የደሱ ግጥሞች @dygojjam Channel on Telegram

የደሱ ግጥሞች

@dygojjam


☞ የስብህና ልቀት ለማምጣት ከመፃህፍት ጋር እናዉጋ
☞ በዚህ ቻናል ተወዳጅ የሆኑ ግጥሞችንና አስተማሪ ታሪኮችን ይቀርቡበታል
👇👇👇👇👇👇👇
ለሃሳብ አስተያዬታች
@Almnu6
@Almnu6

የደሱ ግጥሞች (Amharic)

የደሱ ግጥሞች በስብህናውን ለማምጣት ወደመፃህፍት ግጥሞች እናዉጋ። በዚህ ቻናል ተወዳጅ የሆኑ ግጥሞችንና አስተማሪ ታሪኮችን የተለያዩ ሃሳብ አስተያዬቶችን በመነጋገር ላይ በመተንበር ቋሚ እንዲሰማና አስተካክለዉ ማህበረሰብን የመግለፅ አስተካክላችሁ። እናመሰግናለን በ@Almnu6 ላይ።

የደሱ ግጥሞች

15 Jan, 13:03


♡ህይወትን የሚያስውቡ ውብ ሰዎች አሉ፣ሳትፅፍ ያነቡሀል፣ሳትናገር ይረዱሀል፣ውለታን ሳይሹ መልካም ይውሉልሀል፣በእነዚህ ሰዎች ውስጥ መኖር ህይወትህን ውብ💞 ያደርገዋል።
እንዳለመታደል ለኔ እንደዛ አይነት ሰዎች ገጥመውኝ አያውቁም

የደሱ ግጥሞች

10 Jan, 06:22


😍 ከአቅም በላይ ስለወደድኩሽ
      🙏 ይቅር በይኝ!
💞ከማንም በላይ ከአንቺጋ መሆን በመፈለጌ
      🙏 ይቅር በይኝ!
❤️በህይወትሽ ውስጥ ትልቅ ቦታ እንድትሰጪኝ በመጠየቄ
      🙏 ይቅር በይኝ!
💘መካድ እስከማልችል ድረስ ስላፈቀርኩሽ
     🙏 ይቅር በይኝ!
💔መውደዴ ስላልገባሽና በእኔ ውስጥ ያለሽን ቦታ ስላላወቅሽ
    🙏ይቅር እልሻለሁ!

የደሱ ግጥሞች

06 Jan, 19:18


እንኳን አደረሳችሁ ክርስትያን ቤተሰቦቼ🥰🥰🥰

የደሱ ግጥሞች

06 Jan, 17:29


🙆‍♀.ተወለደ....
ከከብቶች ማደሪያ
በግርግሙ ስፍራ ባለች ጥሪኝ ቦታ፣
የሰይጣንን ወጥመድ
ድር ማጉን በጥሶ በጥበብ ሊረታ፣
ስለ ሰው ልጅ ድህነት
ከመፍጠሩ ይልቅ
ያዳነበት ጥበብ
ሚስጢሩ እንዲገርመን ተወለደ ጌታ።
ተፃፈደሱ
እንኳን አደረሳችሁ🥰🥰🥰

የደሱ ግጥሞች

06 Jan, 07:47


በለስላሳ ጣቷ እየዳበሰችኝ፣
ቀዝቃዛው ገላዬን
ከቆፈን እንዲለቅ
በሰጋር ትንፋሿ ሙቀት ስትለግሰኝ፣
ከአቀረቀርኩበት
ቀና ያልኩ ጊዜ አይኖቿ ፈጠዋል፣
ያልገባትን መልስ
አንደበቷ አውጆ ጠይቂው ይላታል፣
ትኩር ብዬ አየሗት
ስቃ እንዲህ አለችኝ
ከሰራ አካላትህ ሰሪው ከለገሰህ፣
የትኛው ገላህን ይበልጥ ትወዳለህ?
እኔም መለስኩላት፦
ከአካላቴ ሁሉ ወደዋለሁ ጥርሴን፣
በሳቅ ይሸፍናል ሀዘንተኛ ነፍሴን።
ተፃፈ✍️ደሱ

የደሱ ግጥሞች

04 Jan, 17:49


አላችሁ🖐

የደሱ ግጥሞች

02 Jan, 18:56


#ስላንቺ
ዕልፍ ነው ጠያቂው፣ሚሊዮን ነው መልሴ፣
በቅጣት ጨንገርሽ፣ስለ ደማች ነፍሴ፣
ለጠየቀኝ ሁሉ ብዙ መልስ ባገኝም፣
ስላንቺ......ከንግዲህ፦
ዝምታ ነው አቅሜ፣ሌላ መልስ የለኝም፣
ተፃፈ✍️ደሱ

