Dilla Don Bosco Catholic Secondary School @dbict Channel on Telegram

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

@dbict


Dilla Don Bosco Catholic Secondary School (English)

Welcome to Dilla Don Bosco Catholic Secondary School Telegram channel, also known as @dbict! Our channel is dedicated to providing students, parents, and the community with updates, news, and information about our school. Dilla Don Bosco Catholic Secondary School is a prestigious educational institution with a long history of excellence in academics, sports, and extracurricular activities. Our channel is the perfect place to stay connected with the latest happenings at our school. From announcements about upcoming events to important reminders for students and parents, @dbict has you covered. Join our channel today to be a part of our vibrant school community and never miss out on any important information. We look forward to welcoming you to the Dilla Don Bosco Catholic Secondary School family!

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

06 Jan, 17:35


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የትምህርት ቤታችን መምህራን፣ተማሪዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!


በአሉ የሰላም ፣የመተሳሰብ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንልን እንመኛለን።

መልካም በዓል

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

05 Jan, 07:56


የ2017 ዓ.ም ፈተናዎች ይዘትን በተመለከተ ባስተላለፈው መልዕክት፤ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ 9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ገልጿል።

ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው ሊዘጋጁ እንደሚገባ አገልግሎቱ ጠቁሟል።

#tikvahuniversity

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

02 Jan, 10:04


#ለተደረገልን_ድጋፍ_እናመሰግናለን

በዋለሜ ዶን ቦስኮ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የተማሩት አንደኛ ኑሮውን እና ስራውን በአሜሪካ ያደረገው የቀድሞ ተማሪያችን #ተሻለ_ቢዘልቅ እና ሁለተኛ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ውጤታማ የሆነው የቀድሞ ተማሪያችን #ዮሴፍ_አለሙ በ2016 ዓ.ም የቀድሞ የት/ቤቶቻችን ተማሪዎች ለት/ቤታቸው ድጋፍ እንዲያደርጉ በዚሁ ፌስቡክ ገፃችን ጥሪ በተላለፈው መሰረት በትምህርታቸው ጎበዝ ሆነው አመታዊ የትምህርት ቤት ክፍያ ለመክፈል ለተቸገሩ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ ሁለት እንዲሁም ከአምስት እስከ ስምንትኛ ክፍል ላሉ ሁለት ተማሪዎች በድምሩ #ለአራት ተማሪዎች 16,300 (#አስራ_ስድስት_ሺህ_ሶስት_መቶ) ብር ወጪ በማድረግ አመታዊ የትምህርት ክፍያ ድጋፍ አድርገዋል።

እነዚሁ ተማሪዎች ባለፈው አመትም ለዚሁ ት/ቤት 52 በአዲሱ ካሪኩለም የተዘጋጁ መፃህፍትን መለገሳቸው ይታወሳል።

ይህን ድጋፍ በዛሬው እለት በት/ቤቱ በመገኘት ለት/ቤቱ አስተዳደር ድጋፉን አስረክቤያለሁ።

ለተደረገላቸው ድጋፍ የት/ቤቱ ም/ር/መምህር #መምህር_ታምራት በተማሪዎቹ ስም #ከልብ_አመስግነዋል።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

30 Dec, 15:30


ጥቆማ፦
አዲስ ኮደር ለክረምት ከ9–11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ፓይተን ፕሮግራሚንግ ኮርስ በነፃ ለ1 ወር ለመስጠት ምዝገባ ጀምሮ ነገ ይጠናቀቃል።

ስለሆነም ወላጆች ልጆቻችሁን አስመዝግቡ። በዚህ ሊንክ አፕላይ አድርጉ። https://apply.addiscoder.com/apply/
አፕላይ ለማድረግ ለምን እንደፈለጋችሁት የሚገልፅ አጭር ማመልከቻ እና የትራንስክሪፕት የ2 ቅርብ አመታት ኮፒ ማያያዝ አለባችሁ። ቀጥታ ት/ቤቱ ትራንስክሪፕታችሁን መላክ ከፈለገ ይህን ኢሜይል ይጠቀም። [email protected]
የ2 ቅርብ አመታት ትራንስክሪፕት ማለት፤ ለምሳሌ፦ የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነ አመልካች የ9 እና 10ኛ ክፍልን ትራንስክሪፕት ያያይዛል።

አሰልጣኝ መሆን የምትፈልጉም ፓይተን ፕሮግራሚንግ የምትችሉ ከሆነ እስከ ነገ በዚህ ሊንክ አመልክቱ። https://apply.addiscoder.com/ta-apply/

በየአመቱ የተወሰኑ ጎበዝ የሃይስኩል ልጆችን መርጦ ወደ MiT፣ Harvard፣ Stanford፣ Berkeley… ዩኒቨርስቲዎች ስኮላርሺፕ እንዲያገኙ ያደርጋል። የአዲስ ኮደር መስራቹ ፕሮፌሰር ጀይላኒ ጥሩ ነው። ሶሊድ የሆነ አካዳሚክ ዕውቀት አለው። አልጎሪዝምን ያውቀዋል በጥሩ!
ከ8 አመት በፊት ይህን የሃርቫርድ ሌክቸሩን እዩት።
https://youtu.be/0JUN9aDxVmI?si=uPybqWQgeL3wfG6F

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

30 Dec, 11:46


የዲላ ዩኒቨርስቲ ማ.ሆ የስርዓተ ፆታ ማስተባበሪያ ቢሮ ለ12ኛ ክፍል ሴት ተማሪዎች ስለ ስርዓተ ፆታ ስልጠና ሰጠ።

ዲላ፣ ታህሳስ 21፣ 2017 (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)

