የውስጥን በቃላት @yewestenbekalat Channel on Telegram

የውስጥን በቃላት

@yewestenbekalat


➻ስለ ፍቅር የምናወጋበት
➻ ስለ ክህደት የሚዘከርበት
➻ ስለ ናፍቆት ደስታ
➻ ሀዘኖን የሚገልፁበት
➻ ጭንቀት መከፋትን የውስጣችንን ምንገልፅበት
➻just ስለሁሉም የውስጦን በቃላት የሚገልፁበት ምርጡ ቻናል ይቀላቀሉን

@yewestenbekalat

አስታየት ካላቹ
@Mmssfyhs6

የውስጥን በቃላት (Amharic)

ከታች ከእውነት በፊት የጠፉ ባለሙያዎችን ወስጥን በቃላት ሰምተዋል ብለዋል። በተጨማሪም እና በክፉውም ስለ ፍቅር የምናወጋበት፣ ክህደት የሚዘከርበት፣ ናፍቆት የሚሰጥበት፣ ሀዘኖን የሚገልፁበት፣ ጭንቀት መከፋትን የውስጣችንን ምንገልፅበት እና ሌላው ስለሁሉም የውስጦን በቃላት የሚገልፁበት ምርጡ ቻናል ይቀላቀሉን። በቃላት የተቀመጡና እናድርገዋለን በመሆኑ። የባለሙያዎች እና የአገልግሎቶች ዝግጅት ተዛውሯል።

የውስጥን በቃላት

04 Jan, 13:58


ጠግን ትጠገናለህ ❤️‍🩹....

የውስጥን በቃላት

20 Dec, 03:24


🦋   ጥላ ነው አመልሽ 🦋

ሰማይ አንቃሮ የሚያዬው
መቼም ሳይደክመው አንገቴን
ኮከብ መቁጠሬን አልተውም
እንጨት ሰብሬ ጎጆ መስራቴን

ኖረሽ ሳትጠቅሚ ለሀገር
እኛም ሳናውቀው ሞተሽ
ተናገርሽ አሉ እጅ አውጥተሽ
ከመቃብር  ላይ ዎተሽ
እሳር ቅጠል ሆኖ አንቺ እንደው ዘመድሽ
የኔ አዘን የኔ እንባ የኔ ሞት አይገድሽ
አንቺ እንደው  መባከን ነው ድልሽ
አንቺ እንደው  ጥላ ነው አመልሽ

ጥላ የዛፍ ጥላ የቤት ጥላ የቆጥ ጥላ
        ከጨረቃ
ከኩቫኩብት ከፀሀይ ብርሃን ጋር የሚጣላ
ክፉ አመልሽ ጠዋት ታይቶ ማታ ጠፊ
ሲናገሩሽ ተሎ አኩራፊ ታዳሚሽን ገራፊ
ደጋፊና መራጭሽን  ሆነሽ ገፊ
ታዲያ ለዚህ ሁሉ ወዳጅሽ ሳጠቅሚው
    በምን አቅምሽ ነው
ከጥበብ ጋር ግብግብ የምትገጥሚው
ከሞትሽበት ከመቃብር ገና ዎተሽ
በጥላቻ ከፈታሻት ሚስትሽ ገና ታርቀሽ
   ይልቅ ክፉ ጥላ አመልሽ
   ጠልፎ እንዳይጥልሽ

By Habtishe

@yewestenbekalat
@yewestenbekalat
@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

15 Dec, 19:42


ጓደኝነት ይዞኝ
ቃል ሆኖኝ ሰንሰለት
እንዴት እንደሚከብድ አፈቀርኩሽ ማለት!

እፈራለሁ እንዳልነገርሽ የውስጤን ውስጥ ጉዳጉዱን
እንዳትርቅህ የሚል ሃሳብ አሳሰበኝ እግዞ ስንቱን
ይበላኛል ንዴት ስሬን
አይታከክ እንዳላከው
ምን ስትይኝ ፈዛዛ ሆንኩ
ንፁህ ልቤን የባረከው
እቀናለሁ ሳይሽ ደግሞ
ሆኖ አንገትሽ ሌላ ዘንዳ
እህትህ ናት ይላል ልቤ
አካል ስጋ ሆኖ ባዳ
ጉደኛ ነኝ ኧረ እኔማ
ጉዴ ገና ያላለቀ
ጓደኛ ነን በሚል ሰበብ
እሳት ፍቅሬ ያልተወቀ
አልታጠኩም የድፍረት ሻሽ
ለመናገር የፍቅሬን ቃል
ይነደዋል የዋህ ሆዴ
ጥርሴ ደግሞ ስንቴ ይስቃል
ሲያወሩሽ ባያቸው እንደው የድንገቱን
    አሳሰበኝ እግዚኦ ስንቱን።

ጓደኝነት ይዞኝ
ቃል ሆኖኝ ሰንሰለት
እንዴት እንደሚከብድ አፈቀርኩሽ ማለት!