የደሱ ግጥሞች

01 Jan, 19:48


#አልመጣምን_ምን_አመጣው ??
.
.
ዛሬ ነበር የቀጠርሽኝ፤
እዚህ ነበር "ናልኝ" ያልሽኝ።
ፀሃይ ስትደምቅ በስተምስራቅ ስትፈካ በሀገሩ፣
ከወፍ ጋራ እኩል ሲያዜም ሲዘማምር ጫካ ዱሩ።
የእግዜር በጎች ከልጆች ጋር በየመስኩ ሲሯሯጡ፣
ስስ እንቦሶች ሽር ብንት ሜዳው መሃል ሲቃበጡ።

ያኔ ነበር "ድረስ" ያልሽኝ፤
እዚህ ነበር የቀጠርሽኝ።

እኔ አፍቃሪሽ ያንቺው ንጉስ፤
ናፍቆት ፍቅር እንደታቀፍኩ ከንጋት ጋር ጎህ ቀድጄ፣
የፀደይ ወር እቅፍ አደይ፤ ላፍቃሪ ሩህ ይዤ በእጄ።
ካልሺኝ ቦታ እንደደረስኩ ዙሪያ ገባው ባማትረው፣
ችላ ብትሽ ቀረሽ መሰል ቃልሽ ፍቅሬን ሰባበረው።

አንቺዬ..............፤
እንደ ቀላል እንደ ዘበት፤
"እመጣለሁ" ባለ አንደበት፤
ምን ይሉታል ቃልን ማጠፍ "አልመጣም"ን ምን አመጣው ?
አጀብ መቼም ወንድ መሆን ያልተነሳ እግርሽ ቀጣው።
ብዬ እያሰብኩ ስብሰለሰል እዚሁ ሆኜ ልቤ አረጀ፣
በትዝታሽ ሳቅ... እያለ ይኸው ጊዜም አብሮኝ ጃጀ።

         " አጀብ መቼም ወንድ መሆን !!! "

        ተፃፈ ዓቢይ

የደሱ ግጥሞች

01 Jan, 17:45


ከፀዳል ገላሽ ላይ
የደረብሽው ሸማ
የአይኔ ግርዶሽ ታክቶት፣ቋሚ ህግ ቢያሽረኝ፣
ያዬ አመነዘረ
በሚል ፍርድ ስቀርብ
ተቀጭዋ አንቺ ነሽ ፣ዘማዊው እኔ ነኝ፣
ተፃፈ ✍️ደሱ

የደሱ ግጥሞች

01 Jan, 15:13


በሰንኩላን ፊደል፣በብጣሽ ወረቀት፣
እንዴት ሰው ይፅፍል፣አንቺን ያህል እውነት፣
ተፃፈ✍️ደሱ

የደሱ ግጥሞች

27 Dec, 08:54


#ብክነት
ተዋረድን፣
ከል ለበስን፣
ለነፃነት ደጅ ወጥተን፣
ዲናር መርጠን ተከተልን፣
ነፍሳችን አጎደፍን፣የወንድም ነፍስ አሳዘንን፣
በወንድም ደም፦
ነጠብጣብ ስንኩል ሆሄያት ከተብን፣
ድል ነበር የፍሬያችን፦
ጭብጡ የህዝብ ሳቅ ነበር ቅሉ፣
በጎጥ ድግስ ሰከርን፦
ገና በጥንስሱ ጥላቻ ሆነብንና ብቅሉ💔
ተፃፈ✍️ ደሱ

የደሱ ግጥሞች

27 Dec, 08:08


...........
    # ተማፅኖ
ኢትዮጲያዬ ልጄን ውለጅ፣
አንደወጣ ቀረ ከደጅ፣
አፈር ምሶ የቀበረ፣
ውለጅ ይላል እያረረ፣
ከገጠሩ
ከመንደሩ
ከጎዳና ከድንበሩ
ለዘላለም ለማይደላው
ለምን ? ልጄን ልጅሽ በላው!💔
ተፃፈ✍️ደሱ

የደሱ ግጥሞች

24 Dec, 20:08


ያልተኛችሁ ብቻ ችርስ👍

የደሱ ግጥሞች

18 Dec, 19:10


# የሰልፍ አደባባይ
በሀዘን ደብዝዞ በጨፈገገ ፊት፣
በድካም ተረትቶ በናዎዘ ጉልበት፣
ርሀብ አጎሳቁሎት በተናወጠ አንጀት፣
በሰው ጢሻ ድርድር፣ሰልፍ ውጣ ብለውኝ፣
በዛ በሰው ድርድር፣በሳ በሰው ጫካ፣
ይሰቀል ይሰቀል
እያልኩ ሳንቧርቅ ጩኸቴ እስኪያረካ፣
ጩኸቴን የሰሙ
አብረው የዘመሙ
ዕልፎች ሲገረሙ
ድንገት ብትት ስል
ይሰቀል የምለው፣እራሴን ነው ለካ።
ተፃፈ✍️ደሱ

የደሱ ግጥሞች

17 Dec, 15:23


ነብሴን ጨፈለ‘ኳት ~ ስጋዬ አስገድዶኝ፣
ለኔ ብሎ ሲሞት ~ ለእርሱ መኖር ከብዶኝ፣
ተፃፈ ✍️ደሱ

የደሱ ግጥሞች

17 Dec, 13:37


ጊዜ በሰው ህይወት ፣ዘበት አይታከተው፤
እኔ ምላሽ ባጣም ፣መጠየቄን አልተው፤
ኩታ ገጠም ናቸው፣ አልፋና ኦሜጋ፤
እንዴት ቀን ይመሻል፣በቅጡ ሳይነጋ🙁
ተፃፈ ✍️ደሱ

