BikuZega - ብቁ ዜጋ @bikuzega Channel on Telegram

BikuZega - ብቁ ዜጋ

@bikuzega


ልጆች በአካል፣ በአእምሮ፣ በስነ-ልቦና እንዲሁም በማህበራዊ ህይወታችው ብቁ ና ተወዳዳሪ ትውልድን ሆነው እንዲያድጉ ማስቻል።

Follow us on:
www.facebook.com/ethiobikuzega
www.twitter.com/BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ (Amharic)

ብቁ ዜጋ - በኢትዮቨጋ አዲስ ምሽትና ታሳሪነት እንዴት እንደሚደብቅ እንደሚለያዩ ልጆች አሰራሮችን መቀየረ እና ስነ-ልቦናን መረጃ እንችላለን። ብቁ ህይወታችው ብቁ ና ተወዳዳሪ ትውልድን ሆነው ኢትዮቨጋዊያንን እንዲያድጉ እና እንዴት እንደሚለያዩ አዲስ ምሽትን ሆኗል። በትክክለኛ ቦታ እና አገልግሎት ከሚስጥሩ አካባቢዎች ተወሰነ።

ከዚህ በኋላም እንዲሁም ከዚህ በኋላ በሚከተለው ቢከተለው በቅዳሜና በጥቂት ቀናት ብቁ ማህበሩን እና በእናት እሊኒችን በከንቱ ተጠባቢ። እንደጠቀማችሁ ማስቻለን፡

ከስምምነት የበለጠ ትውልዱን ተናግረዋል፡
www.facebook.com/ethiobikuzega
www.twitter.com/BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

10 Jan, 03:38


Use one of the best PDF Reader. Download free now! http://bit.ly/PDFReader_alldocumentreader

BikuZega - ብቁ ዜጋ

08 Jan, 15:02


እናመሰግናለን 🙏

በ ታህሳስ 26 በሰንዳፋ በCDTRC ግቢ በጣም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰብ ልጆች የህክምና ምርመራ እና የገና በአል አብረን ለማክበር በገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ ነገሮችን በመሸፈን አብራችሁን የነበራቹ ሁሉ በሰጣችሁት ስጦታ በልጆቹ ላይ ትልቅ ደስታና ተጸእኖ ፈጥራችዋል።

በነበረን ጊዜ

-የህክምና ምርመራ
- የጤና ትምህርት ( የወር አበባ፣ ከጉርምስና ጋር ተያይዞ የሰውነትና የባህሪ ለውጥ
- የጨዋታ ጊዜ
-የእጅ ስራዋች እየሰራን ስለ ገናም አውርተናል።
- የሚታጠብ ሞዴስ፣ ቲሸርት፣ ቅባት፣ሳሙና እና ቫዝሊን ሰጥተናል።

ሁሌም አብራችሁ በመቆም ስለምታበረታቱን እግዚአብሄር ይባርካችሁ።
አብራችሁን የነበራችው ሃኪሞች፣ ነርሶች እንዲሁም በጎ ፍቃደኞች እጅግ አድርገን እናመሰግናለን ያለእናንተ ይህንን ማሰብ ከባድ ነው።


#Fruitfulchildren #holistickids #Bikuzega #CDTRC #childhealth #healthscreening #holidays #volunteer #giving #lovesharing

BikuZega - ብቁ ዜጋ

25 Dec, 07:51


https://www.facebook.com/share/p/12yASuXsdPTfMJQm/

BikuZega - ብቁ ዜጋ

19 Dec, 15:51


የገና በአልን ምክንያት በማድረግ ታህሳስ 26 በ የልጆች እድገት ስልጠናና ምርምር ማዕከል ተገኝተን አቅም ለሌላቸው ልጆች የህክምና ምርመራ፤ የጤና ትምህርት እንዲሁም የሚታጠብ ሞዴስ፣ ሳሙና፣ ልብስ፤ ጫማ በመስጠት አብረን ለማሳልፍ አስበናል።
ለዚህም የቻላችሁትን በማካፈል አብሮነታችሁን እንድታሳዩን አደራ እንላለን።
0930069223
0924054848

BikuZega - ብቁ ዜጋ

13 Dec, 18:52


በልጆች ላይ የሚከሰት ቃጠሎን እና በቤት ውስጥ የምንሰጠው የመጀመሪያ እርዳታ

BikuZega - ብቁ ዜጋ

13 Dec, 18:48


Live stream finished (49 minutes)

BikuZega - ብቁ ዜጋ

13 Dec, 17:59


Live stream started

BikuZega - ብቁ ዜጋ

13 Dec, 16:31


ትንታ እና ቃጠሎ

ትንታና ቃጠሎ በልጆች ላይ ሲከሰት በቤት ውስጥ እንዴት የመጀመሪያ እርዳታ ልንሰጣቸው እንችላለን?

የድንገተኛ ህክምና ክፍል ጠቅላላ ሃኪም ከሆነችው ከ እንግዳችን ከዶ/ር ሄርሜላ ጌታቸው ጋር ትንታና ቃጠሎ በልጆች ላይ ሲከሰት በቤት ውስጥ እንዴት የመጀመሪያ እርዳታ ልንሰጣቸው እንችላለን? የሚለውን የምንወያይ ይሆናል።

በዚህ ሳምንት በብቁ ዜጋ ፖድካስት ትንታና ቃጠሎ በልጆች ላይ ሲከሰት በቤት ውስጥ እንዴት የመጀመሪያ እርዳታ ልንሰጣቸው እንችላለን? የህክምና ተቋም ከመድረሳቸው በፊት ምን ማድረግ ይኖርብናል? የሚለውን የምንወያይ ሲሆን እናንተንም በዚህ ውይይት ላይ እንድሳተፉ እና እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።


ተጋባዥ
▪️ዶ/ር ሄርሜላ ጌታቸው (የድንገተኛ ህክምና ክፍል ጠቅላላ ሃኪም)

አዘጋጅ እና አቅራቢ
▪️ብፅት ኤልያስ




🗓 አርብ ታህሳስ 4
⏱️ማታ ከ3:00 - ከ4:30

#BikuZegaPodcast

@BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

11 Dec, 11:02


ትንታ እና ቃጠሎ

ትንታና ቃጠሎ በልጆች ላይ ሲከሰት በቤት ውስጥ እንዴት የመጀመሪያ እርዳታ ልንሰጣቸው እንችላለን?

የድንገተኛ ህክምና ክፍል ጠቅላላ ሃኪም ከሆነችው ከ እንግዳችን ከዶ/ር ሄርሜላ ጌታቸው ጋር ትንታና ቃጠሎ በልጆች ላይ ሲከሰት በቤት ውስጥ እንዴት የመጀመሪያ እርዳታ ልንሰጣቸው እንችላለን? የሚለውን የምንወያይ ይሆናል።

በዚህ ሳምንት በብቁ ዜጋ ፖድካስት ትንታና ቃጠሎ በልጆች ላይ ሲከሰት በቤት ውስጥ እንዴት የመጀመሪያ እርዳታ ልንሰጣቸው እንችላለን? የህክምና ተቋም ከመድረሳቸው በፊት ምን ማድረግ ይኖርብናል? የሚለውን የምንወያይ ሲሆን እናንተንም በዚህ ውይይት ላይ እንድሳተፉ እና እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።


ተጋባዥ
▪️ዶ/ር ሄርሜላ ጌታቸው (የድንገተኛ ህክምና ክፍል ጠቅላላ ሃኪም)