የት/ምህርት ቤታችን የሴቶች ክበብ እና ኢኮቴ ማዕከል ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የስርዓተ ፆታ ማስተባበርያ ቢሮ ጋር በመተባበር ለት/ቤታችን 12ኛ ክፍል ሴት ተማሪዎች እና ለክበቡ አባላት የስርዓተ ፆታ ስልጠና በዛሬው እለት ሰጥቷል።

ስልጠናውን የሰጡት የቀድሞ የት/ቤታችን ተማሪ
የነበረችው እና በአሁን ሰዓት የስርዓተ ፆታ ቢሮ ኃላፊ #ሜሮን_ተረፈ እንዲሁም ረ/ፕሮፌሰር ሞገስ የዲላ ዩኒቨርሰቲ ማስተማርያ ሆስፒታል የስነ ተዋልዶ ጤና መምህር እና ተመራማሪ ናቸው።

በስልጠናው ስለ ስነ ተዋልዶ እና ተጓዳኝ ጉዳዮች ሰፊ ገለፃ ተሰጧቸዋል።

የክበብ አስተባባሪ መምህርት አበቡ ለተሰጠው ስልጠና የሆስፒታሉ ፕሬዝዳንት የሆኑት የቀድሞ ተማሪያችን አቶ #ትዝለኝ_ተስፉዬ እና ባለሙያዎቹን ከልብ አመስግናለች።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል።

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

27 Dec, 13:02


#እንድታውቁት

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በበየነ መረብ (ኦንላይን) መመዝገብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበት አድራሻ https://register.eaes.et/Online እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የበይነ መረብ (አንላይን) ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self services ) ሲሆን ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከል ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

(እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል ከላይ ይመልከቱ)

(የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

@tikvahethiopia

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

26 Dec, 16:02


የጥንቃቄ መልዕክት

ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ስለሆነ ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከምታውቁት እና ከማታውቁት ) ግለሰብ ሊንክ ቢላክላችሁ መክፈት እንደሌለባችሁ እና ወዲያውኑ እንድታጠፉት እናሳስባለን!!

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

19 Dec, 15:51


የቀድሞ የት/ቤታችን ተማሪ የነበረው #ብሩክ_መኮንን #ለቦስኮ_ኮዲንግ_ክበብ አባላት በቨርቹዎል ገለፃ ሰጠ።

ዲላ፣ ታህሳስ 10፣ 2017 (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)

ከመዋለ ህፃናት ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርቱን በት/ቤቶቻች የተከታተለው እና በ2010 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀው የቀድሞ ተማሪያችን በዛሬው እለት በ2016 ዓ.ም ለተቋቋመው #የቦስኮ_ኮዲንግ_ክበብ አባላት ስለ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ቆይታው ፣ በአሁን ሰዓት በኃላፊነት ስለሚሰራበት A2SV (African to Silicon Valley) ድርጅት እንዲሁም የክበቡ አባላት በየትኞቹ የቴክኖሎጂ ሴክተሮች ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው መማር ስላለባቸው የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ሰፊ ገለፃ ሰጥቷል።

#ብሩክ_መኮንን በA2SV (Africa to Silicon Valley) ውስጥ የትምህርት አካዳሚ ምክትል ኃላፊ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ።

ከክበቡ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችም ማብራሪያ ሰጥቷል።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

13 Dec, 16:42


ማስታወቂያ

ለ2017 12ኛ ክፍል ተማሪዎች

በማህበራዊ ድህረ ገፅ እየተዘዋወረ ያለው የIT እና Agriculture ትምህርቶች በብሔራዊ ፈተና ተካቶል የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አሳውቃለሁ።

ለሁለት ቀናት የ2017 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን ምዝገባ ስልጠና ከወሰድን በኋላ በምዝገባው ድህረ ገፅ ላይ መከታተል በተቻለው መሰረት ከላይ የተጠቀሱት የትምህርት አይነቶች በዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም።

ስለሆነም ከነዚህ አሳሳች መረጃዎች እራሳችሁን በማራቅ ጥናታችሁ ላይ ትኩረት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በኦንላይን መመዝገብ ስለምንጀምር ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እንገልፃለን።

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

12 Dec, 12:39


የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስተር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራው ልዑካን የት/ቤታችንን የቴክኖሎጂ ማዕከላት ጎበኙ።

ዲላ፣ ታህሳስ 3፣ 2017 (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)

በት/ቤታችን ለረጅም ጊዚያት አገልግሎት ሲስጥ የቆየው ኢኮቴ ማዕከል እና የት/ቤታችን አስተዳደር ከካማራ ኤዱኬሽን ኢትዮጵያ እና ዴል ቴክኖሎጂ ትብብር በ2015 ዓ.ም የተቋቋመው የኤሌክትሮኒክ መማሪያ ማዕከል በልኡካኑ ተጎብኝቷል።

ከ2013 ዓ.ም በራስ ተነሳሽነት ስለ ጀመርኩት የኮዲንግ ለህፃናት ስልጠና ሰፊ ገለፃ ሰጥቻለሁ። በዚህም በአሁን ሰዓት እንደ ሀገር የተጀመረው የ5ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና ትምህርት ቤታችን ቀደም ብሎ መጀመሩ የሚደነቅ እና የሚበረታታ መሆኑን ክብርት ሚኒስትሯ እና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ገልፀዋል።

