ጤናዎ በእጅዎ @ba051219 Channel on Telegram

ጤናዎ በእጅዎ

@ba051219


ጤናዎ በእጅዎ (Amharic)

ይህ የቴሌግራም ቻናሎች በፊትና በነፃ ለሴቶች በትኩረት እንዲሰጡ ሊያገኙ ነው። 'ጤናዎ በእጅዎ' ላይ የሚኖሩ ጥቅሶች እና አካባቢዎች በነገር እየተረፈ እንደመሆኑ ሲከተሉ በተጎደፍሁበት ማውረድ ስለሚጠናቀቅ መረጃ፣ ሊምሰጎበት ፈልጉን እንዲያውቁ ሊናገሩ ይገባል። ስለዚህም ይህ ባለፈው ቻናሉ በእናንተና በሴቶች ባለመረኳዳ እንጠቀሙ፡፡

ጤናዎ በእጅዎ

13 Feb, 08:41


6. #ለቆዳ_ጤና_ጠቃሚ_ነው
====
ሙዝ የቫይታሚን ሲ እና አንቲኦክሲዳንትስ የበለፀገ ምንጭ ነው፣ ይህም የቆዳ ጤናን ይደግፋል እና የቆዳ እድሜን ይቀንሳል ። 

7. #ለአዕምሮ_ጤና_እና_ስሜት_ማሻሻያ 
ሙዝ ትሪፕቶፋን ይዟል፣ ይህም ወደ ሴሮቶኒን ይቀየራል፣ ይህም ስሜትን ያሻሽላል እና የአዕምሮ ጤናን ይደግፋል። በተጨማሪም፣ ቫይታሚን B6 የአዕምሮ እንቅስቃሴን ያሻሽላል ። 


#ማሳሰቢያ
ሙዝ በጤና ላይ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ፍሬ ነው። ከልብ ጤና እስከ አንጀት ጤና፣ ከክብደት እርግጠኛነት እስከ አዕምሮ ጤና ድረስ የሚያበረታታ ነው። በዕለት ተዕለት አመጋገብ ውስጥ ሙዝን ማካተት የጤና ጥቅሞችን ለማግኘት ቀላል እና ውጤታማ መንገድ ነው።

ምንጭ:
Health line

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

13 Feb, 08:41


#የሙዝ_የጤና_በረከቶች
======
የሙዝ የጤና በረከቶች በሰፊው ይታወቃሉ፣ እና ይህ ፍራፍሬ በተለያዩ የአካል እና የአዕምሮ ጤና ጥቅሞች የበለፀገ ነው።
ከዚህ በታች የሙዝ ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች ተዘርዝረዋል።

1. #ለልብ_ጤና_ጠቃሚ_ነው
====
ሙዝ ፖታሲየም የበለፀገ ምንጭ ነው፣ ይህም የደም ግፊትን ለመቆጣጠር እና የልብ ሕመምን ለመከላከል ይረዳል። ፖታሲየም የደም ሥሮችን ያለማለቅ እና የሶዲየምን ተጽእኖ ያሳካል፣ ይህም የልብ ጤናን ይደግፋል ።

2. #ለጡንቻ_እንቅስቃሴ_እና_ማገገም
=====
ሙዝ በስኳር እና ፋይበር የበለፀገ ሲሆን፣ በተለይም ከስራ በኋላ ለሰውነት ኃይል ማደስ እና የጡንቻ ማገገም ይረዳል። ፖታሲየም እና ማግኒዚየም የኤሌክትሮላይትስን ያሟላሉ፣ ይህም የጡንቻ ማጥረሻን ይቀንሳል ።

3. #ለአንጀት_ጤና_ጠቃሚ_ነው
====+
ሙዝ የሚያበረታታው ፋይበር የምግብ መፈጨትን ያሻሽላል፣ የምግብ መፈጨት ስርዓትን ያስተካክላል፣ እና የምግብ መፈጨት ችግሮችን ይቀንሳል።

4.#ለክብደት_እና_የስኳር_መጠን_ለማስተካከል
====
ሙዝ የስኳር መጠንን በማስተካከል እና የስኳር መጠን እርግጠኛነትን በማስተካከል ይረዳል። የሙዝ ፋይበር የስኳር መጠንን በማስተካከል እና የስኳር መጠን እርግጠኛነትን በማስተካከል ይረዳል ።

ጤናዎ በእጅዎ

11 Feb, 05:33


#ድንገት #በእባብ #ብንነደፍ #ምን #ማድረግ #አለብን?
""""""""""""""""""  """""""""""""""" """""""
✳️ አብዛኛዎቹ እባቦች መርዛማ አይደሉም፡፡ ይሁንና እባቦች መርዛማና መርዛማ ያልሆኑ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡ መርዛማ እባቦች ፋንግ የሚባሉ መርዝ የሚረጩባቸው ሁለት ትላልቅ ጥርሶች በላይ በኩል አሏቸው፡፡ በተነከሰበት ቦታ ላይ ከሌሎች ጥርሶች በጣም የተለዩ ሁለት ትላልቅ ምልክቶች ይተዋል፡፡ ስለሆነም  መውሰድ ያለበት እርምጃ እንደሚከተለው ይሆናል፤

ተነዳፊው ሰው ፀጥ ብሎ የተነከሰውን የአካል ክፍል ሳይንቀሳቀስ ይቀመጥ፡፡ ካስፈለገም በቃሬዛ ( በአልጋ) ማንቀሳቀስ እንጂ  በእግሩ ትንሽም ቢሆን ባይጓዝ መልካም ነው፡፡ ይህም መርዙ በአካሉ ውስጥ እንዳይሰራጭ ለማድረግ ይረዳል፡፡

የተነደፈውን አካል  ወደ ታች ዝቅ አድርጎ መያዝ መርዙ ቶሎ ወደ ሰውነት እንዳይሰራጭ ይረዳል፡፡

ቆዳውን ቶሎ በውሃ በሚገባ ማጠብ፡፡

በረዶ ከተገኘ በተነከሰው የአካል ክፍል ላይ በጨርቅ ጠቅሎ ማስቀመጥ፡፡

የኢንፌክሽን ምልክት ካሳየ አምፒሲሊን፣ቴትራሳይክሊን ወይም ሌላ አንቲባዮቲክ መጀመር ይገባል፡፡ ካልተሻለው ወደ ሕክምና ተቋም መውሰድ፡፡

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

07 Feb, 18:45


#የዶ/ር #አንዷለም_ዳኘን #ቤተሰቦች #መርዳት_ለምትፈልጉ
=====
#የጥምር_ሂሳብ_ቁጥር_ስም:-

1- ዶ/ር ኃይለማርያም አወቀ እንግዳው
2- ዶ/ር አምሳሉ ወርቁ መኮንን
3- ዶ/ር መኳንንት ይመር አድማሴ

የጥምር ሂሳብ ቁጥር:-

1. የንግድ ባንክ= 1000 676 116 978
2. የአዋሽ ባንክ= 013 200 903 947 800
3. የአቢሲኒያ ባንክ= 218 081 487
4. የአማራ ባንክ= 9900 037 383 825

ጤናዎ በእጅዎ

07 Feb, 13:33


#ምክንያቶች
=====
1. የድስክ ስርዓት ችግር (Herniated Disc): በጀርባ ውስጥ ያሉ ድስኮች (Discs) ሲንሸራተቱ ወይም የመቆጣት ስሜት ሲኖራቸው ሲያቲክ ነርቭ ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ::

2. የአከርካሪ አጥንት ጥበት (Spinal Stenosis): ከቅንጭላት የሚመጡ ነርቮች የሚወጡበት የጀርባ አከርካሪ አጥንት ሲጠበብ ሲያቲክ ነርቭ ላይ ጫና ያሳድራል።

3. የጡንቻ መሸማቀቅ (Muscle Strain): በጀርባ ወይም በጉልበት ውስጥ ያሉ ጡንቻዎች ሲጎዱ ሲያቲክ ነርቭ ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ።

4. ሌሎች ምክንያቶች: እንደ የጀርባ አከርካሪ አጥንቶች አደጋ፣ የመቀመጫ አጥንት ችግሮች፣ አንዳንዴም በእርግዝና ወቅት በሚፈጠር የጀርባ አከርካሪ ጫና እንድሁም በመርፌ መድሀኒት ሲሰጡ በድንገት ነርቩ ከተወጋ።

#ህክምና
====
1.#የተለመዱ_እና_የሚታወቁ_መድሃኒቶች_መውሰድ

   - ህመም ማስታገሻዎች (Pain Relievers) መውሰድ ለምሳሌ አይቡፕሮፌን (Ibuprofen) ወይም ናፕሮክሰን (Naproxen)።
   - የነርቭ ህመም ለማከም መድሃኒቶች (Gabapentin ወይም Pregabalin)።
   - በከባድ ሁኔታዎች ውስጥ የስቴሮይድ መድሃኒቶች (Steroids)።

2. #የአካል_ብቃት_እንቅስቃሴ ስራ (Physical Therapy):

   - የጀርባ አንገት እና የጉልበት ጡንቻዎችን ለማጠናከር የሚያገለግሉ ልምምዶች።

3. #በከባድ ሁኔታዎች እንዳስፈላጊነቱ :
   - ቀዶ ሕክምና (Surgery) ለምሳሌ :የድስክ መንሸራተት ሲኖር
            :የጀርባ አከርካሪ አጥንቶች ጥበት ሲኖር

#መከላከል
===
1. ትክክለኛ የሰውነት አቀማመጥ (Posture): በተለይ በተቀመጥበት ወይም በቆመበት ጊዜ።

2. የአካል ብቃት ልምምድ: የጀርባ አንገት እና የጉልበት ጡንቻዎችን ማጠናከር።

3. ከባድ ነገሮችን ከመስራት መቆጠብ: በትክክል የማይሰሩ የአካል ብቃት ልምምዶችን ማስቀረት።

#ማስታወሻ

የሲያቲካ ህመም በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት ቢሆንም፣ በአብዛኛው ጊዜ በትክክለኛ ሕክምና እና በአካል ብቃት ስራ ሊታከም ይችላል። ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ወደ የሕክምና ባለሙያ መሄድ አለባቸው።

=====

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

07 Feb, 13:33


#ከባዱ_የነርቭ_ህመም((#የሲያቲካ_ህመም )
====
የሲያቲካ ህመም(sciatica pain) በሲያቲክ ነርቭ (Sciatic Nerve) ላይ የሚከሰት ህመም ነው።
ይህ ነርቭ ከበታች የጀርባ አንገት (Lower Back) ጀምሮ በእግር ውስጥ እስከ ጣቶች ድረስ የሚዘረጋ ትልቅ ነርቭ ነው።

የሲያቲካ ህመም ብዙውን ጊዜ በአንድ ወገን (አንድ እግር) ላይ ይሰማል፣ እና ከቀላል እስከ ከባድ ህመም ሊሆን ይችላል።

#ምልክቶች
====
1. የጀርባ እና የዳሌ ህመም:
ህመሙ ከበታች የጀርባ አንገት ጀምሮ በእግር ውስጥ ወደ ታች ይዘረጋል።
ከዳሌ ጀምሮ ወደ ታች ወደ ጉልበት የሚነዝር ህመም የህመም ስሜት ይኖረዋል
2. በእግር ውስጥ ህመም: ብዙውን ጊዜ በአንድ እግር ውስጥ ይሰማል፣ እና ከጉልበት ጀምሮ እስከ ጣቶች ድረስ ሊዘረጋ ይችላል።

3.ንዝረት ወይም እብጠት: በእግር ውስጥ የሚሰማ የንዝረት ስሜት፣ አልፎ አልፎም የጫማ እብጠት ሊኖረው ይችላል ።
4. የእግር አጥብቆ አለመርገጥ(ደካማነት): በእግር ውስጥ የኃይል እጥረት ወይም አጥብቆ አለመርገጥ ሊያስከትል ይችላል።

5. የማቃጠል ስሜት: በእግር ውስጥ የሚሰማ ንዝረት (Tingling) ወይም የማቃጠል ስሜት (Burning Sensation)።

ጤናዎ በእጅዎ

06 Feb, 14:45


#የዓለምን_ክብረ_ወሰን_ሰበሩት🙏🙏🙏
====
ኢትዮጵያዊቷ የመቀሌ ነዋሪ እናት በ75 ዓመታቸው የወለዱት ወ/ሮ መድህን በህንዳዊቷ ወ/ሮ ኢራማቲ ማንጋማ የተያዘውን ክብረወሰን ሰብረውታል::
ህንዳዊቷ ኢራማቲ ማንጋማ በነጮቹ አቆጣጠር በመስከረም ወር 2019 G.C በ73 ዓመታቸው ሁለት መንታ ሴት ልጆችን በመውለድ ነበር ክብረ ወሰኑን ይዘውት የቆዩት።