አዘጋጅ እና አቅራቢ
▪️ብፅት ኤልያስ




🗓 አርብ ታህሳስ 4
⏱️ማታ ከ3:00 - ከ4:30

#BikuZegaPodcast

@BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

08 Dec, 07:26


📖 ክቡር ልጆች
✍️ ብርሃኑ በላቸው አሰፋ
@childdevtnetwork

⚠️  ጤና ቢስ አካላዊ ንክኪ
:::::::::::::::::::::::::::
አካላዊ ንክኪ እንደ ልጆች እድሜ እና እድገት ይለያያል፡፡ ልጆች እያደጉ ሲመጡ አካላዊ ንክኪው እንዲቀንስ ይመከራል፡፡ ልጆች እድሜያቸው በአስራዎቹ ሲሆኑ ፍቅርን የምንገልፅበት መንገድ ይለያል፡፡ በአስራዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኙ ታዳጊዎች ፍላጎታቸው፣ ስሜታቸው ሊከበሩላቸው ይገባል፡፡ እንኳን አካላቸው አከባቢያዊ ነፃነታቸው (Physical boundary) ሊከበርላቸው ይገባል፡፡ 

በልጆች ላይ ፆታዊ ጥቃት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ዘጠና ሦስት በመቶ ልጆች ፆታዊ ጥቃት የሚደረስባቸው በቅርብ ሰዎቻቸው ሲሆን ቀሪው ሰባት በመቶ ደግሞ ቀደም ብለው በማያውቁት እንግዳ ሰዎች ነው፡፡

ወላጆች ይህንን እውነት በመረዳት ለልጆቻቸው አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግ ለፆታዊ ፍላጎት ማርኪያ (Paedophilia) ከመሆን ለመታደግ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

መታቀፍ አልያም ጀርባ መዳበስ ምቾች የሚነሳቸው ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ያለፈቃዳቸው ፈፅሞ ሊነኩ አይገባም፡፡ ጤና ቢስ አካላዊ ንክኪ ትኩረት ተሰጥቶት መፍትሄ ያስፈልገዋል፡፡ ጤና ቢስ አካላዊ ንክኪ የምንለው አንድ ሰው በማንኛውም ወቅት የልጆችን ያልተፈቀዱ የግል አካላቸውን በመነካካት የሚያስጨንቅ፣ የሚያስፈራራ፣ የሚያበሳጭ፣ ግራ የሚያጋባ እና ምቾትን የሚነሳ ስሜት የሚፈጠርባቸው በተለይም ፆታዊ ትንኮሳን ሲያካትት ነው፡፡

ይህ አጀንዳ በተለይ ለእኛ አገር ከባድ ጉዳይ ነው፡፡ ጉዳዩን ከባድ የሚያደርገው ደግሞ በወላጅ እና ልጆች መካከል በግልፅ የመወያየት ልማድ አለመኖሩ ነው፡፡

BikuZega - ብቁ ዜጋ

06 Dec, 21:17


ምግብ ለመመገብ የሚያስቸግሩ ልጆችን በምን ዘዴዎች  እናብላቸው?

ብዙ ወላጆች ልጆቻቸው አንበላም አሉን ምን ይሻላል? የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄን ሲያነሱ ይስተዋላል። በእርግጥ ልጆችን ማብላት ትዕግስት እና ጥበብ የሚጠይቅ ሂደት ነው። ለዛሬ ልናበላቸው ስንል ማድረግ ከሚገባን ነገሮች ዉስጥ በጥቂቱ ለመዳሰስ እንሞክራለን።

1፡ ለመመገብ በተቀመጥን ወቅት ማውራትና ማጫወት

መመገብ ህጻኑ እንደ አንድ ማኅበራዊ ግንኙነት እንዲመለከተው ማድረግ እንዲሁም ለህጻኑ ጠጣር ምግብ ስናቀርብለት አንድ አዲስ ነገር ከሚወደው ሰው እንደተሰጠው እንዲሰማው ማስቻል።

ስለምግቡ በማውራት ለምሳሌ “ቤቢ ካሮት እየበላ ነው፤ ካሮት ይወዳል" በማለት ማብላት የምንችል ሲሆን በዚያውም አዲስ ቃልም እንዲያውቅ እንረዳዋለን። በተጨማሪም አብረን አፋችንን በመክፈት ህጻኑም በማጉረስ የመመገቢያውን ሰአት ወደ መዝንኛ መቀየር አንዱ መንገድ ነው።

2፡ እንደምንበላ ማስመሰል

በምናበላው ጊዜ እራሳችን እንደምንበላ በማስመሰል ለምሳሌ ማንኪያ ሙሉ የህጻኑን ምግብ በመዉሰድ እንደምንበላ አፋችንን ከፍተን እንደ በላን በማስመሰል እንዲጓጓ በማድረግ ማብላት።

3፡ አለማስገደድ

በምናበላቸው ጊዜ አለመፈለግ፣ ጭንቅላታቸውን ማዞር እና አፋቸውን አለመክፈት ያለመፈለግ ምልክት ስለሚሆኑ ባለማስግደድ እስኪርባቸዉ መጠበቅና ፈልገው እንዲበሉ ማድረግ ይኖርብናል። የምናስገድጋቸዉ ከሆነ ሊጠሉ ስለሚችሉ ባናስገድዳቸው ይመከራል።

4፡ ማታ ጠጣር ምግብ አለመመገብ

ህጽኑ ወደ አልጋ በመሄጃዉ ሰዓት ጠጣር ምግብ ማታ እንዳይነሳ ብሎ መመገብ ህጻኑን የሚረብሸው እና በቂ እንቅልፍ እንዳያገኝ ያደርገዋል። ጠጣር ምግብ ላይፈጭና ድርቀት ሊያመጣ ስለሚችል ማታ ወይም ከመተኛቱ በፊት የጡት ወተት ወይም ፎርሙላ ማጥባት ይመከራል።

5፡ እራሳቸዉ እንዲበሉ ማበረታታት

ህጻኑ 6 ወር ሲሞላው ሁለት ችሎታዎችን ያዳብራል። እነርሱም #መቀመጥ እና #መያዝ ናቸው። በዚህ ጊዜ ልጆች ለመያዝ በሚያመቻቸው መጠን ፍራፍሬዎችን በመቆራረጥ እራሳቸው አንስተው እንዲበሉ ማበረታታት ያስፈልጋል።

6፡ ምግብ መቀያየር

አንድ አይነት ምግብ ሁሌ መመገብ ህጻኑ እንዲሰላቸውና እንዲጠላው ስለሚያደርግ የተለያ ምግብ በመቀያየር ማብላት ይገባል።

7፡ የተቀላቀለ ምግብ አለመመገብ

አንድ ምግብ ብቻ ለህጻኑ ማስተዋወቅ አላርጂ የሆነውን መለየት እንድንችል ያደርገናል። ስለዚህ በመጀመሪያ ጠጣር ምግብ ስናስተዋውቀው ብዙ ምግቦችን በመቀላቀል ከሚሆን አንድ ብቻ በማብላት መጀመር ይመከራል።

8፡ ጨውና ስኳር አለመጠቀም

በመጀመሪያ ጠጣር ምግብ በምናስተዋውቅበት ጊዜ ስኳር እና ጨው አለመጠቀም የሚመከር ሲሆን ጣፋጭና ጨዋማ ምግብ ለልጆች በህጻንነታቸው ጊዜ አይመከርም።

[ @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የቀረበ ]

@TikvahethMagazine

BikuZega - ብቁ ዜጋ

29 Nov, 07:57


ለህጻናት ጠጣር ምግብን መቼ እና እንዴት እናስተዋውቃቸው?            

