E.Z መረጃ @ezmereja Channel on Telegram

E.Z መረጃ

@ezmereja


ይህ የEZ መረጃ የቴሌግራም ገፅ ነዉ

ለአስተያየት እና ጥቆማ

Ethiopian music (English)

Are you a fan of Ethiopian music? Look no further than the latestethiopianmusic Telegram channel! This channel is dedicated to bringing you the best and most up-to-date Ethiopian music from a variety of genres. Whether you're into traditional Ethiopian music, modern Ethiopian pop, or even Ethiopian hip-hop, you'll find something to love on this channel. Stay connected with the latest releases, music videos, and news from the vibrant Ethiopian music scene. Join our community of music lovers and discover the rich sounds of Ethiopia. Don't miss out on the opportunity to immerse yourself in the beautiful melodies and rhythms of Ethiopian music. Subscribe to latestethiopianmusic today and start exploring the diverse world of Ethiopian music!

E.Z መረጃ

12 Nov, 08:35


መረጃ ‼️

ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ መሃመድ ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን አሉ

በኦሮሚያ እና በሱማሊ ክልል መካከል የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸዉ የሞያሌ እና የድሬደዋ ከተሞች ላይ ህዝበ ዉሳኔ እንዲሰጥ የሱማሊ ክልል ፕሬዝዳን ሙስጠፌ መሃመድ ለፌዴሬሺን ም/ቤት ደብዳቤ መላካቸዉ ተሰማ ፡፡

በደብዳቤዉ እንደተመላከተዉ በሁለቱ ክልሎች ለዘመናት የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸዉን ከተሞች የፌደሬሺን ም/ቤት ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥበት ይጠይቃል ፡፡

አንኳር መረጃ ከደብዳቤዉ ለመገንዘብ እንደሞከረችዉ ህዝበ ዉሳኔዉን ለማድረግ ሱማሊ ክልል ሃላፊነቱን ለመዉሰድ መዘጋጀቱን ይገልፃል ፡፡

E.Z መረጃ

12 Nov, 08:29


ዩክሬን የሩሲያን “ሚ-8 ኤምቲፒአር -1” የውግያ ሄሊኮፕተር ለመጥለፍ ያደረገችው ሙከራ መክሸፉ ተሰማ፡፡

የሀገሪቱ የስለላ ድርጅት አባላት ሩሲያዊው አብራሪ ሄሊኮፕተሩን ለዩክሬን እንዲያስረክብ ከዛም 750 ሺ ዶላር እንደሚከፍሉት ሲያግባቡ ተደርሶባቸዋል፡፡

አብራሪው የደህንነት ሰዎቹ በቴሌግራም እንዳነጋገሩት፣ የተጠየቀውን የሚፈጽም ከሆነ ከሚከፈለው ገንዘብ ባለፈ የቼክ ሪፐብሊክ ፓስፖርት ተዘጋጅቶለት ከሀገር እንደሚያስወጡት ቃል እንደገቡለት ተናግሯል፡፡

ከዚህ ባለፈም “ሰርጌይ” በሚል የቴሌግራም ስም ሲያወራው የነበረው የዩክሬን የስለላ ድርጅት አባል አብራሪው ሄሊኮፕተሯን ወደ ዩክሬን ይዞ ከማምራቱ በፊት ባልደረቦቹን መመርዝ እንዳለበት እንደተነገረው ገልጿል፡፡

ለዚህም በማንኛውም ፋርማሲ ውስጥ ሊገዙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን ያካተተ ገዳይ ድብልቅ በምግብ ውስጥ የሚጨምርበትን መመሪያ እንደተላከለት ይፋ አድርጓል፡፡

ሂደቱን እስከመጨረሻው የተከታተለው የሩስያ ደህንነት አገልግሎት በተጠቀሰው ቦታ ሄሊኮፕተሩን ለመቀበል ሲጠባበቁ በነበሩ የዩክሬን ወታደሮች እና የስለላ አባላት ላይ የሚሳይል ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።

በተጨማሪም ሰላዮቹ የሩስያ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችን በመርዝ እና በተለያዩ መንገዶች ለመግደል ከብሪታንያ እና ሌሎች ምዕራባውያን የስለላ ድርጅቶች ጋር አብረው እንደሚሰሩ እንደተደረሰበት የሩሲያ የደህንነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ባለፈው አመት ሰኔ ወር ኤፍኤስቢ የሩሲያ አብራሪ “ቲዩ-22ኤም3” የተባለ ኒዩክሌር መሸከም የሚችል የጦር አውሮፕላን ወደ ዩክሬን እንዲበር ለማሳመን በኪቭ የተደረገውን ተመሳሳይ ያልተሳካ ሙከራ ማክሸፉ ተዘግቧል፡፡

@ezmereja

E.Z መረጃ

11 Nov, 18:07


የእስራኤል ጦር አንድም የሊባኖስን መንደር አልተቆጣጠረም - ሂዝቦላህ

የእስራኤል ጦር አንድም የሊባኖስን መንደር መቆጣጠር እንዳልቻለ ሂዝቦላህ ተናገረ፡፡

ከሐማስ ጎን ተሰልፎ እስራኤልን እየተዋጋ የሚገኘው የሊባኖሱ ሂዝቦላህ በእስራኤል ላይ የአየር ጥቃቶችን ሲደርስ የቆየ ሲሆን ከ45 ቀናት በፊት እስራኤል ጦሯን ወደ ሊባኖስ አስገብታለች፡፡

ባለፉት ቀናት እስራኤል የሂዝቦላህ ዋና ሃላፊን ጨምሮ በርካታ ወታደራዊ አመራረሮችን በቤሩት እና ሌሎች ከተሞች ገድላለች፡፡

ሂዝቦላህ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የእስራኤል ጦር በ45 ቀናት በቆየው ጦርነት ውስጥ እንድ መንደር እንኳን መቆጣጠር አልቻለም ብሏል፡፡

የሂዝቦላህ ቃል አቀባይ የሆኑት ሞሀመድ አፊፍ በደቡባዊ ሊባኖስ በሰጡት መግለጫ እስራኤል ጦሯን ወደ ሊባኖስ ብትልክም እስካሁን የያዘችው ቦታ የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እስራኤል በበኩሏ ከሂዝቦላህ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ስለሚደረግበት ሁኔታ ፍንጭ ሰጥታለች፡፡

የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳር እንዳሉት ሂዝቦላህን ከእስራኤል ድንበር አባረናል፣ ከእንግዲህ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ መታጠቅ አይችልም፣ የተኩስ አቁም ለማድረግ ከአሜሪካ ጋር እየተነጋገርን ነው ብለዋል፡፡

@ezmereja

E.Z መረጃ

11 Nov, 04:32


አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ ፥ በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን እንዲሁም በዴቼ ቬለ ሬድዮ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል።

ጋዜጠኛ ዜናነህ ለረዥም ጊዜያት ባደረበት ህመም ህክምናውን ሲከታተል ከነበረበት እስራኤል ቴል አቪቭ ዛሬ ጠዋት ኣፏል።

በስልሳ ስምንት ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ አዘዞ ጎንደር ነው የተወለደው።

ከ1970ዎቹ እስከ ሰማኒያዎቹ አጋማሽ ድረስ በኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት በተለይ በዜና አንባቢነት አገልግሏል።

በ1980ዎቹ አጋማሽ ወደ እስራኤል ያቀናው ዜናነህ በህመም ተዳክሞ ከሥራው እስኪርቅ ድረስ በኢየሩሳሌም የዶቼ ቬለ ራዲዮ ዘጋቢ በመሆን ሲያገለግል ቆይቷል።

" ይህ ዶቼ ቨለ ነው !! " ከሚለው የዲቼቬለ ሬድዮ ጣቢያ መለያ አንስቶ የተለያዩ ዝግጅቶች መክፈቻም የአንጋፋው ጋዜጠኛ ድምፅ ነው።

የዶቼ ቬለ አድማጮች ዜናነህን ከመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤል አረብ ግጭት እና ጦርነቶች ብሎም በቀጣናው በሚነሱ ፖለቲካዊ ዘገባዎች ያውቁታል።

የዜናነህ መኮንን የቀብር ሰነ ስረዓት ቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኝ ፓርክ ያኮም መካነ መቃብር እንደሚፈጸም ልጁ ቢታንያ ዜናነህ ገልጻለች።

ዜናነህ ባለትዳር እና የሶስት ሴቶች ልጆች አባት ነበር።

#ዶቼቨለ

@ezmereja

E.Z መረጃ

10 Nov, 06:44


ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የመቄዶንያ ብራንድ አምባሳደር ሆነ!