#ክብር_ለእናቶች🙏🙏🙏

ምንጭ:የኔታ ቱዩብ


ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

03 Feb, 21:21


ወጣትና ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ከነበራቸው የዕውቀት መሻት እና ከተገነዘቡት ከፍተኛ የወገን ችግር በመነሳት የጉበት፣ የሀሞት ከረጢት እና የቆሽት ሰብ ስፔሻላይዜሽን ት/ት በአ•አ• ዩኒቨርሲቲ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተከታትለው በ2016 ዓ•ም• አጠናቀው ዕንቁ ባለሙያ ለመሆን ችለው ነበር።
ዶ/ር አንዷለም ዳኜ በተለያዩ የት/ት እርከን ሲያልፉ በተለያዩ የውጭ ሀገራት ማለትም በጀርመን፣ በእንግሊዝ፣ በህንድ፣ በደ/አፍሪካ እና በቱርክ የተለያዩ ስልጠናዎችን የወሰዱና በዚህም ከፍተኛ ከበሬታን እንዳተረፉ የሙያ አጋሮቻቸው፣ መምህሮቻቸው፣ ተማሪዎቻቸው እና ታካሚዎቻቸው ይመሰክራሉ።

በስራቸውም ደከመኝ ሰለቸኝ የማያውቁ ቅን ፣ ትሁት፣ ሰው አክባሪ አዛኝና ሩህሩህ ሐኪም ነበሩ:: ለዚህም ብዙ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ተቋማት ለቅጥር ሲያጯቸው <<የማስቀድመው፣ እየተቸገረ ያስተማረኝ ማህበረሰብ አለ>> በማለት ለሚቀርብላቸው አጓጊ ገንዘብ እና ክብር አልተንበረከኩም::
ዶ/ር አንዱዓለም ዳኜ ህዝባቸውን ለማገልገል ካላቸው ከፍተኛ ፍቅር የተነሳ የሚሰጣቸውን ኃላፊነት ሁሉ በቅንነት ፈጽመዋል:: ዶ/ር አንዱዓለም ዳኜ ሀይማኖተኛ፣ ለሰው ሁሉ መልካም አሳቢ፣ ታጋሽ፣ ደግ፣ አንደበተ ርቱዕ ነበሩ::

የቤተሰባቸውን ሁኔታ በተመለከተ ጋብቻቸውን በስርዓተ ተክሊል በታላቁ ደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም በ2006 ዓ•ም• የፈጸሙ ሲሆን ከውድ ባለቤታቸው ከወ/ሮ ቤዛየ ግርማ የስምንት ዓመትና የአምስት ወር ዕድሜ ያላቸው ሁለት ሴቶችና የአምስት ዓመት ዕድሜ ያለው አንድ ወንድ ልጅ አፍርተዋል። ለቤተሰባቸውም ፍቅር የሚሰጡ፣ እጅግ የሚናፈቁ ተወዳጅ አባት ነበሩ::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወጣቱ ሐኪም፣መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር አንዱዓለም ዳኜ ሩቅ አስበው ስራ ውለው ወደ ቤታቸው ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው መኪናቸውን እያሽከረከሩ እያለ በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ጥር 24/2017 ዓ• ም• በተወለዱ በ 37 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል::

ሥርዓተ ቀብራቸውም ቤተሰቦቻቸው፣ የሥራ ባል ደረቦቻቸው፣ ተማሪዎቻቸው፣ታካሚዎቻቸው እና ወዳጆቻቸው በተገኙበት ጥር 25 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ7:00 በባህር ዳር ከተማ በድባንቄ መካነ-ህያዋን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን እየተመኘን ፤ ነፍሳቸውን በአባቶቻችን በአብርሃም፣ በይስሀቅ እና በያዕቆብ ቦታ በአጸደ ገነት ያሳርፍልን።

የሀዘን እንጉርጉሮ
==========
በክፉ በደጉ ከፊት የሚቀድም ፣
አንዷለም አንዷለም አንዱ እንቋችን የለም።
ለጆሮ ይከብዳል ውስጥን ለማሳመን ፣
ይኸንን ሞት መስማት እንደምን ያሳዝን።
ስንቱ እየለመነህ ስንቱ እያማተረ፣
ዕንቁ ጭንቅላትህ ቆሼ ላይ አደረ፣
የወዳጅ ዘመድህ ልቡ ተሰበረ።
ሜዳሊያ ያንተ ነው ሞራልና ወርቁ፣
አንተን የሚመሰል አይገኝም ዕንቁ።
አሜሪካ አማትራህ ለምኖህ አውሮፓ፣
ለወገንህ ፍቅር በገንዘብ ሳትለካ፣
ሌት ተቀን ስትለፋ ነበር የምትረካ።
ጉበቱና ጣፊያው  ቆሽቱ ተቃጠለ፣
አንተ እምታክመው ለአንተ ሲል ቀለለ፣
ሀዘኑ ቅጥ አጣ <<ምን ልበል>> እያለ።

በዶር ዓለማየሁ ባዬ

ጤናዎ በእጅዎ

03 Feb, 21:21


የዶ/ር አንዷለም ዳኜ ጠብቀው አጭር የህይወት ታሪክ
========================

[“ሕያው ሁኖ የሚኖር፣ ሞትንስ የማያይ ሰው ማን ነው?" መዝሙር 89:48]
ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ከአባታቸው ከአቶ ዳኜ ጠብቀው እና ከወ/ሮ ደጌ ጥጉ ግንቦት 5 ቀን 1980 ዓ•ም• በምዕራብ ጎጃም ዞን ጓጉሳ ወንበርማ ወረዳ ቡራፈር ቀበሌ ተወለዱ። በወላጆቻቸው እንክብካቤ አድገው ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በቡራፈር የመጀመሪያ ደርጃ ት/ቤት፣ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሽንዲ ከተማ ሽንዲ ት/ቤት ተከታትለዋል።

ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርታቸውን በቡሬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተምረዋል። ከዚያም የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሁሉንም የትምህርት ዓይነት <<A>> በማምጣት በከፍተኛ ነጥብ አልፈዋል። ከዚያም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የላቀ ውጤት በማምጣት አጠቃላይ ከት/ቤቱ አንደኛ በመሆን አጠናቀዋል።
ከዚያም በ2000 ዓ•ም• ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ በውስን የህክምና ተማሪዎች የተያዘውን ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በ2005 ዓ•ም• የመጀመሪያ የህክምና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ የወርቅ ሜዳሊያና በዩኒቨርሲቲ ደርጃ የዋንጫ ተሸላሚ ሁነዋል።

በመቀጠልም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሌክቸረርነት ማዕረግ ተቀጥረው ከማስተማሩ እና ከምርምሩ  ጎን ለጎን የሚውዱትን የህክምና ሙያ በመተግበር እያሉ ለላቅ ብቃት ደግሞ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቀዶ ህክምና ት/ት ክፍል ውስጥ በመማር በ2011 ዓ•ም• ተመርቀው ታዋቂ የቀዶ ህክምና ሀኪም ለመሆን በቅተዋል። በተጨማሪም በበጎ አድራጎት ህክምና በተለያዩ ሆስፒታሎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ለማህበረሰባቸው ሰጥተዋል።

ጤናዎ በእጅዎ

03 Feb, 08:50


#100ሺህ_የሚሆኑ_HIV_ቫይረስ_ያለባቸው_ሰዎች_መድሀኒት_አይጠቀሙም_ተባለ!🎗

በኢትዮጵያ 100 ሺሕ የሚደርሱ በኤች አይቪ ኤድስ የተያዙ ሰዎች የመድኃኒት ክትትል እንደማያደርጉ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

በሀገር አቀፍ ደረጃ በግምት 100 ሺሕ የሚደርሱ ዜጎች በኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ተይዘው የመድኃኒት ክትትል ሳያደርጉ ይኖራሉ ተብሎ እንደሚታሰብ በጤና ሚኒስቴር የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ዴስክ ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

አሐዱም "እነዚህ ዜጎች የቫይረሱን ስርጭት እንዳያባብሱ እንደ ተቋም የመድኃኒት ክትትል እንዲያደርጉ በማፈላለግ ረገድ ምን እየሰራችሁ ነው?" ሲል በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቭ ኤድስ የመከላከል ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አብነት አሰፋን ጠይቋል፡፡

ኃላፊዋ በምላሻቸው እነዚህን ዜጎች በስፋት የት ነው የሚገኙት በሚል እቅድ በመንደፍ፤ ከፍተኛ የማህበረሰብ ክፍል የሆኑት ተለይተው በትኩረት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተረደገ ጥናትም መድኃኒቱን ከማይወስዱት ውስጥ በአብዛኛው ወይንም 18 በመቶ የሚሆኑት በሴተኛ አዳሪነት ሥራ ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

"ይህንን የምርምር ጥናት ለማድረግ መነሻ የሆነውም 'በሀገር አቀፍ ደረጃ 605 ሺሕ የሚደርሱ ዜጎች በኤች አይቪ ቫይረስ ተይዘዋል' ተብሎ ምዝገባ ቢደረግም፤ አሁን ባለው ሁኔታ 500 ሺሕ የሚደርሱ ብቻ ናቸው የመድኃኒት ክትትል እያደረጉ ያሉት" ሲሉ ወ/ሮ አብነት ተናግረዋል፡፡

ጤናዎ በእጅዎ

03 Feb, 08:50


እንደ ተቋም በተደረገ ጥናት በአፍላ ወጣት ሴቶች ላይ የበሽታው ስርጭት ወደ 3 ነጥብ 7 መድረሱን ተከትሎ፤ ይህን ለመቀነስ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አክለዋል፡፡

"ለዚህ ሥርጭት መጨመር ዋነኛ ምክንያት የሆነው ሴቶች በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ክስተቶች ተጋላጭ ስለሆኑ ነው" ሲሉም ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

"ምንም እንኳን በቫይረሱ የተያዙ ዜጎችን የመለየት ሂደቱ ፈታኝ ቢሆንም አሁን ባለው ሁኔታ 94 በመቶ በቫይረሱ የተያዙ ዜጎችን ክትትል ተደርጎ መድኃኒታቸውን በአግባቡ እየወሰዱ ነው" ያሉት ኃላፊዋ፤ "ከዚህ ውጭ የሆኑ ዜጎችም በቫይረሱ ተጠቂ ሆነው ራሳቸን ከመደበቅ  ይልቅ የመደኃኒት ክትትል ማድረግ አለባቸው" ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ጤናዎ በእጅዎ

01 Feb, 15:34


#ህክምናው
====
የወባ በሽታ ለማከም የሚያገለግሉ የሕክምና ዘዴዎች እና መድሃኒቶች አሉ፦
1. አንቲማላሪያል መድሃኒቶች:
   - አርተሚስኒን (Artemisinin) የተመሰረቱ ውህዶች (ACTs - Artemisinin-based Combination Therapies)
   - ክሎሮኪን (Chloroquine) - በአንዳንድ አካባቢዎች ብቻ ይሠራል።
   - ኩዊኒን (Quinine)
2. የተጨማሪ ሕክምና: በከባድ ሁኔታዎች ውስጥ የአንጎል ወባ ወይም የደም እጥረት ካለ የተጨማሪ ሕክምና ያስፈልጋል።


#መከላከል_መንገዶች
=====
1. የትንኝ መረብ (Mosquito Nets): በተለይ በመርጋት የተቀባ መረቦች (Insecticide-Treated Nets)።
2. የትንኝ መከላከያ ስርዓቶች: በቤት ውስጥ የትንኝ መበላሸት (Indoor Residual Spraying)።
3. መድሃኒት በመውሰድ መከላከል: ለጉዞ ወደ ወባ በሽታ የተጋለጡ አካባቢዎች ለመሄድ የሚያስፈልጉ መድሃኒቶች።
4. አካባቢን ንፅህና ማድረግ: የትንኝ መርገጫ ቦታዎችን ማስወገድ።

---

#ማስታወሻ
የወባ በሽታ የህይወት አደጋ ያለው በሽታ ነው፣ በተለይም ለሕፃናት እና ለእርግዝና ላይ ለሚገኙ ሴቶች። ስለዚህ ምልክቶች ከታዩ ወዲያውኑ ወደ የሕክምና ባለሙያ መሄድ አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም በወባ በሽታ በተጋለጡ አካባቢዎች ውስጥ የመከላከል ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋል።


ለብዙዎች እንድደርስ በቀናነት #ሸር ያድርጉት!!!

