ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት) @ethioasmat111 Channel on Telegram

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

@ethioasmat111


የተለያዩ መናፍስታዊ ጥበቦች፣ ትምህርቶች ፣ የአባቶች ሚስጥር እና ምክር።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት) (Amharic)

በዚህ ወቅታዊ ግምትና፣ ኢትዮ አስማት እና ሐተታ መናፍስት አቅም አግኝቶትን ለማሳየት፣ ሃምሌ የተለያዩ መናፍስትዊያንን እና ሁለቱን አስተውሎ ትምህርታላጭ። ይህ ታሪኩን መጽሐፍት፣ መማርክትና ምልክታት ማለት አስገራሚ ነው። ከትንሳኤዊያኑ አፍ ወደ በለቴንድ፣ ማህበረሰብ የተመሠረተ፣ የትንሳኤ ት/ቤት፣ ስልኩ ሞባ አባቶች ሚስጥርን ወደ መማርክተኞችዎ ላይ፣ መከላከያን እና ምክርዋን በመምራት የተለያዩ መናፍስቲያንን በጥበብ እየጀመረ እና ሕዝቦችን ለመገኘት ብለናል። አዲሱ ገበያዎችን ለመገንባት እና የስራችንን መልክቶች የቀደምበው ሚስጥረን ይመልከቱ።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

06 Jan, 17:42


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን ልጆቼ ወገኖቼ ሁሉ። ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ ለዓለም መዳን እንደተወለደ አሁንም ውልደቱ በልደቱ  ለመላው ወገኖቼ ልጆቼ ሰላምን ፍቅርን መዋደድን መከባበርን ያመጣልን ዘንድ እነሆ አባት ሆይ ስማን እንማፀንሃለን። አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ላጠፋንውም ሁሉ ይቅር በለንና በምህረትህ በቸርነትህ እኛን ልጆችህን አስበን አሜን አሜን አሜን።
የሰማይ የምድሩ ጌታ ፈጣሪ አንጠርጣሪው አምላክ
ሁሉንም ወገኖቼን ይህን በዓል የሰላም የፍቅር የሙላት ያደርግ ዘንዳ መልካም መኞቴ ነው ልጆቼ።

መምህር፡ዓይና

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

10 Sep, 17:12


      ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
    *******
ውድ፡ኢትዮጵያውያን ፡ ወገኖቼ ልጆቼ  ሙሃባዎቼ በሀገርም ይሁን ባህር ተሻግራችሁ ላላችሁ በሙሉ በእውነቱ የሰማይ የምድሩ ጌታ የፍጥረታቱ ሁሉ ባለቤት ከአስከፊ ጊዜ ከአስከፊ ሁኔታ ሁሉ ጠብቆ ለዝህች ቀን ለዚህም ዘመን ላደረሰን በከበረ መንበሩ እነሆ ምስጋና ይድረሰው። የዘመናት፣የዓመታት፣የወራት፣የቀናት እና የቅፅበታት ሁሉ ባለቤት ከቅፅበታው ህልፈት ከጊዜም መዓት ጠብቆ አሻግሮናልና እነሆ ምስጋና ይሁን ይሁን ይሁን። ፀሀይም ሳትጠፋብን ጨረቃም ሳትቀርብን ከዋክብትም ሁሉ ጊዜ ቀመር ኡደትን ሳይስቱብን ላቆየን  ደግ አምላክ ተመስገን።

  ልጆቼ ያዘናችሁ፣የተራባችሁ፣የታመማችሁ፣ሀዘን የደረሰባችሁ ጭንቀት የገባችሁ ሁሉ በእውነት በእውነት አፅናኙ የልዑል ፈጣሪ መንፈስ ያፅናችሁ ያበርታችሁ በቃ ብሎ ወደ ፍስሐ ፣ሙላት፣ጥጋብ እና መሻር ያሸጋግራችሁ ወገኖቼ። ሀገራችንን ወገኖቻችንን ፈጣሪ በምህረቱ ይጎብኝ ሰላም ፣ጤና ፣በረከት ይሁንልን ይሁንልን። አውቀንም ሳናውቅም አጥፍተን ስላሳዘነው ፈጣሪ በምህረቱ በቃችሁ ብሎ ጤና ፣በረከት ፣ሰላም ሙላት ያድርግልን።  የመሻሪያ የመደሰቻ የሙላት ዘመንን እነሆ እንደ ሀገርም እንደ ግለሰብም አንድ ብለን ጀምረን የምንኖርበት ዘመን ይሁን ይሁን።  በሐይማኖት፣በብሔር በማንነት ሳንከፋፈል በፈጣሪ አንድነት ምሳሌ አንድ ሆነን በደስታ በሰላም የምንኖር ጀግና ያድርገን ደጉ ጌታ። በሰማይ እንደሆነ ሁሉ በምድርም ይሁን።


መምህር፡ዓይና።
።።።ከጌቶቹ ከደጋጎቹ ሀገር።።።
።።።ኢትዮ-አስማት።።።።።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

02 Jun, 19:51


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
-----የጨረቃ ዑደት የ28ት ቀናቱ----
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰላም ለሁላችሁ ልጆች ወገኖቼ ሰላም ለሩቅ ለቅርቡ
ለባህር ተሻጋሪዎቹ። ሁሉን ዘይን ሁሌ ዘበይን ይኩነ አምላክ ሰላም፣ጤና፣ልቦና፣ ፍቅሩን ይደለን የፍጥረታቱ ባለቤት። ሀገር ወገን ሁሉ ባለበት ማስተዋሉን ያድለን ፈጣሪ ተሁሉ አቅጣጫ ተመልክተን የፊት የሗላውን መዝነን የምንጓዝ ያድርገን ፈጣሪ አምላከ ዝንቱ ዓለም።