በሀይማኖታዊ አስተምሮቶቹ የሚታወቀውናአመለ ሸጋዉና አንደበተ ርቱዕ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የመቄዶንያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ የበጎ ፈቃድ ብራንድ አምባሳደር በመሆን የስምምነት ፊርማ ስነስርዓት ዛሬ ጥቅምት 30/02/2017ዓ.ም. ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በመቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ሐያት በሚገኘዉ በዋናው ግቢ ውስጥ (መቄዶንያ) ታላቁ ዝግጅት ተከናዉኗል!

ማዕከሉ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌን የመቄዶንያ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርጎ በበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ሰፊ ስራ እንዲሰሩ ሀላፊነት የሰጠ መሆኑን መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ተገኝተን ተመልክተናል!

ዲ/ን ሄኖክ በሜቄዶንያ አምባሳደርነቱ ማእከሉን በመወከል ፣ በማስተዋወቅ ፣ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ላይ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገልጿል።

" መቄዶንያ ተሳልመን ባንገባም የተቀደሰ ስፍራ ነው ። ይህን ማዕከል ለማገልገል መመረጥ ለኔ ክብር ነው "  በማለትም ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ተናግሯል ።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ባዚልያድ የተሰኘዉን አዲስ መፅሐፍ ምረቃና መሉ የመፅሐፉ መፅሐፉን ሽያጭ ገቢ ለመቄዶንያ እንዲሆን በይፋ አበርክቷል!

@ezmereja

E.Z መረጃ

09 Nov, 15:10


ሰሜን ኮሪያ ጂፒኤስ በመጥለፍ የአውሮፕላንና መርከቦችን ጉዞ ማወኳን ደቡብ ኮሪያ ገለጸች‼️

በአመት ከ56 ሚሊየን በላይ ሰዎች የሚያጓጉዘው የደቡብ ኮሪያ ዋነኛው አውሮፕላን ማረፊያ ከሰሜን ኮሪያ ከ100 ኪሎሜትር ባነሰ ርቀት ላይ ይገኛል
ሰሜን ኮሪያ ከሳተላይቶች መረጃ በመሰብሰብ አቅጣጫ የሚጠቁመውን የጂፒኤስ ስርአት መጥለፏን ደቡብ ኮሪያ ገለጸች።
ፒዮንግያንግ ትናንት እና ዛሬ የጂፒኤስ ስርአት ላይ ለመጥለፍ ባደረገችው ሙከራ በደርዘን የሚቆጠሩ አውሮፕላኖች እና መርከቦች ጉዞ መታወኩንም ነው የደቡብ ኮሪያ የመከላከያ ሚኒስቴር ያስታወቀው።
የአቅጣጫ እና ሌሎች መረጃ ማቀበያ የጂፒኤስ ስርአቱ ኬሶንግ በተባለችው ከተማ ስለመጠለፉ የገለጸችው ሴኡል፥ መርከቦች እና አውሮፕላኖች በምዕራባዊ ሰሜን ኮሪያ አቅራቢያ ጉዞ እንዳያደርጉ አሳስባለች።
ሰሜን ኮሪያ በምን መንገድ ጂፒኤስ እንደጠለፈች እና ምን ያህል አውሮፕላኖች እና መርከቦች ጉዟቸው እንደተስተጓጎለ ግን አላብራራችም።
“ሰሜን ኮሪያ ጸብ አጫሪ ከሆነው የጂፒኤስ ጠለፋ ልትታቀብ ይገባል፤ በዚህ ምክንያት ለሚደርስ ጉዳትም ሙሉ ሃላፊነቱን እንደምትወስድ ልናሳስብ እንወዳለን” ብሏል የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ።
በሩሲያ የሰፈሩት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች የወሲብ ፊልሞችን በማየት መጠመዳቸው ተገለጸ
በፒዮንግያንግ የቆሻሻ ፊኛዎች ምክንያት በረራው ተስተጓጉሎ የነበረው የደቡብ ኮሪያ ዋነኛው አውሮፕላን ማረፊያ የጂፒኤስ ስርአት ጠለፋው ሰለባ ሊሆን እንደሚችል አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
በአመት ከ56 ሚሊየን በላይ ሰዎችና ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን ቶን በላይ ጭነት የሚያጓጉዘው የኢንቾይን አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከሰሜን ኮሪያ ከ100 ኪሎሜትር ባነሰ ርቀት ላይ ይገኛል።
ፒዮንግያንግ ከወራት በፊት በቆሻሻዎች የተሞሉ ፊኛዎችን 12 ጊዜ በዚህ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በመጣሏ ምክንያት ለ265 ደቂቃዎች በረራዎች መዘግየታቸው ተገልጾ ነበር።
ደቡብ ኮሪያን በህገመንግስቷ ጭምር “ጠላት” አድርጋ የፈረጀችው ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል እና ኒዩክሌር ፕሮግራሟን አጠናክራ በቅርቡም አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏ ይታወሳል።
ይህን ሙከራዋን ተከትሎ አሜሪካ ከአጋሮቿ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ጋር የሶስትዮሽ የአየር ልምምድ ማድረጓ አይዘነጋም።
ፒዮንግያንግ ለዚህ ምላሽም አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ባካሄድችበት እለት (ማክሰኞ) በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች።
በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው የሁለቱን ኮሪያዎች መሪዎች ከጦርነት ነጻ በሆነው ቀጠና (ዲኤምዜድ) እጃቸውን ያጨባበጡት ዶናልድ ትራምፕ ዳግም መመረጣቸው የኮሪያ ልሳነ ምድርን ውጥረት ሊያረግበው እንደሚችል ተገምቷል

@ezmereja

E.Z መረጃ

09 Nov, 07:03


ትራምፕ በመጀመሪያ ቃለ መጠይቃቸዉ ህገወጥ ስደተኞችን በጅምላ የማስወጣት እቅዳቸዉን እንደሚተገብሩ አስታወቁ‼️

47ኛዉ የዩናይትድ ስቴትሰ ፕሬዝዳንት የሚሆኑት ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ስራቸው የአሜሪካን ድንበር ጠንካራ ማድረግ መሆኑን እና የአስተዳደራቸዉ የጅምላ ማፈናቀል መርሃግብርን ከመተግበር ዉጪ ምንም አማራጭ አይኖርም ብለዋል፡፡

የኢሚግሬሽን ፖሊሲያቸዉ በምርጫዉ ለማሸነፋቸዉ አንዱ ምክንያት ነው ያሉት  ትራምፕ መራጮች ወደ አሜሪካ “ጤናማ አስተሳሰብ ለማምጣት” እንደ እኔ ዓይነት እጩ እየፈለጉ ነበር ብለዋል።ምርጫውን ተከትሎ ከምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ እና ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ጥሪ “በሁለቱ በኩል በጣም የተከበረ ነበር” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በምርጫዉ ዋይት ሐውስ እና የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ከዲሞክራቶች እጅ ወጥተዋል። ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝደንት ሲሆኑ ሴኔቱ ደግሞ በሪፐብሊካኖች የበላይነት ተይዟል።ነገር ግን የተወካዮች ምክር ቤት የበላይነቱን የትኛው ፓርቲ ይይዛል የሚለው እስካሁን አልተወሰነም።አሁን ባለው ሁኔታ የተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ፓርቲ 211 መቀመጫዎችን እንደሚያሸንፍ ተገምቷል። ነገር የምክር ቤቱን የበላይነት ለማግኘት 218 መቀመጫዎቸን ማግኘት አለበት። በተቃራኒው ዲሞክራቶች እስካሁን ያገኙት መቀመጫ 199 ነው።

25 መቀመጫዎች እስካሁን አሸናፊያቸው ያልታወቀ ሲሆን ውጤታቸው በቅርቡ ይገለፃል ተብሎ ይጠበቃል።

@ezmereja
@ezmereja

E.Z መረጃ

08 Nov, 15:12


🙏🙏🙏

ሀልተንስ መዲሀኒት ቤት

አዲስ አበባ ሳርቤት አካባቢ እነዚህን የተከፈለባቸው መድሃኒቶች  በሃልተን ፋርማሲን ያገኛሉ።

* መድሀኒት መግዛት ለማይችሉ

እና

* አቅም ለሌላቸው የተከፈለበት ነው ውስዱ ::

Via እሊና ጌታቸው

ተመልከቱ እንደዚህ የሚያደርጉ ሰዎች
ምን ያህል እድለኞች ናቸው::