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

01 Feb, 15:34


#የወባ_በሽታ (Malaria)

በአይን በማይታዩ  ጥቃቅን ተህዋሲያን (Plasmodium) የሚመጠ እና ደምን የሚያጠቃ በሽታ ነው።

ይህ ፓራሲት በባለ ስምንት እግር ትንኝ (Anopheles mosquito) የሚተላለፍ ሲሆን፣ ይህ ትንኝ የያዘውን ፓራሳይት ወደ ሰው ሰውነት ደም በሚመጡበት ጊዜ ያስተላልፋል።

የወባ በሽታ በተለይ በሙቀት ያሉ አካባቢዎች (ለምሳሌ በአፍሪካ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ) የተለመደ ነው።

በሀገራችን ኢትዮጵያም በብዙ በረሀማ:ቆላማ እና ወይና ደጋ አካባቢዎች በብዛት ይገኛል።

#የወባ_በሽታ_ምልክቶች
====
የወባ በሽታ ምልክቶች ከተላለፈ ፓራሲት በኋላ ከ10-15 ቀናት ውስጥ ሊታዩ ይችላሉ። ዋና ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦
1. ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት (ትኩሳት)
2. ብርቱ ማቅለሽለሽ
3. ራስ ምታት
4. የጡንቻ ህመም
5. ድክመት
6. ማቅለሽለሽ እና ሙቀት በማዞር መምጣት (በተለይ በተወሰኑ የወባ ዓይነቶች)

#በከባድ_ሁኔታዎች ውስጥ የሚከተሉት ሊያስከትል ይችላል፦
====
- የቅንጭላት(አንጎል) ወባ (Cerebral Malaria)
- የደም እጥረት
- የኩላሊት ችግር
- የሳንባ ችግር


#የወባ_በሽታ_አምጭ_ተህዋሲያን_ዝርያዎች
====
የወባ በሽታ በርካታ ዓይነቶች(ዝርያዎች) አሉት፣ እነሱም፦
1. Plasmodium falciparum: በጣም ከባድ እና ህይወትን የሚያሳጣ ዓይነት።
2. Plasmodium vivax: በአንዳንድ አካባቢዎች የተለመደ፣ ነገር ግን ከPlasmodium falciparum ያነሰ ክብደት ያለው።
3. Plasmodium ovale እና Plasmodium malariae: ከባድ ያልሆኑ ዓይነቶች።

ጤናዎ በእጅዎ

01 Feb, 10:07


የሐሞት ጠጠር ሕመም ወደ ጨጓራ እና ወደ ቀኝ ትከሻና ጀርባ የመሠራጨት ባሕሪም አለው፡፡ የህመም ስሜቱ የቅባት እህል ከተመገብን በኋላ መባባስ ከጨጓራ ሕመም እንደንለየው ይረዳል፡፡
• ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
• ምግብ ያለመፈጨት እና የመክበድ ስሜት
• ማስገሳት
• ሆድ የመንፋት ስሜት
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ

ከዚህ በተጨማሪ የሐሞት መተላለፊያ ቱቦ በሚዘጋበት ወቅት/ Obstructive jaundice:
• የዓይን እና የቆዳ ቀለም ቢጫ መሆን
• ሰውነት ማሳከክ
• የሽንት ቀለም ቢጫ መሆን
• የሰገራ ቀለም መቀየር
• በሰውነት ላይ ቀያይ ነጠብጣብ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

መፍትሔው
አብዛኛውን ጊዜ ምንም ዓይነት የህመም ስሜት ስለማያስከትል የሕክምና ዕርዳታ ላያስፈልገዉ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሕመም ስሜትን ካስከተለ የቅባት ምግቦችን መመገብ ማቆም እና የሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መውሰድ ለጊዜው የሕመም ስሜትን ያስታግሳል፡፡ ዘላቂ መፍትሔውም ቀዶ ህክምና /cholecystectomy/ ነዉ።

#ከአብክመ_ጤና_ቢሮ

ለብዙዎች እንድደርስ በቀናነት #ሸር ያድርጉት!!!

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

01 Feb, 10:07


#የሐሞት_ጠጠር /Cholelithiasis
======
የሐሞት ከረጢት የሚባለው የሰውነት ክፍል ከጉበት ሥር የሚገኝ አነስተኛ ከረጢት ሲሆን ለምግብ መፍጨት ሂደት አስፈላጊ የሆነዉ የሐሞት ፈሳሽ የሚጠራቀምበት አካል ነው፡፡

የሐሞት ፈሳሽ ጨዋማ ንጥረ ነገሮችን ያዘለ ሲሆን የምንመገበዉን ቅባት እና ቫይታሚኖች እንዲፈጩ ያግዛል፡፡

የሐሞት ጠጠር እንዴት ይከሰታል?
የሐሞት ጠጠር በሐሞት ከረጢት ውስጥ ወይንም ሐሞትን ከጉበት ወደ አንጀት በሚወስዱት ቱቦዎች ውስጥ የጠጠር ክምችት ሲኖር ነዉ፡፡

ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች
• ከ40 – 50 የዕድሜ ልክ ውስጥ ያሉ ሴቶች
• ነፍሰ ጡር
• ዉፍረት
• ቅባታማ ምግቦችን ማዘዉተር
• ስኳር ህመም
• በአጭር ጊዜ ክብደትን መቀነስ ናቸዉ

የሐሞት ጠጠር ህመም ምልክቶች
ሐሞት የሚወጣበት ቱቦ በሐሞት ጠጠር በሚዘጋበት ጊዜ በቀኝ ጎናችን የላይኛው ክፍል ላይ እየመጣ የሚመለስ ወይም የማያቋርጥ የሕመም ስሜትን ያስከትላል፡፡

ጤናዎ በእጅዎ

28 Jan, 07:31


#መከላከያ #መንገዶችና #ህክምና

• እጅዎን እና እግሮትን በየጊዜው ይታጠቡ
• በተቻለወት መጠን እግርዎትን ያናፍሱ
• የቆሰለውን ጥፍርዎን ከነኩ በኋላ እጆችዎን ይታጠቡ
• ከታጠበ በኋላ ጥፍሮችዎን ያሞቁ
• በጥንቃቄ ጥፍሮችን አስተካክለው ይቁረጡ
• ላብ-መምጠጥ የሚችሉ ካልሶችን ይልበሱ
• በየቀኑ ንፁህ ካልሲ ይልበሱ
• አየር የሚያስገቡ ጫማዎችን ይምረጡ
• የቆዩ ጫማዎችን ያስወግዱ ወይም በፀረ-ተባይ መድሃኒቶች ያፅዱአቸው
• በመኝታ ክፍሎች እና ሻወር ቤት ውስጥ ጫማዎችን ይልበሱ
• መድሃኒቶች፡ በአፍ የሚወሰዱ ወይም የሚቀቡ ፀረ ፈንገስ መድሃኒቶችን እና የጥፍር ፖሊሽ ወይም ክሬም መጠቀም
• የጥፍር ቀዶ ጥገና ማድረግ።

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

28 Jan, 07:31


#የጥፍር #ፈንገስ/ Onychomycosis

የጥፍር ፈንገስ/ Onychomycosis/ የእጅ ወይም የእግር ጣት ጥፍርን የሚያጠቃ ሲሆን የጥፍርን ቀለም ወደ ነጭ፡ቢጫ ወይም ቡናማ ቀለም የሚቀይር በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ ኢንፌክሽን ነው፡፡

ከጠቅላላው ህዝብ በአማካይ10% (ከ 2 እስከ 14%) የሚሆነው በዚህ በሽታ ይጠቃል፡፡

#ምልክቶች

• የጥፍር መወፈር
• በጥፍር አካባቢ ያለ ቆዳ መድረቅ
• የጥፍር ቀለም ወደ ነጭ፡ቢጫ፡አረንገ ወይም ጥቁር ቀለም መቀየር
• የጥፍር በቀላሉ መሰባበር ወይም መፈርፈር
• የጥፍር መቁሰል እና መጥፎ ሽታ

#መንስኤዎች

• የእድሜ መግፋት፡
• በጣም ላብ መብዛት
• የእግር መቁሰል
• በባዶ እግር መሄድ በተለይም ሻወር ቤት እና መዋኛ ገንዳዎች አካባቢ
• የቆዳ ቁስል
• የስኳር በሽታ,የደም ዝውውር ችግር ወይም የበሽታ መቋቋም አቅም ማጣት

ጤናዎ በእጅዎ

27 Jan, 21:24


#እሬት #ለቆዳችንና #ለፊታችን #የሚሰጠን #ጥቅም
======
የእሬት ተክል በሚሰጠው ከፍተኛ የጤና ጥቅምና አካላዊ የውበት መጠበቂያነት የሰው ልጆች ለዘመናት ሲገለገሉበት ኖረዋል።

ሬት በውስጡ በሚገኙት ከፍተኛ የሆኑ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ይዘት በአሁኑም ዘመን በርካታ የመዋቢያ ቅባቶችን እንዲሁም የቆዳ ድርቀትን እና ፎሮፎርን ማስወገድ የሚችሉ ሳሙናዎችን፣ የቆዳ ክሬሞችን፣ የፀጉር ቅባቶችንና ሻምፖዎችን ለመስራት በስፋት ጥቅም ላይ ውሎ ይገኛል፡፡

እሬት ውስጥ የሚገኘውን ዝልግልግ ፈሳሽ በጭማቂ መልክ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ ማዋል የሚቻል ሲሆን፤ ባለው የንጥረ ነገር ይዘት ሰውነታችን ውስጥ ተጠራቅሞ የሚገኘውን መርዛማ ነገሮችን የማስወገድ እንዲሁም የቆዳ ድርቀትን አስወግዶ ወዘናን በመመለስና ያረጀውን በማደስ የወጣትነት ገፅታን ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ መመለስ የሚያስችል ትልቅ አቅም አለው፡፡

እሬት ለስውነታችችን አስፈላጊ በሆኑት ቪታሚንስ፣ፕሮቲን እና ልዩ ልዩ መዐድናት የበለፀገ ነው። ይህም በቀላሉ የአሎ ቬራን ቅጠል ብቻ በመጠቀም የቆዳችንን ጤንነት እና ውበት ለመጠበቅ ይረዳናል።

☑️ በተጨማሪም እሬት ቆዳችንን:-

💎 ከድርቀት ይከላከላል
💎 በቆዳችን ላይ የሚገኝ ብግር
💎 የቆዳችን ሴሎች በማነቃቃት ቶሎ እንዳናረጅ ይረዳል
💎 በተለያዩ ነፍሳት እና ተባይ ከተነከስን ቶሎ እንዲድን ይረዳናል
💎 በቆዳችን ላይ ያለ ቁስል ቶሎ እንዲድን ያግዘናል
💎 በቆዳችን ላይ ያለ ሸንተረር ጎልቶ እንዳይታይ ያግዛል
💎 የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ቃጠሎን ያክማል
💎 98 በመቶ የሚሆን ውሃ በውስጡ ስለያዘ ቆዳችን እርጥበት እንዲኖረው ያደርጋል
💎 በፈንገስና በባክቴሪያ መመረዝን ያክማል

ምንጭ: ሜዲካል ኒውስ ቱደይ

ጤናዎ በእጅዎ

27 Jan, 07:26


☸️የብልት ጋዝ Vaginal flatulence☸️

     ✅️ብዙ ሴቶች ቁጭ ካልኩበት ስነሳ ስፖርት ስሰራ ሳስል ከብልቴ እንደፈስ አየር ይወጣል በዚህም ምክንያት ሰው ጋር ለመቅረብ አሳፈረን ይላሉ ታዲያ ይሄ ሁኔታ ምንድነው? ምክንያቱስ?
  
