EAG Primary BTU

@eagprimarybtu


This is the channel of the one and only true Labour: EAGPBTU

EAG Primary BTU

20 Oct, 09:35


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ከዉህደቱ ቡሐላ ያደረገው የመጀመሪያ የምክር ቤት ጉባኤ በምስል👇👇

EAG Primary BTU

20 Oct, 09:28


ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በሙሉ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር (EAGPBTU) ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር (EAGBTU) ጋር ታሪካዊ ዉህደት ባደረገ ማግስት የመጀመሪያዉን የመክፈቻ የምክር ቤት ጉባኤውን አደረገ።

አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበር ጋር ያደረገዉን ታሪካዊ ውህደት ተከትሎ የመጀመሪያዉን የምክር ቤት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ጥቅምት 7 እና 8 ቀን 2017 ዓ.ም ያደረገ ሲሆን ይህም ሠራተኛ ማህበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሰራተኞችን ውክልና እና ድምጽ ለማጎልበት የሚያደርገውን ጥረት አዲስ ምዕራፍ የሚያመለክት ነው።

ጥቅምት 7 እና 8 በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የተካሄደው የሁለት ቀናት ጉባኤ ከሁለቱም የቀድሞ ማህበራት የተውጣጡ እና አሁን በአንድ አመራር የተዋሃዱ መሪዎችን አሳትፏል። ቀዳሚ አጀንዳው የሰራተኞችን ጉዳይ ለመፍታት ስትራቴጂ በመቅረጽ እና የሰራተኞችን ጥቅም ማስጠበቅ፣ እንከን የለሽ ሽግግርን ማረጋገጥ እና ለቀጣይ ተግባራት መሰረት መጣል ላይ ያተኮረ ነበር።

የመጀመሪያ ቀን አዲስ የተቋቋመው ምክር ቤት በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት ማህበሩን በቅንነት፣በታማኝነት እንዲሁም በታላቅ የአደራ ስሜት እንዲመሩ አቶ መገርሳ አስፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ፕሬዝደንት ሆነው እንዲያገለግሉ በምክር ቤቱ ሙሉ ድምፅ መርጧል። ከዚህም በመቀጠል ፕሬዝደንት መገርሳ አስፋው በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት ሶስት የአብራሪ ሰራተኞችን ጨምሮ 12 (አስራ ሁለት) አባላት ያሉትን የስራ አስፈፃሚ አካላትን ፤ እንዲሁም 3 (ሶስት) አባላትን ያቀፈ የስራ ሂደት ገምጋሚ አካላትን ለምክር ቤቱ በማቅረብ አፀድቀዋል።