የእናት ጡት ለህጻኑ የሚያስፈልገውን ንጥረ ነገር በሙሉ የያዘ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ በቂው ነው።

6 ወር ከሞላው ቦኃላ ከጠጣር ምግብ ጋር ልጁን ማስተዋወቅ መጀመር የሚኖርብን ሲሆን ጡትም ለማስጣል ህጻኑን ጠጣር ምግብ ቀስበቀስ ማስለመድ ይኖርብናል።

ጠጣር ምግብ የጡት ወተትን ሙሉ በሙሉ ስለማይተካ ጡት ማጥባት እስከ 2 አመት ማቆም አይኖርባትም።

1፡ መቼ እንጀምር ?

▪️ቤተሰብ ምግብ በሚመግብበት ጊዜ ህጻኑን ምግብ ጠረጵዛ ዙሪያ አብሮ በማቅረብ እና የህጻኑን የምግብ ፍላጎት መመልከት ይቻላል።

▪️ምግብ በምንመገብ ጊዜ ህጻኑ የሚያሳየዉ ምልክቶች ለምሳሌ ፦ሳህን አካባቢ ለመድረስ እና ለመያዝ፣ ስንጎርስ የመጓጓት አፍ የመክፈት፣ ማንኪያችንን መያዝ፣ የመሳሰሉት ምልክቶች ልጆች ጠንካራ ምግብ ለመብላት ፍላጎት የማሳየት ምልክቶች ናቸዉ።

2፡ የመጀመሪያ ጉርሻ

የመጀመሪያ ጠጣር ምግብ ስንጀምር አላርጂክ ሊያስከትሉ የሚችሉ ምግቦችን ለይተን ማወቅና ማስወገድ ይኖርብናል፣ የመጀመሪያው ጉርሻ  ለጡት ወተት የቀረበ ጣዕም ያላቸዉ ቢሆኑ ይመረጣሉ።

አላርጂክ ሊያስከትሉ የሚችሉ ምግቦች

▪️የወተት ተዋዖዎች ፣ እንቁላል፣ ለዉዝ፣ የአሳማ ስጋ፣ስንዴ፣አኩሩ አተር ወዘተ

አላርጂክ በብዛት የሌላቸዉ ምግቦች

▪️አፕል ፣ አቮካዶ ፣ ቀይ ስር ፣ ብሮክሊ ፣ ካሮት፣አበባ ጎመን፣አጃ ፣ ማንጎ ፣ ፓፓዬ ፣ ሩዝ ፣ የሱፍ ዘይት ፣ የስኳር ድንች ፣ የዶሮ ስጋ

▪️መጀመሪያ ጉርሻ ለምሳሌ የተፈጨ ሙዝ፣ የተፈጨ ስኳር ድንች በጡት ወተት ወይም በፎርሙላ ወተት የተቀላቀለ ሊሆን ይችላል።

የመጀመሪያ ጉርሻ መሆን ያለበት በእጃችን ማቅመስ ቢሆን ይመከራል። በመጀመሪያ በጣታችን የተፈጨዉን ሙዝ በማንሳት ለህጻኑ ከንፈር ላይ በማድረግ በቀስታ እንዲቀምስ መተዉ።

ከቀመሰው ቦኋላ ጣታቸንን እንዲጠባ በማድረግ ከጠጣር ምግብ ጋር ማለማመድ፣ አንዴ ከቀመሰ ቦኋላ መጠኑን በመጨመር ወደ ህጻኑ ምላስ በማድረግ ማብላት፣ ህጻኑ እየበል ከሆነ ካልተፋ ወዶታል ማለት ነዉ፣ በተደጋጋሚ የሚተፋ ከሆነ ግን ለመመገብ ዝግጁ አይደለም ማለት ነዉ።

በመጀመሪያው ሙከራ ህጻኑ አልተመገበም ብለን ተስፋ መቁረጥ የለብንም፣ በመደጋገም ሙከራ ማድረግ ይኖርብናል።

3፡ በምን ያህል መጠን እንጀምር?

በሙዝ የጀመርነውን የመጀመሪያውን ጠጣር ምግብ ህጻኑ ከወደደው ለጅማሮ ከሙሉ ጣት ወደ ግማሽ ማንኪያ ከዚያም ወደ አንድ ማንኪያ፣ ከዚያም ወደ አንድ ሙሉ የሾርባ ማንኪያ፣ ከዚያም ወደ ግማሽ ብርጭቆ ማሳደግ ይቻላል።

የምንመግበዉ ጠጣር ምግብ በሾርባና በጁስ መልክ መሆን አለበት። ማስታወስ ያለብን እስካሁን ከጠጣር ምግብ ጋር ህጻኑን እያስተዋወቅን መሆናችንን ነዉ።

ከመጀመሪያው ጉርሻ በኋላ ህጻኑ ጠጣሩን ምግብ ከወደደውና መብላት ከጀመረ ቀስ እያልን መጠኑን እየጨመርን እንሄዳለን ፣ማስታወስ ያለብን የህጻኑ ሆድ ትንሽ የእጅ ጭብጥ መጠን መሆኑና ብዙ እንዲበላ ማስገደድ እንደሌለብን ነዉ። ምናልባት ህጻኑ 2 ወይ 3 ማንኪያ ብቻ በቀን ውስጥ ቢበላልን በቂ ነው።

4፡ መቼ እናብላዉ?

▪️በመጀመሪያ ጠጣር ምግብ ባስተዋወቅንበት ቀናት ህጻኑ ተናዳጅ፣ ያለመፈለግን ምልክት ሊያሳይና ይችላል፣ በዚህ ጊዜ ሁለታችሁም አካሄድዱን መቀየር ሊኖርባቹ ይችላል።

▪️በመጀመሪያ በጣም ምቹ ሰአትን መምረጥና የአመጋገብ ሁኔታም ከተለመደዉ ወጣ ያለና ጫወታን የቀላቀለ ለማድረግ መጣር ይኖርብናል።

ጠዋት የህጻናት የጣሳ ወተት (formula)  ለሚጠጡ ልጆች ጠጣር ምግብ ለማብላት ወደ ማታ ጊዜ ምቹ ነው። የጡት ወተት በሚቀንስበት ሰአት ጠጣር ምግብ ለማብላት መዘጋጅት ምቹ ሰአት ነው። ለህጻኑ ጠጣር ምግብ ማብላት ያለብን ጡት በማጥባት በመሀል ነው።

ጠጣር ምግብ ምናልባት በጡት ወተት ውስጥ ያለውን ጠቃሚ ንጥረ ነገር ሊወስድ  ስለሚችል (ለምሳሌ አይረንን) በአንድ ላይ ጠጣር ምግብና ጡት ማጥባት አይመከርም።

▪️በምንመግባቸው ጊዜ በፍጥነት አብልተን ለማስነሳት መቸኮል አይገባንም። ህጻናት በጣም ቀስ እያሉ እየተጫወቱ ስለሚበሉ ትዕግስት ያስፈልገናል።

[ @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የቀረበ ]

@TikvahethMagazine

BikuZega - ብቁ ዜጋ

22 Nov, 20:25


ልጆቻችን ምን ይመልከቱ?

