Tengert Sport Online Media @tengertsport Channel on Telegram

Tengert Sport Online Media

@tengertsport


Woman's sport information Source

Tengert Sport (English)

Are you a woman who is passionate about sports and wants to stay informed about the latest news and updates in the world of sports? Look no further than Tengert Sport! This Telegram channel, with the username @tengertsport, is your go-to source for all things related to women's sports. Whether you're into soccer, basketball, tennis, or any other sport, Tengert Sport has you covered. From game schedules to player profiles, from match highlights to exclusive interviews, this channel has it all. Stay connected with the exciting world of women's sports through Tengert Sport. Join us today and be a part of a community that shares your enthusiasm for women's sports!

Tengert Sport Online Media

07 Feb, 19:31


የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዠግጅት የአምስተኛ ቀን ልምምዱን አጠናክሮ እየሰራ  ይገኛል።

በዛሬው መርሐ ግብር እንደወትሮው ጠዋት በጂምናዚየም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የመስክ ልምምዱን ያከናወነ ሲሆን ሁሉም ተጫዋቾች በጥሩ ጤንነት እና መነቃቃት ላይ ይገኛሉ።

ከአሰልጣኞች ቡድን ጋር በተያያዘ አሰልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆኖ እንዲሰራ ተመድቧል።

Tengert Sport Online Media

03 Feb, 18:47


የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን  ዝግጅቱን በዛሬው ዕለት ጀምሯል

ለ2026 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ  ከዩጋንዳ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በትላንትናው ዕለት በመሰባሰብ ማረፊያውን አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው  ጋራ ላይ ሆቴል በማድረግ ለጨዋታው የሚያደርገውን የመጀመሪያ ቀን ዝግጅት ዛሬ ከቀኑ 10:30  ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም አከናውኗል።

ልምምዱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ፣ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቂናጤ እና የህክምና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል የሺዋስ ተገኝተው ቡድኑን አበረታተዋል።

በመርሐ ግብሩ ጅማሮ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ  ዮሴፍ  ገብረወልድ ጥሪ ካደረጉላቸው 29 ተጫዋቾች 25ቱ በሀገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱት ተገኝተው የመስክ ልምምዳቸውን የሰሩ ሲሆን ለበርካታ ዓመታት ሀገሯን ያገለገለችው ብርቱካን ገ/ክርስቶስ ራሷን ከብሔራዊ ብድን ተጫዋችነት ማግሏን አሳውቃለች።

የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ አብረዋቸው የሚሰሯቸው ረዳቶችን ያሳወቁ ሲሆን በምክትል አሰልጣኝነት ምትኬ አስማረ፣ በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት አስናቀች ቲቤሶ የአሰልጣኙ ረዳቶች ሆነው የሚሰሩ ይሆናል።

Tengert Sport Online Media

01 Feb, 10:03


የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ለአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ለ29 ተጫዋቾች ጥሪ አደርገዋል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ነገ (እሁድ ጥር 25) ከ8፡00 ጀምሮ አዲሱ ገበያ አካባቢ የሚገኘው " ጋራ ላይ ሆቴል " ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።

Tengert Sport Online Media

31 Jan, 18:05


የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በየካቲት ወር አራት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ያከናውናሉ።

በአሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ2026 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ ከዩጋንዳ ጋር የካቲት 14 እና የካቲት 19 የሚያከናውን ሲሆን ለማጣርያ ጨዋታዎቹ ዝግጅት እንዲረዳ ከጅቡቲ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር በመጪው የካቲት 5 እና የካቲት 9 በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋሉ።

የሴቶች ብሔራዊ ቡድናችን ለተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ከዕሁድ ጥር 25 ጀምሮ ለማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅቱን የሚጀምር ይሆናል።
EFF

Tengert Sport Online Media

17 Jan, 14:39


Ethiopian women's national team
The head coach has been announced.

Coach Yosef Gebrewold has been working as the head coach of the Hawassa women's team and the Arbaminc city women's team, and last year started coaching the Ethiopian under-20 women's national team at the African Games in Accra, Ghana.

Coach Yossef has agreed to coach the Ethiopian women's national team for two years.
They will break their contract in Arbaminc City and focus on a fully national team.

Coach Yosef will begin his national team work by preparing the team to face Uganda for the 2026 Women's Africa Cup of Nations qualifiers, which will begin one month from now.


#EthiopianWomen #Africasport #EWPL #TengertSportOnline Media

Tengert Sport Online Media

17 Jan, 13:57


የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ከዚህ ቀደም የሀዋሳ ከተማ ሴቶች ቡድን እንዲሁም ያለፉትን ሦሰት ዓመታት የአርባምንጭ ከተማ ሴቶች ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ባለፈው ዓመት በጋና አክራ የአፍሪካ ጨዋታዎች ላይም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድንን ማሰልጠናቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኝ ዮሴፍ የብሔራዊ ቡድኑን ኃላፊነት እንዲረከቡ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን አሰልጣኙም የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንን ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ለማሰልጠን ተስማምተዋል። የአርባምንጭ ከተማ ኃላፊነታቸውን በመልቀቅ ሙሉ ለሙሉ ትኩረታቸውን ብሔራዊ ቡድኑ ላይ ለማድረግም ተስማምተዋል።

አሰልጣኝ ዮሴፍ ከአንድ ወር በኋላ በ2026 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ዙር ዩጋንዳን የሚገጥመውን ቡድን በማዘጋጀት የብሔራዊ ቡድን ሥራቸውን ይጀምራሉ።


#EthiopianWomen #Africasport #EWPL #TengertSportOnlineMedia

Tengert Sport Online Media

16 Jan, 10:25


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የአዲስ አበባ ከተማ ቆይታ ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ዙር በአዲስ አበባ ሲደረግ ቆይቶ በዛሬው እለት ፍፃሜውን አግኘቷል።

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድሩ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የውድድር እና ስነስርዓት ኮሚቴ እንዲሁም የሴቶች ልማት ኮሚቴ ያደረጉት ጥረት ሊያስመሰግናቸው የሚገባ ነው ።
የሁለተኛ ዙር የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ ከየካቲት 29 ጀምሮ የሚጀምር ይሆናል ።

#EWPL #TengertSportOnlineMedia #AfricanSport #SupportHer

Tengert Sport Online Media

16 Jan, 09:17


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ አራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር የጨዋታ ውጤት!

Tengert Sport Online Media

16 Jan, 08:53


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሶስተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

89'ሳራ ነብሶ

ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ 4-1 አርባምንጭ ከተማ
02'78 ሰናይት ቦጋለ   _  06 ምርቃት ፈለቀ
68'መሣይ ተመስገን
89 ሳራ ነብሶ

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

16 Jan, 08:43


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሶስተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

78 ሰናይት ቦጋለ

ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ 3-1 አርባምንጭ ከተማ
02'78 ሰናይት ቦጋለ   _  06 ምርቃት ፈለቀ
68'መሣይ ተመስገን

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

16 Jan, 08:31


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሶስተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

68 መሣይ ተመስገን

ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ 2-1 አርባምንጭ ከተማ
02'ሰናይት ቦጋለ   _  06 ምርቃት ፈለቀ
68'መሣይ ተመስገን

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

16 Jan, 08:08


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሶስተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

46'

ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ 1-1 አርባምንጭ ከተማ
02'ሰናይት ቦጋለ   _  06 ምርቃት ፈለቀ
   
#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

16 Jan, 07:53


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሶስተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

እረፍት!

ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ 1-1 አርባምንጭ ከተማ
02'ሰናይት ቦጋለ   _  06 ምርቃት ፈለቀ
   
#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

16 Jan, 07:26


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሶስተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

20'

ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ 1-1 አርባምንጭ ከተማ
02'ሰናይት ቦጋለ   _  06 ምርቃት ፈለቀ
   
#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

16 Jan, 07:12


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሶስተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

06 ምርቃት ፈለቀ

ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ 1-1 አርባምንጭ ከተማ
02'ሰናይት ቦጋለ _ 06 ምርቃት ፈለቀ
   
#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

16 Jan, 07:11


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሶስተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

02 ሰናይት ቦጋለ'

ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ 1-0 አርባምንጭ ከተማ
02'ሰናይት ቦጋለ
   
#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

12 Jan, 09:34


Ethiopian Women's Premier League:-

The first round of the Ethiopian Women's Premier League is coming to an end and the leaders of the league, the Commercial Bank of Ethiopia, have only two games left. The Ethiopian Women's Premier League continues to highlight the talent and competitiveness of women's football in Ethiopia.

The Commercial Bank of Ethiopia is leading the competition with a wide margin of points.

Commercial Bank of Ethiopia showed exceptional performance in the first round. He played 11 games without defeat and led the table with 31 points and 20 clean sheets. In today's game, Commercial Bank beat Addis Ababa City with a score of 2-1.

The team has two games left to officially complete the first round of the game against Arbaminch City and Dredawa City.

Top scorers and outstanding players!

CBE's forward Senaf Waquma is leading the league's top scorer with 14 goals, which she has been scoring in the series of games she has played so far. As well as Serkalem Basa and Mahlet Metku Betelehem Mentelo ... each scored five goals and contributed to the success of their teams.

Upcoming matches and second round

The first round will be officially completed when CBE plays the remaining two games against Arbaminca City and Dredawa City.

Following this, the second round of the league is scheduled to start on Saturday, March 8, 2025 in Hawassa city.