ሰነፍ ሴት የዛሬ እሳቷን ለነገ አዳፍና ካላደረችና ነግ ረጥቦም ቢያድር እሳት እንደገና ብታያይዝ ድካሟን የወደደች ሰነፍ ናትና በባለተቤቷ "አዳፍኔን" የማታውቅ ከንቱ ሴት ተብላ ትናቃለች ሰለዚህ የመራቀቅን ሳይሆን የመንቃትን ነገር ይገባት ዘንዳ ባልንጀሮቿ ይምከሯት ።
-------------------------------------------------------
እድሜ ሁሉ ፣አለማዊ ነገር እና መንፈሳዊ ነገር ሁሉ በ28ቱ የጨረቃ ዑደት ይወከላል። ከ28ቱ የሚያልፍ የለም የዓለምም የተፈጠረ ነገር ሁሉ እድሜው ልክ እንደ 28ቱ የጨረቃ ዑደት ነውና አጥብቆ ይሰብ ያስተውል።
28ቱ የጨረቃ ቀናት እያንዳንዳቸው የየራሳቸው መልካም እና ክፉ መልክ አላቸው። ሁሉ ለበጎ ቢፈጠር ኖሮ ፈጣሪ እና ፍጥረታት ባልተዋወቁ ነበር ለዚያ ነው ፈጣሪም በቃሉ "እኔ የምፈጥርም የማጠፋም ነኝ ያለው".
ህጉን ጠብቆ ለሄደ ምስጢሩ ዓይኑ ስር ነው አሊያ ግና የሩቅ ዓለም ሰው ሁኖ ማለፍ ነውና አስተውሉ ልጆቼ።
-------------------------------------------------------
ማንኛውም ፀሎት ወድጋም በጎ ለሆነ ከሆነ የሚከወነው ጨረቃ ሙሉ ልትሆን ሰባት ቀን ሲቀራት ጀምሮ እስከ ሙሉ ጨረቃ ቀን ነው። አስተውሉ ይህን ምክር።
--------------------------------------------------------
መልካም ነገሮችን በጎዶሎ ጨረቃ ቀናት(ሽናት) ከተገበርን ልክ መልካም ምግብን ባረረ ምጣድ ጥዶ እንደማቃጠል ነውና የበሰለ ሳይሆን ያረረ ምግብ ነው ውጤቱ አለሞቼ። የዚህ ሁሉ ምክር የጨረቃ ዑደት ለመንፈሳዊም ለዓለማዊም ጉዳዮች ሁሉ መሰረት መሆኑን አትዘንጉ። ሴት ልጆቻችን የወር አበባን በወሩ የሚያዩት ቀጠሮ ይዘው ሳይሆን በተፈጥሮ የጨረቃ ዑደት ህግ መሆኑን ላስተዋለ ተዚህ በላይ የጥበብ መገለጥ የለምና አስተውሉ አስተውሉ ።

ቸር ያቆየን ደጉ አምላክ።
።።።፣መምህር ፡ዓይና።።።።።።።
።።።።ከጌቶች ሐገር።።።።።።።።
፨፨፨፨፨ኢትዮ -አስማት፨፨፨፨፨፨

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

04 May, 16:26


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
   ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
    ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ልጆቼ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆናችሁ  በመላ ዓለም ያላችሁ እንኳን እንኳን በሰላም ፣በጤና ለትንሳኤው አደረሰነ የትንሳኤው ባለቤት። ለታመመው ምህረትን፣ለታረዘው ሙላትን፣ውሉ ለጠፋው መንገዱን፣ለተጨነቀ መፍትሔውን የፍጥረታቱ ባለቤት አሐዱ አምላክ ይስጠን ይለመነን።

ለሀገራችን ለወገኖቻችን በሙሉ የሰላም፣የመግባባት፣የመዋደድ፣የአብሮነት ትንሳኤ ይሆንልን ዘንድ ኦ! አባት ሆይ እንደ ጥፋታችን ሳይሆን እንደ ቸርነትህ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ምድሪቱንም ጎብኝ አሜን አሜን አሜን።
"ሁሉም ኃላፊ ነው በፍቅር በአንድነት እንኑር ልጆቼ "

መምህር፡ዓይና።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

10 Feb, 17:23


፨፨፨፨መክስተ ፡ስራይ፡፨፨፨፨፨፨
ውድ የሀገሬ ልጆች ሊቃውንት ጠቢባን እነሆ ትንሹ ነገር ትልቁን ጋን ይከፍታልና ማስተዋል የጥበብ ቁልፉ ነው።

ብዙ ሰዎች መፍትሔ ስራይ እንዲህ ታዋቂ የሆነው በእውነቱ መፍትሄ ብቻ ስለሆነ ነው ይላሉ። እነሆ መልሱን ለእናንተው ውድ ወገኖቼ። መፍትሄ ስራይ ውስጥ ትልቁ ምስጢር "መክስተ ስራይ"  ነው።  መክስተ ስራይ የሚገኘው መፍትሔ ስራይ ፀሎት ውስጥ ነው በውል ላስተዋለው። መክስተ ስራይ ግለሰቡ የተሰራበትን ስራይ እና የሰራውን ያሰራውን ሰው ማንነት የሚገልጥ ሲሆን ነገር ግና መፍትሄ ስራዩ የተሰራውን ስራይ መሻሪያ ነው ማለት ነው ። መክስተ ስራይ ግለሰቡ በቤቱ ፣በመኖሪያው፣በሚሰራበት ስፍራ ሁሉ የተቀበረ ካለ ይገሌፃል ውድ ወገኖቼ ቀሊል ኢይመስልክ። የሰራው ያሰራው ጠላት ሳይታወቅ መፍትሔ መከወኑ ፍፁም ድካም እና ሐሰት ነው። ለዚህ ነው በመፍትሔ ስራይ ውስጥ መጀመሪያ ጠቢቡ  መክስተ ስራዩን የሚዋሃደው ልጆቼ።  እነሆ ምስጢር ላስተዋለው። ወንዝ ያሻግራል ይላሉ ከሪሞቹ።

