Ethiopian Athletics Federation (EAF) @ethiopianathleticsfederation Channel on Telegram

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

@ethiopianathleticsfederation


Amateur sports team.

Ethiopian Athletics Federation (EAF) (English)

Welcome to the Ethiopian Athletics Federation (EAF) Telegram channel! Are you a fan of track and field athletics? Do you want to stay updated on the latest news, events, and achievements of Ethiopian athletes? Look no further, as this channel is the perfect place for you. The Ethiopian Athletics Federation (EAF) is dedicated to promoting and developing athletics in Ethiopia. As an amateur sports team, the EAF works tirelessly to support and nurture talented athletes, helping them reach their full potential and represent their country on the international stage. By joining our Telegram channel, you will have exclusive access to behind-the-scenes content, interviews with athletes and coaches, live event updates, and much more. Stay informed about upcoming competitions, training camps, and results of Ethiopian athletes competing in various track and field events around the world. Whether you are a die-hard fan of Ethiopian athletics or simply interested in learning more about this exciting sport, the EAF Telegram channel is the place to be. Join our community of like-minded individuals who share a passion for athletics and support the talented athletes of Ethiopia. Don't miss out on the opportunity to be part of the journey of Ethiopian athletes as they strive for excellence in the world of track and field. Join the Ethiopian Athletics Federation (EAF) Telegram channel today and be a part of something truly special!

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

07 Feb, 09:10


የአፋር ክልል ባህል፣ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ ከክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ እና ዳኞች ማህበር ጋር በመተባበር የሀገር ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ የአትሌቲክስ ዳኝነት ስልጠና የሀገር ውስጥ አንደኛ ደረጃ ላላቸው የአፋር ክልል ዳኞች በአፋር ክልል አብኣላ ከተማ መስጠት ጀምረ።
የክልሉን የአትሌቲክስ ዳኞችን ቁጥር ለማሳደግ እና በክልል ደረጃ የሚደረጉ ውድድሮችን በከፍተኛ ብቃት መዳኘት እንዲያስችላቸው በማሰብ የወቅቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዳኞች ማህበር ፕሬዝዳንት በሆኑት አቶ አዲሱ ካሳ አስተባባሪነት 30 ለሚሆኑ የክልሉ ዳኞች የሁለተኛ ደረጃ የሀገር ውስጥ የአትሌቲክስ ዳኝነት ስልጠና በአፋር ክልል ኪልበቲረሱ ዞን አብአላ ከተማ መስጠት ተጀምሯል።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱልን የአብኣላ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ወጣቶች ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም የወቅቱ የአፋር ክልል አትሌቲክስ አሰልጣኞች ማህበር ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ አብደላ አሚን ሲሆኑ ስልጠናውን በሚገባ በመከታተል የክልላችንን የአትሌቲክስ ዳኝነት በአንድ ደረጃ ከፍ እንዲያደርጉ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሰጠንን እድል በሚገባ እንድንጠቀም አሳስበዋል።
ስልጠናውን የክልሉ ባህል፣ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ ከክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ከአትሌቲክስ ዳኞች ማህበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ለስልጠናው መሳካት የተከበሩ አቶ አሊ ጊልሳ የአብአላ ሆስፒታል ሀላፊ(አዳራሽ በመስጠት)፣ አቶ ኑሩ አሚን የአሳአሌ ኮሌጅ ምክትል ሀላፊ(ፕሮጀክተር በመስጠት) ስልጠናው የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
ስልጠናውን የኢትዮጵያ እና የክልሉ የአትሌቲክስ ዳኞች ማህበር ፕሬዚዳንት በሆኑት እና የአለምአቀፍ 1ኛ ደረጃ እንዲሁም ለአለም አቀፍ ሁለተኛ ደረጃ የዳኝነት ስልጠና ያለፉትና በተጨማሪም በRace walking የbronze level የዳኝነት ደረጃ ላይ በሚገኙት አቶ አዲሱ ካሳ እና የኢትዮጵያ እና የክልሉ የአትሌቲክስ ዳኞች ማህበር ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑትና የአለምአቀፍ 1ኛ ደረጃ የዳኝነት ሰርተፍኬት ባላቸው እንዲሁም ለአለም አቀፍ ሁለተኛ ደረጃ ባለፉት ወ/ሮ ማህሌት ሹሜ አማካኝነት የሚሰጥ ይሆናል።
ስልጠናው ከጥር 28-የካቲት 7/2017 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

06 Feb, 17:18


ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ምዘና ውድድር ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው።
#####################################################
ጥር 29/2017ዓ.ም

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል "የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለአሸናፊ ሀገር"በሚል መሪ ቃል በጋራ የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ምዘና ዉድድር ተጠናክሮ ቀጥለዋል።

በዛሬዉ ዕለት በተከናወኑ የተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ፍፃሚያቸውን አግኝቷል ።
በዚህ መሰረት :-

👉በሴቶች ርዝመት ዝላይ
1ኛ አጁሉ አጅላ -ጋምቤላ -4.34
2ኛ ሀዊ ሆጤሳ -ኦሮሚያ- 4.28
3ኛ ናሜል ኒያል -ጋምቤላ -4.25

👉 በወንዶች ርዝመት ዝላይ
1ኛ በየነ ትርፈሳ -ኦሮሚያ 5.54
2ኛ ዘቤር አማን- ሱማሌ 5.21
3ኛ መስፍን ተሻለ -ኦሮሚያ 5.18

👉 ወንድ 100 ሜትር
1ኛ ናትናኤል ጥላሁን- ኦሮሚያ 11.92
2ኛ ያብሥራ በቀለ- ኦሮሚያ12.26
3ኛ ሳዳም አብዲ- ሱማሌ 12.43

👉 ሴት 400 ሜትር
1ኛ የኔነሽ ማርቆስ- ሲዳማ 01'04'05
2ኛ ፊዮሪ ታደሰ- ኦሮሚያ 01'05'18
3ኛ እፀሂወት ደሳለን- ኦሮሚያ 01'06'42

👉ወንድ 400 ሜትር
1ኛ ሞቱማ አበራ- ኦሮሚያ 54'24
2ኛ ፀጋዬ በለጠ- ደቡብ ኢትዮጵያ 56'49
3ኛ ሀጫሉ ወሊስ -ኦሮሚያ 57'24

👉 ወንድ 200 ሜት
1ኛ ነቢሣ ብርሃኑ- ኦሮሚያ 24'38
2ኛ ሚኪያስ አለሙ -ኦሮሚያ 25'42
3ኛ ይበልጣል መሀመድ -አማራ 25'50

👉ሴት 800 ሜትር
1ኛ ርብቃ ኤፍሬም- ኦሮሚያ 02'31'91
2ኛ ኤልሣ ስጦት -አማራ 02'32'63
3ኛ ሂሩት ለገሰ- ሲደማ 02'33'39

👉 ወንድ 800 ሜትር
1ኛ ወንዶ-ወሰን ፍቃዱ -ኦሮሚያ 02'02'42
2ኛ አብረሃም ለማ- ኦሮሚያ 02'02'74
3ኛ ኪሩቤል አለባቸዉ -ኦሮሚያ 02'04'40

በነገዉም ከጥዋቱ 2:00 ጀምሮ የተለያዩ
የአትሌቲክስ የፍፃሜ ዉድድሮች ይከናወናሉ ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

03 Feb, 14:22


42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ውጤት :-

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

02 Feb, 06:19


42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል።

https://t.me/EBCNEWSNOW?livestream

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

01 Feb, 21:27


ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን !

የኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አርባ ሁለተኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ነገ ጥር 25/2017 ዓ.ም ደረጃውን በጠበቀ፣ባማረ እና በልዩ ድምቀት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቀዋል ።

ሻምፒዮናው በኢቲቪ መዝናኛ ፣በኢቲቪ ዜና ቻናሎች እንዲሁም በኢቢሲ ዶትስትሪም ከማለዳው 1:00 ጀምሮ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

ስለሆነም ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን
በዚህ ታሪካዊ ሻምፒዮና ላይ ቦቦታው እና በስዓቱ ተገኝታችሁ የሚድያ ሽፋን እንድትሰጡ በማክበር እንጠይቃለን ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

01 Feb, 16:02


የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ዋና ፀሀፊ እና የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ካውንስል አባል ዶክተር ኢንጅነር ሳዲቅ ኢብራሂም
42ኛውን የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ለመታደም አዲስአበባ ገቡ።
************
ጥር 24/2017 ዓ.ም

በአለም አቀፍ አትሌቲክስ የዉድድር ኮሚሽን አባል ፣የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባልና የምስራቅ አፍሪካ ሪጅን አትሌቲክስ ዋና ፀሀፊ የሆኑት ዶ/ር ኢንጂነር ሳዲቅ ኢብራሂም በ42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ለመታደም አዲስአበባ ገብተዋል ።

በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ አቀባበል አድርጎላቸዋል ።

የኬንያ እና የሱዳን አትሌቶች ሻምፒዮናው ላይ ለመሳተፍ አዲስአበባ መግባታቸው የሚታወስ ነው።

ሻምፒዮናው በኢቲቪ መዝናኛ፣ በኢቲቪ ዜና ቻናሎች እንዲሁም በኢቢሲ ዶትስትሪም ከማለዳው 1:00 ጀምሮ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል::

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

01 Feb, 14:43


42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ፕሮግራም
42nd Janmeda International Cross Country Championships Schedule

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

01 Feb, 06:38


የ42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ካርታ

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

01 Feb, 05:03


ኬንያውያን አትሌቶች 42ኛውን የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ አዲስአበባ ገቡ።
************************************************************************
ጥር 24/2017 ዓ.ም

ኬንያውያን አትሌቶች በ42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ አዲስአበባ ገብተዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ነገ በድምቀት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል ።

ከኬንያውያን አትሌቶች ባለፈ ትናንት ማታ የሱዳን አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ሻምፒዮናው ላይ ለመካፈል አዲስአበባ ገብተዋል።

ሻምፒዮናው በኢቲቪ መዝናኛ፣ በኢቲቪ ዜና ቻናሎች እንዲሁም በኢቢሲ ዶትስትሪም ከማለዳው 1:00 ጀምሮ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል::

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

31 Jan, 19:35


የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 42ኛውን የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮናን በቀጥታ ስርጭት ያስተላልፋል ።
**************************
ጥር 23/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የፊታችን እሁድ 25/2017 ዓ.ም በድምቀት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል ።

የፌዴሬሽኑ የሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮሚቴ ዛሬ ጥር 23/2017 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቀጥታ ስርጭት ቡድን መሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል ።

ሻምፒዮናው በኢቲቪ መዝናኛ፣ በኢቲቪ ዜና ቻናሎች እንዲሁም በኢቢሲ ዶትስትሪም ከማለዳው 1:00 ጀምሮ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል::

ሻምፒዮናው በጥራት ለማስተላለፍ እና ስኬታማ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑንም ኮሚቴው ገልጿል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

30 Jan, 17:55


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቀዋል ።
#####################################################
ጥር 22/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የፊታችን እሁድ 25/2017 ዓ.ም በድምቀት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል ።

ፌዴሬሽኑ ዛሬ በቤልቪው ሆቴል ለመገናኛ ብዙሃን በሻምፒዮናው ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ እና የፌዴሬሽኑ ውድድር እና ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ በጋራ በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የሻምፒዮናው ዓላማ አትሌቶች በአገር ውስጥ የውድድር እድል እንዲያገኙ ለማድረግ፣ክልሎች ፣ከተማ አስተዳደሮችን፣ክለቦችንና የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት በጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር በማሳተፍ የእርስ በእርስ የልምምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ እድል ለመፍጠር መሆኑን በመግለጫው ተጠቁመዋል ።

በሻምፒዮናው ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሻገር የኬንያ እና የሱዳን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን፣በውድድሩ ላይም የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ፣አምባሳደሮች ፣የቀድሞ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ታዋቂና አንጋፋ አትሌቶች ፣የሚድያ አካላት ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ በመግለጫው ላይ ተብራርቷል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

30 Jan, 00:54


የቤልግሬድ 3ሺህ ሜትር ውድድር በአትሌት መሰረት የሻነህ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ።
###################################################

ጥር 22/2017

በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት መሰረት የሻነህ አሸነፈች፡፡

👉አትሌት መሰረት 8:56.32 በመግባት ውድድሩን አሸንፋለች ።

👉አትሌት መሰረት የሻነህ በ2022 በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው ከ20 አመት በታች የአትሌቲክ ሻምፒዮና በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የነሃስ ሜዳሊያ አሸናፊ መሆኗን የሚዘነጋ አይደለም ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

25 Jan, 12:11


ለመገናኛ ብዙሃን !

የኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአንደኛ ደረጃ የአለም አትሌቲክስ አሰልጣኝነትና ዳኝነት ስልጠና ምርቃት መርሀግብር ጥር 19/2017 ዓ.ም ያከናውናል ።

ስለሆነም የምርቃት መርሃግብሩ ሰኞ 19/2017 ከቀኑ 10:00 ላይ በብሉ ስካይ(Blue Sky) ሆቴል ስለሚከናወን ተገኝታችሁ የሚድያ ሽፋን እንድትሰጡ በማክበር እንጠይቃለን ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

23 Jan, 15:15


የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ ዳኝነት ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል።
##################################################
ጥር 15/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ ዳኝነት ስልጠና በአዲስአበባ ስፖርት ስልጠና ማዕከል እየሰጠው የሚገኝ ስልጠና አጠናክሮ ቀጥሏል።

ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ ዳኝነት ስልጠና በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ቀጥሎ ውለዋል ።

ስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች የተወጣጡ ሰልጣኞች እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን፣ስልጠናው በኢትዮጵያዊ ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሽመልስ ዳዊት እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው እስከ ጥር 18/2017 ዓ.ም የሚቀጥል መሆኑን የወጣው መርሀግብር ያመላክታል::

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

22 Jan, 14:12


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ ዳኝነት ስልጠና መስጠት ጀመረ።
##################################################
ጥር 14/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ ዳኝነት ስልጠና በአዲስአበባ ስፖርት ስልጠና ማዕከል ዛሬ ጥር 14/2017 ዓ.ም መስጠት ጀምረዋል ።

በስልጠናው መርሀግብር ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ ይህንን የስልጠና እድል ከዓለም አትሌቲክስ ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ በተደረገ ውይይት የተገኘ መሆኑን በማንሳት ፣ፌዴሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ከሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት አንዱ የአትሌቲክስ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑን በመጠቆም ፣ፌዴሬሽኑ ለስልጠናው ውጤት እና ስኬታማነትም በቂ በጀት መመደቡን፣ በኢትዮጵያዊ ኢንስትራክተር ስልጠናው መሰጠቱ ለአገራችን ትልቅ ኩራት መሆኑን አስገንዝበዋል ።

