Ethiopian Coffee and Tea Authority @ectauthority Channel on Telegram

Ethiopian Coffee and Tea Authority

@ectauthority


Ethiopian Coffee and Tea Authority

Ethiopian Coffee and Tea Authority (English)

Are you a coffee or tea lover looking to expand your knowledge and appreciation for these beverages? Look no further than the Ethiopian Coffee and Tea Authority Telegram channel! This channel is dedicated to all things related to Ethiopian coffee and tea, showcasing the rich history, culture, and traditions behind these beloved drinks. From the various brewing techniques to the different flavor profiles, you'll find everything you need to know to enhance your coffee and tea experience.nnThe Ethiopian Coffee and Tea Authority channel is a community of like-minded individuals who share a passion for these beverages. Whether you're a beginner looking to learn the basics or a connoisseur seeking to deepen your understanding, this channel has something for everyone. You'll have the opportunity to engage with fellow enthusiasts, exchange recommendations, and discover new and exciting brews from Ethiopia.nnWho is the Ethiopian Coffee and Tea Authority? It is a platform that celebrates the rich heritage and unique flavors of Ethiopian coffee and tea. What is the Ethiopian Coffee and Tea Authority? It is a hub for coffee and tea enthusiasts to connect, learn, and explore the world of Ethiopian beverages.nnJoin the Ethiopian Coffee and Tea Authority Telegram channel today and embark on a journey of discovery and delight. Let your taste buds be tantalized, your mind be expanded, and your love for coffee and tea be taken to new heights. Cheers to a world of flavorful possibilities!

Ethiopian Coffee and Tea Authority

05 Dec, 09:02


ለዉድ ተገልጋዮቻችን በሙሉ
የኢትጵያ ቡና ሻይ ባለስልጣን ረቂቅ የአገልግሎት ስታንዳርድ አዘጋጅቶ የእናንተ አስተያየት በማካተት ስታንዳርዱን ለማሳተም በድህረ ገጽ በመጫን አገልግሎቱን ግልፅ ተገማች እና ተጠያቂነት ያለበት የአገልግሎት ስርአት ለመዘርጋት አቅዶል። በዚሁ መሰረት የእረስዎ አስተያየት ጠቃሚ በመሆኑ አስተያትዎን በአሜይል [email protected] ወይንም በስልክ ቁጥር 0900065962 እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን
ቅድሚያ ለተገልጋይ

Ethiopian Coffee and Tea Authority

03 Dec, 18:34


የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት ልዑክ ቡድን ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አመራሮች ጋር ምክክር አደረገ!
  የሁለቱ ሀገራት የቡና ንግድ ወደ ላቀ ደረጃ ይደርሳል ተብሏል፡፡
(ህዳር 20/2017 ዓ.ም፡ኢ/ቡ/ሻ/ባ)፡- የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት ልዑክ ቡድን ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አመራሮች ጋር የጋራ ምክክር አደረገ፡፡ እንደ ልዑክ ቡድኑ ገለፃ ቻይና የኢትዮጵያን ቡና በተለይም የይርጋጨፌ ቡናን የምትገዛ ሲሆን የሁለቱን ሀገራት የቡና ግብይት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ የልዑክ ቡድኑ አበይት ዓላማ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ ዶ/ር አዱኛ ደበላ ለልዑክ ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ የቡናን ምርትና ምርታማነት በመጨመርና ጥራትን በማስጠበቅ እንዲሁም የቡና ግብይቱን በማዘመን ረገድ በርካታ ስራዎችን በመስራት ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል፡፡ በተያያዘም በበጀት ዓመቱ 300 ሺህ ሜትሪክ ቶን ቡና በመላክ ከ1.4 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ማግኘት የተቻለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ቻይና የምትወስደው የቡና ምርት መጠን ከአመት ዓመት መጨመሩን ጠቁመው በአንፃሩ ግን በግብይት ሂደቱ ላይ አንዳንድ ችግሮች እንደገጠሙና በህግ አግባብ እየተሄደበት ስለመሆኑ አብራተዋል፡፡ ዶ/ር አዱኛ በርካታ የቻይና ሀገር የቡና ገዥዎች እየመጡና እንደተቋም በጥምረት እየተሰራ ቢሆንም ሀገራችን አግባብነት የሌለው የግብይት ሂደትን አጥብቃ የምትቃወምና የሁለቱን ሀገራት መልካም ግንኙነት የሚያጠለሽ እንዳይሆን የቻይና መንግስት በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ለልዑክ ቡድኑ አሳስበዋል፡፡
የልዑክ ቡድኑ መሪ Xu Junjun በበኩላቸው ስለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አመስግነው በኢትዮጵያ እና በቻይና መንግስት መካከል ያለውን የንግድ ትስስር ወደ ተሻለ ደረጃ በማድረስ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት መልካም ለማድረግ አብረው እንሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ የልዑክ ቡድኑ የኢትዮጵያ ቡና በጥራቱ እና ጣዕሙ በቻይና እጅግ ተፈላጊ እንደሆነና ለጥራትም ዋጋ ሊከፈል እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ ለዚህም ቡናችንን በሀገረ-ቻይና በስፋት የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራለት ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ዶ/ር አዱኛ ደበላ ቡናችን ፕሮሞት ማድረግ በመቻሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበው የቡድኑ ሀሳብ ለቡናችን ጥራት የበለጠ እንድንሰራ የሚያበረታታ መሆኑን ገልፀው ኢትዮጵያ እንደ ቡና መገኛ ሀገር ከይርጋጨፌ ቡና በተጨማሪ በርካታ የቡና ዝርያዎች ያሏት በመሆኑ ለንግድ ትስስራችን ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ ስለሆነም በቀጣይ ተዘጋጅቶ በሚቀርብልን የስምምነት ሰነድ(MoU) መሰረት ተፈራርመን የጋራ ግንኙነታችን የበለጠ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል፡፡