ዛሬ ግዜ መፍትሔ ስራይ የትም ይገኛል ይላሉ ያላስተዋሉ ነገር ግና ዋናው ጥያቄ መክስቱ ምንድነው ይላል አዋቂው።

እውቀት አንድ እግር ነው ማስተዋል ግና ሙሉ አካል ማለት ነው። ጠቢባን ማስተዋል የተሰጣቸው እንጂ እውቀትን የሰበሰቡ አይደሉም አደራ።

።።።።።ኢትዮ አስማት።።።።
፨፨፨፨ከጌቶቹ ከሩኀኒያዎቹ ሐገር፨፨፨፨

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

22 Jan, 14:49


፨፨፨፨፨፨ምክር ለወዳጅ ለልጅ፨፨፨፨፨፨
ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ ወገኖቼ በሙሉ ሰላም ለሀገራችን ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው።ዛሬ ይጥቀማችሁ አይጥቀማችሁ እንጃ እኒህን ሁለት ታላላቅ ምክሮች እለግሳለሁ አስተውሎ ለሚጠቀመው ሁሉ መልካም ምግብ ነው ልጆቼ።
------------------------------------------------
፨፨ምክር አንድ ፨፨
*(1)አል_ጣባሩህ ወአሊል አርዋህ*
ይኽ ህግ ማለት ማንኛውንም አስማት እና ፀሎት  ከየትኛውም ክታብ አሊያም ተጥበበኛ ስታገኙ መጀመሪያ ያንን ፀሎት ወአስማት ከመከወናችሁ ፊት እንደቀኑ ለየኔቢጤዎች እንደዝክር ሳንቲም (ገንዘብ) መስጠት ማለት ነው ልጆቼ። የዚህ ጥቅሙም ያ ፀሎት አስማት ይሰራ ዘንድ በዚያ ፀሎት እና አስማት ላይ ለተሾመው ወኪል ይከውንላችሁ ዘንዳ ለእኔቢጤ የምትሰጡት ገንዘብ ዝክር ሆነ ማለት ነው ስለዚህ ያ አስማት እና ድጋም ይሰምራል ማለት ነው። ተዚያ ተጨማሪ ይህ ዝክር አስማቱ ወይም ፀሎቱ እንዳይሰምር የሚያደርገውን አይነ ጥላ በጊዜያዊነት ያነሳል ማለት ነው። ታላቅ ምክር ነው በብዙ ቦታ ቢሸነቆር የሚያነድ የሚያብላላ ነው ወገኖቼ አስተውሉ እና ተጠቀሙ ጥቀሙ በመልካም ።
       **ለእያንዳንዱ ቀን እንደ ቀኑ ለእኔቢጤው የሚሰጠው የዝክር ገንዘብ መጠን ይለያያል እነሆ ዝርዝሩ :
     1)እሁድ-1 ብር ወይም 11 ብር ወይም 111ብር
    2)ሰኞ- 2 ብር / 22ብር  /222 ብር
  
   3)ማክሰኞ- 3ብር / 33ብር  /333 ብር

   4)እሮብ- 4ብር  /44ብር  / 444 ብር

  5)ሐሙስ-5ብር  / 55ብር / 555ብር

6)አርብ- 6ብር / 66ብር / 666ብር

7)ቅዳሜ- 7ብር /77ብር / 777ብር
ተእነዚህ ፀሎት እና አስማቱን የምትከውኑበትን ቀን መርጣችሁ ተዚያ ከሶስቱ የገንዘብ መጠን አንዱን በመምረጥ ያንን መጠን ለእኔቢጤው በዝምታ መስጠት ነው ልጆቼ።
----------------------------------------------------
፨፨ምክር ሁለት፨፨
።የተዋለባቸው ወርቅ እና ብር ።።
ከተለያዩ የወርቅ እና ብር ቀለበት ሀብል መሸጫ መደብሮች እኒህን ወርቅ እና ብሮች ስትገዙ ብዙዎቻችሁ የማታስተውሉት እና ብዙዎችን ለብዙ ዓመታት እጅጉን የጎዳ እና የብዙዎችን ህይወት ያበላሸ ምስጢር አለ ወገኖቼ ይህም ብዙ ወርቅ እና ብር ሻጮች ለእናንተ ከመሸጣቸው በፊት ቀን ተመርጦ ሁሉም ወርቅ አሊያም ብር ተሰብስቦ ይዋልበታል። ይዋልበታል ማለት እድል እና ንዋይ የሚሰልብ ከፍተኛ ሀይል ያለው ድጋም ይደገምባቸዋል። ሲደገምም ይህንን ቀለበት አሊያም ብር ያደረገ ሁሉ እድሉን ለእኔ እገሌ (የወርቅ ብር ቤቱ ባለቤት ስም) አምጣልኝ ንዋዩን ስረቅልኝ ስሃብ ስሃብ እየተባለ ይዋልበታል ተዚያም በየወርቅ ብር መደርደሪያው ተደርድሮ ለሽያጭ ይቀርባል ።የተለያዩ ሰዎች ለጋብቻ አሊያም ለቃልኪዳን እያሉ ወርቁን ወይም ብሮቹን ይገዛሉ ያደርጋሉ በዚህ ጊዜ የእዚያን ግለሰብ እድል እና ንዋይ ባደረገው ቀለበት አማካኝነት ለወርቅ ወይም ብር ሻጩ ይዘዋወራል። ልጆቼ በዚህ የብዙ ሰው ህይወት ተበላሽቷል እድሉም ተሰውሯል።ብዙዎች ያለእድላቸው በመከራ ይኖራሉና ይህን ምክር እነሆ እላችኋለሁ ።