ከዚህም በማስከተል አቶ መገርሳ እና የምክር ቤት ቡድናቸው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና የስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና WST ማናጅመንት ጋር ወደተዘጋጀው የምሳ እና የትዉውቅ መርሀ ግብር በክብር ተጋብዘዋል። በመርሀ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር የስራ አስፈፃሚ አካላት እንዲሁም የምክር ቤት አባላት ከድርጅቱ የስራ አስፈፃሚ አካላት ጋር ትዉውቅ ያደረጉ ሲሆን ቀጣዩን የስራ ዘመን የሰራተኛ መብት ፣ጥቅማ ጥቅም እና የስራ ዋስትና በሚረጋገጥበት እንዲሁም አመቺ የስራ ሁኔታ በሚፈጠርበት አግባብ ላይ በመነጋገር እና በመደራደር ዉጤት ተኮር የሆነ ስራ በጋራ ለመስራት የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ፕሬዝደንት አቶ መገርሳ አስፋዉ በቅርበት ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ውጤት ተኮር የአመራር ስልት በመከተል የሚታወቁት አቶ መገርሳ አስፋዉ የሁለቱን ማህበራት ዉህደት እዉን ለማድረግ ቁልፍ ሚና የተጫወቱትን የቀድሞ የማሕበሩ አመራሮችን ያመሰገኑ ሲሆን በዚሁ ቀን ከቀትር በኋላ ዉሎ የማህበሩ የስራ አስፈፃሚ አባላት በተገኙበት በቅርቡ ማህበራችን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ጋር ያደረገዉን የዉህደት ስምምነትን አስመልክቶ ይፋዊ ጋዜጤዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ሁለተኛ ቀን ማለትም ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ምክር ቤቱ እና የስራ አስፈፃሚው መልሶ የተገናኘ ሲሆን በወሳኝ ኹነቶች ላይ ውይይት አድርጓል። ምቹ የስራ ሁኔታን ለመፍጠር፣የሰራተኛ መብትን ለማስጠበቅ፣የሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም ለማሳደግ እና የስራ ደህንነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቷል። በዉይይቱ መክፈቻ የማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ መገርሳ አስፋዉ ለአስራ ሁለቱ የስራ አስፈፃሚ አካላት የስራ ድርሻ ክፍፍል ያደረጉ ሲሆን በተሰጣቸው የስራ ኀላፊነት በ ኮርፖሬት ደረጃ መዳሰስ ያለባቸዉን የሠራተኛ የወል ጉዳዮች ላይ ከድርጅቱ የበላይ አካላት ጋር በመነጋገር እና በመደራደር አመርቂ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በፅኑ አሳስበዋል። አቶ መገርሳ አስፋዉ አክለውም በመጪዎቹ ሶስተ ወራት መሠራት ስለሚገባቸው የሠራተኛው የወል ጉዳዮች እንዲሁም በዲቪዥን ደረጃ ስለሚፈቱ ጉዳዮች የትኩረት አቅጣጫወችን አስቀምጠው ማብራሪያ ሰተዉበታል። በዚህም መሠረት የወል ጉዳዮች ተብለው ለተዘረዘሩት አንኳር ነጥቦች ሶስት አባላትን የያዘ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል ፤ ከዚህ በተጨማሪ በ ዲቪዥን ደረጃ ለሚፈቱ ጉዳዮች የማህበሩን ምክትል ፕሬዝደንት እና ጀነራል ሰክሬተሪን ጨምሮ ሁለት ሁለት አባላትን የያዘ ታስክ ፎርስ በመጪወቹ ሣምንታት በሁሉም የድርጅቱ ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚ የሚመሩ ክፍሎች ጋር ጉዳዮቹ መፍትሔ በሚያገኙበት አግባብ ዉይይት እንዲደረግ አቅጣጫ ተሰትዋል። የእነዚህን ጉዳዮች አስፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የተቋቋሙት ግብረ ሃይሎች የሰራተኛ ማህበሩን ስትራቴጂካዊ ግቦችን በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ አዲሱ አመራር ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት ቁርጠኛ ነው ብለዋል አቶ መገርሳ።

ፕሬዝደንቱ ስለ ማህበሩ የወደፊት ተስፋ ያላቸውን ስሜት ገልፀው፣ ይህ ውህደት ሰራተኞቻችንን የሚወክል ጠንካራ የመደራደር አቅም ያለው አመራር ፈጥሯል ፤ ይህም የሁሉም ሰራተኞች የስራ ደህንነትና ጥቅማ ጥቅምን ለማሻሻል እና ለመጠበቅ ትልቅ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ መገርሳ አስፋው የስራ አስፈፃሚ አካላቱን እንዲሁም የምክር ቤት አባላቱን ከተከበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች የተጣለበትን ታላቅ አደራ በብቃት እና በቁርጠኝነት እንዲወጣ የአደራ መልእክታቸውን አሰተላልፈዋል።

ለበለጠ መረጃ ከታች ባለው አድራሻ ይጎብኙን:
Mr. Motolomi Bitena
EAGPBTU Executive and Communication officer
Phone: +251901224581