Respect

❤️❤️❤️🙏🙏🙏


@ezmereja

E.Z መረጃ

08 Nov, 14:16


#መልዕክት❤️

የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባልደረባ ዶ/ር ዳዊት እሸቱ ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ ለወላጆች መልዕክት አስተላልፈዋል።

" በተለይም አራስ ህፃናት ሲጠቡ የሚያልባቸው ፣ የሚደክማቸው ፣ በአጣዳፊ የሚተነፍሱ ፣ ኪሎ አልጨምር የሚሉ ፣ ጉንፋን በቶሎ ቶሎ የሚይዛቸው ፣ እድገታቸው የሚዘገይ ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ህክምና መሄድ ይገባል በዚህም ከበሽታው መታደግ ይቻላል " ብለዋል።

Via tikvah


@ezmereja
@ezmereja

E.Z መረጃ

08 Nov, 08:04


ፑቲን  ትራምፕ ደፋር ነዉ አሉ‼️

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር  ፑቲን ተመራጩን  የአሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን እንኳን ደስ አልዎት ብለዋቸዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕም  ለፑቲን እደዉላለሁ    ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በሶቺ ቫልዳይ ጉባዔ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት  ፑቲን  ትራምፕ ደፋር ሰዉ ነዉ  ብለዋል፡፡

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት  የተናገረዉን ሁሉ ማመን ባይቻልም ነገር ግን ከዩክሬን ቀዉስ ጋር ተያይዞ  ያነሳዉን ሀሳብ ትኩረት መስጠት  ይገባል ነዉ ያሉት ፑቲን፡፡

ከዚህ በተጨማሪም  ዶናልድ ትራም ደፋር ነዉ ያስገርመኛል ያሉት ፑቲን  ከፖለቲካ ይልቅ የቢዝነስ  ሰዉ  በመሆኑ ብዙ ስህተቶችን  ከዚህ ቀደም  ይሰራ ነበር ሲሉም  አንስተዋል፡፡

ሞስኮ  ከዋሽንግተን ጋር  ለመነጋገር በሯ  ክፍት  ስለመሆኑም  ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

ኔቶን አስመልከተዉ ሲናገሩም  የጦር ጎራዉ  ጊዜዉን የሳተ ስብስብ ሲሉ ወርፈዋቸዋል፡፡

የትራምፕን መመረጥ ተከትሎ አስቸኳይ  ስብሰባ የተቀመጡት የአዉሮፓ አገራት መሪዎቸ አደጋ ዉስጥ  ነን እያሉ ነዉ፡፡

አውሮፓ ካማላ ወይም ትራምፕ ስለተመረጡ ሳይሆን የራሱን እጣፈንታ የሚወስንበትን አቅም ሊገነባ ይገባል  ብለዋል፡፡

ይህም በመላው አውሮፓ በሚገኙ ሀጋራት ላይ ከፍ ያለተጽዕኖ ሊያስከትል እንደሚችል ኤፒ ዘግቧል፡፡
==============================


@ezmereja

E.Z መረጃ

08 Nov, 06:56


ህይወቱ ካለፈ ሰው አካውንት ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ከባንክ ለማውጣት የሞከሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በወላይታ ሶዶ በሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ እና ህይወቱ ያለፈ ሰውን ማስረጃ በመጠቀም ከባንክ ገንዘብ ለማውጣት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከአማራ ክልል በተፃፈ ደብዳቤ የመከላከያ አባላት መሆናቸውን የሚገልፅ እና የሟች ልጆች እንደሆኑ የሚገልጽ የውክልና ማስረጃ ለባንኩ በማቅረብ በሟች ስም የተቀመጠ  16ሚሊየን 400ሺ ብር ለማዛወር የሚያስችላቸውን ሙሉ ሒደት እየጨረሱ በነበረበት ወቅት የባንኩ ስራ አስኪያጅ ለመጨረሻ ጊዜ የውክልና ሰነዶችን ሲመረምር በመጠራጠሩ ለህግ አካል መረጃ በመስጠት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ  ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በባንኩ የተቀመጠውን ብር በስማቸው አውጥተው እንዲካፈሉ ያመቻቸ ነው የተባለ በከተማው ፋና ወንባ ቀበሌ ነዋሪ ና ቀደም ሲል የቀበሌው ጸጥታ ሀላፊ የነበረ አስራት ኤርገና የተባለ ግለሰብም በተጠርጣሪዎቹ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

ፖሊስ በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩትን ሦስቱን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን  የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ  ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
Via_dagu

@ezmereja

E.Z መረጃ

07 Nov, 19:43


‼️ሊጠናቀቅ አንደ ቀን ብቻ ቀረው‼️

እንዳትቆጩ፣ትራምፕ መመረጡን ተከትሎ መጪው ጊዜ የክሪፕቶ ነው
Major 1 ቀን ብቻ ቀረው‼️
ዋጋው እየጨመረ የመጣው ፕሮጀክት‼️
በራሱ በቴሌግራም መስራቾች እና በሌሎች የቴሌግራም entrepreneur የተመሰረተው Major ፕሮጀት ወደ ገንዘብ ሊቀየር 1ቀን ብቻ ቀርተውታል።
አሁንም ላልጀመራችሁ ሊንኩ ከስር ተቀምጧል ጀምሩት👇👇
https://t.me/major/start?startapp=6626214729
https://t.me/major/start?startapp=6626214729

E.Z መረጃ

07 Nov, 16:40


በአዳማ  ስጋ በሚቆርጥበት ቢላ  የሬስቶራንቱን ስራ አስኪያጅ በስለት ወግቶ የገደለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በአዳማ ከተማ ደምበላ  ክፍለከተማ የአንድ ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ በስለት ተወግታ መገደሏን ተከትሎ ተጠርጣሪዉን ግለሰብ ፖሊስ በተከራየበት ሆቴል ውስጥ በወለጪቲ ከተማ መያዙን አስታውቋል።

በአዳማ ከተማ አስተዳደር ደምበላ ክፍለከተማ  ወንጂ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ  የአንድ ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ የሆነችውን  የ24 ዓመት  ወጣት  ተጠርጣሪዉ በስለት ወግቶ መሰወሩን እና በፖሊስ ብርቱ ክትትል ተጠርጣሪውን መያዙን የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ  የኮሙኒኬሽን  ጽ/ቤት  ሃላፊ የሆኑት ኢንስፔክተር  ወርቅነሽ ገልሜቻ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  ተናግረዋል።

ተጠርጣሪው የእቴቴ ባርና ሬስቶራንት   ስራ አስኪያጅ  የሆነችውን ሃሴት ደርቤ  ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በሬስቶራንት ውስጥ የስጋ ቆራጭ ሆኖ እየሰራ ባለበት  በስራ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት  ስጋ በሚቆርጥበት  ቢላዋ ወደ የግል ተበዳይን ወግቶ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉ ተገልጿል።

ግለሰቡ ድርጊቱን  ከፈጸመ በኋላ ከአካባቢው የተሰወረ ሲሆን  ተጠርጣሪው ግለሰብ እና  ተጎጂዋ በስራ ምክንያት በተደጋጋሚ ይጋጩ እንደነበር  ተጠቁሟል።ፖሊስ ድርጊቱን ከፈጸመ እለት ጀምሮ  ክትትል እና ምርምር  እያደረገ  እንደነበረ እና በሂደቱ እገዛ ላደረጉ አካላት በሙሉ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ምስጋና ማቅረባቸውን ብስራት ዘግቧል።

Via Bisrat FM
@ezmereja

E.Z መረጃ

07 Nov, 09:38


😎😎😎

* ኢንትሬነቱ አብዷል
* አፍሪካም አብዳለች

ሰውየው የብዙ ሺህ ትዳር እንዲበተን ሳይሆን
ሴት ልጅ ምን ያህል ከባዶች እንደሆነ አሳይቷል

ጥናት :-

ባሁን ስአት በአፍሪካ ያገቡ ወንዶች ሲንግል መሆን ፍላጎት እንዳላች

ያላገቡ ደሞ ጭራሹን ማግባት እንዳማይፍልጉ በዚህ በ24 ስአት ውስጥ የተጠና ጥናት ተናግሯል::

መላጦች በጣም ከባድ መሆናቸውን አስመስክሯል

1. ከኢምሬትስ ዱባይ የሚመራው ቴሌግራም በጣም ስራ በዝቶበታል የዚህን ሰውዬ ቪዲዮ የጫኑ ቻናሎችን ሲያጠፋ ውሏል

2. ነገር ግን ወዲያው ሲያጠፋ ሌላ ቻናል እየከፈቱ ቴሌግራም ምን ጉድ መጣብኝ እያለ ይገኛል::