የደሱ ግጥሞች

13 Dec, 18:42


#ደሀና ጦር ሜዳ...
ለንግስናው ፅናት
ለሀብቱ ደህንነት
ሹምና ሀብታሙ፣በፍክክር ሜዳ የሚቆምሩበት፣
በሸካራ መዳፍ፦
ተዳብብሶ ያደገ፣በዛ ሚስጊን አባት፣
በጎበጠ ወገብ፦
ለአቅመ አዳም የበቃ
የጭራሮ ድርድር ባደከማት እናት፣
ያ ሚስጊን ደሀ ልጅ
ሀገርህ ዘመመች፣ድረስ ያሉት ለታ፣
ባላወቀው ሴራ፣ባልገባው ጨዋታ፣
ጠላቱን ሊገድል፣ድንገት ሳበ ቃታ፣
ጠላቱ ወደቀ
ገዳዬ ፎከረ
የደም ጀብድ አስክሮት በደስታ እየረካ፣
ግና ምን ዋጋ አለው
ደስታ ሁሉ ከንቱ
ፉ'ከራ ሁል ብላሽ
ያ ሚስጊን ደሀ ልጅ
ገድሎ ሚ'ፎክረው ወንድሙ ነው ለካ💔
ተፃፈ✍️ ደሱ

የደሱ ግጥሞች

13 Dec, 17:00


#ትርፋና ኪሳራ...
አፈር እየለጋ
እንደሚዘል ጅረት፣ህይዎት ላንቺ ድራኝ፣
በሚናፍቅ ፍቅር
እንደምስጊኑ አፈር፣ጥለሽ ጠልዘሽኝ፣
ጅረት ሆንሽ በኔ
አፈር ሆንኩኝ በኔ
ሽ ጊዜ ረግጠሽኝ፣ሽ ጊዜ ማልነጥፍ፣
ዘነጋኝ ሲመስልሽ፣እያፈቀርኩሽ እጥፍ፣
እኔ እኔን ብከስርም፣ላንቺ ለካ ነኝ ትርፍ።
ተፃፈ✍️ ደሱ

የደሱ ግጥሞች

26 Nov, 17:31


አለውኮ ወገን ረሳችሁኝ በአዲስ መልክ ልመጣ ነው

የደሱ ግጥሞች

08 Nov, 01:05


"ቆንጆ ሴት እንደ ጎመራ እሸት ነው ማንም የሚቀጥፈው የሚያልፍ የሚያገድመው የሚበጥሰው መንገድ ዳር የተዘረጋ ሰርዶ አይነት፣በቆንጆ ሴቶች ዘንድ ፍቅር እንደ ተረት ራሱ አይከበርም የሚመካ በቁንጅና ይመካ ተባብለው ስለ ፍቅር ያፌዙ ነው የሚመስለው.
"ፍቅር ለማንም የሚታደል ሳይሆን አምላክ ለሚወዳቸው የሚሰጠው አያሌ ሀዘን የታጀበበት የስቃይ ላይ ደስታ ነው፣በፍቅር ውስጥ ያለች ልቅሶ በደስታ ቤት ካለች ሳቅ ይበልጥ ታረካለች..
"ፍቅር እየተከፉ ማንባትን፣እያጡ ማልቀስን፣አጅባ በንፁሃን ሰዎች ዘንድ የለመለመች ቅዱስ ኪዳን ነች ለታደሉ የዘሩትን በደስታ የሚኖሩባት ላልታደሉ ከነ አካቴው ራሳቸውንም የሚያጡባት የሰቶ መቀበል እውነታ ናት ፍቅር...
"ፍቅር ከሀይማኖትም በላይ የሆነ ረቂቅ ነገር ነው፣ልታስቀሪው ተው ልትይው የማትችይ ራስን የሚቀማ፣የመናፍስቱን ጥበብ ያስናቀ ረጅም ተስፋን ያዘለ እውነታ ነው...💋💋💋💋
"ፍቅር ንጉሱንና ንግስቲቱን፣ወዛደሩንና ወዛደሯን፣ ሸቃላውንና ሸቃሊትን፣ቆንጆውንና ቆንጂቱን አንድ ላይ አያጣምርም ይልቁንስ ቆንጆዋን ከፉንጋዋ፣ንጉሱን ከሰራተኛዋ፣ወዛደሩን ከንግስቷ የሚያስተሳስር የእውነት መንገድ ነው መውደድ...💪💪💪💪💪
ተፃፈ ✍️ደሱ(ሌሊት 9:30)እንቅልፍ እምቢ ሲለኝ የተፈላሰፍኩት ነው 😏😏