     ✅️የብልት ጋዝ :አየር ከውጪ ወደ ብልት ውስጥ በመግባት ይያዝ እና :በአንዳንድ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ተገፍቶ ሲወጣ የሚፈጠር ድምፅ ያለው ክስተት ነው

     ✅️በግንኙነት ጊዜ :ስፖርት ሲሰራ :ሳል ሲኖር ከቅምጥ ብድግ ሲባል :በማህፀን ምርመራ ሲደረግ ይሄ ድምፅ ሊከሰት ይችላል

     ✅️በአብዛኛው ከወሊድ በኃላ የብልት አከባቢ ጡንቻዎች መላላት ስለሚኖር በአንዳንድ ሴቶች ላይ ይሄ ሁኔታ ይከሰታል

     ✅️አልፎ አልፎ የጋዝ ማፈትለኩ ምክንያት ፊስቱላ ወይም ፈሳሽ በሚያመጡ የብልት ኢንፈክሽኖች ምክንያት ሊሆን ይችላል

     ✅️የሚወጣው ጋዝ ምንም ሽታ የለውም

    ✅️በአብዛኝው ከሚያስከትለው የስነልቦና ጫና በዘለለ የሚስከትለው ጉዳት የለም እንደከባድ

    ✅️የብልት አከባቢ ጡንቻዎችን የሚያጠነክር እስፖርት(Kegel Exercise) በመስራት መከላከል  ማከም ይቻላል::

@Cleveland Clinic

#በቅንነት#ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba05121

ጤናዎ በእጅዎ

26 Jan, 15:41


#አጋላጭና #አባባሽ #ምክንያቶች
=====
ጭንቀንና የእንቅልፍ እጦት
ሰዎች በራሳቸው ጥርስ የአፍን ፣ የምላስን፣ የጉንጭን ንጣፍ መጉዳት
አስፈላጊ የምግብ ግባአት እጥረት (የቪታሚን፣ ቢ፣ ፎሌት ፣ አይረን)
የጥርስ ሳሙና ይዘቶች
የወር አበባ የቫይረስ ኢንፌክሽን

በህክምናው አፍተስ አልሰርን እንዴት ይታወቃል?

በአብዛኛው የቁስለቱን አይነት በመመልከት የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን ተጨማሪ ምርመራ በማድረግ አጋላጭ ምክንያቶችን (የድም ማነስ፣ የፎሌት እጥረት፣ የእንጀት ቁስለት /crohon's diasease, cealic diseaese) ካሉ ማወቅ ይቻላል።

#የህክምና #አማራጮች
====
ቁስለቱ በአብዛኝው በራሱ ሚጠፋ ቢሄንም ነገር ግን በተደጋጋሚ የሚከስት ቁስለት ከሌሎች ህመሞች ጋር ግኑኝነት ሊኖረው ስለሚችል ፣ ያሉትን አጋላጭ ምልንያቶች ማወቅና ማከም አስፈላጊ ነው።

ቁስለቱን ፈዋሽ መድሀኒት ስለለ ቁስሉ ቶሎ እንዲድን ማገዝና ህመም እንዳይሰማ/እንዲቀንስ ማድረግ የህክምናው ዋና አላማ ናቸው።

እንዲሁም ቁስሉን በሚቀቡ ቅባቶች (steriods) ማደንዘዣ ቅባቶች (local anethsetics )
ፀረ ተዎስይን የያዙ መጉመጥመጫዎች
እንዲሁም አባባሽ ምክንያቶችን ማስወገድ ህክምናዎቹ ናቸው።

ዶ/ር ሚሊዮን በየነ (የአፍ ፣ የፊትና የመንጋጋ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት)

https://youtube.com/@user-mf7dy3ig3d



#በቅንነት#ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba05121

ጤናዎ በእጅዎ

26 Jan, 15:41


#የአፍ #ውስጥ #ቁስለት (Aphtous ulcer)
====
አፍተስ አልሰር አፍ ውስጥ ከሚወጡ ቁስለቶች በመጀመሪያ ደረጃ ይመደባል ፣ ብዙዎች ሰዎች ያውቁታል። በአለም 20% የሚሆኑ ሰዎች ላይ ይከሰታል

አፍተስ አልሰር በአፍ ውስጥ በተለይ ምላስ ፣ ከምላስ ስር ፣ በጉንጭ በውስጠኛው ክፍል ፣ እንዱሁም በከንፈር በውስጠኛው ክፍል ላይ ይወጣል።

ይህ ቁስለት ከ1 ሳምንት እስከ 1 አንድ ወር ድረስ ሳይድን ሊቆይ ይችላል እንዲሁም መላልሶና በየግዜው ቦታ እየቀየረ ይወጣል በተጨማሪም ጣባሳ ሊስከትል ይችላል።

አፍተስ አልሰር ብዙ አይነት ሲሆን በተላይ ደሞ በአፍ ውስጥ በቁጥር በዛ ብሎ የሚወጣው የቁስለት አይነት በአብዛኛው ይታወቃል። እንዲሁም አፍ ውስጥ አንድ ብቻ ሆኖም ሊወጣ ይችላል፣አልፎ አልፎ የላንቃን የሗላኛውን ክፍል ሊያለብስ ይችላል።

#አፍተስ #አልሰር #ምልክቶቹ #ምንድናቸው?
====
አፍተስ አልሰር ከመከሰቱ በፊት የሚከሰትበት ቦታላይ ወደ ቢጫ ቀለም የመቀየርና ቦታው ከፍ ብሎ ይታያል ከተወሰኑ ቀናት በሗላ ቦታው የተቦጨቀ በመምሰል ከፍተኛ ህመም ይፈጥራል ፣መናገር፣ምግብ ማኘክና ማውራት ሊከለክል ይችላል።

#ምክንያትና #አጋላጭ #ነገሮች #ምንድናቸው?
=====
አፍተስ አልሰር ምክንያቱ ባይታወቅም አሁን ያሉ የጥናት ውጤቶች የአፍ ውስጥ ንጣፍ /mucosa/ የበሽታ የመከላከል አቅማቸው ከፍተኛ የሆነባቸው ሰዎች ላይ የራሳቸው ሰውነት የአፍ ንጣፍ በማጥቃት ለቁስለት እንደሚዳርግ ያሳያሉ።

ጤናዎ በእጅዎ

26 Jan, 08:38


#የበሽታው_ምልክቶች
=====

👉🏿 ከጨጓራ ባክቴሪያ ኢንፌክሽን H.Pylori Infection) ጋር የተያያዙ ምልክቶች እነዚህን ይመስላሉ:-

🔹የሆድ መነፋት ስሜት
🔹ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
🔹በተደጋጋሚ ግሳት ወይም ማግሳት
🔹የምግብ ፍላጐት ማጣት ወይም መቀነስ
🔹ያልተጠበቀ የሰውነት ክብደት መቀነስ ናቸው።

ነገር ግን እነዚህ የተለመዱ ምልክቶች ስለሆኑ በሌሎች ሁኔታ ወይም በሽታዎች ምልክቶቹ የመታየት አጋጣሚ አላቸው።

አንዳንድ የጨጓራ ባክቴሪያ ምልክቶች በጤናማ ሰው ላይ ሊታዮ ወይም ሊከሰቱ ይችላሉ።

እነዚህ ምልክቶች የተለመዱ ናቸው። ነገር ግን ከእነዚህ አንዱ በቀጣይነት ወይም በተከታታይነት የሚታይብዎት ከሆነ፤ ወደ ህክምና መስጫ ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራና ህክምና ያድርጉ።

ዓይነ ምድርዎ ወይም ሠገራዎ ጠቆር ያለ መልክ ካለው ወይም ደም የተቀላቀለበት ከሆነ (የሚያስመልስዎ ትውከት ጭምር) ሃኪምዎን በፍጥነት ያማክሩ።

#ከተመቻችሁ_ለሌሎች_ሸር_ያድርጉት

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

26 Jan, 08:37


#የጨጓራ_ባክቴሪያ (H.pylori) #ምልክቶች
=====

የጨጓራ ባክቴሪያ ያለባቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች ምንም አይነት የበሽታው ምልክቴች አይታይባቸውም።

ነገር ግን ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ቁስለት በሚፈጥርበት ወቅት የበሽታው ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ።

በተለይ ሆድዎ ባዶ በሚሆንበትና ምግብ ከተመገቡ ከጥቂት ጊዜ ወይን ሠዓታት በኋላ እንደ:- የሆድ ህመም ዓይነት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ። ይህ በሽታ ሄድ መጣ የሚል ህመምን ያስከትላል።

ምግብ መመገብ ወይም ፀረ-አሲድ (Anti-Acid) መድሃኒቶችን መውሰድ ይህን በሽታ ለማስታገስ ይረዳል።

ጤናዎ በእጅዎ

18 Jan, 15:42


#ቶሎ_መጨረስ_በወንዶች

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሶስት ወንዶች አንዱ በፆታዊ ግንኙነት ወቅት ቶሎ መጨረስ ያጋጥመዋል።

በዲኤስኤም 5 መስፈርት(DSM 5 Criteria) መሰረት ቶሎ መጨረስ የሚባለው በተደጋጋሚ ከአንድ ደቂቃ በታች ሲሆን ነው።

ነገር ግን ሰዎች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት ጊዜን በትክክል መለካት ስለሚያስቸግራቸው ቶሎ መጨረስ ህክምና የሚያስፈልገው በግለሰቡ፣ በአጋሩ ወይም በፍቅር ግንኙነታቸው ላይ ጫናና ጭንቀት የሚያስከትል ሲሆን ነው።

ቶሎ መጨረስ በይበልጥ የሚታየው በወጣት ወንዶች በግንኙነት የመጀመሪያ ጊዜያት ሲሆን በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ ይሄዳል።
ይሁን እንጂ በሚከሰትበት ወቅት መሸማቀቅ ወይም ሀፍረት እንዲሰማቸው ወይም ፆታዊ ግንኙነት ለማድረግ ሲያስቡ እንዲጨነቁ ሊያደርግ ይችላል።
ጭንቀት የሚፈጥር ከሆነ በተደጋጋሚ የመከሰት እድሉን ይጨምረዋል።

ቶሎ መጨረስ ስነ ልቦናዊ ምክኒያቶቹ ብዙ ሲሆኑ:

🌻 በፆታዊ ግንኙነት ፀፀት መሰማት፣
🌻በስንፈተ ወሲብ ምክኒያት መጨናነቅ፣
🌻በስራ መወጠር፣
🌻ከአጋር ጋር ያለመግባባት እንዲሁም ተለያይቶ መቆየት ይጠቀሳሉ።

ከአጋር ጋር በጉዳዩ ላይ በግልፅ መወያየት ዘና የማለት ስሜት ስለሚፈጥር ሁኔታው እንዲሻሻል ይረዳል።
'ቪያግራ' ቶሎ መጨረስን ለማከም አያገለግልም።

ችግሩ የሚደጋገም ከሆነ የስነ ልቦና ባለሞያ ወይም የአእምሮ ሀኪም በማናገር የሚያግዙ መድሀኒቶች በይበልጥ ደግሞ የንግግር የስነ ልቦና ህክምና ማግኘት ይቻላል።

#ከተመቻችሁ_ለሌሎች_ሸር_ያድርጉት

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

15 Jan, 13:51


መከላከያ መንገዶችስ ምንድናቸው?
====
• ክትባት
• ቤት ዉስጥ ማንኛዉም ጭስ አለማጨስ
• ቤት ዉስጥ በቂ የ አየር ዝውውር እንዲሮር ማድረግ
• የተመ ጣ ጠ ነ ምግብ መመገብ
• እስከ 6 ወር ያሉ ህፃናት የእናት ጡት ወተት ብቻ እንዲወስዱ ማድረግ
• ልጆች የፀሀይ ብርሃን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኙ ማድረግ
• ልጆችን ጉፋን ከያዛቸዉ ሰዎች በተቻለ መጠን ማራቅ ይገባል::

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

15 Jan, 13:51


ልጆችን ለሳም ባምች(pneumonia) የሚያጋልጡ ነገሮች
=====
1.የላይኛው የትንፋሽ አካላት ኢንፌክሽን ለምሳሌ ጉፋን፤ የቶንሲል ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉት
2. ቤት ዉስጥ የሚጨሱ ማንኛዉም የጭስ አይነቶች ለምሳሌ የሲጋራ የከሰል እና የእንጨት ጭሶች በሀገራችን በከፍተኛ መጠን ብዙ ህፃናትን ለሳምባ ምች እያጋለጣቸው ይገኛል::
3. ዝቅተኛ የበሽታ መከላከል አቅም(በምግብ እጥረት ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት)
4. በጣም ተጠጋግቶ መኖር እና በቂ የሆነ የአየር ዝውውር በሌለበት ቤት እና አካባቢ መኖር
5. የሳምባ የተፈጥሮ ችግሮች
6. የቫይታሚን ዲ እጥረት(ሪኬትስ)፦ በተለይ ፀሐይ በደምብ ያልሞቁ ህፃናት ለሳምባ ምች ተጋላጭ ናቸው::

ምልክቶቹ ምንድናቸው?
====
• ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
• ትንፋሽ ማጠር እና ለመተፈስ መቸገረ
• ትኩሳት
• ማቃሰት
• ትውከት
• የደረት ውጋት ወይም ህመም
• ህፃናት ሲተነፍሱ የታችኛው ደረት ክፍል ወደ ዉስጥ ግብት ግብት ማለት ናቸው::
• ልጆት ላይ እነዚህ የተጠቀሱት ምልክቶች ካሉ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መውሰድ እና ማሳከም ይኖርቦታል::

ልጆች ሳምባምች(ኒሞኒያ) እንዳይዛቸው ምን እናድርግ

ጤናዎ በእጅዎ

20 Nov, 15:22


ከሰብዓዊነት ውጪ የሆነ ለማየት፤ ለመስማትም የሚሰቀጥጥ ተግባር
ሰው እንዴት የህፃን ልጅ አንገት ያ*ዳል😭

ጤናዎ በእጅዎ

20 Nov, 15:19


#የሰውን_ልጅ_እንደ_በግ_በስመዓብ_ብለው_አ*ዱት😭😭😭

ከሰብዓዊነት ውጪ የሆነ ለማየት፤ ለመስማት የሚሰቀጥጥ ተግባር
ሰው እንዴት የህፃን ልጅ አንገት ያ*ዳል😭

ያየነውን ቪዲዮ በእውነት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ በጣም በጣም ተጨካክነናል::

ማንም ይሁን ማንም የሚመለከተው አካል እነዚህ አጥፊዎችን ይዞ ለህግ ማቅረብ አለበት::

ያማል ድምፅ ሁኑ ሼር አድርጉት 🙏🙏🙏

ነብስ ይማር ወንድማችን😭😭

ጤናዎ በእጅዎ

18 Nov, 18:35


ጥያቄ- 3: ወደ ህክምና መሔድ ያለብን መቼ ነው?

