📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech @yonidishtech Channel on Telegram

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

@yonidishtech


አዲስ አበባላይ ሆነው ዲሽ ማሰራት ከፈለጉ ፈጥነው እኛን ያናግሩን አስተማማኝ ስራ ከዋስትና ጋር ከኛ ያገኛሉ!!!

CREATORS:-

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech (Amharic)

ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech የምሁራን እና የሺሉፕላንዳን በቅናሽ እና ቴክንኮም በጋራ የቆይታ እና ሞገስ ላይ በማቅረብ የተለያዩ የቴክኖም መጽሃፍ እና መሣሪያዎችን አፕልንን በመሸበር ነው። እኛ አዲስ አበባላይ ሆነው ዲሽ ማሰራት ከፈለጉ ፈጥነው እኛን ያናግሩን አስተማማኝ ስራ ከዋስትና ጋር ከኛ ያገኛሉ።

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

26 Jan, 07:33


ዛሬ ላይ 7 ቀን ብቻ ነው የቀራው 🔥🔥

* ይሄ ኤርድሮፕ 100% የተረጋገጠ የDurov Airdrop ነው

* በቻላችውት መጠን በብዙ አካውንት ለመጨወት መክሩ

* በስንት ጊዜ የሚገኝ ምርጥ ኤርድሮፕ ነው

* አጠቃላይ የኤርድሮፑ ቆይታ 8 ቀን ብቻ ሰለሆነ ዋጋው ስንት ሊሆን እንደሚችል መገመት ትችላላቹ

* ቴሌግራም ስለተቀላቀላቹ 100 ticket እንዲሁም ስቶሪ ስለለቀቃቹ 50 Ticket ማግኘት ትችላላቹ

* እደግመዋለው በብዙ አካውንት ስሩ ታተርፉበታላቹ

ያልጀመራቹ ለመጀመር 👉 https://t.me/DurovCapsBot/caps?startapp=639262072

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

25 Jan, 18:34


👁ETHIOSAT ላይ የሚገኙት SPTV 1 እና SPTV 2 ቻናሎች እንዴት ማስከፈት እንችላለን?

🔥 SPTV የሚሰራው ከታች ባሉት Reciver ስለሆነ ከታች ያሉትን ሞዴል በደንብ ያንብቡ

👌👌👌👌👌👌👌
🔘REALSTAR 1010 HD
🔘REALSTAR 5050 HD
🔘REALSTAR SIRIUS HEVC 265

💥KingStar 99HD Prime
💥Kingstar 9080HD
💥Kingstar 7060HD
💥Kingstar 8070HD

🔥LEG N24 FOREVER
🔥LEG N24 PROMAX
🔥LEG N24 Jaguar ULTRA
🔥LEG JAGUAR ULTRA 4K
🔥LEG H14 
🔥LEG M18 
🔥LEG M18Pro
🔥LEG Nurstar N24 የቅርቡ

⚡️GOLDSTAR 7200HD
⚡️GOLDSTAR 7500HD
⚡️GOLDSTAR 8600HD
⚡️GOLDSTAR 8800HD
⚡️GOLDSTAR 9000 GHOST
⚡️SUPERSTAR 6565HD Mega
⚡️SUPERSTAR 6464HD Mega
⚡️LIFESTAR 6060HD SMARTn
⚡️LIFESTAR 8080HD SMART
⚡️LIFESTAR 8585HD++
⚡️LIFESTAR 9090HD ዳይመንድ