የደሱ ግጥሞች

07 Nov, 23:25


ቀሰሙ ተነክሯል..ብራናው የለፋ
ብዕርማ ሞልቷል..ወረቀት መች ጠፋ፤
አገሩ የጥጋብ፣ጉርሻው ተርፎ ከአፍ፣
ካመመኝ ቆይቷል ፣ምናባቴ ልጻፍ ?
✍️ #ዘአማኑኤል

የደሱ ግጥሞች

30 Oct, 03:05


https://t.me/ethioyaried

የደሱ ግጥሞች

14 Oct, 18:08


ዝምታዬ አላስጨነቃችሁም😃

የደሱ ግጥሞች

28 Sep, 06:26


ቃል መተርጉማኑን ሲስት
ንዋ ህሊናን ቀምቶ፣ሰውነትን ሲሸረሽር፣
ምናለ እኔም ብረሳሽ
ፍቅርሽ እኔን ትቶልኝ፣ለራሴ መኖር ብጀምር!
ተፃፈደሱ

የደሱ ግጥሞች

26 Sep, 05:35


"የሰማዕታት አደራ........
እኔና ጓዶቼ ስንሰዋ ብታይ፣
ወድቀን አታልቅሽ፣ሳቅሽ ይድረስ ሰማይ፣
ይሄ ነው ማልለው፣እድሜ ላይጨመር፣
ምንድን ነው ማልቀስሽ፣ለዐማራ ስቀበር፣
ይልቅ እኔና ጓዶቼ፦
ከልባችን ግርጌ፣ፀድቆ የታነፀው፣
በመኖራችን ውል፣ለንጋት ያጨነው፣
የዐማራ ሲቃ አለ፣ሙተን የገደልነው፣
ብቻ ዐማራ ሲሞት ነው፦
የኔና ጓዶጄ የሞታችን ብክነት ለልቅሶ የሚበቃው፣
ደሞ ያልነገርኩሽ፦
እኔና ጓዶቼ ከሞታችን፣በፊት ስናዎራ ብታይ፣
ጉድ ይል ነበር ጠላት፣ይስቅ ነበር ሰማይ፣
ዝናብ ተደምሞ፣አጀብ ብሏል ፀሀይ፣
እውነት ነው የምልሽ
ማመን እስኪያቅትሽ
እኔና ጓዶቼ ስለ ዐማራ፣ሲቃ ስንናባ ብታይ፣
ድሮ ይለወጣል በሞት፣ማልቀስ ይሆናል ዘመናይ፣
ገዳይን ቀዝፌ
ትውልዴን አትርፌ
ዶፉን እየታገልኩ፣ድንገት ስወድቅ ካየሽ፣
ከቶ እዳትከፊ፦
ዐማራ እንዲኖር ነው፣ህዝቤ ከሞት ሊሸሽ፣
አደራ በውድቀቴ ሰበብ
ጥሻ እንዳትጥሺ፣
ልጄ የሚለውን ትዝታ አትቀስቅሺ፣
ባልኖርሽው መንደርሽ እንባ እንዳታፈሺ፣
ግን በዐማራው ሰማይ ላይ
ገዳይ ተሰናብቶ፣ህዝብ ሲስቅ ካዬሽ፣
በድኔ ነው ያለው፣፧በድኔ ነው ያዬሽ
ተፃፈደሱ

የደሱ ግጥሞች

08 Sep, 21:46


አንዳንዴ፦
መኖር ከህይዎት ሳይጠምር፣
እርባና አልባ ቀናት ስቆጥር፣
ሰው መሆን ማቅ አልብሶኝ፣
እድሜዬን በዋይታ ሲሾም፣እኔን ከኔ ቀምቶኝ፣
የፈተና ስንኩል ስሆን፣ካቃተኝ ዛሬን መሻገር፣
ምና'ለ ባልተፈጠርኩኝ፣እናቴ መህና በነበር።
አንዳንዴ፦
ዕልፍ ሰቀቀን ልታቀፍ፣
በትላንት ትዝታ ስገረፍ፣
ፀዳል አምናዎች፣ህያውነቴን ያዘሉ፣
በዛሬው መርገም አለሜ፣ሀሳቤ ሁነው ከዋሉ፣
እኔ ነኝ መፃጉ፣የህይወት ደዌ ሰንክሎኝ፣
የመርገም በትሩን አውሬዶ ፈጣሪ፣በምድር የቀጣኝ፣
አንዳንዴ፦
እኔ'ነቴ አደናቅፎኝ
ቀኔን በትላንት ጋርዶብኝ
አለቅሳለው በትዝታሽ፣የእቅፍሽ መንበር ሲታዎሰኝ፣
ብቻ የኔ አንዳንዴ፣ለሌላው እኩ'ያ ባይሆንም፣
ሁሉም የራሱ አንዳንዴ አለው፣
ሳቅና ልቅሶውን በጥርሱ ከልሎ፣የቆመ እንደምንም!!!
ተፃፈደሱ አለው እየመጣው ነው

የደሱ ግጥሞች

03 Sep, 16:57


(ባምሳልሽ ፈጠረን)

