የዕለቱን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ አስ/ፋይ/ም/ዲን ዶ/ር ማስረሻ መኩሪያ እንደገለፁት በዚህ ስልጠና ተመሪቂዎች ወደ ሥራው ዓለም በሚሰማሩበት ወቅት በኮሌጅ ቆይታቸው እና ከዚህ ስልጠና ያገኙትን ዕውቀት በአሁኑ ጊዜ የተዘነጋውን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት ለተመግታት ማዋል እንዳለባቸው ገልፀዋል።
የኮሌጁ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና ስነ-ተዋልዶ ጉዳዮች ክፍል አስተባባሪ እንደገለጹት በዓለማችን እጅግ በርካታ ዜጎች ዛሬም ህይወታቸውን በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክንያት እያጡ ይገኛሉ፤ በመሆኑም ተመራቂዎች ከዛሬው ስልጠና ባገኙት ግንዛቤ ራሳቸውን እና ያስተማራችሁን ወገን ከዚህ ወረርሽኝ ለመከላከል ጉልሀ አስተዋጸኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል::
ስልጠናው ከገ/ፃ/ሻዎ ሆስፒታል በተጋበዘ ባለሙያ የተሰጠ ሲሆን ሁሉም የት/ክፍሉ ተማሪዎች፥የክበብ አስተባባሪ መ/ራን እንዲሁም የተማሪዎች ዲን በስልጠናው ተሳታፊ ሆነዋል::
ቦንጋ የት/ኮሌጅ
ዘወትር ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/BCE1991
ቴሌግራም፦ https://t.me/BCE1991
መምህራን ላይ መስራት ትውልድ ላይ መስራት ነው!
Investing in Teacher, Investing in future!