Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት @wubishet_mulat Channel on Telegram

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

@wubishet_mulat


Want to live the life of my choice!

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት (Amharic)

ውብሸት ሙላት - ውብሸት ሙላት የሚሰራበት ከባለው ሥር እና እስከ ሦስት ዓመት ውብሸት ሙላት ሲሆን እውን ለማግኘት አጋልጠናል። ምርጥ እና በተወጋገዝ ያለው ውብሸት ሙላት እናውቃለን። ውብሸት ሙላት ውብሸት ፣ የሽማቀት እና ምስሊግ ማንኛውንም ወቅታዊ ምርጥ ርዕስ በተናገሩ ይሰራል። ስለውብሸት ሙላት በቅናት የእርስዎን ሀምሌ ስለእናንት ውብሸት ሙላት የሚነሳቸው የመስራት ነገሮችን ለመማር አጋልጠናል። ውብሸት ሙላት ላይ እና ጽኑ ትብብር አሉት የውብሸት ሙላት ፣ የሕልም ውሳኔን እና የቢሮችን ልብስና አስፈላጊ አዝናኝ አስተናግዶ የማይሆን ነገር ነው።

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

10 Sep, 20:40


እንዲህ ነው እየተደረገ ያለው!

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

10 Sep, 19:48


አባ ባሕርይ በመጽፋቸው መጨረሻ እንዲህ ይላሉ፦

"ወአልቦ ከማነ ዘረከበ ፀረ ዘይተግህ ለገቢረ እከይ"

የአማርኛ ፍቺውም፦

"ክፋት ለማድረግ የሚተጋ ጠላት እንደኛ ያገኘ የለም።" ማለት ነው።

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

24 May, 19:01


Channel photo updated

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

24 May, 18:58


ጄኔራል ሑሴን አህመድ

ስለ ጄኔራል ሑሴን አህመድ የሰማሁት በልጅነቴ ነው። ዕድሜዬ 7 ወይም 8 ዓመት ገደማ እያለ። ወቅቱ ኢትዮጵያ ከወያኔና ከሻዕቢያ ጋር የሚደረገው ጦርነት በእኛ ሰፈርም ደርሶ ነበር። በተለይ በ1982 ጥቅምትና ጥር እንዲሁም በ1983 ደግሞ ከዓመቱ አጋማሽ በኋላ። በሰፈራችን ምሽግ ከነበራቸው የሠራዊቱ አባላት ጋር ቅርርቦሽም ነበረን። ስለወታደር፣ ስለጠላት ወዘተ እንሰማለን፤እናውቃለን፤ልጅ የሚያውቀውን። የጦርነቱን ኹኔታ በራዲዮ ማዳመጥ የተለመደ ቋሚ ልማድ ነው። ሱስም ነበር። የኢትዮጵያ ራዲዮ፣ዶቼቬሌ፣ቪኦኤ... ጣቢያና ኳርት እያስተካከሉ ሕጻን አዋቂ ሳይሉ ጸጥ ብሎ መስማት የወቅቱ ግዴታ ነበር።

በዜናዎች መካከል፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ስማቸው ከሚነሱ ወታደራዊ አዛዦች መካከል አንዱ ሜ/ጄ ሑሴን አህመድ ነበሩ። የእሳቸው ስም ሲነሳ፣ አባታችን "ጄኔራል ሑሴን እኮ የከድጆ ሰውን ነው" ይለን ነበር። ከድጆ፣ ወሎ፣ ደሴ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ያለ ሰፈር (ቀበሌም ማለት ይቻላል) ነው። እኛ መንደር ሆኖ አሻግሮ ይታያል፤ የቀበሌያችን አዋሳኝም ነው።። ከሰፈራችን፣ ከአስር እስከ አስራ አምስት ኪሎሜትር ቢርቅ ነው። እኛም የእኛ አቅራቢያ አካባቢ የሆነ ሰው ጄኔራል ሆኖ፣ በጀግንነት ስሙ እየተወሳ በራዲዮ ሲነገር፣ ከ local identity የመነጨ የሚመስለኝ፣ ኩራት ይሰማናል። እናም አእምሯችን ታትሞ ቀርቷል። በዚህ መነሻነት በልጅነት አእምሮ የሠረፀ አክብሮት አለኝ።

በእርግጥ ኋላ፣ ጦርነቱም አልቆ፣ ዓመታትም አልፈው ጄኔራል ሑሴንም መጽሐፍት ጽፈው፣ ሌሎችም ስለእሳቸው ጽፈው አንብቤያለሁ። የእሳቸውን "መስዋዕትነትና ጽናት" የሚለውን ሳነብ "ሬትና ማር" የሚለውን ግን መጽሐፉን ባለማግኘትም (አጥብቆ ካለመፈለግ በመነጨ ስንፍናም ጭምር) አላነበብኩትም።

"መስዋዕትነትና ጽናት" አጠር ቀልበጭ ያለች መጽሐፍ ናት። ስለጦርነትና ውትድርና ዳራ ከኢትዮጵያ አንጻር ማስታወሻዎችን በማስቀደም፣ ጄኔራሉ በሐረር የጦር አካዳሚ በ1953 ተመርቀው ፣ ሆለታ ገነት አስተማሪ ሆነው እንደጀመሩ የ53ቱ መፈንቅለ መንግሥት ስለተከሠተ በወቅቱ መፈንቅለ መንግሥቱን ለማክሸፍ ተመድበው ስለነበር ያዩትንና የተረዱትን አካትተዋል። በመቀጠል፣ በትምህርት ቤቱም፣ በመከላከያ ሚኒስቴርም የነበራቸውን ታሪክ፣በተለይም ስለደርግ መንግሥት አቋቋም ሒደት በቅርብ የማያውቁትንና የታዘቡትን አጋርተውናል። ከዚያም ስለራዛ ዘመቻ ውድቀት እና አሳዛኝ የገበሬዎች እልቂት፣ በ"ታጠቅ" የሚኒሻው ሥልጠና ጀምሮ በኤርትራ ስለነበራቸው ከ12 ዓመታት በላይ ቆይታ፣ ከብርጌድ መሪነት እስከ ኹለተኛው አብዮታዊ ሠራዊት አዛዥነት የነበራቸውን ወታደራዊ ታሪክ፣ ስለ 1981 የመንፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኤርትራ ስለነበረው ሁኔታ፣ እንዲሁም መንግሥቱ ኃይለማርያም ግንቦት 13 ቀን 1983 ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ አስመራና ዙሪያው እስከ ከረን ስለነበረው የአገር መከላከያ ሠራዊትና የአስመራ ሕዝብ ሁኔታ ብሎም የእሳቸውን ውሳኔና ወደሳዑዲ መሔድ ማብራሪያዎች ይዟል።

በመጽሐፉ ማጠቃለያም ከሕይወት ተሞክሯቸው ዕውቀታቸው በመነሳት ስለመንግሥት ሥልጣን አያያዝ፣ ሥልጣን ላይ ለወጡ ሰዎች እና ሕዝብ፣ የተወሰኑ ምክረ ሐሳቦች አካፍለዋል። የትዝብታቸው መነሻ የደርግ መንግሥት ነው፤ ይኹን እንጂ ለአኹንም ለወደፊትም የሚሆኑ ምክረ ሐሳቦች ናቸው። ከእነዚህ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።