የሰው ልጅን ሁሉ
ባንድ አምሳል ፈጠረ፣ ይላልና ቃሉ
ፍጥረታት ውብ ሆነው፣ ባንቺ ይደምቃሉ።
እኔም
ባልደርስም ከልክሽ
ቆንጆ ነኝ ከሰራኝ፣ በአምሳለ መልክሽ።
(ከነፉንጋ መልኬ)
እስካንቺ ነውና፣ ውበትን ሲለኩ
እግዚሐርም ቆንጆ ነው፣ ከሰራሽ በመልኩ።

እረሳችሁኛ😃😃😃

የደሱ ግጥሞች

22 Aug, 05:06


በአዲስ መንፈስ
ወንድነቴ ከጦር ወሬ፣ተገላግሎ ፍቅር ሻተ፣
ለመኖር ስል
አለመኖርን መናቅ ጀመርኩ፣መስከረሜም ባተ ፣
ላልል ነገር
በዘመን ጎር ተንሳፍፌ
በሀጥያቴ ፅድቅሽን ገፍፌ
ለመከራ የዳርኩሽ
ምስጊን ነፍሴ፣ይቅር በይኝ፣
ትላንትም ፣ዛሬም፣ነገም እኔ ፍረደኛ ነኝ ፣
ተፃፈደሱ

የደሱ ግጥሞች

12 Aug, 19:40


ሰዎች በአዲስ መልክ እየመጣው ነዎ

የደሱ ግጥሞች

06 Jul, 10:31


ዓፄ ናዖድ ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ

ጻድቁ ንጉሥ የነገሡት ከ1487 ዓ.ም እስከ 1499 ዓ.ም ጻድቁ ከስምንተኛው ሺህ አታድርሰኝ ከእህል ከውሃው አታቅምሰኝ እያሉ ይጸልዩ ነበር። ጸሎታቸውም ተሰምቶላቸው ስምንተኛው ሺህ መስከረም 1 በ1500 ዓ.ም ሊገባ እርሳቸው ነሐሴ 7 ቀን በ1499 ዓ.ም ዐርፈዋል::

በስምንተኛው ሺህ በሬው ሻኛ የለው፣
ገብሬው ምርት የለው፣
ላሙ ወተት የለው፣
ቆንጆው አፍላ የለው፣
ጎበዝ ጉልበት የለው፣
ችግር ማብቂያ የለው፣
ንጉሥ እምነት የለው፣
ውሸት ማብቂያ የለው፣
ቄሱ ትምህርት የለው፣
መናኝ ገዳም የለም ፣
ዳኛው ችሎት የለው፣
አማኝ ምግባር የለው፣
ጎልማሳ ሚስት የለው፣
ለሰው ፍቅር የለው።
ወገኔ ስማኝ እንዲህ ያለ ጊዜ አይቼም አላውቅ፣
ሲገናኙ መውደድ ሲለዩ ቦጨቅ።
በእንዲህ ያለ ጊዜ ምግባር በሌለበት፣
ታላቁ ታናሹን ሰውን በብላበት፣
በስምንተኛው ሺህ ጉድ ነው መሰንበት፣
አዛባ መዛቅ ነው እሾህ ያለበት።
በስምንተኛው ሺህ ባላው ተንካ ተንካ፣
እባክህ ወንድሜ እከከኝም ቢልህ ራሱን አትንካ፣
የነቢያት ትንቢት ተፈጸመ ለካ።