By ዮኒ
    ኣታን

🦋@yewestenbekalat🦋

የውስጥን በቃላት

13 Dec, 19:38


ጨረቃ🌝


ነፋሱ ይነፍሳል
ውርጩ ይጋረፋል
አራዊት ይጋፋል
ሰካራም ይዘፍናል
ጨለማውም ገኗል


ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ
                  በሌት እያዜምኩት
ቀጠሮ ይዤ ነው
                ደጅ  የተቀመጥኩት
ከጨረቃ ጋራ
                  የሆዴን ላወራት
                  ህመሜን ልነግራት

እንዴትነሽ ጨረቃ    አንቺ እንደምን አለሽ
ለኔ  አትታይኝም   ምን ነው የከለለሽ
ምነዋ ጨረቃ  ለኔ የለግምሽው
                    ፍርሀቴን እያወቅሽው
ለጥቁሩ ጨለማ 🌚  ቦታ የለቀቅሽው
     ምነዋ ጨረቃ🌕
     ቀረሽ በፈረቃ

ህልቆ መሳፍርቱ
ቢከትም ከቤቱ
እዬጠበኩሽ ነው   ልቤን አምነዋለሁ
ታረፍጃለሽ እንጂ አትቀሪም አውቃለሁ
    
        አትቅሪ ጨረቃ

By Kerim

@yewestenbekalat
@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

12 Dec, 18:39


,        ፃዲቅ መሳይ

ነጠላ ለባሽ ፃዲቅ መሳይ
ውብ ሸጋ ልጅ አምሮባት ሳይ
ድንገት ተንደርድሬ ተጠጋኋት
ትኩር ብዬ ደግሞ አዬኋት
    አዬኋት አው አዬኋት
ድብቅ ሚስጥር የልቤን በር ከፈትኩላት
ትገባ እንደው ብዬም ፈቀድኩላት
ልቧን ሳላውቅ ከሷስ ሌላ አለም ይብቃኝ
እያልኩ አወራለሁ መስሎኝ ልፅድቅ ምታበቃኝ
ፃዲቅ ያልኳት ለነብሴ የምትሆን
እንኳን ለኔ ለራሷም ሳትሆን
ነጠላ ለባሽ ፃዲቅ መሳይ ያረባች
ለራሷም ሳትሆን እኔን ይዛኝ ሲኦል ገባች
@yewestenbeklat

የውስጥን በቃላት

10 Dec, 16:43


የተሸጡ እውነቶች



ኧረ ተይ ሀገሬ፣ ኧረ ተይ ኧረ ተይ
ፀሐይሽን ከድተሽ ጨረቃ አትከተይ።
        እስኪ ተመልከቺ...
መድኃኒት ውጬ ሞትኩ - መርዝ ወግተውኝ ነቃሁ፣
ስጨርስ ጀመርኩኝ - ስጀምር አበቃሁ፣
ቁልቢ ተገኘ ቋራ ያስቀመጥኩት
አራምባ ላይ ታየ፣ ቆቦ ላይ ነው ያልኩት
ጣዝማ ማር ቀምሼ፣ መረረኝ እንደ ሬት
እንዲህ ነው የሚሆን፣ እውነቶቿን ሽጣ በከበረች መሬት።

           
             _^_

 
    - ደሱ ፍቅርኤል፣
ተይው ፖለቲካን...
       

@yewestenbekalat
@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

01 Dec, 18:57


መሞትሽ አደለም መውደቅሽ አደለም...

የውስጥን በቃላት

29 Nov, 15:34


▣►▸የተገዙት ወርቆች◂◄▣

የዝምታ ሀይል ገብቶት ያገሬ ሰው
        ዋጋውን ተረድቶ

ወርቅ ነው ይሉታል ጥቅሙን ከጉዳቱ
         በጥበብ አስልቶ።
:
:
የቃላቱ   ትርጉም   ስሌቱ ሲዛባ
        አሁን በኛ ዘመን

ወርቅ የሆንን መስሎን እንዲያው እንደዘበት
          ተለጉመን ቀረን።
:
:
ዋጋ እንዲኖረው ጥቅም እንዲሰጠን
           ሚኖረን ዝምታ

መተግበር ግድ ይላል ባስፈላጊው ጊዜ
           በተገቢው ቦታ
:
:
ካለበለዚያማ

የኛ ዝምተኞች  በመጠን ቁጥራችን
        በሀገር ከበዛ

ለምን ይገርመናል ገዢ ቢበረክት
        ወርቆችን ሚገዛ።

⌲ Share     ⌲ Share



            ለተጨማሪ ግጥሞች👇👇
     ╔════════════════╗
 👉JOIN: @yewestenbekalat
 👉JOIN:
@yewestenbekalat
     ╚════════════════╝