በአሁኑ ሰዓት በርካታ ልጆች ለዲጂታሉ አለም በቶሎ በሚኖራቸው ተጋላጭነት ሳቢያ ላልተመረጡ ፕሮግራሞች እና ኮንተንቶች ሲጋለጡ ይስተዋላል።

ከዚህም ባለፈ አንዳንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ምድባቸው የመዝናኛ ይሁን እንጂ ይዘታቸው ለህጻናት የሚመጥን ሳይሆን ብዙ ሰዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ ይደመጣል።

እነዚህ ፕሮግራም እና ቪዲዮዎች የልጆች አስተዳደግ እና አስተሳሰብ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖዎች አላቸው።

በተለይ ደግሞ ልጆች የቋንቋ እና የአስተሳሰብ ችሎታቸው የሚዳብረው በመጀመሪያ ሰባት አመት በመሆኑ በዚህ እድሜ ላልተመረጡ ፕሮግራሞች የሚኖራቸው ተጋላጭነት ላልተፈለጉ ጫናዎች ይዳርጋቸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳን ላይ ጠቅላላ ሃኪም እና ሁለንተናዊ የህጻናት እድገት ባለሞያ የሆኑትን ዶ/ር ቱሚም ጌታቸውን አነጋግሯል።

ዋና ዋና ነጥቦች፦

- ልጆች በመጀመሪያው ሰባት አመት ከፍተኛ የአዕምሮ እድገታቸው የሚጀምርበት እድሜ ነው፤

- ከ ሰባት ዓመት በታች ያሉ ህጻናት እንደ እድሜያቸው አስተማሪ የሆነ ፕሮግራሞችን ቢያዩ ይመከራል፤

- ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ቢሆኑም እንኳን ከ ሰባት ዓመት በታች ያሉ ህጻናት በቀን ከ ሁለት ሰዓት በላይ ስክሪን እንዲመለከቱ አይመከርም።

- ሚዲያዎች በወላጅ ድጋፍ እንዲመለከቷቸው የሚያስታውሱ የጽሁፍ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉት ፕሮግራም ላይ ማስቀመጥ ቢችሉ መልካም ነው።

- ወላጆች ለልጆቻቸው እነሱ አስቀድመው ያዩትን እና የፈተሹትን ቢያሳዩ ያንን ባይችሉ እንኳን ልጆቻቸው ሲያዩት አበረው ቁጭ ብለው ቢያዩ እና የሚያዩትን ነገር ለልጆቻቸው ማስረዳት ቢችሉ ይመከራል።

- ልጆች በልጅነታቸው የተራዘመ የስክሪን ቆይታ ሲኖራቸው እድሜያቸው እየጨመረ በሚመጣበት ወቅት ለዲጂታል ጾታዊ ጥቃት ተጋላጭነታቸውን ያሰፋዋል።

- ወላጅ ልጆቼን እንዴት አድርጌ ልቆጣጠራቸው እችላለሁ የሚለውን ማወቅ ያለባቸው በመሆኑ በተቻለው መጠን ስለ ኤሌክትሮኒክስ ያላቸው እውቀት ሊያሳድጉ ይገባል።

ሙሉ ቃለመጠይቁን ያንብቡ https://telegra.ph/ETH-11-22-5

@TikvahethMagazine

BikuZega - ብቁ ዜጋ

21 Nov, 19:28


ለልጆቻችን ምን እንመግብ ?

በሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ዩኒሴፍ ዘገባ 38.6% ከ5 አመት በታች ያሉ ልጆች የቀነጨሩ ሲሆኑ 21% የሚሆኑ 5 አመት በታች ያሉ ልጆች ከሚጠበቅባቸዉ ክብደት በታች ያሉ ሲሆን ከ15-49 ያሉ ሴቶች በምግብ እጥረት የተጎዱ ናቸው።

ስለተመጣጠነ ምግብ ማውራት ብዙ ሰው ቅንጦት ይመስለዋል፤ ነገር ግን ቅንጦት ሳይሆን እጅግ በጣም ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።

ምክኒያቱም የምግብ ጉዳይ ከጽንስ ጅምሮ እስከ 2 አመት ለልጆች የምናበላዉ እስከ ህይወት ፍጻሜያቸዉ ድረስ ተጽኖ ስለሚያመጣ ትኩረት ልናደርግ ይገባል። 

ለልጆች መመገብ ካለብን ውስጥ፦

1፡ ጥሩ ቅባት (smart fat)

ህጻናት ትክክለኛ ቅባት/ fat /ያስፈልጋቸዋል። ይህ ማለት ዝቅተኛ ቅባት ሳይሆን ምርጥ ቅባት ያለዉ ምግብ ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው።

-:ለህጻናት ጥሩ ቅባት ምንጭ ከሆኑ ምግቦች መካከል የባህር ምግብ(salmon)፣ ተልባ(flax oil)፣ አቮካዶ ፣ የአትክልት ዘይት ፣ ለውዝ (አላርጂክ ሊያስከትል ስለሚችል ከ2 አመት በኋላ)

- ለህጻናት ጥሩ ያልሆኑ ቅባቶች፡ ዘይት የበዛባቸውና የተጠበሱ ምግቦች፣ ብስኩት (crackers)

2: ጤናማ ስኳር (Best Carbs)

ህጻናት በተፈጥሮአቸዉ ስኳርና ጣፋጭ ነገሮችን ይወዳሉ፣ ሰዉነታቸዉም ይፈልጋል። ስኳር የሰዉነታቸዉ ዋናዉ ነዳጅ እና ሀይል ሰጪ ነዉ።

ጤናማ ስኳር የያዙ ምግቦች፦

አፕል ፣ ሙዝና ፍራፍሬ ፣ የጡት ወተት ፣ የወተት ተዋዖዎች (በተለይ ባዶ እርጎ) ፣ ትኩስ ፍራፍሬ፣ ፓስታ፣ ድንች ፣ አኩሪ አተር። ስኳር ድንች ፣ አትክልት እና አዝእርቶች።

3፡ ፕሮቲን 

ፕሮቲን ገንቢ ምግብ በመባል ይታወቃል። ፕሮቲን ለእድገት፣ ለሰዉነትን ግንባታ ትልቁ ድርሻ ይወስዳል።

በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች፦

የባህር ምግብ ፣ የወተት ተዋዕዖ (እርጎ፣ቺዝ እና ወተት) ፣ ጥራጥሬ (አኩሪ አተር፣ ምስር፣ ቦሎቄ)፣ ስጋና የዶሮ ስጋ፣ እንቁላል የለዉዝ ቅቤ ፣ያልተፈተጉ እህሎች (ስንዴ፣ ሩዝ፣ አጃ፣ በቆሎ እና ማሽላ)

4፡ በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን ማዘውተር

ፋይበር/ቃጫ/ የምንለዉ የማይፈጨው የአትክልት እና የፍራፍሬ አካል ነው። በተፈጥሮ አንሸራታችነት ባህሪ ስላለዉ ከሰውነታችን አላስፈላጊ የሆኑ ቆሻሻዎችን  ለማሶገድ ይረዳል። ለህጻናት በፋይበር የበለጸገ ምግብ ሰገራቸዉ እንዲለሰልስና አላስፈላጊ ቆሻሻ ቶሎ እንዲወገድ ከመርዳቱም ባሻገር ድርቀትን ይከላከላል።

በፋይበር የበለጸጉ ምግቦች፦

አትክልት( ድንች ከነልጣጩ)፤ ያልተፈተጉ እህል፤ ቡኒ ሩዝ፤ ቦለቄ የመሳሰሉት፤ ካልተፈተገ እህል የተዘጋጀ ፓስታ፣ መኮረኒ፣ አጃ፣ ጥራጥሬ።

5፡ ቪታሚን

ከሶስቱ ዋና የምግብ ክፍሎች ( ቅባት፣ ፕሮቲን፣ ሃይል ሰጪ ምግቦች) በተጨማሪ ቪታሚን ለህጻናት እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል። እንደ ዋና ምግቦች( Macro nutrients) እኚህ ቪታሚንና ሚኒራለስ (micro nutrients) በቀጥታ ለሰዉነታችን ሃይል አይሰጡንም። ነገር ግን ለህጻናት የበሉት ምግብ በአግባቡ እንዲጠቅማቸውና የሰውነት ክፍላቸው በአግባቡ እንዲሰራ ያደርጋል።

ሰውነታችን እነዚህን ንጥረነገሮች ካላገኘ በአግባቡ መስራት አይችልም። ሰውነታችን 13 ቪታሚኖች ያስፈልጉታል። ቪታሚን A, C, D, E, K, እና  8 የ B ቤተሰቦች ማለትም thiamine, niacin riboflavin, pantothenic acid, biotin, folacin, B6 and B12.

