲያውም ይህ የሲጋራ ጭስ መነሻውን ያውቃል፡፡ እኔ ግን መነሻና መድረሻዬን የማላውቅ፣ ከየት መጥቼ ወዴት እየሄድኩ እንደሆነ ያልተረዳሁ ምስኪን ሠው ነኝ፡፡ ሲጋራውን ጠላሁት፡፡ ጭሱን ማየት ቀፈፈኝ፡፡

መሬት ላይ ጣልኩትና በጫማዬ ደፈጠጥኩት፡፡ ኪሴ ውስጥ የነበረውን ሁሉ እያወጣሁ ስብርብር አደረግኩት፡፡
ነፍሴ ስትረጋጋ ታወቀኝ፡፡ በዛፎቹ መካከል እየተሽሎከለከ እኛ ወዳለንበት ጎጆ ቤት የሚገባው ነፋስ አዲሱን የህይወቴን ገጽ መግለጥ ጀመረ፡፡
ከዚህ በፊት የማላውቀው አዲስ ስሜት ውስጤ ገብቶ ቦታ ሲፈልግ አገኘሁት፡፡ ልቤን ሰጠሁት፡፡ በደስታ ተሞላሁ፡፡ መጮህ አማረኝ፡፡ ሮማን በሁኔታየ ግራ ተጋብታለች፡፡ ከአፏ ቃል ሳታወጣ በጭንቀት እየተነፈሰች የማደርገውንና የምሆነውን ትከታተላለች፡፡
የውስጤን ስሜት ሳዳምጥ ቆይቼ ዝቅ ባለ ድምጽ‹‹ አመሰግናለሁ ›› አልኳት፡፡ ከፀጉሯ ጋር በጣቷ እየተጫወተች በዝምታ ተመለከተችኝ፡፡

‹‹ ከረዥም ጊዜ ፍቅረኛዬ ጋ አለያዬሽኝ ›› ደነገጠች፡፡ ‹‹ ምን; ›› እንደምንም ከአፏ የወጣ ቃል ነው፡፡
‹‹ ለረዥም ጊዜ እንደ ፍቅረኛዬ ስንከባከበው ከነበረው ሱስ ጋር ዛሬ አለያየሽኝ››

ከተቀመጠችበት ድንገት ተነስታ ተጠመጠመችብኝ፡፡ ሽቶዋ ልቤን አጠፋው፡፡ ከልቤ ጋር ፍርሃቴም አብሮ ጠፋ፡፡ ለካ የፍርሃት ቤቱ ልብ ነው!
እንደተቃቀፍን የመጣው ይምጣ ብዬ ከንፈሯን ፍለጋ ስኳትን ያ- ክልፍልፍ አስተናጋጅ ዘው ብሎ ገባ፡፡
‹‹ ጠራችሁኝ እንዴ? ›› እያለ፡፡

📓ተፈፀመ📓



JOIN & SHARE @ken_leboch
CONTACT US @tesfish2

💞ቅን ልቦች
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

🎶 ሆፕ lyrics🎶

17 Jun, 12:39


💗💗💗💗

ክፍል6⃣

🖍...አለባበሷ እንደነገሩ ነው፡፡
‹‹ከስራ ቦታ በቀጥታ ነው እንዴ የመጣሽው?›› አልኳት ደግማ ስለመዘግየት እንዳታወራኝ አቅጣጫ ለማስቀየር፡፡

ቀስ በቀስ ፍርሃቴ እየጠፋ መጥቷል፡፡
‹‹አዎን ከዚያው መምጣቴ ነው›› አለች አረማመዷን ከኔ ፍጥነት ጋር ለማስተካከል እየሞከረች፡፡ ዝናቡ ማንጠባጠብ ጀምሯል፡፡ መናፈሻ ውስጥ ካሉት ትንንሽ ጎጆ ቤቶች መካከል አንዱን መርጠን ገባን፡፡ ወዲያው የሆነ ክልፍልፍ አስተናጋጅ እየተንደረደረ መጥቶ የምንፈልገውን ጠየቀን፡፡ ፈጥኖ መምጣቱ አበሳጭቶኛል፡፡ ‹‹ቡና!›› አልኩት በቁጣ፡፡ የኔን ትዕዛዝ ተቀብሎ በመጣበት አኳኋን እየተክለፈለፈ ተመልሶ ሄደ፡፡
ሳቄ መጣ፡፡ ከጥድፊያው የተነሳ እሷን ሳይታዘዛት ነው የሄደው፡፡ እጄን ላጨበጭብ ስዘጋጅ ሮማን ድንገተኛ ወሬ ጀመረች፡፡
‹‹ያው ለዛሬ የቀጠርኩህ.....›› ከማለቷ አስተናጋጁ ተመልሶ መጣ፡፡
‹‹ለእርስዎስ ምን ላምጣልዎት እመቤቴ?›› ሲል ጠየቃት እየተቅለሰለሰ፡፡
‹እርስዎ› ስላላት ይሁን ወይም ንግግሯን ስላቋረጣት እንጃ ቆጣ ብላ ‹‹ለኔም ቡና!›› አለችው፡፡ እየሮጠ ወጣ፡፡
ሲሮጥ ድንጋይ አደናቅፎት ሊወድቅ ነበረ፡፡ እንደሰካራም ተንገዳግዶ ለጥቂት ተረፈ፡፡ እሱ እንደወጣ ሮማን ንግግሯን ቀጠለች፡፡
‹‹ምን መሰለህ? ለዛሬ የቀጠርኩህ...እ...›› ጭኗ ላይ ያስቀመጠችውን ቦርሳ መደባበስ ያዘች፡፡ ልቤ በድንጋጤ መምታት ጀምሯል፡፡ አፈቅርሃለው የምትለዋን ቃል ለመስማት መቁነጥነጥ ያዝኩ፡፡
ግን ምንድነው የምመልስላት? እኔም አፈቅርሻለሁ ልበላት? ይሄ እንኳን አይሆንም፡፡ ገና በአንድ ቀን እንደዛ ብላት ትንቀኛለች፡፡ በቃ ላስብበት እላታለሁ፡፡

ወይኔ ጉዴ! ምንድነው የሚያቃዠኝ?
እኔ በሃሳብ ስዳክር ሮማን ጉሮሮዋን አፅድታ የጀመረችውን ንግግር ጨረሰችው፡፡
‹‹ያው ለዛሬ የቀጠርኩህ.....

ይቀጥላል....

አንብቦ ማለፍ ትንሽነት ነው፡፡የ👍 ምልክት በመጫን አበረታቱን።

JOIN & SHARE @ken_leboch
CONTACT US @tesfish2

💞የፍቅር ጐጆ
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

🎶 ሆፕ lyrics🎶

16 Jun, 13:32


💗💗💗💗

ክፍል6️⃣

🖍...አለባበሷ እንደነገሩ ነው፡፡
‹‹ከስራ ቦታ በቀጥታ ነው እንዴ የመጣሽው?›› አልኳት ደግማ ስለመዘግየት እንዳታወራኝ አቅጣጫ ለማስቀየር፡፡

ቀስ በቀስ ፍርሃቴ እየጠፋ መጥቷል፡፡
‹‹አዎን ከዚያው መምጣቴ ነው›› አለች አረማመዷን ከኔ ፍጥነት ጋር ለማስተካከል እየሞከረች፡፡ ዝናቡ ማንጠባጠብ ጀምሯል፡፡ መናፈሻ ውስጥ ካሉት ትንንሽ ጎጆ ቤቶች መካከል አንዱን መርጠን ገባን፡፡ ወዲያው የሆነ ክልፍልፍ አስተናጋጅ እየተንደረደረ መጥቶ የምንፈልገውን ጠየቀን፡፡ ፈጥኖ መምጣቱ አበሳጭቶኛል፡፡ ‹‹ቡና!›› አልኩት በቁጣ፡፡ የኔን ትዕዛዝ ተቀብሎ በመጣበት አኳኋን እየተክለፈለፈ ተመልሶ ሄደ፡፡
ሳቄ መጣ፡፡ ከጥድፊያው የተነሳ እሷን ሳይታዘዛት ነው የሄደው፡፡ እጄን ላጨበጭብ ስዘጋጅ ሮማን ድንገተኛ ወሬ ጀመረች፡፡
‹‹ያው ለዛሬ የቀጠርኩህ.....›› ከማለቷ አስተናጋጁ ተመልሶ መጣ፡፡
‹‹ለእርስዎስ ምን ላምጣልዎት እመቤቴ?›› ሲል ጠየቃት እየተቅለሰለሰ፡፡
‹እርስዎ› ስላላት ይሁን ወይም ንግግሯን ስላቋረጣት እንጃ ቆጣ ብላ ‹‹ለኔም ቡና!›› አለችው፡፡ እየሮጠ ወጣ፡፡
ሲሮጥ ድንጋይ አደናቅፎት ሊወድቅ ነበረ፡፡ እንደሰካራም ተንገዳግዶ ለጥቂት ተረፈ፡፡ እሱ እንደወጣ ሮማን ንግግሯን ቀጠለች፡፡
‹‹ምን መሰለህ? ለዛሬ የቀጠርኩህ...እ...›› ጭኗ ላይ ያስቀመጠችውን ቦርሳ መደባበስ ያዘች፡፡ ልቤ በድንጋጤ መምታት ጀምሯል፡፡ አፈቅርሃለው የምትለዋን ቃል ለመስማት መቁነጥነጥ ያዝኩ፡፡
ግን ምንድነው የምመልስላት? እኔም አፈቅርሻለሁ ልበላት? ይሄ እንኳን አይሆንም፡፡ ገና በአንድ ቀን እንደዛ ብላት ትንቀኛለች፡፡ በቃ ላስብበት እላታለሁ፡፡

ወይኔ ጉዴ! ምንድነው የሚያቃዠኝ?
እኔ በሃሳብ ስዳክር ሮማን ጉሮሮዋን አፅድታ የጀመረችውን ንግግር ጨረሰችው፡፡
‹‹ያው ለዛሬ የቀጠርኩህ.....

ይቀጥላል....