3. የአፍሪካ ሴቶች ከሚኒስቴር ጀምሮ በዚህ ሰውዬ ወረርሽኝ ተጠልፈው ወድቀዋል::

5. ልጆች ከእናት እና ከአባት አላያይቷል

6. ከ100 ሺህ በላይ የቤተሰብ አባላት በዚህ ሰውዬ ምክንይት በተዘዋዋርም ሆነ በቀጥታ ችግር ውስጥ ገብተዋል::

7. የአፍሪካ ባሎች ትዳራቸውን እንዲጠራጠሩ ምክንያት ሆኗል::

8. በመጨረሻ ሴት ልጅ Cheat ማድረግ ከፈለገች ሰይጣን ራሱ አያውቅባት ሲል አንድ የአፍሪካ መፅሄት አስነብቧል::

9. ሰውየው ከ400 ቪዲዮ በላይ ተባለ እንጂ ከዛ በላይ ቪዲዮ እንዳለው እየተነገረ ይገኛል

10. እስካሁን አንድ ሰው 300 ቪዲዮዎች በማየት ሪከርድ ሰብሯል

11. አንዳንዶች እያስከፈሉም የሰውየውን ቪዲዮ እየላኩ ይገኛል::

አፍሪካውያንም የክፍል ዘመኑ ጉደኛ ሰው እያለው ይገኛል::

እኛ ሀገርስ እንደዚህ አይነት

* ሴቶች
እና
* ሰውዬ ይኖሩ ይሆን


via gurasha

@ezmereja

E.Z መረጃ

07 Nov, 07:06


ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል።

የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው።

ሌቪት ፥ ትራምፕ በአሜሪካ ህዝብ ዘንድ አስደናቂ የተባለ ድል ማስመዝገባቸውን ገልጸው “ ይህ ድል ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ ‘ ትዕዛዝ ‘ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል “  ብለዋል።(Addis_News)

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

E.Z መረጃ

06 Nov, 18:05


#ጥንቃቄ🚨

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት የጨቅላ ህፃናት እንዳይጠቀሙት የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳስቧል፡፡

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት ኖቫርቲስ ፋርማ ሽዌይዝ AG/ Novartis Pharma Schweiz AG በተባለ የገበያ ፍቃድ ባለው የመድኃኒት አምራች ፋብሪካ የሚመረት ነው።

ቴግሬቶል (ካርባማዜፔይን) 100 mg/5ml Oral Suspension (OS) የተሰኘው መድኃኒት አብዛኛውን ጊዜ አጠቃላይ ለሚጥልና ከፊል መንቀጥቀጥ/ management of generalized tonic clonic and partial seizures ለማከም የሚያገለግል ነው።

ይሁን እንጂ የተጠቀሰው መድኃኒት በውስጡ በሚይዘው ፕሮፓይሊን ግላይኮል (propylene glycol) የሚባል ንጥረ-ነገር መጠን ምክንያት ለጨቅላ ሕፃናት ማለትም ከ4 ሳምንታት በታች ለሆኑ ሕፃናት ወይም በሶስት ወራት የመወለድ ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት ሊወስዱት እንደማይመከር ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

ተቋሙ ፥ በዚህ ምርት ውስጥ ከሚገኙት ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነው ፕሮፓይሊን ግላይኮል ለምግብ እና ትንባሆ ምርቶች እንዲሁም ለፋርማሲዩቲካል እና መዋቢያዎች በአጠቃላይ በአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (FDA) ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ይታወቃል ብሏል።

ይሁንና በዚህ ምርት ውስጥ ያለው መጠን በዚህ የማሳወቂያ መልዕከት ላይ ከተጠቀሱት ለጨቅላ ሕፃናት እና ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ ከደህንነት ገደብ በላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ነው ያለው።

ስለሆነም ይህንን መድኃኒት በጨቅላ ሕፃናት ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ መጠቀም ጉዳቱ ከጥቅሙ የሚያመዝን በመሆኑ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች መድኃኒቱን ለተጠቀሱት የእድሜ ክልል ከማዘዝ እና ከማከፋፈል እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ህብረተሰቡም መድኃኒቱን እንዳይጠቀም መልዕክት አስተለልፏል።



@ezmereja
@ezmereja

E.Z መረጃ

06 Nov, 11:30


ነብስ ይማር 😭😭😭

አዳማ አንብታለች

ወጣቷ  በሥራ ባልደረባዋ በስለት ተገደለች

በአዳማ ከተማ  ወንጂ ማዞሪያ  እቴቴ ሬስቶራንት በተባለ ጊቢ ውስጥ ነው ወንጀሉ የተፈፀመው ከቀኑ  7:33 በጠራራ ፀሐይ ሲሆን እድሜዋ 20 መጨረሻዎች የምትገኝ ወጣት ናት

በሆቴሉም ገንዘብ ያዢነትና  የሂሳብ  ሰራተኞችን  የመቆጣጠር ሃላፊነት አላት። 

ጥቃት  የፈፀመባት ከትላንት በስቲያ  አብሯት በሚሰራ ሰራተኛ ነው። ግለሰቡ ለሬስቶራንቱ ፍየል አራጅ  ሲሆን "ቀን አብረው ገበያ ውለው መተዋል ሲሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል።

በግዢ ሰዓት አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር እና ወደ ስራ ቦታ ከተመለሱም  በኋላ ወደ ውስጥ እናውራ ብላ  ይዛው ገባች ነገር ግን እንዳሰበችው መነጋገር  ሳይችሉ በሩን ቆልፎ  ያለ ርህራሄ ጀርባዋን ፣ታፋዋን፣ እጇን እና አንገቷን ወጋግቶ እና አርዶ እንደገደላት ተሰምቷል።

ታዲያ  በሩን ሰብሮ  እርዳታ  ለመስጠት የፖሊስ የአንቡላንስ አገልግሎት ማግኘት  የተቻለው  ከአንድ ሰዓት በኃላ ህይወቷ ካለፈ በኃላ ነበር💔😭 

ወጣቷ በማደጎ ያለ እናት እና አባት
ያደገች መሆኑ ተነግሯል 😥
    
ፍትህ ታገኝ ዘንድ
ድምፅ ሁኗት 🤲

ሼር በማድረግ በግፍ ለሚሞቱ ሴቶች  ፍትህ ጠይቁ!!!

ያማል

Via gurasha


@ezmereja

E.Z መረጃ

04 Nov, 18:51


ካማላ ሀሪስ እና ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝደንት ለመሆን የትኞቹን ግዛቶች ማሸነፍ አለባቸው?

አሜሪካ 50 ግዛቶች አሏት። ሁለቱ አውራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ዲሞክራት እና ሪፐብሊካን እኒህን ግዛቶች ተቀራምተዋቸዋል።

ይህ ማለት የትኛው ግዛት ለየትኛው ፓርቲ ድምፁን እንደሚሰጥ ይታወቃል ማለት ነው።

ነገር ግን ሰባት ግዛቶች ለየትኛው ፓርቲ ድምፃቸውን እንደሚሰጡ አይታወቅም፥ ለዚህ ነው ወላዋይ የሚባሉት።

እኒህ ግዛቶች ኔቫዳ፣ አሪዞና፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ጆርጂያ፣ ዊስኮንሲን፣ ሚሺጋን እና ፔንሲልቬኒያ ናቸው።

በአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዕጩዎች በርካታ ድምፅ ስላገኙ መንበረ-ሥልጣኑን ማግኘት ይችላሉ ማለት አይደለም።

ሁለቱ ዕጩዎች የሚፎካከሩት በ50ዎቹ ግዛቶች የሚደረጉትን ምርጫዎች ለማሸነፍ ነው የሚታገሉት።

እያንዳንዱ ግዛት ኢሌክቶራል ኮሌጅ የሚባል ቁጥር አለው። ይህ የሚሆነው በሕዝብ ቁጥር ብዛት ላይ ተመስርቶ ነው።

በአጠቃላይ 538 ኢሌክቶራል ኮሌጆች አሉ፤ ዕጩዎቹ ከእነዚህ መካከል 270 እና ከዚያ በላይ ማግኘት አለበባቸው።

ይህ እንዲሆን ደግሞ ከሰባቱ ወሳኝ ግዛቶች ቢያንስ በሶስቱ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።

@ezmereja

E.Z መረጃ

04 Nov, 11:08


ትራምፕ ሊገደሉ ይችላሉ” ----- ሩሲያ

ሩሲያ ለምን እንዲህ አለች?