6: ሚኒራልስ

እንደ ቪታሚንስ ሚኒራልስ (micro nutrients) የሚካተት ሲሆን ለህጻናት እድገት አስፈላጊ ንጥረነገር ነው። ሚኒራል የምንላቸው ካልሽየም፣ ፎስፈረስ፣ ማግኒዝየም እነዚህ ሶስቱ ጠንካራ አጥንትን ለመገንባት ይጠቅማሉ።

አይረን እና ኩፐር (copper) ደምን ይገነባሉ። ዚንክ( zinc) በሽታ የመከላከል አቅምን ይገነባል፣ሶዲየምና ፖታሺየም( sodium and potassium) ኤሌክትሮ ላይት የምንለዉ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የውሃ መጠን ይቆጣጠራል።
           
7፡ የአይረን መጠንን መጨመር

እያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል( organs) በአግባቡ እንዲሰራ ብረት በጣም አስፈላጊ ንጥረነገር  ነው። ዋናው ስራውም ሂሞግሎቢንን (hemoglobin) መገንባት እና በቀይ የደም ሴል ውስጥ ያለውን ኦክስጅን የሚሸከም ነው።

አንድ ህጻን ልጅ ከ9_10 ወራት ውስጥ ሂሞግሎቢኑ መለካት አለበት፣ ይህም የሚሆንበት ምክኒያት ህጻኑ የደም ማነስ እጥረት ይኑርበት አይኑርበት ለማጣራት ነው።

በአይረን የበለጸጉ ምግቦች፦

የጡት ወተት፣ በብረት የበለጸጉ የህጻናት ወተቶች፣ የቲማቲም ጁስ፣ምስር፣ አኩሪ አተር፣አሳ፣ የዶሮ ስጋ፤ ቦለቄ እና የመሳሰሉት።

[ @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የቀረበ ]

@TikvahethMagazine

BikuZega - ብቁ ዜጋ

14 Nov, 15:03


የሰሞኑን ጉንፋን

ሰምኑን ብዙ ህፃናት እና አዋቂዎች ላይ የሚታየው ጉንፋን ዋና መንስኤዎቹ በሳል እና በማስነጠስ የሚተላለፉ የተለያዩ እና ራሳቸውን በሚቀያይሩ ቫይረሶች የሚመጣ በሽታ ነው::

ለምሳሌ: ኮሮና ቫይረስ ፣RSV ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ እና የመሳሰሉት ቫይረሶች ጉንፋንን ሊያመጡ ይችላሉ::

ምልክቶቹ

👉🏻የጉሮሮ ህመም፣ከፍተኛ ትኩሳት፣ኃይለኛ ሳል፣ኃይለኛ ራስ ምታት፣ አፍንጫ መታፈን እና ፈሳሽ ፣ብርድ ብርድ ማለት፣ የመገጣጠሚያ የጀርባና የጡንቻ ህመም፣ምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ድካም

ለጉንፋን ተብሎ የተዘጋጀ ፈዋሽ መድሃኒት የለም ሆኖም ቤት ውስጥ በማከም ለውጥ ማምጣት እና ማገገም ይቻላል !

ምን እናድርግ?

አራስ/ጨቅላ ህፃናት የሚተነፍሱት በዋናነት በ አፍንጫቸው ነው:: በጉንፋን ምክንያት አፍንጫቸው ከተደፈነ በ አፋ መተንፈስ ስላለመዱ በጣም ይጨናነቃሉ::

🤧🤱ስለዚህ አፍንጫቸው ከተደፈነ መጀመርያ በጀርባ ማስተኛት እና ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው (saline water) አድርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 3-5 ጠብታ ማድረግ 30 ሰከንድ ጠብቀን ከተኙበት አንስተን ወደ ታች ዘቅዘቅ አርገን መያዝ እና የአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ (Nasal suction bulb) ማጽዳት ወይም መምጠጥ

🤱የጡት ወተት በደንብ ማጥባት ፡ ምክንያቱም በአፍንጫ ፈሳሽ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል ::

🫵🏻አስተውሉ: የጡት ወተት ዉስጥ በሽታ ተከላካይ ንጥረ ነገሮች አሉ!!


🥛 የጣሳ ወተት የሚወስዱ ከሆነ ለብ እያርጉ መስጠት ከሌላው ጊዜ መጠኑን ጨመር አድርጎ መስጠት

🛌 ስናስተኛቸው ቢያንስ 30 ዲግሪ ከፍ ማድረግ

🍵 ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት(ከ 7 ወር በላይ) ለምሳሌ ሾርባ የብርቱካን ሻይ እና የመሰሳሰሉት
🍱 ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ
🧹 የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት እና ማናፈስ
🏡 ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን
በቂ እረፍት/እንቅልፍ እንዲያገኙ ማድረግ
🧄 ነጭ ሽንኩርት በመጠኑ ከምግባቸው ጋር እየጨመሩ አብስሎ መስጠት
🤒 ትኩሳታቸው ለመቀነስ መጀመርያ ልብሳቸውን መቀነስ ከዛም ለብ ያለ ዉሃ ውስጥ ፎጣ እየነከሩ ግንባራቸው እና ሰውነታቸው ላይ ማድረግ

ከላይ ባለዉ ዘዴ ሰውነታቸው ካልቀዘቀዘ ባለሙያ አማክሮ የህመም ማስታገሻ መስጠት ።

እነዚህን መፍትሄዎች እያረጋችሁ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ፣ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የመቆራረጥ ምልክት በህፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል‼️

ጉንፋን በቀላሉ ወደ ኒሞንያ ሊሻገር ስለሚችል ከታች ያሉትን ምልክቶችን ካዩ ልጅዎን ባአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል መውሰዱ እአስፈላጊ ነው

📍 ጡት አልጠባም ካሉ
📍ትኩሳታቸው 38.5 በላይ ከሆነ
📍ኃይለኛ ሳል እና ተደጋጋሚ ትውከት
📍 ማንቀጥቀጥ ካለ
📍በጣም መደካከም ካለ
📍ተቅማጥ ካለ
📍ቶሎ ቶሎ መተንፈስ እና ማቃሰት
📍እንቅልፍ ለመተኛት የሚቸገሩ ከሆነ
📍ረጅም ሰአት ማልቀስ ካለ

🫵🏻የፀረ ባክቴርያ (Antibiotics) መድሃኒቶች ለምሳሌ : (Amoxacillin,Augementin, Azithromycin) ..... ለጉንፋን በሽታ ማስታገሻዎች አይደሉም

Join 👇🏻

telegram:- https://t.me/currrrrrr99

Tik tok:- https://www.tiktok.com/@dr.tumim.getachew?_t=8mDNslc442P&_r=1

Facebook:- https://www.facebook.com/Drtumim?mibextid=LQQJ4d

BikuZega - ብቁ ዜጋ

12 Nov, 10:05


ጉዞ ወደ ሳይንስ ሙዚየም

ትምህርትታዊ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ና ቴክኖሎጂ ፍካሊቲ (ASTU) ወደሚገኘው ሳይንስ ሙዚየም

ልጆች ፈፅሞ አትንኩ ወደ ማይባሉበት እና ስለሳይንስ እየነካኩ፣ እየዳሰሱ፣ እየገነቡ፣ እያፈረሱ በተጨባጭ የሚማሩበት፣ ለብዙ ውስብስብ የሳይንስ ጥያቄዎቻቸው መልስ የሚያገኙበት እና ልጆች ሳይንስን በቀላሉ የሚማሩበት ጉዞ በብቁ ዜጋ እና በሆለስቲክ ክድስ ተዘጋጅቶሎታል። ኑ ልጆቾን በተግባር ሳይንስን ያስተምሩ።

ጉዞው ምን ያካትታል?
▪️ትራንስፖርት
▪️አስጎብኚ
▪️ካሜራ
▪️ውሃ
▪️መክሰስ
▪️ምሳ


መቼ? ቅዳሜ ህዳር 7
መገናኛ ቦታ ፡ CMC ሳሊተ ምህረት
መገናኛ ሰአት ፡ ጠዋት 1:30

መመለሻ ሰአት፡ 7:00
የተሳታፊ እድሜ፡ ከ 7-16 አመት

ዋጋ 1500 ብር ብቻ

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገብ
ለበለጠ መረጃ

📞 0930069223 ይደውሉ

BikuZega - ብቁ ዜጋ

08 Nov, 19:44


በጉርምስና እድሜ ካሉ ልጆች ጋር እንዴት መግባባት እንችላለን?