አንብቦ ማለፍ ትንሽነት ነው፡፡የ👍 ምልክት በመጫን አበረታቱን።

JOIN & SHARE @ken_leboch
CONTACT US @tesfish2

┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»✽̶┉┉┄┄

🎶 ሆፕ lyrics🎶

15 Jun, 20:01


💗💗💗💗

ክፍል5⃣

🖍...ድንጋጤዬን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ
‹‹ ነገ .. ነገ .. ነገ .. እ .. ነገ ስራ የለኝም! ›› አልኳት፡፡ ግን ውሸቴን ነበር፡፡ አያቴን ወደክሊኒክ ለመውሰድ ቀጠሮ ይዤ ነበር፡፡
‹‹ እንግዲያማ መገናኘት እንችላለን ማለት ነው ›› አለች ሮማን፡፡
‹‹ እ .. አዎ .. እንችላለን ››አልኩ ፈጠን ብዬ ሀሳቧን እንዳትቀይር የፈራሁ ይመስል፡፡
ከጥቂት ቆይታ በኋላ ሮማን ከመቀመጫዋ ተነስታ እጄን ጨበጠችኝና የጠጣንበትን ሂሳብ ከፍላ የቀጠሮውን ቦታ ነግራኝ ተሰናብታኝ ሄደች፡፡
የካፌው ተሰተናጋጆች ሮማንን ከኋላዋ በአይኖቻቸው አጀቧት፡፡ እንደዚያ አፍጥጠው ሲያዩዋት ተበሳጨሁ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ጉሮሮአቸውን ፈጥርቄ ከግድግዳው ጋር ባጋጫቸው ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ቅናት ወረረኝ፡፡ ፍቅረኛዬ ላይ አይናቸውን ማፍጠጣቸው አንገበገበኝ፡፡ ሲጋራዬን እያወጣሁ አፌ ላይ መጣድ ጀመርኩ፡፡ ጭሱ በግንባሬ በኩል በቀስታ እየተመመ የካፌውን ጣሪያ ለመንካት ጉዞ ሲጀምር ቀና እያልኩ እመለከተዋለሁ እኔን ይመስለኛል፡፡ የማላውቀውን፣ መቼ እንደጠፋብኝ ያልተገነዘብኩትን ህልም እንደምፈልገው፡፡
በሃሳብ ውስጥ ስናውዝ ድንገት የሞባይል ስልኬ ጠራ፡፡ ደዋዩ ጓደኛዬ ዩሐንስ ነው፡፡ አለቃዬ ሲፈልገኝ እንደነበር ሊነግረኝ ነው የደወለው፡፡
‹‹እሱን ተወው ባክህ! ይልቅ አንድ ወሬ ልንገርህ›› አልኩት፡፡
‹‹ምንድነው የምትነግረኝ....ዝም ብለህ ለሰውየው ብትደውልለት ይሻላል›› ሲል መለሰልኝ፡፡
‹‹በቃ እሺ እደውልለታለሁ... ዛሬ ምን እንደተፈጠረ ልንገርህ?››
‹‹ምንድነው ምን ተፈጠረ?››
‹‹ፍቅረኛዬን አገኘኋት!››
‹‹አገኘኋት?››
‹‹አዎ አገኘኋት.. ወይም አገኘችኝ! ቆይ አስተዋውቅሃለው... ብታያት በቃ ልዕልት ናት! Princess›› የካፌው ተስተናጋጆች ዘወር ዘወር እያሉ ተመለከቱኝ፡፡ ሳላውቀው በጣም እየጮህኩ ነበር ለካ፡፡
****
‹‹ዘግይቻለሁ እንዴ ግን?›› ጠየቀችኝ ሮማን ጎን ለጎን ሆነን ወደመናፈሻው እየገባን ሳለን፡፡ ምን ነካት ልጅቷ ስንት ጊዜ ነው የምትጠይቀኝ? መዘግየት ብርቅ መሰላት እንዴ?
‹‹እንዲያውም ፈጥነሽ ነው የመጣሽው›› ስል መለስኩላት ለአፍታ በአይኖቼ እየቃኘኋት፡፡
አለባበሷ እንደነገሩ ነው፡፡

ይቀጥላል..........




┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

🎶 ሆፕ lyrics🎶

15 Jun, 11:06


⚽️⚽️😂 እግር ኳስ MEME🤣⚽️⚽️

#fb ላይ የምታውቁት እግር ኳስ meme በቴሌግራም መቷል

ኳስ የምትወዱ ብቻ Join አርጉና ፈታ በሉ ይመቻችሁ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE8YTXcLvcD0PnTefw

🎶 ሆፕ lyrics🎶

12 Jun, 12:58


💗💗💗💗

ክፍል4⃣

🖍...ይሁንና አንዴ ሲጋራውን ሌላ ጊዜ ደግሞ አይኔን እያፈራረቀች መመልከቷን አላቆመችም፡፡ ይህቺ ቆንጆ ሴት ከዚህ በፊት እንደምታውቀኝ እርግጠኛ ሆኛለሁ፡፡ በውበቴ ሳትነደፍ አልቀረችም፡፡ የአበሻ ልማድ ይዟት እንጂ የፍቅር ጥያቄ ልታቀርብልኝ ፈልጋለች፡፡
አይኖቿ ውስጥ ‹እወድሃለው› የሚሉ ፊደላትን እያስነበበችኝ ነው፡፡
በአፏ የምታወራው ግን የማይጨበጥ ነገር ነው፡፡
‹‹እነዚህ አስተናጋጆች አለባበሳቸው በጣም ያምራል፤ አለባበስ ደንበኞችን ለመሳብ ከሚያስፈልጉ ወሳኝ ነገሮች አንዱ ነው፡፡›› ትለኛለች፡፡ እኔ ጭንቅላቴን ከመነቅነቅ ውጪ መልስ አልሰጣትም፡፡ ትንሽ ቆይታ ደግሞ ሎተሪ አዟሪ በፊታችን ሲያልፍ አይታ
‹‹ሎተሪ አዟሪዎች እድለኛ ባይሆኑም ሊከፋቸው አይገባም፡፡ ምክንያቱስ በለኝ.....››

የምትፈልገውን ልልላት ምላሴን ሳዘጋጅ የኔን ‹ምክንያቱስ› ሳትጠብቅ
‹‹ምክንያቱስ ብትለኝ ሎተሪ አዟሪዎች እድል ባይኖራቸውም ይዘውት የሚዞሩት ግን አድልን እራሱን ነው፡፡ ስለዚህ ደስ ሊላቸው ይገባል›› አለችኝ፡፡ ሀሳቧ ቢገባኝም እኔ ግን ምንም አልተናገርኩም፡፡
በዚህ መሃል ‹‹የጋዜጠኛ ነገር የኔን ወሬ ብቻ እንድታዳምጥ አደረግኩህ አይደል?›› አለችኝ ያንኑ ልብ የሚሰውር ፈገግታዋን በፊቷ እየረጨች፡፡ ተገረምኩ፡፡ ከአንደበቴ ድንገተኛ ቃላት ወጡ፡፡
‹‹እንዴ ጋዜጠኛ ነሽ እንዴ?›› ስል ጠየቅኳት፡፡
‹‹ምነው አንሳለሁ ወይንስ....››
‹‹አይ እንደዛ ማለቴ ሳይሆን........››

ንግግሬን ገታ አድርጌ ፈገግ ለማለት ሞከርኩ፡፡ ለጥቂት ጊዜ በመካከላችኝ የፀጥታ ድባብ ተዘረጋ፡፡ በዝምታ ውስጥ ሆነን በአይን መጠናናት ያዝን፡፡ ከዚያም ድንገት ‹‹ነገ 12 ሰዓት አካባቢ ስራ ይኖርሃል፡፡ ማለቴ ‹ቢዚ› ነህ?›› ጠየቀችኝ፡፡ የፈጣሪ ያለህ! ድንጋጤ ነፍሴን ሊነጥቀኝ ደረሰ፡፡ የልብ ትርታዬ ከመጠን በላይ መታ፡፡
ማራቶን የሮጥኩ መሰለኝ፡፡ ‹እወድሃለሁ› የሚል ቃል ብትናገር ምን ልሆን ነው?
ድንጋጤዬን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ

ይቀጥላል...

አንብቦ ማለፍ ትንሽነት ነው፡፡የ👍 ምልክት በመጫን አበረታቱን።

JOIN & SHARE @ken_leboch
CONTACT US @tesfish2

💞የፍቅር ጐጆ
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

🎶 ሆፕ lyrics🎶

11 Jun, 05:22


💗💗💗💗

ክፍል3⃣

🖍...በትናንትናው ቀፋፊ ቀን ከአለቃዬ ጋር በመጣላቴ በንዴት ስራ አልገባሁም ነበር፡፡ ቀኑ ብርዳምና አልፎ አልፎ እንደህፃን ልጅ ሽንት እየተቆራረጠ የሚዘንብ ካፊያ ዝናብ የነበረበት ቀን ነው፡፡
የጥጥ ነጋዴ የሚያስመስለኝን ወፍራም ካፖርት ለብሼ የለመድኳት ካፌ ውስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ፡፡ ራሴን ከብርዱና ከንዴቱ ለመገላገል አስቤ ኪሴ ውስጥ ያከማቸሁትን የተጨማተረ ሲጋራ በጣቶቼ እያልመዘመዝሁ በላይ በላዩ ማጨሴን ተያያዝኩት፡፡
ካፌዋ ‹ማጨስ ክልክል ነው› የሚል ማስታወቂያ የተለጠፈባት ቢሆንም ለኔ አይሰራም፡፡ ደንበኛቸው ስለሆንኩ አንድም ቀን ተናግረውኝ አያውቁም፡፡
ያዘዝኩትን ቡና አጋምሼ ጠረጴዛው ላይ እንዳስቀመጥኩት አንዲት ሴት ወደኔ ተጠግታ ሰላምታ አቀረበችልኝ፡፡ የለመድኩት ፍርሐቴ መጣ፡፡

ለሰላምታዋ ምላሽ ለመስጠት ዘገየሁ፡፡ ወደውስጥ የሳብኩትን የሲጋራ ጭስ ረሳሁት፡፡ ሳንባዬን አስጨንቆት ኖሮ በትንታ ተጣደፍኩ፡፡
ልጅቷ ተደናግጣ ስትመለከተኝ ቆየችና ‹‹ይቅርታ›› አለችኝ፡፡ ከዚያም ከጎኔ ያለውን ወንበር በጣቷ እያመለከተች ‹‹ወንበሩ ሰው አለው?›› ስትል ጠየቀችኝ፡፡ አንገቴን ግራና ቀኝ በማወዛወዝ ሰው እንደሌለው አሳወቅኳት፡፡ ቁጭ አለች፡፡

የተቀባችው ሽቶ አፍንጫዬን አልፎ ወደ ውስጤ ሲገባ አንዳች ልዩ ስሜት ውስጤን አናወጠው፡፡ እንደምንም ቀና ብዬ ለአፍታ አየኋት፡፡ ፀጉሯ አጭር ሲሆን የፊቷ ውበት ግን እንከን አይወጣለትም፡፡ ላነጋግራት ብፈልግም ቃላቶች ለዚያን ሰዓት ያልተፈጠሩ ይመስል አንደበቴ ዝግ ሆነ፡፡ በቃ ዝም-ዝም፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ‹‹መተዋወቅ ጥሩ ነው....እንተዋወቅ የኔ ስም ሮማን ወርቅ ይባላል ›› አለችና እጇን ዘረጋችልኝ፡፡ ፈገግታዋ ልብን ያሸብራል፡፡

እጆቼ እንዳይንቀጠቀጡ በመጠንቀቅ የተዘረጋውን እጇን ጨበጥኩትና የኔንም ስም ነገርኳት፡፡ ከዚያ ስለዓየር ሁኔታው፣ ስለተቀመጥንበት ወንበርና ስለሌሎችም ነገሮች አወራን፡፡ ብዙውን እሷ ናት የምታወራው፡፡

ሮማን ያዘዘችውን ማኪያቶ በማንኪያ እያገላበጠች ሲጋራ የጨበጥኩበትን እጄን ደጋግማ ስታይ ማጨስ የፈለገች መሰለኝና ከተጨማደዱት ሲጋራዎቼ አንዱን አውጥቼ ጋበዝኳት፡፡ ትንሽ ፈገግ ብላ እንደማታጨስ ነገረችኝ፡፡ አላግደረደርኳትም፡፡ ለራሴው አጨስኩት፡፡

ይቀጥላል...