መፍትሄው- ሁልጊዜ ወርቅ እና ብር ስትገዙም ይሁን ስጦታ ስትቀበሉ በጨው ውሃ እና ድኚ ውህድ እጠቡት ያፈርሳልና ድጋሙን። እንደእምነታችሁም ፀልዩበት መጀመሪያ።
*ወርቅ እና ብር በተፈጥሮ ባህሪው አስማት ድጋምን ለጥሩም ለመጥፎም ተሎ ይይዛል ለዚያ ነው በዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚጠቀሙበት ።

***አደራ አደራ ልጆቼ ወገኖቼ ሁሉም የወርቅ እና ብር ነጋዴ ይህንን ያደርጋል ማለቴ እንዳልሆነ ልብ ትሉልኝ ዘንድ እማፀናለሁ።  ነገር ግና ክፉን የሚያደርጉ አሉና አውቆ መጠንቀቁ አይከፋም ብዬ ነው ።

መምህር:ዓይና

፨፨፨፨፨ከጌቶች ሀገር፨፨፨
።።።።ኢትዮ አስማት።።።።።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

19 Jan, 15:05


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለከተራ እና ለበዓለ ጥምቀቱ አደረሳችሁ አደረሰን። አቤቱ! ሀገራችንን እና ህዝቦቿን በምህረት ጥምቀት ሰላም ታድልልን ዘንዳ እንማፀንሃለን።
።++++++++++++++++++++++።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

06 Jan, 17:00


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
++++++++++++++++++++++++++
እንኳን፡በሰላም ፡በጤና፡ ለበዓለ፡ልደቱ ፡አደረሳችሁ፡ውድ፡ የክርስትና፡እምነት፡ ተከታይ፡ወገኖቻችን ፡በሙሉ።
በዓሉ ፡ለወገኖቻችን፡በመላ፡የሰላም፣የፍቅር፣የመቻቻል፡እና፡ የአንድነት ፡ይሆን፡ዘንዳ ፡ምኞቴ፡ነው፡ወገኖቼ። ፈጣሪ ፡በምህረቱ፡ እና በሩህሩህነቱ፡ ሀገራችንን፡ እና፡ህዝቦቿን፡ያስብልን፡ እነሆ፡ፀሐይ፡ጨረቃን፡እና፡ክዋክብትን፡ ፍጥረታትንም፡ሁሉ፡የሚያዝ፡እና፡የሚገዛ፡አምላክ፡ በሀገራችንም፡ሰላም፣ፍቅርን ፡እና፡አንድነትን ፡ይዘዝልን።

በስምንቱም፡አቅጣጫ፡የሰላም፡ንፋሱን፡የምህረት፡አዋጁን፡ያውጅልን።

"ሁላችንም፡ሞት፡እንዳለ፡አንዘንጋ፡ዳግም፡ውልደትም፡በበጎ፡ስራ፡ብቻ፡የፈጣሪን፡መንግስት፡መውረስ፡ነውና፡እናስተውል።"

፨፨፨፨፨ኢትዮ አስማት፨፨፨፨
፨፨፨፨ከጌቶቹ ሐገር፨፨፨፨፨

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

05 Dec, 16:58


 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
።።።የህቡዕ፡ስሞች(አስማት)፡ምስጢር።።።
---------------------------------------------------
የአስማኡል፡ሁስና፡ የአስማተ፡መለኮት፡ወህቡዕ፡ስም፡አጠቃቀም፡ምስጢር፡ ምክር፡ለልጅ ፡ለወዳጅ፡የሚበጅ።

ስላም ፣ጤና ፣ፍቅር ይሁን ለውድ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ ልጆቼ ሁሉ እመኛለሁ። ሰላም ፍቅር ለሀገራችን ይሁን ውድ ወገኖቼ ።ፈጣሪ በምህረቱ እኛንም ሀገራችንንም ይጎበኘን ዘንድ ምኞቴ ነው።

ዛሬ በተለያዩ የሐይማኖት እና ጥበብ መፅሐፍት እና ጥቅል ክታቦች በተለያዩ ፀሎቶች ተፅፈው የሚገኙ የተለያዩ አስማኡል ሁስና(የኣላህ 99 ስሞች )፣ መለኮታዊ አስማት እና ህቡዕ ስሞች በቀላሉ እናገኛለን  ነገር ግን ብዙዎች እኒህን ህቡዕ ስሞች ተጠቅመው ውጤት አያገኙም የዚህም ዋናው ምክንያት ሁለት ነው። አንደኛው ከጥበበኛ አባት ፍቃድ በረካ አለማግኘት እና ሁለተኛው ደግሞ ህቡዕ ስሞቹን እንዴት መጠቀም እንዳለብን አለማወቅ ነው ልጆቼ።