Ethiopian Coffee and Tea Authority

02 Dec, 17:49


በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች አራት ቤቶች ተገምብቶ ተሰጡ

ኅዳር 23/2016
አዲስ አበባ

በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 10 ለሚኖሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ አራት ነዋሪዎች በኢትዬጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንና በክፍለ ከተማው የጋራ ትብብር የተገነቡ አራት ባለሁለት ክፍል ቤቶች ለነዋሪዎቹ ርክክብ ተካሂዷል። በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር፣ የባለስልጣኑ የሥራ ኃላፊዎች፤ የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አዲሱ ሻንቆ፤ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሠ እና የክፍለ ከተማው ወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነኢማ ሎባ ተገኝተዋል።

ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ባደረጉት ንግግር'' ባለስልጣን መ/ቤቱ ከተሰጡት ተልዕኮና የስራ ተግባር አንጻር በቡናው ሻይና ቅመማ ቅመም ዘርፎች ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ተወዳዳሪና ጥራት ያለው ምርት እንዲመረትና ሃገራችን ኢትዬጵያ ከዚህ ክፍለ ኢኮኖሚ የሚገባትን የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝና የዘርፉ ተዋናዬች የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማገዝና ማስቻል ቢሆንም ከዚህ ጎን ለጎን ባለስልጣን መስሪያቤቱ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያየ ወቅት አነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ቤት በመገንባት በቦንጋ አንድ ከነሙሉ የቤት ዕቃ አስረክቧል'' ብለዋል። አያይዘውም ይህን በጎ ተግባር አጠናክረን በመቀጠል ከቂርቆስ ክፍለከተማ እና ከወረዳ 07 አስተዳደሮች ጋር በመተባበር በወረዳ አስር ለሚኖሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች አራት ባለሁለት ክፍል ቤቶች አስገምብቶ ለባለቤቶቹ ሲያስረክብ ደስታችን የላቀ ነው ካሉ በኋላ እናንተ ዛሬ አዲስ ቤታችሁን የተረከባችሁ እማወራዎችና አባወራዎች እንኳን ደስ ያላችሁ'' ካሉ በኋላ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባስመዘገባቸው ከፍተኛ ውጤቶች ያክል በዚህ በጎ ተግባርም ደስተኛ ነን" ሲሉ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል። በማስከተልም "በቀጣይም ማኅበራዊ ግዴታዎቻችንን ለመወጣት አቅም በፈቀደ መጠን እንሰራለን" ብለዋል። በስተመጨረሻም በዚህ በጎ ተግባር የተሳተፉ አካላትን አመስግነዋል።

የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸው "መንግስት ሰው ተኮር ተግባራት ብሎ ከቀረጻቸው ፕሮግራሞች ከሆኑት መካከል አንዱ የሆኑው የአቅመደካሞችን ቤት መገንባት እንደመሆኑ መጠን በዛሬው እለት ተመርቀው ለተጠቃሚዎች የተላለፉት ቤቶች አንዱ ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።

በቦታው ተገኝተን እንደተረዳነውም ከቤት እገዛ በተጨማሪ የምግብ ዱቄት፣ ዘይትና ማጣፈጫዎች፤ የንጽህና መጠበቂያ ፈሳሽና ጠጣር ሳሙና እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ እገዛ ተደርጓል።

በዝግጅቱ ማብቂያም ባለስልጣኑ ላደረገው በጎ ተግባር በቂርቆስ ክ/ከተማ እና በክፍለከተማው ወረዳ 07 ጽ/ቤት የተዘጋጀ የምስጋና እና የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

Ethiopian Coffee and Tea Authority

28 Nov, 06:54


https://youtu.be/tyjx6jCtKqY?si=93ox42I3dPkKrJ0h

Ethiopian Coffee and Tea Authority

21 Nov, 19:24


በቡናው ዘርፍ ለ8ኛ ጊዜ የሰለጠኑ ተማሪዎች ተመረቁ!!
ህዳር 12/2017 ዓ.ም
ኢ/ቡ/ሻ/ባ
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን እና በዩኒዶ ትብብር የተገነባው የቡና ማሰልጠኛ ማዕከል በቡናው ዘርፍ በቡና ቅምሻ በሁለት ፈረቃ ያሰለጠናቸውን 38 ተማሪዎች እንዲሁም በባሬስታ ሙያ ለ8ኛ ዙር 13 ሰልጣኞችን በድምሩ 51 ሰልጣኞች አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አዱኛ ደበላ እና ምክ/ዋና ዳይሬክተር እና የልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታጋይ ኑሩን ጨምሮ የባለስልጣን መ/ቤቱ ከፍተኛ እና የበላይ አመራሮች፣ መምህራን እና ተመራቂዎች ተገኝተዋል፡፡
ክቡር ዶ/ር አዱኛ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት ባለስልጣን መ/ቤቱ ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር የቡናውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ የሚስችሉ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ በተለይም በዘርፉ እንደችግር ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት እና የቡና ጥራት ችግር በመሆኑ ማዕከሉ ይህንን ክፍተት በመሙላት ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
በጥራት ቁጥጥር ረገድ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ባለሙያዎችን ማሰልጠን አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ያስረዱት ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ማዕከል ዩኒዶን ከመሳሰሉ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በማቋቋም በ8 ዙሮች 350 በላይ የሚሆኑ ብቁ ባለሙዎች ማሰልጠን መቻሉን ተናግረዋል፡፡ እንደ አገርም ይህን ማፍራት በመቻላችን ኩራት ይሰማናል ካሉ በኋላ ተመራቂዎችን የተጣለባችሁን አደራ በታማኝነት እንድትፈጽሙ ሲሉ ተናግረዋል::
ክቡር አቶ ታጋይ በበኩላቸው ቡና ለአገራችን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ቁልፍ ሚና ያለው እና ከአገሪቱ ህዝብ ቁጥር ሩብ ያህሉ የኑሮ መሠረት በመሆኑ ተማሪዎች በዚህ ዘርፍ ላይ መሠልጠን በመቻላቸው እድለኞች መሆናቸውን ለተመራቂዎች ጠቁመዋል:: ይህ ማዕከል በዘርፉ ስልጠና ለመስጠት ሙሉ እውቅና የተሰጠው እና በምስራቅ አፍሪካም ተወዳዳሪ የማይገኝለት በመሆኑ እድለኞች መሆናቸውንና ለዚህም በፍፁም ታማኝነትና የህዝብ ፍቅር ዜጎችን ማገልገል እንደሚኖርባቸው አደራ ጥለውባቸዋል፡፡
ከዚህ በመቀጠልም ማዕከሉ በቡና ቅምሻ ሙያ ያስለጠናቸውን ተማሪዎች የሰርተፊኬት መስጠት ስነ ስርዓት የተከናወነ ሲሆን በውጤታቸው ብልጫ ለነበራቸው ተማሪዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
መረጃዎቻችንን፦
በፌስቡክ @ethiocta
በቴሌግራም፡- https://t.me/ECTAuthority
በድረገጽ፡- https://www.etiocta.gov.et
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/@ethiopiancoffeeandteaautho1042
ተከታተሉን:: እናመሠግናለን!!!