የውስጥን በቃላት

27 Nov, 16:51


ልሳነ አፍቅሮት

ለቃል
   ለትዕዛዙ
      ብርሀንም
      ጨለማም
       ተገዝቷል ።
      
    ለበጋ
          ወቅቱ በጋ
     ሆኗል።
ለማበብ
      አበባ ፈክቶ
               ደምቆ
              አሸብርቋል ...።
  .......
.....
ኩሉ አላፊ
       ወፈላሲ
    ሆኖ ሳለ



ከማስበው
     ስሩ
            ስሩ
ከውስጥ
          ከውስጥ
ከልቤ ላይ
እሷን መጥራት
መጥቀስ አለ
ቃል የሆነ
አልፋ ኦሜጋ
ልሁን ያለ
     
                  ምክያስ አለምሰገድ(mik)

የውስጥን በቃላት

27 Nov, 16:49


ወደ አላህ በምንመለስባቸው ጊዜያት ሁሉ ነፍሳችን ምልስ ትላለች።
ሰው ነንና
አንዳንዴ ይደክመናል፤ ሁሌም ኢስቲቃማ አይኖረንም እንንሸራተታለን። ሳይታሰብ እንወጣለን ።
የወጣን ቀን በዚያው ከመንገዱ ወጥተን አንቅር።
ስንሄድ አንዳችንን በዚያው አንሂድ። እየተመለስን እሺ።

ወደ አላህ
መሳአል ኸይር❤️

የውስጥን በቃላት

26 Nov, 10:35


#የማንነታችን_አራቱ_ክፍሎች

1 #ግልፁ ማንነት፦
-----------
ይሄኛው ስለራሳችን እኛም ሌላውም ሰው የሚያውቀው ሲሆን ድርጊቶችን፣ እውቀትን፣ ክህሎትን ያጠቃልላል፡፡ ስለዚህኛው ማንነታችን ከሰዎች ጋር ለመነጋገር ችግር የለብንም በተጨማሪም ሰዎች ስለዚህ የማንነታችን ክፍል በሚሰጡት አስተያየት በብዛት እንስማማለን፡፡

2 #ድብቁ ማንነት፦
------------
ይህ ማንነት ራሳችን የምናውቀው ሲሆን ከሌሎች የተደበቀ ነው፡፡ በዚህ መስኮት ውስጥ ያሉ ማንነቶቻችንን ስለምናፍርባቸው ወይም የግል ህይወታችን ስለሆኑ  ተጋላጭ እንዳንሆን ከሌሎች እንደብቃቸዋለን፡፡ በተመሳሳይ በትህትና ምክኒያት ሰዎች እንዲያውቁ የማንፈልጋቸው ችሎታዎቻችን እውቀታችንንም ያካትታል፡፡

3 #የተሰወረ ማንነት፦
-------------
ይሄኛው ሌሎች ሰዎች የሚያዩት ከኛ ግን የተሰወረው ማንነት ነው፡፡ ምክኒያታዊ እንደሆንን እናስብ ይሆናል ሰዎች ግን ግትር እንደሆንን ነው የሚያውቁት፡፡ ወይም ራሳችንን 'ምንም እንደማያውቅ 'ልናስብ እንችላለን ሰዎች ግን በጣም ብልህና አስተዋይ እንደሆንን ሊረዱ ይችላሉ፡፡  በዚህ መስኮት ውስጥ ነው ሰዎች ቃላችን እና ድርጊታችን እንደሚለያይ የሚያስተውሉት፡፡

4 #ጨለማ ማንነት፦
----------
ይህ ማንነት በራሳችንም ሆነ በሌሎች የማይታወቅ ክፍል ነው፡፡ ጥሩም ጥሩ ያልሆኑ ሀሳቦች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡


#Share

🔅[ @yewestenbekalat ]🔅
🔅[ @yewestenbekalat ]🔅

የውስጥን በቃላት

25 Nov, 18:47


ሰዎች ሁል ጊዜ አይመክሩህም, የሚመክሩህ በሚያውቁህ ልክ ነውና::
እራስህን ሁል ጊዜ ምከር ,ካንተ የተሻለ ሌሎች ሰዎች አያውቁህምና::
تلك الدنيا...
Copy

