Fano Media ፋኖ ሚድያ @fanomediaa Channel on Telegram

Fano Media ፋኖ ሚድያ

@fanomediaa


Fano Media ፋኖ ሚድያ (Amharic)

የፋኖ ሚድያ ተስፋሁን ስለዚህ ዝግጅት መነሻ ላይ ይመዝግቡ! ፋኖ ሚድያ በእምነት ፊልሞችን እንዲያቆሙ፣ እንዲሞቅሙና እንዲሻሻሙ እንከፍተው ይዘናል። በቀኑ በአሮጊሺያዊ ምኞታው ላይ ተወዳጁን ለመመልከት፣ እና አጫጭም እየተሾመነ አልቀረም ረሃብ ትበሉ ዘንድ ወደ ስራው ይጠብቁ። ፋኖ ሚድያ የደረሰውን ትንተናና ምርጥ መጀመሪያዎችን እንዲደክምና እንዲሞቁ ይቃችሁ።

Fano Media ፋኖ ሚድያ

21 Nov, 16:29


ሰበር ዜና!

ከአርጆ ጉደቱ እና ከነቀምት ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የነበሩ አንድ ተሽከርካሪ ሙሉ የተፈናቀሉ አማራዎች እንዳያልፉ ክልከላ ተደረገባቸው።

ከአርጆ ጉደቱ እና ከነቀምት ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የነበሩ አንድ ተሽከርካሪ ሙሉ አማራዎች ምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮቲቤ ሲደርሱ እንዳያልፉ ክልከላ የተደረገባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

ህዳር 12/2015 ከነቀምት ተነስተው ወደ አዲስ አበባ ብሎም ወደ ወሎ ኮምቦልቻ ለማቅናት በአንድ ቅጥቅጥ አይሱዙ እየተጓዙ የነበሩ ከእነ ህጻናቱ ከ70 በላይ አማራዎች ምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮቲቤ ላይ ሲደርሱ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ወደነቀምት እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጧል።

እንዲመለሱ የተደረገውም በባኮ ቲቤ ፖሊሶች ሲሆን መኪናውን አስቁመው ፍተሻ ካደረጉ በኋላ ከምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በማንነታቸው ብቻ ተፈናቅለው በከፍተኛ ችግር የከረሙ መሆናቸውን የገለጹላቸው ቢሆንም ሾፌሩን አስገድደው እንዲመልስ አድርገውታል።

ተፈናቃይ ወገኖችም ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን፣ ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ እና በርሃብ እየተቆሉ መሆናቸውን ቢገልጹም ፖሊሶች ከተደዋወሉ በኋላ ለመደብደብ በመዘጋጀታቸው ተገደው ወደ ነቀምት እንዲመለሱ መደረጉ ታውቋል።

እነዚህ እየተንገላቱ ያሉ ተፈናቃዮች ሰኔ 11/2014፣ ነሃሴ 23/2014 እና ጥቅምት 23ለ24/2015 ከጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ለሶስተኛ ጊዜ ተፈናቅለው ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ከተባባሪ የመንግስት አካላት ማንነት ተኮር ጥቃት የተረፉ እና የሚደርስላቸው ያጡ አማራዎች ናቸው።

@Fanomediaa

Fano Media ፋኖ ሚድያ

21 Nov, 14:58


ሰበር ዜና

የሸኔው አውራ ክፉኛ ቆስሏል
ሰኚ የተባለው አመራር ተሰናብቷል

ሀገር ማተራመስና ንጹሐንን መግደል የትግል ስልት  በማድረግ የሚታወቀው የሸኔ አሸባሪ ቡድን አውራ ለጥቂት ከሞት እንዳመለጠ ታማኝ የመረጃ ምንጮች አስታወቁ፡፡

በቄለም ወለጋ ዞን ቄለም አካባቢ አሽንፋ የተባለ ቦታ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ኅዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም በተወሰደው እርምጃ የሸኔ መሪ ነኝ የሚለው መሮ (ኩምሳ ድርባ) ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶበት በሞትና ሕይወት መካከል የሚገኝ ሲሆን፤ ሰኚ የተባለው የቡድኑ ቁልፍ አመራር ደግሞ መሞቱ ታውቋል።