👉እምብርት ወይም እትብቱ የተበከለ ወይም ኢንፌክሽን የፈጠረ ከመሰለ። ይኸውም:
👉👉ትኩሳት ከተከሰተ፣
👉👉አካባቢው ከቀላ፣
👉👉 ፈሳሽ ካመጣ
👉👉የመነጫነጭ ስሜት ካለው፣
👉👉 ሲነካ ህመም ካለው መታየት አለበት።
👉ኢንፌክሽን ከለሌው እስከ 6 ሳምንት መጠበቅ ይቻላል። እስከ 6 ሳምንት ካልወደቀ ግን ሆስፒታል መሄዱ እና መታየቱ ግድ ይላል።

 
አዘጋጅ:
   ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:
     የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር

 
ተመጥኖ የተወሰደ

ጤናዎ በእጅዎ

18 Nov, 18:35


👉 ስለእምብር ጉቶ ወይም እትብት(Umbilical Cord) መውደቅ አለመውደቅ ብዙ ወላጆች  ከሚያስጨንቃቸው ነገር አንዱ ነው።

🌡መጨነቁ መልካም ቢሆንም የሚከተሉትን እውነታዎች በመገንዘብ ማድረግ የሚገባቸውን ነገር ማድረግ ተገቢ ነው።

ጥያቄ- 1: የእብርት እትብት(ጉቶ) አወዳደቅ ሒደቱ እንዴት ነው?

👉ጠነኛ ጉቶ ወይም እትብት ምንም የተለየ ህክምና አያስፈልገውም።

👉 እንዲደርቅ ብቻ ማድረግ ያስፈልጋል(የተፈጥሮ ማድረቅ ይባላል)።

👉ምክንያቱም እትብቱ ከመውደቁ በፊት መድረቅ ስላለበት ነው።

👉 ሲደርቅ ከተለምዶ ቀለሙ ይለውጣል። ይህም ከሚያብረቀርቅ ቢጫ ቀለም ወደ ቡናማ ወይም ግራጫ ፣ ቆይቶ ጥቁር ይሆናል።

👉ከዛም  በ1 እና 3 ሳምንታት መካከል በመደበኛነት ይወድቃል።
👉ይህ የተፈጥሮ ሒደቱ ነው።

ጥያቄ- 2: ቶሎ እንዲወድቅ የሚደረግ እንክብካቤ አለ ወይ?

👉የአብዛኛዎቹ ህፃናት በ10 እና 14 ቀናት መካከል ይወድቃል።
👉መደበኛ የመውደቂያ ጊዜው ከ7 እስከ 21 ባሉት ቀናት ሲሆን ቀስ በቀስ ይወድቃል፣ ታጋሽ መሆን ያስፈልጋል።

👉ወላጆች ሊረዷቸው ከሚገቡ አንዳንድ የእንክብካቤ ምክሮች መካከል የሚከተሉት ናቸው።

🩺🩺አልኮልን መጠቀም የለብንም🩺🩺

🌡🌡በአልኮል እየታሸ ከቆየ እትብቱ እንዲወድቅ የሚረዱትን ጥሩ ባክቴሪያዎችን ሊገድል ይችላል።
🌡🌡ይህም መዘግየትን ያመጣል!


🩺🩺የሽንት ጨርቅ ወይም ዳይፐር አጠቃቀም ማስተካከል ያስፈልጋል።

🌡🌡ዳይፐር እምብርት አካባቢ እንዳይደርስ በማጠፍ  እትብቱ በፍጥነት እንዲደርቅ ማድረግ ያስፈልጋል።
👉እንደ አማራጭ:
🌡🌡ሊጣል የሚችል ዳይፐር አንድ ቁራጭ ይቁረጡ፣ ከዚያም ጠርዙን በፕላስተር ያሲዙት።
🌡🌡ምክንያቱም እትብቱ ቶሎ እንዲደርቅ አየር ማግኘት አለበት።

ጤናዎ በእጅዎ

17 Nov, 11:31


#መቃብር_ቦታ_ላይ_በመጨፈር_ሙታን_ላይ_ሲቀልዱ_የነበሩት_ነውረኞች_ተይዘዋል።

እንኳን ደስ ያላችሁ 🙏❤️

እንዚህ 4 ልጆች የዛሬ 20 ቀን በመቃብር ስፍራ ሄደው

* አረ መላ መላ የኔ አለም *
* አረ መላ መላ የኔ አለም *

እያሉ ሞተው እንኳን እረፈት ያላገኙትን ወገኖቻችንን እየጨፈሩ ቪዲዮ በቲክቶክ ለቀው የነበረ ሲሆን

እኛም በወቅቱ እነዚህ ልጆች የምታውቁ ለአካቢያችሁ ላው የፓሊስ ጣቢያ አሳውቁን ብለን ፓስተን ነበር

ይህው ህብረቱሰቡም ለፓሊስ ጠቁሞ እነዚህ ልጆች በአሁን ስአት በቁጥጥር ስር ይገኛሉ::

ሲያዙም እኛ ሰው እንዲያይልን ነው ለview ብለን ነው ብለዋል።

አነዚህ ልጆች እንዲያዙ አስተዋጾ ያደረጋችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ክብር ይገባችዋል::

🙏🙏🙏

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

14 Nov, 10:14


#ዛሬ_ዓለም_አቀፍ_የስኳር_በሽታ_መታሰቢያ_ቀን_ነው።
=======
በየአመቱ በፈረንጆች November 14 አለም አቀፍ የ ስኳር በሽታ ቀን ታስቦ ይውላል።

በሃገራችንም ለ34ኛ ጊዜ ህዳር 5 "የስኳር ህመምና ምሉዕ ደህንነት፡- ለስኳር ህመም ህክምና እና ክብካቤ ተገቢውን ተደራሽነት ካገኙ ሁሉም የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች በተሟላ ጤንነት የመኖር እድል አላቸው!” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

የስኳር በሽታ ስጋቶችን ለመቀነስ እና በስኳር በሽታ የተያዘ ማንኛውም ሰው ፍትሃዊ ፣ አጠቃላይ ፣ ተመጣጣኝ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው ህክምና እና እንክብካቤ እንዲያገኙ ሊደረግ ይገባል።

በሃገራችን ከ1.9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከስኳር ህመም ጋር እንደሚኖሩ ሲገመት ከነዚህም 50 በመቶ የሚሆኑት ህሙማን ምንም አይነት የስኳር ምርመራ ያላደረጉ በመሆናቸው የህክምና እርዳታ እያገኙ አይደለም፡፡

💥የስኳር በሽታ ምርመራዎች ምንድን ናቸው?

💥 የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ምን ምንድን ናቸው?

💥የስኳር በሽታ የሚያስከትላቸው ችግሮች ምንድን ናቸው?

💥 የስኳር በሽታን እንዴት መከላከል ይቻላል?

ጤናዎ በእጅዎ

14 Nov, 10:13


#ደጋጎች_ተመስግናችኋል🙏🙏🙏
#እግዚአብሔር_ይመስገን💖🙏

ይህች አንጀት የምትበላ የ8ወር ህፃን #ሄመን_ስምኦን በልብ ክፍተት ህመም እየተሰቃየች አስቸኳይ ቀዶ ጥገና ያስፈልጋታል ተብላ በእናንተ ልበወርቆች እገዛ ታዝማ የልብ ማዕከል ከ3ሰዓት በላይ የፈጀውን ቀዶጥገና በተሳካ ሁኔታ አጠናቃለች!አባቷም "ላደረጋችሁልኝ ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ🙏ፈጣሪ ከሁሉም ነገር ይጠብቃችሁ" ብሏችኋል! #ተመስገን🙏 እንኳን ደስ አለህ!!
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

#ባይሽ_ኮልፌ_በጎ_አድራጎት

ጤናዎ በእጅዎ

03 Nov, 07:54


በመንፈራገጥ ህመም ጊዜ መደረግ የሌለባቸው ድጋፎች

ሀ. የሚንፈራገጥ ሰውን መንፈራገጡ ለማስቆም መያዝ አያስፈልግም፣

ለ. የሚንፈራገጥ ሰውን በጥርሶቹ መሀል ምንም አይንት ነገር መክተት አያስፈልግም (የሚንፈራገጥ ሰው ምላሱን የመንከስና ከፍተኛ ጉዳት የማስከተል እድሉ አነስተኛ ነው)፣

#መደረግ_የሌለባቸው_ነገሮች

1. ተጎጂውን ከቦ አየር አለማሳጠት

2. ክብሪት ለኩሶ አፍንጫ ላይ አለማድረግ

3. ተጎጂው እስኪነቃ ድረስ ምንም ዓይነት ምግብም ሆነ መጠጥ አለመስጠት

የተለያዩ ዓይነት የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎች ምን ዓይነት እንቅስቃሴ ሊኖራቸው እንደሚችል በሚከተለው አድራሻ ቴሌግራም ላይ አጭር ቪድዮ አስቀምጠናል ማየት ይችላሉ።
https://t.me/ba051219

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

03 Nov, 07:54


#የሚጥል_በሽታ (Epilepsy)
====
በአንጎል ሕዋሶች ውስጥ ትክክለኛ ያልሆኑ መልእክቶች ሲተላለፉ(abnormal electric discharge) ሚከሰት ድንገተኛ በሽታ ነው። የሚጥል በሽታ ከአንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው አይተላለፍም፡፡

#የህመሙ_ምልክቶች

Ø ለአጭር ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ መሬት ላይ መንፈራገጥ

Ø አረፋ መድፈቅ

Ø እራስን መሳት

አንድ ሚጥል በሽታ ያለበትን ሰው #ሲወድቅ_ብናው_እንዴት_ልንረዳው_እንችላለን?