መንግሥትነትን በእጃቸው ስላደረጉ ሰዎች ወይም ስለመንግሥት እንደሚከተለው ይመክራሉ፤ ጄኔራሉ፦

አንድ፦
"በአጋጣሚም ሆነ በዕቅድ ሥልጣን ላይ የሚቀመጥ መንግሥትም ‹‹መካር የሌለው ንጉስ ያለ አንድ ዓመት አይነግስ›› የሚባለው እንዳይሆን ሥልጣን በመያዙ ትምክህቱንና መቆነኑን ትቶ ለሥልጣንና ለጥቅም ምላሳቸውንና ጅራታቸውን የሚቆሉትን ሳይሆን በሳል እና ለሀገር ተቆርቋሪ የሆኑትን በማስጠጋት በምክራቸውና በችሎታቸው በመጠቀም አመራሩን ማፅናት አለበት፡፡ የአንድ መንግሥት ፅናቱ ፍትሃዊ ሥርዓት መዘርጋቱ ስለሆነ ሆደ ሰፊ በመሆን የምህረትና የፍትሕ ባለቤትም መሆን ይገባል፡፡" (ገጽ -209)

ኹለት፦
ጀኔራሉ የባለሥልጣናት ተረጋግቶ የማሰብ ዝንፈት የበሳል ሰዎችን ምክር ወደጎን መግፋት፣ ከምክንያት ይልቅ ስሜትን፣ ከአእምሮ ይልቅ ልብን መጠቀም የሚያስከትለውን ጉዳት የራዛ ዘመቻንና የመንግሥቱ ኃይለማርያምን ውሳኔ አስረጂ አድርገው የሚከተለውን ይመክራሉ። "መንግሥቱ በነበራቸው አቅም ብዙ ጊዜ በጉጉት፤ በስሜትና በልባቸው ስለሚሰሩ ሎጅኩን (ሂሳቡን) ትተው ሙያቸው ያልሆኑ ሰዎች የሰጧቸውን ሀሳብ አስተናገዱ እናም የራዛ ዘማች እንደቅጠል እረገፈ፡፡" (ገጽ -215)

ስለሕዝቡም የሚከተለውን አስፍረዋል፦

ሦስት፦
"ሕዝቡም ቢሆን ቀድሞውኑ ደፋር (ባለጌ) እና ያለአዋቂ ሥልጣን ላይ እንዳይወጣ መታገልና መፀለይ እንጂ አንዴ ሥልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጠ በኋላ እሪ ማለት ከንቱ ነው፡፡ ያለ አቅሙና ያለ ችሎታው እንዲሰራ ከመጠበቅ ይልቁንስ በቅርብ በምክርና በችሎታ በማገዝ አመራሩን እንዲያሻሽል ልብ እንዲገዛ መርዳት ነው፡፡" (ገጽ 210-1)

ባለጌና አቅመቢስ አንዴ ሥልጣን ከያዘ ሕዝብና አገር ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጠቋቁመዋል።

****
ጄኔራል ሑሴን አህመድ በብዙ መጽሐፍት ስማቸው በበጎነት፣ በአባታዊነታቸው ከሚነሱት የጦር መሪዎች አንዱ ናቸው። እርግጥ ነው፣ ውቃው እዝ ላይ በደረሰ የጠላት ጥቃት ታስረው ያውቃሉ። ከዚያ ያለፈ ግን፣ የሚነሳው በሠራዊቱ ዘንድ ስለነበራቸው አባታዊ አስተዳደርና አመራር ይበዛዋል።

ጀኔራል ሑሴን ደሴ ወ/ሮ ስኂን እስከ 8ኛ፣ አዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን እስከ 12 ድረስ ተምረው የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ሐረር መድኃኔ ዓለም ተፈትነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻ ኮሌጅ መመር እንደጀመረ በንጉሣዊ ትእዛዝ የሐረር የጦር አካዳሚ በመግባት የመጀመሪያ ኮርስ ተመራቂ ናቸው። በሕዝብ አስተዳደር በመጀመሪያ ድግሪ አዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ተምረዋል።

ጄኔራል ሑሴን አህመድ ግንቦት አጋማሽ 1983 ከአስመራ ወደ ሳዑዲ ሔዱ። ከ32 ዓመታት በኋላ ግንቦት አጋማሽ ሕይወታቸው አልፎ ሥርዓተ ቀብራቸው ሌላ አገር (አሜሪካ) ተፈጸመ።

ፈጣሪ ለነፍሳቸው ዘላለማዊ ዕረፍት፣ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናቱን ይስጣቸው!

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

10 May, 15:04


አንድ በጣም የሚገርም፣ ምናልባትም የሚያሳዝን፣ መንግሥትነትን ከተቃዋሚነት ጋር ደርቦ የመጓዝ አካሔድ በኢትዮጵያ ተለምዷል። ይሄውም፣ መንግሥት መር የተቃውሞ ሰልፍ ነው። ኢትዮጵያ ላይ ጫና የሚፈጥሩ፣ ጣልቃ የሚገቡ አገራትን ወይም ቀጠናዊ፣አኅጉራዊ ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በመቃወም እንደአገር በመንግሥት አስተበባሪነት ሰልፍ ቢደረግ፣ መረዳት ይቻላል። ብሔራዊ በዓላትን መነሻ በማድረግ አንድነትን አርበኝነትን ወዘተ ለማጠናከር ሰልፍ ቢደረግም፣ መረዳት ይቻላል። ምርጫ ቀርቦ፣ መንግሥትነትን የጨበጠ ገዢ ፓርቲ (በፓርቲነቱ) የድጋፍ ሰልፍ የጠራና ቢያደርግ፣ የተለመደ ነው፤መረዳት ይቻላል።

ነገር ግን፦

መንግሥት ሆኖ ስለ አገር ውስጥ ጉዳዮች በተለይም በሕጋዊና አስተዳደራዊ አካሔድ መፍትሔ ሊሰጥባቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች እንዲሁም መንግሥታዊ ፖሊሲዎችንና የፖለቲካ ውሳኔዎችን የሚመለከቱ መንግሥት መር ሰልፎች ማካሔድ አስገራሚ ነው። እንዲህ ዓይነት ሰልፎች በደርግ ጊዜ ነው በስፋት በኢትዮጵያ የተዋወቁት። ደርግ/መንግሥቱ ሊወስዳቸው ያሰባቸውን እርምጃዎች (ለምሳሌ የኢሕአፓ አባላትን ወይም ኢሕአፓ ተብሎ የተጠረጠረን)፣ ሕዝቡ ስለጠየቀ ነው የሚል ሰበብ ለመስጠት ደርግ መር ሰልፎች ተካሒደዋል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ደርግ/መንግሥቱ የወሰዳቸውን እርምጃዎች (ለምሳሌ የእነ ብ/ጄ ተፈሪ በንቲን ግድያ ተከትሎ) ሕዝብን ሰልፍ በማስወጣት "አብዮቱን ከቀልባሾች እንከላከላለን" ዓይነት ይዘት ያላቸውን መፈክሮች በማሰማት ግለሰባዊ/መንግሥታ(ቷ)ዊ ሕገወጥና ቅጽበታዊ ግድያዎችን (Summary Execution) ሕዝብም ደግፏቸዋል የሚል የማታለያ ምክንያት (justification) ለማቅረብ ሰልፍ ይደረግ ነበር። ደርግ/መንግሥቱ የሚፈቅድላቸው ድርጅቶች፣ለምሳሌ መኢሶን፣ እነኢሕአፓ በመንግሥት/በደርግ እንዲመቱ ሰልፍ ሲደረግም ይፈቀድ ነበር፤ያው መንግሥት መር የተቃውሞ ሰልፍ ስለሆነ። ይሁን እንጂ በተቃራኒው ደርግን የሚቃወም ሰልፍ በእነ ኢሕአፓ ቢጠራ ደርግ አይፈቅድም፤አይደረግም። ከተደረገም እስራት፣ድብደባ ወዘተ መከተሉ አይቀሬ ነው። በአጭሩ፣ በደርግ ዘመን መንግሥት መር የተቃውሞ ሰልፎች በኢትዮጵያ በስፋት ተዋወቁብን፣ተለመዱብን።