#TengertSportOnlineMedia #EWPL #Africasport #EthiopianWomen'sFootball

Tengert Sport Online Media

12 Jan, 09:34


Ethiopian Women's Premier League:-

Tengert Sport Online Media

12 Jan, 09:02


ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ያለመሸነፍ ግስጋሴውን አስቀጥሏል።


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ተስተካካይ የጨዋታ መረሀ ግብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዲስ አበባ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2-1 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፎ በድጋሚ ያለመሸነፍ ግስጋሴውን አስጠብቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሁለት የማሸነፊያ ግቦች ሴናፍ ዋቁማ እና ንግስት በቀለ አስቆጥረዋል የአዲስ አበባን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ምስር ኢብራሂም አስቆጥራለች።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአስደናቂ ሁኔታ በ11 ጨዋታዎች 31 ነጥብ በመሰብሰብ የደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ተቀምጧል።

በአንፃሩ አዲስ አበባ ከተማ ምንም እንኳን ከወትሮ በተለየ መልኩ ጠንክረው ወደ ሜዳ ቢገቡም በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረባቸው ግብ ሽንፈት አስተናግደዋል። አዲስ አበባ ከተማ በ13 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

#TengertSportOnlineMedia #EWPL #Africasport #EthiopianWomen'sFootball

Tengert Sport Online Media

12 Jan, 08:50


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሁለተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

87' ጎል ንግድ ባንክ

አዲስ አበባ ከተማ 1-2 ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ

   71'ምስር ኢብራሂም   |   8'ሴናፍ ዋቁማ 
87'ንግስት በቀለ
#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

12 Jan, 08:36


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሁለተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

72' ጎል አዲስ አበባ

አዲስ አበባ ከተማ 1-1 ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ

   71'ምስር ኢብራሂም   |   8'ሴናፍ ዋቁማ 

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

12 Jan, 07:56


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሁለተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

እረፍት !

አዲስ አበባ ከተማ 0-1 ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ
                             8'ሴናፍ ዋቁማ 

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

12 Jan, 07:36


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሁለተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

30'
አዲስ አበባ ከተማ 0-1 ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ
                             8'ሴናፍ ዋቁማ 

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

12 Jan, 07:18


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የሁለተኛ ሳምንት መረሀ ግብር ጨዋታ !

15'
አዲስ አበባ ከተማ 0-1 ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ
                            8'ሴናፍ ዋቁማ 

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

10 Jan, 08:51


የሁለተኛ ዙር የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የምከናወንበት ቦታ ታውቋል።

የ2017 ዓ.ም የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ዙር ውድድር ከየካቲት 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ የሚካሄድ መሆኑን የውድድር ዳይሬክቶሬት አሳውቋል።

Tengert Sport Online Media

09 Jan, 14:10


https://t.me/Sendstarssssssbot?start=_tgr_p_h_LDhiM2Nk

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 15:27


ቀጣዩ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ......

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ያለ አሰልጣኝ እንደሚገኘ ይታወቃል ከፊታችን ወር ጀምሮ የካቲት 10- 19 2017  ከኡጋንዳ ጋር የመጀመሪያ ዙር የአፍሪካ የሴቶች ዋንጫ የማጣሪያ ውድድር ያከናውናል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ዋና አሰልጣኘ ለመሾም ከአሰልጣኝ ጋር ንግግር መጀመሩን ለማወቅ ችለናል።

በቀጣይም ትዕንግርት ስፖርት ትክክለኛ እና የተረጋገጠ የተሾመውን የአሰልጣኘኑ  መረጃ ይዛ ትቀርባለች።

#TengertSportOnlineMedia #NationalTeam #Africasport #EthiopianWomen'sFootball

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 10:02


The first round of the Ethiopian Women's Premier League 2024/25 season is drawing to a close, with Ethiopia Commercial Bank FC (CBE) leading the pack. With three crucial games remaining, the team is determined to maintain their dominant form as they face Addis Ababa City, Arba Minch City, and Dire Dawa City.

CBE's First Round Dominance
Ethiopia Commercial Bank FC has been the standout team of the first round, leading the league standings with 28 points from 10 games and an impressive goal difference of +19. Their well-rounded performance, from defense to attack, has set a high standard for the competition.

A key figure in CBE's success has been their prolific forward, Senaf Wakuma, who currently leads the league's top scorers with an outstanding 14 goals. Her ability to find the back of the net consistently has been instrumental in securing vital points for her team.

Remaining Matches in the First Round
CBE still has three matches to play before concluding the first round:

Sunday, January 12, 2025: Addis Ababa City vs. Ethiopia Commercial Bank

Thursday, January 16, 2025: Ethiopia Commercial Bank vs. Arba Minch City

TBD: Dire Dawa City vs. Ethiopia Commercial Bank


These matches will be crucial in determining whether CBE can finish the first round undefeated and solidify their lead in the standings.

League Overview
The competition remains tight across the league. Teams like Hawassa City and Mechal SC are close behind, sitting in second and third place, respectively. While CBE has set the pace, the battle for the top spots is far from over.

Top Scorers' List
Senaf Wakuma's dominance as the league's top scorer with 13 goals makes her a standout player in this season. Other players, including Serkalem Basa, Mahilat Metku, Metke Berhnu, Emushe Daniel, and Betelhem Mentelu, each with 5 goals, are also making their mark in the league.

Tengert Sport Coverage
As the first round nears its conclusion, Tengert Sport will continue providing extensive coverage. Don’t miss the action as we broadcast selected matches live on our YouTube channel and share match updates, analysis, and interviews on our social media platforms.

Join the Journey!
Be part of the excitement as we celebrate the growing prominence of women's football in Ethiopia. Follow Tengert Sport for all the latest updates and join us in supporting these talented athletes as they showcase their skills on the national stage.


#TengertSportOnlineMedia #EWPL #Africasport #EthiopianWomen'sFootball

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 10:01


Ethiopian Women's Premier League :-

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 09:08


የጨዋታ ሪፖርት፡- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሊጉ መሪ ሆኗል!

የመጀመርያው ሳምንት የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ የጨዋታ መረሀ ግብር ንግድ ባንክ እና መቻል እረፋድ 4:00 ባከናወኑት ጨዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸናፊነት ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማሸነፊያ ሦስት ግቦች ረድኤት አስረሳኸኝ ፣ መሳይ ተመስገን እና ሴናፍ ዋቁማ አስቆጥረዋል። የመቻል ብቸኛ ግብ ቤቴሌሄም ታምሩ አስቆጥራለች።

ሴናፍ ዋቁማ በውድድሩ ዓመቱ ያስቆጠረችውን የግብ ብዛት ወደ 13 በማድረስ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ደረጃን እየመራች ትገኛለች።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተስተካካይ ሦስት የጨዋታ መረሀ ግብር እየቀሩት ሊጉን በ28 ነጥብ እየመራ ይገኛል።

የአንደኛ ዙር ውድድሩን ለተከታታይ ሳምንታት በአንደኛ ደረጃ ሲመራ የቆየው ሀዋሳ ከተማ ደረጃውን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማስረከብ ተገዷል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያው ዙር ውድድር በይፋ መጠናቀቁ ይታወሳል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተስተካካይ የጨዋታ መረሀ ግብር እየቀረው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ መቀጠሉ እያሳየ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚቀጥሉት ቀናት በቀሪዎቹ ግጥሚያዎቻቸው ላይ ነጥብ የሚይዙ ከሆነ ከተከታዬቻቸው በብዙ የነጥብ እርቀት ሊጉን የሚመሩ ይሆናል።

የኢትዮጵያ የአፍሪካ ሴቶች እግር ኳስ አዳዲስ መረጃዎችን እና ጥልቅ ዘገባዎችን ለማግኘት ከትዕንግርት ስፖርት ጋር ይቆዩ


#EthiopianWomensPremierLeague #MatchReport #SupportHer @Tengertsport #ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 08:56


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የአንደኛ ሳምንት ጨዋታ !

90' ጎል ንግድ ባንክ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3-1 መቻል

52'ረድኤት አስረሳኸኝ | 32'ቤቴሌሄም ታምሩ
87' መሳይ ተመስገን
89'ሴናፍ ዋቁማ


#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 08:45


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የአንደኛ ሳምንት ጨዋታ !

87' ጎል ንግድ ባንክ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2-1 መቻል

 52'ረድኤት አስረሳኸኝ | 32'ቤቴሌሄም ታምሩ
87' መሳይ ተመስገን


#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 08:38


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የአንደኛ ሳምንት ጨዋታ !

80'

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1-1 መቻል

 52'ረድኤት አስረሳኸኝ | 32'ቤቴሌሄም ታምሩ


#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 08:17


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የአንደኛ ሳምንት ጨዋታ !

60'

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1-1 መቻል

 52'ረድኤት አስረሳኸኝ | 32'ቤቴሌሄም ታምሩ


#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 08:10


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የአንደኛ ሳምንት ጨዋታ !

53' ጎል ንግድ ባንክ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1-1 መቻል

 52'ረድኤት አስረሳኸኝ | 32'ቤቴሌሄም ታምሩ

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 08:05


https://t.me/ChristianBookss_bot?start=_tgr_HY-CimAwZDRk

Tengert Sport Online Media

08 Jan, 07:50


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ የአንደኛ ሳምንት ጨዋታ !

እረፍት !

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-1 መቻል
                             32'ቤቴሌሄም ታምሩ

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

07 Jan, 04:02


🌲 ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!

🎅 መልካም የገና በዓል ይሁንልዎ!

Tengert Sport Online Media

05 Jan, 21:03


https://youtu.be/zfhTXzn0I-0?si=5HbMZuzmOGODv9Jp

Tengert Sport Online Media

05 Jan, 21:01


https://youtu.be/t2a54ieCcEg?si=j_U4Dp_z1J3mh30y

Tengert Sport Online Media

05 Jan, 17:42


https://t.me/TgAdsPlatformBot?start=_tgr_eOEO_Wk5ZjVk

Tengert Sport Online Media

05 Jan, 17:16


Ethiopian Women's Premier League 13th week general information!


#TengertSportOnlineMedia #EWPL #Africasport #EthiopianWomen'sFootball

Tengert Sport Online Media

05 Jan, 14:45


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ9:00 ሰዓት ጨዋታ ውጤት !