BikuZega - ብቁ ዜጋ

08 Nov, 19:41


Live stream finished (1 hour)

BikuZega - ብቁ ዜጋ

08 Nov, 17:55


Live stream started

BikuZega - ብቁ ዜጋ

07 Nov, 13:07


በጉርምስና እድሜ ካሉ ልጆች ጋር እንዴት መግባባት እንችላለን?

ልጆት በጉርምስና እድሜ ላይ ናቸው? መግባባትስ ተቸግረዋል? የባህሪውን ማያቁት ልጅ ሆነው ተቸግረዋል? ኑ ስለልጆቻችን እንወያይ፣

ከወ/ሪት በረከት ደስታ ጋር በጉርምስና እድሜ ካሉ ልጆች ጋር እንዴት መግባባት እንደምንችል የምንወያይ ይሆናል።

በዚህ ፖድካስት ላይ የጋበዝናት በረከት ደስታ በባዮሎጂ የባችለር ዲግሪ እና በወጣቶች ሚኒስቲሪ እና የትምህርት አመራር ሁለት ማስተርስ ዲግሪ ያለት ሲሆን ከህጻናት ማሳደጊያ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድረስ በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች በመምህርነት ሰፊ ልምድ ያለት። በአሁኑ ጊዜም የባህርይ እድገት አስተማሪ፣ የተማሪ አማካሪ፣ እና ለወጣቶች እና ለአደጊ ልጆች የግል አማካሪ ሆና ታገለግላለች። በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች የሚያጋጥሟቸውን አካላዊ፣ አእምሯዊና የሆርሞን ለውጦች ለይቶ በማወቅና በማስተካከል ላይ ያተኮረ ስራ ትሰራለች። ከትምህርቷ በተጨማሪ ለወጣቶች ደህንነት በመተባበር ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በትጋት ታሠለጥናለች።

በዚህ ፖድካስት ላይም በሰፊው በብዙ ርዕሶች ላይ እንወያያለን እናንተንም እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

ተጋባዥ
▪️ወ/ሪት በረከት ደስታ

አዘጋጅ እና አቅራቢ
▪️ብፅት ኤልያስ እና
▪️ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው

ሆልስቲክ ኪድስ (Holistic Kids) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ።


🗓 አርብ ጥቅምት 29
⏱️ማታ ከ3:00 - ከ4:30

#BikuZegaPodcast

@BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

25 Oct, 19:35


ልጆችን በጥናታቸው እንዴት እንርዳቸው?

BikuZega - ብቁ ዜጋ

25 Oct, 19:33


Live stream finished (1 hour)

BikuZega - ብቁ ዜጋ

25 Oct, 18:09


https://t.me/BikuZega?livestream=02a6c13d2b77efffd9

BikuZega - ብቁ ዜጋ

25 Oct, 17:59


Live stream started

BikuZega - ብቁ ዜጋ

25 Oct, 17:59


ልጆቻችንን በጥናታቸው እንዴት እንደምንረዳቸው የምናደርገው ውይይት ከጥቂት ደቂቃ ባኃላ ይጀምራል ተከታተሉን

BikuZega - ብቁ ዜጋ

24 Oct, 13:21


ልጆች እንዴት ማጥናት አለባቸው፣ በትምህርታቸውስ እንዴት ጎበዝ መሆን ይችላሉ?

ልጆቾዎ በትምህርት ውጤታማ እንዲሆኑ እና ውጤታማ የአጠናን ዘዴ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ?  ከአቶ በረከት ያኪም ጋር ተማሪዎች እንዴት ጎበዝ ተማሪ መሆን እንደሚችሉና ውጤታማ የአጠናን ዘዴ ማጥናት እንዳለባቸው የምንወያይ ይሆናል።

በዚህ ፖድካስት ላይ የጋበዝነው በትራንስፎርሜሽናል አመራር ማስተርስ ያለው አቶ በረከት ያኪም ሲሆን በዚህ ፖድካስት ላይም በሰፊው በብዙ ርዕሶች ላይ እንወያያለን እናንተንም እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

ተጋባዥ
▪️አቶ በረከት ያኪም

አዘጋጅ እና አቅራቢ
▪️ብፅት ኤልያስ


🗓 አርብ ጥቅምት 15
⏱️ማታ ከ3:00 - ከ4:30

#BikuZegaPodcast

@BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

21 Oct, 04:55


የሕፃናት እድገት ላይ ወሳኝ ከሆኑት ነገሮች አንዱ መንፈሳዊ እድገት ነው። ልጆችን መጸለይን ማስተማር በህወታቸው ውስጥ ትልቅ ሚና አለው። ከሃይማኖታዊ ትርጉሞቹ ባሻገር፣ ጸሎትን መረዳት ልጆች ለአጠቃላይ ደህንነታቸው እና ለግል እድገታቸው የሚያበረክቱ ጠቃሚ የህይወት ክህሎቶችን ይሰጣል።

ልጆችን ስለ ጸሎት ማስተማር ለምን አስፈላጊ ነው?
♦️ከ ፈጣሪ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠነክሩ
♦️ስሜታቸውን እንዲገልጹ እድልን ይከፍታል። ይህም በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ጽናትን ይሰጣቸዋል።
♦️ስለሌሎች እንዲያስቡ፣ ርህራሄን እና የማህበረሰብ ስሜትን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።
ጸሎት እንደ ደግነት፣ ታማኝነት እና ምስጋና ያሉ ዋና እሴቶችን ያጠናክራል፣ ይህም ልጆች ጠንካራ የስነምግባር መሰረት እንዲያዳብሩ ይረዳል።
♦️ልጆች እራሳቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ እና እራሳቸውን እንዲያውቁ ይረዳቸዋል።
♦️ልጆችን በአዎንታዊ እይታ የህይወትን እርግጠኛ አለመሆን እንዲመሩ ይረዳቸዋል።

ወላጆች፣ አስተማሪዎች እና ተንከባካቢዎች፣ ልጆች ጸሎትን ከህይወታቸው ጋር እንዲያዋህዱ መምራት እንችላለን። ቀጣዩ ትውልድ በጸሎት ልምምድ ጥንካሬን፣ ዓላማን እና ግንኙነትን እንዲያገኝ እናበረታታ።

ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው (ጠቅላላ ሀኪም እና ሁለንተናዊ የህጻናት እድገት ባለሞያ)