በዘመነ ኢሕአዴግም፣ የተቃውሞ ሰልፎች አልፎ አልፎ ቢደረጉም መንግሥት መሮች የተቃውሞ ሰልፎችም አልፎ አልፎ ነበሩ። ይሁን እንጂ የኢሕዴግ ትኩረት ተቃዋሚዎች የሚያካሒዷቸውን የተቃውሞ ሰልፎች በሰበብ አስባቡ መከልከል እንጂ መንግሥትነትንም ተቃዋሚነትንም በመደረብ መንግሥት መር የተቃውሞ ሰልፍ ማካሔድ እምብዛም አልነበረም።

በዘመነ ብልጽግና የሚካሔዱት ሰልፎች ደግሞ፦

፩. የሌሎች አገሮችን/ድርጅቶችን ጣልቃገብነት በመቃወም ለመንግሥት/ለአገር የሚደረግ የድጋፍ ሰልፍ፣

፪. ለብልጽግና ወይም ለመሪዎቹ የሚደረጉ የድጋፍ ሰልፎች፣

፫. መንግሥት ሊወስዳቸው ያሰባቸውን እርምጃዎች ታሳቢ ያደረጉ መንግሥት መር የተቃውሞ ሰልፎች (ሸኔን፣ ሕወሃትን፣ ጽንፈኞችን፣ የእነ እንቶኔን ገዳዮች ወዘተ እናወግዛለን የሚሉ)፣ ናቸው።

እንዲህ ዓይነቶቹ ሰልፎች በመንግሥት በተደጋጋሚ ተካሒደዋል። መካሔዳቸውም ቀጥሏል። በዘመነ ብልጽግና እውነተኛና የምር (Serious ጉዳዮች ላይ) የመንግሥትን አካሔድ፣ ውሳኔዎች፣ ዝምታዊ ድጋፎች ወዘተ በመቃወም ድምጽ ለማሰማት የተቃውሞ ሰልፎችን ማድረግ፣ በተለይም በአዲስ አበባ፣ 'ፍጹም ክልክ' ሆኗል። የተጠሩ የተቃውሞ ሰልፎች ሰበቦችን በመደርደር ተከልክለዋል። ለምሳሌ ባልደራስ ፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን የጠራቸውን መጥቀስ ይቻላል። መንግሥት/ብልጽግናና መር የሆኑ ግን የትየለሌ ሰልፎች ተደርገዋል።

ሰልፍ በማድረግ ተቃውሞን የመግለጽ መብት መነሻውና ጥበቃ የተደረገለት ዜጎችን እና/ወይም ሰብአዊ ፍጥረትን ታሳቢ በማድረግ ነው። ለዚህም ነው የሰብአዊ መብት፣ የማንኛውም ሰው መብት የሆነው። ሰልፍ "የድሆች ሚዲያ ነው" የሚባለውም ለዚህ ነው። መንግሥት የሰዎችን መብት የተቃውሞ ሰልፍ የማድረግ (the right to protest or conduct demonstration) መብትን እንዲከበር (ከማደናቀፍ በመቆጠብ የማክበር-the duty to respect)፣ በሌሎች እንዳይደናቀፍ ጥበቃ በማድረግ የማስከበር (duty to ensure respect) እና ሰልፍ የማካሔድ መብትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዙ ነገሮች (ለምሳሌ የሰልፍ ቦታ...) የማሟላት (duty to provide) ግዴታ ነው ያለበት።

እንዲሁም፣ ትንሽ ነፍስ ያለው መንግሥት ቢኖረን የተቃውሞ ሰልፍ በሚደረግበት ጊዜ/ቦታ የሚመለከታቸውን ባለሥልጣናት በመመደብ በተቃውሞው ሰልፍ የተነሱትን ጉዳዮች መስማት፣ ለሰልፈኞች ምላሽ መስጠት የመሳሰሉትን መፈጸም መንግሥትነት ግዴታ ነው፤ ተቃውሞን አልሰማም ብሎ መደበቅ ሕዝብን መናቅ ነው፤ ለዜጎች ድምጽ ደንታቢስ መሆን ነው። በዓጼ ኃይለሥላሴ ዘመን ሰልፎች ሲደረጉ የሰልፈኞቹን ድምጽ ለመስማት፣ ለጥያቄያቸው ምላሽ ለመስጠት ብዙ ጊዜ ባለሥልጣናት ይመደቡ እንደነበር ብዙ አስረጂዎችን በዋቢነት መጥቀስ እንችላለን።

ከደርግ ጀምሮ ወደአገራችን የገባው የተቃዋሚን መብት (የዜጎች፣የማንኛውም ሰው መብት) መንግሥትነት ወሰደውና በመንግሥታዊ ሥልጣንና ኃይሉ ላይ ተቃዋሚነትንም ደረበቡት። የፓርቲና የመንግሥትን መዋቅር መሠረት አድርጎ መንግሥት መር የተቃውሞ ሰልፍ ሲጠራ፣ የእኛ አገር ገዢ ፓርቲዎች በቀለኝነታቸው የበዛ ነውና በቀልን ፍራቻ በርካታ ሰው ሰልፍ መውጣቱ የሚቀር አይደለም።

መንግሥት መር በአገር ውስጥ ጉዳዮች ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ከተካሔደ፣ መንግሥት ሊወስደው ያሰበው እርምጃ አለ ማለት ነው። እየወሰዳቸው ላሉ አደገኛ እርምጃዎች ሕዝቡ ስለጠየቀ ወይም ስለደገፋቸው ነው እንዲህ ያደረኩት የሚል የማስመሰያ justification ለመስጠት ነው። እንዲህ ዓይነት አካሔድ ፍትሕን ይደፈጥጣል፤ ለሕገወጥ ውሳኔ ሽፋን ማበጀት ነው። ውሎ አድሮ መዘዙ የተባበረ ተቃውሞ መጥራት ነው። እና ሌላ የጥፋት አዙሪት!