የውስጥን በቃላት

25 Nov, 18:22


ከገራሚው መፅሐፍ የተወሰደ part 1

የሕይወት ፈተናዎች በኑሯችንና በአኗኗራችን ላይ በጎም ይሁን መጥፎ ተጽዕኖ ወይም ለውጥ ይፈጥራሉ። እነዚህ ለውጦች ደግሞ ጥያቄ እንድናነሳ ያስገድዱናል። ብዙዎቻችን መልካም በሆንና መልካም ባስብን ያላሰብነው መከራ ወደ ሕይወታችን ሲመጣና ላይ በጎ ያልሆነ ለውጥ ሲከሰት የምንጠይቀው የመጀመሪያው ጥያቄ "ለምን?"፣ "ለምን እኔ?" ወይም "ለምን በእኔ?" የሚል ነው። በዚህ ዓለም ላይ "ለምን?" ብለን የምንጠይቅባቸው ነገር ግን በቂ ምላሽ የማናገኝባቸው ብዙ ጉዳዮች አሉ። ሞት፣ህመም፣ማጣት ፣መራብ ፣የተፈጥሮ አደጋና የመሳሰሉት ችግሮች ፈልገንም ይሁን ሳንፈልግ "ለምን?" እንድንል ያደርጉናል ። የምንኖርባት ዓለም እንቆቅልሿ ብዙ ነው። ክፋት እንደ ጀብድ እየተወራ ጨዋነት የሚታፈርበት ፣ የሰው ነፍስ ያጠፉና የዘረፉ እንደጀግና የሚሞገሱበት፣ ውሸታሞች የሚከበሩበት ፣ፍርደ ገምድነት ህግ የሆነበት ጊዜ ላይ ነንና ።
ፍርድ በጉበኞች፣ ገንዘብ በአጥፊዎች ፣ መሳሪያ ፣በገዳዮች ፣ ስብከትም በኢ- አማኒዎች ገብቷልና ዓለም ለመረጋጋት ብዙ እየከፈለች ነው። አንዳንድ ባለጸጎች በድርድር ፎቅ ቤታቸው ውስጥ በልጅ እጦት ቀዝቃዛ ኑሮ ሲገፉ፣ የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው አንዳንድ ድሆች በአስር ልጅ ይታጀባሉ ፤ብዙ መልካም ስራ ይሰራሉ የተባሉ ሰዎች እየሞቱ ለራስም ለወገንም የማይበጁ ሰዎች በሕይወት ይኖራሉ፣አቅም ቢኖራቸው ለብዙዎች የሚተርፉ ሰዎች እየተቸገሩ፣ ስግብግቦች ገንዘብ ይተርፋቸዋል ። ተርፏቸው የሰረቁ ነጻ ሆነው ርቧቸው የሰረቁ ሌባ ታስረዋል። ለምን?ለምን?ለምን?
ይህ ጥያቄ በአንድ በኩል ተፈጥሮአዊ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ምክንያታዊ ይመስላል።

ከተመቻቹ👍 በማድረግ
Share & join
@yewestenbekalat
@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

24 Nov, 20:15


አብሽር የነገው ቀን እንዴት ያልፍ ይሆን? እያልክ
እራስህን ጭንቀት ውስጥ አትጨምር።
ምን ይታወቃል ከህልምህና ከምኞትህ የሰፋ
ሪዝቅ ወደአንተ እየገሰገሰ ይሆናል።😍👍

@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

24 Nov, 19:12


ስንቶቻችን ነን በዚ ህመም የምንሰቃየው....💔

የውስጥን በቃላት

24 Nov, 05:11


እንደ ነቢዩ ሱለይማን ሥልጣን ቢሠጠኝ ኖሮ የተወሰኑ ጅኖችን ልኬ ነበር የምወስድሽ አላት።

ጉረኛ! እስቲ የጅኑን ነገር እርሳና የተወሰኑ ሸማግሌዎችን ብቻ ልከህ ውሰደኝ።
አለችው።

Copy

የውስጥን በቃላት

22 Nov, 19:58


የትናንቱን ወንጀላችንን ሳንረሳ፣ የምሽቱ ኃጢታችን ሳይደርቅ ዛሬም በማለዳ ተነስተን ሌላ የምንጀምረው ነገርስ።

አላህ ሆይ!አልፋታ ብሎ ዕድሜ ልካችንን የሚከታተለንን ጥፋታችንን ቁረጥ።

ኃጢአቱ አብሮት ያልተነሳ ሰው ምንኛ ታደለ!ለንፁህ ተውበት አድለን - ያ ረብ።
@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

22 Nov, 18:19


በብርሀን ፍጥነት ከጎኔ ቁጭ ይላል...

የውስጥን በቃላት

21 Nov, 19:13


😢ናፍቀኸኛል💔

..አዎ አንተ 🫵
________
💔@yewestebekalat💔
________

የውስጥን በቃላት

21 Nov, 03:41


<አንቺ ካለሽ>

ኤልያስ ሽታሁን🥰

የውስጥን በቃላት

21 Nov, 03:40


Na zem belh ekefegne❤️...