LIFESTAR 9200HD SMART
LIFESTAR 9300HD SMART
LIFESTAR 1000HD SMART
LIFESTAR 2000HD SMART
LIFESTAR 3000HD SMART
LIFESTAR 4000HD SMART
LIFESTAR 9200HD GOLD
LIFESTAR 9300HD GOLD
LIFESTAR 1000HD GOLD
LIFESTAR 2000HD GOLD
LIFESTAR 3000HD GOLD
LIFESTAR 4000HD GOLD
LIFESTAR 9200HD Smart miniLIFESTAR 9300HD Smart mini
LIFESTAR 9200HD MINI
LIFESTAR 9300HD MINI
SUPERSTAR 9200HD Smart V8
SUPERSTAR 9300HD Smart V8
SUPERSTAR 9200HD Super V8
SUPERSTAR 9300HD Super V8.
SUPERSTAR 95HD SMART
SUPERSTAR 96HD SMART
SUPERSTAR 97HD SMART
SUPERSTAR 98HD SMART
GOLDSTAR 7600HD
GOLDSTAR 7700HD
GOLDSTAR 7800HD
GOLDSTAR 7900HD

👉👉👉እባካቹህ ከላይ የተቀመጡትን  ማብራርያ በደነብ አንቡቡ በዋነኘነት የሪሲቨር አይነቶቹን💧

🔥የሚሰሩትም ከላይ የተጠቀሱ ብቻ ናቸው ከዚህ ውጪ ድምፁ ቢኖርም በምንም reciver አይሰራም  !


🔥SPTV ነፃ ቻናሎች አይደሉም በክፍያ የሚሰሩ ቻናሎች ናቸው ዋጋቸውም እንደ እየ ሪሲቨሮቹ ይለያያሉ

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

19 Jan, 04:26


ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ ❤️

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

15 Jan, 18:54


📻ዶቼ ቨሌ Radio
🛰ኢትዮሳት 57°E
🆔10985 H 45000 ላይ ስርጭት መጀመሩን አስታውቋል።
TV/RD Button በመንካት ወደ Radio ቀይራችው ማዳመጥ ትችላላችሁ።

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

14 Jan, 11:58


ጥር 6፤2017 - ቲክቶክ የሚዘጋበት ቀን እየተቃረበ መምጣቱን ተከትሎ በርካታ አሜሪካውያን ሬድኖት የተሰኘውን ቻይና ሰራሽ ፕላትፎርም እየተቀላቀሉ መሆኑ ተሰማ

እራሳቸውን "የቲክቶክ ስደተኞች" ብለው በሚጠሩት ተጠቃሚዎች እርምጃ ምክንያት ሰኞ እለት ሬድኖትን በአፕል ዩኤስ አፕ ስቶር ላይ በብዛት ከወረዱ አፕሊኬሽኖች አንዱ እንዲሆን አድርጎል። ሬድኖት በቻይና፣ ታይዋን እና ሌሎች የማንዳሪን ተናጋሪ ወጣቶች ዘንድ ታዋቂ የሆነ የቲክቶክ ተወዳዳሪ መተግበሪያ ነው።

ሬድኖት ወደ 300 ሚሊዮን የሚጠጉ ወርሃዊ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን ቲክ ቶክ እና ኢንስታግራምን ያጣመረ ባህርይ እንዳለውም ተነግሯል። የመተግበሪያው ተጠቃሚዎች በአብዛኛው ወጣትና የከተማ ሴቶች ሲሆኑ ከፍቅር ጓደኝነት እስከ ፋሽንና ሌሎች የአኗኗር ምክሮችን እንዲለዋወጡ ያስችላቸዋል። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ቲክ ቶክ የአሜሪካ ድርሻውን ለመሸጥ ወይም በሀገሪቱ ውስጥ እገዳ እንዲጣልበት እሰከ ጥር 19 ደረስ ቀነ ገደብ ተቀምጦለታል።

ቲክ ቶክ የአሜሪካን ንግድ ድርሻው እንደማይሸጥ ደጋግሞ ተናግሯል። ጠበቆቹም እገዳው በአሜሪካ ውስጥ ያሉ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች የመናገር ነፃነትን እንደሚጥስ አስጠንቅቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን RedNote አዲሶቹን ተጠቃሚዎቹን እየተቀበለ ይገኛል። አዲስ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን እንዴት ማሰስ እንደሚችሉ እና መሰረታዊ የቻይንኛ ሀረጎችን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ በሚማሩበት "የቲክ ቶክ ስደተኛ" በሚለው ርዕስ ስር እስካሁን ድረስ 63ሺ ቪድዮዎች መሰራታቸው ተገልፆል።