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

10 May, 13:20


ደርግ፤ የብልጽግና መስተዋት ወይም ብልጽግና ማለት ደርግ በኢሕአዴግ ተከሽኖ፤


የደርግን አመሠራረት፣ ዙፋን ላይ መውጣት፣ ሥልጣንን ማደላደል፣ ወዲያውኑ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን (ዋናዎቹ መሬትና የከተማ ትርፍ ቤት፣ የግል የልማት ድርጅቶችን መውረስ፣ የሠራተኛ ሕግ ማውጣት፣ የእስልምና ዕምነትን የሚመለከቱ ናቸው) በማድረግ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማቅረብ (ከኢሕአፓ በስተቀር) በአንድ ላይ በመሥራት (መኢሶን፣ ወዝሊግ፣ ኢጭአት፣ ማሌሪድ እና ሰደድ)፣ ከዚያም መጀመሪያ ላይ ያስጠጋቸውን ድርጅቶች ቀስ በቀስና አንድ በአንድ ካፀዳቸው በኋላ ደርግንም ጭምር አጥፍቶ ኢሰማአኮን ከዚያም ኢሰፓን በመመሥረት መንግሥቱ የሁሉም ነገር ቁንጮ አደረገ።

ከሦስተኛው ክ/ጦ የመጡ እና/ወይም በመሀላ ከተሣሠሩት ከለገሰው አስፋው፣ ከገብረየስ ወልደሃና፣ ከተስፋዬ ገብረኪዳን፣ ከመንግሥቱ ገመቹና ከደመቀ ባንጃው እንዲሁም የደርግ አባል ያልነበሩ ነገር ግን ከመንግሥቱ ጋር ተመሳሳይ ማኅበራዊ መደብ ስላላቸው ከተስማሙት ወይም በዚህ ምክንያት አመኔታ ከተጣለባቸው ውጪ ያሉት ተራገፉ።

ደርግ ሲመሠረት ለንጉሠ ነገሥቱ ታማኝነቱን ገለፀ። ለንጉሠ ነገሥቱ በመታመን ሚኒስትሮችን አሰረ። ሚኒስትሮችን አስሮ ሲጨርስ ወደ ጃንሆይ ዞረ። የደርግ መሥራች የነበሩና በትምህርታቸውና በፖለቲካ ግንዛቤያቸው የተሻሉትን በሙሉ አስወገዳቸው። ወደመጀመሪያው ገደማ ከነ ዶ/ር ሰናይ ልኬ(ወዝሊግ)፣ ከእነ ኃይሌ ፊዳ(መኢሶን)፣ ከእነ ዘገዬ አስፋው (ኢጭአት)፣ ከደጃዝማች ከበደ መንገሻ፣ ከእነሚካኤል እምሩና ከሌሎችም ምሁራኖች ምክር ይሰማ ነበር። ቀስ እያለ ሁሉን አዋቂ በመሆን ማንንም መስማት አቆመ።

የእሱን አቋም በመጻረር የተለየ ሐሳብ ያላቸውን የደርግ አባላትን ሳይቀር በሙሉ አስወገዳቸው። ደርግን የፈጠረውን፣ ሻለቃ አጥናፉ አባተንም ጭምር ገደለ። ከዚያ መንግሥቱን ቀና ብሎ ማየት ሳይቀር አስፈሪ ሆነ።

መንግሥቱ ኃይለማርያም ወደ ሆለታ ወታደራዊ ማሠልጠኛ የገባው 9ኛ ክፍል እያለ ነው። አንድ ዓመት ወታደራዊ ሥልጠና ወስዶ በምክትል መቶ አለቃነት ተመረቀ። ከዚያም የ3ኛው ክፍለ ጦር አባል ሆነ። ወደ አሜሪካ በመሔድ ወታደራዊ የድርጅት አስተዳደር (Military Logistics Management) ሥልጠና ወስዷል። ከዚህ መደበኛ ትምሕርት የለውም። [አንዳንድ ሰዎች የማታ በመማር 12ኛ ክፍል ጨርሷል ይላሉ።] ነገር ግን በውትድርናው፣ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በታሪክ ወዘተ በሁሉም ነገር ራሱን አዋቂ አድርጎ ቆጥሯል። የሁሉም ነገር መቋጫውና ተፈጻሚ የሚሆነው የእሱ ዕውቀት ነው። አደጋው ይሄ ነው።

መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ ከመደበኛ ፖሊስና ደኅንነት ወይም የፀጥታ አደረጃጀት ውጪ የተለየ መቺ ኃይል፣አፋኝና ገዳይ ቡድን አደራጅቷል። ፀረ-መንግሥቱ ኃይለማርያም የሆኑትን ወይም ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው የተገመቱትን የሚያስወግዱ ናቸው። የእንዲህ ዓይነት ቡድን አባላት የሆኑ ሰዎች ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ራሳቸውም እንዲወገዱ እየተደረገ በሌላ ይተካሉ። ብዙ ከቆዩ ምስጢር ይወጣላ! ለመንግሥቱ ኃይለማርያም መደበኛው መንግሥታዊው መዋቅር በቂው አልነበረም።

ደርግ ማለት መንግሥቱ ሆነ። አማሌድህም ማለት መንግሥቱ ሆነ። ኢሰፓአኮም ማለት መንግሥቱ ሆነ። ኢሰፓም ማለት መንግሥቱ ሆነ። የኢሕዲሪ ሕገ መንግሥትም ማለት መንግሥቱ ሆነ። ከመንግሥቱ የተለየ ደርግ፣ኢሰፓአኮ፣ ኢሰፓ፣ ኢሕዲሪ አልነበረም። የእነዚህ ድርጅቶች፣ፓርቲዎች አባላትም መንግሥቱ ኃይለማርያም ከሚናገረው ምናልባትም ከሚያስበውም ጭምር ውጪ መናገርም ማሰብም እንዳይችሉ ተደረጉ። ለአርሶ አደሩ መኢገማ፣ ለሴቶች፣ አኢሴማ፣ ለወጣቶች አኢወማ ተደራጅቶ ፓርቲው (መንግሥቱ ኃይለማርያም) ሁሉም ጋር ደረሰ። የጦር ሠራዊት አባላቱን ሳይቀር የፓርቲ እንዲሆኑ አደረገ። በሠራዊቱ ውስጥ (ሠራዊት፣ በኮር፣ በክፍለጦር፣ በብርጌድ፣በሻለቃ ወዘተ) ሳይቀር የፓርቲ ኃላፊዎች ተመድበው ሁሉም ነገር በአንድ ሰው ቁጥጥር ሥር ዋለ። ለወታደራዊ ፓለቲካ ሻምበል ገብረየስ ወልደሃና (ኋላ ብርጋዴር ጄኔራል የተባለ)፣ ለፓርቲው መጋቢ ሃምሳ አለቃ (ኋላ ሻምበል የተባለ) ለገሰ አስፋው ተመደቡ። እነዚህ የመሃላ ጓደኞቹ ናቸው። እንዲህ እያደረገ ሁሉንም ነገር በመዳፉ አስገባ። ከዚያም "እንደንጉሡ አጎንብሱ" ሆነና ሁሉም እንደመንግሥቱ ተንፍሱ ሆነ ነገሩ።

የደርግ ወደ ሥልጣን አመጣጥ፣ በተለይም የመንግሥቱ ኃይለማርያም አካሔድ፣ሥልጣን ማደላደል፣ ሕዝብን ያታለለበትና ያስመሰለበት ሁኔታዎች፣ እያደር የተገለጠው የመንግሥቱ ማንነትና ስብእና ወዘተ በደንብ ላጤነ ሰው ብልጽግና ፍንትው ብሎ ይታየዋል። የደርግ አባላት የሕዝቡን ትግል ነፋስ አምጥቶላቸው የተቀበሉ ናቸው፤ እራሳቸው ያልታገሉ፤ ነጥቀው የወሰዱ። የአሁኑ የብልጽግና ቡድንም መሪና የጠራና የታወቀ ግብ ያልነበረውን የፀረ-ኢሕአዴግ ተቃውሞ የትግል ውጤት "ቲም ለማ" ወዘተ በሚል አፈፍ አድርጎ ቀጨም አድርጎ የወሰደ ነው። ደርግና ብልጽግናን የሚያመሳስላቸው የትየለሌ ነው። ወደሥልጣን አመጣጡ፣ አብረው የመጡትን የተራገፉበት አኳኋን፣ ከኢሕአዴግ ወደብልጽግና ያደረገው ሽግግር፣ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር አብሮ የመሥራት ሙከራ (አሁንም የቀጠለ)፣ መጠነኛ የሕግና የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግና ማቆም፣ ትይዩ የፀጥታ ኃይል ማቋቋም...... እነዚህ በጣም ጥቂቶች ናቸው። እንደውም ከመመሳሰልም አልፎ ብዙ ነገር ተኮርጇል። ግለሰባዊ ባሕርያትም ጭምር!