1 .ህመምተኛው አደገኛ ቦታ ላይ ከወደቀ እንዳይጎዳ ጥንቃቄ ማድረግ

2. ማንቀጥቀጡ አስኪያቆም ድረስ በሽተኛውን አለመንካት

3. መንፈራገጡ ሲቆም እራሱን ስቶ ትንሽ ጊዜ ስለሚቆይ የሚተነፍስ ከሆነ ወዲያውኑ በጎኑ ማስተኛትና አፉን ማጽዳት

4. በሽተኛው ስኳር በሽተኛ መሆኑን ካወቁና ራሱን ሙሉ በሙሉ ካልሳተ ወይም ምግብ በአፉ መውሰድ የሚችል ከሆነ ስኳር ያለበት ነገር መስጠት፣

5. የዚህ አይነት ህመምተኞች በዚህ ጊዜ ሽንታቸውን ሊስቱ ስለሚችሉ ሲነቁ ሐፍረት እንዳይሰማቸው ሰዎችን ከአካባቢው ማራቅና፤ህመምተኛውን ማበረታታት፣

6. ሕመምተኛው ወደ ሕክምና ድርጅት ሔዶ እንዲታከም መምከር፤ ወይም ወደ ሕክምና ድርጅት በቶሎ መውሰድ

7. መንፈራገጡ በሙቀት ምክንያት የመጣ ከሆነ ቀዝቃዛ ቦታ መውሰድ/ማቀዘወቀዝ፣

ጤናዎ በእጅዎ

31 Oct, 09:02


ከፍተኛ የወባ ስርጭት ያለባቸው አካባቢዎች ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከቦታ አቀማመጥ ጋር በተያያዘ  እንደሚከሰት ጠቁመዋል፡፡

በደቡብ አካባቢ ከታቆረ ውኃ በዘለለ በእንሰት ተክል ውስጥ የሚገኝ ውኃ ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ነው ያነሱት፡፡

የመተላለፊያ ወቅቶች ከመጀመራቸው በፊት የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እንደሚከናወኑ የገለጹት ዶ/ር ሕይወት፤ በመኖሪያ ቤቶች እና አካባቢዎች በውኃ የታቆሩ ጉድጓዶችን እና አጋላጭ ቦታዎችን ማጽዳት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል፡፡

ለወባ ትንኝ ተጋላጭ ናቸው ተብለው በተለዩ አካባቢዎች የመኝታ አጎበር እንደተሰራጨ ገልጸው፤ የጸረ-ወባ ትንኝ መድኃኒት እርጭት መከናወኑንም አመላክተዋል፡፡

ከፍተኛ የወባ ሥርጭት ያለባቸው ቦታዎች ላይ የጤና ኤክስቴንሽን ስራዎች በስፋት  እየተሰሩ እንዳለም ጠቁመዋል፡፡

በሜሮን ንብረት

ጤናዎ በእጅዎ

31 Oct, 09:02


ከፍተኛ የወባ በሽታ ስርጭት እስከ ታህሳሥ ወር ድረስ ሊኖር ይችላል፦ የጤና ሚኒስቴር
***

ከፍተኛ የሆነ የወባ በሽታ ስርጭት እስከ ታህሳሥ ወር ድረስ ሊኖር እንደሚችል የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በተያዘው ዓመት በሦስት ወር ውስጥ ብቻ ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በወባ በሽታ መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

የዝናብ ወቅትን ተከትሎ ከመስከረም እስከ ታህሳሥ ወር ባለው ወቅት የወባ በሽታ ስርጭት ከፍተኛ እንደሚሆን ነው ዶ/ር ሕይወት የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያ የወባ በሽታ ሥርጭት ካሉባቸው ሀገሮች መካከል እንደምትጠቀስ ገልጸው፤ ይህንን ለመከላከል ከ8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የትንኝ ንክሻን ቅድመ መከላከል ስራ እንደተከናወነ ጠቅሰዋል፡፡

የወባ በሽታ መንስኤ የወባ ትንኝ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ሕይወት፣ በውኃ የታቆሩ ጉድጓዶች ለወባ ትንኝ ስርጭት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ነው የገለጹት፡፡

በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ ክልሎች የወባ በሽታ ሥርጭት በከፍተኛ ደረጃ የሚታይባቸው አካባቢዎች መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ጤናዎ በእጅዎ

30 Oct, 19:27


#በምንም_ምክንያት_ተስፋ_አትቁረጥ 🙏🏻
======
ይህ ሰው ጃክ ማ (Jack Ma) ይባላል።

ለሁለት ጊዜ የኮሌጅ መግቢያ ውጤት አልመጣለትም።

30 ግዜ ለስራ አመልክቶ አልተሳካለትም።

KFC ቻይና ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፈት ከእሱ ጋር 24 ሰዎች ለስራ ተወዳድረው እሱ ብቻ እድሉን አጣ።

ለፖሊስነት አመልክቶ እሱ ብቻ ተቀባይነት አጣ።

አሜሪካ ለሚገኘው ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ለመቀጠል ጠይቆ rejecte ተደርጓል።

በሕይወቱ ውስጥ በጣም ብዙ ውድቀቶችን አስተናግዷል::

ግን ተስፋ ቆርጦ እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም።

በ1994 ስለ ኢንተርኔት ሰማ። በ1995 ከትውልድ አገሩ ቻይና ወደ አሜሪካ ባጋጣሚ ያቀናል:: በዚህም ጊዜ በጓደኛው እርዳታ ስለ ኢንተርኔ ምንነት ማወቅ ቻለ። ኢንተርኔትን እንዳወቀ መጀመርያ የፈለገው ቃል "beer" የሚል ነበር። በዚህም ስለ ቢራ የተለያዩ መረጃዎችን ከተለያዩ አገሮች ያገኝ ቢሆንም ከአገሩ ቻይና ግን ምንም አይነት መረጃ ማግኘት አልቻለም።

በዚህም ተበሳጨና ስለ ቻይና አጠቃላይ መረጃ መፈለግ ተያያዘ አሁንም ውጤቱ 0 ነበር። በዚህም ቁጭት ከጓደኛው ጋር ሆኖ ሰለ ቻይና መረጃ የሚሰጥ ድህረ ገጽ ፈጠሩ፡፡ ድህረ ገጽ በተከፈተ በአምስት ሰዓት ውስጥ ከተለያዩ ቻይናዊያን የአብረን እንስራና እንተዋወቅ ጥያቄዎች ቀረቡለት። በዚህም ኢንተርኔት አዋጭ ስራ እንደ ሆነ ተገነዘበ፡፡ እንደዚህ እያለ የአለማችንን ግዙፍ ተቋም የሆነውን ALIBABA GROUP ለማቋቋም በቃ፡፡ አሁን የ 25.6 billion USD ቢሊየን ዶላር የተጣራ ተቀማጭ ረብጣ owner የሆነው ማክ የአለማችን 45ተኛ ቱጃር ነው። በማንኛውም ሁኔታ በምንም ምክንያት ተስፋ አትቁረጥ ዛሬ ባይሳካ ነገ ሌላ ብሩህና መልካም ቀን ነው።

ጤናዎ በእጅዎ

29 Oct, 12:53


#ነጻ_ሕክምና ለከንፈር እና ላንቃ ታካሚዎች
====
ትረስት የበጎ አድራጎት ማህበር ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ፣ ከወላይታ ልማት ማህበር፣ ከወላይታና ከጋሞ ዞን ጤና መምሪያዎች እና ከአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ከቀን 21- 24/02/2017 ዓ.ም #በነጻ ይሰጣል። ስለሆነም ዕድሜያቸዉ ከ4 (አራት) ወር በላይ የሆኑ ሕጻናትና አዋቂዎች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እናሳስባለን።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0977720145/44 ማግኘት ይቻላል።

#ማሳሰቢያ፦ በሆስፒታሉ ቆይታ የምግብ፣ የመድኃኒት እና የደርሶ መልስ ትራንስፖርት #በነጻ መሆኑን እንገልፃለን።

#በቅንነት_ሸር_አድርገው_ለሌሎችም_ያድርሱ፡፡🙏🙏🙏

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

23 Oct, 06:04


የ93 አመት እድሜ ባለጸጋ አዛውንት በድንገት ራሳቸውን ይስቱና መተንፈስ አቅቷቸው ወደ ሆስፒታል ይወስዳሉ። እናም ለ 24 ሰዓታት ኦክስጅን ተሰጥቷቸው ይቆያሉ። ከጥቂት ሰዓት በኋላ ተሽሏቸው ወደቤታቸው እንዲመለሱ ተወሰነ። ዶክተሩም ‘’እስካሁን ለተደረገልዎት የህክምና እርዳታ 5000 ዶላር መክፈል ይጠበቅብዎታል’’ ይልና ሂሳቡን ያሳያቸዋል።

አዛውንቱም ሂሳቡን አይተው ማልቀስ ጀመሩ። ዶክተሩ በሂሳቡ ምክንያት ከሆነ እንዳያለቅሱ ነገራቸው። አዛውንቱ ግን "በገንዘብ ምክንያት አላለቅስም። ገንዘቡን በሙሉ መክፈል እችላለሁ። ያለቀስኩበት ምክንያት ለ 24 ሰአታት ኦክሲጅን በመጠቀሜ 5000 ዶላር መክፈል አለብህ አላችሁኝ። ነገር ግን 93 አመት ሙሉ ፈጣሪዬ የሰጠኝን አየር ስተነፍስ ቆይቻለሁ። ግን ይህን ያህል ዘመን ምንም አልከፍልም ነበር። ከፈጣሪዬ ምን ያህል ዕዳ እንዳለብኝ ታውቃለህ? ይህ ቸርነቱ ነው ያስለቀሰኝ።’’ ብለው መለሱለት።

ዶክተሩም አንገቱን ደፍቶ ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ።

ይህን ለምታነቡ ሁሉ፣ ለፈጣሪ ምንም የምንከፍለው ነገር ሳይኖር ለዓመታት ነፃ አየር ስንተነፍስ ኖረናል፣ እንኖራለንም።

በህይወታችን ውስጥ ይህን ሁሉ በገንዘብ የማይተመን አገልግሎት በነፃ ለሰጠን ፈጣሪያችን 2 ሰከንድ ብቻ ወስደን ማመስገን ይከብደናል?

ፈጣሪያችንን እናመስግነው!
ከዚሁ መንደር የተገኘ

ጤናዎ በእጅዎ

17 Sep, 08:39


??👉#ማድያትን #በቤት#ዉስጥ #ለማከም #የሚረዱ #መንገዶች

📌 የሎሚ ጭማቂ -የሎሚን ጭማቂ ፊትን ቀብቶ ለ2 ደቂቃ ማሸት ለ20 ደቂቃ ካቆዩ በኋላ መታጠብ እንዲሁም የሎሚ ጭማቂ እና ማርን በመቀላቀል ፊትን መቀባት እና በሞቀ ዉሃ ዉስጥ ተነክሮ የወጣ ፎጣጨምቆ ለ15 ደቂቃ ፊትን ሸፍኖ ማቆየት እና መታጠብ
📌 አጃ- የተፈጨ የአጃ ዱቄት ከማር ጋር በመለወስ መቀባት እና ለግማሽ ሰአት አቆይቶ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ
📌 የአፕል አቼቶ-1 ማንኪያ የአፕል አቼቶ ከ1 ማንኪያ ውሀ ጋር በመደባለቅ መቀባት እና ከ3 እስከ 5 ደቂቃ በኋላ አቆይ
📌 እርድ- 1 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ እርድ ከ 2-3 የሻይ ማንኪያ ወተት ጋር በመቀላቀል ማዋሀድ መቀባት እና ለ 20 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ
📌 እሬት- 1 የእሬት ቅጠል ዉስጥ ያለዉን ፈሳሽ በመቀባት ለ 2 ደቂቃ ማሸት ከ 15-20 ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለ ውሀ መታጠብ
📌 ፓፓያ - ግማሽ የሻይ ሲኒ የበሰለ ፓፓያ መፍጨት ከ 2 ማንኪያ ማር ጋር ቀላቅሎ መቀባት ለ 20 ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለ ውሀ መታጠብ
📌 አንድ ቲማቲም በመፍጨት ከአንድ የሻይ ማንኪያ እርጎ እና አንድ የሻይ ማንኪያ የአጃ ዱቄት በመቀላቀል ፊትን በደንብ አዳርሶ በመቀባት ለ20 ደቂቃ ቆይቶ ሲደርቅ መታጠብ

#በቅንነት_ሸር_አድርገው_ለሌሎችም_ያድርሱ፡፡🙏🙏🙏

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

17 Sep, 08:39


#ማድያት

ማዲያትት (Melasma) ለቆዳችን ቀለም የሚሰጡ ህዋሶች (Melanocytes) ከመጠን በላይ ሲመረቱ ከተለመደዉ የቆዳችን ቀለም ለየት ባለ መልኩ የቆዳ መጥቆር ሲኖር ይከሰታል፡፡ይህ ችግር በየትኛዉም የቆዳ ክፍል ላይ የሚወጣ ሲሆን በአብዛኛዉ ፊት ላይ ሲከሰት ይስተዋላል፡፡

👉?? #ለማድያት #የሚያጋልጡ #ሁኔታዎች

📌 ለከፍተኛ ፀሀይ/ጨረር መጋለጥ
📌 የሆርሞን መለዋወጥ
📌 እርግዝና
📌 ጭንቀት እና ድባቴ
📌 የፊት መታጠቢያ እና መዋቢያ ነገሮች
📌 የወሊድ መከላከያ አማራጮች
📌 የእንቅርት በሽታ (የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት)
📌 የሆርሞን ህክምና
📌 የቫይታሚን ቢ12 እጥረት

👉👉 #ለማድያት #የሚደረግ #ህክምና

ማድያትን በቅድሚያ ለማድያት የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን ማከም ያስፈልጋል ከዛ በተጨማሪ በባለሙያ የሚታዘዙ የቆዳ ቀለም ሰጪ ህዋሶችን የሚቀንሱ እና የጸሐይ መከላከያ መድሐኒቶች ይታዘዛሉ፡፡

ጤናዎ በእጅዎ

16 Sep, 18:05


ልብ ብለው ያንብቡት!