በ2022 በአፍሪካ ደረጃ በተደረገው የኮዲንግ ቻሌጅ ውድድር በኢትዮጵያ አሸናፊ የነበረችው ተማሪ መልካም አስራት ከሁለት አመት በፊት የህፃናት የኮዲንግ ስልጠና ከተከታተለች በኋላ የሰራችውን በጌዴኡፋ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ አፕሊኬሽን ለእንግዶች አቅርባ ከፍተኛ አድናቆት ተችሯታል።

የዞኑ አስተዳደር ስራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት አንንዲችል ሙሉ ወጪውን አስተዳደሩ እንደሚሸፍኑ ቃል ገብተዋል።

ይህ ጉብኝት እንዲሳከ ለተባበሩን የዞኑ እና ከተማ አስተዳደሩ የሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ከልብ እናመሰግናለን።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቤታችንን የማህበራዊ ድህረ ገፆች ይጠቀሙ:

#ፌስቡክ:
https://m.facebook.com/groups/715959666071910/?ref=share&mibextid=NSMWBT

#ቴሌግራም:
https://t.me/dbict

#ዩቱብ:
https://www.youtube.com/@DBICTC

#ኢሜል:
[email protected]

#ቴሌግራም_ቦት

@DonBHS_bot

#ዋትስ_አፕ
https://whatsapp.com/channel/0029Vaa2AUE6buMFIk04MO29

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

25 Nov, 07:22


የ2017 ዓ.ም የሚድ ተርም እና የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያው ሞዴል ፈተና ተጀመረ።

ዲላ፣ ህዳር 16፣ 2017 (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ) የት/ቤታችን የ2017 ዓ.ም ከ9-11ኛ ክፍል የሚድ ተርም እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በዛሬው እለት ተጀምሯል።

በጠዋቱ መርሀ ግብር 10ኛ እና 12ኛ ክፍል እንዲሁም በከሰዓቱ መርሀ ግብር 9ኛ እና 11ኛ ክፍሎች ይፈተናሉ። የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ሲባል በ14 ክፍሎች እስከ 25 ተማሪዎች ብቻ ተደልድለው ይፈተናሉ።

ፈተናው ለተከታታይ አምስት ቀናት ይሰጣል። በዘንድው አመት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በ12 ክፍሎች 291 ወንዶች 333 ሴቶች በድምሩ 624 ተማሪዎች በት/ቤቱ ውስጥ ይማራሉ።

እንደሚታወሰው በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል #በኦንላይን ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት 163 ተማሪዎች 159 ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ የገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 95 ተማሪዎች ከ50% በላይ ያመጡ ናቸው። በዞን እና ከተማ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በት/ቤታችን ተማሪ የሆነው #በተማሪ_ልደቱ_ወንይፍራው ነበር። ውጤቱም 542/600 (አምስት መቶ አርባ ሁለት ከስድስት መቶ ነው)
የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቤታችንን የማህበራዊ ድህረ ገፆች ይጠቀሙ:

#ፌስቡክ:
https://m.facebook.com/groups/715959666071910/?ref=share&mibextid=NSMWBT

#ቴሌግራም:
https://t.me/dbict

#ዩቱብ:
https://www.youtube.com/@DBICTC

#ኢሜል:
[email protected]

#ቴሌግራም_ቦት

@DonBHS_bot

#ዋትስ_አፕ
https://whatsapp.com/channel/0029Vaa2AUE6buMFIk04MO29

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

23 Nov, 15:53


#ማስታወቂያ
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግል መደበኛ ኘሮግራም (Private regular) መማር የሚፈልጉ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የቀረቡ መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች ከቀን 16-27/03/17 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርስቲ ዋናው ሬጂስትራር በአካል ቀርባችሁ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

23 Nov, 08:31


የ6ኛው ዙር የኮዲንግ፣ፓይተን እና ድረ ገፅ ስልጠና ለህፃናት ተጀመረ።

ዲላ፣ ህዳር 14፣ 2017 (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ) በዲላ ዶን ቦስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢኮቴ ማዕከል ላለፉት አራት አመታት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና የ2017 ዓ.ም 6ኛ ዙር በዛሬው እለት ተጀምሯል።

በዲላ ከተማ ውስጥ ካሉ ት/ቤቶች የተውጣጡ 60 የክፍል ደረጃቸው ከ7ኛ-10 ያሉ ተማሪዎች ለስልጠናው ተመዝግበው ስልጠናቸውን ጀምረዋል።

ስልጠናው አምስት ወራት የሚፈጅ ሲሆን ዘወትር ቅዳሜ ከ2:00 እስከ 5:00 ሰዓት ይቆያል።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ለሰልጣኞች ሰርተፍኬት እና ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ የማበረታቻ ሽልማት እንዲሁም በ2018 ዓ.ም #የቦስኮ_ኮዲንግ_ክበብ አባላት ይሆናሉ። በተጨማሪም በተለያዩ የኮዲንግ እና ድረ ገፅ ውድድሮች ት/ቤታችንን በመወከል ይወዳደራሉ።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

22 Nov, 13:27


የቀድሞ የትምህርት ቤታችን ተማሪ የነበረው #ዶክተር_ሙሉአለም_ተኩ ትምህርት ቤታችንን ጎበኘ።

ዲላ፣ ህዳር 13፣ 2017 (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)
ዶ/ር ሙሉአለም ተኩ የዶክተሬት ዲግሪውን ከታዋቂው የህንድ ዩኒቨርስቲ በኮምፒውተር ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ አግኝቷል። ለረጅም አመታት በህንድ ዩኒቨርስቲዎች ሲያስተምር የቆየ ሲሆን በአሁን ሰዓት ወደ ትውልድ ሀገሩ በመምጣት በመረጃ መረብ ደህንነት( #INSA) በከፍተኛ የስራ ዘርፍ እያገለገለ ይገኛል።