ድሬዳዋ ከተማ 0-3 ሀዋሳ ከተማ
                      3' ታሪኳ ጴጥሮስ
                      27' ታሪኳ ጴጥሮስ
87' ማአድን ሰዓሉ

የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ፍጻሜውን ሲያገኝ በቀሪ ጨዋታ ረቡዕ የሚቀጥል ይሆናል!

Tengert Sport Online Media

05 Jan, 12:20


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት 6ኛ ጨዋታ በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ!

09፡00

ድሬዳዋ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ

በቀጥታ ለመከታተል 👉
https://www.youtube.com/live/klfsaVJA65I?si=j8L3y20vAT9KsqB4

Tengert Sport Online Media

05 Jan, 12:19


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት  ሁለተኛ ቀን የ7:00 ሰዓት ጨዋታ ውጤት

ልደታ ክ/ከተማ 0-0 አርባምንጭ ከተማ


እየተከናወነ ያለ ጨዋታ !
ድሬዳዋ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ


#Tengertsportonilinmedia #Africasport #SupportHer #EthiopianWomensPremierLeague

Tengert Sport Online Media

05 Jan, 10:27


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት 6ኛ ጨዋታ በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ!

07፡00

አርባምንጭ ከተማ ከ ልደታ ክ/ከተማ

በቀጥታ ለመከታተል 👉 https://www.youtube.com/live/BKZjVIe73K8?si=795hNcFLsdHGC4no

Tengert Sport Online Media

05 Jan, 10:24


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት  ሁለተኛ ቀን የ5:00 ሰዓት ጨዋታ ውጤት

ሀምበርቾ 0-1 አዲስ አበባ ከተማ
55'ሩት ያደታ


እየተከናወነ ያለ ጨዋታ !
ልደታ ክ/ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ


#Tengertsportonilinmedia #Africasport #SupportHer #EthiopianWomensPremierLeague

Tengert Sport Online Media

05 Jan, 08:03


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት  ሁለተኛ ቀን የ3 ሰዓት ጨዋታ ውጤት

ሲዳማ ቡና 2-0 ቂርቆስ ክ/ከተማ


ቀጣይ ጨዋታ !
ሀምበርቾ ከ አዲስ አበባ ከተማ


#Tengertsportonilinmedia #Africasport #SupportHer #EthiopianWomensPremierLeague

Tengert Sport Online Media

04 Jan, 19:09


https://youtu.be/NlgH9mDrRLU?si=mCay3-fZOKhi4DSj

Tengert Sport Online Media

04 Jan, 14:15


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት የ9:00 ጨዋታ ውጤት !

Tengert Sport Online Media

04 Jan, 13:49


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት  1ኛ ቀን የ9:00 ሰዓት ጨዋታ!

85'

ንግድ ባንክ 2-1 አዳማ ከተማ
40 ሴናፍ ዋቁማ /74 ገነሜ ወርቁ
64 ረድሄት አስረሳሀኝ

#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 14:43


Ethiopian Women's Premier League 12th week general information!


#TengertSportOnlineMedia #EWPL #Africasport #EthiopianWomen'sFootball

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 14:03


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ9:00 ጨዋታ ዉጤት !

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 13:36


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ9:00 ጨዋታ !

70'

ሀዋሳ ከተማ 1-2 አርባ ምንጭ ከተማ

13'እሙሽ ዳንኤል | 49'ምርቃት ፈለቀ
                            53'ስመኝ ምረቴ
#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 13:22


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ9:00 ጨዋታ !

53'ጎል አርባምንጭ ስመኝ ምረቴ

ሀዋሳ ከተማ 1-2 አርባ ምንጭ ከተማ

13'እሙሽ ዳንኤል | 49'ምርቃት ፈለቀ
53'ስመኝ ምረቴ
#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 13:16


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ9:00 ጨዋታ !

49'ጎል አርባምንጭ ምርቃት ፈለቀ

ሀዋሳ ከተማ 1-1 አርባ ምንጭ ከተማ

13'እሙሽ ዳንኤል | 49'ምርቃት ፈለቀ

#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 13:11


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ9:00 ጨዋታ !

46'

ሀዋሳ ከተማ 1-0 አርባ ምንጭ ከተማ
13 እሙሽ ዳንኤል

#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 12:56


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ9:00 ጨዋታ !

እረፍት!

ሀዋሳ ከተማ 1-0 አርባ ምንጭ ከተማ
13 እሙሽ ዳንኤል

#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 12:38


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ9:00 ጨዋታ !

30'

ሀዋሳ ከተማ 1-0 አርባምንጭ ከተማ
13 እሙሽ ዳንኤል

#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 12:22


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ9:00 ጨዋታ !

13'ጎል ሀዋሳ እሙሽ ዳንኤል

ሀዋሳ ከተማ 1-0 አርባመንጭ ከተማ
13'እሙሽ ዳንኤል

#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 12:07


ጨዋታው ተጀምሯል!
አርባምንጭ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ  ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ከአበበ ቢቂላ ስታዲየም በቀጥታ የጹሁፍ ስርጭት ! አዳዲስ መረጃዎችን በፍጥነት ይጠብቁ !

01'

ሀዋሳ ከተማ 0-0 አርባምንጭ ከተማ

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 12:04


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ሦስተኛ ጨዋታ

09፡00

ሀዋሳ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ

በቀጥታ ለመከታተል 👉 https://www.youtube.com/live/APVPFc7Wy_g?si=s26tr2MzPJGbEPWQ

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 11:59


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ7:00 ጨዋታ ዉጤት

Tengert Sport Online Media

01 Jan, 11:48


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የ7:00 ጨዋታ !

85'

ቂርቆስ ክ/ከተማ 0-1 ድሬዳዋ ከተማ
                         06 ቤቴሌም ሽመልስ


#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

31 Dec, 12:19


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት አራተኛ ጨዋታ

09፡00

አዳማ ከተማ ከ ባህር ዳር ከተማ

በቀጥታ ለመከታተል 👉 https://www.youtube.com/live/Xe3PGoHmv-o?si=WnaAfEG_YkkbUy5A

Tengert Sport Online Media

31 Dec, 12:08


ጨዋታው ተጀምሯል!

አዳማ ከተማ ከ ባህርዳር ከነማ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ከአበበ ቢቂላ ስታዲየም በቀጥታ የጹሁፍ ስርጭት ! አዳዲስ መረጃዎችን ይጠብቁ !

Kickoff! አዳማ ከተማ 0-0 ባህርዳር ከተማ

#TengertSportLive
#Tengertonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

31 Dec, 12:04


የ7:00 ሰዓት ጨዋታ ዉጤት !

Tengert Sport Online Media

31 Dec, 11:43


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን የ7:00 ጨዋታ !

75'

ኢትዮ ኤሌትሪክ 1-1 ሲዳማ ቡና
  64ቤቴሌም በቀለ      _  32' ምትኬ ብርሀኑ


#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

31 Dec, 11:31


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን የ7:00 ጨዋታ !

64'ጎል ኤሌትሪክ ቤቴሌም በቀለ'

ኢትዮ ኤሌትሪክ 1-1 ሲዳማ ቡና
  64ቤቴሌም በቀለ      _  32' ምትኬ ብርሀኑ


#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

31 Dec, 11:24


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን የ7:00 ጨዋታ !

65'

ኢትዮ ኤሌትሪክ 0-1 ሲዳማ ቡና
                        32' ምትኬ ብርሀኑ


#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

31 Dec, 11:10


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን የ7:00 ጨዋታ !

46'

ኢትዮ ኤሌትሪክ 0-1 ሲዳማ ቡና
                        32' ምትኬ ብርሀኑ


#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport Online Media

31 Dec, 10:55


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን የ7:00 ጨዋታ !

እረፍት

ኢትዮ ኤሌትሪክ 0-1 ሲዳማ ቡና
                        32' ምትኬ ብርሀኑ


#TengertSportLive
#Tengertsportonilinmedia #Africasport
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ

Tengert Sport

27 Nov, 17:20


ልደታ ክ/ከተማ ፅግነሽ አዴ ራሷ ላይ ባስቆጠረችው ብቸኛ ጎል ቦሌ ክፍለ ከተማን 1ለዐ ካሸነፈበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

https://youtu.be/ucLdirOvsmA?si=GbX6ihdOb9S49MEj

Tengert Sport

27 Nov, 09:56


ልደታ ክ/ከተማ ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የ1ኛ ቀን የ05:00 ሰዓት ጨዋታ ልደታ ክ/ከተማ ከ ቦሌ ክ/ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ልደታ ክ/ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ድል አድርጓል።

የልደታ ክ/ከተማን አንድ ግብ ቤተልሄም ከፍያለው አስቆጥራለች።

በስድስት ጨዋታዎች ምንም ግብ ሳይቆጠርባቸው በወጥ አቋም ግሩም እንቅስቃሴ እያሳዩ የሚገኙት ልደታዎቹ #በ12 ነጥብ በጊዚያዊ የደረጃ ሰንጠረዥ #2ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ በቀጣይ #በ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ሀምበርቾ ጋር ይገናኛሉ።

ሽንፈት ያስተናገዱት ቦሌ ክ/ከተማ #በ6 ነጥብ በጊዚያዊ የደረጃ ሰንጠረዥ #7ኛ ደረጃ ላይ ሲሆኑ በቀጣይ #በ7ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

27 Nov, 09:42


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የ1ኛ ቀን የ05:00 ሰዓት ጨዋታ !

80'


ልደታ ክ/ከተማ 1-0 ቦሌ ክ/ከተማ

54' ቤተልሄም ከፍያለው




#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL

Tengert Sport

27 Nov, 09:22


ጎልልል ልደታ ቤተልሄም ከፍያለው


ልደታ ክ/ከተማ 1-0 ቦሌ ክ/ከተማ

54' ቤተልሄም ከፍያለው




#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL

Tengert Sport

27 Nov, 08:51


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የ1ኛ ቀን የ05:00 ሰዓት ጨዋታ !