ሰውዬው በሀሳብ ተውጦ በመጓዝ ላይ ሳለ ድንገት በአንድ የገበሬ ግቢ ውስጥ ዝሆኖች በገመድ ታስረው ቆመው ይመለከታል። ቆሞ አስተዋለ። "እነዚህን የሚያካክሉ ግዙፍ ፍጥረታት እንዴት በነዚህ ቀጫጭን ገመዶች ታዘው ሊቆሙ ይችላሉ?" በዚህ ቁመናቸው በረትም ሆነ ብረት ሰባብረው መሄድ እንደሚችሉ አሰበ።

የዚህን ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ጉዞውን ለመቀጠል አዕምሮው አልፈቀደለትም። ቀጥ ብሎ ወደ ውስጥ ገባና ገበሬውን አገኘው። "ለመሆኑ እንዴት ቢሆን ነው በዚች ቀጭን ገመድ ታስረው ሊቆሙ የቻሉት?" ሲል ጠየቀው።

ገበሬውም የሰውየው መገረም አግባብ እንደሆነ ከገለጸለት በኋላ ...."ምን መሰለህ ጌታዬ! ዝሆኖቹን ከህጻንነታቸው ጀምረን በነዚሁ ገመዶች ነው የምናስራቸው። ህጻን በነበሩ ጊዜ ይሄ ገመድ እነሱን ይዞ ለማስቀረት በቂ ነበር። እያደጉ ሲሄዱም ምንም እንኳን በአካል ቢገዝፉም ዛሬም ድረስ ገመዱ ሀይል ያለው ይመስላቸዋል። ስለዚህ በጥሶ ለመሄድ ምንም ጥረት አያደርጉም!" ሲል መልሰለት።

የሰው ልጅም እንዲሁ ነው። ልጆች ሳለን በብዙ ቀጫጭን ገመዶች እንታሰራለን። ስናድግ እነዚህ ገመዶች በአዕምሯችን እንደገዘፉ ይቀሩና ዘመናችንን ሁሉ ጠፍንገው እንዳሰሩን እንኖራለን። በነዚሁ ገመዶች እንደተተበትብን እናስባለን፣ እንምላለን፣ እንከራከራለን፣ እንጣላለን፣ ...ወዘተ! እነዚህ ገመዶች ደግሞ በባህል፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት፣ በዘርና በጎሳ ሰበብ የሚመጡ ናቸው።
ሰው ግን የታሰረበትን ገመድ በጥሶ ሳይሆን ፈትቶ መላቀቅ የሚችል ባለ አዕምሮ ነው። ይህንንም የሚያደርጉት በጣም ውስን ሰዎች ናቸው። እናንተስ?

ጤናዎ በእጅዎ

13 Sep, 05:12


🍀ሴሊኒየም የተባለ ሜኔራል ምንጭ ነው

በቅቤ ውስጥ የሚገኝው ሴሊኒየም ጠንካራ የሆነ ፀረ-ኦክሲዳንት ባህሪ አለው።

ኤክስፕርቶች እንደሚናገሩት ሴሊኒየም ኢንፍላሜሽንን በመቀነስና ለካንሰር የመጋለጥ እድልን በመቀነስ በጣም ጠቃሚ ነው።

በተጨማሪም ሴሊኒየም ከቫይታሚን ኢ ጋር በመጣመር ተጨማሪ ፀረ-ኦክሲዳንት አገልግሎት ሲኖረው ለቆዳ በጣም ጠቃሚ ነው።

🍀 የሆርሞኖች ዓይነት ጥቅም አለው

ቅቤ ወልዝን ፋክተር የተባለ የሆርሞን መሰል ባህሪ ያለው ንጥረ ነገር አለው፤ ይህ ንጥረ ነገር የመገጣጠሚያ መገተርን እና ከአርትራይተስ ጋር ተያይዞ የሚመጣን ኢንፍላሜሽን ይከላከላል።

በተጨማሪም ካልሲየም በመገጣጠሚያዎች አካባቢ እንዳይቀር (ጉዞው እንዳይቋረጥ) እና በቀጥታ አጥንቶች ጋር እንዲደርስ በማድረግ ይጠቅመናል።

ቅቤ በምንገዛበት ጊዜ ትኩስ (ጥሬ) እና ተፈጥሮአዊ የሆነ ከምንም ነገር ጋር ያልተቀላቀለ በመግዛት ከላይ የተጠቀሱትን ጥቅሞች በሙሉ ማግኝት እንችላለን።

በተጨማሪም እርጥብ ሳር ከምትመገብ ላም የተገኘ ቅቤ ቢሆን በጣም ተመራጭ ነው።

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

13 Sep, 05:12


#ቅቤ #የሚሰጠን #የጤና #ጥቅሞች
=======
ቅቤ ሳቹሬትድ የሆነ ፋት (Saturated Fat) በውስጡ ይዟል። ይህ ማለት ሃይድሮጂኔትድ ፋት (Hydrogenated Fat) ከያዘው ማርጋሪን በጣም የተለየ እና ጤናማ ነው።

ከብዙ አመት በፊት ማርጋሪን በጣም እርካሽ እና ጤናማ ቅቤን በመተካት የሚያገለግል ሆኖ ቀርቧል፤ ቢሆንም ቅሉ ሳይንሳዊ ጥናቶች በመጨረሻ እንዳረጋገጡት ቅቤ ከማርጋሪን እጅግ በጣም የተሻለ መሆኑን አሳይተዋል፡፡

ማንበብዎን በመቀጠል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማርጋሬት ወይም ሌሎች ቅቤን የሚተኩት ነገሮችን መጠቀምዎን በማቆም የተፈጥሮ ቅቤን መጠቀም ይጀምሩ፡፡

☑️ የሚከተሉት በጣም አስገራሚ ቅቤ የሚሰጠን የጤና ጥቅሞች ናቸው ይጠቀሙባቸው:-

🍀 ቅቤ በቫይታሚን ኤ የበለፀገ ነው

በጣም በርከት ያሉ የቫይታሚን ኤ ምንጮች አሉ ነገር ግን ከቅቤ የምናገኘው ቫይታሚን ኤ በጣም ተመራጭ ነው።

ምክንያቱም ከቅቤ የምናገኘው ቫይታሚን በቀላሉ ከሰውነታችን ጋር የሚዋሃድ ስለሆነ ነው።

ቫይታሚን ኤ ጤናማ የሆነ አይን እንዲኖረን በጣም አስፈላጊ ነው።

በቅቤ ውስጥ ያለው ይህ ቫይታሚን በሰውነታችን ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ዕጢዎች ተግባራቸውን በትክክል እንዲወጡ አስፈላጊ ነው።

🍀ጤናን በሚለግሱ ፋቲ አሲዶች ክምችት የተሞላ ነው

ጤናዎ በእጅዎ

11 Sep, 20:27


*የተለያዩ ምግቦችንና መጠጦችን በአንድ ላይ ቀላቅሎ አለመመገብ።
*የምናዘጋጀው ምግብ ንጽህናን በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀት።
*ምግቦቻችን ቅባት የበዛባቸው እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ።
*ስንመገብ ቀስበቀስ ጨጓራን በማላመድ፣ በልክ እና ከመጠን ባላለፈ መልኩ መመገብ
*ጣፋጭ ምግቦችን እና የአልኮል መጠጦችን ከልክ በላይ አለመውሰድ
*ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች አለመመገብ

አጿዋማትን ተከትለው በሚመጡ በዓላት አመጋገብን ማስተካከል እንደሚገባ የሥነ ምግብ ባለሙያዎች  ያስረዳሉ።

በዓላት በመጡ ቁጥር አንዳንድ ሰዎች ቅባት የበዛበት ምግብ ተመግበው ለሕመም የሚጋለጡበት ሁኔታ ይከሰታል።በዚህም የተነሳ በዓሉን በጤና ተቋም የሚያሳልፉት ጥቂት አይደሉም።

ታዲያ በዓልን በሰላም ለማክበር ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ጉዳዮች የበዓላት ሰሞን አመጋገብ አንዱና ዋነኛው ስለሆነ፣ ጤናማ የበዓል አመጋገብን በመከተል ጤናን መጠበቅ ያስፈልጋል።  በጤና የታጀበ በዓል ይሁንሎ። መልካም በዓል!!

@ጤናዎ በእጅዎ


#ሸር_አድረገው_ለሌሎችም_ያድርሱ:

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

11 Sep, 20:27


#ስለበዓላት_ሰሞን_አመጋገብ_ምክር_አለን🌻🌻🌻
=====

በሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ በዓላቶች የመኖራቸውን ያህል  በርካቶች ከወትሮው የተለዩ የምግብና መጠጥ ዓይነቶችን የሚጠቀሙበት አጋጣሚ የበዛ ይሆናል።

በዚህም የአመጋገብ ጥንቃቄ ባለማድረግ ብቻ የጤና መቃወስ የሚገጥማቸው ሰዎች መኖራቸውን በተለያዩ የህክምና ተቋማት እናያለን።

በበዓላት ወቅት የምንከተለው ያልተገባ አመጋገብ ጤና የሚነሳ ወይም ላልተጠበቀ አደጋና እስከ ሕይወት ማለፍ ሊዳርጉ የሚችሉበት አጋጣሚም ጥቂት አይደለም።

በተለይም
*ከመጠን በላይ መመገብ፣
*ስጋና የእንስሳት ተዋጽኦን ማዘውተር እንዲሁም
*የአልኮል መጠጦችን አብዝቶ መጠጣት የጤና እክል የሚያስከትል ነው።

አጽዋማትን ተከትለው በሚመጡ በዓላት ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች መመገብ፣ የእንስሳት ተዕዋጽዎ ምግቦችን፤ ማለትም:- ሥጋ፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ወተት፣ ቅቤ እና መሰል ምግቦችን መመገብ እንዲሁም የአልኮል መጠጦችን መጠጣት የተለመደ ነው።

ይህም ለረጅም ጊዜ ከቅባት ርቆ የቆየን ጨጓራ ለህመም የመዳረግ ዕድሉ ከፍተኛ ስለሚሆን፤ የሆድ መነፋት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጨጓራ ማቃጠል ህመሞችን ሊያስከትል ይችላል። ይህም ጥንቃቄ ካልተደረገ ላልተጠበቀ የጤና ችግር የሚዳርግ ሊሆን ይችላል።

ታድያ ይህን ለማስቀረት በበዓላት ወቅት እነዚህ ጥንቃቄዎች እንዲደረጉ ጤናዎ በእጅዎ ምክር አለን እያለች ነው:-

ጤናዎ በእጅዎ

08 Sep, 06:11


#ህክምናው
_ያመጣውን ነገር በምርመራ ከተረጋግጥ ወይም ከታወቀ በኋላ መንሰኤውን ማከም
_በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ መድሀኒቶችን በአግባቡ መውሰድ
_በፋይብር የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ፣ ሙቅ ውሀ ላይ መዘፍዘፍ(የፊንጢጣ  ኪንታሮት፣የፊንጢጣ መሰንጠቅ ከሆነ ያመጣው)
እንደማጠቃለያ ደም የቀላቀለ ሰገራ በትንሽ (በቀላል) እንዲሆም ከበድ ባሉ ምክንያቶች በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ የሚከሰት እና ምልክቶቹ ቶሎ የማይስተዋሉ ሰለሆነ እንዳወቁ የጤና ባለሙያ ያማክሩ።

#ሸር_አድረገው_ለሌሎችም_ያድርሱ:

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

08 Sep, 06:11


#ደም #የቀላቀለ #ሰገራ
======
ደም የቀላቀለ ሰግራ ማለት በየትኛውም የአንጀት ክፍል መድማት ሲያጋጥም በሰገራ መልኩ ደም ሲታይ ነው። ከተቀመጡ በኋላ ሰገራው ላይ እና የሽንት ቤት ወረቀት ላይ ደም ሲታይ ደም ሰገራ ላይ እንዳለ ይታወቃል ።

#ምክንያቶቹ
· የአንጀት ክፍል ላይ የወጣ ቀዳዳ መሰል ነገር(Diverticular Diseeas )
· የፊንጢጣ ኪንታሮት(Hemorrhoide)
· የፊንጢጣ መሰንጠቅ(Anal fissuer)
· የአንጀት መለብለብ(Colitis)
· የአንጀት አካባቢ ደም ስሮች ላይ ችግር ሲኖር(Angiodysplasia)
· የጨጓራ ቁስለት
· አንጀት ላይ ትርፍ ስጋ መሰል ነገር ሲያድግ(Polyps)
· አንጀት ካንሰር
· የምግብ ትቦ ላይ ችግር ካለ(Esophageal problem)
· የአንጀት ላይ ኢንፌክሽን

#ምልክቶቹ
አብዛኛው ሰው ምልክቶቹን ላያስተውል ይችላል ።በሌላ በኩል ደግሞ ከሚከሰቱ ምልክቶች ውስጥ
* የሆድ ህመም
*ማስመለስ
*ድካም
*ለመተንፈስ መቸገር
*ተቅማጥ
*ራስን መሳት
*የሰውነት ክብደት መቀነስ የማሳሰሉት ናቸው።

ጤናዎ በእጅዎ

07 Sep, 06:36


አንድ ሚጥል በሽታ ያለበትን ሰው #ሲወድቅ_ብናው_እንዴት_ልንረዳው_እንችላለን? 

