FDRE Government Communication Service @gcsfdregovernment Channel on Telegram

FDRE Government Communication Service

@gcsfdregovernment


Use This Link For More Information

https://www.facebook.com/FDRECommunicationService?mibextid=ZbWKwL

https://twitter.com/fdreservice?lang=en

https://www.youtube.com/@gcsInfo-yj2pd

FDRE Government Communication Service (English)

Are you looking for reliable and up-to-date information from the Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE) Government? Look no further than the FDRE Government Communication Service Telegram channel! As the official communication channel of the FDRE Government, this channel provides the latest news, announcements, and updates directly from the government authorities. Whether you are a citizen, a journalist, or simply interested in staying informed about the government's activities, this channel is your go-to source for accurate and timely information. Stay connected with the FDRE Government Communication Service Telegram channel to receive notifications about press releases, policy changes, and other important government communications. Join today and be part of the conversation! For more information, visit our Facebook page at https://www.facebook.com/FDRECommunicationService, follow us on Twitter at https://twitter.com/fdreservice?lang=en, and subscribe to our YouTube channel at https://www.youtube.com/@gcsInfo-yj2pd.

FDRE Government Communication Service

08 Dec, 10:59


19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ  በታላቅ ድምቀት በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
#GCSEthiopia

FDRE Government Communication Service

03 Dec, 18:30


ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት ለመሆን ያላትን ሰፊ አቅም በስራ ላይ እያዋለች ትገኛለች። ይህ ርዕይ የሀገራችን ግብርና የጀርባ አጥንት በሆኑት ረፍት አልባ ታታሪ አርሶ አደሮች እና ወደፊት አርቆ በሚመለከተው አመራር የዘላቂ እድገት ምቹ ፖሊሲዎች ላይ የተገነባ ነው።

#pmoethiopia

FDRE Government Communication Service

03 Dec, 14:52


በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ በክላስተር እየለማ ያለው የመኸር ስንዴ ምርት
#GCSEthiopia

FDRE Government Communication Service

03 Dec, 06:03


በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ እየተሰበሰበ ያለው የመኽር ስንዴ ምርት
#GCSEthiopia

FDRE Government Communication Service

02 Dec, 06:39


ባህር ዳር
በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ ያለዉ የኮሪደር ልማት በምስል
#EBC

FDRE Government Communication Service

29 Nov, 18:06


የኮሙኒኬሽን ተቋማት በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የተናበበና የተቀናጀ የመረጃ ተደራሽነትን ይበልጥ ማጠናከር እንዳለባቸው ተገለፀ።
https://www.facebook.com/share/p/15bAHAbUuQ/

FDRE Government Communication Service

06 Nov, 05:57


📷
እንግዶች በቤተ- መንግሥት

FDRE Government Communication Service

05 Nov, 18:53


“የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል” - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
***

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች ሥራዎች በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች የመረጃ ተደራሽነትን በማጠናከር ለስኬታማነታቸው የበለጠ መስራት እንደሚገባ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ።

https://www.facebook.com/share/p/15FwkiGCTX/
    

FDRE Government Communication Service

01 Nov, 02:07


በቅርቡ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ለተሸሙት ክብርት ሰላማዊት ካሳ ሽኝት ተደረገላቸው፡፡
***

ላለፉት ሦስት ዓመታት በመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ላገለገሉትና በቅርቡ በቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት ክብርት ሰላማዊት ካሳ በአገልግሎቱ ላበረከቱት ቀና አስተዋጽኦ በአገልግሎቱ አመራርና ሠራተኞች ምስጋናና ሽኝት ተድርጎላቸዋል፡፡
https://www.facebook.com/share/p/14Xrgh4mwK/

FDRE Government Communication Service

31 Oct, 07:58


ሪዘርቭን በተመለከተ ደግሞ የብሔራዊ ባንክ ሪዘርቭ 161 በመቶ አድጓል፡፡
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

FDRE Government Communication Service

31 Oct, 07:42


ባለፉት 3  ወራት ብቻ ከExport 1.5 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል፡፡ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

FDRE Government Communication Service

31 Oct, 07:28


ከዚህ ዓመት ጀምሮ የምናንሠራራበት ጊዜ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

FDRE Government Communication Service

24 Oct, 06:24


የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት!!

በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረግነው ጥልቅ ውይይት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመሰግናለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነታችን እያደገ ቀጥሏል። ከዚህ በተጨማሪ የጋራችን የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል።

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

FDRE Government Communication Service

23 Oct, 18:29


የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አዳዲስ የዕድገት መንገዶችን ከፍቷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
************************

ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገችው የምትገኘው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አዳዲስ የዕድገት መንገዶችን መክፈቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት 3ተኛዋ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ሀገር መሆኗን ጠቁመዋል፡፡

ሀገሪቱ ለውጥ መፍጠር የሚችል ወጣት ኃይል፣ ለእርሻ ተስማሚ የሆነ ሰፊ ለም መሬት እና የታዳሽ ኃይል ምንጭ ባለቤት መሆኗንም ገልጸዋል፡፡

እነዚህ ሐብቶች ወደር የለሽ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንደሚከፍቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ''የባለብዙ ወገን ግንኙነት ለሚዛናዊ የዓለም ልማት እና ደኅንነት'' በሚል ጭብጥ በተካሄደው16ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡
#EBC

FDRE Government Communication Service

23 Oct, 11:59


ዛሬ ጠዋት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግር ያደረጉበት ''የተጠናከረ የባለብዙወገን ግንኙነት ለሚዛናዊ የአለም ልማት እና ደኅንነት'' በሚል ጭብጥ የ16ኛው የብሪክስ ጉባኤ ዝግ ስብሰባ ተካሂዷል።

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 ወደብሪክስ እንዲቀላቀሉ ከተጋበዙት ሀገራት መካከል መሆኗ ይታወቃል። ከጥር 2024 ጀምሮም የአባልነታችን እንቅስቃሴ በይፋ ጀምሯል።

#PMOEthiopia

FDRE Government Communication Service

22 Oct, 07:20


የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ሊወሰዱ የሚገቡ መፍትሔዎች፦

*ሰላምን ማፅናት
*አርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ በአካባቢ ባለው የውሃ አማራጭ በመጠቀም በጥምረት የመስኖ ስራን መስራት
*የተጀመረውን የስንዴ ኢኒሼቲቭ ምርትን ክረምት ከበጋ አጠናክሮ መቀጠል
*በከተማ እና ገጠር ተግባራዊ እየሆነ ያለው የሌማት ትሩፋት ስራን አጠናክሮ መቀጠል
*ዘላቂቅ እና ዘመን ተሻጋሪ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራን እንደየ አካባቢው መስራት
*በየጊዜው በምርምርና አዳዲስ ፖሊሲ ስራውን መደገፍና ማጠናከር
*በጉዳዩ ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራን በሁሉም አማራጮች መስራት
*የስራ እድል አማራጮችን ማስፋፋትና አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት ጥቅም ላይ ማዋል
*የገበያ አማራጭ እና የቁጠባ ዘዴዎችን መዘርጋት
*ተቋማዊ ጥረት ማጠናከር
*በዘርፉ የሀገር በቀል እውቀቶችን ማዘመን እና ጥቅም ላይ ማዋል
*ለጉዳዩ ተገቢውን ምላሽ መሰጠቱን መፈተሽ

FDRE Government Communication Service

20 Oct, 08:05


"በደቡብ ወሎ ዞን በወረኢሉ ወረዳ በ620 ሄክታር ላይ የለማው ስንዴ አመርቂ ውጤት አሳይቷል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓም

FDRE Government Communication Service

18 Oct, 11:12


የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ማናቸው?
***************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል። በዛሬው ዕለት የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ማናቸው?

ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ የእንግሊዘኛ መምህር በመሆን አገልግለዋል።

በ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽንን (ኢቢሲ) በመቀላቀል በተለያዩ ሀገራት ተዘዋውረው በጋዜጠኝነት አገልግለዋል።

በባልደረቦቻቸው ዘንድ ጠንካራ፣ ሥራ ወደድና የእቅድ ሰው ናቸው የሚባልላቸው የአሁኗ የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፣ቀጠናዊ አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በሰፊው ትንተና በመስጠትም ይታወቁ ነበር።

በ2009 ዓ.ም ፋና ብሮድካስትን በመቀላቀል በጣቢያው የራሳቸውን አሻራ ስለማኖራቸውም ይነገራል።

የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሳ በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ በቆዩባቸው ከአሥርት ዓመት በላይ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በመንቀሳቀስ አገልግለዋል።

በ2013 ዓ.ም በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ ለአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባል ሆነው የተመረጡት ሚኒስትሯ፤ ቀጥሎም ለመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሚኒስትር ዲኤታነት በመስከረም 29 ቀን 2014 ዓ.ም ተሹመዋል።

ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ እስከዛሬ በመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሚኒስትር ዴኤታነት ያገለገሉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስተር በመሆን ተሹመዋል።
#EBC

FDRE Government Communication Service

18 Oct, 10:56


ጥቅምት 8፣ 2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡

1. ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስ፦ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር
2. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፦ የቱርዝም ሚንስቴር ሚንስትር
3. ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ፦ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር

FDRE Government Communication Service

18 Oct, 07:49


አሁን ያለው ትውልድ በትብብር መወሰን ያለበት አንድ ነገር ቢኖር ልጆቻችን ላይ አብዝተን በመስራት የድህነት መጠሪያችንን በልጆቻችን መበቀል እንዳለብን ነው።

@AbiyAhmedAliofficial

FDRE Government Communication Service

16 Oct, 18:15


📷
የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች የተለያዩ ተቋማት ጉብኝት