DSA NEWS Media @dsa_media Channel on Telegram

DSA NEWS Media

@dsa_media


DSA NEWS Media (English)

Welcome to DSA NEWS Media, your go-to source for all things related to data structures and algorithms! Our Telegram channel, @dsa_media, is dedicated to providing the latest news, updates, tutorials, and tips in the world of DSA. Whether you're a student, a professional, or just someone interested in sharpening your coding skills, our channel is the perfect place for you. We cover a wide range of topics, including sorting algorithms, search algorithms, dynamic programming, and much more. Stay informed and stay ahead of the game with DSA NEWS Media! Join our channel today and take your DSA knowledge to the next level.

DSA NEWS Media

14 Feb, 15:28


ውድ ወላጆች
ነገ ቅዳሜ የካቲት 8 ቀን 2017 ዓ.ም
ሁሉም የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች
ለግማሽ ቀን ትምህርት እንዳላቸው
ለማሳወቅ እንወዳለን!!!
ትምህርት ክፍሉ!!!

DSA NEWS Media

07 Feb, 09:10


ቀን 30/05/2017 ዓ።ም። ለዉድ ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ:: በቅድሚያ ያክብሮት ሰላምታችንን እያቀርብን የ2017 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 3/2017 ዓ.ም ይጀምራል፡፡ ስለዚህ ተማሪዎቻችን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እና የትምህርት ቤቱን ዩኒፎርም በመልበስ ወንዶች ጸጉራችሁን በመስተካከል ሴቶችም ተገቢውን ጸጉር አሰራር በመሰራት የመማሪያ ቁሳቁሶቻችሁን (ደብተር መጻሕፍት . . . . .) ይዛችሁ በሰዓታችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን። ትምህርት ክፍሉ

DSA NEWS Media

02 Feb, 15:43


It is Economics Note for Grade 12

DSA NEWS Media

31 Jan, 07:26


ለዉድ ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ::
    በቅድሚያ ያክብሮት ሰላምታችንን እያቀርብን የአንደኛ መንፈቅ ዓመት ትምህርት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እጅግ በጣም ጥሩ እና ጤናማ በሆነ ሂደት በሰላም የተጠናቀቀ መሆኑን እየገለፅን ቀጣይ ያሉ መርሃ-ግብሮችን እንደሚከተለዉ እናሳዉቃልን::
አርብ በቀን 23/05/2017ዓ.ም እስከ6:00 ሰዓት ድረስ ተማሪዎች በአካል በመገኘት የፈተና ወረቀት የሚውስዱበት እና ከ100% ያስመዘገቡትን ዉጤት የሚያቁበት እንዲሁም ከመምህራኞች ጋር የሚናበቡበት ይሆናል:
ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከ2፡30- 5፡00 ድረስ ጥሪ ከተላለፈላቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና ወላጆች ጋር የጋራ ውይይት ይደረጋል፡፡ (በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው ተማሪዎች ከወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው/ ጋር መገኘት አለባቸው)
ከጥር 26 - የካቲት 2/2017ዓ.ም ድረስ ለተማሪዎች የእረፍት ጊዜ ይሆናል::
የካቲት 03/2017ዓም የሁለተኛ- መንፈቅ ዓመት ትምህርት የሚጀምርበት ይሆናል::

DSA NEWS Media

14 Jan, 03:06


ዛሬ በቀን 02/05/2017, ዓ.ም በን/ስ/ላ ክ/ከተማ  ት/ት ጽ/ቤት  ፍሬህይወት ቁ.2 ክላስተር ማዕከል የ12ኛ ክፍል ጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል።
በዚህም መሰረት የድሪም ሰክሰስ ተማሪዎች
1. አቤል አባይነህ እና ጽዮን ተስፋዬ በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስክ በጋራ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ሲያጠናቅቁ በተመሳሳይ ሁኔታ አሜን ዳዊት  እና ሻሎም በሀይሉ በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስክ በጋራ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቃቸው እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ሁሉም የትምህርት ቤቱ አካላት ጥረትና ልፋታችሁ እንዲህ በአደባባይ እንዲወጣ ስላደረጉ ትምህርት ክፍሉ ተማሪዎቻችንን ከልብ ያመሰግናቸዋል። የስኬቱ ባለቤቶች ደግሞ ከላይ ከባለሀብቶቹ ጀምሮ የትምህርት ክፍሉ፣ የመምህራን እንዲሁም የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ጥረት ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ። ይህንን ድል ተማሪዎቻችን በሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት እንደሚደግሙት ሙሉ እምነት አለን።
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ።

DSA NEWS Media

27 Dec, 12:57


ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም
ለ ውድ የድሪም ሳክሰስ ኣካዳሚ ተማሪ ወላጆች
ጉዳዩ- ትምህርት ያላቸውን ክፍሎች ስለማሳወቅ

ነገ ማለትም ታህሳስ 19 ቀን2017 ዓ.ም
የማካካሻ ትምህርት ያላቸው ክፍሎች
9ኛ CD , 11ኛ AB እና 12ኛ ABCD
ብቻ ናቸው።

DSA NEWS Media

18 Oct, 09:45


ቀን 08/02/2017 ዓ.ም.   
ዜና ድሪም ሰክሰስ
የድሪም ሰክሰስ አካዳሚ በ2016 ዓ.ም. ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈትነው ከ 500 በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ተከናውኗል። መርሀ ግብሩ የተማሪዎቹ ወላጆች፣ የትምህርት ቤቱ ባለቤቶች፣አመራሮች፣መምህራን፣  እና ሁሉም ተማሪዎች በተገኙበት የትከናወነ ሲሆን እነዚህ ውጤታማ የሆኑ ተማሪዎች ልምዳቸውን እና ለዚህ ውጤት ያበቃቸውን ተሞክሮ በ 2017 ዓ.ም. ለሚፈተኑ ተማሪዎች አካፍለዋል።

DSA NEWS Media

16 Oct, 13:23


                    ቀን 05/02/2017 ዓ.ም.
በ2017 ዓ.ም. ሀገር አቀፍ(ብሄራዊ) ፈተና የሚፈተኑ የድሪም ሰክሰስ አካዳሚ ተማሪዎች በጎ እድሎች፣ በፈተናው ውጤታማ እንዳይሆኑ ሊያደርጉ የሚችሉ ተግዳሮቶች እና በወላጆች፣ በተማሪዎች፣ በመምህራንና በትምህርት ቤቱ በኩል መሰራት ስለሚገባቸው ስራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅዳሜ ጥቅምት 2  ቀን 2017 ዓ.ም. ውጤታማ የሆነ የጋራ ምክክር ተካሂዷል።
በዚህ ውይይት ላይ በትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህርና ምክትል ርእሰ መምህር አማካይነት የመወያያ መነሻ ሀሳብ ከቀረበ በኋላ ወላጆች፣ ተማሪዎችና መምህራን እንዲወያዩበት ተድርጎ በማጠቃለያው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራም ሆነ በተናጥል የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ  ማሳሰቢያ እና ጥሪ ተላልፏል።

DSA NEWS Media

15 Oct, 16:02


ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን ፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!

2,194

subscribers

584

photos

6

videos