JOIN & SHARE @ken_leboch
CONTACT US @tesfish2

💞የፍቅር ጐጆ
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

🎶 ሆፕ lyrics🎶

09 Jun, 07:45


💗💗💗💗

ክፍል2⃣

🖍....ፈገግ አለች፡፡ ፈገግታዋን ከመብረቁ ብልጭታ ጋር ማወዳደር ጀመርኩ፡፡ በምድር ስትመጣ እንዳላየኋት ሁሉ ከሰማይ የወረደች መሰለኝ፡፡ እኔም ፈገግ አልኩላት፡፡ ጥርሶቼን ግን አልገለጥኳቸውም፡፡
ሁሌም እንዲህ ነኝ፡፡ በዓይኖቼ እንጅ በጥርሶቼ አልስቅም፡፡ በልጅነቴ ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ እያለሁ ጓደኞቼ አይኖቼ እንደሚያምሩ ይነግሩኝ ስለነበር

ከጥርሶቼ ይልቅ በአይኖቼ እኮራለሁ፡፡ በርግጥ ያኔ ጥርሶቼ ያምሩ ነበር፡፡ ዛሬ ግን በሲጋራ ጭስ በልዘው አፌን የሲኦል መንገድ አስመስለውታል፡፡

ሮማን እጆቿን ለሰላምታ ዘረጋችልኝ፡፡ ስለኔ ጥርስና ስለእሷ ውበት እያሰብኩ ለሰላምታ የትኛውን እጄን መዘርጋት እንዳለብኝ ጠፋኝ፡፡ ሁለት እጆቼን አነባብሬ ሰጠኃት፡፡ በሚያማምሩ ጣቶቿ የቀኝ እጄን ለቀም አደረገችውና ለአፍታ በአይኖቿ ገላይን ከላይ እስከታች ዳበሰችው፡፡
ዛሬ ያለወትሮዬ ሽክ ብያለሁ፡፡ አለባበሴን እንደወደደችው ከአስተያየቷ ተረዳሁ፡፡ ከጓደኛዬ የተዋስኩትን ጥቁር ሱፍ ጀርባዋ ከተቀደደ ባለነጠብጣብ ሸሚዝ ጋር ለብሻለሁ፡፡
የጨበጠችውን እጄን ሳትለቅ ‹‹ ወደመናፈሻው እንግባ?›› ስትል ጠየቀችኝ፡፡ ስትናገር የምትዘፍን ትመስላለች፡፡
‹‹ደስ ይለኛል›› አልኳት ሊስም ፈልጎ ያሞጠሞጠ ከንፈሬን ወደ ቦታው እየመለስኩ፡፡

ሰላሳኛ አመቴን እየደፈንኩ ቢሆንም ካሁን በፊት የሴት ጓደኛ ኖሮኝ አያውቅም፡፡ ፍቅሬን ለሲጋራ እንጂ ለሴት የሰጠሁበት ጊዜ አልነበረም፡፡ የወንድ ጓደኞቼ በየጊዜው ፍቅረኛዬ ናት እያሉ የተለያዩ ሴቶቻቸውን ያስተዋውቁኝና
‹‹ያንተን ፍቅረኛ ግን ለምን አታስተዋውቀንም?›› ይሉኛል፡፡
‹‹የለኝም›› ስላቸው አያምኑኝም፡፡
‹‹እንዴት ላይኖርህ ይችላል አንተኮ ለሴት እንጂ ለወንድ የማይገባውን ውበት ይዘሃል፡፡
መልከ መልካም ነህ፡፡ በዚያ ላይ ገንዘብ ባይኖርህ እንኳ አሪፍ ጭንቅላት አለህ፡፡ ታዲያ እንዴት ፍቅረኛ የለኝም ትላለህ?›› ይሉኛል፡፡ ዝም እላቸዋለሁ፡፡ እነሱን ለማስረዳት ከምሞክር ከአዲስ አበባ ባህርዳር በእግሬ ብጓዝ እመርጣለሁ፡፡ ፈፅሞ ሊያምኑኝ አይችሉም፡፡
እኔና እግዚአብሔር በምናውቀው ሃቅ ግን እኔ እንኳን ሴት ፍቅረኛ ሴት እህት የለኝም፡፡ ብዙ ጊዜ ቆንጆ ሴቶችን ሳይ ቀድሞ ጉልበቴ ይዝላል፡፡ ላብ በጀርባዬና በግንባሬ ይፈሳል፡፡ ያደኩት ህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ከወንዶች ጋር ስለነበር ሴቶች ባሉበት ቦታ መገኘት ያስፈራኛል፡፡

ሴቶችን እንዴት ማናገር እንዳለብኝ እንኳን ጠንቅቄ አላውቅም፡፡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እያለሁ ጓደኞቼ ከሴቶች ጋር ‹በግተራ› ሲያመሹ እኔ ቤተመፅሐፍት ውስጥ ተቀብሬ ምሽቱን አሳልፍ እንደነበር አልዘነጋውም፡፡ አንዳንዴ ፍቅረኛ የሚኖረኝ መቼ ነው ስል እራሴን እጠይቅና አንድ ቀን በሚል መልስ እዘጋዋለሁ፡፡ እንዳልኩትም ያ - አንድ ቀን ከረጅም አመታት በኋላ ዛሬ ከተፍ አለ፡፡

ይቀጥላል...



JOIN & SHARE @ken_leboch
CONTACT US @tesfish2

💞የፍቅር ጐጆ
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

🎶 ሆፕ lyrics🎶

08 Jun, 14:56


💗💗💗💗
          
(አጭር ልቦለድ)

ክፍል1⃣

📝...የሰማዩ ገጽ ጠቁሯል፡፡ በቁጣ የተሞላ ይመስላል፡፡ ያረገዘውን ዝናብ ወደመሬት ለመጣል ይቁነጠነጣል፡፡ ከአፉ የሚተፋው የመብረቅ ብልጭታ በድምጽ ታጅቦ ከደመናው በታች ይታያል፡፡ ከፊት ለፊቴ ሰዎች ወዲያና ወዲህ ሲሯሯጡ እመለከታለሁ፡፡ ከመጣው መአት ራሳቸውን ለማዳን የሚሸሸጉበት ጥግ ፍለጋ በደመነፍስ ይጓዛሉ፡፡ እኔ ግን እዚህ ቁሜያለሁ፡፡
የመናፈሻውን በር ተደግፌ እሷን በመጠበቅ ላይ እገኛለሁ፡፡ በዚህ ጥቁር ሰማይ ስር ጫፍ አልባ ሩጫ የሚሮጡን ሰዎች በአይኔ እየማተርኩ የቀጠረችኝን ሴት ከነሱ መካከል ለማግኘት እፍጨረጨራለሁ፡፡ ቀይ፣ አፍንጫዋ ጎራዳ፣ አጭር ጸጉርና ረጅም ተክለ ቁመና ያላት ሴት እይታየ ውስጥ እንድትገባ መጸለይ ይዣለሁ፡፡

ቀጠሯችን 12 ሰዓት ነው፡፡ 10 ደቂቃዎች አልፈዋል፡፡ ‹ምነው ዘገየች? የውሸቷን ነበር እንዴ የቀጠረችኝ?› እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ፡፡
ይሄን ክፉ ሃሳቤን ልቀጥልበት ስንደረደር ድንገት በትከሻዋ ቦርሳ ያነገበች ረጅም ሴት የመንገዱን ጠርዝ ይዛ እየተጣደፈች ወደእኔ ስትመጣ ተመለከትኩ፡፡ እሷ ናት፡፡ ሮማን፡፡ ልቤ መዝለል ጀመረ፡፡
በሴትና ወንድ ግንኙነት ውስጥ የማላውቃቸው፣ የማይገቡኝ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር በመጀመርያው ቀን ቀጠሮው ሲገናኝ ሰላምታ የሚሰጣት እንዴት ነው? ጉንጯን መሳም? ከንፈሯን መሳም? በትከሻው ትከሻዋን መደለቅ? ወይስ ምን? አላውቅም፡፡ በዚህ ጉዳይ ጓደኞቼን ማማከር ነበረብኝ፡፡ ልደውልላቸው ይሆን? ሞባይል ስልኬን ፍለጋ ኪሶቼን ስፈታትሽ ፊት ለፊቴ መጥታ ቆመችና

‹‹ይቅርታ! ዘገየሁ እንዴ?›› አለች፡፡ ድምጽዋ በጣም ያምራል፡፡
‹‹ድምጽሽ ያምራል›› አልኳት አፌ ላይ እንደመጣልኝ፡፡
‹‹ አመሰግናለሁ! ብዙ አስጠበኩህ? ›› እንደገና ጠየቀችኝ፡፡
‹‹ አይ .. ደህና ነኝ .. ምንም አልል ... ማለቴ ብዙ ጠበቅኩሽ እንዴ? ›› መናገር የፈለኩት ጠፋብኝ፡፡ ተንተባተብኩ፡፡

ይቀጥላል ...