በዲላ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት እየተከበረ ላለው 6ኛው የሳይንስ ሳምንት ከተጋበዙት እንግዶች አንዱ ነበር።
በፕሮግራሙም ላይ ስለ ሳይበር ሴኩሪቴ ገለፃ አድርጓል።

ባደረኩለት ግብዣ የቀድሞ ት/ቤቶቹን ( መስቀለ እየሱስ 1ኛ ደረጃ እና ዶን ቦስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶቹን)
ጎብኝቷል።

በዶን ቦስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ያሉትን ሁለቱን የኮምፒውተር ላብ እና ኤሌክትሮኒክስ ማስተማሪያ ማዕከላትን የጎበኘ ሲሆን ለተማሪዎች ስለሚሰጡት ስልጠናዎች ስለ አዲሱ #ቦስኮ_ኮዲንግ_ክበብ ፣ ስለ ህፃናት ኮዲንግ ስልጠና እና በየጊዜው በተማሪዎች የተሰሩ ስራዎች ሰፊ ገለፃ ተሰጥቶታል።

ዶ.ር ሙሉአለም ስለተደረገለት ገለፃ እንዲሁም ስለማዕከላቱ አደረጃጀት እና በተማሪዎቹ ስራ እጅግ እንደ ተደነቀ ገልፆል።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቤታችንን የማህበራዊ ድህረ ገፆች ይጠቀሙ:

#ፌስቡክ:
https://m.facebook.com/groups/715959666071910/?ref=share&mibextid=NSMWBT

#ቴሌግራም:
https://t.me/dbict

#ዩቱብ:
https://www.youtube.com/@DBICTC

#ኢሜል:
[email protected]

#ቴሌግራም_ቦት

@DonBHS_bot

#ዋትስ_አፕ
https://whatsapp.com/channel/0029Vaa2AUE6buMFIk04MO29

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

12 Nov, 10:34


#ለተደረገልን_ድጋፍ_እናመሰግናለን

በ2016 ዓ.ም ከቀድሞ ተማሪዎቻችን እንዳሻው ቾንቤ እና ሰውነት ታሪኩ ጋር በመሆን የመፀሐፍት ልገሳ አድርጎልናል #አዲሱ_ኪዳኔ።

በ20017 ዓ.ም ደግሞ በመምህርት አበቡ አስተባባሪነት በት/ቤታችን የተለያዩ ስራዎችን ለሚሰራው #የሴቶች_ክበብ አንድ ካርቶን የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጓል።

በት/ቤቱ ማህበረሰብ ስም ለተደረገልን ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

11 Nov, 15:01


#እናስተዋውቃችሁ

ተማሪዎች በየትምህርት ቤቶቻቸው ከመደበኛ ትምህርት ጎን ለጎን በተለያዩ ተጓዳኝ ትምህርት ክበባት እንደፍላጎታቸውና ዝንባሌያቸው ይሳተፋሉ፡፡

ክበባቱም የክፍል ውስጥ ትምህት ከተግባር ጋር ለማቀናጀት በመድረክነት ከማገልገላቸውም በላይ ተማሪዎች #የሀብረት ስራን እንዲማሩ፣ #የአመራር ጥበብን እንዲቀስሙ፣#ራሳቸውን በብቃት ለመግለጽ እንዲችሉ፣#ከአከባቢያቸው ጋር ያላቸውን ቁርኝት እንዲያጠናክሩና #የአስተሳሰብ አድማሳቸውን እንዲያሰፉ ይረዳቻዋል፡፡

ይህንን ተሃሳቢ በማድረግ በዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በየአመቱ የተለያዩ ክበባት ይንቀሳቀሳሉ።

እነዚህም ክበባት
1. የበጎ አድራጎት
2. አይ.ሲ.ቲ
3. ኮዲንግ
4. ሚኒ ሚዲያ
5. ስፖርት
6. ሴቶች
7.ስነ ዜጋ እና ስነ ምግባር
8. የደም ጠብታ
9. ሳይንስና ቴክኖሎጃ

ናቸው።

የክበባት አስተባባሪ መምህራንም ከዋናው የማስተማር ስራቸው ጎን ለጎን ከተማሪዎች ጋር የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ።

የነዚህ ክበባት አባል የነበራችሁ ቀድሞ ተማሪዎቻችን እና አሁንም በክበባቱ እየሰራችሁ ያላችሁ ክባቱ ለናንተ ምን ጠቀሟችሁ? የየትኞቹ ክበባት አባል ነበራችሁ?
ሃሳባችሁን አካፍሉን

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

10 Nov, 07:47


#አስደሳች_ዜና
ለኮምፒውተር ኮዲንግ እና ደረገፅ ግንባታ ስልጠና ፈላጊዎች።

ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት አራት አመታት ተማሪዎችን በማሰልጠን እና በተለያዩ የኮዲንግ ቻሌንጅ ውድድር ሰልጣኞቹ እንዲያሸንፉ ያደረገው የት/ቤቱ ኢ.ኮ.ቴ ማዕከሉ በ6ኛው ዙር የክፍል ደረጃቸው ከ7ኛ እስከ 10ኛ ክፍል የሆኑ ተማሪዎችን ለማሰልጠን ይፈልጋል።