የውስጥን በቃላት

20 Nov, 17:48


የሲስተርን ልጅ እያስጠናሁት "በቅሎ" ለምን መውለድ እንደማትችል ንገረኝ ስለው...

በቅሎ ሲጀመር ከስሙ እንደምንረዳው እራሷ ተወልዳ ሳይሆን "በቅላ" ነው አለኝ 😳😳😜🤣

የውስጥን በቃላት

20 Nov, 13:33


....አሪፍ ነው አብረን ዝም እንድንል...

የውስጥን በቃላት

20 Nov, 03:30


ዝም ብላ ምትስቀው
ልቤን  እስክትሰርቀው

ያወራሁት ወሬ
ሚገርማት አስሬ

ስሜን በየቦታው
[ ሺ ግዜ ምትፈታው ]
ምጥን ንግግሯ
  ቃሏ ሚጣፍጠው
ዝም ያለ አንደበቴን
  ማብራሪያ ምትሰጠው

ህልሜን ከእውኔ ጋር
    አይኔን ልትገልጠው
በቄንጥ ተራምዳ
  መርጣ ምትረግጠው

ፀጉራ ሲዘናፈል
ሽንጧ ሲውረገረግ
ከአለም ነጥላ 
  ከስሯ ለማድረግ

እስካልቆጥር እድሜ
የሆነችኝ ህልሜ

ከ'ናት በላይ ቀርባኝ
ሆዴን ምታባባኝ

ዜማ ወረብ ሳቋን
የመኖር ሲር ሀቋን

አሳይታኝ ልትበር
ከጎኔ ያረፈችው
እስክወዳት ነበር


🌹@yewestenbekalat 🌹
🌹 @yewestenbekalat 🌹

የውስጥን በቃላት

16 Nov, 03:30


Yemarshe...
Yanureh🤗

የውስጥን በቃላት

13 Nov, 18:57


አላህ የምትወዱትንና የምትጓጉለትን ነገር ስላዘየገባችሁ ብዙ አትዘኑ፡፡ የማትፈልጉትን ዓይነት ስላኖራችሁም ብዙ አትተክዙ፡፡ የጠበቃችሁት ቀርቶ ያልጠበቃቸሁት ሲሆንም ነገሮችን በእርጋታ ተቀበሉ፡፡ በሁሉም ነገር ታገሱ፣ አላህ የወደደላችሁን ዉደዱ፣ በአላህ ላይ ተሳሰቡ፣ ፈገግ በሉ፡፡

እኛ በማናውቀው መልኩ ከመጋረጃ በስተጀርባ ኸይር ነገር አለ፡፡ ስንደርስ እናያለን፡፡ ይጋገር፣ ይብሰል አትቸኩሉ፡፡

@yewestenbekalat
@yewestenbekalat
@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

12 Nov, 20:29


➻ስለ ፍቅር የምናወጋበት
➻ ስለ ክህደት የሚዘከርበት
➻ ስለ ናፍቆት ደስታ
➻ ሀዘኖን የሚገልፁበት
➻ ጭንቀት መከፋትን የውስጣችንን ምንገልፅበት
➻just ስለሁሉም የውስጦን በቃላት የሚገልፁበት ምርጡ ቻናል ይቀላቀሉን

@yewestenbekalat

አስታየት ካላቹ
@Mmssfyhs6
https://t.me/yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

12 Nov, 09:55


#ተጣልተናል_እኮ
.
እንደማንመለስ ምለን በታቦቱ፣
ንግግር ካቆምን አልፈዋል ወራቱ፣
ኧረምን ወራቱ አመታቱም ነጉዷል፣
ሌላ ወድጃለው እሱም ሌላ ወዷል፣

ግና....
ቁልምጫ በሚሉት እዳ ተለክፌ፣
ሙሉ ስሙን መጥራት አለመደም ኣፌ፣
ተጣብቆብኝ አንዴ የቁልምጫው ነገር፣
ስለሱ ስጠየቅ ለሰዎች ስናገር፣
ውዴ፡ ማሬ፡ ፍቅር፡ ላለማለት ስጥር፣
ይቀድመኛል ኣፌ ባስታዎስኩት ቁጥር።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው



ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት📱📲
        🥀@yewestenbekalat
         🥀@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