ምንም እንኳን ሬድ ኖት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘ ቢሆንም ልክ እንደ ቲክ ቶክ በቻይና መንግስት ላይ በሚሰነዘረው ትችት ላይ ሬድኖት ተመሳሳይ የሳንሱር ሪፖርቶች ይቀርቡበታል። በታይዋን፣ የቻይና ሶፍትዌሮች የደህንነት ስጋት ስላለባቸው የመንግስት ባለስልጣናት Rednote እንዳይጠቀሙ ተገድበዋል።

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

14 Jan, 05:13


Telegram secret chat

📍ቴሌግራምን መጠቀም የአብዛኞቻችን የዕለት ተለት ተግባር በሆነበት ዘመን ቴሌግራም ላይ የምንላላካቸው ነገሮች ሚስጥራቸው የተጠበቀ መሆን አለባቸው። አንዳንዴም የላክናቸው መልእክቶች ወዴትም እንዳይተላለፉ እና ቶሎ እንዲጠፉ እንሻለን።

📍ቴሌግራም እርስበርስ ሚስጥር ተጠባብቀን የምናወራበት አንድ feature አለው። Secret chat ይሰኛል። ሰዎች መረጃ እርስ በርስ ብቻ የሚቀባበሉበት feature ነው። ማለትም ያ መረጃ ከሰዎቹ መካከል አፈትልኮ እንዳይወጣ የሚያደርግ ነው።

📍ከቴሌግራም Secret chat አገልገሎቶች መካከል፦
- የተላላክነውን መልዕክት ከላኪው እና ከተቀባዩ በስተቀር ማንም ማየት አይችልም።
- Screenshoot ማንሳት አይቻልም።
- forward ማድረግ አይቻልም።
- በቴሌግራም ሰርቨሮች ላይ የተላላክናቸው መረጃዎች አይቀመጡም።
- ማንኛውንም መልዕክት ስንላላክ በራሱ ጊዜ እንዲጠፋ ሰዓት set ማድረግ እንችላለን።
- የላክነውን መልዕክት በምናጠፋበት ወቅት በላኪውም በተቀባዩም ዘንድ ይጠፋል።

📍ከሰዎች ጋር secret chat ለማድረግ ወደ ምትፈልጉት ሰው ፕሮፋይል ውስጥ ገብታችሁ 3 ነጥብ በመንካት እና start secret chat የሚለውን በመንካት secret chat ማድረግ ትችላላችሁ።

📍ከዚህ በተጨማሪ ለማንም ሰው ቢሆን ማንነታችንን የሚያጋልጡና 3ኛ ወገን እጅ ላይ ቢገቡ ሊያሳፍሩን የሚችሉ የፅሁፍ፣ የድምፅ እንዲሁም የፎቶ መረጃዎችን ከመላክ መቆጠብ። ከላክንም ነገ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለማይታወቅ ከሁለቱም ወገን በፍጥነት ማጥፋት።


       @YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

12 Jan, 19:16


አሁን Live የ Barcelona Vs Real Madrid  ጨዋታ

➡️ NileSat 7w ነፃ ቻናል MBC IRAQ HD

11315 V 27500

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

11 Jan, 11:53


🔥ዛሬ እለተ ቅዳሜ
🏆FA Cup
09:15 ላይ
⚽️Liverpool 🆚  Accrington
📺SPTV 1

12:00 ላይ
⚽️Chelsea 🆚  Morecambe
📺SPTV 1

02:45 ላይ
⚽️Man City 🆚  Salford City
📺SPTV 1

🏆Laliga 🇪🇸
10:00 ላይ
⚽️Alaves 🆚  Girona
📺SPTV 2

🏆Bungesliga 🇩🇪
11:15 ላይ
⚽️Hoffenhem 🆚  Wolfsburg
📺SPTV 1

🏆 Seria A 🇮🇹
02:30 ላይ
⚽️Juventus 🆚  Torino
📺SPTV 2

04:45 ላይ
⚽️Ac Milan 🆚  Cagliari
📺SPTV 2

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

07 Jan, 09:26


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሠላም አደረሳችው

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

04 Jan, 12:58


LIVE  - SPTV   1
        TOT vs NEW
         
    💥 በ Ethiosat 57°E SPTV 1 ላይ በቀጥታ በእንግሊዘኛ ኮሜኔታር ይከታተሉ 11050 H 04000

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

26 Dec, 16:01


መረጃዎች በቴሌግራም እየተመዘበሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በዛሬው ዕለት በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ፡፡