ኃላፊው በመጨረሻም ሰልጣኞቹ ስልጠናውን በአግባቡ እንዲከታተሉ በማሳሰብ፣ መልካም ምኞታቸውን ገልጿል ።

ስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች የተወጣጡ ሰልጣኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

ስልጠናው፣በኢትዮጵያዊ ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሽመልስ ዳዊት እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው እስከ ጥር 18/2017 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

20 Jan, 12:06


https://www.facebook.com/100063841415228/posts/pfbid027H4HLvGf2A3QDmF9YaTXTWPbM3EK9xBXyuZs31Xy8MnQ1Cr72q74UkczZxTxEKsSl/?app=fbl

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

17 Jan, 17:55


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል።
#####################################################
ጥር 09/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየሰጠ ይገኛል ።

ፌዴሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ከሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት አንዱ የአትሌቲክስ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ስልጠና ሲሆን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና በተግባር እና በንድፈ ሀሳብ በተጠናከረ ሁኔታ እየቀጠለ ይገኛል ።

ስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የተወጣጡ ሰልጣኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

17 Jan, 17:53


አትሌት እታለማሁ ስንታየሁ በዶሃ ማራቶን አሸነፈች ።
##################################################
ጥር 9/ 2017

ዛሬ በኳታር በተካሄደው የዶሃ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀናጅቷል።

በሴቶች ማራቶን አትሌት እታለማሁ ስንታየሁ አሸንፋለች።

አትሌት እታለማሁ ርቀቱን 2 :21.43 በመጨረስ ያሸነፈች ሲሆን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችም እስከ 5ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።

👉 ሙሉሃብት ጸጋ 2ኛ
👉ዝናህ ሰንበታ 3ኛ
👉 አሚነት አህመድ 4ኛ
👉 ስንታየሁ ጥላሁን 5ኛ በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል።

👉በወንዶች የማራቶን ውድድር

👉አትሌት ባለው ይሁኔ 2ኛ
👉 ምትኩ ጣፋ 3ኛ
👉 ድንቅዓም አየለ 4ኛ ደረጃን ይዟል፡፡

በወንዶች ኬንያዊው አትሌት እዝራ ኪፕኬተር ታኑይ ውድድሩን 2:7. 28 በመግባት በአንደኝነት አጠናቋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

17 Jan, 17:20


https://youtu.be/etvNC7L7Pek?si=hIGuo1Clx5EP94Ew

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

17 Jan, 13:09


አትሌት እታለማሁ ስንታየሁ በዶሃ ማራቶን አሸነፈች ።
##################################################
ጥር 9/ 2017
ዛሬ በኳታር በተካሄደው የዶሃ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀናጅቷል።
በሴቶች ማራቶን አትሌት እታለማሁ ስንታየሁ አሸንፋለች።
አትሌት እታለማሁ ርቀቱን 2 :21.43 በመጨረስ ያሸነፈች ሲሆን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችም እስከ 5ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።
👉 ሙሉሃብት ጸጋ 2ኛ
👉ዝናህ ሰንበታ 3ኛ
👉 ሚነት አህመድ 4ኛ
👉 ስንታየሁ ጥላሁን 5ኛ በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል።
👉በወንዶች የማራቶን ውድድር
👉አትሌት ባለው ይሁኔ 2ኛ
👉 ምትኩ ጣፋ 3ኛ
👉 ድንቅዓም አየለ 4ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
በወንዶች ኬንያዊው አትሌት እዝራ ኪፕኬተር ታኑይ ውድድሩን 2:7. 28 በመግባት በአንደኝነት አጠናቋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

17 Jan, 12:44


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች ሸጎሌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC)ዋና መስሪያቤት ጎበኙ ።
በተጨማሪም ከተቋሙ አመራሮች ጋር በአትሌቲክሱ እና በሚድያው ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርጓል ።
ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

06 Jan, 06:18


ዛሬ በተከናወኑ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀናጅተዋል።
###################################################

ታህሳስ 27/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ እና አትሌት ሩቲ አጋ በ2025 የዢያሜን የማራቶን ውድድር አሸንፈዋል፡፡

በሺያመን ማራቶን 2025 የወንዶች ውድድር

👉አትሌት ዳዊት ወልዴ 2:06:06 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸንፏል፡፡

👉አትሌት አሰፋ ቦኪ ውድድሩን በ2፡06፡32 በማጠናቀቅ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡

👉 በሴቶች አትሌት ሩቲ አጋ ውድድሩን 2፡18፡46 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸንፋለች ።

👉በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ በቻይና ሆንግ ኮንግዙሃይማካው ድልድይ በተካሄደው የወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር 1፡1፡27 በመግባት አሸናፊ ሆኗል።

👉በሌላ ዜና በስፔን ኢልጋቡር በተደረገ የአገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፏል ።

በወንዶች የ10 ኪሎሜትር ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ 29 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በመግባት በቀዳሚነት አጠናቋል ።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በ29 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ 3ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል ።

በሴቶች 5 ኪሎሜትር አትሌት መልክናት ውዱ በ26ደቂቃ 31 ሰከንድ 2ኛ በመሆን ውድድሯን አጠናቃለች ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

05 Jan, 08:13


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የተሰማውን ደስታ ገለፀ ።
###########################################################
ታህሳስ 27/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባካሄደው ምርጫ ላይ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አድርጎ በመምረጡ የተሰማውን ደስታ ገልጸዋል ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቢሮ በመገኘት የእቅፍ አበባና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሞዴል አውሮፕላን በማስታወሻነት በማበርከት ደስታቸውን ገልፀውላቸዋል ።

ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገራችን ኩራት መሆኑን ካነሱ ብኃላ ፌዴሬሽኑ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ በመሆን ኢትዮጵያን ማስጠራታቸው አንስተዋል ።

ፕሬዚዳንቱ አክሎም አየር መንገዱ የአትሌቲክሱ የጀርባ አጥንት መሆኑን በማንሳት ቀጣይም በርካታ ስራ መስራት እንደሚገባና በአለምአቀፍ ደረጃ አገራችንን ውጤታማ ለማድረግ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

Ethiopian Airlines Congratulates Commander Athlete Sileshi Sihine on Election as Ethiopian Athletics Federation President

Ethiopian Airlines proudly congratulates Commander Athlete Sileshi Sihine on his recent election as the President of the Ethiopian Athletics Federation.

Higher officials from Ethiopian Airlines visited Commander Athlete Sileshi Sihine at his office to express their happiness and extend their support.

During their visit, they presented him with a bouquet of flowers as a symbol of their appreciation and encouragement for his leadership.

In his speech following the gift presentation, Commander Sileshi praised Ethiopian Airlines, describing it as a source of national pride.

He compared the two institutions to "two sides of the same coin," emphasizing their interconnected roles in promoting Ethiopia's image and success.

Commander Sileshi expressed his commitment to working closely with Ethiopian Airlines, promising to foster greater achievements together.

Furthermore, he acknowledged the airline's pivotal role as the backbone of the Ethiopian Athletics Federation and appealed for its continued support.

Commander Sileshi urged Ethiopian Airlines to maintain its significant contributions to Ethiopian athletics.