ዕረፍት'


ልደታ ክ/ከተማ 0-0 ቦሌ ክ/ከተማ




#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL

Tengert Sport

27 Nov, 08:33


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የ1ኛ ቀን የ05:00 ሰዓት ጨዋታ !

30'


ልደታ ክ/ከተማ 0-0 ቦሌ ክ/ከተማ




#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL

Tengert Sport

27 Nov, 08:17


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የ1ኛ ቀን የ05:00 ሰዓት ጨዋታ !

15'


ልደታ ክ/ከተማ 0-0 ቦሌ ክ/ከተማ




#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL

Tengert Sport

27 Nov, 08:04


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን የ05፡00 ጨዋታ

ልደታ ክ/ከተማ ከ ቦሌ ክ/ከተማ

በቀጥታ ለመከታተል 👉 https://www.youtube.com/live/d9iHkGlJN-c?si=76OWcG6Z-ZUSDgcn

Tengert Sport

27 Nov, 08:01


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የ1ኛ ቀን የ05:00 ሰዓት ጨዋታ !

ተጀምሯል !


ልደታ ክ/ከተማ 0-0 ቦሌ ክ/ከተማ




#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL

Tengert Sport

27 Nov, 07:53


ሀዋሳ ከተማ በጊዚያዊነት የሊጉ መሪ ሆኗል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመጀመሪያ ጨዋታ 03:00 ሰዓት ላይ ሀምበርቾ ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግብ ከዕረፍት በፊት እሙሽ ዳንኤል እና ፀጋ ንጉሴ ሲያስቆጥሩ ከዕረፍት መልስ ቅድስት ቴቃ አስቆጥራለች።

የሀምበርቾን አንድ ግብ ሄለን ዘብዲዮስ አስቆጥራለች።

ድል ማስመዝገብ የቻሉት ሀዋሳ ከተማ #በ13 ነጥብ በጊዚያዊ የደረጃ ሰንጠረዥ #1ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በቀጣይ #በ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ባህር ዳር ከተማ ጋር ይገናኛሉ።

ስድስት ጨዋታዎችን አድርገው #10 ግብ ተቆጥሮባቸው ነጥብ ማግኘት ያልቻሉት ሀምበርቾ በቀጣይ #በ7ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ልደታ ክ/ከተማ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL
📸Soccer Ethiopia
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

26 Nov, 15:54


የቀጥታ ሥርጭት ጥቆማ!

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ሁለተኛ የሆነውን የልደታ ክ/ከተማ እና የቦሌ ክ/ከተማ ጨዋታ ነገ ከረፋድ 4፡30 ጀምሮ በተሻለ ጥራት በኦሎምፕያድ ስፖርት ሚዲያ ይጠብቁ!

✔️ የአሰልጣኞች ቅድመ ጨዋታ እና ድኅረ ጨዋታ አስተያየት

✔️ ሙሉ ጨዋታ ከኮሜንታሪ እና ትንተና ጋር

✔️ ተደጋጋሚ እና ጥራት ያላቸው መልሶ ምልከታዎች ( ኃይላይት )

✔️ ታክቲካል ዕይታዎች እና ጥቆማዎች

ኦሎምፕያድ ስፖርት ሚዲያ

LINK 👉 https://youtube.com/@olympiadsport?si=Dw8sBvq-d0iB_DkV

Tengert Sport

26 Nov, 15:09


የኢትዮጵያ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ የ1ኛ ሳምንት አጠቃላይ ሙሉ መረጃዎች !

- የደረጃ ሰንጠረዥ
- የ2ኛ ሳምንት ሙሉ ፕሮግራም
- የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃ

#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWHL

Tengert Sport

22 Nov, 12:05


የጨዋታ ኃይላይት እና የአሰልጣኞች አስተያየት

መቻል በቤተልሔም መንተሎ ብቸኛ ግብ አርባምንጭ ከተማን 1ለ0 ካሸነፈበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

ተከታዩን LINK ተጭነው የጨዋታውን ኃይላይት እና የአሰልጣኞች አስተያየት ይመልከቱ 👉
https://youtu.be/cyKhiteyjs8?si=nrR4Lwcb1IHcLt1N

Tengert Sport

22 Nov, 08:59


የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በመቻል ድል አድራጊነት ተጠናቋል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመጀመሪያ ጨዋታ 04:00 ሰዓት ላይ መቻል ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ መቻል 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፏል።

የመቻልን የማሸነፊያ ግብ ቤተልሄም መንተሎ አስቆጥራለች።

የሳምንቱን ተጠባቂ ጨዋታ የበላይ በመሆን ድል የተጎናጸፉት መቻል #በ10 ነጥብ በጊዚያዊ የደረጃ ሰንጠረዥ #2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት በቀጣይ #በ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ድሬዳዋ ከተማ ጋር ይጫወታሉ።

ሁለተኛ ሽንፈታቸውን ያስመዘገቡት አርባምንጭ ከተማ #በ4 ነጥብ በጊዚያዊ የደረጃ ሰንጠረዥ #9ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ በቀጣይ #በ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ አዲስ አበባ ከተማ ጋር ይገናኛሉ።


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL
📸Soccer Ethiopia
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

22 Nov, 06:51


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ

4፡00

መቻል ከ አርባምንጭ ከተማ

ጨዋታውን በቀጥታ ለመከታተል 👉 https://www.youtube.com/live/0BUT14GvzZw?si=thS1ZTsXnzHz5Z2H

Tengert Sport

21 Nov, 13:30


የቀጥታ ሥርጭት ጥቆማ!

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት የመጀመሪያ የሆነውን የመቻል እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ነገ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በተሻለ ጥራት በኦሎምፕያድ ስፖርት ሚዲያ ይጠብቁ!

✔️ የአሰልጣኞች ቅድመ ጨዋታ እና ድኅረ ጨዋታ አስተያየት

✔️ ሙሉ ጨዋታ ከኮሜንታሪ እና ትንተና ጋር

✔️ ተደጋጋሚ እና ጥራት ያላቸው መልሶ ምልከታዎች ( ኃይላይት )

✔️ ታክቲካል ዕይታዎች እና ጥቆማዎች

ኦሎምፕያድ ስፖርት ሚዲያ

LINK 👉 https://youtube.com/@olympiadsport?si=Dw8sBvq-d0iB_DkV

Tengert Sport

20 Nov, 11:42


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ4ኛ ሳምንት አጠቃላይ መረጃዎች | የቀጣይ ሳምንት ፕሮግራም !

-የደረጃ ሰንጠረዥ
-የ4ኛ ሳምንት ውጤት
-የ5ኛ ሳምንት ፕሮግራም


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL

Tengert Sport

20 Nov, 08:53


ሲዳማ ቡና መሪነቱን አጠናክሯል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ረፋድ 04:00 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉት ጨዋታ በሲዳማ ቡና 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ሁለት ግብ ከዕረፍት በፊት ምትኬ ብርሃኑ ስታስቆጥር ከዕረፍት መልስ ቤዛዊት መንግስቱ (በራሷ ላይ) አስቆጥራለች።

ባህር ዳር ከተማ ከሽንፈት ያልታደገች አንድ ግብ መንደሪን ታደሰ አስቆጥራለች።

አራት ጨዋታዎችን አድርጎ #10 ነጥቦችን በመሰብሰብ #1ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎቹ በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ጨዋታውን ያከናውናል።

የድል ግስጋሴያቸውን ማስቀጠል ያልቻሉት ባህርዳር ከተማ ተከታታይ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን ሲያስመዘግቡ #በ4 ነጥብ #9ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይጫወታሉ።


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL
📸Soccer Ethiopia
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

19 Nov, 19:31


የጨዋታ ኃይላይት እና የአሰልጣኞች አስተያየት

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በማህሌት ምትኩ ብቸኛ ግብ ሀምበርቾን 1ለ0 ካሸነፈበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

ተከታዩን LINK ተጭነው የጨዋታውን ኃይላይት እና የአሰልጣኞች አስተያየት ይመልከቱ 👉
https://youtu.be/xI8Vd9UPSVI?si=EiLssT8OijjzWjE_

Tengert Sport

19 Nov, 13:52


ኤሌክትሪክ ወደ ድል ተመልሷል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የ2ኛ ቀን የ09:00 ሰዓት ጨዋታ ሀምበርቾ ከ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ኤሌክትሪክ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፏል።

የኤሌክትሪክን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ከዕረፍት በፊት ማህሌት ምትኩ አስቆጥራለች።

ወደ ድል የተመለሱት ኢትዮ ኤሌክትሪክ #በ6 ነጥብ በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ #5ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ባህር ዳር ከተማ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

አራተኛ ሽንፈታቸውን ያስመዘገቡት ሀምበርቾ የደረጃ ግርጌ ላይ ሲቀመጡ በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ቂርቆስ ክ/ከተማ ጋር ይገናኛሉ።


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL
📸Soccer Ethiopia
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

19 Nov, 12:55


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት 5ኛ ጨዋታ

ዕረፍት !

ሀምበርቾ 0-1 ኢትዮ ኤሌክትሪክ

በቀጥታ ለመከታተል 👉 https://www.youtube.com/live/VCPb5bYZofA?si=_7dJWIexT8wjrzcU

Tengert Sport

19 Nov, 11:52


ልደታ ክ/ከተማ ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን አስመዝግቧል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የ2ኛ ቀን የ07:00 ሰዓት ጨዋታ ልደታ ክ/ከተማ ከ ቂርቆስ ክ/ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ልደታ ክ/ከተማ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የልደታ ክ/ከተማን የማሸነፊያ ሁለት ግብ ሳሮን ሰመረ እና ይታገስ ተገኘወርቅ አስቆጥረዋል።

በአሰልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለ የሚመራው እንዲሁም ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን ድል ማድረግ የቻሉት ልደታዎቹ #በ8 ነጥብ በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ #2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

ሦስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቂርቆስ ክ/ከተማ #በ3 ነጥብ በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ #11ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ሀምበርቾ ጋር ይጫወታሉ።


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL
📸Soccer Ethiopia
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

18 Nov, 17:55


የቀጥታ ሥርጭት ጥቆማ!