ለምሳሌ፡
-አል አዚዝ---ከክፉ ጠላት ለመጠበቅ ።
-አል ጀባር---ግርማ ሞገስ ለማግኘት።
-አል ሙተከቢር---ጥሩ ተናጋሪ የሚያደርግ።
-አል ሙሰዊር---መናፍስትን ለማቅረብ።
-ብያም ድያም ልያም ልምም ድምም
-ሜላህ መልኺ
-ያህ
-ኤልሻዳይ
እኒህን እና የመሳሰሉትን አስማት ብዙ ቦታ ታገኛላችሁ ነገር ግን የራሳቸው አጠቃቀም ፣ምስጢር ፣ስነስርዓት አላቸው እንጂ እንዲሁ ተመፅሐፍ ስለተገኘ 49 አሊያም 99 ጊዜ ቢደግሙት አይሰምርም ውድ ወገኖቼ። ጥበብ የራሱ ስነስርዓት እና አካሄድ አለው ለዚያ ነው በስነምግባር ተአዋቂው ተጠግቶ የተማረው የተረዳው ብቻ የሚሰምርለት።
እነሆ የእኒህን አስማት(ህቡዕ ስሞች) አጠቃቀም እንደሚከተለው ለውድ የሀገሬ ልጆች እገልጣለሁ በፈጣሪ ፍቃድ ። በማስተዋል ተከተሉ።

*መጀመሪያ ተማንኛውም የመንፈሳዊ የጥበብ አባት ለስሞቹ በረካ ፍቃድ ጠይቁ እና ተቀበሉ። አደራ ማንኛውም በረካ ፍቃድ ገንዘብ አይከፈልበትም ነውር ነው ስለዚህ ይህን የሚጠይቋችሁ ተሆነ ተሌላ ጠይቁ አይሰምርም ውድ ልጆቼ። በረካ ፍቃድ ነፃ ነው ከፈጣሪ የተሰጠ ነው ለዚያ የጥበብ አባት። አይሸጥም አይለውጥም በረካን።

*ሁለተኛው እና ዋናው የስሞቹ አጠቃቀም ነው።
ንፁህ ተሁኖ ከእንስሳት ተዋፅዖ ተቆጥቦ ተሴት ግንኙነት እና አደፍ ከምታይ ሴት ተቆጥቦ ያንን የሚፈልጉትን ህቡዕ አስማት ማታ ስትተኙ በቀኛችሁ አሊያም በግራችሁ ጎን ተኝታችሁ  አስማቱን ያለማቋረጥ መድገም ነው እንቅልፍ በዚያው እንዲወስዳችሁ።
ይህንን ተግባር ለሰባት ቀን ከውኑ። ተሰባተኛው ቀን በሗላ ያንን አስማት ለጉዳያችሁ መጠቀም ትችላላችሁ ማለት ነው። እንግዲህ ልጆቼ እኒህ ሰባት ቀናት አስማቱን ማንገሻ መዋሃጃ ነው ማለት ነው። ማንኛውም ህቡዕ አስማት በዚህ ዓይነት ዘዴ እና ስርዓት ሳይነግስ ሳይዋሃድህ ይሰምርልኛል ማለት ጅልነት ነው ወገኖቼ።

ተላይ በገለፅኩላችሁ ምስጢር መሰረት እጅግ ብዙ አስማትን ተሌሎች ክታቦች የምታገኙትንም ማንገስ እና መጠቀም ትችላላችሁ ማለት ነው ወገኖቼ። ከነገሰ ከተዋሃደ ሗላ በገቢሩ መሰረት መጠቀም ነው።ይህ ታላቅ ስጦታ ነውና በማስተዋል እና ፈጣሪን በማመስገን ተጠቀሙ ጥቀሙበት እላለሁ እኔ መምህር ዓይና።

**አስተውሉ ህቡዕ ስሞች የክርስቲያን የእስላም ተብሎ አይለይም ሁሉም መጠቀም ይችላል መለኮታዊ ናቸውና እንደሰው በሐይማኖት እና በባለፀጋነት አይለዩም ውድ ወገኖቼ።

።።።።።።።ኢትዮ አስማት።።።።
።።።።።።ከጌቶች ሐገር።።።።።።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

29 Nov, 19:46


𐩺𐩨𐩥𐩵𐩱𐩽𐩣𐩵𐩺𐩢𐩬𐩱𐩬𐩬𐩺𐩩𐩽
ምስለ፡ኩርኩም፡ዓይነ፡ጅብ፡ በምስል፡በመሃረብ ፡አሳየው፡ያውቃል፡ባለስልጣኑን።
ተመልከት፡በለው፡ የግራ፡አውራ፡ጣቱን፡ይዘህ። 
ይኸውልህ፡ዘሩን፡ያውቀዋልና።
።።።።።ከጌቶቹ ሐገር።።።።።።።።
።።።።።ኢትዮ አስማት።።።።።።።።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

11 Sep, 16:30


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨🌼🌼🌼፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨መልካም፡አዲስ፡ዓመት፡ይሁን፡ይሁን፡ይሁን።፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሰላም ለውድ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ ልጆቼ  የሰማይ እና የምድሩ ጌታ በቸርነቱ እና ምህረቱ ለዚህ ስላበቃን ምስጋና ይድረሰው። በተለያዩ ምክንያቶች ወዳጅ ዘመድን በሀዘን ላጣችሁ ፈጣሪ መፅናናቱን ያድላችሁ።
ለታመመ ምህረቱን፣ላጣ ማግኘትን፣ላዘነ ለተጨነቀ ፍስሐን ሙላትን ፈጣሪ ደጉ አምላክ ያድልልን። አሐዱ አምላክ ቸርነቱ የማያልቅበት እንኳን ከ ዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ አሸጋገራችሁ፡