ዓፄ ናዖድ እንዲህ እያሉ ሲናገሩ ሕዝብ ያዳምጥ ነበር ይባላል።

ነሐሴ 7 ቀን 1500 ዓ.ም - በስመ መንግሥት አንበሳ በፀር ይባሉ የነበሩት ዓፄ ናዖድ በዚህ ዕለት አርፈው የ12 ዓመት ልጃቸው ዓፄ ልብነ ድንግል ወናግ ሰገድ ተብለው ነገሡ።
ዐፄ ልብነ ድንግል እርሳቸው በነገሱ ጊዜ ጦርነት በሀገሪቱ እንዲኖር ወይም የሚዋጋቸው እንዲፈጠር ፀሎት ያስደርጉ ነበር።
ዓፄ ልብነ ድንግል (የዙፋን ስም "አንበሳ ሰገድ" ወይም ዳግማዊ ዳዊት ) ነው።
የኢትዮጵያና አዳል ጦርነትም የተጀመረው በኒህ ንጉስ ዘመን በ1528 እ.ኤ.አ. ነበር። ሚስታቸውም ሰብለ ወንጌል ትባል ነበር።
ዓፄ ልብነ ድንግል የዓፄ ናዖድ ልጅ የዓፄ በአደ ማርያም የልጅ ልጅ ናቸው። ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብም ቅድመ አያታቸው ናቸው።
ዓፄ ናዖድ 13 ዓመት ገዝተው ሲሞቱ በ1500 ዓ.ም. ዓፄ ልብነ ድንግል ገና የ12 ዓመት ወጣት እያሉ ነገሡ። ስመ መንግሥታቸውም ወናግ ሰገድ ተባለ። ወናግ ማለት በኦጋዴን (ሱማሌ) ቋንቋ አንበሳ ማለት ነው።
የግዕዙን ወይም የአማርኛውን ቋንቋ «አንበሳ ሰገድ»ን ትተው በኦጋዴን ቋንቋ ወናግ ሰገድ የተባሉበት ምክንያት ምናልባት ያን ጊዜ በይፋትና በፈጠጋር ያለውን ግዛት የሚያውኩ ያዳልና የሱማሌ ተወላጆች ስለሆኑ እነሱ በሚያውቁት ቋንቋ ተሰይሞ ለማስፈራራት ይሁን ወይም የነሱ ገዥ ጭምር መሆናቸውን ለማስታወቅ ይሁን ወይም ከአባታቸው ከዓፄ ናዖድ ስመ መንግሥት (አንበሳ ሰገድ) በትርጉም ቢቀር በአጠራር እንዲለያይ ይሁን በትክክል አይታወቅም።
ዓፄ ልብነ ድንግል ራሳቸው ለፖርቱጋል ንጉሥና ለሮማ ሊቀ ጳጳስ በጻፉዋቸው ደብዳቤዎች ላይ «ስሜ ልብነ (ዕጣን) ድንግል ትርጓሜው ድንግል ያበራችለት ይሄም ስም የተሰጠኝ ቅድስት ጥምቀትን በተቀበልኩበት ቀን ነው፤ በነገሥኩ ጊዜ ደግሞ ዳዊት ተባልኩኝ» ስለሚል በዳዊት ላይ ተጨማሪ ወናግ ሰገድ ሆኖ በሁለት ስመ መንግሥት ይጠሩ ነበር ማለት ነው።
ዓፄ ልብነ ድንግል በነገሡ ጊዜ ወጣት ስለነበሩ በመንግሥቱ ሥራ እናታቸው እቴጌ ናዖድ ሞገሳ የቅድመ አያታቸው የዓፄ በአደ ማርያም ባለቤት እቴጌ እሌኒ በሞግዚትነት ያግዟቸው ነበር።
እነ ራስ ወሰን ሰገድ ና እነ ራስ ደገልሃ ን የመሳሰሉትም ታላላቅና ታናናሽ መኳንንት የመንግሥቱ የሥልጣንና የሥራ ተካፋይ ነበሩ።
በመጀመሪያ፣ የዓፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት የሰላምና የደስታ ቢሆንም የመጨረሻ ጊዜያቸው በግራኝ መነሳት ምክኒያት የጦርነት፤ የሁከት፤ የመከራና የስደት ጊዜ ሆኖባቸዋል።
ከፖርቱጋል መንግሥት በቀጥታም ሆነ በእቴጌ እሌኒ በኩል ቢወዳጁ የጀመሩት ወዳጅነት ለጊዜው ጠቡን አጣደፈው እንጂ ከወረራ ሊያድናቸው አልቻለም።
አለቃ ተክለየሱስ ዋቅጅራ የኢትዮጵያ ታሪክ ብለው በጻፉት መጽሐፋቸው ዓፄ ልብነ ድንግል ጦርነት ከመውደዳቸው የተነሳ የገዳም አባቶችን ጦርነት የሚገጥመኝ እንዲነሳ ፀሎት ያስደርጉ እንደነበር ገልጸው ። አህመድ ግራኝም እንዲፈጠር ያደረጉት እርሳቸው ናቸው በማለት ይገልፁታል።

ምንጭ፦ ተክለ ጻድቅ መኵሪያ፤ 1953 ዓ.ም.፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከዐፄ ልብነ ድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ
ምንጭ ፦ ምጽአተ ክርስቶስ

የደሱ ግጥሞች

02 Jul, 10:08


ካልጠበቁት ሰው እንደሚሰነዘር ጥቃት አሳማሚ ህመም የትም የለም !!

በሂወቴ ከምጠላው ማንነቴ ስሜት
እና እውነቴን ተከትዬ ቀድሜ ማጥቃት አለመቻሌ ነው !!

እስከመቼ የምችለው ቀድሞኝ እያጠቃኝ ይጥለኛል ?? እስከመቼ ነገሮች ከብዙ አቅጣጫ ለማየት ስወናወን ከአንድ አቅጣጫ የሚያይ ይረታኛል ??

ጨካኝን አረመኔ ሳንሆን ፣ ጥቅመኛን ስግብግብነት ሳይጠናወተን ፤ ደደበን ሳንደነቁር እንዴት ማሸነፍ ይቻለናል ??

እስከመቼ መቀደሜ እልህ እና ድብርት ወልዶ መጥመልመሌ ፍቅር ይመስለኛል ??

በጠላትነት የምንቆጥረው ፣ የማንወደው፣ የማይወደን ፣ ከዚ ቀደም የበደለን ፤ ከዚ ቀደም የበደልነው ። ሊበድለን ምቹ ግዜ የሚያመቻች ነው ብለን በዓይነ ቁራኛ የምናየው ቢበድለን ... ህመሙ አጥንታችንን ዘልቆ አይፍቀንም !