ይሁን እንጂ ብልጽግና ሁለት አደገኛ የክፋት እርምጃዎችን ወደፊት ተሻግሯል። አንዱ እንደደርግ የፓርቲና የመሳሰሉት አደረጃጀቶች መጠቀም ሳያስፈልገው ዜጎችን በስልክና በሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ያገኛቸዋል፤ ይደርስባቸዋል። ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ ወደ ጠቅላይነት (totalitarian) የተደረገ ሽግግር። ሁለተኛው፣ ብልጽግና ከደርግም በተጨማሪ ኢሕአዴግን አክሎበታል፤ ደርግ በኢሕአዴግ ተከሽኖ እንደማለት። ደርግ ላይ ዘረኝነት! በጣም አደገኛውና የከፋው ይሔ ነው፤ ሁለተኛው። በደርግነት ላይ ኢሕአዴግነት!

አሳዛኝ የጥፋት አዙሪቱ እንዲህ እያለ ይሽከረከራል! ተቋም መገንባት ያልቻለ አገር የመንግሥቱ ኃይለማርያም ዓይነት ሰዎች መጫወቻ ሆና ነው የምትቀረው። በሳል መሪ እና የጠራ ዓላማና ግብ የሌለው ትግል፣ ውሎ አድሮ ትግሉ ቢገፋና አገዛዝን የሚቀይር ጉልበት ቢፈጥር እንኳ፣ ጫፉ ላይ ሲደረስ በመጨረሻው ሰዓት በመንግሥቱ ኃይለማርያም ዓይነት ደፋርና ዓይናቸውን በጨው ባጠቡ ሰዎች መነጠቁ የማይቀር ነው። ለዚህ ደግሞ ከደርግም በተጨማሪ ብልጽግና ሁለተኛው ምስክር ነው! ለዚያውም በደርግነት ላይ ኢሕአዴግነትን የደረበ!

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

25 Apr, 21:05


(ከታች የቀረበው ጽሑፍ ከትግርኛ የተመለሰ- የኤርትራ/ውያን ምልከታ ነው።)

ቀናት ያለፈበት ሥጋ ከመሽተት አይድንም
==================
ሞኛሞኝ ሴት የራሷ ወጥ ይጣፍጣል ይሉት ተረት እንደዛሬ ሁነኛ ትርጉሙን አግኝቶ አያውቅም ።

ብልሆች ለአመታት ፤ ሞኞች ደግሞ የእለቱን ያስባሉ ።
ከባዱ የጨለማ ጊዜ ሲያልፍ አያ ገብስ ክረምቱን ባሳለፈ ጎመን ላይ ሲመፃደቅበት ማየት ንቡር ሆኖ በገሃድ በኢትይጵያ ሰማይ ስር አይተናል ።

በአሁናዊ የምስራቅ አፍሪካ ላይ ቆሞ መፃኢውን መተንበይ አስቸጋሪ መጠላለፍ የሞላበት መሆኑ ነጋሪ ሳያሻው ፀሐይ የሞቀው እውነት ሆኗል ። አንዳንዱ አቅም አጥቶ ፤ ማሰሪያ እንዳጣ ሰው ፍልጡን መሬት ላይ ዘርግፎ ይሰንዳል ፤ አንዳንዱ ቂጡን ገልቦ እንደ አዞ ይውጣል ፤ አሳህን ከሱዳን ጀምረህ ወደ ኢትዮጵያ ገብተህ ስትፈትሽ እየህነው ያለው ሁሉ ግርም ይላል ።

መቼም የኢትዮጵያ ፖለቲካን ልክ እንደ ሁለቱ ሰካራሞች ነው ፤ ፑል ሲጫወቱ አምሽተው በብር ይጣሉና በአረቄ የሚታረቁ አይነት ነው ፤ እግራቸው እስኪሽመደመድ ሲጋቱ አድረው ተደጋግፈው የሚሄዱ አይነት ነው ፤ ሰክረዋል ስትላቸው ፈትል ገትረው በፈትል የሚራመዱ ፤ ውሃ ጠጥተዋል ሲባሉ ደግም በተቃራኒው ዝርግት ብለው ሜዳ የሚንደባለሉ ፤ የት ናቸው ? ወዴት ነው አቅጣጫቸው ፍፁም የማይገባ ውንግርግር ያለ ሆኗል ነገሩ ሁሉ ።

በመንገዱ ላይ እየተመላለስክ ፤ በመንገዱ ላይ ሂያጅ ሴት ትፈልጋለህ !

አንድ አገር ነው አሉ ሁለት ሴቶች በአንድ ወንድ ተቀናኑና ፤ አገሬው ከቦ በትዝብት እያዬ እየተቧቀሱ ሲናጩ ማየት ይዟል ፤ አንዷ ድስት ስትወረውር አንዷ ፈርኔሎ ( የከሰል ምድጃ ) ትወረውራለች ፤ በአጠቃላይ ከተማው ሁካታ ነገሰበት ፤ ጎረቤቶች ተረበሹ ፤ ለአይን ያዝ ሲያደርግ ወደ ረብሻው እንዳይገቡ የአካባቢው መሰብሰብ ጀመረ ፤ በመጨረሻም አገሬው አቅሉን አሟጦ የነዚህ ረብሸኞች ጉዳይ ለፍርድ መቅረብ አለበት ወደሚል ውሳኔ ገቡ፤ በዚህም መሰረት ሴቶቹ ተከሰው ወደ ችሎት እንዲቀረቡ ተደረገ ።

ታላላቅ የሀገር ሽማግሌዎቹም በነዚህ ሁለት የተለከፉ ሴቶች ከጉዳያቸው እንዲቀሩ ሆነ ፤ ሁሉም ከዋርካ ዛፍ ጥላ ስር እንዲሰበሰቡ ግድ ሆነ ፤ ወንድም ጭራውን ሴቱም ነጠላውን አንጠልጥለው ወደ ችሎት ወረዱ ። የአገሬው ሹም የነዚህ ሴቶች ጉድ ለመስማት በሽበት የተሸፈወነውን ጆሮአቸውን እየኮረኮሩ ሲሰሙ ከቆዩ በኋላ እንዲህ የሚል ሃሳብ ሰጡ - -

"መቼስ ምቀኛ ጠላቱን ይተክላል ፤ ወዳጁን ደግሞ ይነቅላል አይደል የሚባለው ፣ እናንተ ደግሞ በጣም የምትቀራረቡ የልብ ወዳጆች እንደነበራችሁ ነው አገሬው የሚያውቀው ፤ ይሁንና በአንድ ወንድ ምክንያት አንባጓሮ ውስጥ ነው የቆያችሁት ፤ አሁን አገር ስለታወከ ጉዳያችሁን እናያለን
"
በማለት ጉዳያቸው እልባት እንደሚበጅለት አወጁ ።