Ethiopian Coffee and Tea Authority

21 Nov, 19:23


Ethiopia Launches National Coffee Platform
21 November/2024
Addis Ababa
ECTA
National Coffee Platform has launched today here in Addis in order to properly utilize the resources of the sector by addressing the existing challenges.
During his opening remark, the Director General of Ethiopian Coffee and Tea Authority Adugna Debela /PHD said that, the establishment of this platform have an immense importance in addressing challenges in the sector and utilize opportunities effectively and push the coffee sector one step ahead.
According to the Director General, it has been earned less than 600,000 and 700,000 US Dollars before some years. But this is already doubled since the last three consecutive years. This year the government launched to generate 2 billion Dollars from coffee alone. He also called the development partners gathered here to support the sector in a very strong manner.
Doctor Adugna also noted that this National Coffee Platform is a crucial step forward in tackling the challenges and seizing the opportunities within the sector. Not only this, the platform provides an access for all stakeholders to discuss on various coffee related issues from cultivation to the market with the view to enhance coffee productivity and quality.
State Minister of Ministry of Finance Semerita Sewasew on her part said that, the Platform is designed to foster dialogue and promote a shared vision among stakeholders with diverse interests and concerns. Not only this, the platform will make a significant contribution to ensuring compliance with EUDR. It will serve as a milestone in creating new commitments toward a unified vision and collective action to address the unique challenges facing Ethiopia.
She added that the establishment of this platform will play a pivotal role in shaping the future of the coffee sector in Ethiopia and it is crucial to step forward in tackling the challenges and seizing the opportunities in the sector.

መረጃዎቻችንን፦
በፌስቡክ @ethiocta
በቴሌግራም፡- https://t.me/ECTAuthority
በድረገጽ፡- https://www.etiocta.gov.et
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/@ethiopiancoffeeandteaautho1042
ተከታተሉን:: እናመሠግናለን!!!

Ethiopian Coffee and Tea Authority

19 Nov, 19:40


ለመላ የባለስልጣን መ/ቤቱ አመራር እና ሰራተኞች "የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ ዕድገት" በሚል መሪ መልዕክት በዛሬዉ ዕለት በመ/ቤቱ አዳራሽ ሲሰጥ ዋለ!!
ህዳር 10/2017

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በዛሬው እለት "የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ ዕድገት" በሚል መሪ መልዕክት ለመላ የባለስልጣን መ/ቤቱ አመራርና ሰራተኞች ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ ተገኝተው መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አዱኛ ደበላ ሲሆኑ "የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል ዛሬ የሚሰጠው ስልጠና በሀገሪቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በላቀ ስኬት በመፈፀምና ተሞክሮን በማስፋት፣ ዕዳዎችን ወደ ምንዳ በመቀየር የህዝብና የሀገርን ጥቅም ለማረጋገጥ አመራሩም ሆነ ባለሙያው አቅም የሚገነባበት ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ዉይይት እንደሚደረግ አመልክተዋል።

ዶ/ር አዱኛ እንዳሉት የመተባበርና አብሮነት እሴቶቻችንን በማጉላት ለሕብረ-ብሄራዊ ትርክት ግንባታ አቅም አድርጎ በመጠቀም አፍሪካዊ እንዲሁም ዓለማቀፋዊ የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች ሀገርን ዕውን የማድረግ ህልምን ለማሳካት መላ የባለስልጣን መ/ቤቱ አመራር እና ሰራተኞች አዉዱን ተረድተው የሚጠበቁባቸውን ተግባራት በከፍተኛ ወኔና የአርበኝነት ስሜት ለመፈፀም እንዲያስችላቸው የሚያደርግ ስልጠና ስለመሆኑ አብራርተዋል።

ምክ/ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር አቶ ሻፊ ዑመር የሰነዱን የመጀመሪያ ክፍል ሲያቀርቡ እንደተናገሩትም ብዙሃነትን ማስተናገድ የሚችል ጠንካራ ሀገረ-መንግስትን ለመገንባት አሰባሳቢ ትርክቶች ላይ አፅንኦት የሚሰጥ፣ የአስተሳሰብና ተሻጋሪ ትውልድ ቀረጻ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ስልጠና እንደሆነ ጠቁመዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ካስቀመጠው ራዕይና ከህዝብ አዳጊ ፍላጎት አንፃር ካስመዘገበው አመርቂ ስኬት ከፍ ያለ ድል ማስመዝገብ እንዲቻል የአመለካከትና የተግባር አንድነትን ማጎልበት ከስልጠናው የሚጠበቅ ውጤት መሆኑንም ገልጸዋል።

ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ በባለስልጣን መ/ቤቱ ምክ/ዋና ዳይሬክተርና የልማት ዘርፍ ሀላፊ በበኩላቸው ስልጠናዉ በጠንካራ ፓርቲ ጠንካራ የመንግስት አፈፃፀምን ዕዉን በማድረግ ፓርቲው ለህዝብ የገባቸውን ቃሎች በተጨባጭ ያረጋገጠበትን ዝርዝር ነጥቦች በየደረጃዉ ለሚገኙ አመራር እና ሰራተኞች እኩል ግንዛቤ እንዲኖር የሚያግዝ እና የነበሩ ተግዳሮቶችንም በግልጽ የሚያስረዳ ሰነድ እንደሆነ አስረድተዋል።
ስልጠናው ሀገር ቀያሪም፣ ሀብት ፈጣሪም ሰው በመሆኑ፣ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች፣ ከተሞችና የፌዴራል ተቋማት ያለው አመራር እና ሰራተኛ በተመሳሳይ የፓርቲው ተልዕኮዎች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመያዝ ለተሻለ ውጤት እንደሚያተጋው አብራርተዋል።

መሪነት ራስን መስጠትን፣ ሆደሰፊነትንና ዓላማን የማሳካት ቁርጠኝነትን እንደሚጠይቅ ጠቁመው፣ ሰራተኛው የወሰደው ስልጠናም የመሪነት ቁልፍ መርሆዎችና ባህሪያትን በአግባቡ እንዲገነዘብ ያደረገ በመሆኑ ፈጣንና እመርታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ አቅም ይፈጥራል ሲሉም ገልፀዋል።

ሰነዱ በበላይ አመራሮች በኩል ከተብራራ በኃላ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል። መረጃዎቻችንን፦
በፌስቡክ @ethiocta
በቴሌግራም፡- https://t.me/ECTAuthority
በድረገጽ፡- https://www.etiocta.gov.et
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/@ethiopiancoffeeandteaautho1042
ተከታተሉን:: እናመሠግናለን!!!

Ethiopian Coffee and Tea Authority

19 Nov, 10:01


በዓለም ታዋቂና ተወዳጅ የሆነውን የሀረር ቡና ወደቀደመ ዝናው ለመመለስ ትልቅ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ!!
የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ጥራቱን ለማሻሻል እና ህገወጥነትን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡

ህዳር 10/2017
ድሬዳዋ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ከተማ የቡና ምርታማነት እና ጥራት ማሻሻያ በሚል መሪ ቃል ታላቅ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡
በንቅናቄው መድረክ ላይ ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ተገኝተዋል፡፡ ከእነሱ በተጨማሪ የባለስልጣን መ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ክቡር አቶ ሻፊ ዑመር እና ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ፣ ክብርት ወ/ሮ መሰረት አሰፋ የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ መሀመድሳኒ አሚን የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክ/ኃላፊና ሌሎች ከፌዴራል ከክልል፣ የዞን እና ወረዳ እንዲሁም ከተለያዩ ምርምር ተቋማት የተውጣጡ ከ200 በላይ አመራር እና ባለሙያዎች፣ አ/አደሮች፣ አቅራቢዎች፣ አልሚዎች እንዲሁም ላኪዎች ተገኝተዋል፡፡
የንቅናቄ መድረኩን በቦታው ላይ በመገኘት ያስጀመሩት ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ እንዳሉት ቡና በአገራችን ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት የመሪነቱን ሚና የሚጫወት ወሳኝ የግብርና ምርት ሲሆን ለዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና ለብልጽግና ጉዟችን መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው፡፡ በዚህ መሰረትም መንግስት ምርቱንና ምርታማነቱን በመጨመርና ጥራቱን በማሻሻል በአለም ገበያ ተፎካካሪነታችንን የበለጠ በማሳደግ ኤኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግሩን ዕዉን ለማድረግ እንዲችል ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት እየተንቀሳቀሰ በመሆኑም አገራችን የቡናን ምርት ለዓለም ገበያ ማቅረብ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በተለይም በባለፉት ሶስት እና አራት አመታት ታላላቅ ድሎች እየተገኙ መምጣታቸውን አስረድተዋል፡፡
ከቡና የሚገኘውን ምርት እና ምርታማነት ለመጨመር እንዲቻል፣ ጥራቱም የተጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን የጠቆሙት ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ «የቡና ምርታማነት እና ጥራት ማሻሻያ» በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ቡና አምራች አካባቢዎች ታላቅ የንቅናቄ መድረክ እየተፈጠረ መሆኑን ይህ የዛሬው መድረክም የዚያ አካል እንደሆነ ተናግረው፤ በዓለም ታዋቂና ተወዳጅ የሆነው የሀረር ቡና፣ በተለይም በሳውዲ አረቢያ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ገቢ እና ተፈላጊነት ያለው ቢሆንም ጥራቱም ሆነ መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ በመሄድ ላይ መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች እያሳዩ በመሆናቸው ወደቀደመ ዝናው እና ክብሩ ለመመለስ ትልቅ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የስብሰባው ተሳታፊዎችም በዚህ በኩል ያሉ ችግሮችን ነቅሰው እንዲያወጡ እና የጋራ መፍትሄ አስቀምጦ ወደ ስራ መግባት እንደሚገባ በአጽንዖት አሳስበዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በበኩላቸው እንግዶቹን የፍቅር ከተማ ወደሆነችው ድሬዳዋ አስተዳደር እንኳን በደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ለዜጎች ኑሮ መሻሻል፣ ለኢኮኖሚ እድገት እና ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ገቢ መሻሻል የሚያግዙ የተለያዩ ኢንሼቲቮች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረጉ፣ የተለያዩ የፖሊሲ ማሻሻያዎችም እየተካሄዱ ተጨባጭ ለውጦች እየመጡ በመሆናቸው ልንኮራ ይገባናል ብለዋል፡፡ በቡና ዘርፍ እየታዩ ያሉ እድገቶች ለዚህ አብነት መሆናቸውን የጠቆሙት ክቡር ከንቲባው የምርት ጥራት እየተሻሻለ፣ የሚገኘውም ገቢ እያደገ በመሆኑ የበለጠ መስራት የበለጠ ወደላቀ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ጥራቱን ለማሻሻል እና ህገወጥነትን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላትም በጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው፣ ከአርሶ አደሩ እና አቅራቢ በተጨማሪ ላኪዎችም የቡና ጥራትን በማሻሻል በኩል ያላቸው ሚና ቀላል ባለመሆኑ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ላኪው በቴክኖሎጂ፣ በግብአት፣ በእውቀት ሽግግር እንዲሁም ሌሎች ዘርፉ የሚጠይቃቸውን ጉዳዮች በመደገፍ ከአ/አደሩ ጋር ተቀራርበው መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ነው አቶ ከድር የተናገሩት፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ እንዲሁም ምክ/ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሻፊ ዑመር አጠቃላይ አገሪቱ በቡና ዘርፍ ያላትን አቅም፣ የምርት መጠን፣ በጥራት በኩል በተሰሩ ስራዎች የታዩ ለውጦች፣ የኤክስፖርት መዳረሻ አገራት እና አገራችን የኤክስፖርት ግኝቱን ለማስፋት እየተከተለች የምትገኘውን ስትራቴጂ በተመለከተ ሰፋ ያለ በፓወር ፖይንት የተደገፈ ማብራሪያ ካቀረቡ በኋላ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፋ ያለ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የተለያየ ዝርያ እና ጣዕም ያላቸው ሀረር ቡናዎችም ቀርበው በባለሙያዎች እንዲቀመሱ ተደርጓል፡፡ መረጃዎቻችንን፦
በፌስቡክ @ethiocta
በቴሌግራም፡- https://t.me/ECTAuthority
በድረገጽ፡- https://www.etiocta.gov.et
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/@ethiopiancoffeeandteaautho1042
ተከታተሉን:: እናመሠግናለን!!!