አስተዳደሩ እንዳለው ከዛሬ ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች በተጠቀሰው የማስገሪያ (ፊሺንግ ሊንክ) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ነው ፡፡

በዚህም ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት) ግለሰብ ሊንክ ቢላክ መክፈት ተገቢ እንዳልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

25 Dec, 05:25


video በማየት ብቻ ብር የሚከፍል ዌብሳይት ነው ከናንተ የሚጠበቀው አካውንት ከፍታችሁ video ማየት ብቻ 100$ ሲደርስ withdrew ማረግ ትችላላችሁ

ዌብሳይቱ
👉 https://dollartub.com/93ct8

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

23 Dec, 17:17


❇️ Best telegram bots

📍
@EmojiTitleBot የራሳችሁን የፅሁፍ sticker የምትሰሩበት bot ነው። በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው።

📍
@DevToolsForbot የ telegram bot developer ከሆናችሁ  ይህንን bot ለብዙ ነገር መጠቀም ትችላላችሁ።

📍
@Txt2Filebot የላካችሁለትን ማንኛውንም file download ሊደረግ ወደምችል file format የሚቀይርላችሁ bot ነው።

📍
@stickercanvasbot ይህ webapp የፎቶ stickers የምንሰራበት webapp ነው።

📍
@korwordbot ይህንን bot በመጠቀም የkorea ቋንቋ መልመድና የምንፈልገው chat ላይ በEnglish የጻፍነውን ወደ ኮርያ ቋንቋ እየቀየረ ይልክልናል።

📍
@shortener_tiny_url_bot ማንኛውንም ሊንክ የምያሳጥርልን bot ነው።

📍
@CleaningToolboxBot የቻናል ወይም የግሩፕ content ለመቀየር አልያም መሸጥ ስትሹ ቻናላችሁ ወይም ግሩፓችሁ ላይ የተፖሰቱትን ሙሉ ማጥፋት አድካሚ ቢሆንም በዚህ bot መገላገል ትችላላችሁ።

      

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

13 Dec, 13:33


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...

| ምትሰበስቡት ነጥብ ቀጥታ ወደ ቶክን ይቀየራል
| ፕሮጀክቱ ለጥቂት ግዜ የሚቆይ ስለሆነ አያሰላቻም
| አጨዋወቱ እንስሶችን በተሰጣችሁ Feed መመገብና Upgrade ማድረግ ነው
| ብዙ ሰው ስላልበዛበት በግዜ ብትጀምሩ ይመረጣል
| አጨዋወቱን በቪዲዮ በቅርብ ግዜ ዉስጥ እንለቅላችኋለን

ለመጀመር t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref639262072

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

08 Dec, 16:53


🔥🔥Arezo TV 🔥🔥
🛰Yahsat 52.5°E
🆔12015 H 27500

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

06 Dec, 15:02


Yandex ይባላል በአጭሩ የራሺያ googl በሉት ከጠቀማችሁ ተቀሙበት ብዬ ነው

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

01 Dec, 13:53


🔥 ኳስ ምታዩበት ገራሚ አፕልኬሽን

ከዚ በፊት ከጠቀምኳችሁ አፕልኬሽኖች ይሄኛው የተሻለ ነው

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

23 Nov, 18:42


New football app 😍
ፅድት ያለች app ናት
ለስማርት ቲቪም ፅድት ብሎ ይሰራል

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

23 Nov, 13:49


ማታ 12:00 ሳት

Arsenal vs Notingham

ETV ላይ ይተላለፋል 😁🔥

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

19 Nov, 15:42


ፍቅር እስከ መቃብር የፍርድ ቤት እግዱ ተነስቶ በቅርቡ
📺በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን(ETV) ዳግም ሊመጣ ነው