ረጅም አመት የማስተማር ልምድ ባለው መምህር እና በተደራጁ ሁለት የኮምፒውተር ማዕከላት ስልጠናው ይሰጣል።

ስልጠናውን ለመከታተል ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች ከህዳር 2-6 /2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ አስተዳደር እየመጣችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።

ስልጠናው ቅዳሜ ህዳር 14/2017 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ሰዓት ይጀምራል።

የሚኖረን ቦታ ውስን ስለሚሆን ፈጥነው ይመዝገቡ

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢ.ኮ.ቴ ማዕከል።

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

08 Nov, 14:00


#ቃል_በተግባር

በ2016 ዓ.ም የተጀመረው የቀድሞ የት/ቤታችን ተማሪዎች ለትምህርት ቤታቸው ድጋፍ የማድረግ መርሀ ግብር በዘንድሮ አመትም ቀጥሏል።

ከሶስት ሳምንት በፊት በት/ቤታችን በመገኘት ለተማሪዎች መልእክት ያስተላለፈው እና የት/ቤት ክፍያ ለመክፈል የአቅም ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎች ክፍያ ለመክፈል ቃል የገባው የትምህርት ቤታችን ብርቅዬ ተማሪ የነበረው #ካፒቴን_ጥበቡ_ጤና ቃሉን በማክበር በእሱ እና ቤተሰቡ ስም በት/ቤታችን #የበጎ_አድራጎት_ክበብ ለተመረጡ አራት ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የአመት ሙሉ ክፍያ 28,000 / #ሃያ_ስምንት_ሽህ/ ብር ክፍያ ፈፅሟል።

ላደረገልን ከፍተኛ ድጋፍ በተማሪዎቹ ስም #ከልብ #እናመሰግናለን።

ከዚህ በፊት አንድ የቀድሞ ተማሪያችንም ለአንድ የ11ኛ ክፍል ተማሪ 7,500 (#ሰባት_ሺ_አምስት_መቶ/ የአመት ሙሉ የትምህርት ቤት ክፍያ ፣ 4 የማጣቀሻ #መፃህፍት እና #ሳይንትፊክ_ካልኩሌተር ገዝቶ ሰጥቶታል።

ለተደረገልን ድጋፍ በድጋሚ ከልብ እናመሰግናለን።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በት/ቤቶቻችን እያየን ያለው ነገር ካለው ከፍተኛ የኑሮ ጫና አንፃር የት/ቤት ክፍያ፣ዩኒፎርም እና የመማሪያ ቁሳቁስ ማሟላት አቅቷቸው ወደ ት/ቤት የማይመጡ ወይም ወደ ሌላ ት/ቤት የሚሄዱ ተማሪዎች እየተበራከቱ መጥተዋል።

ይህን ችግር በተወሰነ መልኩ ለመቅረፍ አቅሙ እና ፍላጎቱ ያላችሁ የቀድሞ ተማሪዎቻችን፣ወላጆች እና ሌሎች ሰዎች ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፉለን።

"ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው" እንደሚባለው እንተባበር እና ተማሪዎቻችንን ወደ ት/ቤታቸው እንመልሳቸው።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል እና የበጎ አድራጎት ክበብ።

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

06 Nov, 11:57


An old man meets a young man who asks:

“Do you remember me?”
And the old man says no. Then the young man tells him he was his student, And the teacher asks:

“What do you do, what do you do in life?”
The young man answers:
“Well, I became a teacher.”
“ah, how good, like me?” Asks the old man.

“Well, yes. In fact, I became a teacher because you inspired me to be like you.”
The old man, curious, asks the young man at what time he decided to become a teacher. And the young man tells him the following story:

“One day, a friend of mine, also a student, came in with a nice new watch, and I decided I wanted it.
I stole it, I took it out of his pocket.

Shortly after, my friend noticed the his watch was missing and immediately complained to our teacher, who was you.

Then you addressed the class saying, ‘This student's watch was stolen during classes today. Whoever stole it, please return it.’

I didn't give it back because I didn't want to.
You closed the door and told us all to stand up and form a circle.

You were going to search our pockets one by one until the watch was found.
However, you told us to close our eyes, because you would only look for his watch if we all had our eyes closed.

We did as instructed.
You went from pocket to pocket, and when you went through my pocket, you found the watch and took it. You kept searching everyone's pockets, and when you were done you said ‘open your eyes. We have the watch.’

You didn't tell on me and you never mentioned the episode. You never said who stole the watch either. That day you saved my dignity forever. It was the most shameful day of my life.

But this is also the day I decided not to become a thief, a bad person, etc. You never said anything, nor did you even scold me or take me aside to give me a moral lesson.
I received your message clearly.
Thanks to you, I understood what a real educator needs to do.

Do you remember this episode, professor?
The old professor answered, ‘Yes, I remember the situation with the stolen watch, which I was looking for in everyone’s pocket. I didn't remember you, because I also closed my eyes while looking.’