ፍቅራችንን፣መቻቻላችንን፣መደጋገፋችንን ፈጣሪ መልሶ ያፅናልን ወገኖቼ። አውቀንም ባለማወቅም ባጠፋን በበደለን ፈጣሪ ይቅር ብሎ በምህረቱ ይጎብኘን። ውዷ ሀገራችን ኢትዮጵያን መሰብሰቢያችንን በፍቅር በመቻቻል እንጠብቅ ዘንዳ በአባትነቴ እማፀናለሁ ወገኖቼ።
ሁሉም ያልፋል ሰው በስራው ይመዘናልና ለማያልፈው  መንግስቱ በበጎ ስራችን ያድርሰን።

የአንድ እናት የአንድ አባት ልጆች ነን እንቻቻል እንዋደድ ውድ ወገኖቼ። የታረዙ የታመሙትን አምላክ በምህረቱ በቸርነቱ ይጎብኝልን።

መልካም ዘመን ይሆንልን ዘንድ ምኞቴ ነው።

መምህር፡ዓይና።

።።።።ከጌቶቹ ፡ሀገር።።።።።
።።።ኢትዮ-አስማት።።።።።።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

29 Jul, 18:48


ህቡዕ፡ጠልሰም፡ለኩሉ

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

29 Jul, 18:48


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
።።።ህቡዕ፡ ማህተም፡ ለኩሉ፡ገቢር፡ይከውን።።።
    ለሁሉ፡ጉዳይ፡የሚሆን፡ምስጥራዊ፡ማህተም
.--------------------------------------------------------------.
ሰላም ለሀገራችን ሰላም ለወገኖቻችን ሁሉ በምድር መላ ላላችሁት ውድ ወገኖቼ ውድ ልጆቼ። ሰላመ ፈጣሪ ተሁላችን ይሁን በረከት እና ሰላም ፣አንድነት በውስጣችን ያስርፅልን የዓለማቱ ሁሉ ባለቤት። ሰው የሆነን ፍጡር ሁሉ የሚጠላ ፣የሚነፍቅ እርሱ ከፈጣሪ ህግ የወጣ እና ቤቱንም ያፈረሰ እንደሆነ ይወቅ ይላል እና ቃሉ አንድነትን እና ማስተዋልን ያድለን ደጉ ጌታ።
______________________________________
ውድ ወገኖቼ ይጥቀማቹ አይጥቀማቹ ባላውቅም ዛሬ እኔ መምህር ዓይና ለሰው ልጅ ሁሉ በሚስጥሩ ብዙ ነገር የሚገለፅበትን ታላቁን ህቡዕ ማህተም እገልፃለሁ። ይህ ማህተም ማንኛውንም አለማዊ ጉዳይ ጠይቆ ለማግኘት የሚጠቅም የሚበጅ የመንፈሳዊ ዓለም  አንዱ
ማህተም ነው በቀመር እና በስእል የተጣመረ። ማንኛውንም ጉዳያችሁን በዚህ ማህተም እና ጠልሰም መከወን እና መሙላት ትችላላችሁ። ተዚያ ተጨማሪም ላስተዋለው ብዙ ምስጢር ይገልጣል እና ፈትሻቹ ፈጣሪን አመስግኑት ስለማይነገር ስጦታው።

በዚህ ማህተም ፈጣሪ የሾማቸው ከአንድ ሺህ በላይ የተወከሉ ሩኻኒያዎች አሉት። ስራቸውን ግና እርሱ ፈጣሪ አንጠርጣሪው ብቻ ነው አዋቂው ልጆቼ።
______________________________________
መጀመሪያ ጠልሰሙን አሳትማቹ ተዚያ በጥቁር አሊያም ቀይ ነድ ቀለም በበላዩ ስላችሁ እና ጠልሰሙን እጣን ከርቤ አጥናችሁ በመቀጠል ለፈለጋችሁት ጉዳይ ለመልካም ነገር እሮብ፣ ለጠቅላላ ጉዳይ ሐሙስ እንዲሁም ለጠላት ቅዳሜ  ከለሊቱ ስድስት ሰዓት በሗላ ጠልሰሙን ከፊታችሁ አቅርባችሁ እጣን እያጨሳችሁ የሚስጥር የሆኑትን ስሞች ሶስት ወይም ሰባት አሊያም 49 ጊዜ ደግማችሁ በመቀጠል

"ኦ ፈጣሪዬ ሆይ ኦ በዚህ ጠልሰም የተወከላቹ ሩኻኒያን ለእኔ ለእገሌ ይህንን ጉዳዬን ሙሉልኝ በተሎ በፍጥነት ። እኔም በዓመት በዓመት በእጣን ከርቤ እዘክራችሗለሁ "

በሉና ሶስት ጊዜ ጠልሰሙ ላይ እፍ እፍ እፍ በሉና ያዙት በኪስ በቦርሳ ።ጉዳዩ ያለጥርጥር ይሞላል። ነገር ግን የዓመት ዝክሩን እንዳትረሱ አደራ ።

ይህ በበረካ የሰጠሁት ነው በነፃ ስለዚህ ያለምንም ክፍያ ተጠቀሙ ጥቀሙበት እላለሁ እኔ መምህር ዓይና።


>>ህቡዕ ስሞቹ
"ያ አላህ  
ያ ሰሚ'  
ያ አሊም 
ያ ሰሪ' 
ያ ዋሲ'   
ያ አድል
ያ አሊይ
ያ አዚም
ያ ሙታ'ኣል
ያ አዚዝ
ያ አፉው
ያ ባ'ኢስ
ያ ፋ'ኣል
ያ ራፊ'
ያ ማኣቡድ
ያ ማኒ
ያ ሙኢድ
ያ ናፊ
ያ ጃሚ
ያ ባዲ'