JOIN & SHARE @ken_leboch
Contact Us @tesfish2

💞የፍቅር ጐጆ
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

🎶 ሆፕ lyrics🎶

16 May, 15:34


​​💍ሐሊማ🙋

የመጨረሻው ክፍል🙌😍



...ቀድማ ነበር የደረሰችው ብዙም ሳትቆይ ሳሊም መጣ የቀዘቀዘ
ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ቀጥታ ወደ ጉዳያቸው ገቡ ሀሊማ
ይህንን አላማዋን ለማሳካት ያደረገችውን ነገር ነገረችው እንዴት
ብዪ ነው የምተወው እያለች ያደረገችውን ነገር ሁሉ ነገረችው....
ብዙ ነገር አድርገሽ ሊሆን ይችላል ግን ሁሉንም ያደረግሽው
ለክፋ ነገር ነው ደግሞ ሰሚራን ብትገድያት ምንም የምታገኝው
ነገር የለም እንደውም በተቃራኒው የህሊናሽ ወቀሳ ነው
የምታተርፊው መቼም ሰላም አታገኝም አላህ አንድን ነገር
ሲያደርግ ያለ ምክንያት አያደርግም ምን አልባት እናትሽ በሂወት
ብትኖር ኖሮ ዛሬ እዚህ መግባት አትቺይም ነበር ለምን ልትይኚ
ይሆናል አንቺ አሁን እንደዚ ትምህርትሽ ላይ ጠንክረሽ
የምትማሪው አንደኛው ምክንያት ሰሚራን ለመጉዳት ነው ግን
አንቺ ለክፋት አስበሽ ቢሆንም የተማርሽው ግን አንቺን ነው
የሚጠቅመው እናትሽ ብትኖር ግን እንደ አሁኑ ወጤታማ ላትሆኝ
ይችል ነበር
እያለ ብዙ ከመከራት በኃላ ውሳኔው የ አንቺ ነው
እሺ አስብበታለሁ ስለምክርህ እና አብረኃኝ ስለሆነክ
አመሰግናለሁ ብላው ሄደች ቀኑ ሀሙስ ነበር አርብ ቀን ነው
ሀሊማ ወደ ቤቷ የምትሄደው ቀኑን እንዲሁ ሁሉም ሲጨነቁ
ሲያስቡ አለፈ አርብ ጠዋት ሀሊማ ከድር ጋር ደውላ ሰላምታ
ከተለዋወጡ በኃላ
... ባባ ዛሬ ብቻዬን አይደለም የምመጣው ላሳውቅህ ብዪ ነው
ከድርም እሺ ብሎ ስልኩን ዘግቶ ሰሚራ ጋር ደውሎ ነገራት
ሀሊማ ለሳሊም ደውላለት አብሯት እንዲሄድ ለምናው እሺ አላት
ከጁምአ በኃላ እንገናኝ ብላ ስልኩን ዘጋችው ሀሊማ በጣም
ፈርታለች ጁምአ ሰግዳ ከሳሊም ጋር ተደዋውለው ወደ ሀሊማ
ቤት ሄዱ ሲደርሱ አንኳኩ ሰሚራ በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ
እንዲገቡ ጋበዘቻቸው ሁለቱም ወደ ሳሎን ቤት ገቡ ሀሊማ እቤት
ስትደርስ ለ ከድር ደውላ እቤት እንዲመጣ እና ሰው
ልታስተዋውቀው እንደሆነ ነግራው ስልኩ ተዘጋ ብዙም ሳይቆይ
ከድር እቤት ደረሰ ምግብ ቀርቦ ሁሉም አብረው ተመገብ ሰሚራ
እና ሀሊማ እቃዎቹን አነሳስተው መጨዋወት ጀመሩ ትንሽ
አንደተጨዋወቱ ሀሊማ አንዴ በቅድሚያ እንግዳዬን
ለስተዋውቃቹ ሳሊም ይባላል ልክ እንደ ሴት ጓደኛዬ ነው እና
ለምን ይዤው እንደመጣሁ በኃላ አነግራችኃለሁ ዛሬ
የማውቀውን ልነግራቹ እና አፋ እንድንባባል ነው አለች ሰሚራ
እና ከድር ግራ ገብቷቸው ሀሊማ የምትለውን ነገረ ማዳመጥ
ጀመሩ ሀሊማ ያየችውን የሰማችውን ነገር አንድ በአንድ
ነገረቻቸው ሰሚራ የምትገባበት አጣች ከድርም በጣም ደንግጦ
ባለበት ደርቆ ቀረ እስከዛሬ አታውቀውም ብለው የሚያስቡትን
ነገር እያወቀች ዝም ማለቷ ከድርን አሸመቀቀው ሳሊም በተራው
መናገር ጀመረ ያለፈውን ረስታቹ ይቅር ተባብለቹ በሰላም ኑሩ
ብሎ ዝም አለ ሁሉም ዝም አሉ ሰሚራ ለሀሊማ አፉ በይኝ ይሄን
ሁሉ ነገር እያወቅሽ አብረሽኝ እንዴት ኖርሽ ከበደልም በላይ
በድዬሻለሁ አፉ በይኝ ከድርም አፉ በይኝ ብሎ በፀፀት ጠየቃት
ሀሊማ ሁለታችሁንም አፋ ብያቸዋለሁ ሁሉም ተቃቅፈው አለቀሱ
ሳሊምን ይዤው የመጣሁት እንድታመሰግኑልኝ ነው እንደዚህ
የመሆኑ ምክንያት እሱ ነው ብላ ተናገረች.......ቀኑ በ
ደስታ አሳለፋት ሊመሽ አካባቢ ሳሊም ወደ ቤቱ ሄደ በነጋታው
በዘይነባ ስም ሰደቃ አድርገው ለሚስኪኖች አከፋፈሉ........
ከ 15 ቀናት በኃላ ከድር እና ሰሚራ አነስ ባለ ዝግጅት ኒካ አሰሩ
ሳሊም እና ሀሊማም ከድር እና ሰሚራ ኒካ ባሰሩ በሳምንቱ አነሱ
ኒካ አሰሩ ሁለቱም ከተመረቁ በኃላ ተጋብተው አብረው መኖር
ጀመሩ ፡፡ እነሱ ሲጀምሩ እኔ እዚህ ላያ ጨረስኩ🙏፡፡

ይህንን ታሪክ ያነበባቹ በሙሉ ከዚህ እንደምትማሩ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

. . . ህይወት ይቀጥላል . . .


....... ተ ፈ ፀ መ......

♥️•═••• የፍቅር አለም •••═•❤️
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••

━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━

🎶 ሆፕ lyrics🎶

15 May, 19:54


​​💍ሐሊማ🙋

🤍ክፍል 14💖




...ሳሊም አስቀድሞ ከተቀጣጠሩበ ቦታ ደርሶ እየጣበቃት ነው
ሀሊማ ብዙም ሳትቆይ መጣች ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ
ተቀመጠች ስለ ተለያዪ ነገሮች ካወሩ በኃላ ለምን
እንደፈለገችው ጠየቃት ሀሊማ እንዴት እንደምትነግረው ግራ
ገባት ዝም አለችው እንድትነግረው ማግባባት ጀመረ....
.
ከድር እንደተጨነቀ ነው ግን ለምን ያሰብኩትን አልነግራትም
ብሎ አሰበ ከስራ ሲመለስ ለመንገር ወሰነ ሰሚራ ከከድር ብዙ
ነገሮችን ተምራለች በይበልጥ ከሀሊማ ጥሩነት ለሷ
በምታደረጋቸው ነገሮች የሰራችው ስራ በጣም እየፀፀታት ነው
ተውበት አድርጋ ወደ አላህ ተመልሳለች ግን ሀሊማን ይቅርታ
መጠየቅ አለባት ግን ምን ብላ ልትነግራት ነው ምን ያህል
ጨካኝ እንደሆነች አሰበች ብነግራት ይቅርታ ታደርግልኝ ይሁን
ወይስ ይበልጥ ትጠላኛለች እያለች ከራሷ ጋር እያወራች ነው........
....ሀሊማ ለሳሊም እንደምንም ከራሷ ጋር ታግላ ሁሉንም ነገር
ነገረችው ሳሊም የምትነግረውን ነገር በተመስጦ እያዳመጣት
ድንገት እንበው ጉንጭላይ ዱብ ዱብ ማለት ጀመሩ ሀሊማ
የበለጠ ተረበሸች እሷም አብራው ማልቀስ ጀመረች ለቅሶዋን
ማቆም አልቻለችም ሳሊም ከራሱ አልፎ ሀሊማን የማባበል
አቅም አጣ ከአጠገቧ ትንሽ ራቅ አለ እሱም ለቅሶውን ለማቆም
እየሞከረ ነው ግን አልቻለም በዛ እድሜዋ እንደዚ አይነት ነገር
ተቋቁማ መኖር መቻሏ በጣም አሳዘነችው ለምን ብቻዋን
እንደምትሆን አሁን ነወ የገባው እንደምንም እራሱን አረጋግቶ
ሀሊማ አጠገብ ሄደ "አሁን ላለፈ ነገር ማልቀስ የለብሽም አንቺ
በጣም ጠንካራ ልጅ ነሽ እስከዛሬ ኖረሻል ከ አሁን በኃላ ከዚህ
በላይ ወጤታማ ሆነሽ ትኖሪየለሽ ሲላት ድንገት አቋርጣው
...ሰሚራን ሳልበቀል ሰላም አላገኝም አለችው.....ሳሊም በሀሊማ ንግግር በጣም ደነገጠ ምን አድረገሽ ነው
የምትበቀያት....
...እናቴን እንዳደረገቻት አደርጋታለሁ
ማለት ልትገድያት
አዎ
ሳሊም ደንንግጦ ይሄን ካአንቺ አልጠብቅም እሷን ከገደልሻት
እናትሽን መመለስ ተችያለሽ?
...አትመለስም ግን እናቴ ያየችውን ስቃይ ማየት አለባት ሀሊማ
አንዲህ አድርገሽ ይበልጥ ስቃይሽን አታብዢው ለአንቺም ሰላም
እንድታገኚ ሁሉንም ነገር እንደምታውቂ ንገሪያቸውና ይቅርታ
አድርጊለቸው ሁሉንም እያወቅሽ አብረሻቸው መኖርሽን ሲያውቁ
ውስጣቸው የሚሰማቸው ስሜት በራሱ ትልቅ በቀል ነው፡፡
አላህ ይቅር ባይ ነው ይቅር ባዮችን ይወዳል.....ምንም ብትለኝ አልሰማህም ብላ ጥላው ሄደች
አስቢበት አላት ዝም ብላው ሄደች ሀሊማ ቀጥታ ወደ ዶርሟ
ነበር የሄደችው ነገሮች እንደጠበቀችው ስላልሆነ ተናዳለች
ሳሊም ከተቀመጠበት ሳይነሳ ስለ ሁኔታው ማሰብ ጀመረ ሀሊማ
በጣም አሳዝናዋለች ግን ደግሞ ሀሳቧን በጭራሽ
አይደግፈውም ሀሊማ በበኩሏ ሳሊም ያለትን ነገር መቀበል
በጣም ከብዷታል አንድ በአንድ እያብጠረጠረች ማሰብ
ጀምራለች.....
.
....ከድር ለሰሚራ እንዴት መንገር እንዳለበት እያሰበ ነው
እንዳላስከፋት ብሎ ፈርቶዋል..... ሰሚራም ምን ማድረግ
እንዳለባት ግር ብሏታል ሀሊማን ነው ወይስ ከድርን ነው
በቅድሚያ ማናገር ያለብኝ ለነገሩ ለምኑም ለምኑም ለከድር
መንገር የተሻለ ነው ግን ባይቀበለኝስ እንቢ ቢለኝስ ሀሊማን
እስከመጨረሻው ይቅርታ መጠየቅ አልችልም ማለት ነው ይሄ
ደግሞ እንዲሆን አልፈልግም እያለች በቻዋን ታወራለች
አእምሮዋ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች ተፈጠሩ አንዱ ላይ ወስና
መቆም አልቻለችም.....ሁሉም ተጨንቀዋል አንዱ ለአንዱ ምን
ማለት እንዳለበት ግራ ገብቶታል ሁሉም እንደተጨነቁ ናቸው
እንደማይመሽ የለምና መሸ ከድር ወደ ቤቱ መሄድ በጣም
ከብዶታል መንገዱ ሙሉ ምን እንደሚላት እያሰበ ነው ቤቱ
የደረሰው የግቢውን የበር ቁልፉ ከኪሱ አወጥቶ በሩን ከፍቶ ገባ
ሰሚራም በጣም ተጨንቃለች ልንገረው ወይስ ይቅር እያለች ከ
ራሷ ጋር ሙግት ጀምራለች የሳሎኑን በር አንካኩቱ ወደ ውስጥ
ገባ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ከድር መጅሊሱ ላይ አረፍ አለ
ሰሚራ እራት ለማቀራረብ ወደ ውስጥ ገባች እራት አቅርባ
ሁሉም አብረው በሉ የተወሰነ ሰአት ከተጨዋወቱ በኃላ ሀያትና
መሀመድ ወደ ክፍላቸው ገብተው ተኙ ከድር እና ሰሚራ
ብቻቸውን ቀሩ ሁለቱም ያሰቡትን መናገር አቅቷቸው አይን
ለአይን ተፈጠዋል እንደ ድንገት ሁለቱም...እንትን ብለው ሁለቱም ዝም አሉ ከድር ምንድን ነው
ሰሚራም ምንድን ነው አለች..
እነግርሻለሁ ባይሆን ምን ልትነግሪኝ ፈልገሽ ነው ቀድመሽ ንገሪኝ
አለ ከድር ግድ የለም ቀድመህ ያንተን ንገረኝ የኔ ከ አንተ በኃላ
ይደርሳል.....አንተ አንቺ እየተባባሉ በመጨረሻ ሰሚራ ቀድማ
ለመናገር ተስማማች እና መናገር ጀመረች፡፡
ከድር እኔ ጥሩ ሰው እንዳልነበርኩ አውቃለሀ ግን ከ አሁን
ወዲህ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳ ባልሆን መጥፎ ሰው መሆን
አልፈልግም ሁሉንም ነገር በ አዲስ መልኩ መጀመር
እፈልጋለሁ....... እና ለሀሊማ ሁሉንም ልነግራት አስቢያለሁ....ከዛስ... አለ ከድር በንግግሯ ደንግጦ ለሀሊማ ሁሉን ነገር
ከነገረቻት እሱም ሰራው ውስጥ እንዳለበት ካወቀች
እንደምትጠለው ያውቃል.. ይሄን ደግሞ ከድር መቋቋም
አይችልም.... ከዛማ ይቅርታ ከደረገችልኝ አደረገችልኝ ካልሆነ
እንደፈለገች ታድርገኝ ብላ በረጅሙ ተነፈሰች ከድር ዝም አለ
እሱም ቢሆን ነግራት ሰላም ቢያገኝ በጣም ደስተኛ ነው ግን
የሚመጣው ውጤት አስፈርቶታል ከድር ለሰሚራ ሊነግራት
የነበረውን ነገር ትቶ ስለ ሀሊማ መልስ መጨነቅ ጀመረ
ከተቀመጠበት በዝግታ ተነስቶ ወደ መኝታው ሄደ ሰሚራ እዛው
ሳሎን ቤት ወስጥ ባለችበት ጋደም አለች.......
.
....ሀሊማ በአንድ በኩል ሳሊም የተናገራትን ነገር እያሰበች
በሌላ በኩል የእናቷን ደም እንደፈሰሰ ሊቀር እንደሆነ እያሰበች
በጣም ተጨንቃለች ለሀሊማ በቀሏ እስከ አሁን ድረስ
የለፋችለት ነገር ነው አላማዋ ነው እስከ አሁን በትእግስት
የኖረችበት ምክንያትም ነው ይሄን መተው ለሀሊማ ከመሞት
አይተናነስም ይሄን መተው በጣም ከብዷታል እየተጨነቀች
እንቅለፍ የሚባል ነገር በአይኗ ሳይዞር ነጋ፡፡ ሀሊማ ከ አልጋዋ
ላይ ሳትነሳ ስልኳን ከትራሷ ወስጥ አውጥታ ሳሊም ጋር ደወለች
ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ልታገኘው እንደምትፈልግ ነገረችው
ይቅርታ ሀሊማ ሀሳብሽን ካለቀየርሽ ላገኝሽ አልፈልግም
ሀሳብሽን ከቀየርሽ እንገናኝ.....
ሀሳቤን አልቀየርኩም ማለት ምንም መወሰን አልቻልኩም
እባክህን ላግኝህና እርዳኝ ትንሽ ካንገራገረ በኃላ እሺ
የተለመደው ቦታ አጠብቅሻለሁ ብሏት ስልኩ ተዘጋ......ሀሊማ
ከተኛችበት ተነስታ ታጥባ ቀያይራ ወደ ተቀጣጠሩበት ቦታ ሄደች....