This is the essence of teaching:
If to correct you must humiliate; you don't know how to teach.”
Keep following _ Learn English With Majeed Baniyan

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

05 Nov, 10:18


የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ ላደረገው ድጋፍ ተመሰገነ።

በ2016 ዓ.ም የት/ቤታችን 12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የነበረችው #ተማሪ_ልእልና_አሰፉ ለከፍተኛ ህክምና ወደ ውጪ ሄዳ ለመታከም የሚያስፈልግ ገንዘብ በት/ቤታችን #የበጎ_አድራጎት_ክበብ አስተባባሪነት ከት/ቤቱ ማህበረሰብ እና ሌሎች ሰዎች ከ200,000 ብር በላይ በማሰባሰብ ለወላጆቿ መሰጠቱ ይታወሳል።

ተማሪያችን ልእልናም በውጪ ህክምናዋን ተከታትላ ጨርሳ ወደ ሃገሯ ተመልሳለች።

ወላጅ አባቷ #አቶ_አሰፉ በዛሬው እለት በት/ቤቶቻችን በመገኘት በፀሎት እና በገንዘብ ለደገፎቸው ሁሉ ከልብ አመስግነዋል።

የትምህርት ቤታችን ር/መምህር #ወንድም_አስመሮ ባስተላለፈው መልዕክት በተደረገው ፀሎት እና የገንዘብ ድጋፍ ተማሪዋ ከህመሞ መፈወሷ መልካም ዜና እንደሆነ እና በቀጣይ ወደ ትምህርቷ እንድትመለስ ት/ቤቱ አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ገልጿል።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቤታችንን የማህበራዊ ድህረ ገፆች ይጠቀሙ:

#ፌስቡክ:
https://m.facebook.com/groups/715959666071910/?ref=share&mibextid=NSMWBT

#ቴሌግራም:
https://t.me/dbict

#ዩቱብ:
https://www.youtube.com/@DBICTC

#ኢሜል:
[email protected]

#ቴሌግራም_ቦት

@DonBHS_bot

#ዋትስ_አፕ
https://whatsapp.com/channel/0029Vaa2AUE6buMFIk04MO29

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

04 Nov, 16:00


Don Bosco Catolic Secondary School-Dilla             
List of Students who Passed the 2017 E.C Coding Club Entrance Exam             
             
No  Name  Grade  Section       
1  Abel Tesema  9  C       
2  Etsub rarekegn  11  B       
3  Ezedin Hulle  10  A       
4  Fenet Merga  10  B       
5  Fraol Abreham  10  C       
6  Getinet Eshete  10  B       
7  Israel haile  10  C       
8  Kenean Antenbye  11  A       
9  Kidist Workayehu  11  A       
10  Kidus Tekalign  10  A       
11  Kirubel Hailu  10  C       
12  Koket Girma  11  B       
13  Mastewal Asrat  10  B       
14  Melkam Asrat  11  B       
15  Melkamu Mezgabu  11  B       
16  Mercy Habtamu  10  A       
17  Mesay Fikadu  11  A       
18  Naomi Mekonnen  9  C       
19  #Mintesenot Mesfin  11  B       
20  Nuhamin Ayele  10  C       
21  Saron Avrahalign  10  B       
22  Sudeys Muhaba  10  A       
23  Yearsema Tesfaye  11  A       
24  Yigebawal Abrham  9  C

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

02 Nov, 16:59


ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በአምስት ዙር 200 ተማሪዎችን #በኮዲንግ_ለህፃናት መርሀ ግብር በግል ተነሳሽነት መሰረታዊ የኮዲንግ ስልጠና በዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መስጠቴ ይታወቃል።

ሰልጣኞቹን እና ሌሎች ተማሪዎችን በቅርበት ሆኖ ድጋፍ ለመስጠት እንዲሁም ለቴክኖሎጂ የትምህርት መስኮች ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች ለመርዳት በማሰብ #የኮዲንግ_ክበብ በሐምሌ 8/ 2016 ዓ.ም በት/ቤታችን ተቋቁሟል ።

በ2017 ዓ.ም በት/ቤቱ ውስጥ እየተማሩ ላሉ 9ኛ፣10ኛ እና 11ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች በመመዝገብ ቅዳሜ ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና ተሰጥቷቸዋል። በክበብ ውስጥ ላለው 24 ቦታ ወደ 100 ተማሪዎች የተመዘግበዋል።

በሚቀጥለው ሳምንት በመግቢያ ፈተናው የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን በመግለፅ የክበቡ የመጀመሪያውን ስብሰባ እናደርጋለን።

ኮዲንግ ክበብ

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

31 Oct, 08:55


ኮዲንግ እና የመረጃ ትንተናን ጨምሮ በርቀት ስራዎች ለ26 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል።
================
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጠት ማብራርያ የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ በተያዘው በጀት ዓመት ለ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ 700 ሺህ ለሚሆኑት የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ለመፍጠር እቅድ የትያዘ እቅድ ነው ብለዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ባለፉት ሶስት ወራት ለሰለጠኑ ለ100 ሺህ ዜጎች በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

በኦንላይን ስራ ፣ ኮዲንግ ፣የሶፍትዌር ልማትን እና የመረጃ ትንተናን ጨምር 26 ሺህ ዜጎች በሀገር ውስጥ ሆነው ለተለያዩ ሀገራት ድርጅቶች የመስራት እድል ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል።

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

30 Oct, 10:12


👉ተማሪዎች ቢያንስ ሶስት ቋንቋዎችን እንዲማሩ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

👉እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ያሉ ተማሪዎችን በደረጃ ማስቀመጥንም ረቂቅ አዋጁ ይከለክላል


ኢትዮጵያ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን ለማሻሻል ያለመ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅታለች፡፡ ይህ ረቂ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ በትናንትናው ዕለት ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም ይህን ረቂቅ አዋጅ ተጨማሪ ውይይቶች እና ሌሎች ግብዓቶች እንዲታከሉበት በሚል ለዝርዝር እይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

