#ማሳሰቢያ #ለሁሉም #የመካከለኛ #ደረጃ #ተማሪዎች እና #የተማሪ #ወላጆች/አሳዳጊዎች
ት/ርት ቤቱ የተማሪዎችን የተማሪዎችን ውጤታማነት ለማሳደግ አቅዶ በትኩረት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ከእቅዱ ማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ በተለይ የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከመደበኛ የትምህርት መርሀ ግብር ባልተናነሰ መልኩ የሚከናወን የማጠናከሪያ ክፍለ ግዜ በማዘጋጀት ተማሪዎቹ በመደበኛ የትምህርት ክፍለ ግዜ የተማሩትን የበለጠ ማብላላት ይችሉ ዘንድ ተጨማሪ ሰዓቶችን በማጠናከሪያ ትምህርት ላይ እንዲያሳልፉ ማድረግ ዋነኛው ተግባር ነው። በዚሁ መሰረት ይህ የማጠናከሪያ ትምህርት ክፍለ ግዜ የተዘጋጀ ሲሆን ተማሪዎቹ በእረፍት ግዜያቸው,ማለትም በየሳምንቱ አርብ ከሰአት ከ8-10 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት ከ2:30-6:15 የማጠናከሪያ ትምህርት በመምህራን የሚሰጣቸው ይሆናል። በመሆኑም ከህዳር 13,2017 ጀምሮ ሁሉም ከ7-8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች መገኘትና ትምህርታቸውን መከታተል የሚጠበቅባቸው ይሆናል።በእቅዱ መሰረት መምህራ ከመደበኛው የትምህርት አሰጣጥ በተለየ መልኩ ተማሪዎችን ለማብቃት የተለያዩ ዘዴዎችን እንዲከተሉ የሚጠበቅ ሲሆን የተለያዩ ጥያቄዎችን በማሰራት እና መልመጃዎችን እንዲሁም ሞዴል ጥያቄዎችን ያሰራሉ።
ይህን ማድረግ ለአማራጭ የሚቀርብ ጉዳይ ባለመሆኑ ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር የምናደርግ መሆኑን ሁሉም አካላት እንዲገነዘቡና በሂደቱ ላይ እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።ለዚህም ስኬት ይረዳ ዘንድ መደበኛ የስም መጥሪያ የሚዘጋጅ ሲሆን የተማሪዎችን መገኘት በስም መጥሪያ ታግዘው የሚከታተሉ 2 መምህራን ተመድበዋል።እነሱም
1.መምህር ገሰሰ:-የ8ኛ ክፍል ተቆጣጣሪ
2.መምህር አብረሀም የ7ኛ ክፍል ተቆጣጣሪ ሆነው ተመድበዋል።