,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••

━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━

🎶 ሆፕ lyrics🎶

10 May, 18:28


​​💍ሐሊማ🙋

🤍 ክፍል 13 💖




...የሀሊማ እህትና ወንድም አሪፍ ወጤት አምጥተው ወደ አምስተኛ
ክፍል አልፈዋል ሀሊማ 12ኛ ክፍልን በጣም በጥሩ ውጤት ነው
አልፋ አዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ ተመድባ ጥቅምት ላይ ትምህርት
ትጀምራለች እህትና ወንድሞቿ ትምህርት ጀምረዋል ሀሊማ እንደ
በፊቱ እነሱን መንከባከብ አትችልም ምክንያቱም ደግሞ በ
ሳምንት ሁለት ቀን ብቻ ነው የምታገኛቸው ፡፡
.
...ሀሊማ ትምህርት ጀምራለች እንደተለመደው የመጀመሪያውን
ሴሜስተር በአሪፍ ውጤት አጠናቃለች እህትና ወንድሟም ቢሆን
አሪፍ ወጤት አምጥተዋል በጊዜው ሁሉምእረፍት ላይ ስለሆኑ
አንድ ላይ እቤት ውስጥ ነው የሚውሉት ሀሊማም በሳምንት ሁለት
ቀን ብቻ ስለምታገኛቸው ቶሎ ቶሎ ይናፍቋታል ከ 15 ቀን እረፍት
በኃላ ሁሉም ትምህርት ጀመሩ ሀሊማም ጀምራለች ሀሊማ
አብዛኛውን ግዜዋን የምታሳልፈው ላይብረሪ ውስጥ ነው ከ ዶርሟ
ተማሪዎችም ጋር ብዙ ቅርርብ የላትም አሁንም ብቸኛ
ናት........ሀሊማ እንደ ወትሮዋ ወደ ላይብረሪ ለመሄድ ከዶርሟ
ወጥታ ወደ ላይብረሪው የሚወስደውን መንገድ ይዛ በዝግታ
እየተራመደች ነው ሀሊማ እድሜዋ እየጨመረ በሄደ ቁጥር ቁጭ
እናቷን እየመሰለች ነው ሀለማ ቀጥ ያለ አፍንጫ ያለት አይኖቿ
ጎላ ጎላ ያሉ በጣም የሚስብ የፊት ከለር ያለት የፊቷ አቀማመጥ
በዛ ላይ የደም ግባቷ ተጨምሮ ቁመቷ ከመልኳ ጋር ምጥን
ተደርጎ የተሰጣት ነው የሚመስለው የምትለብሳቸው ልብሶች
ለእሷ ብቻ ተብሎ የተሰሩ ነው የሚመስሉት ባጠቃላይ እንደ
ዘይነብ ሀሊማም እጅግ በጣም ውብ ነች ፡፡
.
....ሀሊማ ወደ ላይብረሪ ልትደርስ ትንሽ መንገድ ሲቀራት ድንገት
ከላይብረሪው በጥድፊያ የሚወጣ አንድ ተማሪ ሀሊማ ወደ
ምትመጣበት አቅጣጫ በፍጥነት እየተራመደ ሀሊማ አጠገብ
ሲደርስ ገፍትሯት በእጇ የያዘቸውን መፅሀፍ ደብተር አንዳለ መሬት
ላይ ተበታትኖ ወደቀ ይቅርታ ብቻ ብሏት አለፈ ሀሊማ በልጁ
ሁኔታው ተናደደችበት፡፡
.
... ልጁ ግን ድጋሚ እንኳ ሳይዞሮ ትቷት ሄደ ሀሊማ በጣም
ተናዳለች የወዳደቁትን መፅሀፍ እና ደብተር ሰብስባ ወደ
ለይብሪው ገባችግን በጣም ተናዳ ስለነበረ ተረጋግታ ማጥናት
አልቻለችም መፅሀፉን ከፍታዋለች እያነበበች ነው ግን ምንም
እየገባት አይደለም እራሷን አረጋግታ ማጥናት ስላልቻለች
ላይብሪውን ለቃ ወጣች ቀጥታ ወደ ዶርሟ ሄዳ ብቻዋን
ተቀመጠቸ ግን ልጁን መርሳት አልቻለችም......
.
በሚገርም ሁኔታ ሰሚራ ከማንም በላይ ሀሊማ ናፍቃታለች
በእርግጥ ሁሉም ሀሊማን ናፍቀዋታል ቤቱ ያለ ሀሊማ በጣም
ያስጠላል እንደ ቤተሰብ ባይሆኑም ከወዲህ ወዲያ የምትለው
ነገር ቤቱን ጭር አድርጎታል እህትና ወንድሞቿን እያሳቀች ቤቱን
ታደምቀው ነበር ፡፡ከድር እና ሰሚራ ማን ያውራቸው በትንሹም
ቢሆን ሀሊማ ታወራቸው ነበር ከድር አንዳንድ የሚፈልጋቸውን
ነገሮችን ሀሊማን ነበር የሚጠይቀው አሁን እሷ ስለሌለች የግድ
ሰሚራን ነው የሚጠይቃት ይሄ በትንሹ ማውራት ለሁለቱም
የጠቀመ ይመስላል ሰሚራና ከድርን እንደ አዲስ እያግባባቸው
እየተቀራቡ ነው፡፡
.
ሀያት እህቷን ለመተካት ይመስል እንደሷ ለመሆን እየሞከረች
በትንሹም ቢሆን ሰሚራን ትረዳታለች በዚህ ደግሞ ሰሚራ
ተደስታለች ሰሚራ የራሷ ልጅ ባይኖራትም የከድር ልጆችን እንደ
ልጇ ተቀብላ ማሳደግ ጀምራለች በዚህ ደግሞ ደስተኛ እየሆነች
ነው........
..... ሀሊማ ንዴቷ ረገብ ሲልላት ለምንድን ነው ይሄን ያህል
የተናደድኩት ብላ እራሷን ጠየቀች ነገረ ስራዋ ለራሷ ገረማት......... ከ 1 ወር በኃላ ያኔ ከገፈተራት ልጅ ጋር የገፈተራት ቦታ
ላይ በድጋሚ ተገናኙ ሀሊማ ብዙም ትኩረት ሳትሰጠው
ልታልፍው ስትል የኔ እህት ባለፈው እንደዛ ገፍትሬሽ ስለሄድኩ
በጣም ይቅርታ አላት ችግር የለውም ብላው አልፋው ሄደች ፡፡
.
ትኩረት አለመስጠቷ ትንሽ ገረመው ሳሊም እንኳን እንዲ አውርቶ
አይደለም ያየችው ሴት ሁሉ የምታደንቀው አይነት ሰው ነው
መልኩ ስነስርአቱ እርጋታው ወንዳወንድነቱ ሁሉም ነገሩ
የትኛዋም አይነት ሴት የምታደንቀው አይነት ወንድ ነው ለነገሩ
ሱና ማንን አያሳምርም!! ሀሊማ ግን በሙሉ አይኗ እንኳ ሳታየው
ነው ያለፈችው....... ከዛ ቀን በኃላ ግን ሀሊማ እና ሳሊም
ለይብረሪ ውስጥ ይገናኛሉ አልፎ አልፎ ሰላምታ ይለዋወጣሉ ፡፡
አልፎ አልፎ የነበረው ሰላምታ ቀስ በቀስ ቀን በቀን ሆነ ሀሊማ
ለመጀመሪያ ግዜ ከ ቤተሰቧ ወጪ ሌላ ሰው ተግባባች አንዳንድ
ነገሮችን ማውራት ጀምረዋል.... ግን ሀሊማ ሌላ ሰው ቀርባ
ስለማታውቅ ብዙም ነፃ ሆና አታወራውም

..••እንዲህ እየተባለ ሀሊማ የ4ኛ አመት ተማሪ ሆናለች በአሁኑ
ሰአት ሳሊም እና ሀሊማ በጣም ተግባብተዋል በይበለጥ ግን
ሳሊም ሁሉን ነገሩን ያጋራታል አብዛኛውን ነገር አብሯት ነው
የሚያደርገው ግን ይሄ ሁሉ ሲሆን አንድም ቀን ተጨባብጠውም
ሆነ ተነካክተው አያውቁም ነበር.............. በከድር እና ሰሚራ መካከል የነበረው ክፍተት በጣም
እየጠበበ መጥቶዋል ከድር ከ 3 አመት በፊት በሀሊማ
ጎትጓችነት ኢስላማዊ ትምህር ከሚሰጡ ሰዎች ጋር አብሮ
መዋል መማር ጀምሮዋል እና የ እሱና የ ሰሚራ ግንኙነት ሀራም
እንደሆነ ተገንዝቦዋል ግን ምን ማድረግ እንዳለበት አለወቀም
ኒካህ እንሰር ቢል እንኳ ሀሊማ ትከፋለች መመለስ
የማይችላቸው ብዙ ጥያቄዎችን እንደምትጠይቀው አሰበ ታዲያ
ለሰሚራ ሀራም ስለሆነ አብረን መኖር አንችለም ብሎ ሰሚራን
ማባረር በጣም ከብደው ሚስቱ እንኳ ባትሆን ይሄን ያህል አመት
ልጆቹን እሱን ስትንከባከብ ቆይታለች ምንም እንኳ ሚስቱን
የማጣቱ ምክንያት ብትሆንም ከድር በጣም ተጨንቆ እያሰበ
ነወ፡፡
ሀሊማ ለሳሊም ስለ ቤተሰቧ ልትነግረው አስባለች በጣም
ስለተቀራረቡ ይረዳኛል የሚል እምነት አላት የግድ የሚረዳት
ሰው እንደሚያስፈልጋት ስለገባተ ለ ሳሊም ለመንገር ወስና ሌላ
ቀን የሚገናኙበት ቦታ ላይ ቀጠረችው••••••