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

25 Dec, 19:04


ለስፓርት መገናኛ ብዙሃን
******************
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአጭር፣መካከለኛ፣ የ3000 ሜትር መሠናክል ርምጃ የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከታህሳስ 22-26/2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ያካሂዳል ።

ፌዴሬሽኑ ያደረገውን የውድድሩ ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ዓርብ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ስለሚሰጥ ተገኝታችሁ የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡ በማክበር እንጠይቃለን፡፡

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

25 Dec, 19:03


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ አትሌት መሰረት ደፋርን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።
#######################

ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም

28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ፕሬዚዳንት እንዲሁም ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩትን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መምረጡ የሚታወስ ነው።

በጉባኤው የተመረጠው አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ የመጀመሪያ ሰብሰባውን በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት አድርጓል ።

በኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የሚመራው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን ኢንጅነር ጌቱ ገረመው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት እና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም አትሌት መሰረት ደፋር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት በማድረግ መርጧል ።

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ጨምሮም የተለያየ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን :-

👉ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ አቃቤ ንዋይና የአስተዳደር ፋይናንስ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አቶ ቢኒያም ምሩፅ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ወይዘሮ ሳራ ሀሰን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የሃብት አሰባሰብ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አቶ አድማሱ ሳጂ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የስነምግባርና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ዶክተር ኢፍራህ መሀመድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የህክምናና ፀረ አበረታች ቅመሞች ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አትሌት በላይነሽ ኦልጂራ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል

👉አትሌት የማነ ፀጋይ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በማድረግ ስብሰባውን አጠናቀዋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

25 Dec, 12:56


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በፌዴሬሽኑ ሠራተኞች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።
##############################################################
ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም
28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 12-13 /2017 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ በስካይላይት ሆቴል
መከናወኑን የሚታወስ ነው።
በዚህም መሰረት አዲስ ፌዴሬሽኑ ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩትን በፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የተመራ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በፌዴሬሽኑ ሠራተኞች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
ስራ አስፈጻሚው ኮሚቴው በተጨማሪም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሠራተኞች ጋር ትውውቅ አድርጓል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

22 Dec, 17:09


28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለቀጣይ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን የሚመሩ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በመምረጥ ተጠናቋል ።
##################################

ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም

በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለቀጣይ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን የሚመሩት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቀዋል ።

በዚህም መሰረት :-

1.ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን -ፕሬዚዳንት
2.አትሌት መሠረት ደፋር
3.ወይዘሮ ሳራ ሀሰን
4.ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ
5.ዶክተር ኢፍረህ መሀመድ
6.አቶ አድማሱ ሳጂ
7.አቶ ቢኒያም ምሩፅ
8.ኢንጅነር ጌቱ ገረመው
9.ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ
በመሆን የተመረጡ ሲሆን በጉባኤው ላይ ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

ረዳት ኮሚሽነር ክብርት አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአመራርነት ቆይታቸው አብረዋቸው ለነበሩት አካላት በማመስገን አዲስ ለተመረጡት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለአትሌቲክሱ እድገት ጠንክሮ መስራት እንዳለባቸው በመጠቆም መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ እና አደራ በመስጠት የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንቡን ለአዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን
አስረክበዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በበኩላቸው ለተሰጣቸው እድል በማመስገን በአደረጃጀት ፣በሪፎርም በተለይም በስፖርት በማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ስራ እንደሚሰሩ አብራርተዋል።ፕሬዝዳንቱ አክሎም ዘመናዊ የአትሌቲክስ ስልጠናን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አሳስበዋል ።

በጉባኤው ተገኝተው የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ መኪዩ መሀመድ አትሌቲክስ ለኢትዮጵያውያን ስፖርት ብቻ ሳይሆን ማንነት ጭምር ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክሎም አትሌቲክስ በአለም ያስተዋወቀን ገናና ስም እንዲኖረን ያደረገ የጥቁር ህዝቦች ኩራት መሆኑን በማንሳት ከዚህ ገናናነት ለምን ወደ ኋላ ተመለሰሰን ለምንስ የሜዳልያ ቁጥራችን ቀነሰ የሚለው ቁጭት አድሮባችሁ በትጋት እንድትሰሩ አሳስባለሁ ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ጀግኖች አትሌቶቻችን ትላንት የጻፋትን ታሪክ እያሰባችሁ ለማስቀጠል በርትታችሁ መስራት ይጠበቅባችኋል ሲሉ ጠይቀዋል።

በመጨረሻም የተመረጡ አዲስ አመራሮች የተጣለባችውን ሀላፊነት በመወጣት ህዝብን በቅንነት እና በታማኝነት እንድታገለግሉ ሲሉ ከአደራም ጭምር ጋር አሳስበዋል።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

01 Dec, 18:06


እንኳን ደስ አለን!!!
የ2024 የዓመቱ በሴቶች ተተኪ ወጣት (Rising Star) በመሆን አትሌት ሲምቦ አለማየሁ በዓለም አትሌቲክስ ተመርጣለች።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

01 Dec, 18:05


እንኳን ደስ አለን!!!
ከስታዲየም ውጭ በተደረጉ ውድድሮች የ2024 የዓመቱ ምርጥ አትሌት ታምራት ቶላ በዓለም አትሌቲክስ ተመርጧል።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

01 Dec, 18:05


በቫሌንሺያ ማራቶን አትሌት መገርቱ ዓለሙ አሸነፈች::
###############################################################

ህዳር 22/2017

ዛሬ ረፋድ ላይ በተካሄደው የቫሌንሺያ ሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት መገርቱ ዓለሙ አሸናፊ ሆናለች።

አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:16.49 ወስዶባታል፡፡

እንዲሁም አትሌት ጥሩዬ መስፍን ሦስተኛ ደረጃን ስትይዝ፥ ዑጋንዳዊቷ ስቴላ ቼሳንድ ሁለተኛ ሆና አጠናቅቃለች፡፡

በተያያዘ በወንዶች ቫሌንሺያ ማራቶን ዴሬሳ ገለታ 2:02.38 በመግባት ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

29 Nov, 18:29


5ኛው የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር አዳዲስ ስራ አስፈፃሚ አባላትን በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቋል ።
###############################################################

ህዳር 20/2017 ዓ.ም

5ኛው የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስአበባ ቶፕ ቴን ሆቴል ተካሄዷል ።

በጠዋቱ መርሃግብር ላይ አጠቃላይ የ2014-2016 ዓ.ም የተከናወኑ አበይት ተግባራት ዝርዝር አፈፃፀም ሪፖርት በማህበሩ ጵ/ቤት ኃላፊ አትሌት ሙሉጌታ ደምሴ የቀረበ ሲሆን በጉባኤተኞቹ ለቀረቡት ጥያቄዎች በረዳት ኮሚሽነር አትሌት ማርቆስ ገነቲ ፣ በአትሌት መሰለች መልካሙ እና በጵ/ቤት አመራሮች ማብራሪያ እና መልስ ተሰጥቶባቸዋል ።

በመቀጠልም ለቀጣይ አራት ዓመታት በስራ አስፈፃሚነት የሚመሩት አባላት በጉባኤው ላይ ተመርጠዋል ።በዚህ መሰረት :-

👉አትሌት የማነ ፀጋይ- ፕሬዝዳንት
👉አትሌት ተመስገን ወርቁ
👉አትሌት መርሲት ገብረእግዚአብሔር
👉አትሌት በላይነሽ ኦልጂራ
👉አትሌት ግርማ ጥላሁን
👉አትሌት ባንቺአየሁ ተሰማ
👉አትሌት በሽንቄ እመሼ

ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ማርቆስ ገነቲ አዲስ ለተመረጡት የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ አባላት መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ማህበሩን የጀመረውን በጎ ተግባራት እንዲያስቀጥሉ አደራ ሰጥቷል ።

በመጨረሻም አዲሱ ስራ አስፈፃሚ ቃለ መሃላ በመፈፀም ከበፊቱ አመራር አደራውን ተቀብሎ ስራውን ለመስራት ቃል በመግባት ጉባኤውን አጠናቋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

29 Nov, 13:11


5ኛው የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ አትሌት የማነ ፀጋይ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ ።
ህዳር 20/2017 ዓ.ም

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

29 Nov, 08:10


5ኛው የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በቶፕ ቴን ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል ።
################################################################

ህዳር 20/2017 ዓ.ም

5ኛው የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስአበባ ቶፕ ቴን ሆቴል በመካሄድ ላይ ሲሆን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ጉባኤውን አስጀምረዋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

26 Nov, 10:23


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለቀጣይ አራት አመታት በፕሬዝዳንትነትና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት ለመምራት የቀረቡ እጩዎች
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ህዳር 17/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታህሳስ 12-13/2017 በአዲስ አበባ ከተማ በሚያካሂደው 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት አመታት የሚመሩ ፕሬዝዳንትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን እንደሚመረጡ ይታወቃል።

በመሆኑ የእጩዎች ማቅረቢያ ቀነ ገደብ ህዳር 16/2017 ከቀኑ 11:30 ድረስ ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች እጩዎቻቸውን አሳውቀዋል። ስለሆነም በእጩዎች ተገቢነት ላይ አስፈላጊው ማጣራት እየተካሄደ መሆኑን ከግንዛቤ ገብቶ ከክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የተላኩት እጩዎች እንደሚከተለው ይሆናሉ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

23 Nov, 18:25


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአማራ ክልል ዳባት ኢንስትራክተር እንዳልክ ቀለምወርቅ የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ላይ ጉብኝት አደረገ ።
######################

ህዳር 14/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌክስ የፌዴሬሽን በአትሌቲክስ ልማት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከላት እና ተቋማት ለሚከፍቱ ባለድርሻ አካላት የድጋፍ አሰጣጥ መመሪያ መሰረት ለተቋቋሙት ማዕከላት እዉቅና በመስጠት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ነዉ።

በዚሁ መሠረት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ እና ኢ.አ.ፌ. የአትሌቲክስ ፋሲሊቲ ማህበራት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በቀለ በጋራ በመሆን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዳባት ኢንስትራክተር እንዳልክ ቀለመወርቅ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ላይ ጉብኝት አድርጓል ።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ ማዕከሉ ያለበት ደረጃ በማወቅ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍና እዉቅና ለመስጠት መሆኑን ምክትል ፕሬዝዳንትዋ ጠቁመዋል ።

ምክትል ፕሬዝዳንትዋ አክሎም ለአገራችን አትሌቲክስ እድገት እና ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ኢንስትራክተር እንዳልክ ቀለመወርቅ ማዕከሉ መሰየሙን ተገቢ መሆኑን በማንሳት ማዕከሉ በቀጣይም ፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያደርግ ጠቁመዋል ።

በምልከታው ላይ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቢምረው ካሳን ፣ አቶ ጋሻው ተቀባ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የወጣቶችና ስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ፣አቶ በአንተአምላክ ሙላት የስፖርት ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጨምሮ ፣ከፍተኛ የዞኑ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

18 Nov, 23:25


አትሌት ሰውመሆን አንተነህ የሁለተኛ ዙርና የመጨረሻ ምዕራፋ የአይን ቀዶ ጥገና ህክምና ለማድረግ ዳግመኛ ወደ ህንድ ተጓዘ ።
################################################################

ህዳር 9/2017 ዓ.ም

አትሌት ሰውመሆን አንተነህ የሁለተኛ ዙር እና የመጨረሻ ምዕራፍ የአይን ቀዶ ጥገና ህክምና ለማድረግ ዛሬ ማታ ወደ ህንድ ተጉዘዋል ።

አትሌት ሰው መሆን አንተነህ በልምምድ ላይ አያለ ባልታወቁ ሰውች በደረሰበት ጥቃት በግራ አይኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ለተሻለ የአይን ህክምና ለማግኘት ወደ ህንድ አገር ቼናይ ከተማ መጓዙን የሚታወስ ነው።

በመሆኑም በተሳካ ሁኔታ የመጀመርያ ዙር ህክምና ያደረገው አትሌት ሰውመሆን አንተነህ በህንድ አገር ቼናይ ከተማ ድሪር የአይን ህክምና ሆስፒታል የመጨረሻ ምዕራፋ ህክምና ያደርጋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የህክምና ባለሙያ ወይዘሮ ቅድስት ታደሰ ከአትሌቱ ጋር አብረውት ተጉዘዋል ።

አትሌቱ በአሁኑ ስዓት በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ቀናት የሚደረግለትን ህክምና እየተከታተልን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

17 Nov, 07:46


በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች ሽልማት ተሰጠ
***

በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ አሸናፊ ለሆኑት አትሌቶች ሽልማት የመስጠት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ 1ኛ ለወጣችው አትሌት አሳየች አይቸው ሽልማት አበርክተዋል፡፡

በውድድሩ ሁለተኛ የወጣችው አትሌት የኔዋ ንብረት ከሶፊ ማልት ተወካይ ሽልማቷን የተቀበለች ሲሆን፣ አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም ሦስተኛ ለወጣችው አትሌት ቦሰና ሙላቱ ሽልማቱን አበርክቷል፡፡

እንዲሁም በወንዶች 1ኛ የወጣው አትሌት ቢኒያም መሐሪ ሽልማቱን ከቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ እጅ ተቀብሏል፡፡
https://web.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid02NJjeudCAuSxkWF6FyNyzDsQ2shWXEfWQ4RCwCFqFQBdaBYmBYY31x7CmW85g9Euil

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

17 Nov, 07:46


አሳየች አይቼው በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሴቶች 10 ኪሎ ሜትር አሸናፊ ሆነች
***************

በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ አሳየች አይቼው አሸንፋለች።

የክለብ አጋሯ የኔዋ ንብረት ደግሞ ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቅቃለች፡፡

📸EBC DOTSTREAM
#GreatEthiopianRun #ኢትዮጵያ #EBC #etv #Ethiopia #EBCDOTSTREAM #ታላቁ_ሩጫ

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

17 Nov, 07:45


ቢኒያም መሐሪ ለሁለተኛ ጊዜ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን አሸነፈ
**************

ቢኒያም መሐሪ በወንዶች 10 ኪሎሜትር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፏል።

የኢትዮጵያ እና ሌሎች ሀገራት ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉበት የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር በቢኒያም መሐሪ አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡

ቢኒያም በሩጫው ታሪክ በተከታታይ በማሸነፍ ባለታሪክ ሆኗል፡፡

📸EBC DOTSTREAM
#GreatEthiopianRun #ኢትዮጵያ #EBC #etv #Ethiopia #EBCDOTSTREAM #ታላቁ_ሩጫ

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

16 Nov, 07:43


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ እያደረገ ይገኛል ።
##################################