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት 5ኛ የሆነውን የሀምበርቾ እና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ ነገ ከ8፡40 ጀምሮ በተሻለ ጥራት በኦሎምፕያድ ስፖርት ሚዲያ ይጠብቁ!

✔️ የአሰልጣኞች ቅድመ ጨዋታ እና ድኅረ ጨዋታ አስተያየት

✔️ ሙሉ ጨዋታ ከኮሜንታሪ እና ትንተና ጋር

✔️ ተደጋጋሚ እና ጥራት ያላቸው መልሶ ምልከታዎች ( ኃይላይት )

✔️ ታክቲካል ዕይታዎች እና ጥቆማዎች

ኦሎምፕያድ ስፖርት ሚዲያ

Link 👉 https://youtube.com/@olympiadsport?si=PosoJhyNHhM-OQFu

Tengert Sport

18 Nov, 08:15


የቀድሞ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ፣ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ የድሬዳዋ ከተማ ቡድንን ማሳለፍ የቻለችው እንዲሁም ፣ የቀድሞ የድሬዳዋ፣ የአዲስ አበባ አሁን ደሞ የኢትዮ ኤሌክትሪክ ዋና አሰልጣኝ እና ኢንስትራክተር መሰረት ማኔ የድሬ አዋርድን በስፖርቱ ዘርፍ ተሸላሚ በመሆን ሽልማቷን ወስዳለች።

Tengert Sport

18 Nov, 05:01


መቻል 2 ለ 0 አዲስ አበባ ከተማ

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት የ1ኛ ቀን የ09:00 ሰዓት ጨዋታ መቻል በቤተልሄም መንተሎና በትዕግስት ወርቄ ግቦች  አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ የጨዋታው እንቅስቃሴዎችን እና ግቦችን እነሆ !
#HIGHLIGHTS​ | Addis Abeba 0-2 Mechal | Ethiopian Women's Premier League GW
https://youtu.be/llxz255DQWw?si=oZrTlWCWcSs2Svaq

Tengert Sport

17 Nov, 20:23


አርባምንጭ ከተማ 0-1 አዳማ ከተማ

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን የ7 ሰዓት ጨዋታ አዳማ ከተማ በጽዮን ዋጅና ብቸኛ ጎል አርባምንጭ ከተማን 1ለ0 የረታበት ጨዋታ ኃይላይት እነሆ !

https://youtu.be/USXTnNhTdT8?si=jp3H_yq7WrY2f1rc

Tengert Sport

17 Nov, 13:59


መቻል ድል አድርጓል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የ1ኛ ቀን የ09:00 ሰዓት ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማ ከ መቻል ጋር ያደረጉት ጨዋታ መቻል 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የመቻልን የማሸነፊያ ሁለት ግብ ቤተልሄም መንተሎ እና ትዕግስት ወርቄ አስቆጥረዋል።

በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን ድል ማድረግ የቻሉት መቻል #በ7 ነጥብ በሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ በግብ ክፍያ ተበልጠው በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ #4ኛ ደረጃ በመያዝ በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ጨዋታውን ያከናውናሉ።

በሦስት ጨዋታ #1 ነጥብ ብቻ ማግኘት የቻሉት አዲስ አበባ ከተማ በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ #12ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ቦሌ ክ/ከተማ ጋር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL
📸Soccer Ethiopia
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

17 Nov, 11:57


አዳማ ከተማ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የ1ኛ ቀን የ07:00 ሰዓት ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ ከ አዳማ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ በአዳማ ከተማ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የአዳማ ከተማን ብቸኛ የሆነችውን የማሸነፊያ አንድ ግብ ፅዮን ዋጅና አስቆጥራለች።

የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ #በ4 ነጥብ በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ #6ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ መቻል ጋር ይገናኛሉ።

የመጀመሪያ ድል ያስመዘገቡት አዳማዎቹ #በ5 ነጥብ በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ #5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ድሬዳዋ ከተማ ጋር ይጫወታሉ።


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL
📸Soccer Ethiopia
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

17 Nov, 09:24


ሀዋሳ ከተማ ሦስተኛ ተከታታይ ድላቸውን አስመዝግበዋል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የአንደኛ ቀን ጨዋታ 04:00 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማ ከ ቦሌ ክ/ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሀዋሳ ከተማን ግብ ከአምላክነሽ ሀንቆ እና ሰላማዊት ጎሳዬ አስቆጥረዋል።

ተከታታይ ሦስተኛ የድል ግስጋሴያቸውን ማስቀጠል የቻሉት ሀዋሳ ከተማ #በ9 ነጥብ በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ #1ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ልደታ ክ/ከተማ ጋር ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

ሦስተኛ ተከታታይ ሽንፈት ያስመዘገቡት ቦሌ ክ/ከተማ #በ3 ነጥብ በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ #9ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ በቀጣይ #በ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ አዲስ አበባ ከተማ ጋር ይገናኛሉ።


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL
📸 soccer Ethiopia
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

16 Nov, 19:10


ኤዶ ኩዊንስ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፏል !

በምድብ ሁለት ሌላኛው ጨዋታ የሆነው ድራማዊ ትዕይንት የተመለከተበት ጨዋታ የደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ከ ናይጄሪያው ኤዶ ኩዊንስ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እስከ 90+4 1 ለ 0 ሲመሩ ቢቆዩም ኤዶ ኩዊንስ በሽርፍራፊ ደቂቃ በ90+5 እና በ90+10 ባስቆጠሩት ሁለት ግቦች ታግዘው አንጋፋውን ቡድን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጥለው ወደ ግማሽ ፍፃሜ ተቀላቅለዋል።


#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

16 Nov, 18:58


ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተረቷል !

በካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከግብጹ ተወካይ ኤፍ ሲ ማሳር ጋር ያደረጉት የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የኤፍ ሲ ማሳርን የማሸነፊያ ግብ ሳንድሪኔ ኒዮንኩሩ እና ያስሚን ሀሳኒን አስቆጥረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከሽንፈት ያልታደገች አንድ ግብ ሴናፍ ዋቁማ አስቆጥራለች።

ኢትዮጵያን በመወከል በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የተጫወተው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውድድሩ ላይ ያለምንም ነጥብ አንድ ግብ ብቻ ሲያስቆጥሩ በተቃራኒው በሦስት ጨዋታ #9 ግቦች ተቆጥሮባቸው ከምድብ ተሰናብተዋል።

ኤፍ ሲ ማሳር ከምድቡ አንደኛ በመሆን ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፏል።


#CAFWCL2024
#TengertWomenSportET
@tengertsport
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

16 Nov, 18:52


የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 3ኛ ጨዋታ !

90+4' ንግድ ባንክ ጎልልልል

ማሳር 2-1 ንግድ ባንክ


#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

16 Nov, 18:43


የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 3ኛ ጨዋታ !

86' ጎልልልል

ማሳር 2-0 ንግድ ባንክ


#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

16 Nov, 18:31


የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 3ኛ ጨዋታ !

75'

ኤፍ ሲ ማሳር 1-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

22' ሳንድሪኔ ኒዮንኩሩ


#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

16 Nov, 18:03


የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 3ኛ ጨዋታ !

45'

ኤፍ ሲ ማሳር 1-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
22' ሳንድሪኔ ኒዮንኩሩ


#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

16 Nov, 17:49


የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 3ኛ ጨዋታ !

እረፍት !

ኤፍ ሲ ማሳር 1-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
22' ሳንድሪኔ ኒዮንኩሩ


#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

16 Nov, 17:29


የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 3ኛ ጨዋታ !

30'

ኤፍ ሲ ማሳር 1-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

22' ሳንድሪኔ ኒዮንኩሩ


#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

16 Nov, 17:21


የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 3ኛ ጨዋታ !

21' ጎልልልል

ማሳር 1-0 ንግድ ባንክ


#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

16 Nov, 17:07


የጨዋታ ኃይላይት እና የአሰልጣኞች አስተያየት

ድሬዳዋ ከተማዎች ከመመራት ተነስተው ባህር ዳር ከተማን 3ለ1 ካሸነፉበት የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

ተከታዩን LINK ተጭነው የጨዋታውን ኃይላይት እና የአሰልጣኞች አስተያየት ይመልከቱ
https://youtu.be/Qb5Oth_HvMw?si=pCXtj3q0U5LDi8uD

Tengert Sport

16 Nov, 17:01


የካፍ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ 3ኛ ጨዋታ

ጨዋታው ተጀምሯል !

01 '| ማሳር 0-0 ንግድ ባንክ


#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

16 Nov, 16:49


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ ታውቋል !

የካፍ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ 3ኛ ጨዋታ

02፡00 ሰዓት ላይ ማሳር ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Tengert Sport

10 Nov, 11:08


የጨዋታ ቀን !