,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••

━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━

🎶 ሆፕ lyrics🎶

09 May, 18:10


​​💍ሐሊማ🙋

💖ክፍል 12💖




...ሰሚራ የከድርን አፍ አፍ እያየች የሚለውን እየጠበቀች ነው ከድር
ግን አንዲትም ቃል ትንፍሽ ሳይል ወደ መኝታ ቤት ሄደ ሰሚራ
በጣም ከፋት ዝም ከማለት ውጪ አማራጭ የላትም ጭለማው
አልፎ በብርሀን ተተካ ሀሊማ እህትና ወንድሟን ለትምህርት ቤት
አዘጋጅታ እሷም ተዘጋጅታ ሁሉም በአንድ ላይ ቁርስ በልተው
ሀሊማ እህትና ወንድሟን ይዛ ወጣች ሰሚራ በድጋሚ ልጠይቀው
ፈልጋ ነበር ግን ሊመልስልኝ ይችላል ብላ ዝም አለች ከአሁን
አሁን ምን ተናገረ እያለች ስትጠብቅ እሱም ልብሱን ቀያይሮ ደና
ዋይ ብሏት ወጣ ምንም ሳትመልስለት በዝምታ በአይኗ ሸኘችው
............
እነ ሀሊማ ከትምህርት ቤት መምጫቸው ደርሷል ሰሚራ አንድ
ነገር አስባለች ........ እነ ሀሊማ አስኪመለሱ ያላትን ሞያ
ተጠቅማ ቆንጆ ምግብ ሰርታ ጠበቀቻቸው እነ ሀሊማ ሲመለሱ
በሞቀ ፈገግታ ተቀበለቻቸው ሀሊማ ግን ፈገግታውን
አሎደደችውም ያለመደባትን ብላ ግራ ገባት በውስጧ ምን ተገኘ
እያለች አሰበች በሰአቱ ሀሊማ የ 10 ክፍል ማትሪክ ፈተና ልቶስድ
2 ወር ብቻ ነበር የቀራት ሰሚራ የሚበሉትን አቀረበችላቸው::
ሀሊማ.....እኔ አቀርበው ነበር እኮ ለምን ተቸገርሽ......ስለደከመሽ ብዬ ነው ምን ነው ችግር አለው?......ኧረ የለውም ብላ መመገብ ጀመረች:: በጣም ይጣፍጣል
አለቻት ሀሊማ ሰሚራ በአድናቆቱ ተደሰተች መሀመድ እና ሀያት
በልተው ወደ ቁርአን ቤት ለመሄድ ወጡ ሀሊማም እነሱን ተከትላ
ለመውጣት ስትነሳ አንዴ ሀሊማ የአንድ የማናግርሽ ነገር አለ
እነሱ ይሂዱ አለቻት ሀሊማም እሺ ብላ እንዲሄዱ ነግራቸው እሷ
ተቀመጠች......ምንድን ነው ንገሪኝ እየሰማሁሽ ነው....እሺ እነግርሻለሁ ብላ በረጅሙ ተነፈሰች ካቀረቀረችበት ቀና
ብላ እኔ እና አባትሽ አንድ ላይ መኖር ከጀመርን ረጅም ጊዜ
ሆኖናል እና.... ብላ ዝም አለች......እና ምን እናእማ ለእኔ ልጅ ለእናንተ ደግሞ ታናሽ ወንድም
ያስፈልጋችኃል.......ታዲያ እኔ ምን እንዳደርግ ነው የምትፈልጊው.... ከእኔ ይልቅ አባትሽ አንቺን ስለሚሰማሽ እንድትጠይቂው ነው...ምን ብዬ....ልጅ ወለዱ በይው...ምን እንዴት ነው እንደዚህ የምለው ብላ አፈጠጠችባት ሀሊማ
እናቷ እንደሞተች እንደማታውቅ ለማስመሰል እየሞከረች... እናቴስ እሷ እያለች እንዴት ነው ከአንቺ እንዲወልድ
የምጠይቀው ደግሞ ምን ያህል ሀራም እንደሆነ አታውቂም እንዴ
ብላ በንዴት ተናገረቻት ስሚኝ ድጋሚ እንደዚህ አይነት ነገር
እንዳትጠይቂኝ ብላት ወጣች ፡፡
ሰሚራ ያሰበችው ባለመሳካቱ ተበሳጨች እንጂ የሀሊማ ንግግር
ምንም አልመሰላትም ተስፋ ሳትቆርጥ የመጨረሻ እድሏን
ለመመኮር ወሰነችከድር ሌላ ቀን ከሚመጣበት ሰአት አርፎዶዋል
ሀሊማ እና ሰሚራ ሲቀሩ ሌሎቹ ተኝተዋል ሀሊማም መጠበቅ
እያቃታት ነው ወደ ክፍሏ ገባች ለሰሚራ ከአሰበችው በላይ እቅዷ
እየተሳካ ነው ሀሊማ መተኛቷን ካረጋገጠች በኃላ መጀመሪያውኑም
ሳሎን ቤቱንም መኝታ ቤቱንም ከሌላ ግዜ በተለየ አሳምራዋለች
በተለይ መኝታ ቤቱን አልጋውን ቆንጆ አድርጋ አስተካክላዋለች
ፍዝዝ ያለ አንፖል ብቻ ለመኝታ ቤቱ ውበት ይሰጠዋል ያለችውን
ነገር ሁሉ አድርጋለች ሀሊማ እንደተኛች ሰሚራ አሪፍ የምትለውን
ቀሚስ ለብሳ መልኳን ይበልጥ ጎላ ብሎ እንዲታይ የተወሰነ
ሜካፕ ተቀብታለች በጣም አምሮባታል ጨራርሳ ከድርን መጠበቅ
ጀመረች..... ብዙም ሳይቆይ ከድር በሩን ከፍቶ ገባ........ከምንመ ግዜውም በላይ በፈገግታ ተቀበለችው ከድርም ሲያያት
በጣም ደሰ አለው የሰራችውን አሪፍ እራት አቀረበችለት ደስ
እያለው በላ ሰሚራ ያሰበችወ ለማሳካት ግማሽ መንገድ ሄዳለች
ሌላው ቢቀር ዛሬ ፊት አነሳትም የተቀባችው ሽቶ ከ እሩቁ ይስባል
ከድር በልቶ ሲጨርስ እቃውን አነሳስታ አጠገቡ ተቀመጠች
ሁለቱም ዝም ተባባሉ ሰሚራ ወሬ ለመፍጠር ያህል...ስራ እንዴት ነበር ብላ ጠየቀችው.....አሪፍ ነበር.....በሰላም ነው የቆየኃው....አው ያልጨረስኩት ስራ ነበር አላት
ሌላ የምታወራውን ነገር ማሠብ ጀመረች......ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እንዲህ ያማረብሽ ከድር ነበር ያለው
ሰሚራም ትንሽ ሰአት ዝም ካለች በኃላ አው ሁሉም ነገር እንደ
ድሮ እንዲሆን ፈልጌ ነው ብላ የተወሰነ ወደ ከድር ጠጋ አለች
እሱም ወደ እሷ ጠጋ ብሎ ጥሩ ሀሳብ ነው አላት ሰሚራ በመልሱ
በጣም ተደሰተች ከድር እኔም ተስማምቻለሁ ብሎ አቀፋት ሰሚራ
ከከድር እቅፍ ውስጥ ሳቶጣ እሱም እንዳቀፋት ለ እረጅም ሰአት
ቆዮ ዛሬ አተኛም እንዴ ኧረ እተኛለሁ ቡሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ
ወደ መኝታ ቤት ለመሄድ አንድ እግሩን ሲያነሳ ሰሚራ እጁን ጎትታ
አስቀመጠችወ ደንግጦ ተቀምጦ ወደ ሰሚራ ሲዞር ሳያስበው
ሰሚራ ግጥም አድርጋ ሳመችው ከድር የተደበላለቀ ስሜት
ተሰማው ደንግጦ ስለ ነበር የሚላት ነገር ጠፋው እንደመጣለት
ተናገራት
...... ምን ማድረግሽ ነው እንደ ድሮ እንሁን ማለት በእንደዚህ
አይነት ሁኔታ ከሆነ እንደመጀመሪያችን ብንሆን ነው የሚሻለን
ብሏት እንደተቀመጠች ትቷት ወደ መኝታ ቤት ገባ እንደዛ ለፍታ
ያስተካከለችውን መኝታ ቤት በአትኩሮት እንኳ ሳይመለከተው
ልብሱን ቀያይሮ ሳሎን ቤት ተኛ ሰሚራ የመጨረሻ እድሏን
ሞክራለች ቅስሟ ተሰባበረ መኝታ ቤት ገብታ ከልቧ አለቀሰች
ሰሚራ እንደዛ ቀን ከፍቷት አያውቅም........
ሰሚራ ተስፋ ቆርጣ መኖር ጀምራለች ሀሊማ ለሰሚራም
ለከድርም ከመጀመሪያው በላይ ጥሩ እየሆነች ነው ከድር እና
ሰሚራም እንደ በፊቱ ናቸው ሀሊማ 10 እና11 ክፍልን በጥሩ
ወጤት አልፍለች ሀያትና መሀመድም እንደዛው ሀሊማ በአሁኑ
ሰአት የ 12 ክፍልማትሪክ ፈተና ተፈትና ወጤት እየጠበቀች
ነው.......