በቡድኑ አመራሮች ላይ የተወሰደው ድንገተኛ ጥቃት በታጣቂው ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ መፍጠሩንና የስነ ልቦና ጫና ውስጥ እንደከተታቸው የሚገልጹት በስፍራው የሚገኙ ታማኝ የመረጃ ምንጮች፤ ክስተቱ በቡድኑ አመራሮች መካከል መጠራጠር እንዲፈጠር ማድረጉን  ያመለክታሉ፡፡   በተለይ በመሮ ዙሪያ ከሚገኙ አመራሮች እና ጠባቂዎች መካከል ለመንግሥት አካላት መረጃ የሚሰጡ ይኖራሉ የሚለው መላምት  አንዱ ሌላውን እንዳያምን እርስ በእርሳቸውም እንዲወነጃጀሉም እያደረገ መሆኑን ይጠቁማሉ።
 
መሮ ሕክምና የማያገኝ ከሆነ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ሕይወቱ ሊያልፍ እንደሚችል በቅርቡ ያሉ ሰዎች እየገለጹ መሆኑን ከታማኝ  ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

@Fanomediaa

Fano Media ፋኖ ሚድያ

21 Nov, 14:43


እኔ ከአንድ ካድሬ አንድ የለሊት ልብስ (ቢጃማ) ዋጋ ያነሰ ደመወዝ የሚከፈላቸው ዩኒፎርም ለባሽ የድሀ ልጆች ጋር ችግር የለብኝም። ነፍሴን ሊያጠፉ ብዙ ሺህ ጥይቶች ተኩሰውብኝ እንኳን አልጠላኋቸውም። ፈጽሞ አልጠላቸውምም አንድ ቀን ያውም በቅርብ አንድ ህዝባዊ ዩኒፎርም እንደምንለብስ እርግጠኛ ነኝ!

ዘመነ ካሴ💪

@fanomediaa

Fano Media ፋኖ ሚድያ

17 Nov, 15:44


ታስሮ የነበረው የምስራቅ አማራ ፋኖ ም/አዛዥ ፋኖ እስራኤል በዛሬው እለት ተፈቷል።

@shewapress

Fano Media ፋኖ ሚድያ

12 Nov, 14:43


አማራ ባንክ ሁልዪ የሚተማመኑበት ባንክ
💚💛❤️

@Fanomediaa

Fano Media ፋኖ ሚድያ

06 Nov, 17:48


ጥቅምት 27/2015 አ.ም ራያ ቆቦ
ለሃገራቸው በክብር መስዋዕትነት ለከፈሉ ለጥምር ጦሩ ጀግኖች የሃገር መከላከያ ሰራዊት ለአማራ ልዩ ሃይል ፋኖና ሚሊሻ በራያ ጢነኛ ሲቪክ ማህበር (የአማራ ወጣቶች ማህበር በራያ ቆቦ) አዘጋጅነት የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

በመታሰቢያ ፕሮግራሙ ላይም የትግራይ ወራሪ ሃይልን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የኢትዮጵያ ጠላቶች እንደሚታገሉ ከተሳታፊዎች ጠንከር ያለ መልዕክት ተላልፏል፡፡
"ፋኖነት ለኢትዮጵያዊነት ህያው ምስክር ነው፡፡"

ምስራቅ አማራ ፋኖ

@fanomediaa

Fano Media ፋኖ ሚድያ

04 Nov, 19:21


መረጃ!!!

በዘመነ ካሴ ላይ መደበኛ ክስ መከፈቱ ተሰምቷል።

ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ክሱን በማረሚያ ቤት እንዲደርሰው አድርገዋል። በዚህ መሰረት ዘመነ ካሴ በቀጣይ ሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ላይ በባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባል።

Fano Media ፋኖ ሚድያ

04 Nov, 18:41


ወልቃይት ጠገዴ ስሜን ጃናሞራ ፣
ሰውም ጎንደሬ ነው፣ መሬቱም የአማራ

Fano Media ፋኖ ሚድያ

03 Nov, 13:12


ራያ አላማጣ ኔትወርክ ተለቋል‼️

Fano Media ፋኖ ሚድያ

03 Nov, 09:08


ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ሰሜን ዕዝ፣ ማይካድራ!😭

@Fanomediaa