Join 👇🏻

telegram:- https://t.me/currrrrrr99

Tik tok:- https://www.tiktok.com/@dr.tumim.getachew?_t=8mDNslc442P&_r=1

Facebook:- https://www.facebook.com/Drtumim?mibextid=LQQJ4d

BikuZega - ብቁ ዜጋ

13 Oct, 06:58


በቆስጣ ፣ በካሮትና በዶሮ ስጋ የሚዘጋጅ ለልጆች ምሳ ለት/ቤት የሚቋጠር

ግብዓቶች ለ2 ልጆች


▪️150 ግራም የዶሮ ሥጋ አጥንቱ የወጣ
▪️2 መለስተኛ ካሮት
▪️4 ቅጠል ቆስጣ
▪️½ ቀይ የፈረንጅ ቃሪያ ከተገኘ(በ 1 ቲማቲም መተካት ይቻላል)
▪️1 አነስተኛ ቀይ ሽንኩርት
▪️2 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት (እንደአስፈላጊነቱ )
▪️ሩብ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ዝንጅብል
▪️1 የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ ሮዘማሪ ቅጠል
▪️ቁንጥር ጨው
▪️ቁንጥር ቁንደ በርበሬ
▪️ሩብ የሻይ ማንኪያ እርድ
▪️2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
▪️ውሃ እንደአስፈላጊነቱ

አዘገጃጀት
▪️የዶሮ ስጋውን አጥቦና ጠፈፍ ሲል በስሱ መክተፈ
▪️አትክልቶቹን በሙሉ አጥቦ ከትፎ ማዘጋጀት
▪️ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርቱን ልጦ መክተፍ
▪️ቆስጣውን ግንዱንና ቅጠሉን ለየብቻ ከትፎ ማዘጋጀት
▪️መጥበሻ ወይም ድስት በመካከለኛ ሙቀት ለኩሶ ዘይት
▪️መጨመርና የዶሮ ስጋውን ቡናማ እስኪሆን መጥበስ

▪️ካሮቱ፣ ዝንጅብል፣ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርቱንና የተከተፈውን የቆስጣውን ግንድ አከታትሎ ጨምሮ እርዱን መጨመርና ለ 5 ደቂቃ ያክል መጥበስ

▪️እንደአስፈላጊነቱ ውሃ ጠብ ማድረግ አስከትሎም የቆስጣ ቅጠሉን፣ ቃሪያውን ( ቲማቲሙን)ና ሮዘማሪ ቅጠሉን ጨምሮ ቀጣይ 3 ደቂቃ ማብሰል

▪️በመጨረሻም በጨውና ቁንዶ በርበሬ አጣፍጦ ከምድጃው ማውጣት
▪️በአትክልትና በዶሮ የተዘጋጀውን ምግብ በተቀቀለ ሩዝ፣በመኮረኒና በፓስታ ማቅረብ ወይም ለት/ቤት መቋጠር ይቻላል።


ማሳሰቢያ ፡
- ምግብ ከማዘጋጀታችን በፊት እጃችንን በደንብ መታጠብ ይኖርብናል፣
- የምንሰራበት ቦታና የምንጠቀምባቸው እቃዎች ንጹህ መሆን አለባቸው።


@BikuZega #HealthyCooking

BikuZega - ብቁ ዜጋ

04 Oct, 17:36


ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ የነበረን ውይይት እንግዳችን ካቅም በላይ በሆነ ችግር ስለገጠመው ወደ ሚቀጥለው አርብ ያዘዋወርነው መሆኑን በታላቅ ይቅርታ እናስታውቃለን። እናመሰግናለን።

BikuZega - ብቁ ዜጋ

03 Oct, 14:32


ልጆች እንዴት ማጥናት አለባቸው፣ በትምህርታቸውስ እንዴት ጎበዝ መሆን ይችላሉ?

ልጆቾዎ በትምህርት ውጤታማ እንዲሆኑ እና ውጤታማ የአጠናን ዘዴ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ?  ከአቶ በረከት ያኪም ጋር ተማሪዎች እንዴት ጎበዝ ተማሪ መሆን እንደሚችሉና ውጤታማ የአጠናን ዘዴ ማጥናት እንዳለባቸው የምንወያይ ይሆናል።

በዚህ ፖድካስት ላይ የጋበዝነው በትራንስፎርሜሽናል አመራር ማስተርስ ያለው አቶ በረከት ያኪም ሲሆን በዚህ ፖድካስት ላይም በሰፊው በብዙ ርዕሶች ላይ እንወያያለን እናንተንም እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

ተጋባዥ
▪️አቶ በረከት ያኪም

አዘጋጅ እና አቅራቢ
▪️ብፅት ኤልያስ


🗓 አርብ መስከረም 24
ማታ ከ3:00 - ከ4:30

#BikuZegaPodcast

@BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

27 Sep, 07:22


እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሣችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!

መልካም የመስቀል በዓል!
Happy Meskel Holiday!


ጅምላዞን ትሬዲንግ

BikuZega - ብቁ ዜጋ

24 Sep, 05:34


ልጆች የስክሪን ጊዜ

ልጆች  እንዳይረብሹ ስልክ፡ ታብሌት መስጠት፡ ቴሌቪዥን መክፈት እከንደመፍትሄ  የሚታየው በሁሉም ሰው ቤት ሆኗል።የስክሪን ጊዜ በልጆች በእድገታቸው ላይ ያለው ተፅዕኖ ምንድን ነው? ጥቅሙስ ምንድን ነው? በምን አይነት መልኩ እንፍቀድላቸው?

የስክሪን ጊዜ ምን ማለት ነው?

የስከክሪን ጊዜ ማለት ህፃናት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ማለትም እንደ ቴሌቪዥን ስልክ ታብሌት ኮምፒውተር ላይ የሚያሳልፉት ጊዜ ማለት ነዉ ።

ለምን ያህል ሰአት ይጠቀሙ?

- ከ 2አመት በታች ለስክሪን መጋለጥ የለባቸውም!
- ከ2-5 አመት ከ1 ሰአት ያልበለጠ በወላጅ የተመረጠ !
- ከ6-17አመት  ከ2 ሰአት ያልበለጠ በወላጅ የተመረጠ!

የስክሪን ጊዜ ሲጨምር ጉዳቱ ምንድን ነዉ ?

- የቋንቋና የንግግር ብቃታቸው ይቀንሳል
- የትምህርት አቀባበል ብቃታቸው ይቀንሳል
- ጨረሩ የአይን ጉዳት ሊያመጣ ይችላል
- የእንቅልፍ ሰአት መዛባት
- ስሜትና እራስን መቆጣጠር አለመቻል
- ወጣ ያለ ባህሪ ማሣየት
- የአመጋገብ ስርአት መስተጓጐል
- የሰውነት እድገትና ክብደት ላይ ተፅእኖ ይፈተጠራል
- አእምሮአቸው ላልዳበረበትና መረዳት ለማይችሉት የተለያዩ ነገሮች ይጋለጣሉ።

በቂ የስክሪን ጊዜ ጥቅም ምንድን ነው?

- ለትምህርታቸው እንደ አጋርነት ያገለግላል።
- ለወደፊቱ በ ቴክኖሎጂ ላይ ፍላጎት ላላቸው ልጆች ብዙ እውቀት ያስጨብጣል።
- በአንዳንድ "Game" ጫዋታዎች የተለያዩ ችሎታዎችን እንዲያዳብሩ ይረዳል።

እንዴት እንቆጣጠራቸው?