Ethiopian Coffee and Tea Authority

08 Nov, 10:38


አገራችን ለምለምነቷ ይደንቃል!! አየሯ፣ ምድሯ የሰጡትን ለማብቀል አፍታም አይቦዝንም፡፡
በመዲናችን ጊዮን ሆቴል ለሁለተኛ ጊዜ ለለቀማ የተዘጋጀውን ቡና ምስል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዲህ አጋርቶናል፡፡ መረጃዎቻችንን፦
በፌስቡክ @ethiocta
በቴሌግራም፡- https://t.me/ECTAuthority
በድረገጽ፡- https://www.etiocta.gov.et
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/@ethiopiancoffeeandteaautho1042
ተከታተሉን:: እናመሠግናለን!!!

Ethiopian Coffee and Tea Authority

31 Oct, 17:52


ሴቶች በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ተሳትፎ ከወንዶች እኩል እድል እንዲያገኙ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ፤
በባለስልጣን መ/ቤቱ እና በስፓኒሽ ኮኦፐሬሽን ድጋፍ የተዘጋጁ የዘርፉ የሴቶች ግብይት ስትራቴጂ፣ ጋይድ ላይን እና ዳሰሳ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል::
**************************************************************************************
ጥቅምት 21/2017
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በዛሬው እለት ለመ/ቤቱ መካከለኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ባለስልጣን መ/ቤቱ ከስፓኒሽ ኮኦፐሬሽን ጋር በትብብር ባዘጋጃቸው የቡና ዘርፍ የሴቶች ግብይት ስትራቴጂ፣ ጋይድ ላይን እና ዳሰሳ ጥናቶች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል::
በውይይቱ ላይ ተገኝተው መድረኩን የከፈቱት ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ የባለስልጣን መ/ቤቱ ምክ/ ዋና ዳ/ር እና የልማት ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ በአገራችን ቀደም ሲል በነበሩ የተለያዩ ጎጂ ልማዶች እና አስተሳሰቦች ምክንያት ሴቶችን እኩል በማህበራዊ፣በፖለቲካ እና ኢኮኖሚው ዘርፍ ባላማሳተፋችን ኢትዮጵያ ግማሽ የሰው ሃይሏን እየተጠቀመችበት እንዳልነበር እና ሴት ልጆች በቤት ውስጥ የስራ ጫና ስለሚበዛባቸው ከወንዶች እኩል ተሳትፎ እንዳያደርጉ ማነቆ ሆኖባቸው ቆይቷል ብለዋል፡፡
ሆኖም ግን አሁን ካለንበት ተጨባጭ ሁኔታ የሴቶች ተሳትፎ በብዙ መልኩ እየተሻሻለ መምጣቱን እና በአመራር እና ውሳኔ ሰጪነት ደረጃ ሳይቀር ቁጥራቸው በሚፈለገው ደረጃም ባይሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ ሴቶች በህብረተሰቡ ውስጥ ያላቸውን ሚና ማጉላት አስፈላጊ ነው ያሉት ምክ/ ዋና ዳይሬክተሩ ከቤተሰብ ጀምሮ ያለው የሴቶች ሚና አጠቃላይ እንደማህበረሰብ ብሎም እንደአገር ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ያስችላል፡፡
አቶ ታጋይ አያይዘውም በቡና፣ ሻይና ቅ/ቅመም ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙት ሴቶች ቁጥራቸው ቀላል የማይባል እንደሆነና ከተጠቃሚነት አንጻር ግን ብዙ የሚቀር በመሆኑ በጥናት እና ስትራቴጂ በመመራት የበለጠ ተሳትፏቸውን ማስፋት፣ ከወንዶች እኩልም ተጠቃሚ እንዲሆኑ አበክሮ መስራት ለነገ ተብሎ የሚተው ጉዳይ አለመሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