ህዳር 07/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በፍሬንድሺፕ ሆቴል እያደረገ ይገኛል ።

በመድረኩ ላይ ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ውይይቱን አስጀምረዋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

14 Nov, 17:16


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ማድረጉን አሁንም አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው ::
################################################################

ህዳር 05/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሲያደርገው የነበረው የስፖርት አልባሳት ትጥቅ ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል ጉዞውን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ ላይ አድርጓል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለሙያ አቶ ቢንያም ሙሉጌታ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ በመገኘት ለክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቁን አስረክበዋል ።

በርክክቡ መርሀግብር ላይ አቶ የሺዋስ ዓለሙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አባላት የተገኙ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ላደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን የስፖርት ትጥቁን ተረክበዋል።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

12 Nov, 12:49


የአለም አትሌቲክስ እና ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአበረታች ቅመምች (doping)ህግ ጥሰት በፈፀሙ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ።
#################################

👉🏾አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ ፣ አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን እና አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ የአበረታች ቅመሞች ህግ ጥሰት የፈፀሙ መሆኑ ተረጋግጧል።

🔷በዚህም መሠረት፦
1.አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ እ.ኤ.አ February 29/2023 በተካሄደው ምርመራ ኢፒኦ (EPO) የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሙ በመረጋገጡ ለ 2 ዓመታት (እ.ኤ.አ ከApril 17/2024-April 16/2026 በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳይሳተፍ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡

2. አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን በተደረገላት የአትሌት ባይሎጂካል ፖስፖርት (ABP) ምርመራ አበረታች ቅመም መጠቀሟ የተረጋገጠ ሲሆን እ.ኤ.አ ከNovember 30/2023-November 29/2027
ለ4 ዓመታት በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳትሳተፍ ቅጣት ተጥሎባታል።

3.አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ ቻይና ሀገር ውስጥ በነበረው ውድድር ላይ በተካሄደው ምርመራ Triamcinolone acetonide የተባለውን በውድድር ወቅት የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሟ የተረጋገጠ በመሆኑ ለ2 ዓመታት(እ.ኤ.አ ከJune 3/2024-June 2/2026 በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳትሳተፍ ቅጣት ተጥሎባታል፡፡

👉🏾የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ማንኛውም አይነት የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት የሚቃወም መሆኑን እያሳወቀ ንፁህ ስፖርትን መሰረት ያደረገ አትሌቲክስ እንዲኖር በማድረግ በጋራ ዶፒንግን እንከላከል በማለት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

08 Nov, 14:30


የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ማድረጉ ፌዴሬሽኑ አሁንም አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።
********************************************************************************************
ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ለአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ ፕሮጀክቶች፣ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደሮች አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ማድረግ ነው ::

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወደ ተለያዩ ክልሎች በማቅናት የስፖርት ትጥቅ ስርጭት ሲያከናውን የቆየ ሲሆን ዛሬም ወደ አፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰመራ ከተማ በማምራት ለክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ፎዚያ እድሪስ እና የፌዴሬሽኑ የውድድር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብስራት ለጥይበሉ ለክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሰመራ ከተማ ተገኝቶ ትጥቁን አስረክበዋል ።

በርክክቡ መርሀግብር ላይ አቶ ኡመር መሀመድ የክልሉ ስፖርት፣ ባህልና ወጣቶች ኮሚሽን ምክትል ቢሮ ኃላፊ ፣ አቶ ኡመር ኢብራሂም የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ የተገኙ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ላደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን ትጥቁን በጋራ ተረክበዋል።

የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አሁንም የሚቀጥል ይሆናል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

06 Nov, 17:18


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ማድረጉን እንደቀጠለ ነው።
##########################

ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ለአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ ፕሮጀክቶች፣ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደሮች አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ማድረግ ነው ::

በዚሁ መሰረት :- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጉዞውን ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማምራት ለክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አሶሳ ከተማ በመገኘት የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ተስፍይ አስገዶም እና የኢት/አት/ፌዴ/ የእቅድ እና በጀት ቡድን መሪ አቶ ጎሳ ግርማ በጋራ በመሆን ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ትጥቁን ያስረከቡ ሲሆን ክልሉን በመወከል የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዮሱፍ አልበሽር ፣የስፖርት ማህበራት ዳይሬክተር አቶ አስማማው አዲሱ እና የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አላዛር ፀሐይ ትጥቁን በጋራ ተረክበዋል።

ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ፌዴሬሽኑ ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ክትትል ለክልሉ እንደሚያደርግ ዶክተር ተስፋይ አስገዶም በርክክቡ መርሀግብር ላይ አስገንዝበዋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

06 Nov, 15:14


አትሌት ታምራት ቶላ የ2024 ከስታዲየም ውጭ ውድድር የመጨረሻ እጩ ውስጥ ተካተተ
#######################

ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም

የዓለም አትሌቲክስ የ2024 ከስታዲየም ውጭ በተደረጉ ውድድሮች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ውስጥ ታምራት ቶላ የመጨረሻ እጩ ውስጥ ተካቷል፡፡

በወንዶቹ ዘርፍ የኦሊምፒክ አሸናፊው ታምራት ቶላ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሆኖ ለማሸነፍ ቅድመ ግምትን ያገኘ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆኗል።

የ33 ዓመቱ የረዥም ርቀት አትሌት ታምራት በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ 2:06:26 በመግባት በውድድሩ የተገኘውን ብቸኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሩ አስገኝቷል፡፡

👉🏾ከስር ባለው ሊንክ በመግባት ድምጽ እንድትሰጡት በአክብሮት እንጠይቃለን
👇👇

to vote 👉 bit.ly/3YxLVx8

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

05 Nov, 11:03


ለረጅም አመታት በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል እና ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ያገለገለችው ወ/ሮ አልጊቱ ታምራት ህልፈተ ህይወት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለሁለቱም ክልሎች እንዲሁም ለቤተሰቦቿና ወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ይመኛል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

04 Nov, 16:44


ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ተደረገ፤
#################################

ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም ዱራሜ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለፕሮጀክት ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና የስፖርት አመራሮች ዓመታዊ የስልጠናና የውድድር አልባሳት ለማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዱራሜ ከተማ በመገኘት የስፖርት ትጥቅ ድጋፉን አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አቃቢ ንዋይ አቶ ተፈራ ሞላ እና የኢት/አት/ፌዴ/ የአይሲት ባለሙያ አቶ ሰብስቤ ደሳለኝ በጋራ በመሆን ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ትጥቁን ያስረከቡ ሲሆን ክልሉን በመወከል የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ሌሊሾ ፣ የማዕ/ኢት/ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰይፈ አለሙ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ብላቱ፣ የማዕከላዊ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አላባት እና የጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ማርቆስ ባሴሮ ትጥቁን በጋራ ተረክበዋል።

ከትጥቅ ርክክቡ ጎን ለጎን የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና የቢሮ ሃላፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አት/ፌዴ/ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ብላቱ የአልቾ፣ የጉመር እና የማሻ አትሌቲክስ ፕሮጀክት ላይ ሰፊ ስራ እየተከናወነ መሆኑን በመግለፅ ፌዴሬሽኑ ያደረገውን ድጋፍ በማመስገን በቀጣይ ክልሉ በሚሰራቸው የአትሌቲክስ የልማት ስራዎች እንዲደገፍ ጠይቀዋል።