በዚህ ጫጫታ በበዛበት ሙግት " እሽሽሽ እሽሽሽ እስኪ ዝግ በሉ " በማለት አፋቸው አስያዙአቸውና ፤ ወደ ጠቡ ያስገባቸውን ወንድ ጠሩና
" አንተ እሳ ማንኛዋን በመረጥክ ነበር ?"
በማለት ጠየቁት ። በአጎቶቹ መሀል ተቀምጦ ሙግቱን ሲሰማ የነበረው ወንዱ ሰው

" አይ - ክቡር ሆይ ፤ ከነቀዝ እና ከምስጥ ማንን ይመርጣሉ ቢባሉ ማንን ይመርጡ ነበር "
በማለት ጥያቄው በጥያቄ ለአገሬው ሹም መለሰላቸው ። ሹሙ ጥያቄው ግራ ገባቸው እና እኔ እንጂ ሲሉ መለሱለት ፤ በመልሳቸው የልብ ልብ የተሰማው ወንዱ ሰው " ሁለቱም የእህል ቀበኞች ናቸው ፤ ምን በረከት አላቸው " በማለት ሊድን በማይችል ጉዳይ ላይ መፍትሔ ለማምጣት በከንቱ ሲደክሙ እንደቆዩ ለአገሬው መርዶውን አሰማ ።

--------------------------------------
ዓይናችን አድማ እያደረገ እንጂ የምናየው ነገርስ ....
--------------------------------------

ወያኔ (ትህነግ )--- የኢትዮጵያ መንግስት በምዕራባውን ሃገራት ጫና አጀንዳዎቹ አደጋ ላይ የወደቀ ከመሆኑ አንፃር ፤ ውስጣዊ አንድነቱን ማፅናት የቸገረው ብልፅግና ስልታዊ አንድነት ( Tactical alliance ) በመመስረት
የ" ጊዜ መግዣ ዕድሎችን በማማተር " ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛል ። የብልፅና ሰልፍ በሁለት ጎራ መከፈሉ ለወያኔ ( ለትህነግ ) መሪዎች ፍንትው ብሎ ተገልጾ ታይቷቸዋል ።

ወያኔ ( ትህነግ ) -

የውስጥ አንድነቱን መፍጠር ያልቻለው ብልፅግና ፤ የሒሳብ ስሌት ሲያጣፋ ወደ ቆየው ጠ/ ሚኒስትር ቀርቦ ሲሸረሽረው መሠንበቱ ብዙም ሊገርመን አይገባም ።
በአማራ ክልል የተሳው ህዝባዊ እንቢተኝነት ለኢትዮጵያ መንግስት እንቅልፍ የሚሰጥ አልሆነም ። በተራዘመ ሂደት የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትሩን ሊያዳክመው እንደሚችል ይገመታል ። ነገርየው እንጨት ሲፈልጥ የዋለ አባወራ ሺህ ፍልጦችን በአንዲት ልጥ ሊያስር እንደሚሞክር ማለት ነው ። ልጧ ብጥስ ያለች ጊዜ ፍልጦቹ ተበትነው ወደ መሬታቸው እንደማለት ነው ።

ደምረን ስናየው....

ሀ ) የኢዮጵያ መንግስት
ለጭፍራ ማሌሌት ( ትህነግ) ይቅርታ ያደረገላት ፤ ከሰራችው ወንጀል ነፃ ሆና እንድትኖር ሲሆን የከበሮ ድለቃው ግን ከነፃነት አልፋ ሥልጣን ለመካፈል የተስማማች ይመስላል ። ይህ ምንን ይወልዳል ? በጊዜ ሂደት በዝግታ የሚመለስ ይሆናል ።

ለ ) ጭፍራ ወያኔ ( ትህነግ ) " የፕሪቶሪያ ስምምነት በጥምር ኃይሉ ፣ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መንግስታት ጥርጣሬ (ስንጥቃት ) ይፈጥራል " የሚል እምነት ይዛ እንደገባችበት ቁልጭ ብሎ በገሃድ ግልፅ ሆኗል ። ስልታዊ ወዳጅነታቸውንም በሚገባ እየተገበሩ ነው ማለትም ይቻላል ።

ሐ ) የፕሪቶሪያ ስምምነት ፤ ብዙዎች በጥርጣሬ አይን የጎሪጥ እያዩት መሆኑ አገር ያወቀው ነው ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ በያዘው አካሄድ ለመሄድ ከመረጠ ፤ ጥንቃቄ ማድረግም አስፈላጊያችን ነው ፤ ምክንያቱም እያንዳንዷ እርምጃ እራሷን የቻለች ትርጓሜ ስለሚኖራት ።

መደምደሚያ-- የኢትዮጵያን ኩነቶች በአፅንኦት እና በትኩረት መከታተል የምንገደድበት ጊዜ መጥቷል ። በአጠቃላይ ሁኔታው ፡ ለሰው ብለህ በላከው እጅህ ድንጋይ የመዝገን አይነት ነው የሚመስለው ፤ በእርግጥም ጥንቃቄ የሚጠይቅ ነው ።

***
ዋናውን ጽሑፉ ከእነ ባለቤቱ ከሚከተለው አድራሻ ያገኙታል።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=727507619159038&id=100056994202753&mibextid=Nif5oz

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

07 Apr, 15:21


ስለልዩ ኃይሎች የወሰነው ማን ነው?

ልዩ ኃይሎች የተቋቋሙት በክልል መንግሥታት ነው። በጀታቸውም የሚሸፈነው በክልል ነው። ተጠሪነታቸውም ለክልል መንግሥት ነው።

እነዚህን የክልል ልዩ ኃይሎች መልሶ ማደራጀትም ይሁን ትጥቅ ማስፈታት የሚችሉት፣ ሕጋዊ ሥልጣን ያላቸው የክልል መንግሥታት ናቸው።

ገዢው ፓርቲ (በሥራ አስፈጻሚው ይሁን ወይም በማዕከላዊ ኮሚቴ ወይም በሌላ) በመንግሥት (የክልሎችንም ጨምሮ) አማካይነት የሚፈጸሙ አቅጣጫዎችን ሊያስቀምጥ ይችላል- መንግሥትን የሚመራ ገዢ ፓርቲ ስለሆነ። ይህንን የፓርቲ ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ወደመንግሥታዊ ውሳኔ መለወጥ/ማሸጋገር ግድ ይላል።

በዚህም መሠረት ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት ወይም ትጥቅ ለማስፈታት ገዢው ፓርቲ (ብልጽግና) በሥራ አስፈጻሚ ወይም በሌላ መዋቅሩ አቅጣጫ ካስቀመጠ፤ ይህን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የክልል መንግሥታት በካቢኔያቸው (በአስፈጻሚው አካል) ወይም በምክር ቤታቸው ተስማምተው ማጽደቅ ይጠበቅባቸዋል። የተቋቋሙት በደንብ (Regulation) በአስፈጻሚው ከሆነ መልሶ ለማደራጀት ቢያንስ የተቋቋሙበትን ደንብ፣ የተቋቋሙት በክልል ምክር ቤት በአዋጅ (Proclamation) ከሆነ የተቋቋሙበትን አዋጅ ማሻሻል ያስፈልጋል። ለዚህም የክልሎቹ መንግሥታት አስፈጻሚው አካል ወይም ምክር ቤት ውሳኔ ማሳለፍ አለባቸው።