ኢትዮጵያን በመወከል ለመጀመሪያ ጊዜ የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ  ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምድብ የመጀመሪያውን ጨዋታ ዛሬ እሁድ ቀትር 11:00 ሰዓት ከናይጄሪያው ተወካይ ኢዶ ኩዊንስ ጋር ጨዋታውን ያከናውናል።

#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET

Tengert Sport

10 Nov, 06:02


https://youtu.be/E6PmLvHnTZA?si=F4wpJO0hfcRc9use

Tengert Sport

09 Nov, 19:32


2 ጎሎች በ22 ደቂቃ። 🥳

ዛሬ በተጀመረው የካፍ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታ የአስተናጋጇ ሀገር ሞሮኮ ተወካይ የሆነው አስ ፋር የሴኔጋሉን ተወካይ ኤግልስ ዴ ላ መዲናን 3ለ0 ባሸነፈበት ጨዋታ ዶሃ ኤል ማዳኒ በ22 ደቂቃ ሁለት ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችላለች።

#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET

Tengert Sport

09 Nov, 19:26


በአስደናቂ እንቅስቃሴ Sanaa Mssoudy ለ ASFAR የጨዋታው ኮከብ ተብላለች። 🔥

#CAFWCL2024
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

09 Nov, 19:24


የውድድሩ አዘጋጅ እና የ2022 ሻምፒዮና ASFAR በካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የሴኔጋል ተወካዩን አይግል ደላ ሜዲናን 3-0 በማሸነፍ የምድብ ጨዋታውን በድል ጀምረዋል።

#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

09 Nov, 16:52


ላቾ ማርታ የቲፒ ማዜምቤ የጨዋታው ኮከብ ተብላለች። 👏

#TengertWomenSportET
#CAFWCL2024
@tengertsport

Tengert Sport

09 Nov, 16:46


ቲፒ ማዜንቤዌች የመጀመርያ ጨዋታቸውን በድል ተወጥተዋል!

በአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ቲፒ ማዜንቤ ዌስተር ኬፕ ዩኒቨርሰቲን 2ለ 0 በማሸነፍ ጀምሯል

የቲፒ ማዜንቤን የማሸነፍያ ግቦች
ላቾ ማርታ በ61ኛውና ታቼንጋ ናንጁኒ በ77ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል

#CAFWomenCL24
#TengertWomenSportET
@tengertsport
@Arada_Sport

Tengert Sport

09 Nov, 13:13


በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያ የተወከለችበት የካፍ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ዛሬ በሞሮኮ ይጀመራል።

የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ቀትር 11:00 ላይ ከናይጄሪያው ተወካይ ኡዱ ኩዊንስ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን ያከናውናል።

የምድብ አንድ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ጅማሮውን አድርጓል።

#TengertWomenSportET
#CAFWomenCL24
@tengertsport

Tengert Sport

09 Nov, 11:37


የአሰልጣኝ ፍሬው ሀ/ገብርኤል አዲሱ ክለብ የሆነው የዩጋንዳው ካምፓላ ኩዊንስ ዛሬ በሀገሪቱ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ከአሞስ ኮሌጅ ጋር ባደረገው ጨዋታ 2-0 መርታት ችሏል። የድል ጎሎቹ የተቆጠሩት ከዕረፍት በፊት (በ10ኛው እና 42ኛው ደቂቃ) በተቆጠሩ ጎሎች ነው።

Tengert Sport

09 Nov, 11:24


ዛሬ በሞሮኮ የሚደረገው የካፍ የሴቶች ቻምፕዮንስ ሊግ #CAFWCL2024 በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፎባቸው እነሆ! 📺 !

Tengert Sport

09 Nov, 08:58


የሳምንቱን ተጠባቂ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ የሆነው የ04:00 ሰዓት ላይ የጀመረው ሀዋሳ ከተማ ከ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፏል።

የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ እፀገነት ግርማ አስቆጥራለች።

ከሽንፈት ማግስት የውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን ማሳካት የቻለው ሀዋሳ ከተማ በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ በ#3 ነጥብ #6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በቀጣይ #በ3ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ቂርቆስ ክ/ከተማ ጋር ይገናኛሉ።

የ2017 የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ሽንፈት ያስተናገዱት ኤሌክትሪክ #በ3 ነጥብ በጊዚያዊ ደረጃ ሰንጠረዥ #1ኛ ደረጃን ሲይዙ በቀጣይ #በ3ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከ ልደታ ክ/ከተማ ጋር ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።


#TengertWomenSportET
@tengertsport
@EthiopiaWFL
📸Soccer Ethiopia
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

09 Nov, 08:42


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት 3ኛ ጨዋታ ተጀምሯል !

ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

በቀጥታ ለመከታተል https://www.youtube.com/live/HWMvJWPJNus?si=ZT-Z4N7cUlAObDXo

Tengert Sport

08 Nov, 18:00


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሞሮኮ !

የኢትዮጵያ ብሎም የምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ተወካይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሙሉ ሃይል ወደ #CAFWCL2024 ዝግጁ ሆኗል።

Tengert Sport

08 Nov, 06:23


የኢትዮጵያ  የሴቶችፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት የትኞቹ  ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛሉ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፣ ኦሎምፒያድ ስፖርት (አራዳ ስፖርት እና ትዕንግርት ስፖርት ) በመተባበር የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ፣ የከፍተኛ ሊግ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀጥታ የምስል ስርጭት ለማስተላለፍ ተስማምተው ስራ መጀመራቸው ይታወሳል ።

የመጀመርያ ሳምንት ሁለት ጨዋታ  በቀጥታ ያስተላለፉ ሲሆን በቀጣይም የሁለተኛ ሳምንት ሁለት የተመረጡ የጨዋታ መርሐ-ግብሮችን ለእግር ኳስ ተከታታዩ ያስተላልፋል።

በቀጥታ የምስል ስርጭት የሚተላለፍ ጨዋታዎች !

- ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ | ቅዳሜ ጥቅምት 30
4:00 ሰዓት


- አርባምንጭ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ | ሰኞ ህዳር 02
07:00 ሰዓት


በolympiad sport የዩቲዮብ ቻናላችን ሰብስክራይብ በማድረግ  በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ !

https://youtube.com/@olympiadsport?si=WARyJYP882nZvRXS

@tengertsport

Tengert Sport

07 Nov, 19:49


ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምድብ የመጀመሪያ ተጋጣሚ የሆነውን የናይጄሪያው ኤዶ ኩዊንስ ወቅታዊ መረጃ !

የካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ሞሮኮ 2024 ሊጀመር የሶስት ቀናት እድሜ የቀሩት ሲሆን በውድድሩ ላይ ምስራቅ አፍሪካን እና ኢትዮጵያን በመወከል የሚወዳደረው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያ የምድብ ተጋጣሚውን የናይጄሪያው ቡድን ኤዶ ኩዊንስ ወቅታዊ መረጃ አቅርበናል።

ትዕንግርት ስፖርት ስለ ሀገራችን ተወካይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚ  የናይጄሪያው ቡድን ኤዶ ኩዊንስ በማጣሪያው ስላሳለፉት እንቅስቃሴ እና ስለ ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች በጥቂቱ አቅርበንላችዋል ።
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚ የሆነው ኤዶ ኩዊንስ በያዝነው አመት መጀመሪያ የዋፉ ቢን ማጣሪያ በማሸነፍ በካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ መሆን ችለዋል።

የኤዶ ኩዊንስ አስደናቂ እንቅስቃሴ ካሳዩት ተጫዋቾች መካከል ኢመም ኢሴን በዞን ማጣሪያ ውድድር ላይ በአጠቃላይ 5 ጎሎችን በማስቆጠር ከፍተኛ ጎል አግቢ በመሆን አጠናቃለች።

ኤዶ ኩዊንስን በካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ በመሳተፍ ሶስተኛው የናይጄሪያ ቡድን ሲሆኑ፣ ከዚህ ቀደም በውድድሩ የተሳተፉ በ2021 ሪቨርስ አንጀልስ እንዲሁም በ2022 ሶስተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ባዬልሳ ኩዊንስ ናቸው።

የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች የሆነችው ኢመም ኢሴን ለኤዶ ኩዊንስ ያደረገችው የ5 ጎሎች አስተዋፅኦ ብቻ ሳይሆን በኳስ እንቅስቃሴዋ ቡድኗን በማገዝ አሸናፊ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና ተወጣለች። እንዲሁም ኢሜም ከፊታችን በሞሮኮው አስተናጋጅነት በሚደረገው የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ ከወዲሁ ተጠባቂ ተጫዋች ሆናለች።

አሰልጣኙ ሙሴ አዱኩ በናይጄሪያው ኤዶ ኩዊንስ ቡድን ላይ በማጣሪያው ባሳዩት ብቃት እና ዲሲፕሊን ክለቡ በአሰልጣኙ ላይ ትልቅ እምነትን አሳድሯል። የአሰልጣኙ ታክቲክ አቀራረብ እና ተጫዋቾችን የሚያበረታታበት መንገድ እያስመሰገነው ይገኛል።

የናይጄሪያው ቡድን ኤዶ ኩዊንስ ከሁለት ቀን በፊት ውድድሩ የሚደረግበት ሞሮኮ በመግባት ዝግጅቱን እየሰራ ይገኛል።

የሀገራችን ተወካይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትናንት አመሻሽ ላይ ወደ ሞሮኮ ማቅናቱን ይታወቃል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ የፊታችን እሁድ ጨዋታውን ያከናውናል።

#TengertWomenSportET
#CAFWomenCL24
@tengertsport
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

03 Nov, 16:19


https://youtu.be/S60z6FChA4I?si=XuAqYKRV6lIlMHKM

Tengert Sport

03 Nov, 11:49


የዩጋንዳው ክለብ ኢትዮጵያዊውን አሠልጣኝ መሾሙ ታውቋል!