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

01 Nov, 18:10


Al Naser Vs Al hilal

Live on Varzish

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

24 Oct, 06:48


አዲሱ Yacine TV Black
ምንም አይነት External Player አይፈልግም
ለAndroid TV or Android Box እና ስልኮች የሚሆን ነው።

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

20 Oct, 18:22


#flashmod


All pro feature unlocked📌

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

20 Oct, 06:46


🔥🔥Super እሁድ🔥🔥
ቀን 10:ዐ0 ላይ
⚽️Wolves 🆚 Man City
📺SPTV 1
📺Dኤስ TV

ምሽት 12:30 ላይ
⚽️Liverpool 🆚 Chelsea
📺SPTV 1
📺Dኤስ TV

ምሽት 04:00 ላይ
⚽️Sevilla 🆚 Barcelona
📺SPTV 1
📺Dኤስ TV
========
💁‍♂️Satellite Information
====================
🛰ኢትዮሳት 57°E
🆔11050 H 04000
📺SPTV 1
📺SPTV 2

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

19 Oct, 05:48


🏆ተወዳጆቹ የአውሮፓ ሊጎች ዛሬ ይመለሳሉ
ቀን 08:30 ላይ
⚽️Tottenham 🆚 Westham
📺SPTV 1
📺Dኤስ TV

ቀን 11:00 ላይ
⚽️Man United 🆚 Brentford
📺SPTV 1
📺Dኤስ TV

ቀን 11:00 ላይ
⚽️Fulham 🆚 Aston Villa
📺SPTV 2
📺Dኤስ TV

ምሽት 04:00 ላይ
⚽️Celta De Vigo 🆚 Real Madrid
📺SPTV 1
📺Dኤስ TV
========
💁‍♂️Satellite Information
====================
🛰ኢትዮሳት 57°E
🆔11050 H 04000
📺SPTV 1
📺SPTV 2

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

13 Oct, 17:22


🥰 YehSat 52.5 ለ Tv Varzish ተጠቃሚዎች አዲስ የ Sport ቻናል

✔️SolhSport ጥራቱ ደካማ ነው።

⚡️በሪሞታቹ 11660 H 10500 ሰርች በማረግ አስገቡት

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

13 Oct, 10:26


ለtvእናለሪሲቨር ሪሞት ለተቸገራችሁ በዚ አማራጭ ተጠቀሙ

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

13 Oct, 10:25


433 crypto የሚባለው ትልቅ ቻናል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ትልቅ scammer ሆነው እሰሩ ተጠንቀቁ ይሄን ሊንክ እንዳትከፍቱ በፎቶው ላይ ያከበብኩበትን

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

12 Oct, 16:51


❗️❗️Score808 App

የተለያዩ  ጨዋታዎችን Live ለመከታተል አሪፍ App ነው።

➡️ Latest Update ነው

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

12 Oct, 16:51


Now Live Ethiopia ጨዋታ በስልክ ወይም Tv ላይ ለመመልከት ይሄን Application ተጠቀሙ👇👇👇

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

08 Oct, 09:08


canal + በይፋ የኢትዮጵያ ስርጭቱን ሊያቆም ነው😥

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

07 Oct, 16:52


LEG N24 Pro Iron - ሪሲቨር ላይ 24H SPORT 1 እና 2 ለመጠቀም የመጀመሪያ Software ጭኖላችሁ 2ተኛ አልቀበለም ካለ! እና
ERROR- 1 SEC - ብሎ ከፃፈ መፍትሄ የለውም!

ስለዚህ 24H SPORT በ SERIAL NUMBER የምታሰሞሉ እና የምትሞሉ በቅድሚያ 2ተኛውን SOFTWARE እንደተቀበለ እና 24H SPORT የሚለው MULTIMEDIA ላይ እንደመጣ እርግጠኛ ይሁኑ!