በአትሌቲክስ የባለሙያዎች ልማት በርካታ ተግባራት እንደተከናወነና በዚህ ዓመትም የህፃናት አትሌቲክስ በፓይለት ደረጃ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ስልጠናው እንዲሰጥላቸው ፍላጎቱ እንዳላቸው ገልፀዋል።

አቶ ተፈራ ሞላ በማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል የብዙ አትሌቶች መፍለቂያ እና አቅም ያለበት መሆኑን በመግለፅ እየተሰራ ያለውን ስራ አድንቀው ነገር ግን ስራዎቹ በይበልጥ ተጠናክረውና ውጤታማ ሊሆን በሚችልበት አግባብ ለመፈፀም ከአመራሩ ቁርጠኝነትና ብርቱ ስራን የሚጠይቅ መሆኑን አሳስበው በክልሉ በተጀመሩ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም በመመሪያው መሰረት አስፈላጊው ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።

መረጃዎቻችንን፦
በዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/@EthiopianAthleticsFederation1
በቴሌግራም፡- https://t.me/ethiopianathleticsfederation
በኢኒስታግራም፦ https://www.instagram.com/ethiopian.athletics/
በትዊተር፡- https://x.com/eaf_ethio
አድራሻዎቻችን ያገኟቸዋል።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

01 Nov, 09:29


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመቀለ ከተማ ሲሰጠው የነበረ የህፃናት አትሌቲክስ (Kids' Athletics ) ስልጠና አጠናቀቀ።
################################################################

ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መቀለ ከተማ በተመረጡት ትምህርት ቤቶች ሲሰጠው የነበረው የህፃናት አትሌቲክስ (kids's Athletics) ስልጠና አጠናቀዋል ።

ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡት አጠቃላይ ስልሳ ህፃናት እና አሰልጣኞችን በህፃናት አትሌቲክስ (Kids' Athletics ) ንድፈ ሀሳብ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።

በኢ.አ.ፌ. ስልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ እና ኢ.አ.ፌ ስልጠና ጥናትና ምርምር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጊዜ አድነው በጋራ በመሆን በህፃናት አትሌቲክስ ዙሪያ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው ማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ቤት የተግባር ስልጠና በመስጠት አጠናቀዋል ።

የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ /ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ማሙ ለተሰጠው ስልጠና የላቀ ምስጋና በማቅረብ ድጋፍ እና ክትትል እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስልጠና ጥናት እና ምርምር ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ የክልሉ ፌዴሬሽን ላደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን በመጥቀስ ቀጣይም ተግባሩ ጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

31 Oct, 13:52


ለድሬደዋ ከተ/አስ/አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለፕሮጀክት ሰልጣኞች ዓመታዊ የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ተደረገ፤
#########################################
ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለፕሮጀክት ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና የስፖርት አመራሮች ዓመታዊ  የስልጠናና የውድድር አልባሳትን ዛሬ ጠዋት ላይ የድሬደዋ ከተማ አስተዳድር ስፖርት ኮሚሽን ቢሮ በመገኘት የስፖርት ትጥቅ ድጋፉን አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሳራ ሃሰን እና የኢት/አት/ፌዴ/ ምክ/የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ማስተዋል ዋለልኝ በጋራ በመሆን ለድሬዳዋ ከተ/አስ/ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ትጥቁን ያስረከቡ ሲሆን ከተማ አስተዳድሩን በመወከል የድሬደዋ ከተ/አስ/ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ካሊድ መሀመድ፣ የድሬደዋ ከተ/አስ/አት/ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አቶ መሀመድ አብዱ እና የከተማ አስተዳደሩ አት/ፌዴሬሽን የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጽዮን በለጠ ትጥቁን በጋራ ተረክበዋል።

ከትጥቅ ርክክቡ ጎን ለጎን ከፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚዎች፣ የቴክኒክ ባለሙያዎች፣ አሰልጣኞችና የጽ/ቤት ሰራተኞች ጋር በከተማ አስተዳድሩ አትሌቲክሱ በሚስፋፋበትና በሚለማበት ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም ኮሚሽነር ካሊድ የአትሌቲክስ ክለቦች እንዲከፈቱ፣ የማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲስፋፉና በገጠር ቀበሌዎች ጭምር ስፖርት ተዘውታሪና ተፈቃሪ እንዲሆን በተጨማሪም ተተኪ ሃገር የሚወክሉ አትሌቶች እንዲፈሩ ሰፊ ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በአትሌቲክስ የባለሙያዎች ልማት በርካታ ተግባራት እንደተከናወነና በዚህ ዓመትም የህፃናት አትሌቲክስ በፓይለት ደረጃ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ስልጠናው እንዲሰጥላቸው ፍላጎቱ እንዳላቸው ገልፀዋል።

ወ/ሮ ሳራ ሀሰን በከተማ አስተዳደሩ እየተሰራ ያለውን ስራ አድንቀው ነገር ግን ስራዎቹ ይበልጥ ተጠናክረውና ውጤታማ ሊሆን በሚችልበት አግባብ ለመፈፀም ከአመራሩ ቁርጠኝነትና ብርቱ ስራን የሚጠይቅ መሆኑን አሳስበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስም አስፈላጊው ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል፡፡፡

መረጃዎቻችንን፦
በዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/@EthiopianAthleticsFederation1
በቴሌግራም፡- https://t.me/ethiopianathleticsfederation
በኢኒስታግራም፦ https://www.instagram.com/ethiopian.athletics/
በትዊተር፡- https://x.com/eaf_ethio
አድራሻዎቻችን ያገኟቸዋል።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

31 Oct, 12:42


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ አልባሳት ድጋፍ ስርጭቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
##################################
ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሚያከናዉናቸዉ የልማት ተግባራት መካከል በየዓመቱ ለአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ ለፕሮጀክቶች፣ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደሮች አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች የስፖርት ትጥቅ አልባሳትን ድጋፍ ማድረግ ሲሆን በዚህም መሰረት ፌዴሬሽኑ ለሃረሪ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ስርጭት አድርጓል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስጻሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሳራ ሃሰን እና የኢ.አ.ፌ. ም/የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ማስተዋል ዋለልኝ በጋራ በመሆን ለሃረሪ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ትጥቁን ያስረከቡ ሲሆን የሃረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ያሲን ዩሱፍ እና የሀረሪ ክልል አት/ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን መኩሪያ የስፖርት ትጥቁን ተረክበዋል

🔷የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ አልባሳት ድጋፍ ማድረጉን በቀሪ ክልሎችም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

24 Oct, 17:23


የአትሌት መዲና ኢሳ የ5000 ሜትር ውጤት በክብረወሰንነት ፀደቀ ::
################################################################

ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም

የአትሌት መዲና ኢሳ ከ20 ዓመት በታች የ5000 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድር የተመዘገበው ውጤት በክብረ-ወሰንነት ፀደቀ፡፡

በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው ሩጫ አትሌት መዲና ኢሳ በ14:21.89 በመግባት ውድድሩን ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የተመዘገበው 14:30.88 የውድድሩ ክብረ-ወሰን እንደነበር የሚታወስ ነው።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

24 Oct, 10:32


ለአማራ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ተደረገ።
################################################################

ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ለአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ ፕሮጀክቶች፣ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደሮች አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ማድረግ ነው ::

