ብስራት Sport ⚽ @bsrat_sport Channel on Telegram

ብስራት Sport

@bsrat_sport


ለአዳዲ ስፖርታዊ መረጃዎች joine እና share ያድርጎ

ብስራት Sport ⚽ (Amharic)

ለብስራት Sport ⚽ ተወዳጁን ደግሞ ያለን አፕስላይን እና የሴቶች እና ወንድሞች የተጠቀሙ መረጃዎች አዳዲ ስፖርታዊ መረጃዎች ጠቀሙን ያስተካከሉ ፡፡ እናም ለእኛ አንድ ተመልከት ነው የእኛን ድምፅ መምራት መነሻ ለአጠቃቀም ሚናና ፡፡ ሊቆም ያለውን መረጃዎች ለማግኘት እና የተሰጡትን ሴቶች እና ወንድሞች የእኛን መረጃ ማቅረብ ተለዋጠ፡፡ ወንድማችን እና ሴቶችን የሚሽሩ እና ለማለፍ እኛያቀርባቸው ፡፡ ስቶኪንግ እና ላይንም እኛ ላቀረበን ነን፡፡ ኮንትሮሊክሱን እስከ እኛ ያሉ ሴቶችን እና ሀገር አባላትን የግንኙነት ምሁር ለማድረግ ያላቸውን ለማልቀላቀል ውስጥ ያግኙ ፡፡

ብስራት Sport

19 Jul, 16:39


https://t.me/pixelversexyzbot?start=5217565506

https://t.me/pixelversexyzbot?start=6591083686

ለሽልማት በጋራ እንታገል!  የእንኳን ደህና መጣችሁ ጉርሻ ይውሰዱ፡- 💸 2,000 ሳንቲም + 2X ማባዣ በመጀመሪያ 24 ሰአት 🔥 10,000 ሳንቲም + 3X ማባዣ ቴሌግራም ፕሪሚየም ካለ

ብስራት Sport

06 Jul, 16:53


ነፃ telegram ኮይን ዛሬውኑ ይጀምሩ  ሰው invite እያደረጉ
ለማስጀመር 👇👇👇
https://t.me/major/start?startapp=868704510

ብስራት Sport

08 Jun, 11:46


https://t.me/dagu_info/888

ብስራት Sport

24 Dec, 06:25


ሊቨርፑል ከአርሰናል ጋር ነጥብ ተጋርተዋል !

በአስራ ስምንተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከአርሰናል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የአርሰናልን ግብ ጋብሬል ሲያስቆጥር ሞሀመድ ሳላህ የሊቨርፑልን የአቻነት ግብ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ሞሀመድ ሳላህ በውድድር ዘመኑ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች ወደ አስራ ሁለት ከፍ ማድረግ ችሏል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ኛ :- አርሰናል ( 4️⃣0️⃣ ነጥብ )

2️⃣ኛ :- ሊቨርፑል ( 3️⃣9️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ማክሰኞ - በርንሌይ ከ ሊቨርፑል

ሐሙስ - አርሰናል ከ ዌስትሀም ዩናይትድ

@bsrat_sport    

ብስራት Sport

04 Dec, 05:08


ማንችስተር ሲቲ አቻ ተለያይቷል !

በአስራ አራተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የማንችስተር ሲቲን ግቦች ጃክ ግሪሊሽ ፣ ፎደን እና ሰን በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥሩ ለቶተንሀም ሰን ሁንግ ሚን ፣ ሎ ሴልሶ እና ኩሉሴቭስኪ ከመረብ አሳርፈዋል።

የቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ሰን ሁንግ ሚን በውድድር ዘመኑ ዘጠነኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ጃክ ግሪሊሽ የውድድር አመቱ የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ ከ2017 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

3️⃣ኛ :- ማንችስተር ሲቲ ( 3️⃣0️⃣ )

5️⃣ኛ :- ቶተንሀም ( 2️⃣7️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ማክሰኞ - ማንችስተር ሲቲ ከ አስቶን ቪላ

ማክሰኞ - ቶተንሀም ከ ዌስትሀም ዩናይትድ

@bsrat_sport    

ብስራት Sport

03 Dec, 16:23


ሊቨርፑል እና ቼልሲ ድል አድርገዋል !