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

03 Oct, 08:24


#DV2026

የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት ተደርጓል።

ለ2026 DV ለማመልከት https://dvprogram.state.gov/ ይጠቀሙ።

ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።

ማመልከቻው እስከ ህዳር 5 /2024 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ከፍተኛ የመሙላት ፍላጎቶች ድረገጹ ላይ መዘግየቶችን ሊያስከትል ስለሚችል ለመሙላት እስከ የምዝገባው ጊዜ የመጨረሻ ሳምንት ድረስ ባይጠብቁ ይመከራል።

ዘግይተው የሚገቡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

ህጉ ለአንድ ሰው አንድ ጊዜ ብቻ እንዲያመለክት ነው የሚፈቅደው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የሚጠቀመው የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ደጋግሞ የሚገቡ ማመልከቻዎችን የሚለይ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ አንድ ሰው ካመለከተ ሁሉንም የዛን ሰዎች ማመልከቻዎች ይሰርዛል።

ያልተሟላ ማመልከቻም ተቀባይነት የለውም።

ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ከቪዛ አማካሪዎች ፣ ' እንሞላለን ' ከሚሉ ወኪሎችና ከሌሎች አካላት እገዛ ሳይጠይቁ ራስዎ እንዲሞሉ ይመከራል።

ማመልከቻውን እንዲሞላሎት የሰው እርዳታ ካስፈለገ ጥያቄዎችን በትክክል ለመመለስ በሚሞላበት ስፍራ መገኘት ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪም የ ' ልዩ ማረጋገጫ ቁጥሩ ' ን ለመያዝ በስፍራው መገኝት ያስፈልጋል።

አንዳንድ የሚሞሉ ሰዎች ይህን ቁጥር ይዘው በመቀየር ተጨማሪ ብር የሚጠይቁ ስላሉ እንዳይታለሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

የማረጋገጫ ቁጥሩ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ በጥንቃቄ መያዝ አለበት።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራት ሁሉ የሚጠቃልል ነው።

ኢትዮጵያውያንም ለማመልከት ብቁ ናቸው።

አሜሪካ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አማካኝነት እንደምትቀበል ይታወቃል።

🇺🇸 ለአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ 2026 ለማመልከት ይህንን dvprogram.state.gov ሊንክ ይጠቀሙ !🇺🇸

(ተጨማሪ ማብራሪያ እና እንዴት መሙላት እንደሚቻል የሚገልጽ መመሪያ በቀጣይ እናያይዛለን)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

02 Oct, 11:11


አዲስ ነፃ Channel
በ Ethiosat 57°E
10985 H 45000
Goal TV
Huntfish TV
Peek Flick
Baby First

  
@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

📡ዮኒ ዲሽ & ቴክ - Yoni dish & Tech

30 Sep, 13:53


🚨Alert🚨

“ የኢትዮ ቴሌኮም ነጻ ዳታ ሽልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ” በሚል ሰሞኑን ነጻ ሜጋ ባይት ለማግኘት “ ሊንክ ጠቅ ያድርጉ ” የሚል መልዕክት በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ወደተለያዩ ግለሰቦች እየተላከና እየተዘዋወረ ነው፡፡

ይሄው ከሥሩ ሊንክ የተቀመጠበት የሚዘዋወረው መልዕክት ፡-
➡️ 6 ወር ለቆየ ሲም፣ 10GB
➡️ 1 ዓመትና ከዚያ በላይ፣ 20GB
➡️ ከ5 አመት በላይ ለቆየ ሲም፣ 50GB ነጻ ሽልማት ኢትዮ ቴሌኮም እየሰጠ መሆኑን የሚገልጽ ነው፡፡