11 Nov, 19:53


ያው ምትሳተፋትን እያመሰገን🙏🙏🤝

የውስጥን በቃላት

11 Nov, 19:50


ኧረ በቃኝ ይሄስ ዓለም
ቀኔ ጎድሏል ሙሉ አይደለም።
ልሂድ ልግዛ ፣ አንዲት ገመድ
ልጓዝ ልብረር ፣ በሙት መንገድ።
ያስከፋኛል አገዛዙ ፣
ዙሪያው ገባው አያያዙ
የሰው ክፋት ጉድ ፣ መዘዙ
አላፈራም … ከምዘራው
እንባዬን ነው የማዘራው።
:
ልሂድ በቃ ልሰናበት…
ዘመኔ ላይ ልፍረድበት …
አንዲት ገመድ ላንዲት አንገት
በሽንቁሯ ልለፍበት ፤
ብዬ ጀመርኩ የሙት ጉዞ
ልቤ ቀልቤ ተመርዞ … ።
:
ግና ከንቱ…
ምን ዋጋ አለው?
:
አገኘኋት ስረማመድ
ያቺን ሸጋ ልጃገረድ
ገለጠችው ያንን ከንፈር
ይኸው ሳቀች ለክፋቱ
ልኑር በቃ ምናባቱ!

(ሚካኤል አ)

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
         @yewestenbekalat
         @yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

11 Nov, 19:12


እኔ ምለው ምርጦች😍😘 reaction ማድረግ ያስከፍላል እንዴ
አረረረረ ተሳትፍ የለም
የደበራቹን comment 👇
ደስያላቹን በ👍
ያልተመቻቹን ደሞ እድናስተካክል

@Mmssfyhs6
lay asawekun 🫰🫰

Shega meshet yehunlachu

የውስጥን በቃላት

10 Nov, 08:17


ልብህ ያደክምሀል . . .

ታማኝና ንፁህ በመሆንህም ብቻ. . ያንተ ስሜትና ሀሳብ ሌሎችን ሲጎዳና ሲያስቀይም ትመለከታለህ። ከጠበቅካቸው በላይ በክፋታቻው ያስደምሙሀል። ልብህ ለሀዘንህ ያንስሀል። ሀዘንህ ከልብህ ገዝፎ ቃላቶች የውስጥህን ሊገለፁልህም ይሰንፋሉ። ጥፋትህ. . . እውነተኛ መሆንህ ብቻና ብቻ ሆኖ ሳለ!❤️‍🔥

Copy

የውስጥን በቃላት

10 Nov, 08:17


አዳንድ ክህደቶች ከማሳመም አልፈው😢 ማንነታች እስከመለወጥ ይደርሳሉ💔
📝@yewestenbeklat📝
#Share and join

የውስጥን በቃላት

09 Nov, 13:20


ሁሌም ቢሆን ቡቻህን ለመኖር ዝግጁ ሁን....👍

የውስጥን በቃላት

08 Nov, 18:35


እናቴን ለመካስ ነው ...

የውስጥን በቃላት

06 Nov, 19:39


ሲጠየቁ አልሐምዱ ሊላህ❤️‍🩹 ደህና ነን የሚሉ፣ ግን በዉስጣቸው የደከሙ ባሮችህን ሁሉ እርዳቸው ያ ረብ🙏

@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

05 Nov, 17:35


በዚህ  ሰዓት  በጣም  ለናፈቃቹ ሰው  ❤️‍🔥 

አንድ  መልዕክት   አስቀምጡ...

👇👇👇👇

የውስጥን በቃላት

05 Nov, 02:08


መለየት

( በእውቀቱ ስዩም )


የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለሽ
ከፊትሽ ቁጭ ብዬ
ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወሪው ሳይገባኝ
የማወራሽ ሳይገባሽ
ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ
ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @yewestenbekalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
4 any comment             
       @yewestenbekalat
❥❥__⚘_❥❥

የውስጥን በቃላት

01 Nov, 18:45


"ሁላችንም ልናወራዉ የማንፈልገዉ ታሪክ አለን!!

የውስጥን በቃላት

01 Nov, 09:29


ለወንድምህ ልትውለውየምትችለው ትልቁ ውለታ አላህ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲመራውና እና እንዲያፀናው , ምህረቱንም እንዲለግሰው ዱዐ ማድረግ ነው:: ሌሎችም ላንተ ሊውሉ የሚችሉት ትልቅ ውለታ ይኸው ነው ::

"قَالَ رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِأَخِي وَأَدْخِلْنَا فِي رَحْمَتِكَ ۖ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ"

"(ሙሳም)፡- «ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወንድሜም ማር፡፡ በእዝነትህም ውስጥ አግባን፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» አለ፡፡"
الأعراف 7:151

"وَالَّذِينَ جَاءُوا مِن بَعْدِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا اغْفِرْ لَنَا وَلِإِخْوَانِنَا الَّذِينَ سَبَقُونَا بِالْإِيمَانِ وَلَا تَجْعَلْ فِي قُلُوبِنَا غِلًّا لِّلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا إِنَّكَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ"

"እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት «ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችን ምሕረት አድርግ፡፡ በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ፡፡ ጌታችን ሆይ! አንተ ርኅሩህ አዛኝ ነህና» ይላሉ፡፡"
                     الحشر59:10

"ይህን ውለታ ለመዋል ደግሞ ትውውቅና ዝምድናም  አያስፈልግም, የኢስላም ገመድ በቂ ነው:: ምን ይታወቃል አሏህ የማናውቀው ደግሞም  የማያውቀን ሰው በሚደያደርግልን ዱዐ ይምረን ይሆናል:: በዚህ ውስጥም ላስተዋለ የኢስላም ውበት የአሏህ እዝነት ደምቆ ይታያል::

ለእኔም ዱዐ አድርጉልኝ::


تلك الدنيا...

የውስጥን በቃላት

30 Oct, 17:05


በቀብር የምታገኘው ያ ማራኪዉን የአትክልት ሥፍራህን አይደለም
ታመርተው ከነበረዉ ፍራፍሬ ጭምር የተንጣለለው ሰፊ የመኖርያ ግቢህ፣ዙርያህን ከበዉ የነበሩት ቤተሰቦችህ፣ሰራተኞችህ ፣ ውቢቷ ባለቤት ፣ቆንጆዎቹ ልጆችህ እና ወዘተ ሌሎችም ምድራዊ ታላላቅ ሀብቶችንና ወዳጆችህን በሙሉ ትተህ ነው በዚያች ሁለት ሜትር በግማሽ ሜትር ስፍት ባላት መቃብርህ ውስጥ የምትከተተው
ሁሉም መቃብርህ ጋር አድርሰውህ ይመለሳሉ
ከዛ ቡሀላ ቀብር ዉስጥ ብቻህን ነህ
ካንተና ከስራህ ውጪ በዚያች ጠባብ ጉድጋድ ማንም አይገባም
ከስራህ ጋር ፊት ለፊት ትፋጠጣለህ
በመልካም ምግባር እድሜህን ቆጥረህ ከነበረ ጠባቧ ትሰፋለች ጭንቀትም ሆነ ፍርሀትህ ይወገዳል
ከዚህ በተለየ ሕይወት በጥመት አሳልፈህ ከነበር ውይ መጥፋትህ!
በቀብር ዉስጥ ብትቆጭ ትርጉም አይኖረውም😔😭

የውስጥን በቃላት

29 Oct, 18:05


የሰው ልጅ መሰረታዊ ነገር ምንድን ነዉ
ምግብ🍎
መጠለያ🏠
ፍቅር❤️‍🔥

የውስጥን በቃላት

27 Oct, 18:47


አንዳንዴ ምናለ ትንሽ ባርፍ እላለው ምንም ባላይ🫣፣ምንም ባልሰማ ፣😣እንዲው አይኔን ጨፍኜ ቀናቶች ቢአልፉ ....ኦፍፍ በጣም ከፍቶኛል😞💔

ያረብ አበርታኝ🙏
@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

27 Oct, 17:53


Four type of boys when they see a beautiful girl 👧

የውስጥን በቃላት

27 Oct, 17:39


ከእይታ ሁሉ ተሸሽገህ ከጌታህ ፊት በግንባርህ ተደፍተህ የለመንከው ዱኣ ምላሹን አትጠራጠር::
በረሃብ እሳት የተለበለበ ሆድ አንተ እሳቱን አጥፍተህለት   አረፍ ብሎ ያደረገልህን ዱኣ አትጠራጠር::
ርዝቁን ፍለጋ ሲንከራተት ርዝቁንም አላህ አንተ እጅ ያስቀመጠለት ከዛም በጣም ተደስቶ ያደረገልህን ዱኣ አትጠራጠር::

ምክንያቱም የሱጁድ...የተራበ ሆድና...ባንተ የተደሰተ ልብ አላህን ለምኖ ምላሽ ሲከለከል ኣይተን አናውቅምና:::::::

Copy

@yewestenbekalat
@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

27 Oct, 05:14


አላህ ሆይ🙏 የታመሙ ወዳጆች አሉን።😞 የምንወዳቸውን ሁሉ ፈውስልን።❤️‍🩹

@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

25 Oct, 20:23


🫀

የውስጥን በቃላት

23 Oct, 13:27


እብሪት ና እልህ አይወጥራችሁ። ካፈርኩ አይመልሰኝ አትበሉ። "ልክ ነህ ግፋበት" ብሎ የሚደልላችሁንና የውሸት ጉልበት የሚሠጣችሁን ስሜት ወዲያ ግፉ።

  አንዳንድ ጊዜ መለስ በሉና ምን ያህል ትልቅ ሰው እንዳጣችሁ እመኑ። በገዛ እጄ ለዱንያ አኺራዬ የሚጠቅመኝን ማጣት ያልነበረብኝን ሰው እኮ ነው ያጣሁት በሉ።