በተቋቋሙበት አግባብና ባቋቋማቸው አካል ነው ድጋሜ መደራጀት ወይም ትጥቅ መፍታት ያለባቸው፤ መወሰንም ማስፈጸምም የሚችለው። ከዚህ ውጭ የገዢው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ወይም የፌደራል መንግሥት (ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም መከላከያ ሠራዊት ወዘተ) ልዩ ኃይሎችን የማፍረስ ወይም መልሶ የማደራጀት ሕጋዊ ሥልጣን የለውም።

የክልል መንግሥታትም፣ ሕዝብን ባያወያዩም እና የሕዝብ ፍላጎትና ስጋት ግድ ባይላቸው እንኳን፣ እጅግ በጣም ቢያንስ በአስፈጻሚያቸውም ይሁን በምክር ቤታቸው በመወሰን፣ ውሳኔያቸውን ለሕዝብና ለልዩ ኃይሎች ማሳወቅና መተማመን ነበረባቸው። ይኹን እንጂ ይህ ሲኾን አላየሁም፤ አልሰማሁም። የክልል መንግሥታትም ማብራሪያ ሲሰጡ አልሰማሁም።

በመሆኑም፣ ልዩ ኃይሎች እንዲፈርሱም ይሁን ትጥቅ እንዲፈቱ አሊያም ድጋሜ እንዲደራጁ የወሰነው ማን ነው? ውሳኔውስ የት አለ? ይዘቱስ ምንድን ነው? ለምን ለሕዝብስ ይፋ አልተደረገም?

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

06 Apr, 14:57


የአማራ ልዩ ኃይል ከክልሉ አመራር ውጭ፣ የፖለቲካ አመራሩ ትእዛዝ ሳይሰጠው የፈፀመውና የሚፈፅመው ፀጥታ የማስከበር፣ ሕግና ሥርዓት የማስፈን ሥራ የለም። ፈጽሞም አያውቅም።

የአማራ ልዩ ኃይል የአገር ሉዓላዊነትን ከመጠበቅ በዘለለ የአገሪቱ ስጋት ሆኖ አያውቅም። አገርን ከአደጋ ታደገ እንጂ አገርን አደጋ ላይ አልጣለም።


አገርን አደጋ ላይ የጣሉና አገሪቱ ላይ ጦርነት የከፈቱ ኃይሎች ገና ትጥቃቸውን አልፈቱም። እነዚህ ኃይሎች (ትሕነግ፣ ሸኔ፣ የአገው ሸንጎ ወዘተ) ከአገሪቱ ይልቅ ዋና ጠላት አድርገው የተነሱት የአማራ ሕዝብንና ክልልን ነው።

በተለይ ትሕነግ አኹንም ቢሆን በመሪዎቹ አማካይነት በግልጽ የወረራ ዛቻ እየለፈፈ ነው። ወረራው የት የት እንደሆነም በግልጽ ተናግረዋል። ይህ ቡድን በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት መሣሪያ አልፈታም። አነስተኛዎቹ (small arms) ቢቀሩ እንኳን እና የስምምነቱ አካል ባይሆኑም ቢያንስ ቀላል መሣሪያዎችን (Light weapons) መፍታት ነበረበት። ይኽንን ለማስፈፀም የፌደራል መንግሥቱ ፍላጎት አላሳየም። የትሕነግ ወታደሮችና (ልዩ ኃይልና የዞን ሚኒሻዎች) ዲሞቢላይዝ አልተደረጉም።


የአማራ ልዩ ኃይል ትጥቅ ከመፍታቱ አስቀድሞ ለሕዝቡና ለክልሉ ስጋት የሆኑወረራና ጥቃት በመፈጸም ልማድ ያላቸው የታጠቁ ኃይሎች ትጥቃቸውን በመፍታት ድጋሜ ስጋት ሊሆኑ እንዳይችሉ መደረግ አለባቸው። ይኹን እንጂ ይህ አልሆነም። አልተደረገም። እየተደረገም አይደለም። ይባስ ብሎም በተለይ በትሕነግ በኩል፣ የሽግግር መንግሥት አካል ሆነው የተመደቡትና ሹመታቸው የፀደቀላቸው ምክትል አስተዳዳሪዎቹ ወታደራዊ አዛዦች፣ ኢትዮጵያንም የአማራና የአፋር ክልሎችን ለማጥቃት ወራሪ ኃይሎችን የመሩ፣ አገርን በመውጋት ረገድ ከሃዲነታቸውን ያስመሠከሩ ሰዎች ናቸው። የፌደራል መንግሥቱ የእነዚህን ሰዎች ሹመት በእሺታ ሲያጸድቅ በአማራ ክልልና ሕዝብ ዘንድ የዳግሚያ የወረራ ስጋት መጨመሩ የሚቀር አይደለም።

የክልል መንግሥታት እስካልተስማሙ ድረስ የተለያዩ የጸጥታ ስጋቶችንና ዓይነቶችን መሠረት በማድረግ ለልዩ ልዩ የጸጥታ ዘመቻዎች (Special operations) የሚሆኑ ልዩ የፖሊስ ኃይሎችን (Special police forces)፣ ለምሳሌ የአድማ ብተና፣ የፀረ ሽምቅ፣ የእጀባና ጥበቃ ወዘተ የሚያገለግሉ የፓሊስ ልዩ ኃይሎችን ማደራጀት ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን አለው። በመሆኑም ልዩ የፖሊስ ኃይል ማደራጀት ሕገ መንግሥትን የሚቃረን ነው ማለት አይቻልም። ይኹን እንጂ፣ አይደለም ልዩ ልዩ ኃይሎችን ይቅርና መደበኛውን ፖሊስም ቢሆን በፌደራል መንግሥት ሥልጣን ሥር እንዲሆን ቢደረግ እና ለዚህም የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ቢደረግ መልካም ነበር። ከመጀመሪያውም በ devolution ወደ ፌደራል ሥርዓት የተሸጋገሩ አገራት ሊከተሉት ይገባ የነበረው የተማከለ የፀጥታ አስከባሪ ኃይል (ፖሊስንም ጨምሮ) ማደራጀት ነበር። በተለይ ደግሞ በርካታ ብሔረሰቦች ያሉባቸው አገራት። ነገር ግን በእኛ አገር ይህ አልተደረገም። አልሆነምም። ባለመሆኑም የተፈጠረውንና የተደቀነውን ችግር እያየነው ነው።

ይኹን እንጂ አኹን ባለው ተጨባጭ የፀጥታ ኹኔታና ስጋት፣ በክልሎች መካከል በነገሠው አለመተማመን ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ውስጥ የሚገኝን ሕዝብ የተደቀነበትን የፀጥታ ስጋት ሳይቀርፉ ያለውን ኃይል ማሳጣት፣ ትጥቅ ማስፈታት (እውነት ከሆነ) በየትኛውም መለኪያ በአዎንታና በይሁንታ ለመቀበል አስቸጋሪ ነው።