ትራምፕ ምርጫውን አሸንፈው የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም የሚሞክሩ ከሆነ ሊገደሉ እንደሚችል የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡

ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ በነገው ምርጫ የትኛውም ዕጩ ቢያሸንፍ ከሩሲያ ጋር በተገናኘ ምንም የሚፈጥረው ለውጥ የለም ብለዋል፡፡

የሩሲያ የደህንነት ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር እና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ እና የዩክሬንን ግጭት ለማስቆም የሚሞክሩ ከሆነ ሊገደሉ እንደሚችሉ እየገለጹ ነው።
ትራምፕ በዩክሬን ጉዳይ እያንጸባረቁት ያለው አቋም፣ ከአሜሪካ ምዕራባውያን አጋሮች እና ከሀገሪቱ ዋና ዋና ፓርቲዎች ፍጹም የተለየ ነው ያሉት የቀድሞ ፕሬዝዳንት፣ ይህ አቋማቸው ጥላት የሚያነሳሳባቸው ሊሆን እንደሚችል አሳስበዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ የጆን ኤፍ ኬኔዲ እጣ ፈንታ ሊገጥማቸው እንደሚችል ያስጠነቀቁት ሜድቬዴቭ፤ ትራምፕ በአቋማቸው ጸንተው ጦርነቱን ለማስቆም ቢገፉ እንኳን የፓርቲ እና የፖለቲከኞች ተጽዕኖ እንዳሰቡት እንዳይራመዱ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ነው የተናገሩት፡፡
በዚህም በአንድ ቀን አይደለም በሶስት ቀን እና በሶስት ወራት የዩክሬንን ጦርነት ማስቆም ይችላሉ ብየ አላምንም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የሪፐብሊካ እጩ በምርጫው ካሸነፉ በዩክሬን ያለውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በ24 ሰአታት ውስጥ እንደሚያስቆሙ በተደጋጋሚ ቃል ገብተዋል፤ ሆኖም ጦርነቱን ስለሚያስቆሙበት መንገድ ዝርዝር ሁኔታዎችን አልገለጹም፡፡

ተቀናቃኛቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በበኩላቸው ትራምፕ የሚያሸንፉ ከሆነ ዩክሬን እጇን እንድትሰጥ ሊያስገድዱ ይችላሉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

@ezmereja

E.Z መረጃ

04 Nov, 11:06


መምህራን በምገባ መርሐግብር እየታቀፉ ነው

በሸገር ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት ቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪና መምህራን የምግብ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ይገኛል።

በዚህ ፕሮግራም የተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥን ማስወገድ የተቻለ ሲሆን መምህራንም በማስተማር እና በመማር የበለጠ እንዲተጉ አድርጓል ተብላል።

በሸገር ከተማ በሚገኙ 256 ትምህርት ቤቶች የተማሪ እና የመምህራን  ምግብ ፕሮግራም እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን ለ148 ሺ 795 ተማሪዎች እና ለ3 ሺ 707 መምህራን መስጠት ተችሏል።

@ezmereja

E.Z መረጃ

04 Nov, 10:53


ከሰሞኑን በጉራጌ ዞን ውስጥ በታጣቂዎች በተደረገው የግፍ ግድያ በርካታ ስዎች ህይወት ማለፉን እና የተረፉትም ደሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባየው ህክምና ላይ መሆናቸውን ተነግሮዋል


አይ ኢትዮጲያ መች ይሁን ፍዳሽ ሚያልቀው💔

@ezmereja

E.Z መረጃ

04 Nov, 07:51


ታሊባን ሴቶች እርስ በራስ እንዳይነጋገሩ አገደ፡፡

ታሊባን በአፍጋኒስታን ሴቶች ላይ ጠንካራ የእስልምና ህግን ለመጫን ባደረገው የመጨረሻ ሙከራ፤ ሴቶች የሌሎችን ሴቶች ድምጽ እንዳይሰሙ ከልክሏል።

የአፍጋኒስታን የምክትል እና በጎነት ሚኒስትር ኻሊድ ሃናፊ÷ ሴቶች እርስ በርስ እንዳይነጋገሩ የሚያግድ የሚመስለውን “አስገራሚ አዲስ እገዳ” አስታውቀዋል ሲል ዴይሊ ቴሌግራፍ ዘግቧል።

ሚኒስተሩ ዛሬ በተለቀቀው የድምጽ ክሊፕ÷ “ትልቅ ሴት ስትሰግድ እና ሌላ ሴት ስታልፍ እንኳን ጮክ ብላ መጸለይ የለባትም” ብሏል።

የታሊባን ውሳኔ ግልጽ ባይሆንም፤ የአፍጋኒስታን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሴቶች እርስ በርስ እንዳይነጋገሩ በትክክል ታግደዋል ማለት ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ታሊባን ህይወት ያላቸውን ፍጥረታት በቴሌቭዥን እንዳይታይ የከለከለ ሲሆን፤ መልዕክቱ የተላለፈውም በቴሌቪዥን ስርጭት ሳይሆን በድምጽ ቀረጻ ነው።

E.Z መረጃ

03 Nov, 19:03


#የሀዘን_መግለጫ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደራ ወረዳ፣ አድዓ መልኬ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኦነግ ሸኔ(ኦ.ነ.ሠ) ታግተው በግፍ ለተገደሉት የገንዳ አረቡ መስጅድ ኢማም ሼህ ሙሐመድ መኪን ሀጂ አረፉ ፓርቲያችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።

ኢማሙ በአካባቢያቸው የተፈሩና የተከበሩ፣ የተጣላ አስታራቂ እንደነበሩና በመስጅድ ውስጥ ሳሉ ከሌሎች 12 የቅርብ ሰዎች ጋር ታግተው በቅድሚያ ለመልቀቅ መደራደሪያ  3ሚሊዮን ብር ተጠይቆ 1.4ሚሊዮን ሰጥተው መሣሪያ ጭምር ካላመጣችሁ በማለትና ቀሪውን ገንዘብ ሲፈልጉ በግፍ ኹሉንም እንደገደሏቸው ለማወቅ ችለናል። ኢማሙ የታገቱት ከወር በፊት እንደነበርና ለማስልቀቅም ከፍተኛ ርብርብ እንደነበር ሰምተናል። በሣምንት ልዩነት እንዲሁ አንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ 800ሺህ ብር ተጠይቆባቸው ብሩንም ከፍለው ከብዙ እንግልት በኋላ በአሰቃቂ ኹኔታ ገድለዋቸዋል። አካባቢው ከፍተኛ ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ የሚዘወተርበት በአንጻሩ ግፉ እንዳይነገር በሚዲያ በታገዘ ፕሮፓጋንዳ ጭምር የሚድበሰበስበት ነው።

ፓርቲያችን ደጋግሞ እንዳሳሰበው እንዲህ ከነባር ሃይማኖት ኢትዮጵያን ለማፋታትና ወደአዲሱ የዓለም ሥርዓት/New world order/ ለመውሰድ በሚደረገው ጥድፊያና ርብርብ መንግሥታዊ መዋቅር ጭምር ተከትሎ እየተሠራበት እንደሆነ ለዚህም በዋናነት የሃይማኖት ተቋማትን በቃልም በተግባርም መዳፈር፣ የሃይማኖት አባቶችን እያሳደዱ መግደል፣ ምዕመናንን ማሳሳት፣ ማፈናቀል፣ ዕምነት ተኮር ጭፍጨፋ የስልት ትግበራውና መንገድ ጠረጋው አካል ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን ደጋግመን ገልጸናል።

እንዲህ ያለው ተግባር በጥንቃቄ የሚፈጸም በመሆኑ ዛሬ ክርስቲያኑን ነገ ሙስሊሙን ቦታ እየቀያየረ የሚደረግ ነው። እንዲያውም በታሪክ፣ በባህል እንደምናውቀው አንዱ የሌላው መከታና ጠባቂ እንዳይሆን እርስ በእርስ ለማፈጀትም ሴራ ሲጠምቅ ይታያል። ውጤቱ ውሎ አድሮ ያለ ተው ባይና አስታራቂ፣ በጎውን መንገድ ከነውሩ ለይተውና አበጥረው በቃልም በጽሑፍም የሚያመላክቱንን ጠቋሚ አባቶች የሚያሳጣ አካሄድ መሆኑን በውል መረዳት ይገባል።