አቶ ፍፁም መንገሻ በባለስልጣን መ/ቤቱ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ስራ አስፈጻሚ የተዘጋጁትን የዘርፉ የሴቶች ግብይት ስትራቴጂ፣ ጋይድ ላይን፣ community of practice እና ዳሰሳ ጥናቶች በስፋት ያቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎች በቀረቡት ሰነዶች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገው ከመድረክ በቂ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

Ethiopian Coffee and Tea Authority

25 Oct, 09:31


Ethiopian Coffee and Tea Authority signed MOU with its Chinese Counter part
October 24, 2025
ECTA
The Ethiopian Coffee and Tea Authority signed an MOU with the Chinese Circulation of Promotion Center of the Ministry of Comerce of PRC. From the Chinese side Director of Circulation of Promotion Center of the Ministry of Comerce of PRC, His Excellency Mr. Wang Bin where as from the Ethiopian side Director General of Ethiopian Coffee and Tea Authority, His Excellency D/r Adugna Debela signed the MOU.

To the occassion, officials of different bodies of coffee sector organisations from both China and Ethiopia attended. From the Chinese side the deligates were led by Mr. Wang Bin, where as from the Ethiopian side officialss of different coffee assosations were attending.

Ahead of the signing of the Memorandium of Understanding, both Excellencies explained about the coffee situations of their countries. First to explain was H.E Mr. Wang Bin. He said that in China the coffee industry is growing; as a result 170 thousand coffee shops are opened. He also said, ''Ethiopia is the major Coffee exporter to China.’’ ''To import coffee from Ethiopia,'' he added, '' China has been expending 1 milion USD per year and in 2030, he said, it is planned to enhance it and invest 1 hundred milion USD.

In his explanation about activities done concerning coffee, he reported that series of coffee exhibitions (to which Ethiopian Ambasador to China was invited and visited), exhibiting coffee in food expos, coffee festivals and coffee week in different provinces of China were conducted. At the end of his speech, he expressed his gratitude to the Authority for its inviting them to Ethiopia, and he said that he believes such meetings not only increase mutual understanding but also important for promotion and cooperation. In his conclusion, he invited the Authority to attend coffee expoes and exhibitions to be organised in China.

His Execellency Adugna Debela (D/r), on his part, welcomed his guests and briefly explained about Ethiopian coffee production and export. In his explanation he said that in Ethiopia there are 1.1 milion farm lands. Having this resource and others in hand, he added, starting from this year it is planned to produce 1 milion metric tone coffee.

In his explanation about Ethiopia's coffee export, he said that Ethiopia is exporting coffee to 62 countries; of which the largest importers are USA, Japan, Belgium and Germany. In relation to that, he exclaimed that China is also coping up. Therefore, 300 thousand metric tone coffee is expected to export to China; and so far 12 thousand metric tone coffee have been exported, making Ethiopia earn 17 billions USD. Concerning so far relation with China regarding coffee, he informed that different bodies including the Agricultural Standing Committee of the Chinese Parliament have visited Ethiopia in relation to coffee. In his conclusion, he announced that Ethiopia is to organize coffee exhibition in China, and Ethiopian embassy is working on that.

After the speech of both Excellencies, main actors of Ethiopian and Chinese coffee sectors explained about their companies and the performance of them.

Finally, the meeting was concluded with the signing of the Memorandum of Understanding between both parties.