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን የሴካፋ ሻምፒዮን ያደረጉት አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል በጥር ወር መጨረሻ ለአራት ዓመታት ካገለገሉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ኃላፊነታቸው ከተነሱ በኋላ ያለ ስራ የቆዩ ሲሆን በመጨረሻምየዩጋንዳውን የሴቶች ክለብ ለማሰልጠን ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሱከር ኢትዮጵያ አሳውቌል።

አሠልጣኝ ፍሬውን ለማስፈረም የተስማማው ካምፓላ ኩዊንስ የሴቶች ክለብ ሲሆን የፉፋን የሱፐር ሊግ ውድድር አንድ ጊዜ ማሸነፍ የቻለው ካምፓላ ኩዊንስ የዘንድሮውን የውድድር ዓመት በቻርለስ አይኮህ እየተመራ ቢጀምርም ከ5 ጨዋታዎች ማግኘት ከሚጠበቅበት 15 ነጥቦች ዘጠኙን ብቻ በማሳካቱ እና በኩዋምፔ ሙስሊም ሌዲስ በ4 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡን መሪነት በመበለጡ የክለቡ አመራሮች የአሰልጣኝ ለውጥ ለማድረግ ወስነዋል።

በዚህም ኢትዮጵያዊው አሠልጣኝ ፍሬው ኃ/ገብርኤል ቡድኑን እንዲመራ መወሰናቸው ታውቋል። አሠልጣኙም ፊርማውን ለማጠናቀቅ ይህንን ዘገባ ባጠናከርንበር ሰዓት ዩጋንዳ ካምፓላ እንደገባ ታውቋል።

#TengertWomenSportET
@tengert sport

Tengert Sport

03 Nov, 10:04


የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ2017 የውድድር ዘመን ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ጅማሮውን አድርጓል።

በቦሌ ክ/ከተማ እና አዳማ ከተማ መካከል የተደረገውን የመክፈቻ ጨዋታ የኢ/እ/ፌ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሪት ብዙዓየሁ ጀንበሩ፣ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸዋንግዛው ተባባልና ም/ሰብሳቢ ሊዲያ ታፈሰ እንዲሁም የሴቶች ልማት እና ውድድር ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ኢ/ር ጌታቸው የማነብርሃን በክብር እንግድነት በስፍራው በመገኘት አስጀምረዋል።

የመክፈቻ ጨዋታ ውጤት

ቦሌ ክ/ከተማ 3-0 አዳማ ከተማ

13' 51' ሜላት ጌታቸው
90' ዳሳሽ ሰውአገኝ

@EFF
@tengertsport
#TengertWomenSportET

Tengert Sport

02 Nov, 20:19


ትዕንግርት ስፖርትና አራዳ ስፖርት ጥምረት ፈጥረው የኢትዮጵያ የሴቶች ሊግን በቀጥታ ስርጭት ሊያስተላልፉ ነው  !

የ2016 የኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ሊግን ትዕንግርት ስፖርት ከ አራዳ ስፖርት ጋር በጣመርና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ውል በማሰር  በከፍተኛ የምስል ጥራት ጨዋታን እንደሚያስተላልፉ ገልፀዋል።

ሁለቱ ድርጅቶች  በአዲሱ ስያሜ
"ኦሎምፕያድ ስፖርት" በማለትና የሴቶች ሊግ ላይ ትኩረት በማድረግ  በዩቲዮብ በፌስቡክና በቲክታክ ገፃች ላይ በቀጥታ ማስተላለፉን ተግባር ከነገ ጀምሮ ይጀምራሉ።

በነገው እለትም የ2017 የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ  የመክፈቻ ጨዋታ  ቦሌ ክ/ከተማ ከ አዳማ ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ የቀጥታ ስርጭታቸውን ይጀምራሉ !

ቀጥታ የሚተላለፍበት የዮቲዮብ ቻናል ሊንክ https://www.youtube.com/@Olympiadsport

ሰብስክራይብ በማድረግ መከታተል ትችላላችሁ!

Tengert Sport

01 Nov, 11:26


🇪🇹 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ2024 የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታው ተዘጋጅቷል። 🔥

ምን ያህል ርቀት መሄድ ይችላሉ? አስተያየት ይስጡበት🌠

Tengert Sport

01 Nov, 11:11


ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምድብ የመጀመሪያውን ጨዋታ የሚያከናውንበት ቀን ታውቋል።

የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ሻምፒዮን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ የመጀመሪያውን ጨዋታውን በሞሮኮ እሁድ, ሕዳር 1 2017 ከኢዶ ኩዊንስ የናይጄሪያ የሴቶች እግር ኳስ ክለብ ጋር ጨዋታውን የሚያከናውን ይሆናል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የተመለከቱ የተለያዩ መረጃዎችን እና የመጀመሪያው ተጋጣሚው የሆነው ኢዶ ኩዊንስ አዳዲስ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።

#CAFWomenCL24
@tengertsport

Tengert Sport

29 Oct, 18:12


የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ፕሮግራም !

የ2017 የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት የአንደኛ ዙር ከ1ኛ ሳምንት እስከ 13ኛ ሳምንት የሚደረጉ ሙሉ የጨዋታ ፕሮግራሞች ከላይ 👆 በምስሉ አያይዘንላችኋል።


#EWPL
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

24 Oct, 17:42


ታላቅ የዘጋቢ ፊልም ምርቃት

ህልም፣ትጋት፣ጽናት፣ውጣ ውረድ እና በስኬት የታጀበው የአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የ25 አመት የአሰልጣኝነትና የግል ሕይወትን የሚተርክ ዘጋቢ ፊልም ይመረቃል።

በኮራ ወንዝ ዳርቻ በእረኝነት የጀመረው ህይወት በፈተና ታጅቦ ወደ ታላቅነት ተሸጋግሯል።
ይህ ዘጋቢ ፊልም ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ በወርቃማ ብዕር ስሙን የጻፈው አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሰራቸውን ገድሎች አካቶ የፊታችን ጥቅምት 21-2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 በኢትዮጵያ ሆቴል በይፋ ይመረቃል።

ከ1992-2017 ዓ.ም በዘለቀው የአሰልጣኝነት ህይወቱ በ25 አመት 26 ዋንጫዎችን በማሸነፍ ቀደምቶቹ ተርታ ይሰለፋል።

በሕይወት ሁሉ ውስጥ ሊገጥሙ የሚችሉ ፈተናዎችን ፊት ለፊት የተጋፈጠው አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በአንድ ክለብ በርካታ ዓመታትን በአሰልጣኝነት በማሳለፍም ቀዳሚው አሰልጣኝ ነው።

ሀያ አምስት (25) ዓመታት በውጤታማነት ያሳለፈበትን ዘጋቢ ፊልም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሮዲዩስ በማድረግ በዘመን ተሻጋሪው ዶክመንተሪ ላይ ደማቅ አሻራውን አሳርፏል።

ጥቅምት 21 በኢትዮጵያ ሆቴል አይቀርም!

Tengert Sport

24 Oct, 11:26


የ2017 የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የውድድር ዓመት የአንደኛ ሳምንት ፕሮግራም ይፋ ሆኗል !

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የ2017 የውድድር ዓመት ዕጣ ማውጣት ፕሮግራም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በካሌብ ሆቴል እያካሄደ ይገኛል።

የፕሪሚየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የ2017 የውድድር ዓመት የአንደኛ ሳምንት የጨዋታ ፕሮግራሞች በአሁኑ ሰዓት ይፋ እየሆነ ይገኛል።

የአንደኛ ሳምንት ፕሮግራም ከላይ 👆 በምስሉ አያይዘንላችኋል።

#EWPL
#TengertWomenSportET
@tengertsport
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

24 Oct, 11:12


የ2017 የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እና የሴቶች ከፍተኛ ሊግ የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ዙር የሚካሄድበት ከተማ ታውቋል።

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ዙር ውድድር በመዲናዋ አዲስ አበባ ከተማ ጅማሮውን እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በእጣ ማውጣት ፕሮግራም ላይ አሳውቋል።

እንዲሁም የ2017 የኢትዮጵያ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር በውቢቱ ሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ተረጋግጧል።

እንዲሁም ለአሰልጣኞች እና ለቡድኖች ተወካዮች በዘንድሮው የውድድር ዓመትን አስመልክቶ ሦስት አይነት የውድድር ፕሮግራም ምርጫ አቅርበዋል።

የቀረቡት ምርጫዎቹም በሜዳ ፣ ዞናል እና ቶርናመንት ሲሆን በዚህ ጉዳይ ከተወያዩ በኋላ ሙሉ ውድድሩ በቶርናመንት እንዲደረጉ ተወስኗል።


#EWPL
#TengertWomenSportET
@tengertsport
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

21 Oct, 11:41


አሰልጣኝ ብርሃኑ እስካሁን ስላደረጉት ጉዞ፣ የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ምኞታቸውን እና ስለ ኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ያላቸውን እይታ እንቃኛለን።

የሴካፋን ማጣሪያ የማሸነፍ ጉዞ እንዴት ይገልጹታል?

🗣ከባድ ነበር። "አምስቱንም ጨዋታዎች አሸንፈን ዋንጫውን ለዞኑ አነሳን"። በቀደሙት ውድድሮች "የፍጻሜ ውድድር ላይ በመድረሳችን ልምዳችን ረድቶናል"።

በካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ምን ለማሳካት ተስፋ አለህ?

🗣 "የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ እየተሻሻለ ያለበትን ደረጃ ማሳየት እንፈልጋለን"። የምስራቅ አፍሪካ እግር ኳስ "በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ነው" ብለን እናምናለን። በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ "በመጀመሪያ ተሳትፏችን አስገራሚ ቡድን እንደምንሆን ተስፋ እናደርጋለን"።

ውድድሩ ምን ያህል ፈታኝ እንደሚሆን ትጠብቃለህ?

🗣 ከአፍሪካ "ምርጥ ስምንት የሴቶች ቡድን" ጋር የምንወዳደረው በመሆኑ አስቸጋሪ እንደሚሆን ግልጽ ነው። ውድድሩ ከአመት አመት ይሻሻላል, እና "ዝግጁ መሆን አለብን"።

የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ አሁን ያለበትን ደረጃ እንዴት ያዩታል?