አምነን ጥርጣሬያችንን አውልቀን ጥለን ፤ ፍላጎታችን ሰውተን ፣ ቢገፉን የሚገሉን ገደል አፋፍ ላይ ጀርባችን ሰጥተን የመቆም ያህል እምነት የሰጠናቸው ሰዎች ሆን ብለው ሲጨክኑብን የሚያመን ህመም ሰቅጣጭ ነው !!

ጠላቴን እኔው እታገለዋለሁ ወዳጄን ብቻ
አራራልኝ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

የደሱ ግጥሞች

29 Jun, 17:47


"ቀን ሲጨልምብን መኖር ስልችት ሲል
ምናለ አንዳንዴኳ'ን
ሞት በ'ጃችን ስንመርጥ ፈጣሪ ይቅር ቢል

የደሱ ግጥሞች

28 Jun, 08:47


«እኔ ኢትዮጵያውያንን አላምንም ከራሴ ጀምሮ። በጭንብል ተሸፍነን የምንኖር ህዝቦች ነን። ለሰው የምናሳየው ገፅታና እውነተኛው ባህሪያችን የተለያዩ ናቸው። እንደ ተረታችን ፣ ስነ ፅሁፋችንና ንግግራችን ባህርያችንም ሰምና ወርቅ ነው ...

በዚህ ላይ ደግሞ ክፉውና በጎውን ነገር አንዱን ከሌላው ለይተን የምናይበት መለኪያ የለንም ፤ የማንኛውም ነገር መሠረታዊ መለኪያችን የግል ጥቅማችን ነው። ለዚህም ነው ተንኮል የሚበዛው፤ መተማመን የሌለው፤ የወዳጅነት ወይም የጓደኝነት ትርጉሙ የማይታወቀው ፤ ሀሜት አሉባልታና እርስ በዕርስ መበላላት የሚበዛው።

ኢትዮጵያዊያን ስንባል የምናውቀው መርህ አንድ ብቻ ነው ፤ የግል ጥቅም! ከራስ በላይ ነፋስ ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል... ሰውን ማመን ቀብሮ ፥ ይሉታል ከነተረቱ። የሚያሳዝን ነው... ለግል ጥቅማችን የሚበጅ ከሆነ እንዋሻለን። ስንዋሽ ህሊናችንን ቅንጣት ታህል አይቆረቁረንም። እንዴት አድርጎ ለግል ጥቅም የተገዛ ህሊና ሊቆረቁረው ይችላል? ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን ፤ የስጋ ዘመድን አይለይም ቅናት ባህላችን ነው።

ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። በአጠቃላይ ክፉውንና በጎውን ለይቶ የሚያይ ህሊና የለንም፤ ያስተማረንም የለም። የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ይሉ የለም? በአደባባይ ሁሉም ጨዋ፣ ልበ ሙሉ፣ ጀግና፣ አትንኩኝ ባይ፣ ኩሩና ቅን፣ በጎ አሳቢና ታማኝ፣ አስተዋይና ትሁት ነው።

በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው። በግል ኑሮአችን ግን ከስብቅ ፣ ከምቀኝነት ፣ ከተንኮል፣ ከቅናት ፣ ለውሸት፣ ከአሉባልታና ከሀሜት፣ ለግል ጥቅም ለመልከስከስና ለመልፈስፈስ ከፍርሃትና ከአድር ባይነት ርቀን አንገኝም። መለያ ባህርያችን ግብዝነት ነው። የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው። ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!»

በዓሉ ግርማ የቀይ ኮከብ ጥሪ 1972 ዓም ገፅ 234

በፅሑፉ ሃሳብ ትስማማላችሁ?

የደሱ ግጥሞች

27 Jun, 04:22


ምሽት በረንዳ ላይ
(በእውቀቱ ስዩም)

አገር ምድሩ መሽቶ
ሌቱ ምጣድ ሆኖ ፥ በኮከብ ተሟሽቶ
የጎዳናው መብራት ፥ጨለማው ላይ ሲገን
ከመስኮት አምልጦ ፥የወጣ ወጋንን
ሳር ቅጠሉን ሲያሳይ
አጥብቄ ስፈልግ ፥የእለት ያይኔን ሲሳይ
የሌት አይኔን ሲሳይ

በኩርማን ገላዋ፤ እራፊ ደርባ
የራሷ ሻጭ ሆና ፤ለሸመታ ቀርባ
በሌት ይፋ ሆና፥ በቀን ልትደበቅ
ያልቀጠረችውን ፥የምትጠባበቅ
አንዲት ሴት እያየሁ
አሰላስላለሁ ፤

“ አብረዋት ያደጉ፤ ብጤዎቿ ሁሉ
በድሜና በውበት እሷን የሚያክሉ
ተድረው እንደ ሴት፥ ተከብረው እንደ ሰው
የባሎቻቸውን ደረት ተንተርሰው
ፍቅር ሲያጣጥሙ
ወይ በንቅልፍ ሲሰጥሙ
ይች ወገን አልባ
የሌሊት አበባ
በቀትር ተኝታ ለውድቅት የነቃች
የቱን ፍሬ በልታ ለዚህ ፍዳ በቃች ?”