Building a Strong Future Together!!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር!!!
Ethiopian Airlines Group Primary Basic Trade Union (EAGPBTU)

EAG Primary BTU

19 Oct, 15:15


https://youtu.be/GgYv1KzTIRs?si=hXHnFp4iWcGNCr5L

EAG Primary BTU

19 Oct, 15:15


ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች በሙሉ

ማህበራችን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ጋር ያደረገዉን ይፋዊ የዉህደት ስምምነት በማስመልከት የማህበሩ አመራሮች የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ


በቅርቡ ማህበራችን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ጋር ያደረገዉን ይፋዊ የዉህደት ስምምነት በማስመልከት የማህበሩ አመራሮች የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የማህበሩ አመራሮች እንደገለፁት የሁለቱ ማህበራት ዉህደት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አብራርተዋል

መግለጫዉን ማየት የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን

Building a Strong Future Together!!!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር!!!

EAG Primary BTU

10 Oct, 19:26


ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች በሙሉ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ዓመታዊ የጠቅላላ ጉባዔዉን አደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ (EAU Auditorium) እንዲሁም መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ዓመታዊ የጠቅላላ ጉባዔዉን አድርጓል፡፡

የማህበሩ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያዉ ቀን የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ተካልኝ ተርፋሳ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር “ያለፈውን የ2023/24 በጀት ዓመት በስኬት በማጠናቀቅ በዛሬዉ ዕለት ዓመታዊ የማህበራችንን ጠቅላላ ጉባዔ ለማድረግ በመብቃታችን በማህበራችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር እና በራሴ ስም እንኳን ደስ አለን/ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ” ብለዋል። አቶ ተካልኝ አክለዉም የአየር መንገዳችን ስኬት እንዲሁ በቀላል የተገኘ ሳይሆን የድርጅታችን የጀርባ አጥንት በሆናችሁት በእናንተ መላዉ ሠራተኞች የመጣ እና በየሥራ ክፍላችሁ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ በሙሉ መሠጠት ለድርጅታችን ያበረከታችሁት የሥራችሁ አፈፃፀም ዉጤት ነዉ፤ የአየር መንገዳችን ዕድገትና ስኬት እንዲህ በዚህ መልኩ ሲነሳ የእናንተ የመላው ሠራተኞቹ ስም ይጠራል፤ የእናንተ ስም ሲነሳ ደግሞ ማህበራችሁ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ስም አብሮ የሚነሳ መሆኑን አውስተዋል።

በጉባዔዉ ላይ የተገኙት የአየር መንገዳችን የሰዉ ሃብት አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘነበወርቅ ገ/ጻዲቅ በበኩላቸዉ “ከየክፍሉ ተወጣጥታችሁ በዛሬዉ ዕለት በጠቅላላ ጉባዔዉ ለመሳተፍ የመጣችሁ የጉባዔዉ አባላት በሙሉ ድርጅታችን በጥሩ ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ የሚገኝ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ እኔም በጉባዔአችሁ ላይ ስለተገኘሁ የተሰማኝን ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ” ብለዋል፡፡

በጠቅላላ ጉባዔዉ የመጀመሪያ ቀን የጠዋት ዉሎ በርካታ የማህበሩ እንቅስቃሴዎች የተዳሰሱበት ዓመታዊ ሪፖርት እና የ2017 ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድና በጀት የቀረበበት ሲሆን፣ በቀረበዉ ሪፖርት እና የ2017 ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድና በጀት ላይ ሰፊ ዉይይት ተደርጎ ሪፖርቱ እና የ2017 ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድና በጀት በጠቅላላ ጉባዔዉ ጸድቋል። የማህበሩ የ2016 ዓ.ም የዉጭ ኦዲት ሪፖርትም የቀረበ ሲሆን ዉይይት ከተደረገበት በኋላ በጠቅላላ ጉባዔዉ እንዲሁ ጸድቋል። የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብም ለአሠራር እንዲያመች ተደርጎ የተሻሻሉ አንቀጾችና አዳዲስ የተካተቱ ደንቦች ከቀረቡ በኋላ በጠቅላላ ጉባዔዉ እንዲጸድቅ ተደርጓል።