ይህ ረቂቅ አዋጅ እንደሚለው ከሆነ ተማሪዎች ስለ ሚማሯቸው ቋንቋዎች፣ ስርዓት ትምህርት ዝግጅት፣ መምህራን ቅጥር፣ ተማሪዎች ምዘና፣ ትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ መንገዶች እና ሌሎችንም ጉዳዮች ይዟል፡፡
ቋንቋዎችን አስመልክቶ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተቀመጠው የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሚሰጥ ሆኖ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት መሰጠቱ የሚያበቃበትን የክፍል ደረጃ ክልሎች ይወስናሉ ብሏል፡፡

እንዲሁም የእንግሊዘኛ ቋንቋን በማስተማሪያነት በግዴታ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ማስተማር ግዴታ ነው የተባለ ሲሆን ክልሎች ግን ከዚያ በፊትም የማስተማሪያ ቋንቋ ማድረግ ከፈለጉ ይችላሉ ተብሏል፡፡
ተማሪዎች ቢያንስ ሶስት ቋንቋዎችን እንዲማሩ ይደረጋል የተባለ ሲሆን የአፈጻጸም መመሪያ በቀጣይ እንደሚወጣም ረቂቅ አዋጁ ያትታል፡፡
እንዲሁም አንድ ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ቋንቋ ከፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች መካከል የተማሪን አልያም የወላጅን ምርጫ ታሳቢ በማድረግ ከ3ኛ-10ኛ ክፍል ድረስ እንዲማሩ ይደረጋልም ተብሏል፡፡
በአጠቃላይ አንድ ተጨማሪ የውጭ ቋንቋ ክልሎች በሚመርጡት መሰረት ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በአማራጭነት ይሰጣል የተባለ ሲሆን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ደግሞ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

የተማሪዎች ምዘናን በሚመለከት ደግሞ እስከ 1ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የሚባለው እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ተማሪዎችን በደረጃ ማስቀመጥን ይከለክላል፡፡
ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወርን በሚመለከት ደግሞ በሁሉም የትምህርት እርከኖች ከክፍል ወደ ክፍል ማለፍ የሚቻለው ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት አይነቶች 50 ከመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ሲያመጡ ብቻ ነውም ተብሏል፡፡
ክልላዊ ፈተናዎችን ማለፍ ያልቻሉ ተፈታኞች ከሁለት ጊዜ በላይ በነጻ ፈተና ላይ መቀመጥ አይችሉም የተባለ ሲሆን ተፈታኞች በግላቸው እንዲፈተኑ ይደረጋል ይላል ረቂቅ አዋጁ፡፡

በዚሁ ረቂቅ አዋጅ ላይም የመምህራንን ትምህርት እና ስልጠና ጉዳዮችን በሚዘረዝርበት አንቀጽ ስር ሴቶች ለመምህርነት ስልጠና በሚወዳደሩበት ጊዜ ለምልመላ የሚያስፈልጉትን አጥጋቢ መስፈርት አሟልተው በውድድር ወቅት ከወንዶች ጋር እኩል ነጥብ በሚያገኙበት ወቅት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ደንግጓል፡፡
እንዲሁም አንድ መምህር በስራ ላይ እያለ በመንግስት ወጪ ደረጃውን የሚሻሽል ስልጠና ከወሰደ ለእያንዳንዱ የስልጠና ዓመት አንድ ዓመት በሙያው ማገልግል አለበት ሲልም ግዴታ ተጥሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ወሲባዊ ጥቃትን የሚመለከቱ ወንጀሎች መፈጸሙ ተረጋግጦ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መሆኑ የተረጋገጠበት ሰው በማንኛውም የትምህርት ተቋም ውስጥ በመምህርነት እንዳይቀጠር አግዷል፡፡
አንድ መምህር የሙያ ፈቃዱን በየሁለት ዓመቱ ከክፍያ ነጻ በሆነ መንገድ ማሳደስ እንዳለበት የደነገገ ሲሆን የስራ ፈቃድ ለማግኘት ከምረቃ በኋላ የ2 ዓመት ልዩ የመምራን ሙያ ስልጠናን መውሰድ እንዳለበትም በረቂ አዋጁ ለይ ተደንግጓል፡፡
የግል ትምህርት ቤትን ማቋቋም ስለ ሚከለከልበት ሁኔታ በሚያትተው አንቀጽ ስር በፍርድ ቤት የመክሰር ውሳኔ የተሰጠበት ወይም እዳ መክፈል ያልቻለ ሰው፣ ትምህርት ቤቱን ለማቋቋም ፈቃድ ከሚጠይቀው አመልካች ውስጥ ድርሻ ያለው ሰው በወሲባዊ ወንጀል አልያም በህጻናት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆናቸው በፍርድ ቤት የተወሰበት ሰው ፈቃድ ማግኘት አይችልም ብሏል፡፡
በመጨረሻም መንግስት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ትምህርትን በብቃት እና በጥራት ለማዳረስ ያለበትን ግዴታ ለመወጣት ሀገር አቀፍ የትምህርት ፈንድ እንዲቋቋም አዋጁ ይፈቅዳል ይላል፡፡


#MOE

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

28 Oct, 12:22


በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጌዴኦ ዞን፣በዲላ ከተማ እንዲሁም በትምህርት ቤታችን ታሪክ እጅግ ከፍተኛ ውጤት (542 ከ600) ያስመዘገበው #ተማሪ_ልደቱ_ወንድይፍራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙሉ ነፃ ስኮላርሽፕ ተወዳድሮ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ዩኒቨርስቲውን ተቀላቅሏል።