,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••

🎶 ሆፕ lyrics🎶

08 May, 20:30


​​💍ሐሊማ🙋

💞ክፍል 11💖



ሀሊማ ድንገት ወደ ፈጡማ ስትዞር የፋጡማ አይን
ፈጦዋል ሀሊማ ደንግጣ ባባ አክስቴን ተመልከታት ብላ ጮኃችበት
ከድር በጣም ደንግጦ ፋጡማ .....እህት ፋጡማ እያለ ጮኃ
ፋጡማ ግን እስከመጨረሻ አሸልባለች ከድር አይኗን ገርበብ
አደረገላት ሀሊማ ባባ ምን እያደረክ ነው ልጄ አይዞሽ እኔ ከጎንሽ
አለሁ ምን እያልከኝ ነው አክስትሽን ድጋሚ አናገኛትም ሞታለች
አላት ሀሊማ የሰማችውን መቋቋም አቅቷት እራሷን ስታ ወደቀች
ከድር የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው ባንድ በኩል የፋጡማ ሬሳ
አለ በሌላ በኩል ልጁ እራሷን ስታ ወድቃለች ሰሚራ ጋር ደውሎ
እንድትረዳው ጠየቃት ግን እንደ እድል ሆኖ ሰሚራ የፋጡማን ቤት
አታውቀውም በምልክት እንድትመጣ ነገራት ሰሚራም ታክሲ
ተኮናትራ ከከድር ጋር እየተደዋወለች በምልክት ደረሰች ከድር ከ
እቤት ወጥቶ ተቀበሏት አንድ ላይ ወደ ቤቱ ገቡ ሀሊማ ልትነቃ
ስላልቻለች ከድር አቅፎ ወደ ሀኪም ቤት ይዟት ሄደ፡፡
ሰሚራ ከፋጡማ ጋር ብቻዋን ነች በጣም ፈርታታለች ልትቀርባት
አልቻለችም ፋጡማ የቀረ ዘመድ የላትም ሰሚራ ለጥቂት ግዜ
ተረጋግታ አስባ አንድ ሀሳብ መጣላት የፋጡማ ጎረቤቶች ጋር
ሄዶ መናገር ወዲያው ከ ቤቱ ወጥታ ለተወሰነ ሰው ተናገረች
የሰፈሩ ሰው ተባብሮ ድንኳን ተደኮነ ሬሳውንም እንዲከፈን
ተደርገ ሁሉም ነገር ቦታ ቦታ እየያዘ ነው በዚህ መሀል ግን
ሰሚራ እንደዛ በብጣሽ ጨርቅ ጠቅልላ የጣለችው ሬሳ ትዝ
አላት ስራዋ ለእራሷ ቀፈፋት አሁን ቢቀፋትም ባይቀፋትም ከ
አለፈ ወዲያ ምን ያደርጋል ......
ሀሊማ ከተወሰነ ሰአት በኃላ ነቃች ከድር ትንሽ ሰላም ተሰማው
ወዲያውኑ ዶክተሩን ጠራው ዶክተሩም የተወሰነ ነገር ቼክ
ካደረገ በኃላ ከድርን 1 ውጪ ላናግርህ ብሎ አብረው ከክፍሉ
ወጡ በሩን ጠጋ አድርጎላት መነጋገር ጀመሩ ያን ያህል አደጋ
ላይ ሊጥላት የሚችል ነገር የለም አንዳንድ ሰው ከመጠን ያለፈ
ደስታ እና ሀዘን ሲያጋጥመው መቋቋም ያቅተውና እንደዚህ
አይነት ችግር ሊፈጠር ይችላል ብሎ ዶክተሩ ለ ከድር ይነግረዋል
የተወሰነ ሰአት እረፍት ታድርግና ትወጣለች ብሎ ዶክተሩ ከድርን
ተሰናብቶ ይሄዳል ከድር የሀሊማን ጉዳይ ከሰማ በኃላ ወደ
ሰሚራ ጋር ይደውላል ሰሚራ ከሰፈር ሰዎች ጋር አንዳንድ
ነገሮችነ ነው 6፡00 ይላል ሰአቱ የዝሁር ሰላት ሰአት እየደረሰ
ነው ከድር ከሀኪም ቤቱ አሁን ካሎጣ ሰአቱ ይሄዳል ሀሊማንም
ጥሎ መሄድ አይችልም ከድር ወዲያውኑ ወደ ዶክተሩ ቢሮ ሄዶ
ለዶክተሩ ሁኔታውን አሰረዳው ዶክተሩም ሀሊማን ይዟት እንዲሄድ
ፈቀደለት ከድር ዶክተሩን አመስግኖ ያለበትን ሂሳብ ከፍሎ
ሀሊማን ይዞ ወደ ፋጡማ ቤት መሄድ ጀመሩ የሰሚራን ጩኃት
እያሰበ ነው እስከ አሁን ብቻዋን እንደሆነች ነው የሚያውቀው
ወደ ፋጡማ ቤት የሚወስደው ቅያስ ጋር ሲደርስ ሀሊማ
በድጋሚ እራሷን እንዳትስት ፈራ ሰአቱ 6፡25 ይላል ወደ እቤት
ላድርሷት ቢል እንኳ ሰአቱ አይበቃውም አማራጭ ስለሌለው
ሀሊማን ወደ ፋጡማ ቤትይዟት መሄዱን ቀጠለ ቤት ሲደርሱ
ድንኳን ተደኩኖ ያያል ማን እንዲህ እንዳደረገ ለማወቅ በፍጥነት
ወደ ውስጥ ገባ ጭራሽ ያልጠበቀው ነገር ነበር ሀሊማ አካሏ
ነው እንጂ የለችም ማለት ይቻላል ወደ ወስጥ ሲገባ
የሚያለቅስ ሰው ምግብ የሚሰራ ሰው ብቻ ግቢው በሰው
ተሞልቶ ከድር በጣም በተገረመ ሁኔታ ያያል የሰውን ሁኔታ ሲያይ
እሱም ሚስቱ ትዝ አለችው አንገቱን ደፍቶ ወደ ውስጥ ገባ
ሰሚራን በአይኑ መፈለግ ጀመረ ሰሚራ አይታው ስለነበር ወደ
ከድር መጣች ከድር ሰሚራን እንዳገኛት በቅድሚያ የጠየቃት
ስለ ፋጡማ ሬሳ ነበር ሁሉንም ነገር ነገረችው እና ሬሳውም
መስጅድ ወስጥ እንዳለ ነገረችው ሀሊማን ወደ መስጅድ ይዟት
ሄዶ እንድትሰናበታት አደረገ ከዝሁር ሰላት በኃላ ተሰግዶባት
ተቀበረች...........
ሰው ትንሽ ቀዝቀዝ ብሏል ከድር ሀለቱን ለጆቹን ይዞ መጣ
ሁሉም አንድ ላይ ናቸው ሀሊማን ከፋጡማ ሞት ይልቅ የእናቷ
አሟሟት ነው ይበልጥ የጎዳት በስርአቱ እንኳን
አልተለቀሰላትም.....
በዛ ላይ አንድ አለችኝ የምትላት ፋጡማን መጣቷ ጓደኛዋ እናቷ
አክስቷ በቃ ሀሉ ነገሯ ነበረች ሀሊማ አሁን ከምንም ጊዜውም
በላይ ብቸኝነት ተሰማት.....



ዛሬ ፋጡማ ከሞተች ሶስተኛ ቀኗ ነው እንደመጀመሪያው ቀን
የሰፈሩ ሰው በጋራ ሆነው ድንኳኑን አፈረሱት ሀሊማ ሀዘኑን
ለመርሳት እየሞከረችነው ጠንካራ ለመሆን እየጣረች ነው የ
አክስቷን አላማ ለማሳካት ወስናለች ከ ሳምንት በኃላ እነ ከድር
ወደ እቤታቸው ተመለሱ ሀሊማ ሀዘኑ አለቀቃትም ለ እህትና
ለወንድሟ ብላ ጠንካራ መሆን አለባት እሱን እያሰበች ጠንካራ
ለመሆን እየሞከረች ነው ክረምት አልፎ በጋ እየመጣ ነው
ሀሊማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብታለች እህትና
ወንድሞቿም ትምህርት ጀምረዋል ሀሊማ በመጀመሪያ
ሴሜስተር የትምህርት ቤቱ የመጀመሪያው ነጥብ የእሷ ነበር
አባቷ በሀሊማ ውጤት በጣም ተደሰተ የሀሊማ ወንድም እና
እህትም ሀያትና መሀመድ 1ኛ እና 2ኛ ወጡ ይህ ውጤት
የሀሊማ የልፍት ውጤት ነው ሁለቱም ሀሊማን እንደ እናትም
እንደ እህትም ነው የሚያዮዋት እሷም ቢሆን የእናትነቱም
የእህትነቱን ሀላፊነት በሚገባ ትወጣዋለች ሀሊማ ለሰሚራ
ከምንም ግዜ በላይ ጥሩ እየሆነችላት ነው እናቷ የምታደርጋቸው
ነገሮችን ሀሊማም እያደረገች ነው፡፡ ሰሚራ በስራዋ እንድትፀፀት
እያደረገቻት , በይበልጥ ደግሞ ህሊነዋ እንዲወቅሳት
እያደረገቻት ነው ለከድርንም ቢሆን አንድ አይነት ነገር
እያደረችው ነው ሰሚራ በከድር ልጆች የቀናች ይመስላል ከድር
ከስራ እስኪመለስ ጠብቃ እራት በልተው ጨርሰው ሁሉም ተኙ
ከድር እና ሰሚራ ብቻ ሲቀሩ ከድር ከድር አለችው ለዘብ ባለ
ድምፅ አቤት አንድ ጥያቄ ለጠይቅህ ነበር ምንድ ነው ጠይቂኛ
እኔ ለ አንተ ምንህ ነኝ?
ዝም አላት ብትጠብቅ መልስ የለም እሺ አትመልስለኝ ግን ልጅ
መውለድ እፈልጋለሁ ቢያንስ ይሄን መልስልኝ......