*ሀያዎቹ ምስጢር ስሞች ከላይ የተገለጡት ናቸው።

***
,አዋቂው ቀይ ዓይና ይደምር*****

***ህቡዕ ጠልሰሙ ከስር ያለው ነው።

፨፨፨፨፨ኢትዮ አስማት፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨ከጌቶቹ ሐገር፨፨፨፨፨፨

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

01 Jul, 18:20


ሰላም የኢትዮ አስማት የመምህር ዓይና ትምህርት እና ምክር ተከታዮች ተማሪዎች እና የማህበር አባላት የሆናችሁ በሙሉ።
በተለይ የኢትዮ አስማት ፌስቡክ እና ቴሌግራም ተከታታዮች አባካችሁ መምህር ከዚ በፊት እንደተናገሩት ማንኛውም የዛር ወይም የቤተሰብ ነገደ ዛር የተጣላው ህይወቱ የተመሰቃቀለበት የቤተሰብ ዛርን ግብር ባለማወቁ እና ባለመሙላቱ የተቸገራቹ ከዚ በፊት አባ እንደገለፁት መጀመሪያ እኛን ሳይሆን በአካባቢያችሁ ያሉ የነገደ ዛር እና አውሊያ አስታራቂዎችን ሄዳችሁ ማናገር ነው የሚቀድመው። ከዛ ቡሃላ ነው መፍትሄ ከሌለው እና ወደሌላ ገንዳ ወይም አገልጋይ ካዘዋወሯቹህ ብቻ ወደ መምህር ማማከር ያለባቹ እንጂ የምትኖሩበት ቦታን ወኪል ሳታነጋግሩ ዘላቹ መምህር ጋር መምጣት ህግም አይደለም ለእናንተም ወጪ ማውጣት ስለሚሆንባቹ እባካቹ ይሄንን ህግ በደንብ እወቁ። ይሄ ህግ ለመምህር ዓይና ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ግዴታ የሆነ ህግ ነው።

:ኢትዮ አስማት:

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

06 May, 20:12


።።።፣።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰላም፣ ጤና፣በረከተ ፈጣሪ አምላክ ተእናንተ ይሁን ልጆቼ ወገኖቼ በመላ።  
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
-------እርስዎ የየትኛው ፈጣሪ ደጋፊ ነዎት?---------
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጊዜ መጥቶ ጊዜ መርጦ ግፈኛን ከደግ ያዋለ የጅል መንደር ይሉት አበው።  ፍየል በግብሩ ሳይሆን በበሽተኛ ሆድ ተመርጦ በተወደደበት፣ ቃል በአጋፋሪ እጃርስ ሳይሆን በአፈቃላጤ በሚንበለበልበት ዘመነ ሹር አሹር አሹቀ ግርማ መንግስት በተባለበት ቀድሞ በተነገረው ቃል ወዓደ  ወዓውደ መንግስት።    ሰላም ለከ ህዝበ ኢትዮጵያ ህዝበ አብዝህ ንዋየ።     


ሁሉ በግዕዝ ስለተነገረ ግዕዝ ክርስትና የሚመስላቸው በእውነቱ እነርሱ ብፁእ ናቸው።ደግሞም ባህረ ሆድ ናቸው ይል።

እናንተ በሰማይ የእስላም(ሰላም)  ቆብ ያደረገ ፈጣሪ ኩሉ ኣላህ ን የምትከተሉ ናችሁ ወይስ በሰማይ በደመና ዘልቆ ያለውን ፈጣሪ መድኅኒ_ዓለም የምትከተሉ ናችሁ?
ወይስ ክርስቶስ (ኢያሱስ) የተባለውን ፈጣሪ ዓለም የተቀበላችሁ ናችሁ?


በእውነቱ ይህ ሁሉ ፈጣሪ እስላምና ክርስቲያን ሁኖ ያለባት እና አህዛቡ በእስላም ነው ክርስቲያን ነው ፈጣሪ ክርክር ዘመንና ሀገርን የበላች ባለእዳ ይህች ደግ ሀገር ኢትዮጵያ  ናት ብል ማጋነን አይደለም ወገን ልጆቼ።  


በእስላሙ ጀሃና እና ጀሃነም በክርስትያኑ ደግሞ ገነት እና ሲኦል ነው በሚል ተመሳሳይ እውነት ነገር ግና የእውቀት ማነስ ውሸት የእራሱን ልጅ የአባትህ ስም ማነው ብሎ የተወለደን ጨቅላ የአባቱን ስም  አባባዬ ብሎ በመጥራቱ የእራሱን ዘር የበላ ህዝብ እርሱ ኢትዮጵያዊ  ነው በእምነቱ  ሲል ለፈጣሪ የፈጣሪን የእጅ ስራ የሚያፈርስ።


በእውነቱ እኔ አዋቂ ሁኜ ሳይሆን በእውነት ሀቂቃ የእኛ ህዝብ ችግር የእውቀት ማነስ መሆኑን ሁሉ እያወቀ ነገር ግና ይዘነጋውና ይላመደዋል።  እንዴት ሰው አንድ በሆነ ፈጣሪ ዘመንና ትውልዱን  ፈጣሪ እስላም፣ ክርስቲያን፤ ፔንጤ ቆስጤ ነው እያለ የነፍስ ዋጋውን እና የመንፈሳዊ ግዴታውን በማይረባ ነገር ያባክናል ልጆች ንገሩኝ።


በእውነቱ  ፈጣሪ እስላም ነው ወይስ ኦርቶዶክስ ወይስ ክርስቲያን ፔንጤ ቆስጤ?  እስቲ ተናገሩ የእናንተን ፈጣሪ የተለየውን። በእውነቱ በእኛ አዋቂነት ድነናል ወይስ አልቀናል?



