የዋለው ውለታ ቢነገር ተፅፎ ፡
ብዕር አይበቃውም አያልቅም ተነግሮ፡
አባት ለሴት ልጁ የዋለው ውለታ፡
ከአላህ በታች ሁኖ ለሴኬት መድረሻ፡
አሳድጓቷል በደብ አቀማጥሎ፡
ለሷ ሲል ደክሟል እጁ ተሰንጥቋል፡
ሞፈር እና ቀንበር ባንድ ተሸክሟል፡
ዳገት ቁልቁለቱን ባዶ እግሩንም ሂዷል፡
ዝናብ ዘንቦበታል ፀሀይ አቃጥሎታል፡
ብርድ እና ፀሀዩ ተፈራርቆበታል፡
እሱ ከብት አግዶ አሷን አስተምሯል፡
በባዶ እግሩ ሂዶ ለሷ ጫማ አልብሷል፡
የሱን እየሰፋ ለሷ አድስ ልብስ ገዝቷል፡
ለማዕረግ እድትበቃ ለሷ ብዙ ለፍቷል፡
እድትለወጥ ብሎ ጥንድ በሬ ሽጧል፡
መሬቱን አስይዞ ብር ተበድሯል፡
ህልሟ እንድሳካ አረብ ሀገር ልኳል፡
ምንም እንኳ ቢሆን ተሰዳ መሄዷ፡
ሸሪዓን ቢፃረር መሄድ መሰደዷ፡
ያለማወቁ ነው የሰደዳት እሷን፡
ሂጅ ስሪ ብሎ ብር የሰጣት ለሷ፡
እድትቀየር ነው እድትችል ራሷን፡
ወይ ባባ ውለታህ የቱ ተነግሮ የቱ ይተዋል፡
ይቅር አልጨርሰው ...በዚሁ ይበቃል፡፡
:
በተቻለሺ አስደስችው እህቴ!
የአባት ውለታ ከባድ ነው።
እኛም በተራችን እምንከባከባቸው
እምናስደስታቸው እምንጦራቸው ያድርገን
ያአኽዋት ይኑሩልን ለእኛ ስንት መስዋት ከፍለዋል!!
የሞቱትንም አላህ ጀነተል-ፊርዶወስ ይወፍቃቸው
https://t.me/yetkaru