አንዳንድ ሊንኩን የከፈቱ ሰዎችም፣ “ ስንከፍተው መረጃዎት እየተበረበረ ነው ይላል፡፡ ጉድ ተሰርተናል ” ሲሉ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ብዙዎች ደግሞ ይህን ጉዳይ ኢትዮ ቴሌኮም ያውቀዋል ? በማለት እየጠየቁ ነው፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የሚዘዋወረውን መልዕክት ተቋሙ ያውቀዋል? ትክክለኛስ ነው? ሲል ኢትዮ ቴሌኮምን ጠይቋል፡፡

የተቋሙ ቺፍ ኮሚዩኒኬሽን ኢፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ የኛ ቲምም ቼክ አድርጎታል፡፡ Phishing የሚሉት የማጭበርበር መልዕክቶችን የሚልኩ ናቸው፡፡

ታማኝ ከሆኑ ካምፓኒዎች የሚላኩ መልዕክቶችን በማስመስልና የሰዎችን መረጃ የሚወስዱ Phishing  ብለን የምንጠራቸው የሳይበር ጥቃት መንገዶች ናቸው፡፡

እኛ ያስቀመጥነውም እንሰጣለን ያልነው ሽልማትም የለም፡፡ የላክነውም መልዕክት የለም፡፡ የኛ የሴኩሪቲ ቲምም እየተከታተለ ነው፡፡

ሊንክ ልከው እርሱን ንኩ ነው ‘ንኩ’ የሚሉት የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን፡፡ ግን ፐርሰናል መረጃዎችን የመውሰድና ላልተገባ ነገር ሰዎችን ለመዳረግ የሚያደርጉት ጥረት ነው፡፡

ዌብሳይቶቹን የኛ ቲሞች ሞኒተር እያደረጉ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ ቁጥጥር እያደረጉ ነው፡፡

ሳይቶቹን የመዝጋት ሥራዎች እየተሰሩ ነው በቅንጅት፡፡ ስህተት እንደሆነ፣ የኛ እንዳልሆነ ሰው እንዲያውቅ እናደርጋለን፡፡

ይኛው መልኩን ቀይሮ የሰውን መረጃ ለመውሰድ ሆነ እንጂ ብዙ ጊዜ በተለይ ቴሌግራም አካባቢ ላይ ተከታይ ለማግኘት በኢትዮ ቴሌኮም፣ በቴሌ ብር እየተከፈቱ ደንበኛ ለማብዛት የሚደረጉ ጥረቶች አሉ፡፡

ይሄም ኢንቴንሽኑ ሌላ ቢሆንም ያው ነው፡፡ ከእኛም ብቻ አይደለም ምንጩን ስናጣራው ከሌላ አገር ውስጥ የሚመጣ፣ ወደ ሌላ አገር ሪፈር የሚያደርግ ነው ሊንኩ፡፡

የትልልቅ ተቋማት መልዕክት በማስመስል ሊንኮችን አስቀምጠው አጓጊ ሽልማቶችን እየሰጡ የሰዎችን መረጃ የማጭበበርበር ነገር ነው የሚፈጠረውና Phishing በተለያዬ በኢሜይል፣ በቴክስት፣ በጥሪ መልክም ሊመጣ ይችላል፡፡

ሰዎች ሊንኩን ባለመንካት ከእንደዚህ አይነት አሳሳች መልዕክቶች ራሳቸውን ይጠብቁ፡፡ እንዲህ አይነት ጉዳይ ሲገጥማቸውም በ9090 በነጻ ደውለው በዚያ እንዲያሳውቁንም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ” ብለዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) በበኩሉ፣  “ የኢትዮ ቴሌኮም ነጻ ዳታ ስልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ” በሚል መልዕክቶች ወደ ተለያዩ ግለሰቦች እየተላኩ መሆኑን እንዳረጋገጠ አስታውቋል፡፡

አስተዳደሩ፣ “ መልዕክቱ የግለሰቦችን ሚስጥራዊ መረጃዎችን የማጥመድ ጥቃት (Phishing Attack) መሆኑን ማረግገጥ ችያለሁ ” ብሎ፣ ግለሰቦች ሊንኩን ባለመክፈት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

@YonidishTech 🫶
@YonidishTech 🫶

4,269

subscribers

583

photos

12

videos