1)
  ወላጆች ለ Digital and Electronic ያላቸውን እውቀት ማሳደግ አለባቸው። ከልጆቻቸው በተሻለ ወይም ቢያንስ የነሱን ያህል ሊያውቁ ይገባል።

2)  ወላጆችረ ለልጆች ጥሩ ምሳሌ ሊሆቸው ይገባል።

3)  እንዴትና ምን ማየት እንዳለባቸው አስቀድመው አይተው ሊወስኑላቸው ይገባል።

4)  የአጠቃቀም ህጎችን ለልጆች ማውጣት አለባቸው

5)  ጥቅሙንም ጉዳቱንም በደንብ በግልፅ መነጋገር አለባቸው::

6) ሌላ ጫዎታዎችን የሚጫወቱበት መንገድ ማዘጋጀት ለምሳሌ በቤት ውስጥ የስእል፡ የሙዚቃ ፡ የተለያዩ  ክሂሎት ሊያዳብሩ የሚችሉበትን መጫወቻዎች በማዘጋጀት : የሰውነት እንቅስቃሴዎችን በማሰራት የስክሪን ጊዜን መቀነስ ይቻላል።

ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው ( ጠቅላላ ሀኪምና ሁለንተናዊ የህፃናት እድገት ባለሞያ)

[ ይኽ መልዕክት @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ዘወትር #ሐሙስ ለወላጆች የሚያቀርብ ትምህርት ነው። ]

t.me/tikvahethmagazine

BikuZega - ብቁ ዜጋ

06 Sep, 20:01


Live stream finished (2 hours)

BikuZega - ብቁ ዜጋ

06 Sep, 17:58


ልጆቻችንን የፆታ ጥቃት እንዴት እንከላከል በሚል የምናደርገውን ውይይት ይቀላቀሉን።

BikuZega - ብቁ ዜጋ

06 Sep, 17:54


Live stream started

BikuZega - ብቁ ዜጋ

06 Sep, 12:26


ኑ እንወያይ!
—————————————————
ልጆቻችንን ከፆታ ጥቃት እንዴት እንከላከል?

በዚህ ሳምንት በብቁ ዜጋ ፖድካስት እንዴት ልጆቻችንን ከፆታ ጥቃት መከላከል እንችላለን የሚለውን ከ እናንተ ከ ቤተሰቦቻችን ጋር እንወያያለን ሃሳብም እናንሸራሽራለን።

በዚህ ፖድካስትም ብፅት ኤልያስ እና ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው እብረውን ይኖራሉ። እናንተንም በዚህ ውይይት ላይ እንድሳተፉ እና እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

አዘጋጅ እና አቅራቢ
▪️ብፅት ኤልያስ እና ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው


🗓 አርብ ጷግሜ 1
ማታ ከ3:00 - ከ4:30

#BikuZegaPodcast
@bikuzega

Tik tok:- https://www.tiktok.com/@dr.tumim.getachew?_t=8mDNslc442P&_r=1

telegram:- https://t.me/currrrrrr99

Facebook:- https://www.facebook.com/Drtumim?mibextid=LQQJ4d

BikuZega - ብቁ ዜጋ

05 Sep, 14:38


ኑ እንወያይ!
—————————————————
ልጆቻችንን ከፆታ ጥቃት እንዴት እንከላከል?

በዚህ ሳምንት በብቁ ዜጋ ፖድካስት እንዴት ልጆቻችንን ከፆታ ጥቃት መከላከል እንችላለን የሚለውን ከ እናንተ ከ ቤተሰቦቻችን ጋር እንወያያለን ሃሳብም እናንሸራሽራለን።

በዚህ ፖድካስትም ብፅት ኤልያስ እና ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው እብረውን ይኖራሉ። እናንተንም በዚህ ውይይት ላይ እንድሳተፉ እና እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

አዘጋጅ እና አቅራቢ
▪️ብፅት ኤልያስ እና ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው


🗓 አርብ ጷግሜ 1
ማታ ከ3:00 - ከ4:30

#BikuZegaPodcast

@BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

04 Sep, 04:46


🌻🌻አዲሱ ዓመት
80 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለ80 ሰው ግን ጌጥ ነው😀

በዓሉን ወላጆች አብረዋቸው ለማያሳልፉ ልጆች ዛሬ .... አሁን ምላሽ እንስጥ......
😀 ስንት ቲሸርት ይችላሉ?
😆 ዳቦ መድፋት እችላለው?
😃 የአንድ/የሶስት ዳቦ ዋጋ እችላለሁ?
ሌሎችንም መምረጥ ይቻላል😇😇

በህፃናቱ ስም እናመሰግናለን!!🙏👐🙏

ምን ይችላሉ

BikuZega - ብቁ ዜጋ

02 Sep, 11:56


ሩዝ በሙዝና በአቮካዶ የሚዘጋጅ ምግብ (ከ6-8 ወር ላሉ ህፃናት)

ግብዓቶች

▪️1 ኩባያ ሩዝ
▪️1/2 አቮካዶ
▪️1/2 ሙዝ
▪️1 ኩባያ የጡት ወተት ወይም የህፃናት ወተት
 
አዘገጃጀት

▪️በመጀመሪያ ሩዙን በደንብ ማጠብና መቀቀል
▪️በመቀጠል ሙዙንና አቮካዶውን በደንብ አጥቦ በትንንሹ መቆረረጥ ፣ በመጨረሻም ተቀቅሎ የቀዘቀዘውን ሩዝ ሙዝና አቮካዶ አንድ ላይ መፍጫ ውስጥ በመጨመር በወተት በደንብ መፍጨትና ማቅረብ።

▪️መፍጫ ከሌለን በማንኪያ ወይም በሹካ በደንብ መፍጨት ይቻላል።

ማሳሰቢያ ፡
- ምግብ ከማዘጋጀታችን በፊት እጃችንን በደንብ መታጠብ ይኖርብናል፣
- የምንሰራበት ቦታና የምንጠቀምባቸው እቃዎች ንጹህ መሆን አለባቸው።


@BikuZega #HealthyCooking

BikuZega - ብቁ ዜጋ

23 Aug, 08:28


ትንታ

ከ 1 አመት በታች ያለ ልጅ ትንታ ቢያጋጥም ምን ያደርጋሉ?

ትንታ የሚፈጠረው ባእድ ነገር በአየር ቱቦ ውስጥ ገብቶ በሙሉ ወይም በከፊል የአየር ቱቦውን በሚዘጋበት ወቅት ለመተንፈስ የምናደረግው ጥረት ነው፡፡

ትንታ ሲፈጠር ኦክስጅን ወደ ሰውነት በደንብ ስለማይደርስ በህይወት ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊያመጣ ይችላል። ትን ያለው ሰው ያለማቋረጥ በማሳል በአየር ቱቦ ውስጥ የገባውን ባእድ ነገር ሊያስወጣው ይችላል፡፡

የትንታ ምልክቶች
▪️የማያቋርጥ ሳል
▪️ትንፋሽ ማጠር
▪️መናገር አለመቻል /መፍጨርጨር
▪️የከንፈርና የእጅ ጣቶች እንዲሁም የሰውነት መጥቆር (ይህም ሰውነት ውስጥ ከፍተኛ የኦከስጂን እጥረት መኖሩን ይጠቁማል)

👉🏼ከ1 አመት በታች

ከላይ በምስሉ ላይ እንደሚታየው☝️
 
▪️ህጻኑን ፊቱን ወደ ታች ዘቅዝቆ እጅ ላይ በማስተኛት አገጭንና ጭንቅላትን በመደገፍ በአንድ እጅ በውስጥ መዳፋችን ጀርባውን 5 ጊዜ መምታት
▪️ህጻኑን ፊቱን ወደ ላይ በመገልበጥ በሁለት ጣት መሀል ደረት ላይ 5 ጊዜ መግፋት
▪️ይህን ባእድ ነገር እስኪወጣ እየቀጠሉ ወደ ህክምና መውሰድ፡፡

አዘጋጅ - ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው
@currrrrrr99

@bikuZega  #BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

16 Aug, 19:00


Live stream finished (1 hour)