በአስራ አራተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ብራይተንን 3ለ2 እንዲሁም ሊቨርፑል ፉልሀምን 4 ለ 3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች አሌክሳንደር አርኖልድ ፣ ማክ አሊስተር ፣ ኢንዞ እና ሌኖ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ሲያሳርፉ ለፉልሀም ዊልሰን ፣ ቴቴ እና ሬድ አስቆጥረዋል።

የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች ኢንዞ ፈርናንዴዝ (2x) እና ሌቪ ኮልዊል ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለብራይተን ፔድሮ እና ቡናኖቴ አስቆጥረዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች በርንማውዝ ከአስቶን ቪላ ጋር 2 ለ 2 እንዲሁም ዌስትሀም ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

2️⃣ኛ :- ሊቨርፑል ( 3️⃣1️⃣ ነጥብ )

8️⃣ኛ :- ብራይተን ( 2️⃣2️⃣ ነጥብ )

1️⃣0️⃣ኛ :- ቼልሲ ( 1️⃣9️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ዕሮብ - ሼፍልድ ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል

ዕሮብ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቼልሲ

ዕሮብ ብራይተን ከ ብሬንትፎርድ

@bsrat_sport    

ብስራት Sport

11 Nov, 17:10


ማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ድል አድርገዋል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አስራ ሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር አርሰናል በርንሌይን 3 ለ 1 እንዲሁም ማንችስተር ዩናይትድ ሉተን ታውንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ሊያንድሮ ትሮሳርድ ፣ ዊሊያም ሳሊባ እና ዚንቼንኮ ከመረብ ሲያሳርፉ ለበርንሌይ ብራውንሂል አስቆጥሯል።

የማንችስተር ዩናይትድን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቪክቶር ሊንድሎፍ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የመድፈኞቹ የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር ዚንቼንኮ ሁለተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ ካለፉት አምስት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አራቱን በአሸናፊነት መወጣት ችሏል

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

2️⃣ኛ :- አርሰናል ( 2️⃣7️⃣ ነጥብ )

6️⃣ኛ :- ማንችስተር ዩናይትድ ( 2️⃣1️⃣ ነጥብ )

የቀጣይ ሳምንት ጨዋታዎች ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ብሬንትፎርድ ከ አርሰናል

ዕሁድ - ኤቨርተን ከ ማንችስተር ዩናይትድ

- ቀጣይ ጨዋታዎች ከአንድ ሳምንት እረፍት በኋላ ይደረጋሉ።

@bsrat_sport    

ብስራት Sport

09 Nov, 05:54


ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከኮፐንሀገን ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ አራተኛ ጨዋታ 4 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ማንችስተር ዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ራስሙስ ሆይሉንድ ( 2x ) እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል ።

ራስሙስ ሆይሉንድ በመጀመሪያ አራት የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች አምስት ግቦችን በማስቆጠር በማንችስተር ዩናይትድ ታሪክ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆን ችሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከአራት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ሶስቱን በሽንፈት አጠናቋል።

የክለቦች የምድብ ደረጃ ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ. ባየር ሙኒክ ( 1️⃣2️⃣ ነጥብ )

2️⃣ኛ. ኮፐንሀገን ( 4️⃣ ነጥብ )

3️⃣ኛ. ጋላታሳራይ ( 4️⃣ ነጥብ )

4️⃣ኛ. ማንችስተር ዩናይትድ ( 3️⃣ ነጥብ )

@bsrat_sport    

ብስራት Sport

07 Nov, 22:00


ማንችስተር ሲቲ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅሏል !

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ አራተኛ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ከያንግ ቦይስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2x እና ፊል ፎደን ከመረብ አሳርፈዋል።

የጣልያኑ ክለብ ኤሲ ሚላን ከፒኤስጂ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በራፋኤል ሊያኦ እና ኦሊቪዬ ጅሩ ግቦች 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በሰላሳ አራት ጨዋታዎች ሰላሳ ዘጠኝ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኤሲ ሚላን በጨዋታ የውድድር ዘመኑን የመጀመሪያ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ እና ሌፕዚግ ከምድብ ሰባት ከወዲሁ ጥሎ ማለፉን መቀላቀል የቻሉ ክለቦች ናቸዉ።

በሌላ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ ሴልቲክን በአንቷን ግሪዝማን ( 2x ) ፣ ሞራታ ( 2x ) ፣ ሊኖ እና ኒጉዌዝ ግቦች 6 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

ምድብ ስድስት

2️⃣. ፒኤሴጂ:- 6️⃣
3️⃣. ኤሲ ሚላን :- 5️⃣

ምድብ ሰባት

1️⃣. ማንችስተር ሲቲ :- 1️⃣2️⃣
2️⃣. ሌፕዚግ :- 9️⃣

@bsrat_sport    

ብስራት Sport

07 Nov, 21:48


#UCL

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከሻክታር ዶኔስክ ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ አራተኛ ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የጀርመኑ ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ በበኩሉ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረጉትን የሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቦርስያ ዶርትመንድን የማሸነፊያ ግቦች ፉልክረግ እና ብራንድት ከመረብ ሲያሳርፉ የሻካታርን ግብ ሲካን አስቆጥሯል።

ሽንፈት የገጠመው ባርሴሎና በዘጠኝ ነጥቦች ምድቡን ሲመራ ሻክታር ዶኔስክ በበኩሉ በስድስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በሌላኛው ምድብ ዶርትመንድ በሰባት ነጥቦች ምድቡን መምራት ሲጀምር ኒውካስል ዩናይትድ በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

@bsrat_sport    

ብስራት Sport

05 Nov, 06:04


ባርሴሎና ወሳኝ ድል አሳክቷል !

በስፔን ላሊጋ የ 2023/24 የውድድር አመት የአስራ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የባርሴናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግቦ ሮናልድ አራውሆ በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

3️⃣ኛ :- ባርሴሎና ( 2️⃣7️⃣ ነጥብ )

6️⃣ኛ :- ሪያል ሶሴዳድ ( 1️⃣9️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ዕሁድ - ባርሴሎና ከ ዲፖርቲቮ አላቬስ

ቅዳሜ - አልሜሪያ ከ ሪያል ሶሴዳድ

@bsrat_sport    

ብስራት Sport

05 Nov, 06:04


መድፈኞቹ ሽንፈት አስተናግደዋል !

በአስራ አንደኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር አርሰናል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የኒውካስል ዩናይትድን የማሸነፊያ ግብ አንቶኒ ጎርደን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

3️⃣ኛ :- አርሰናል ( 2️⃣4️⃣ ነጥብ )

6️⃣ኛ :- ኒውካስል ዩናይትድ ( 2️⃣0️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - በርንማውዝ ከ ኒውካስል ዩናይትድ

ቅዳሜ - አርሰናል ከ በርንሌይ

@bsrat_sport    

ብስራት Sport

04 Nov, 17:14


ሲቲ የሊጉን መሪነት መረከብ ችሏል !

በአስራ አንደኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር ማንችስተር ሲቲ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 6ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች በርናርዶ ሲልቫ ( 2x ) ፣ ጄርሚ ዶኩ ፣ ፊል ፎደን ፣ አኬ እና አካንጂ ሲያስቆጥሩ የበርንማውዝን ብቸኛ ግብ ሲኒስቴራ አስቆጥሯል።

ቤልጂየማዊው ተጨዋች ጄርሚ ዶኩ በጨዋታው አንድ ግብ አስቆጥሮ አራት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በሌሎች ጨዋታዎች ኤቨርተን ከ ብራይተንን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ሲያጠናቅቁ ብሬንትፎርድ ዌስትሀም ዩናይትድን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ኛ :- ማንችስተር ሲቲ ( 2️⃣7️⃣ ነጥብ )

1️⃣7️⃣ኛ :- በርንማውዝ ( 6️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ዕሁድ - ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ

ቅዳሜ - በርንማውዝ ከ ኒውካስል

@bsrat_sport