,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••

🎶 ሆፕ lyrics🎶

07 May, 18:53


​​​​💍ሐሊማ🙋

💓ክፍል 10💞



....ሀሊማ ቀጥታ ወደ ትምህርት ቤት ነበር የሄደችው ትምህርት
ቤት እንደደረሰች መምህራኖቹ አልመጡም ነበር ሁሉም ተማሪ
ተሰብስቦ እየጠበቃቸው ነው፡፡ ከተወሰነ ደቂቃ በኃላ መምህራን
መምጣት ጀመሩ ሁሉም ተማሪ በየ ክፍሉ እንዲገባ ተደረገ
ሀሊማ እንደ ወትሮዋ ብቻዋን ናት እሷም ወደ ክፍልገባች
ትምህርት ቤቱ ላይ ከፍተኛ ውጤት ታመጣለች ተብላ
የምትጠበቀው ሀናን የምትባል ልጅ ብቻ ነች ከ አባቷ ጋር
የመጣችው ሀናን የነ ሀሊማ ክፍል ተማሪ ነች ውጤት መሰጠት
ተጀምሮዋል እንደተጠበቀውም ሀናን 91.9 ነጥብ አመጣች
ሁሉም አጨበጨቡ እነ ሀሊማ ክፍል ለሁሉም ተሰጥቶ አለቀ ከ
ሀሊማ ውጪ አስተማሪው ሀሊማን በደንብ አያውቃትም ሁሉም
ካለቀ በኃላ የ እኔስ ወጤት ብላ አስተማሪውን ጠየቀችው
አልደረሰኝም ለወደቁ ተማሪዎች አዳራሽ ነው የሚሠጠው አላት
ሀሊማ በጣም ደነገጠች የ አክስቷን ምክር አስታወሰች
እየደበራት ወደ አዳራሽ ሄደች ሁሉም ክፍል ተሰጥቶ ካለቀ በኃላ
ሀሉም ተማሪ ወደ አዳራሽ እንዲገባ ተደረገ ከትንሽ ደቂቃዎች
ቆይታ በኃላ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ንግግር ማድረግ ጀመረ
በዛሬው ቀን የልፋታቹን ውጤት ያገኛችሁበት ቀን ነው
አብዛኞቻቹ እንዳለፋቹ ይታወቃል ለሚቀጥለው ከዚህ የተሻለ
እንደምታመጡ ተስፋ እናደርጋለን የወደቃቹ ተማሪዎች በዚህ
ውጤት ተምራቹ ለሚቀጥለው አመት በቁረጠኝነት ሰርታቹ አሪፍ
ወጤት ለማምጣት ሞክሩ ዛሬ እዚህ አንድትሰበሰቡ ያደረግናቹ
በጣም የገረመን የሚገርም ነገር ስላጋጠመን ነው አስተማሪዎች
አናውቃትም ስላሉ በግሏ ክፍል ውስጥ እንዲሰጣት ስላልፈለግን
እና እኛም ቢሆን ተማሪዋን ማወቅ ስለፈለግን እዚህ መድረክ
ላይ መጥታ ውጤቷን እንድትቀበል ብለን ነው ፡፡....ብለው የተማሪዋን ስም ለመናገር ጎሮሮአቸውን ሲጠራርጉ
መብራት ሄደ የተወሰነ ሰአት ጠብቀው ጄኔኔተር ተገጥሞ
በድጋሚ ለመናገር ጎሮሮውን ጠራርጎ መናገር ጀመረ እሺ
እባካችሁን አንዴ ጆሮአቹን ስጡኝ አዳራሹ በዝምታ ተዋጠ
ሀሊማ ማን ትሁን እያለች በጉጉት እየጠበቀች ነው እሷ ብቻ
ሳትሆን ተማሪው በሙሉ እየጠበቀ ነው እሺ ብሎ መናገሩን
ቀጠለ ተማሪ ሀሊማ ከድር ብሎ ተናገረ፡፡ ተማሪው ማንሾካሸክ
ጀመረ ማን ናት እያለ እባክሽ ሀሊማ ወደ መድረኩ ተማሪው
ማጨብጨብ ጀመረ ሀሊማ ግን ደንግጣ ከተቀመጠችበት
አልተነሳችም እባክሽን ሀሊማ በድጋሚ ሲናገር ሀሊማ
ከተቀመጠችበት ወንበር ተነስታ ወደ መድረኩ ሄጀች ሁሉም
ያልጠበቁት ነገር ነው ትምህርት ቤታችን እስከ ዛሬዋ እለት
እንደዚህ አይነት ወጤት አስመዝግቦ አያውቅም ሀሊማ
የመጀመሪያዋ ናት ያመጣችው ነጥብ 99.9 ሁሉም ተማሪ
ተነስቶ አጨበጨበላት ከ ሀናን ውጪ ሁሉም ተደስቷል
ትምህርት ቤቱ ያዘጋጀላትን ሽልማት ተቀብላ ከመድረክ ላይ
ወረደች
አስተማሪዎቿ እየመጡ ይስሟታል ሀሊማ ከትምህርት ቤቱ
ወጥታ ፋጡማ ጋር እስክትሄድ በጣም ቸኩላለች ሁሉም ተማሪ
ወደ እቤቱ ሲሄድ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ሀሊማን ወደ ቢሮ
እንድትመጣ አድርጎ አድንቆቱን ገለፀላት ከቢሮ ወጥታ ቀጥታ
ወደ ፋጡማ ቤት ሄደች እንደደረሰችም በሩን ለረጅም ሰአት
አንኳኳች ግን አልተከፈተም ልትሄድ ስትል ፍጡማ ያላትን
ጉልበት ተጠቅማ በሩን ከፈተችላት ሀሊማ ፍልቅልቅ እያለች
ሳመቻትና ወደ ውስጥ ገባች ምነው አክስቴ በጣም አመመሽ
እንዴ አንገቷን እየነቀነቀች መታመሟን ነገረቻት
ዛ..ሬ...ም...ን..ድ..ነ...ው..እ..ን..ዲ.ያ...ስ..ደ..ተ..ሽ ልጄ
ብላ ጠየቀቻት የሆነውን ነገረቻት ፍጡማ ወደ እራሷ ሳብ አድርጋ
አቅፋ ሳመቻት ፋጡማ ከድርን ጥሪው አለቻት አይሆንም ብላ
ተከራከረቻት ስትለምናት እሺ ብላ ደወለችለት ባባ አክስቴ
ትፈልግሀለች እሺ መጣሁ ብሎ ስልኩ ተዘጋ ከድር ብዙም
ሳይቆይ መጣ ሰላም ብሏቸው ተቀመጠ ሀሊማን ሱቅ ላከቻት
ከከድር ጋር ለማውራት እና ሁሉንም ነገር ልትነግረው አስባ ነበር
ግን አንዳሰበችው አልሆነም ሀሊማ ከተላከችበት ቦታ በፍጥነት
ተመለሰች የፈጡማ እግር ጋር ተቀመጠች፡፡ ፋጡማ በድጋሚ
ተነሺ ማለት ከበዳት ትንፋሿ እየተቆራረጠ ነው ሀሊማም ሆነ
ከድርም አልተረዷትም ነበር ልትሞት እንደሆነ ታውቋታል ለከድር
ለመንገር የፈለገችው ለዚህም ነው ግን መናገር አልቻለችም
ፋጡማ እጃን ዘርግታ ሀሊማ ወደ እራሷ እንድትመጣ አድርጋ
ሳመቻት የሀሊማን እጅ ለ ከድር አስጨበጠችው ብቻዋን
እንዳትተዋት አደራ አለችው አክስቴ ለምንድ ነው እንደዚህ
የምትይው የተነጋገርነውስ ነገርስ አክስቴ ከድር የሀሊማን እጅ
ይዞ እንዲህ አይባልም ልጄ እያለ እያወራት ሳለ ፋጡማ ወደ
ማይቀርበት አለም አለም ወደ አሄራ ሄደች ሀሊማና ከድር
ፋጡማ እንደሞተች አላወቁም ከድር ከሀሊማ ጋር እያወራ ነው

#ክፍል_አስራ_አንድ_ለማንበብ_የቸኮለ👉🏼♥️


,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••

🎶 ሆፕ lyrics🎶

05 May, 16:42


​​💍ሀሊማ🙋

💞ክፍል ዘጠኝ💞



...ሀሊማ አሁንም እንደተኛች ናት ከድር ወደ ሀሊማ ክፍል ሄዶ
ሲያንንኳኳ መልስ የለም በሩን ለመክፈት የበሩን መክፈቻ ተጭኖ
በሩን ለመክፈት ሲሞክር.....
ዛሬ ፍጡማ ከሌላው ቀን በተለየ በጣም ታማለች ሰአቱ መሽቶዋል
ከድር ጋር ለመደወል ስትሞክር ስልኳ ለመደወል የሚያስችል
ያህል ሂሳብ አልነበረውም "ይቅርታ የሎት ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ነው
እባኮን ሂሳቦን ይሙሉ" ፈጡማ ህመሙ እየበሰባት ነው እቤቱ
ውስጥ ማንም የለም...
ከድር ሊከፍተው የነበረውነ በር መልሶ ተወው ተኝታ ከሆነ
ባልረብሻት ይሻላል ብሎ አስቦ ወደ ሳሎን ቤት ተመለሰ ሰሚራ
እራት አቅርባ መመገብ ጀመሩ ከድር እንዲሁ ቀመስ ቀመስ
አድርጎ በቃኝ ብሎ ተነሳ፡፡
ሰሚራ.... ሀሊማ እራቷን በልታለች ብሎ ጠየቀ አይ አልበለችም
ካልበለች በቃ ልቀስቅሳት ብሎ ድጋሚ ወደ ሀሊማ ክፍል ሄደ
አሁንም በሩን አንኳኳ መልስ የለም በሩን ከፍቶ ወደ ወስጥ ገባ
የበሩን መከፈት የሰማችው ሀሊማ ወዲያው ከእንቅልፏ ነቃች
በፍጥነት ዲያሪዋን ዘጋችው...ከድርም ምን እየሰራሽ ነው እንቅልፍ ይዞሽ የሄደው...እያነበብኩ ነበር...ምንድ ነበር የምታነቢው እስቲ አሳይኝ ሲላት...አይ ዝም ብሎ ነገር ነው ከድርም ከዚህ በላይ ላለማስጨነቅ
እሺ እራትሽን ብይ አላት...እሺ መጣሁ አንተ ሂድ
እሺ ብሎ ወጣ ሀሊማ ዲያሪዋን ማንም የማያገኘው ቦታ
አስቀምጣ ወደ ሳሎን ሄደች ፡፡ እራቷን በልታ እህትና ወንድሞቿን
አይታ ወደ ክፍሏ ሄደች አልጋዋ ላይ ጋደም አለች ነገር ግን
እንቅልፍ ማግኘት አልቻለችም ነበር ድንገት ፋጡማ ትዝ አለቻት
ለምን አልደውልላትም ብላ አሰበች ግን ተኝታ ሊሆን ይችላል
ከተኛች አታነሳውም ሀሊማ ነገ የ 8ተኛ ክፍል ውጤት
የምትቀበልበት ቀን ነው ውጤት ተቀብዬ ስመለስ ወደ እሷ
እሄዳለሁ ብላ አሰበች ሀሊማ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ስለ እናቷ
የሆነውን ሁሉ ለፋጡማ ነግራታለች ፋጡማ በይበልጥ
እንዲያማት ያደረጋት ይህ ዜና ነበር 1 ዘመዷን እንዲ እንደ
ታኘከ ማስቲካ አውጥተው መጣላቸው እንደ እግር እሳት
አቃጠላት ለመክሰስ ፈልጋ ነበር ግን እንደምንም ሀሊማ አሳምና
አስቆመቻት ፋጡማና ሀሊማ ሰሚራንም ከድርንም ለመበቀል
ወሰኑ ነገር ግን ለመበቀል ከፈለግሽ ትምህርትሽ ላይ አሪፍ
ውጤት ማምጣት አለብሽ ምክንያቱም ጠላትሽን በቅድሚያ
የምተበቀይው የ አንችን ስኬት በማሳየት ነው ብላት ነበር ሀሊማ
በራስ ተነሳሽነት ውጤቷ ቢስተካከልም በይበልጥ ሞራል የሆናት
ግን ፋጡማ ምክር ነበር ፡፡
ስለዚህ ልደውልና ካነሳችልኝ ነገ እንደምመጣ ልንገራት ብላ
አሰበች ሀሊማ ወደ ፋጡማ ጋር ደወለች ይጠራል ግን አይነሳም
በድጋሚ ደወለች በሁለተኛው ተነሳ ፈጡማ በጣም በተዳከመ
ድምፅ ሄ...ለ....ው አለቻት ሄለው አክስቴ
አሰለሙአለይኪ ቀሰቀሰኩሽ እንዴ አ...ይ ል...ጄ
አ...ል...ተ...ኛ...ሁ...ም
.. ሀሊማ እሺ አክስቴ ነገ እመጣለሁ ልንገርሽ ብዬ ነው እ....ሺ
አለች እሺ ቻው አክስቴ ብላ ስልኩን ዘጋቸው ብዙም ሳትቆይ
ሀሊማ እንቅልፍ ወሰዳት
እንደ ማይነጋ የለምና ነጋ ሰሚራ ቁርስ ልትሰራ ሽር ጉድ ማለት
ስትጀምር ሀሊማ ያለወትሮዋ ላግዝሽ ብላ አብራት መስራት
ጀመረች ሰሚራ ምንም ነገሩ አላማራትም ይቅርብሽ ብትላትም
አሻፈረኝ አለች ለሀሊማ እንዲህ እንድታደርግ የነገረቻት ፋጡማ
ነች ጥሩ ሁኚላት እና ህሊናዋ እንዲወቅሳት አድርጊያት ብላት
ነበር እሷም የተባለችውን እያደረገች ነው ቁርሱ ሲደርስ ሀሊማ
አቀራረበች ሁሉም አብረው በሉ ከድር ወደ ስራው ሊሄድ ሲነሳ
ሀሊማ እናቷ እንደምታደርገው የሚለብሰውን ልብስ አዘጋጀችለት
ሰሚራ በሁኔታው ብትቀናም ምንም አላለችም ነበር ከድር
ሀሊማን ሲያያት የመልኳ መመሳሰል ሁኔታዋ ሁሉ ነገሯ ዘይነባን
አስታወሰው ሆዱ ተላወሰ በድንገት አለቀሰ ሀሊማ ይህን ስታይ
ደስ አላት አላማዋ ይሄ ስለሆነ እንዳላየ ሆና ወጣች ክፍሏ ገብታ
ልብሷን ቀያይራ ወጣች....


,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••