ፓርቲያችን እንዲህ ያለውን እኩይ ተግባር በጽኑ ያወግዛል፤ ባለ በሌለ ኃይሉም ይታገለዋል።
በድጋሚ በኢማሙ ግፍ ግድያ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጥን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፳፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
@ezmereja

E.Z መረጃ

03 Nov, 11:42


የቅርብ ዘመድ የሌለው ሟች አስከሬንን
ለምርምር መጠቀም እንዲቻል የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ
ለፓርላማ ቀረበ

ይሄ ህግ

1. ፓርላማው ማፀደቅ አለበት

ወይንስ

2. የለበትም ትላላላችሁ

ሀሳብ ስጡ

E.Z መረጃ

02 Nov, 18:39


አቶ ጌታቸው ረዳ ኃላፊነታቸውን ማስረከባቸው ተሠማ

አቶ ጌታቸው ረዳ ኃላፊነታቸውን ያስረከቡት ለምክትላቸው ሌተናል ጀኔራል ታደሰ ወረደ በውክልና መሆኑ ታውቋል።

አቶ ጌታቸው ለህክምና ወደ ውጭ ሊሄዱ በመሆኑ ነው ስልጣናቸውን በውክልና ያስተላለፉት ተብሏል።

ሌተናል ጀኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይን የፀጥታ ኃይል ከመምራታቸው በተጨማሪ የእነ ደብረፂዮን ህውሃት ደጋፊ መሆናቸው ይነገራል።

E.Z መረጃ

02 Nov, 09:04


ከሀገር ውስጥ መንግስት መር አጋች እና አሳዳጅ፣ አፈናቃይ እና አቅበዝባዥ ለማምለጥ በህገ ወጥ መንገድ የሚሰደደው ወገኔ እጣ ፋንታም ይሄው ነው።

እባካችሁ፣ በህገወጥ መንገድ ጉዞ የምታደርጉ ጥንቃቄ አይለያቹ።


@ezmereja

E.Z መረጃ

01 Nov, 17:21


በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አሥተዳዳሪ የሆኑት ንጉሤ ኮሩን በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መገደላቸውን ዋዜማ ዘገበ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አሥተዳዳሪ የሆኑት ንጉሤ ኮሩን ጨምሮ ከ ሃምሳ በላይ የሚሆኑ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ዛሬ ማለዳ ላይ ራሱን ያኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን በተከፈተባቸው ጥቃት መገደላቸውን ነው ዋዜማ ከምንጮች መስማቱን የዘገበው።

የወረዳው አሥተዳዳሪ፣ የዞን አመራሮች እንዲሁም በርካታ የመንግሥት ታጣቂዎች ታጣቂ ቡድኑ በስፋት ይንቀሳቀሳል ወደሚባልበት ካራ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ ዛሬ ማለዳ ለጸጥታ ስራ ተሰማርተው እንደነበር ተገልጿል።

በስፍራው እንደደረሱም ታጣቂ ቡድኑ በከፈተባቸው ድንገተኛ ጥቃት የወረዳ አሥተዳዳሪውን ጨምሮ ከሃምሳ በላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወዲያው ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ የወረዳው የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊውን ጨምሮ በርካቶች ደግሞ ቆስለው ወደ ሙከጡሪ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የዐይን እማኞች አረጋግጠዋል።

በጥቃቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከሙከጡሪ ሆስፒታል ሪፈር ተጽፎላቸው ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን የተገለፀ ሲሆን፤ የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጿል።

ንጉሤ ኮሩ ከዚህ ቀደም በዞኑ የአለልቱ ወረዳ አሥተዳዳሪ በመሆን፣ በዞኑ ደግሞ በተለያዩ ኃላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን÷ በቅርቡ ደግሞ የወጫሌ ወረዳ አሥተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን መረዳት ተችሏል።

ዋዜማ

@ezmereja

E.Z መረጃ

01 Nov, 10:30


ነፍስን አሲዞ የሚደረግ ጉዞ ከአዲስ አበባ ደብረ ማርቆስ



ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ ሲጎዙ የነበሩ የደብረ ማርቆስ ተማሪዎች ኦሮሚያ ክልል ሲደርሱ እንዳትንቀሳቀሱ መባላቸው ከቦታው
ተማሪዎቹ ገልፀውልናል እንዲሁም በየአመቱ ተማሪዎች ሲያልፉ እየተጠበቁ ኦነገ ሸኔ በመባል የሚጠረው የክፉዎች ስብስብ ተማሪዎችን በማገት ከ 1 ሚሊየን በላይ ብር እየጠየቀ መክፈል ያልቻለሁ ደሞ እየገደለ ከርሞዋል

ለሚመለከተው አካል እንዲደርስ ሼር በማረግ ተባበሩን ይላሉ ተማሪዎቹ


@ezmereja
@ezmereja

E.Z መረጃ

01 Nov, 09:10


በአዳማ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የመንግስት  ሀይሎች ወጣቶችን በግዳጂ በማፈስ ወደ ወታደራዊ ማስልጠኛ እያስገቡ መሆኑ ተገለፀ

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ይሀው ድርጊት በተደጋጋሚ እንደሚፈፀም  ሲነገር መቆየቱ የሚታወስ ነው

@ezmereja

E.Z መረጃ

01 Nov, 07:52


አሳዛኝ ዜና!

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በሸኔ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት እስከ 40 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።

ጥቃቱ የደረሰው በዞኑ የሶዶ ወረዳ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ ጋር በሚዋሰንበት አካባቢ ቢርቢርሳና ጋሌ ቀበሌ  ልዩ ስሙ ''ኩሬ'' እንዲሁም ''ቢጢሲ'' ተብለው እስከሚጠሩ ስፍራዎች ነው።

በሸኔ ታጣቂዎች በደረሰው ጥቃት እስከ 40 ሰዎች መገደላቸውንና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ዛሬ ከስፍራው የደረሱን ተደጋጋሚ መረጃዎች አመላክተዋል።

ጥቃቱ ትላንት ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ገደማ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት መራዘሙን የጠቆሙት የአካባቢው ነዋሪዎችና የሟቾች ቤተሰቦች በጥቃቱ ሕጻናትን ጨምሮ እናቶችና አረጋውያን መገደላቸውንም ተናግረዋል።

የተከፈተባቸውን ጥቃት መመከት ያልቻሉ አርሶ-አደሮች ቤታቸው ውስጥ እያሉ በእሳት እንዲቃጠሉ በማድረግ ከነከብቶቻቸው እንዲሞቱ መደረጉንም ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በአካባቢው የመንግሥት መዋቅሮች በኩል እስካሁን ስለጉዳዩ ግልፅ መረጃም ሆነ ድርጊቱን የሚያወግዝ መግለጫ አልተሰጠም።

E.Z መረጃ

31 Oct, 07:10


ኤርትራ የአየር ክልሏን ዘጋች‼️

ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል ውስጥ እንዳይበር መከልከሏን የኤርትራ እና የሶማሊያ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከወራት በፊት የኢትዮጵያ አየር  መንገድ የተጓዦችን ሻንጣ ጥሎብናል በሚል ክስ መስርቻለሁ ማለቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ ማቆሙ ይታወሳል።

አየር መንገዱ በኤርትራ የሚገኘውን ገንዘቡን ማንቀሳቀስ እንዳይችል መደረጉንም መግለፁ ይታወሳል።

@ezmereja

E.Z መረጃ

31 Oct, 06:32


በግጭቶች እና በተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ 5 ሺሕ 568 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል! -ኢሰመኮ

በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች በተከሰቱ እና በቀጠሉ ግጭቶች እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት 5 ሺሕ 568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያተኮረ ባለ 25 ገጽ ዓመታዊ ሪፖርት አውጥቷል።

በሪፖርቱም በትግራይ ክልል 105 ገደማ ትምህርት ቤቶች በጦርነት በመውደማቸውና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በመሆናቸው ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ገልጿል።

እንዲሁም ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 52፣ በአፋር ክልል 17፣ በአማራ ክልል 14፣ በኦሮሚያ ክልል 11፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 11 እና በጋምቤላ ክልል 11 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን አስታውቋል።

ኢሰመኮ በሰኔ ወር እና ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ባሰባሰበው መረጃ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ እና በቀጠሉ ግጭቶች እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት፤ በአማራ ክልል 4 ሺሕ 178፣ በትግራይ ክልል 648፣ በኦሮሚያ ክልል 420፣ በሶማሊ ክልል 195፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 50፣ በጋምቤላ ክልል 40፣ በአፋር ክልል 26 እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 8 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