ፈጣሪ አንድ ብቻ ነው በስም በግብሩ ላወቁት። ይህ ነው እውነት። ይህ ነው እውቀት፣ ጥበብ በእውነቱ። 

ሰው ከሆንን ጀነት፣ገነት ማለት አውቀህ በእምነት የነፍስን ዋጋ ከፍ ማድረግ ነውና ሰው መሆንን አክብሩ ልጆቼ በዚያ ውስጥ አንዱ ፈጣሪ በባርነት እንኳ ቢመስል አለና!!

ፈጣሪ እስላም ነህ ብሎ አይወድም አይጠላም። ክርስቲያን ብሎ አይወድም አይጠላም። ሁሉ በስራው በሰሪው በባለቤቱ ዘንዳ በሐይማኖቱ ሳይሆን በተግባረ ነፍሱ ይለካልና።

መምህር፡ዓይና

።።።ከጌቶች፡ሀገር።።።።።
።።።።።ኢትዮ አስማት።።።።።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

06 May, 20:11


።።።፣።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰላም፣ ጤና፣በረከተ ፈጣሪ አምላክ ተእናንተ ይሁን ልጆቼ ወገኖቼ በመላ።  
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
-------እርስዎ የየትኛው ፈጣሪ ደጋፊ ነዎት?---------
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጊዜ መጥቶ ጊዜ መርጦ ግፈኛን ከደግ ያዋለ የጅል መንደር ይሉት አበው።  ፍየል በግብሩ ሳይሆን በበሽተኛ ሆድ ተመርጦ በተወደደበት፣ ቃል በአጋፋሪ እጃርስ ሳይሆን በአፈቃላጤ በሚንበለበልበት ዘመነ ሹር አሹር አሹቀ ግርማ መንግስት በተባለበት ቀድሞ በተነገረው ቃል ወዓደ  ወዓውደ መንግስት።    ሰላም ለከ ህዝበ ኢትዮጵያ ህዝበ አብዝህ ንዋየ።     


ሁሉ በግዕዝ ስለተነገረ ግዕዝ ክርስትና የሚመስላቸው በእውነቱ እነርሱ ብፁእ ናቸው።ደግሞም ባህረ ሆድ ናቸው ይል።

እናንተ በሰማይ የእስላም(ሰላም)  ቆብ ያደረገ ፈጣሪ ኩሉ ኣላህ ን የምትከተሉ ናችሁ ወይስ በሰማይ በደመና ዘልቆ ያለውን ፈጣሪ መድኅኒ_ዓለም የምትከተሉ ናችሁ?
ወይስ ክርስቶስ (ኢያሱስ) የተባለውን ፈጣሪ ዓለም የተቀበላችሁ ናችሁ?


በእውነቱ ይህ ሁሉ ፈጣሪ እስላምና ክርስቲያን ሁኖ ያለባት እና አህዛቡ በእስላም ነው ክርስቲያን ነው ፈጣሪ ክርክር ዘመንና ሀገርን የበላች ባለእዳ ይህች ደግ ሀገር ኢትዮጵያ  ናት ብል ማጋነን አይደለም ወገን ልጆቼ።  


በእስላሙ ጀሃና እና ጀሃነም በክርስትያኑ ደግሞ ገነት እና ሲኦል ነው በሚል ተመሳሳይ እውነት ነገር ግና የእውቀት ማነስ ውሸት የእራሱን ልጅ የአባትህ ስም ማነው ብሎ የተወለደን ጨቅላ የአባቱን ስም  አባባዬ ብሎ በመጥራቱ የእራሱን ዘር የበላ ህዝብ እርሱ ኢትዮጵያዊ  ነው በእምነቱ  ሲል ለፈጣሪ የፈጣሪን የእጅ ስራ የሚያፈርስ።


በእውነቱ እኔ አዋቂ ሁኜ ሳይሆን በእውነት ሀቂቃ የእኛ ህዝብ ችግር የእውቀት ማነስ መሆኑን ሁሉ እያወቀ ነገር ግና ይዘነጋውና ይላመደዋል።  እንዴት ሰው አንድ በሆነ ፈጣሪ ዘመንና ትውልዱን  ፈጣሪ እስላም፣ ክርስቲያን፤ ፔንጤ ቆስጤ ነው እያለ የነፍስ ዋጋውን እና የመንፈሳዊ ግዴታውን በማይረባ ነገር ያባክናል ልጆች ንገሩኝ።


በእውነቱ  ፈጣሪ እስላም ነው ወይስ ኦርቶዶክስ ወይስ ክርስቲያን ፔንጤ ቆስጤ?  እስቲ ተናገሩ የእናንተን ፈጣሪ የተለየውን። በእውነቱ በእኛ አዋቂነት ድነናል ወይስ አልቀናል?



ፈጣሪ አንድ ብቻ ነው በስም በግብሩ ላወቁት። ይህ ነው እውነት። ይህ ነው እውቀት፣ ጥበብ በእውነቱ። 



መመምህር፡ዓይና

።።።ከጌቶች፡ሀገር።።።።።
።።።።።ኢትዮ አስማት።።።።።

ኢትዮ አስማት (ሐተታ መናፍስት)

21 Apr, 04:01


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ወገኖች በመላ እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ኢድ ሙባረክ።


፨፨፨፨ኢትዮ አስማት።።።።።
፨፨፨፨፨ከጌቶች ሀገር።።።።።

4,479

subscribers

77

photos

3

videos