ለናንተው ለእልኸኞች🤨

© Muhammed Seid

∞@yewestenbekalat
∞@yewestenbekalat
∞@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

22 Oct, 18:29


"ንግግርህ ምርኮኛህ ነው"

ንግግርህ ምርኮኛህ ነው :ካፍህ ከወጣ ደግሞ ምርኮኛው ትሆናለህ።

@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

20 Oct, 17:21


አንዳንድ ሰዎች ግን ታድለው! በዚልክ መፈቀር ፣ከመጠን በላይ መናፈቅ ፣ከሚባለው በላይ አንድ ሰው ልብ ላይ ለማንም ሳያስ ቀሩ ጠቅለው የያዙ 😢ግን.... እኛን በዚልክ የሚ ናፍቀን ሰው ማነው💔 እ.....

የውስጥን በቃላት

19 Oct, 18:37


እውነት ነው አይደል?
የሁላችንም ልብ ውስጥ አንድ ያልዳነ ህመም አለ💔
በጊዜ ሀይል ያረሳ ነው.....

የውስጥን በቃላት

18 Oct, 20:52


2017 lay
Me & relationship 😂😎

የውስጥን በቃላት

18 Oct, 20:25


ብዙ የማያልፉ የሚመስሉን ጊዜያቶች አልፈዋል
በሰዓቱ ግን የማያልፍ መስሎን ታይቶን ነበር
አሁን ላይ ያለንበት ደስታ ይሁን ሀዘን ያልፋል።

በዚህች ምድር የማያልፍ ነገር የለም!!

@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

17 Oct, 20:06


እስኪ ምርጦች😍🥰

አሁን ላይ እስኪ ከትንሽ እስከ ትልቁ እንዲ ድብርታ ውስት ፣ ሀዘን፣ተስፋ መቁረጥ እንዲሰማው ያረገው ምን ይመስላቹአል?

እናንተ የራሳቹን ስሜት መግለፅ ትችላላቹ

comment lay👇

የውስጥን በቃላት

17 Oct, 18:51


በውስጥህ ያንቀላፋውን ጀግና አንቃው፡፡ተዓምር የሚሰራ ሀይል ባንተ ውስጥ አለ፡፡የችግርህን ተራራን ትንዳለህ፡፡ያስጨነቀህን ድንጋይ ትሰብራለህ፡፡የአለምን ህዝብ ታሰደምማለህ፡፡ሞክንያቱም አቅም አለህ፡፡አንተ ልዩ ሰው ነህ፡፡እንደ አንተ አይነት ሰው በዓለም የለም፡፡አንተ አንተን ነህ፡፡ሰዎች ለመመሰል አትጣር፡፡ሀይልህን ታጣለህ፡፡
ከነምናምንህ ራስህን ሁን! ራስህን ካላወክ ራስህን ፍጠር፡፡

የውስጥን በቃላት

16 Oct, 19:46


ተራ ተራ ቀጣዩ ሰው
በሉ ግቡ ያለፈውን ደሞ ልርሳው
            :
የበፊቱን ለትዝታ
ዛሬን ልኑር ሳልምታታ
              :
ነይ ለዛሬ ነይ ለነገ
ዛሬ ይላል ትላንትናን መንቀሳቀስ ያልፈለገ
              :
ለኔ ዛሬ ነገዬ ነው ትላንትና ትዝታዬ
መደበቄ መሸሸጌ ለመኖር ነው ዝምታዬ።


ዮሴፍ።።።።።።።።ለማ።።።።።።።።።።።።

@yewestenbekalat

የውስጥን በቃላት

14 Oct, 18:37


ልጆች እያለን ማደግን እንመኝ ነበር, ካደግን በኋላ ደግሞ ልጅነት ይናፍቀናል,ምናልባት ያ ንፁህ ልባችን ናፍቆን ይሆን?
           አሏህ ንፁህ የሆነን ልብ ይስጠን
ያኔ እስክናድግ መጠበቅ ግድ ነበር , አሁን ደግሞ ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም::
ለሁሉም ጊዜ አለው
 

تلك الدنيا...

የውስጥን በቃላት

13 Oct, 20:40


በወንድ ልጅ በደል ምክኒያት
የሴት ልጅ አይን ካነባች/ካለቀሰች
"በሚራመደው እርምጃ ልክ
መላኢኮች ይረግሙታል!
[ᵃˡⁱʸ ⁱᵇⁿ ᵃᵇⁱ ᵗᵃˡⁱᵇ]

ይሰማል ‼️


ለዚ ወንድሞች እያስተዋላቹ😉

@yewestenbeklat