የጸጥታ ሁኔታው አንጻራዊ መሻሻል ባሳየባቸው አካባቢዎች ደግሞ መምህራን አካባቢውን ለቀው የሄዱ በመሆናቸው የመምህራን እጥረት መኖሩን የገለጸው ኮሚሽኑ፤ በአካባቢዎቹ አስተማማኝ ጸጥታ ባለመኖሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንደማይልኩ አስታውቋል።

በተጨማሪም "በአንዳንድ አካባቢዎች መምህራን ትምህርት ቤት ውስጥ ለመገኘት በተለይም ሴት መምህራን የመደፈር እና የመዘረፍ ሥጋት ያለባቸው በመሆኑ ትምህርት ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል" ሲል ገልጿል።

ኮሚሽኑ በተጨማሪ የጤና ጉዳዮችንም በሪፖርቱ ያነሳ ሲሆን፤ "ባለሙያዎች ደመወዝ ወቅቱን ጠብቆ በአግባቡ ባለመከፈሉ ሳቢያ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሕክምና አገልግሎት እንዲስተጓጎል ምክንያት ሆኗል" ብሏል።

በተጨማሪም "የመድኃኒት እጥረት እና በግጭት ምክንያት የጤና ተቋማት በቂ አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል" ሲል ገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ አክሎም በአማራ ክልል ያለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት የተለያዩ የጤና ተቋማት ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሠሩ ከማድረጉ በተጨማሪ፤ የሕክምና መሣሪያ፣ መድኃኒት፣ ደም፣ ኦክስጂን እና ሌሎች ግብአቶች አቅርቦት እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑንም አመላክቷል።

ኢሰማኮ በሪፖርቱ መንግሥት በትጥቅ ግጭትም ሆነ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠይቋል።

የወደሙ ትምህርት ቤቶች እንዲገነቡ እና መልሰው እንዲቋቋሙ ለማድረግ በቂ በጀት ተይዞላቸው በዕቅድ ውስጥ መካተታቸውን እንዲያረጋግጥ የጠየቀው ኢሰመኮ፤ ትምህርት ቤቶቹ መደበኛ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምሩ መንግሥት ጊዜያዊ የመማሪያ አማራጮችን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሔዎችን እንዲያመቻች እንዲሁም አስፈላጊ የትምህርት ቁሳቁሶችን እንዲያሟላሜ አሳስቧል።

በተጨማሪም በትጥቅ ግጭት ሳቢያ የወደሙትን መሠረተ ልማቶች በመጠገንና አገልግሎቶችን በፍጥነት ወደ ሥራ በማስገባት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች በተሻለ ሁኔታ የሚረጋገጡበትን መንገድ እንዲያመቻች ኮሚሽኑ ምክረ ሃሳቡን ገለፆዋል

E.Z መረጃ

30 Oct, 17:23


‼️ሰበር የድል ዜና‼️
//
የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድን እይዛለሁ ብሎ ከደብረ ማርቆስና ከረቡ ገበያ የወጣው የጠላት ኃይል ባላሰበው መንገድ ገብቶ እየተቀጠቀጠ ነው።
በውጊያው የሶስት ክፍለ ጦር የፋኖ አባላት ታሪክ እየፃፉ ነው።በዚህ ታሪካዊ ጠላትን የመደምሰስ ተጋድሎ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር፣በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር፣ሐዲስ አለማየሁ ክፍለ ጦር እንዲሁም ሌሎች አጎራባች ወረዳ ያሉ ብርጌዶች እየተሳተፉበት በሚገኘው በዚህ አውደ ውጊያ ጠላት ዳግም ወደ ጮቄ ማሰብ አድለም ቃሉን እንዳይጠራ የሚደረግበት ውጊያ ነው።
ዛሬ ለጆሮ  የሚደንቅ የብስራት ዜና ከሰዓታት በኃላ እናበስራለን።
በተረጋጋ መንፈስ ጠብቁን ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን!!
መልክት፦
የፋኖን በትር መሸከም ያቃተው በየሰፈሩ የሚገኘውን ንፁህ አርሶ አደር እንዲሁም በየቦታው ያገኘውን ወንድ ልጅ ሁሉ እየረሸነ ነው።ንፁሐንን ረሸነ ብለን ጠላትን ከመደምሰስ ግን የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም።
አዲስ አብዮት
አዲስ ድል
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችን እና በአንደበታችን እንፈጥራለን።
የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ

መ/ር ታደገ ይሁኔ(ሸርብ)


Via negede amhara

@ezmereja

E.Z መረጃ

30 Oct, 10:20


ምክር ቤቱ ነገ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

በመደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በስብሰባው ይገኛሉ፡፡

@ezmereja

E.Z መረጃ

30 Oct, 07:26


እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ በፈጸመችው ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 93 መድረሱ ተገለጸ።

በቤት ላሂያ ከተማ በሚገኝ ባለ አራት ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ በሚሳኤል ተመቷል።

“በርካታ ሰዎች አሁንም ድረስ በህንጻው ፍርስራሽ ውስጥ ናቸው” ያለው የጋዛ ጤማ ሚኒስቴር፥ ከሟቾቹ ውስጥ ቢያንስ 20 የሚሆኑት ህጻናት መሆናቸውን ገልጿል።

ሁለት እናቶች ከአምስት እና ስድስት ልጆቻቸው ጋር የተገደሉበት የሚሳኤል ጥቃት በሶስት ወራት ውስጥ ከፍተኛው ሞት የተመዘገበበት መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

በጋዛ ጤና ሚኒስቴር የሚወጣውን የጉዳት አሃዝ በተደጋጋሚ የምታጣጥለው እስራኤል ስለትናንቱ በርካታ ንጹሃንን ስለቀጠፈ የሚሳኤል ጥቃት እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም።

የእስራኤል ዋነኛ አጋር አሜሪካ ግን በንጹሃን ፍልስጤማውያን ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት መጨመረ አሳሳቢ ነው ብላለች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ማቲው ሚለር ከ90 በላይ ፍልስጤማውያን የተገደሉበትን ጥቃት “አሰቃቂ ጉዳት ያስከተለ ዘግናኝ ጥቃት ነው” ብለውታል።

ሃማስን ሙሉ በሙሉ ካልደመሰስኩ የጋዛው ጦርነት አይቆምም በሚል አቋሟ የጸናችው እስራኤል ባለፉት ሶስት ሳምንታት በሰሜናዊ ጋዛ ጥቃቷን አጠናክራለች።

@ezmereja
@ezmereja

E.Z መረጃ

30 Oct, 05:49


የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከመንግሥት ኃይሎች ጋር በተካሄዱ ግጭቶች 102 የመንግሥት ወታደሮችንና የጦር መሳሪያዎችን ማርኬያለሁ አለ።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ካለፈው ስምንት አጋማሽ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ግንባሮች ከመንግሥት ኃይሎች ጋር በተካሄዱ ግጭቶች 102 የመንግሥት ወታደሮችንና በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ማርኬያለሁ ሲል አዲስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አማጺው ቡድን በመንግሥት ኃይሎች ላይ ወታደራዊ ድል ተቀዳጅቻለሁ ያለው፥ ድሬ ኢንጪኒ፣ ደራ፣ ወረ ጃርሶ፣ አመያ፣ ዩብዶ፣ ጉቴ፣ ቦጂ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሳሲጋ፣ አባይ ጮመን፣ ሀርጡማ ፉርሴ፣ ኤልዋዬ፣ ገላና፣ ሱሮ ቡርጉዳ፣ በቾ እና ቦራ በተባሉ የግጭት ግንባሮች ነው።

ቡድኑ ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች፣ የግንኙነት መስመሮች አሁንም እንደተቋረጡ ነው ማለቱን ዋዜማ ዘግቧል።

መከላከያ ሠራዊት በበኩሉ፣ በቡድኑ ላይ መጠነ ሰፊ የኃይል ርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጿል።

@ezmereja

E.Z መረጃ

29 Oct, 13:58


በነቀምቴ ከተማ ሁለት ታዳጊ ሴቶችን በቡድን ከደፈሩ ወጣቶች  እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋለ እንደሌለ ፖሊስ ገለጸ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወላጋ ዞን ነቀምቴ ውስጥ ሁለት ታዳጊ ልጆችን በቡድን በመሆን የደፈሩ ወጣቶች እስካሁን ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር አለመዋላቸውን ፖሊስ እና የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናግዋል።

የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሚሽነር ሻሎ ገለታ ወንጀሉ የተፈጸመው ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ባለፈው መስከረም ወር ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ነገር ግን ወንጀሉን ከፈጸሙት መካከል “እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም፤ ሁለት ተጠርጣሪዎችን እየፈለግን ነው” ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ሁለቱ ታዳጊ ልጆች በቡድን ሲደፈሩ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምሥል ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ከተሠራጨ በኋላ በርካቶች ቁጣቸውን እየገለፁ ነው።

ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራው ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ ወንጀሉ የተፈጸመው ጊምቢ ከተማ ነው ቢባልም ነቀምቴ ከተማ መፈጸሙን ጥቃቱ ከደረሰባት ታዳጊ መካከል አንዷ ማረጋገጧን የፖሊስ ኃላፊው ተናግረዋል።

የከተማው የሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ ወንጀሉ መፈጸሙን እንሚያውቅና ተጠርጣሪዎቹን ለፍርድ እንዲቀርቡ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ የሆኑት መብራቴ ባጫ÷ እንዲህ ዓይነት ወንጀሎች ሲፈጸሙ ተከታትሎ ጥቃት አድራሾችን ለፍትህ ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ፤ “ሴቶች በነጻነት ወጥተው እንዲገቡ የሕግ የበላይነት መረጋገጡን እንከታተላለን” ብለዋል።

አክለውም ይህ ዓይነት ከማኅበረሰቡ ሞራል ያፈነገጠ ተግባር እንዳይደገም ቢሯቸው የበኩሉን እንደሚሠራም ተናግረዋል።


@ezmereja

E.Z መረጃ

29 Oct, 09:44


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሊከሰሱ ነው ተባለ

የአትዮጵያ ህዘብ እንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት "ከክልሉ ጎን ለምን ተሳትፎ አላደረጋቸሁም" በሚል ከስራቸው ተሰናበተው ለሁለት አመታት የቆዩት የፖሊስ ሰራዊት አባለት ምላሽ ባለማግኘታቸው ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስደው አስታውቋል።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ጸሃዬ እምባዬ አንደተናገሩት÷ በሚቀጥሉት "አምስት ቀናት" ከጊዜዓዊ አስተዳደሩ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ፕሬዝዳንት እንደሚከሱ ተናግረዋል።

የአምስት ቀኑ ማስጠንቀቂያ ከጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚቆጠር ተናግረዋል፡፡

አቶ ጸሃዬ ፕሬዝዳነቱን የምንከሰው÷ "አሰራሩ ስለሚያስገድድ እና ያሉበት የስራ ሃላፊ እሳቸውን የሚመለከት ስለሆነ እንጂ" ሌላ አላማ ኖሮን አይደለም ብለዋል።

በአሰራሩ መሰረት ፕሬዝዳነቱ ለክስ የሚቀርቡት ለትግራይ ክልል አቃቢ ህግ ቢሆንም አቃቢ ህጉ ደግሞ በክልል ጊዜዊ አስተዳደር ስር በመሆኑ ምክንያት አቃቢ ህጉ ሀላፊውን ለመክሰስ ስለማይችሉ ክሱ ለፌድራሉ ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ቅርንጫ ጽ/ቤቱ የፖሊስ ሰራዊት አባለቱ ወደ ስራ እንዲመለሱ ውሳኔያቸውን እንዳሳለፉ የተናገሩት አቶ ጸሃዬ÷ ውሳኔው ከተወሰነ 33 ቀናት ቢያስቆጥርም እስካሁን ደረስ ምላሽ ባላመገኘቱ ምክንያት "የአምስት ቀን ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነው ወደ ክስ ለመግባት ተገደደድነው" ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍኤም

@ezmereja

E.Z መረጃ

29 Oct, 06:46


እናት ፓርቲ አብያተ እምነት የሰማያዊ መንግሥት ተልዕኮ ማስፈጻሚያ ኤምባሲዎች በመሆናቸው ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ብሎ መግለጫ አውጥቷል።

መንግሥት የወንዝ ዳር፣ ጫካ፣ ኮሪደር… ወዘተ ፕሮጀክት በሚሉ መጠሪያዎች የሚያከናውነውን ፈረሳና የማፈናቀል ተግባር አስመልክቶ በቅርቡ የአገራችን የበላይ ሕግ የሆነውን ሕገ መንግሥትና የሚመለከታችውን አዋጆች ጠቅሰን በትብብር ፓርቲዎች የጸና አቋማችንን መግለጻችን ይታወቃል ያለው ፓርቲው ከዚኹ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች የአምልኮ ሥፍራዎች ሕጋዊ ይዞታዎች ድንበር በማን አለብኝነት እየፈረሰ እንዳለና እንደሚፈርስ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው መገንዘብ ችለናል ብሏል።

@ezmereja

E.Z መረጃ

28 Oct, 18:15


በደቡብ ምዕራብ የተፈፀመ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በከፋ ዛን ግምቦ ወረዳ ከግምቦ ወደ ጎጅብ ገብያ
በቀን 17/02/2017 ዓ.ም ሲጓዝ በነበረ ዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ህገወጥ ቡና ጭኗል በሚል ጥርጣሬ ብቻ የተሳፈረ  ህዝብ ላይ ተኩስ በመክፈት 2 ንፁሀን ዜጎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሰዋል።
መኪናው ምንም የጫነው ቡና አልነበረም ብለዋል። ያለ ምንም ማስረጃ በጥርጣሬ ብቻ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ላይ የመንግሥት የፀጥታ አካላት ተኩስ ከፍተው ንፁሃንን ለጉዳት መዳረገቸው ተገቢ እንዳልሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቁመዋል

Via ayuzehabesha

E.Z መረጃ

28 Oct, 18:10


ተረጋግጧል

Memefi ወደ ገንዘብ የሚቀየረው በዚህ ወር  ጥቅምት 26 መሆኑን የቴሌግራም መስራቹ  Durovs ጓደኛ የሆነው እና የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆነው memefi ceo አሳውቋል።

ምናልባት ያልጀመራችሁ ካላችሁ፣በስልካችሁ ብቻ ገንዘብ መስራት የምትፈልጉ ካላችሁ ሊንኩ ከስር ተቀምጧል፣start በሉት👇👇👇👇👇

https://t.me/memefi_coin_bot/main?startapp=r_5667315a51

E.Z መረጃ

28 Oct, 09:13


የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን በመዋቅሯ የራሷ ፍርድ ቤት በማቋቋሙ ዘርፍ  ጠንክራ ሥራ መሥራት እንዳለባት ተገለጸ፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ፍርድ ቤት እንድታቋቁም መብት ያላት በመሆኑ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል ሲሉ  ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉ የሕግ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚወጡ ሕጎችና መመሪያዎች የማኅበረሰቡን  ሃይማኖትና ባሕልን ያገናዘቡ እና ሀገረ በቀል አስተሳስቦችን ያካተቱ መሆን  ይገባቸዋል ያሉት የሕግ መምህርና በፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃ አቶ መታገስ ውለታው  ከበዓላት አከባበር ጋር በተለይም በአደበባይ በሚከበሩ በዓላት ላይ  የበዓሉን ተሳታፊ የሚያዋክቡ ድርጊቶች መበራከት በሕግ አተገባበሩ ዙሪያ ያለውን ክፍተት ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡

የሕግ መምህሩና ጠበቃው  ቤተ ክርስቲያን ተቋም እንደመሆኗ  በመንግሥት ላይ ተቃውሞም ሆነ ድጋፍ ካላት በግለሰብ አባቶች ሳይሆን በአስተዳደር መዋቅሯ መሠረት በሚመለከተው አካል መገለጽ እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

ሕጎችና መመሪያዎች በሚወጡበት ጊዜም ቤተ ክርስቲያንን ወክሎ የሚሄደው አካል በጥንቃቄ አጥንቶና መርምሮ የቤተ ክርስቲያንን መብት የማይጋፋ መሆኑንና አለመሆኑን ማወቅ ይኖርበታል ያሉት ደግሞ የሕግና አስተዳደር መምህሩ አቶ አሮን ደጎል ናቸው፡፡

አቶ አሮን አክለውም አስተዳደራዊ መመሪያዎች ለማኅበረሰቡ ተደራሽ አለመደረጋቸው በሕግ አተገባበሩ ላይ እንከን መፍጠሩን የጠቆሙ ሲሆን ኦርቶዶክሳውያንም ሃይማኖታዊ አስተምሮን በተመለከተ ያላቸውን መብት ማወቅ ይኖርባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
[ማህበረ ቅዱሳን ]

@ezmereja
@ezmereja