በመጀመሪያዉ ቀን የቀትር በኋላ ዉሎ ጠቅላላ ጉባዔዉ በተለይም በቅርቡ ማህበራችን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ጋር ያደረገዉን ይፋዊ የዉህደት ስምምነት ላይ ሰፊ ዉይይት አድርጓል። በዚህ ረገድ የማህበራችን ፕሬዝዳንት አቶ ተካልኝ ተርፋሳ “ይህ የዉህደት ስምምነት አንድነትን በማጉላት ልዩነትን የሚያጠብ ሲሆን፣ የማህበራችንን ህልዉና የሚያረጋግጥ እንዲሁም የሠራተኛዉን መብትና ጥቅም የሚያስከብር እና የድርጅቱን የኢንዱስትሪ ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ እጅግ ብስለት በተሞላበት አኳኃን የተፈጸመ በርካታ የዉይይት መድረኮችን የወሰደ ታሪካዊ ስምምነት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል። በመቀጠልም ፕሬዚዳንቱ የዉህደት ስምምነቱን አጠቃላይ ዓላማዎች እና የስምምነቱ ዋና ዋና አንቀጾች በማቅረብ ለጉባዔዉ ያስረዱ ሲሆን የጉባዔዉ አባላትም በተደረገዉ የዉህደት ሰምምነት ላይ ሰፊ ዉይይቶችን በማድረግ የማህበሩ አመራሮች ዉህደቱ ዕዉን እንዲሆን ላደረጉት ጥረት እና ላሳዩት ቁርጠኝነት አድናቆታቸዉን ገልጸዋል። በመቀጠልም ጉባዔዉ የተደረገዉን የዉህደት ሰምምነት ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን በስምምነቱ መሠረትም ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ማህበሩን በበላይነት ለመምራት የተወከሉ 35 አባላት የያዘ የምክር ቤት አባላት በጠቅላላ ጉባዔዉ ጸድቋል፤ የምክር ቤት አባላቱም በጠቅላላ ጉባዔዉ ፊት ቀርበዉ ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል።

በጉባዔዉ ሁለተኛዉ ቀን ዉሎ በኢንዱስትሪ ግንኙነት እንዲሁም የአመራር ክህሎት ማጎልበት ላይ ትኩረት ያደረጉ ሁለት የተለያዩ ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ከቀትር በኋላ ደግሞ የድርጅቱ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ፣ የድርጅቱ የንግድ ዘርፍ ዋና አስፈጻሚ (Chief Commercial Officer) አቶ ለማ ያዴቻ እንዲሁም የድርጅቱ ኮርፖሬት የሰዉ ሃብት አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘነበወርቅ ገ/ጻዲቅ ተገኝተዉ በተለያዩ የሠራተኞች የወል ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዉይይቶች ያደረጉ ሲሆን፣ ከጉባዔዉ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በጉባዔዉ ማጠቃለያ ላይ ሶስት አባላት ያሉት የማህበሩ ኦዲት ኮሚቴ ቀርቦ በጠቅላላ ጉባዔዉ የፀደቀ ሲሆን በተለያዩ ዘርፎች የላቀ አበርክቶ ለነበራቸዉ ግለሰቦች የተዘጋጀላቸዉ የዕዉቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።


Building a Strong Future Together!!!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር!!!

Ethiopian Airlines Group Primary Basic Trade Union (EAGPBTU)

EAG Primary BTU

10 Oct, 14:56


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በምስል

EAG Primary BTU

06 Oct, 02:04


እንኳን ለ እሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ.

በዓሉ የሰላም የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችንን እንገልፃለን

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር!!!

Building a Strong Future Together!