እጅግ በጣም የከፋው ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ግልጽና ቅርብ የፀጥታ ስጋት ያለበትን ሕዝብ አስቀድሞ የመከላከያ ኃይሉን እንዲያጣ፣ ኃይል የማሳጣት እና ልዩ ኃይሉን ለማስፈታት ማሟሻ ማድረግ በቅንነት የተወሰነ ነው ብሎ ለመውሰድ ቅንጣት ታክል ሚዛን ለመድፋት የመትመዝን ምክንያት ማግኘት አዳጋች ነው። በዚያ ላይ በድንገትና የፀጥታ ስጋት ባለበት ወቅት ሕዝቡን የሚያሳምን ምክንያት ለሕዝብ አልቀረበም።

በአጭሩ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ የማስፈታት የመቶ ሜትር ሩጫው ጤነኝነት የራቀው ነው። ከላይ እንደገለጽኩት ልዩ ኃይሉ ከፖለቲካ አመራሩ ትእዛዝ ውጭ የሚፈጽመው ወይም የፈጸመው አንዳች ሥራ የለም። ስለሆነም ልዩ ኃይሉ በምንም መለኪያ የፀጥታ ስጋት እንደሆነ የሚጠረጠር አይደለም። በመሆኑም ልዩ ኃይሉ ሳይሆን ጥርጣሬ ውስጥ የገባው (እኔ እንደሚመስለኝ) የፖለቲካ አመራሩ ነው። ወይም ደግሞ፣ ለሕዝብ ግልጽ ባለሆነ ምክንያት የፖለቲካ አመራሩ (የክልሉ) የልዩ ኃይሉን መፍረስ ፈልጎታል ማለት ነው።


በዚህ ወቅት፣ ሕዝቡ በከፍተኛ የፀጥታና ደኅንነት ስጋት ውስጥ ባለበት ወይም የፀጥታና የደኅንነት ዋስትና ባጣበትና እንደሌለው እየተሰማው ባለበት ወቅት፣ የአማራ ልዩ ኃይልን ብቻ ትኩረት አድርጎ ለማፍረስ መረባረብ አደገኛ ሙከራ ነው።

እንደዚህ ዓይነት ውሳኔዎች በሩጫ ሳይሆን በእርጋታ፣ በአምባገነንነትና በእኔ አውቅልሃለሁ ሳይሆን ሕዝቡን በማማከርና በማሳመን ነው መወሰንና መተግበር ያለባቸው።

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

27 Mar, 13:02


በጦርነት ማግስት፥ ጀግናና አርበኛን መጥላት የሿሚዎችና የፈሪዎች ልማድና ጠባይ ነው። "የበሬን ውለታ ወሰደው ፈረሱ" አይደል ተረቱስ? ጀግናና አርበኛ ለእውነትና ለሐቅ ስለሚኖር፤ በተንኮል፣በማጭበርበርና በፍርሃት ለሚኖርና ለሚገዛ ሿሚ ኹልጊዜም ስጋት ነው።

ፈሪና አጭበርባሪ ሿሚ ከጀግና ይልቅ ቦቅቧቃን፣ከአርበኛ ይልቅ ባንዳን ማቀፍ ማሽሞንሞን መሾም ይመርጣሉ፤ ይወዳሉ። ጀግናና አርበኛን ያሳድዳሉ።

ሿሚ፥ ጀግናና አርበኛን የሚወደደው በክፉ ቀን ብቻ ነው። በደጉ ቀን ግን ጠላቱ ነው። ክፉ ቀን ያለፈ ሲመስላቸው ሿሚና ባንዳ መተቃቀፍ፣ ጀግናና አርበኛን ማጥቃት አመላቸው ነው።

ይኼን ዐውቆ መዘጋጀትና መሥራት ነው-መፍትሔው።

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

02 Mar, 14:39


ለጠቅላላ መረጃ፦

የአድዋ ድል በዓል አዲስ አበባ፣ፒያሳ፣ ምኒልክ ዐደባባይ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ወይም ጠቅላይ ሚኒስቴር በተገኙበት እንዲከበር የተወሰነው በአዋጅ ነው፤በሕግ! ሕጉ አሁንም የጸና ነው። አዋጁ ፀንቶ እስካለ ድረስ የአድዋ ድል በዓል የካቲት 23 ቀን የሚከበረው አዲስ አበባ ፒያሳ ምኒልክ ዐደባባይ እንጂ ሌላ ቦታ አይደለም ማለት ነው።

(የሕዝብ በዓላትንና የእረፍት ቀናትን እንዲሁም አከባበራቸውን ለመወሰን የወጡትን አዋጅ ቁጥር 16/1967 እና 28/1967 ን ይመልከቱ።)

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

02 Mar, 14:38


ጣሊያን ወይም ባንዳና ሹምባሽ እንጂ ኢትዮጵያዊ የሆነ (emotional attachment ያለው) ካልሆነ በቀር እንዴት ያለ ምኒልክና ጣይቱን አድዋን ማክበር ያስባል፣ይሞክራል?

የሌሎች ኹነቶችን እንተወውና፣ ቢያንስ ግን አድዋ ሲዘከር የምኒልክ መታወስ ሊያንዘረዝረው ሊያስቃዠው የሚቺለው ጣሊያን ወይም ባንዳና ሹምባሽ እንጂ ሌላ መሆን አይችልም።

በአድዋ ኮርቶ ከድሉ ምኒልክን አስወጥቶ እንዴት ይሆናል?


ማፈሪያና መሳለቂያ መሆናቸንው ካልቀረ በአንድ ፊቱ የአድዋ ድል እንዳይከበር ማወጅ ነው!

Wubishet Mulat - ውብሸት ሙላት

15 Feb, 22:19


ሰላም መውረዱ ወደ ቀድሞ ቤት መመለሱ በጣም መልካም ነው። ውሸት ራቁቱን ቀርቷል። የታቀደው እልቂትም ተገቷል።

ቤተክርስቲያናችን መስቀል እንጂ የጦር መሳሪያ አትገዛም። አልገዛችምም።

ኢትዮጵያን ጠብቅልን እያለች ዘወትር ትለምናለች ትፀልያለች እንጂ ኢትዮጵያን ልታፈርስ መንግሥትን ልትገለብጥ [ከግብጽ እና ከሩዋንዳ (የሩዋንዳው በጣም አስገራሚ ነው) ጋር] መቼም ቢኾን አትሠራም።

ቤተክርስቲያን ላይ ሌላ ሌላም ''ጭቃና ምርጊት'' ለመለጠፍ ተሞክሮ፣ ተዝቶ ነበር። ከተነገረ፥ የማይሰማ ወሬ አይኖርም!

እርቁ ሲፈጸም፣ ቤተክርስቲያን የጦር መሣሪያ አለመግዛቷ፣ ከግብጽና ከሩዋንዳ ጋር ኢትዮጵያን ለማፍረስ መንግሥትን ለመገልበጥ እያሴረችና እየሠራች ነው የተባለው የውሸት የጭቃ ጅራፍ "ተረስቷል"። የውሸት ዕድሜው አጭር ነው።


ከዚህ አብልጦ መዘርዘሩ አስፈላጊ አይደለም። ለማንኛውም፣ "ዘቦ እዝን ሰሚዓ ለይስማ (ጆሮ ያለው መስማቱን ይስማ)" እንዳለው መጽሐፍ ቅዱስ እኛም የተወሩትን በዛቻ የተነገሩትን ኹሉ ጆሮ ያለው ይስማ፤ያስተውልም፤ እንላለን። እኒህ ኹሉ ለፍቅር አልተነገሩምና!