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአማራ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አትሌት መሰለች መልካሙ እና የፌዴሬሽኑ የሂሳብ ባለሙያ ወይዘሮ ብዙአየሁ ድረስ በጋራ በመሆን ባህርዳር ከተማ በመገኘት የስፖርት ትጥቁን አስረክበዋል ።

በርክክቡ ስነስርዓት ላይ መልዕክት ያስተላለፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ እንደተናገሩት ይህ ትጥቅ ድጋፍ የክልሉን የአትሌቲክስ ስፖርት ውጤታማነት ለመደገፍ የተደረገ መሆኑን ጠቅሶ በቀጣይም ከዚህም በተሻለ በርካታ ፕሮጀክቶችን ሊያቅፍ በሚችል መልኩ እንደሚሰራ ገልፀዋል ።

ዶ/ር ዘላለም መልካሙ የአማራ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና አቶ ጋሻው ተቀባ የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ም/ቢሮ ኃላፊ ለተደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን የስፖርት ትጥቁን ተረክቧል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

20 Oct, 10:39


በአምስተርዳም ማራቶን አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች
***************

በአምስተርዳም ማራቶን አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች።

አትሌቷ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ በማጠናቀቅ በአትሌት አልማዝ አያና ተይዞ የነበረውን የቦታውን ክብረወሰን አሻሽላለች።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

19 Oct, 20:00


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ ቀጥለዋል።
################################################################

ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚያደርገውን የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥለዋል።

ፌዴሬሽኑ ለጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበራትና አትሌቶች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በቀለ በጋምቤላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስር ለሚገኙ የአትሌቲክስ ፕሮጀክት ሰልጣኞች የስፖርት ትጥቅ ጋምቤላ ከተማ በመገኘት አስረክበዋል ።

የጋምቤላ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሆት ሮም፣የጋምቤላ ክልል ስፖርት ከሚሽን ተወካይ አቶ ታይዶር ቸንባንግ ፣አቃቢ ነዋይ አዋር ኡጅሉ ቸንኩወት ሮይ ትጥቁን የተረከቡ ሲሆን የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌደሬሽን እያከናወነው ያለዉ የትጥቅና ሞያዊ ድጋፍ የሚያበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

08 Oct, 08:48


2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ሩጫ በአለም አትሌቲክስ የውድድር ደረጃዎች ውስጥ ተካተተ!

መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የአለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪ (World Athletics) የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ሩጫን የሌብል ደረጃ ያለው የጎዳና ላይ ውድድር ((Label Road Race) ሲል ዕውቅና ሰጥቶታል።

የአለም አትሌቲክስ የሌብል ደረጃ ሲል የሰየማቸው ውድድሮች በጥራት ዝግጅቶችን ከማድረግ ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ ከመሆን እና የተሳታፊዎች ውድድሩ ላይ የነበራቸው ቆይታ ፣ የከተማ አስተዳደሮች ለዝግጅቱ ያላቸውን ድጋፍ ፣ እንዲሁም ዝግጅቱ በአትሌቲክስ ውድድር ዘርፍ አበረታች መድኃኒት ላይ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።

እጅግ በርካታ የሩጫ ውድድሮች ባሉበት አለም ይህንን የሌብል ደረጃ ማግኘት ዝግጅቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳየውን ዕድገት እና በአለማችን ካሉ ቀዳሚ እና ተመራጭ የጎዳና ላይ ውድድሮች መሀከል መሆኑን ያሳያል።

የአለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪው አካል (World Athletics) ውድድሮችን በመመዘን በየአመቱ ደረጃዎችን ይሰጣል። የመሮጫ ኮርስ ልኬት ፣ የውድድር ሰዓት ምዝገባ እና የኤሊት አትሌቶች ተሳትፎ ከግምት ውስጥ የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው።

የሌብል ደረጃ የአለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪ (World Athletics) የጎዳና ላይ ሩጫዎችን ካስቀመጠባቸው አራት ዘርፎች መሀከል አንዱ ነው። የኢሊት ፣ የወርቅ እና የፕላቲንየም ደረጃዎች ሌሎቹ ዘርፎች ናችው።

24ኛው ዙር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪሜ ህዳር 8 ቀን 2017 በ50ሺ ተሳታፊዎች ይካሄዳል፡፡



#Greatethiopianrun #worldathlet

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

06 Oct, 16:19


አትሌት ሞስነት ገረመው በሊዝበን በተካሄደው ግማሽ ማራቶን አሸናፊ ሆነ።
################################################################

መስከረም 26/2017 ዓ.ም

በፖርቹጋል ሊዝበን በተካሄደው የግማሽ ማራቶንውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሞስነት ገረመው አሸንፏል ።

አትሌት ሞስነት ገረመው 1:03.08 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ማሸነፍ ችሏል፡፡

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

04 Oct, 21:56


ዓመታዊ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ማድረግ ተጠናክሮ ቀጥለዋል።
################################################################

መስከረም 24/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ለአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ ፕሮጀክቶች፣ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደሮች አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ማድረግ ነው :: በዚሁ መሰረት :-

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶክተር ተስፋይ አስገዶም እና የፌዴሬሽኑ አትሌት አገልግሎት ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ይፍሩ በጋራ በመሆን በመቀለ ከተማ የስፖርት ትጥቁን አስረክበዋል ።

አቶ ሃፍቶም በርሀ የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ለተደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን የስፖርት ትጥቁን ተረክቧል ።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

03 Oct, 13:50


ኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ተደረገ ::
##################################
መስከረም 23/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል ።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ፣ የኢ.አ.ፌ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ እና የኢ.አ.ፌ ማህበራትና አትሌቶች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በቀለ በኩል ለኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስር ለሚገኝ የአትሌቲክስ ፕሮጀክት ሰልጣኞች የስፖርት የትጥቅ ድጋፍ አደርጓል።
በርክክቡ የተገኙት የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ጥላሁን እና የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሽመልስ ዳዊት ለተደረገው ድጋፍ ፌዴሬሽኑን በማመስገን ትጥቆችን ተረክበዋል።

Ethiopian Athletics Federation (EAF)

03 Oct, 13:36


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአዲስ አበባ ከተ/አስ/አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ።
#########################################
መስከረም 23/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ለአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ ፕሮጀክቶች፣ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደሮች አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች የስፖርት አልባሳት ድጋፍ ማድረግ ሲሆን በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ፣ የኢ.አ.ፌ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ እና የኢ.አ.ፌ ማህበራትና አትሌቶች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በቀለ በኩል ለአዲስ አበባ ከተ/አስ/ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስር ለሚገኝ የአትሌቲክስ ፕሮጀክት ሰልጣኞችና አሰልጣኞች እንዲሁም ለከተማ አስተዳደሩ ፌዴሬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች መስከረም 23/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጃን ሜዳ በመገኘት የትጥቅ ድጋፍን አድርጓል።
በርክክቡ ተገኝተው ትጥቆቹን የስረከቡት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፌዴሬሽኑ በመመሪያው መሠረት ስላደረገው ድጋፍ ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ በከተማ አስተዳደሩ በአትሌቲክስ ልማት ዙሪያ መሰራት ስለሚገባቸው ጉዳዮች የስራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን የአዲስ አበባ ከ/አ/ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ መልካሙ ተገኝ እና የአዲስ አበባ ከ/አ/ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ እታፈራሁ ገብሬ ለተደረገው ድጋፍ ፌዴሬሽኑን በማመስገን ትጥቆችን ተረክበዋል።