Ethiopian Coffee and Tea Authority

25 Oct, 09:24


ቻይና የኢትዮጵያን ቡና ለመግዛት እና ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት እያሳየች ነው፡፡
የአገሪቱ የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ተወካዮች እና ባለሀብቶች የልዑካን ቡድን ከክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ጋር ተወያይዋል፡፡
ጥቅምት 14/2017
ኢ/ቡ/ሻ/ባለስልጣን
ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ በዛሬው ዕለት ከአስር በላይ ከሚሆኑ የቻይና የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ተወካዮች እና ባለሀብቶች የልዑካን ቡድን አባላት ጋር በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ክቡር ዋና ዳ/ር ዶ/ር አዱኛን ጨምሮ M.r Wang Bin በቻይና ንግድ ሚ/ር CIPC/Circulation Industry Promotion Center ዳይሬክተር፣ በቻይና የተለያዩ የቡና ኩባንያዎች ተዋናይ የሆኑ እና ንቁ ተሳትፎ ያላቸው ባለሀብቶች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ የተቋማት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የተለያዩ የቡና ማህበራት ፕሬዝደንቶች፣ ሌሎች የቡና ባለሙያዎች እና እሴት ጭመራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተገኝተውበታል፡፡
ቻይናውያኑ እንደገለጹት በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለዝና የሆነውን የኢትዮጵያን ቡና በስፋት ለመግዛት ያላቸውን ፍላጎት የገለጹ ሲሆን ወደፊት በተጠናከረ ሁኔታ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ MOU መፈራረም ችለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ወቅት ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ኢትዮጵያ በቡናው ዘርፍ ያላትን የመልማት አቅም፣ እየለማ የሚገኘውን የቡና መጠን፣ ወደ አለም አቀፍ ገበያ እየተላከ በየዓመቱ እየተገኘ ያለውን ገቢ እና መዳረሻ አገራቱን በተመለከተ ሰፋ ያለ ገለጻ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናዎች በጥራት እየተመረቱ ልዩ ቡና በሚል ለበርካታ አገራት እየተላኩ ጥሩ ገቢ እስገኙ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ከነዚህ መካከልም ቻይና እንደምትገኝበት እና ከአስሩ ዋና መዳረሻ አገራት ተርታ መሰለፍ መቻሏ የሚደነቅ መሆኑን፤ በቅርቡም ከመጀመሪያ ተርታ መሰለፍ እንደምትችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያን ቡና በስፋት ለአለም ለማስተዋወቅም በመንግስት በኩል ሰፋፊ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን ጠቁመው በየአገሩ የሚገኙት ኤምባሲዎችም በዚህ ረገድ ቀላል ያልሆነ ሚና እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም ዛሬ የሚካሄደው ስምምነት የኢትዮጵያን ቡና ከእስከዛሬው በበለጠ ለቻይና ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ እና ሰፊ የገበያ እድል ለመፍጠር አይነተኛ አስተዋጽዖ ሊኖረው እንደሚችል አብራርተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በበኩላቸው በየጊዜው እያደገ የመጣውን የቻይናውያንን የቡና ፍላጎት ጠቁመው በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ከአረቢካ ቡና መገኛነት በተጨማሪ አይነተ ብዙ እና በጣዕማቸው ተወዳጅ የሆኑ ቡናዎች አምራች በመሆኗ መላ ትኩረታቸውን ሊስበው እንደቻለ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ቡናዎችን በስፋት የመግዛት እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ድጋፍ ለማድረግም ያላቸውን ፍላጎት በስፋት ገልጸዋል፡፡
ከተለያዩ ማብራሪያዎች በኋላ የሁለቱ አገራት በቡና በኩል በቀጣይ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምንት የተፈራረሙ ሲሆን የየቡና ማህበራት ተወካዮችም እያከናወኗቸው በሚገኙ ስራዎች እንዲሁም ቀጣይ በጋራ መስራት በሚቻሉባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በባለስልጣን መ/ቤቱ የሚገኘውን የቡና ማሰልጠኛ ማዕከል የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን ወደተለያዩ የአገሪቱ ቡና አብቃይ አካባቢዎችም ምልከታ እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡

Ethiopian Coffee and Tea Authority

24 Oct, 10:27


ሃገር አቀፍ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ላይ ለባለስልጣኑ ሰራተኞች ገለጻ ተደረገ
ከሪፎርሙ ጋር በተያያዘም የባለስልጣኑ የዝግጅት ሁኔታ ለተቋሙ ሰራተኞች ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል!!
ጥቅምት 14 /2016
ኢ/ቡ/ሻ/ባ
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከለውጥ ትግበራ ጋር በተያያዘ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል፡፡ የሪፎርሙ መነሻ ሃሳብ የሆነውም ከዚህ በፊት የነበሩ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሞች በጥናት የተለዩ ሰባት ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲቻል ለማድረግ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ እነዚህንም የሚፈታ ሰባት አምዶች ያሉት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በሃገር አቀፍ ደረጃ እንደተዘጋጀና ከዓላማዎቹም አንዱ እስካለንበት ጊዜ ድረስ የመጣው ተለዋዋጭ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም አስቀርቶ ዘላቂ የሆነ ሪፎርም ለማስፈን እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ለዚህም ዓለማቀፍ ስታንዳርድ መሠረት ያደረገ ሪፎርም እንደሆነም ተብራርቷል፡፡
በዚህ ዙሪያ ሰነዶችን ያቀረቡት የባለስልጣኑ ተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ግርማ የሪፎርሙ ሙሉ ይዘት ምን እንደሚመስል አብራርተዋል፡፡ በገለጻቸውም የብቃት ምዘናን አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የብቃት ምድቦችን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ በሁለት ዘርፎች ማለትም በቴክኒክና ባህሪ ብቃቶች ከአመራሩም ከሠራተኛውም እንደሚጠበቅ በሪፎርሙ የተቀመጠ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በእነዚህም ምዘና አንድ ተቋም እንደተቋምነቱ ለመቀጠል 40 በመቶ ሠራተኞቹ ምዘናዎቹን ማለፍ እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡ አመራርና ሠራተኞች ብቻ ሳይሆን ተቋማትም እንደተቋም ሪፎርሙ ላይ በተቀመጡት መመዘኛዎች ምዘና እንደሚካሄድበቸውና በምዘናውም 85 ከመቶና ከዚያ በላይ ማምጣት እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡ በሰራተኛና አመራሮች በተቋሙ የምዘና ውጤቶች መካከልም ተመጣጣኝነት ያለው መናበብ ግድ እንደሚልም ገልጸዋል፡፡
ከሳቸውም በማስከተል የተቋሙ የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ መሪም ሰዒድ ከሪፎርሙ አንጻር ተቋሙ የተሄደባቸውን ርቀቶች አብራርተዋል፡፡ በማብራሪያቸውም ሰባቱን አምዶች ለመተግበር የሚያስችሉ ሥራዎች እንደተሰሩ ገልጸው ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ሰነዶች እንደተዘጋጁና ሌሎች የተከናወኑ ስራዎችን አቅርበዋል፤ ለሪፎርሙ ዝግጅትም ሆነ ትግበራ የሚያስፈልጉ በጀት ዝግጅት ሁኔታም አሳውቀዋል፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ወቅትም ባለስልጣኑ ለግል ዘርፍ መሰጠት ያለባቸው ዘርፎች መለየት ከሚጠበቁ ስራዎች አንዱ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን አገልግሎት መስጠት ብቻ ሳይሆን እሴት መጨመር ከአመራሩም ከሰራተኛውም በቀጣይ በትኩረት የሚታይ ጉዳይ እንደሆነ ተወስቷል፡፡ እሴት መጨመር ሲባል ምን ማለት እንደሆም ተብራርቷል፡፡
በስተመጨረሻም የባለስልጣኑ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሠፊሳ አባቡ የማጠቃለያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በገለጻቸው የባለስልጣኑን የሪፎርም ስራ እየሠሩ ያሉትን አመራሮችንና ሠራተኞችን አድንቀው በሪፎርሙ ስራ ሁሉም መረባረብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ሪፎርሙ በሕግ ማዕቀፍ የተደገፈ እንደሆነና በዚህም ተጠያቂነትን የሚያስከትል እንደሆነ ከተናገሩም በኋላ በዚህ ምክንያት ሪፎርሙ ጠንካራ እንደሆነና ጠንካር ያለ ዝግጅትና አተገባበበር እነደሚጠበቅ አክለው አሳስበዋል፡፡ በማንበብም ይሁን በተገኘው መንገድ ሁሉ አመራሩና ሠራተኛው በሪፎርሙ ዙሪያ ግንዛቤውን ማስፋት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ ዛሬ የተካሄደው ማብራሪያ በአስተዳደር ዘርፍ ላሉ አመረራር እና ባለሙያዎች ሲሆን በትላንትናው እለት ደግሞ የልማት እና ግብይት ዘርፎች ሲወያዩ መዋላቸው አይዘነጋም፡፡