🗣 እኔ እንደማስበው "የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ትልቅ አብዮት እየተካሄደ ነው"፣ ይህንንም ማሳየት እንፈልጋለን። "ተጫዋቾቻችን በፕሮፌሽናልነት" ወደ ሌሎች ሀገራት እየሄዱ ሲሆን በዚህ ውድድር ላይ "የአውሮፓ ቡድኖችን ትኩረት ለመሳብ እድሉ አላቸው"።

በቡድንዎ ውስጥ ደጋፊዎች ሊመለከቷቸው የሚገቡ ድንቅ ተጫዋቾች አሉ?

🗣 በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ላይ "ኮከብ ተጨዋቾችን" ብንመለከትም በተለይ "ይህ ውድድር የመጀመሪያ በመሆኑ ሁሉም ተጫዋቾቻችን በደስታ እንደሚመለከቱ ተስፋ አደርጋለሁ"።

በዚህ ውድድር ላይ መሳተፍዎ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ምን ተጽእኖ ይኖረዋል?

🗣 "የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሶስት የአፍሪካ ዋንጫዎች የተሳተፈ ቢሆንም ባለፉት 12 አመታት" ማለፍ አልቻለም። ወደ ካፍ የሴቶች ሻምፒዮን ሺፕ ሊግ የምንወስደው መንገዳችን "ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ማበረታቻ ሆኖ ሀገራችንን፣ ክለባችንን፣ አሰልጣኞችን፣ ሰራተኞችን እና ተጫዋቾችን ተጠቃሚ በማድረግ ደረጃችንን ከፍ ያደርጋል"።

የቡድንህን አጨዋወት እንዴት ለመለየት አስበሃል?

🗣 የአፍሪካ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጠንካሮች ናቸው፣ እና ብዙ ቡድኖች ግብ ለማስቆጠር "የተቀመጡ ኳሶችን እና ረጃጅም ኳሶችን" ይጠቀማሉ። ነገር ግን፣ የኛ ቡድን "ከቲኪ-ታካ ጋር የሚመሳሰል ኳስ ላይ የተመሰረተ የጨዋታ ዘይቤ እንጫወታለን"፣ ይህም "ለተመልካቾች መዝናኛ ይሰጣል ብለን እናምናለን"። በዚህ አካሄድ "ጥሩ ቡድን እየገነባን መሆኑን ማረጋገጥ እንፈልጋለን"።

CAF የሴቶችን እግር ኳስ ለመደገፍ ምን አይነት ለውጦችን መተግበር አለበት ብለው ያምናሉ?

🗣 "CAF ህጎቹ በፌዴሬሽኖች መከበራቸውን ማረጋገጥ" አለበት። ለምሳሌ "ሁሉም የወንዶች ቡድን የሴቶች ቡድን ከሌለው በሀገሪቱ ከፍተኛ ሊግ እንዲሳተፉ ሊፈቀድላቸው አይገባም"። ይሁን እንጂ በምስራቅ አፍሪካ አንዳንዶች ይህን ህግ በትክክል ተግባራዊ እያደረጉ ያሉ አይመስለኝም። "CAF በአሁኑ ጊዜ በሴቶች እግር ኳስ ላይ የሚያተኩር ከሆነ እንደ ወንዶች እግር ኳስ ፣ ለአፍሪካ ሴቶች እግር ኳስ የወደፊት ተስፋን ማየት እችላለሁ" በማለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ቃለ ምልልሱን አጠቃሏል።


#CAFOnline.com
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

21 Oct, 11:19


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ብርሃኑ ግዛው በካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ በሴካፋ የማጣሪያ ጨዋታ ቡድናቸው ታሪካዊ የሆነውን ድል ማስመዝገቡን ተከትሎ ከCAFOnline.com ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ በቀጣይ እናቀርብላችኋለን...

👉 ዘንድሮ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኬንያ ፖሊስን 1-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል። ድሉን ተከትሎ ለተጫዋቾች እና ለቡድኑ የካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ጠንካራ ስሜት የሚፈጥር ሲሆን ለክለቡ ትልቅ ምዕራፍ ነው።

👉 የአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ቁርጠኝነት እና አመራር ወደዚህ ታላቅ ውድድር እንዲገባ በማድረግ የሴካፋ ዞንን ወክሎ እንዲሳተፍ አድርጓል።

#CAFOnline.com
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

18 Oct, 11:30


ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚውን አውቋል !

ኢትዮጵያን በመወከል በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴካፋ ሻምፒዮን በመሆን የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከደቂቃዎች በፊት የምድብ ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጣይ በምድብ ሁለት ከMamelodi Sundowns ፣ Touthakhamon ፣ Edo Queen's ጋር የምድብ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

#TengertWomenSportET
@tengertsport
@ግርማ ሠጠኝ

Tengert Sport

16 Oct, 13:45


የካፍ ሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር በሞሮኮ ይካሄዳል !

የአፍሪካ እግር ኳስ የበላይ አካል የሆነው ካፍ ሞሮኮ የ2024 የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ  ውድድር እንደምታዘጋጅ ይፋ ማድረጉን ሱከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።

ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 14  በሞሮኮ አዘጋጅነት እንዲካሄድ መርሃግብር በወጣለት ውድድር የሴካፋ ሻምፒዮኑን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ የወቅቱ የውድድሩ ሻምፒዮን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ፣ ቲፒ ማዜምቤ፣ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ዌስተርን ኬፕ፣ ኤግልስ ዴ ላ መዲና፣ ኤዶ ኲዊንስ፣ ቱታንካሙን እና ‘AS FAR’ የሚሳተፉበት ሲሆን የውድድሩ አሸናፊ ቡድን 400,000 ዶላር እንደሚያገኝ ይፋ ሆኗል።

በውድድሩም ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ በሁለት አጋጣሚዎች ውድድሩን ያሸነፉት ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እና የአዘጋጅዋ አገር ክለብ የሆኑትና ከዚ ቀደም ውድድሩን ያሸነፉት ‘ASFAR’ ውድድሩን ለማሸነፍ ቅድመ ግምት ያገኙ ክለቦች ሆነዋል።

Tengert Sport

15 Oct, 14:27


ናኦሚ ግርማ የቢቢሲ የ2024 የዓመቱ ምርጥ ሴት እግር ኳስ ተጫዋች ዕጩ ኾናለች፡፡

ከኢትዮጵያዉያን አባት እና እናት በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት የተወለደችው ናኦሚ ግርማ የቢቢሲ የ2024 የዓመቱ ምርጥ የሴት እግር ኳስ ዕጩ ተጫዋች ሆና ቀርባለች፡፡

ቢቢሲ የመጨረሻዎቹ አምስት የዓመቱ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ያላቸው ባርባራ ባንዳ፣ አይታና ቦንማቲ፣ ናኦሚ ግርማ፣ ካሮላይን ግርሃም ሃንሰን እና ሶፊያ ስሚዝ ናቸው፡፡

ከኢትዮጵያውያኑ ቤተሰቦቿ በአሜሪካ የተወለደችው የ24 ዓመቷ ናኦሚ ግርማ የአሜሪካው ሳን ዲያጎ ዌቭ ክለብ ተጫዋች ናት፡፡

ባለፈው ጥር ወር የአሜሪካ የሴት እግር ኳስ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብላ የተመረጠችው ናኦሚ ግርማ በተከላካይ ስፍራ ሆና እጩ ውስጥ የገባች የመጀመሪያዋ ተጫዋችም ሆናለች፡፡

ከአሜሪካ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያን ያሸነፈችው ናኦሚ ከክለቧ ሳን ዲያጎ ዌቭ ጋርም የተለያዩ ስኬቶችን ከዚህ ቀደም አስመዝግባለች፡፡

የዩናይትድ ስቴት የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ኤማ ሄይስ “እንደ እሷ ዓይነት ምርጥ የመሐል ተከላካይ በሕይወቴ ዓይቼ አላውቅም” ስትል ናኦሚን አወድሳታለች፡፡

የቢቢሲ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋቾች የሚመረጡት በአሠልጣኞች፣ በተጫዋቾች፣ በእግር ኳስ አሥተዳዳሪዎች እና በጋዜጠኞች መኾኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

#TengertWomenSportET
ምንጭ BBC sport
@tengertsport

Tengert Sport

14 Oct, 06:46


ዲሲ ፖወር የውድድሩን የመጀመርያ ድል አሳክቷል።

ኢትዮጵያዊቷ የግብ አዳኝ ሎዛ አበራ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ በተካተተችበት ጨዋታ ዲሲ ፖወር ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ብሩክሊን እግር ኳስ ክለብን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ሎዛ አበራ በጨዋታው ላይ 77 ደቂቃ የቆየች ሲሆን ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ከማቀበል በተጨማሪ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ከተቃራኒ ቡድን ሳጥን ውጪ ከርቀት በተደጋጋሚ ጊዜ መሞከር ችላለች።

ዲሲ ፖወር በስድስት ነጥብ በደረጃ ሠንጠረዥ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

#ኢትዮጵያን_ተጫዋቾች
#TengertWomenSportET
@tengertsport

Tengert Sport

13 Oct, 18:57


አረጋሽ ካልሳ በያንግ አፍሪካ ልምምድ ጀምራለች።

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመስመር አጥቂ አረጋሽ ካልሳ የታንዛኒያውን ክለብ ያንግ ፕሪንስስ በመቀላቀል ከቡድኑ ጋር ልምምድ ማድረግ ከጀመረች ሰንበትበት ብላለች።

አረጋሽ ካልሳ ከታንዛኒያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈውን ያንጋ ፕሪንስስ ጋር የመጀመሪያዋን ጨዋታ በቀጣይ ቡድኑ የውድድሩን ሦስተኛ ጨዋታ ላይ ትሰለፋለች ተብሎ ይጠበቃል።

@ኢትዮጵያን_ተጫዎቾች
#TengertWomenSportET
@tengertsport