Mizan Aman Health science college @mahscoffical Channel on Telegram

Mizan Aman Health science college

@mahscoffical


This is an official telegram channel of MAHSC, the only public health science college in southwestern region of the country. The icon of Quality.

Mizan Aman Health Science College: Your Gateway to Quality Education (English)

Are you looking for a place that offers quality education in the field of health science? Look no further, as Mizan Aman Health Science College (MAHSC) is here to provide you with top-notch education and training in the southwestern region of the country. As the only public health science college in this area, MAHSC prides itself on being the icon of quality when it comes to education. With a team of dedicated faculty members and state-of-the-art facilities, MAHSC is committed to preparing students for successful careers in the healthcare industry. Join our official Telegram channel, @mahscoffical, to stay updated on the latest news, events, and announcements from MAHSC. Whether you are a current student, an alumni, or someone interested in pursuing a career in health science, this channel is the perfect platform to connect with the MAHSC community and stay informed about all the happenings at the college. Get access to exclusive resources, participate in engaging discussions, and interact with fellow students and faculty members on our Telegram channel. Stay connected with MAHSC and be a part of our journey towards excellence in health science education. Join us today and experience the difference at Mizan Aman Health Science College. Your gateway to quality education awaits at MAHSC! }

Mizan Aman Health science college

30 Sep, 07:30


Urgent Notice

Mizan Aman Health science college

16 Sep, 19:09


6/1/2015 ዓ.ም
በዛሬው ዕለት ኬሞኒክስ (Chemonics, USAID Global Health Supply Chain Program) አስር (10) GX ማይክሮስኮፕ ድጋፍ አድርጎልናል። ይህ የማይክሮስኮፕ ድጋፍ በኮሌጃችን ለሚማሩ የዲግሪና የደረጃ IV ሜዲካል ላብራቶሪ ተማሪዎች ለሚያደርጉት የተግባር ልምምድ ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል።
ኬሞኒክስን እና ይህ ድጋፍ እንዲሳካ ያደረገውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮን እናመሰግናለን።
የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

Mizan Aman Health science college

15 Sep, 09:25


Urgent Notice !!

Mizan Aman Health science college

15 Jul, 18:40


ሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 8/11/2014 ዓ.ም
የኮሌጁ አካዳሚ ኮሚሽንና አስተዳደር አካላት ጋር የጋራ ምክክርና ዉይይት ተካሄዷል።
***************************
የኮሌጁ አካዳሚ ኮሚሽንና አስተዳደር አካላት የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ የተወያየ ስሆን በዋናነት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ለማስቀጠል እያንዳንዱ የባለድርሻ አካላት (መምህራን ,አካዳሚ ኮሚሽኑ የኮሌጁ አስተዳደር አካላት ወዘተ ...) እንደት ሚናውን ስወጣ ነበረ፣ ለቀጣዩስ እንደት መሆን አለበት በምሉ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል ።
ኮሌጁ የትምህርት ተቋም እንደመሆኑ በ2014ዓ.ም በኮሌጁ ስካሄዱ በነበሩት የተለያዩ ተግባራቶች ላይ ስስተዋሉ የነበሩትን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ለመለየት ተችሏል። የነበሩትን ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል እንዳለበት መተማመን ላይ የተዳረሰ ስሆን, ነገር ግን በተለያዩ የሥራ ሂደቶችና የትምህርት ክፊሎች ላይ እየተስተዋሉ ያሉትን ክፊተቶችንና ደካማ ጎኖችን በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው መተማመን ላይ የተዳርሰ ስሆን ለነበሩት ክፊተቶች የተለያዩ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የጋራ መግባባት ላይ ተዳርሷል።

Mizan Aman Health science college

02 Jun, 07:38


ሚ/አ/ጤ/ሳ/ኮ 25/9/2014

የወባ በሽታ ወረርሽንን እንግታ !

በዞናችን ዉስጥ ወረርሽኝ ሆኖ የህዝባችንን ጤንነት ለከፋ ችግር እንድሁም ለሞት እየዳረገ ያለዉን የወባ ወረርሽንን ለመከላከል የሚ/አ/ጤ/ሳ/ኮ የትምህርት ተቋም እንደመሆኑ ኮሌጁ የተለያዩ ግብረ ሃይሎችን በማቋቋም የተለያዩ ተግባሮችን ለማከናወን የተነሳ ስሆን በዋናነት የመከላከያ ዘደዎችን በማስተማር እንድሁም በተግባር ለማሳየት ከተለያዩ ት/ት ክፊል ከተወጣጡ መምህራን:የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎችን በማካተት ወደ ህብረተሰብ ዘንድ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ስለሆነም ህብረተሰቡ የኮሌጁ ማህበረሰብ እየሰጡ ያለዉን የግንዛቤ ት/ትን ተግባራዊ በማድረግ ራሳቸውንና ቤተሰባችሁን ከወባ በሽታ እንድትከላከሉ እናሳስባለን ።

ዋና ዋና የወባ መከላከያ መንገዶች

1- አጎበርን በአግባቡ መጠቀም

2-አጎበርን ማጠብ

# አጎራባችሁን በየአራት ወሩ በልብስ ሳሙና እጠቡት። በጥላ ውስጥ በመስቀል ወይም በማስጣት እንድደርቅ አድርጉት ።

3- ህክምና ማግኘት
# በማንኛውም ጊዜ የትኩሳት ስሜት ስኖራችው በፊጥነት ባቅራቢያችዉ ወደ ሚገኝ የጤና ተቋም መሄድ።

4-ፀረ-ወባ መድሀኒት መዉሰድ
# መድሀኒቱን በታዘዘው ልክ መዉሰድ
# መድሀኒቱን ማቋረጥ ወይም ለሌላ ሰዉ ማካፈል የለበትም ።

5- የፀረ -ወባ ኬሚካል ማስረጨት
# የፀረ ወባ ከሚካል የተረጨዉን ግድግዳ ለ6 ወራት በእበትም ሆነ በጭቃ አትለቅልቁ፣ ወረቀትም አትለጥፉባቸው ።

6- የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ማዳፈን
# በመኖሪያ አካባቢ የሚገኙ ዉሃ የሚይዙና የማይጠቅሙና ቁሳቁሶችን ማፅዳት፣ረግረጋማ ቦታዎችን ማፋሰስ ወይም ማዳፈን ያስፈልጋል።