***
በዓሉ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ለ15ኛ "መፀዳጃ ቤትን በንፅህና መያዝና መጠበቅ ዘመናዊነት ነው " " እጃችን ጤናችን " በሚል መሪ ቃል በዓሉ በድምቀት የተከበረ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ባለድራሻ አካላት፣ ሲቪል ማህበራቶችና የተለያዩ የመንግስትና የግል ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሽመልስ ገዛኸኝ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈው ሆስፒታሉ በጽዱ ኢኒሼቲቭ ተግባራት ላይ እያከናወናቸው ያሉትን ስራዎች አብራርተዋል፡፡
በእለቱ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ የተገኙ ሲሆን ጤና ተቋማትን ጽዱ፣ምቹና ማራኪ በማድረግ ጤናማ ማህበረሰብን ለመፍጠር የተሻሻሉና በቂ ውሃ ያላቸው መጸዳጃ ቤቶች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው አጋርነትና ትብብርን በማጠናከር እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ ሲሆን የውሃወለድ በሽታዎችን ለመከላከልና ወጪን ለመቀነስ የሚያስፈልጉ መጸዳጃቤቶችን መገንባትና በንጽህና መያዝ ዘመናዊነት መሆኑን ገልፀዋል፡
በመጨረሻም የእጅ መታጠብና የመፀዳጃቤትን የሚገልፁ ኤግዚቭሽኖችን እና በሆስፒታሉ የተሰሩ ክንውኖችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