እያልሁ አስባለሁ፥



ደሞ ከደጃፌ ትንሽ ማዶ ርቆ
የመሸበት ለማኝ ፤ መንገዱ ዳር ወድቆ

በግልጥ ይታየኛል
“ ረፍትን ላክልኝ ፥ወይ እንጎቻህን ጣል
በራብ እና በንቅልፍ ሰው እንዴት ይቀጣል"
የሚል ይመስለኛል ፤

በረንዳ ላይ ቆሜ፥ በሌሊት ስምሪት
ከመስኮት በወጣ፥ የብርሀን ቅሪት
አይቼ ማልዘልቀው
ያገሬ ጎዳና የት ላይ ነው የሚያልቀው
መከራና ውበት የሚያፈራርቀው::

የደሱ ግጥሞች

22 Jun, 07:30


👌

አይኑ ተመልክቶ ልቦናው ያልቃኘ
የያዘውን ትቶ ሌላ ያልተመኘ

አካላዊ ወረት ያረገጠው ደጁን
አለወይ ከሰዎች ያልካደ ወዳጁን

ውድ ፍቅረኛውን ልቡ እንዳፈቀረ
በስዋ ተወስኖ ዘላለም የኖረ

እስከ መጨረሻው መንፈሱ ሳይላላ
ከሚወደው በቀር ያልተመኘ ሌላ

ማናት ወይስ ማነው ይህንን የሰራ
በቃሉ የሚገኝ ባአስቀመጡት ስፍራ

ከሴትም ከወንድም ያልተለዋወጠ
ማን ይሆን ወዳጁን በሌላ ያልሸጠ

ተፃፈ💪💪💪💪💪ኩረጃጃ

የደሱ ግጥሞች

13 Jun, 13:52


በዘመን ጠባሳ የደከመ ተስፋ፣
ከሚጨበጥ ጥሪት ላያገኝ ሲለፋ፣
ከመቅፅበት ቢቆቆ ለፀሎት ከአምላኩ፣
እንዴት ሰው ያገኛል ንግስቱን በልኩ።
ተፃፈደሱ(ማነሽ ባለ ግጥሟ)

የደሱ ግጥሞች

08 Jun, 18:27


*የማጋራት ጣዕም*
(በረከት በላይነህ)

ብልህ!
ስንጥቅ ምጣድ ጣደ ፣
ሽንቁር ድስቱን ጣደ ፤
ቅጠሉን ፣
እንጨቱን ፣
ኩበት ...ምናምኑን በእርጥቡ ማገደ ።
.
እንክርዳዱን ፈጨ ፣ ያለእርሾ አቦካ ፤
የነቀዘ ጓያ በሽሮ ስም ከካ ።
.
ዲቃላውን ድንች ፣
ከደረቀው ሽንኩርት ፣
ከወየበው ጎመን ፣
ከሸክላው በርበሬ - ያለጨው ቀየጠው ፤
ከዚያ !
"እንብላ !" ይለናል 'በሰው' ሊያጣፍጠው

የደሱ ግጥሞች

01 Jun, 09:17


ሰው ክቡር እያለ ሹም እንዲህ ሳይበዛ፣
ያኔ ንጉስ ነበርኩ እኔም እንደ ዋዛ!!

የደሱ ግጥሞች

31 May, 04:43


ድምፅሽ ፈውሴ ሊሆን፣
የተስፋዬ ፍሬ በእጆችሽ ሊከወን ፣
ምናለ ከደጅህ
ምናለ ከቤትህ
ብለሽ ሳትጠይቂ ከመረጥሽኝ እኔን፣
መልስ አለኝ ላፈቅርሽ ላወርስሽ ራሴን።
ተፃፈደሱ

የደሱ ግጥሞች

26 May, 16:45


አትጠይቅ (?)

"አትመርምር ፣ አትጠይቅ ፣
ልብህ ቢያስብ እንኳን ፣ ምላስህን ጠብቅ፣
"ዝም በል" የሚሉት ቃል ፦
ተመራምሮ ላየው ፣ ብዙ ያስጠይቃል ።

ሲጀመር ፦
አስተዋይ አዋቂ ፣ ጠያቂ...አዕምሮ፣
ከነፍስ ባህርይ፣ በሥጋ አንጎል ቋጥሮ፣
አምላክ ከፈጠረ
ስለምን ዝም ይበል፣ የተመራመረ ?

ሲቀጥል ፦
ልብ የጠየቀውን ፣ አንደበት አውጥቶ ስላልተናገረ፣
የልብብ ሚያውቅ አምላክ፣ እንዳልተጠየቀ እንዴት ተቆጠረ?

ባጭሩ ፦
የሰነፍ አንደበት ፣ ለመልስ ሲቸግረው፣
መርማሪ አዕምሮን፣ "በአትጠይቅ" አሰረው ።

መላኩ አላምረው

የደሱ ግጥሞች

25 May, 18:53


https://t.me/tapswap_mirror_bot?start=r_1031088718