ወደ ዩኒቨርስቲ ከመሄዱ በፊት በት/ቤታችን በመገኘት ለተማሪዎች መልዕክት አስተላልፏል። ተማሪዎች ትምህርታቸው በርትተው በማጥናት ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ እና የእርሱንም ተሞክሮ አጋርቷል። እሱ ውጤታማ እንዲሆን ላገዙት ቤተሰቦቹ፣መምህራንን እና ጓደኞቹን ከልብ አመስግኗል።

በመጨረሻም በእኔ የተዘጋጀለትን የማስታወሻ ስጦታ በፈተናው በኬሚስትሪ ትምህርት 100% እንዲያመጣ ትልቅ እገዛ ያደረገለት መ/ር #ግርማ_ታደሰ ሰጥቶታል።

መ/ር ግርማም ተማሪውን መልካሙን እንዲገጥመው ከተመኘ በኋላ ለተማሪዎች መልዕክት አስተላልፏል።

ተማሪ ልደቱ ወንድይፍራው በት/ቤታችን በነበረው የትምህርት ቆይታ አንፃር #በአዲስ_አበባ_ዩኒቨርስቲ ማጥናት የሚፈልገው #ሶፍትዌር_ኢንጂየሪንግ እንደሚሆን ቀደም ብሎ ተናግሯል።

ከውጤቱ በኋላ ዲላ በነበረበት ሰዓት የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገበው እና በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ2ኛ አመት የስፍትዌር ኢንጂነሪንግ ተማሪ ከሆነው #ተማሪ_ሮብሰን_መርጊያ ጋር አብረው ተወያይተው ነበር።

በትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ ስም መልካም የትምህርት ጊዜ እንዲሆንለት እንመኛለን።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቤታችንን የማህበራዊ ድህረ ገፆች ይጠቀሙ:

#ፌስቡክ:
https://m.facebook.com/groups/715959666071910/?ref=share&mibextid=NSMWBT

#ቴሌግራም:
https://t.me/dbict

#ዩቱብ:
https://www.youtube.com/@DBICTC

#ኢሜል:
[email protected]

#ቴሌግራም_ቦት

@DonBHS_bot

#ዋትስ_አፕ
https://whatsapp.com/channel/0029Vaa2AUE6buMFIk04MO29

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

26 Oct, 09:23


በ2015 ዓ.ም በዞኑ፣በዲላ ከተማ እንዲሁም በዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ከ700 604 አስመዝግቧል #ተማሪ_ሮብሰን_መርጊያ።

የICT ክበብ አባለ የነበረ ሲሆን ለቴክኖሎጂ ልዩ ፍቅር አለው። በ11ኛ ክፍል ትምህርቱ በት/ቤታችን የድረ ገፅ ግንባታ የተማረ ሲሆን አምስት የተለያዩ ድረ ገፆችን በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ሰርቷል። ከእኔ ጋር በመሆን የመጨረሻው ስራውን በ2015 ዓ.ም ከብሔራዊ ፈተና በኋላ የት/ቤታችንን ድረ ገፅ ሰርቷል።

በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ አመት #የሶፍትዌር_ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነው#

ይህን ስራዉን በክረምት የኮዲንግ ስልጠና መዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ ለታዳሚያን አቅርቧል።

ስራውን በሚከተለው የት/ቤታችን #ዩቱብ_ቻናል ተከታተሉልን።

ለቻናሉን አዲስ ከሆናችሁ
▶️ ሰብስክራይብ
▶️ ሼር እና
▶️ ኮሜንት ይስጡን

እናመሰግናለን

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

https://youtu.be/djPp3CjbWwI?si=zXdG9kvst42qB22z

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

26 Oct, 07:23


I AM A TEACHER...✍️

I May be a School Teacher,
I May be a College Lecturer,
I May be a University Professor !

Behind That Doctor,
It is Me, a Teacher.

Behind That Engineer,
It is Me, a Teacher.

Behind That Statistician,
It is Me, a Teacher.

Behind That Nuclear Physicist,
It is Me, a Teacher.

Behind That Mathematician,
It is Me, a Teacher.

Behind That Scientist,
It is Me, a Teacher.

Behind That Zoologist,
It is Me, a Teacher.

Behind That Entomologist,
It is Me, a Teacher.

Behind That Botanist,
It is Me, a Teacher.

Behind That Economist,
It is Me, a Teacher.

Behind That Entrepreneur,
It is Me, a Teacher.

Behind That Lawyer,
It is Me, a Teacher.

Behind That Political Scientist,
It is Me, a Teacher.

Behind That Psychologist,
It is Me, a Teacher.

Behind That Architect,
It is Me, a Teacher.

Behind That Astrologer,
It is Me, a Teacher.

Behind That Astronomer,
It is Me, a Teacher

I Carry the Light Even though they mostly make Fun of Me by their Uncharitable Jokes

But I am a Teacher.

I don't Qualify for a Bungalow or a Villa nor Earn enough to buy an Expensive House or a Car like Corrupt Officers and Corrupt Politicians.

But Yes, I am a Teacher.

Some Think or even Say that I have too many Holidays. They never know that I Spend those Holidays either correcting Papers or Planning what and how I am going to Teach when I go back to Blackboard or Whiteboard ...

Because I am a Teacher.

Sometimes I get Confused and even get Stressed by the Ever-changing Policies over what and how I have to Teach ...

Despite All That, I am a Teacher and I Love to Teach and I am Teaching.

On Pay-days I don't Laugh as Corrupt Officers and Others do...
But by the Next day I Love to come with a Smile to those that I Teach ...

Because I am a Teacher 👏

@Teachers Network

Dilla Don Bosco Catholic Secondary School

24 Oct, 12:58


#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

#tikvahethiopia