Ethiopian Coffee and Tea Authority

19 Oct, 11:56


And then, the teams of national experts(consultants) present the methodology and approach for conducting the gap analysis and how develop the policy recommendations that will answer all the EUDR standards as an Inception report. After this it is expected that partners can incentivize or buy at premium price from exporters or producers who are working as per the standards of EUDR.At the end many constructive questions,comments and suggestions were given by the participants and windup the workshop

ECTA Public Relations and Communication team covered this news in place

Ethiopian Coffee and Tea Authority

19 Oct, 11:56


The Ethiopian Coffee and Tea Authority in Collaboration with GIZ Made a Kick-Off Meeting on Fit for Fair Project

* The project supports a Due Diligence Regulation Compliance

( October/2024:ECTA): The Ethiopian Coffee and Tea Authority (ECTA) in Collaboration with GIZ has made a kick-off Meeting at Eliana Hotel, Addis Ababa, on Fit for Fair project. The project has supporting the Ethiopian coffee supply chain to align with the German and EU Due Diligence Regulatory framework.

The Meeting has been officially opened by Mr. Sefisa Ababu,the manager of the General Director Office of ECTA. Mr. Sefisa,in his opening speech,said this project is very valuable for Ethiopia to comply the EU- Due Diligence Regulation compliance.

Regarding on the Ethiopia's coffee sector a short and precise overview presentation has given by Mr. Tizazu Edosa,an Alternative Market and Contract Administration Chief Executive of ECTA. He clearly presented on an   overview of Ethiopian Coffee Industry. He focused on the Economic, social and cultural values and contributions of our coffee in Ethiopia. He explained that coffee potentiality,it's variety,and the main markets of Ethiopian coffee . Tizazu added that the radical market change seen today is because of the coffee reforms implemented by ECTA. Due to this,the marketing efficiency has been improved; enable farmers to directly export their coffee and favours cooperation schemes between farmers and investors. Most importantly, Tizazu said, it allows a vertical integration between suppliers and exporters. He also raised Ethiopian coffee production trend for the last seven years that shows an increment from year to year as that of the coffee export value,too.

According to his presentation, all the achievements are gained since ECTA guided by the developed comprehensive Ethiopian Coffee Strategy( 2019-2033); He also added that the strategy aims to improve productivity, quality,and market efficiency of coffee and increasing annual export revenue and farmer incomes significantly.

Miss Feven Bekele,an Economic Advisor of GIZ, SUVASE project,and the representative of Miss Carolina, the manager of SUVASE project , in her part said Fit for Fair project is one of a GIZ global project currently works in supporting the operationalisation of German and EU corporate sustainability Due Diligence legislation in agricultural supply chains. She briefly specify certain activities of Fit for Fair project and it's purpose is as to conducting the gap analysis and develop policy recommendations prepared on the required adjustments to be made. Deven added that GIZ working with ECTA in improving the sustainability of coffee by providing trainings on gender,digitalization inclusion disabled people in coffee value chain,child labor and mainly working on traceability and others .

Mr. Peter Borchert,from GIZ, pointed that ECTA is the primary implementing organization receiving support from GIZ  He added that since EU companies are required to collect relevant information, we engage in a risk analysis, and implement prevention and mitigation measures to minimize human rights and environmental risks. And , as he said, this has direct implications on partner and respective supply chain actors as obligations are passed down the value chain.Peter explained also the main project objectives, key activities,and the global project framework as well as the project approach as a collaborative network and the expected results of the Fit for Fair project,too .

Dr. Inti Schubert, from GIZ, gave his presentation on a brief contextualization of the new European Due Diligence Law on deforestation and human rights (EU-DD Laws) . Dr. Inti explained the contents of the laws in chronological order are German supply Chains Act( LKSG)- 2021/23; European Deforestation Regulation (EUDR)-2024/25 and Corporate Sustainability Due Diligence Directive(CSDDD). Finally, he raised the main challenges for national actors in the supply chain,too .

Ethiopian Coffee and Tea Authority

19 Oct, 03:49


https://www.youtube.com/watch?v=HEmw6EFprkc

Ethiopian Coffee and Tea Authority

19 Oct, 03:47


https://www.2merkato.com/news/trading/8102-ethiopia-exceeds-coffee-tea-and-spice-export-targets-in-first-quarter

Ethiopian Coffee and Tea Authority

19 Oct, 03:46


https://allafrica.com/stories/202410170584.html

4,081

subscribers

3,250

photos

21

videos