1 .ህመምተኛው አደገኛ ቦታ ላይ ከወደቀ እንዳይጎዳ ጥንቃቄ ማድረግ

2. ማንቀጥቀጡ አስኪያቆም ድረስ በሽተኛውን አለመንካት

3. መንፈራገጡ ሲቆም እራሱን ስቶ ትንሽ ጊዜ ስለሚቆይ የሚተነፍስ ከሆነ ወዲያውኑ በጎኑ ማስተኛትና አፉን ማጽዳት

4. በሽተኛው ስኳር በሽተኛ መሆኑን ካወቁና ራሱን ሙሉ በሙሉ ካልሳተ ወይም     ምግብ በአፉ መውሰድ የሚችል ከሆነ ስኳር ያለበት ነገር መስጠት፣

5.  የዚህ አይነት ህመምተኞች በዚህ ጊዜ ሽንታቸውን ሊስቱ ስለሚችሉ ሲነቁ ሐፍረት እንዳይሰማቸው ሰዎችን ከአካባቢው ማራቅና፤ህመምተኛውን ማበረታታት፣

6. ሕመምተኛው ወደ ሕክምና ድርጅት ሔዶ እንዲታከም መምከር፤ ወይም ወደ ሕክምና ድርጅት በቶሎ መውሰድ

7. መንፈራገጡ  በሙቀት ምክንያት የመጣ ከሆነ  ቀዝቃዛ ቦታ መውሰድ/ማቀዘወቀዝ፣
በመንፈራገጥ ህመም ጊዜ መደረግ የሌለባቸው ድጋፎች

ሀ. የሚንፈራገጥ ሰውን መንፈራገጡ ለማስቆም መያዝ አያስፈልግም፣

ለ. የሚንፈራገጥ ሰውን በጥርሶቹ መሀል ምንም አይንት ነገር መክተት አያስፈልግም (የሚንፈራገጥ ሰው ምላሱን የመንከስና ከፍተኛ ጉዳት የማስከተል እድሉ አነስተኛ ነው)፣

#መደረግ_የሌለባቸው_ነገሮች

1. ተጎጂውን ከቦ አየር አለማሳጠት

2. ክብሪት ለኩሶ አፍንጫ ላይ አለማድረግ

3. ተጎጂው እስኪነቃ ድረስ ምንም ዓይነት ምግብም ሆነ መጠጥ አለመስጠት

የተለያዩ ዓይነት የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎች ምን ዓይነት እንቅስቃሴ ሊኖራቸው እንደሚችል በሚከተለው አድራሻ ቴሌግራም ላይ አጭር ቪድዮ አስቀምጠናል ማየት ይችላሉ።
https://t.me/ba051219

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

07 Sep, 05:22


#የሚጥል_በሽታ (Epilepsy)
====
በአንጎል ሕዋሶች ውስጥ ትክክለኛ ያልሆኑ መልእክቶች ሲተላለፉ(abnormal electric discharge) ሚከሰት ድንገተኛ በሽታ ነው። የሚጥል በሽታ ከአንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው አይተላለፍም፡፡

#የህመሙ_ምልክቶች

Ø ለአጭር ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ መሬት ላይ መንፈራገጥ

Ø አረፋ መድፈቅ

Ø እራስን መሳት

ጤናዎ በእጅዎ

07 Sep, 04:23


ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በቅንጅት የተሰራ አንድ ጥናት እንዳስታወቀው #ሞባይል_ስልክ_የጭንቅላት_ካንሰርን_አያስከትም_ተብሏል፡፡

ከ250 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉበት ህ ጥናት የጭንቅላት ካንሰር እና ሞባይል ስልክ ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸውም ዩሮ ኒውስ ጥናቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ለሰባት ዓመታት ተደርጓል የተባለው ይህ ጥናት ሞባይል ስልክ አብዝተው የሚጠቀሙ እና አልፎ አልፎ የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ምንም አይነት ልዩነት እንደሌለ ተገልጿል።

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

07 Sep, 04:23


#ሞባይል_ስልክ_አብዝቶ_ማውራት_እና_የጭንቅላት_ካንሰር_ግንኙነት!!!
=====
የዓለም ጤና ድርጅት የሞባይል ስክ እና ጭንቅላት ካንሰር ያላቸውን ዝምድና አሳውቋል።

ሞባይል ስልክ አብዝቶ መጠቀም ለጭንቅላት ካንሰር ያጋልጣል?

250 ሺህ በጎ ፈቃደኞች እና መራማሪዎች የተሳተፉበት ጥናት ውጤት ሞባይል ስልክ እና የጭንቅላት ካንሰርን ግንኙነት ይፋ አድርጓል
ሞባይል ስልክ አብዝቶ መጠቀም ለጭንቅላት ካንሰር ያጋልጣል?

የሰው ልጅ ተንቀሳቃሽ ስልክን ወይም ሞባይልን ከፈረንጆቹ ከ1990ዎቹ ጀምሮ መጠቀም መጠቀም ጀምሯል፡፡

ሞባይል ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን ህይወት ካቀለሉ ዘመን አመጣሽ ምርቶች መካከል ዋነኛው ሲሆን ቀስ በቀስ የሰው ልጅ እጅግ አስፈላጊ ምርት ወደ መሆን ተሸጋግሯል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ግን ሞባይል ስልክ የራሱ ጥቅም እንዳለ ሆኖ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዳሉትም አያጠያይቅም፡፡

በርካታ ተመራማሪዎች በተለያዩ ጊዜያት ይፋ ያደረጓቸው የጥናት ውጤቶች በሞባይል ስልክ ላይ ያለው ጨረር ወይም ራዲየሽን የራሱ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉት ሲሉ ቆይተዋል፡፡
ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ የሆነው አድኖሲን ምንድን ነው?
ሰዎች በብዛት ሞባይል ስልክን ሲጠቀሙ ከስልኩ ላይ የሚለቀቁት ጨረሮች አዕምሮን በመጉዳት ለጭንቅላት ካንሰር ያጋልጣሉ የሚሉ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር ተብሏል፡፡

ጤናዎ በእጅዎ

02 Sep, 17:18


#የእውነተኛ #ምጥ #ምልክቶች
======
ነፍሰጡር እናቶች የሚከተሉትን ምልክቶች ካዩ በፍጥነት ሀኪምቤት መሄድ አለባቸው

ጠንካራ የማህፀን መኮማተር

የታችኛው ጀርባ ህመም ወይም ግፊት

በሆድ ውስጥ ወይም በሆድ አካባቢ ውስጥ ቁርጠት

በደረት ወይም በታችኛው የሆድ ክፍል ውስጥ የክብደት ስሜት

በደም የተበከለው የንፋጭ ፈሳሽ መፍሰስ

የእንሽርት ውሃ መፍሰስ

የጉልበት መዛል ወይም እረፍት ማጣት

ከላይ የተዘረዘሩት የምጥ ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችል በመጨረሻ የእርግዝና ሳምንታት ላይ ያሉ ነፍሰጡር እናቶች ወድያው ሀኪም ቤት መሄድ አለባቸው።

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

02 Sep, 13:55


6. #ሲጋራ #ማጨስዎን #ያቁሙ👇
======+
ሲጋራ በጤናዎ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው። ሲዲሲ (CDC) ገለፃ ከሆነ በሲጋራ ውስጥ ከ 5,000 በላይ ኬሚካሎች ይገኛሉ እነዚህ ኬሚካሎች ለሰው ጤንነት በጣም ጎጂ ናቸው።

7. #በዘመናዊነት/#በሃላፊነት #ይዝናኑ👇
=====
የአልኮል መጠጥ ስንወስድ እንደ ቶኒክ ወይም እንደ መርዝ ይሰራሉ ነገር ግን ይህ የሚወሰነው በቀን ውስጥ የጠጡት መጠን ላይ ነው። መጠነኛ አልኮል መጠጣት ለልብና ለዝውውር ስርዓታችን በጣም ጠቃሚ እንደሆነ ይወሰዳል። በተጨማሪም በዓይነት ሁለት የስኳር በሽታ እና የሀሞት ጠጠር የመያዝ ዕድላችንን ይቀንሳል።

8. #መልካም #አመለካከት #ይኑርዎት👇
=======
ለህይወት ጤናማና በጎ አመለካከት መኖር ሌላኛው ጤናማ ህይወት እንድንመራ የሚረዳ ሚስጥር ነው። አነጋገርዎና ለህይወት ያለዎት አመለካከት አጠቃላይ ጤንነትዎ ላይ ቀጥተኛ
የሆነ ሚና አለው።

9. #በበዓላትና #የዕረፍት #ቀኖች #ራስዎን #ዘና #ያድርጉ👇
=======
እያንዳንድ ሰው በማንኛውም ዕድሜ፣ ፆታና የሃብት መጠን ላይ ቢገኙም መዝናናት ያስፈልጋቸዋል። ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ
ሲፋቱ እረፍትና መዝናናትን ይዞልዎት ይመጣል።

10. #የቤተሰብዎን #የጤና #ሁኔታ #ታሪክ #ይወቁ👇
====
የቤተሰብዎን የጤና ታሪክ ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው። ስለራስዎና የቅርብ ቤተሰብዎ የተመዘገበ የጤና መረጃ መያዝ በየትኛው የበሽታ ዓይነት የመያዝ ዕድልዎ ከፍተኛ እንደሆነ ፍንጭ ይሰጥዎታል።

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ

02 Sep, 13:52


#ለመቆየት_እነዚህን 10 (#ወርቃማ #ምክሮች #ይከተሉ!!
=========
1. #ጤናማ (አመጋገብ (ይመገቡ👇
=========
የሚመገቡት ምግብ ለሰውነታችን እንደ ነዳጅ በመሆን ያገለግላሉ። የተመገቡት የምግብ ዓይነት እና መጠን በቀጥታ የጤናዎን ሁኔታ ያስተጓጉላል። ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች
በሚመገቡበት ወቅት ሰውነትዎ ለበሽታ በጣም የተጋለጠ ይሆናል።

2. #ፈሳሽ (በብዛት #ይውሰድ👇
=======
ስለ አጠቃላይ የጤናችን ሁኔታ ስንመለከት ሰውነታችን የተትረፈረፈ ፈሳሽ ሊኖረው ግድ መሆኑን እናወራለን። በቂ የሆነ ፈሳሽ ሰውነታችን እንዲኖረው ቀኑን ሙሉ በቂ የሆነ ውሃ መጠጣት አለብን።

3. #ስፖርታዊ #እንቅስቃሴን (የህይወትዎ (አካል (ያድርጉ👇
=======
ጤናማና ከበሽታ ነፃ የሆነ ህይወት ለመምራት መደበኛ የሆነ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ብቸኛው የተሻለ አማራጭ ነው። እንደ ዕድሜዎ ወይም እንደ ብቃትዎ ሁኔታ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጊዜ መስጠት አስፈላጊ ነው።

4. #በተመስጦ #ወደ ውስጥ #መተንፈስን #ይለማመድ👇
=====
ጥልቅ ትንፈሳ ወይም በሌላ አገላለጽ የሚቆጣጠሩት አተነፋፈስ ጤናማ እንዲሆኑ በጣም ጠቃሚ የሆነ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
በተጨማሪም ጠንካራ የሆነ የሰውነት እና የአእምሮ ግንኙነት እንዲፈጠር ይረዳናል።

5. #የሰውነት #ክብደትዎን #በንቃት #ይከታተሉ👇
======
ወደ ሚዛን ላይ መውጣት ልምድዎ በማድረግ የሰውነት ክብደትዎን ቼክ ያድርጉ ወይም ይቆጣጠሩ። የተመጣጠነ የሰውነት ክብደት እንዲኖርዎ በማድረግ ውፍረትን ተከትለው
የሚመጡ በሽታዎች እንደ አርትራይተስ፣ የደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመምን በቀላሉ መከላከል ይችላሉ።