በከተማችን የነዋሪዎችን እንግልት የሚቀንስ እና ብልሹ አሰራርን በዘመናዊና የተሟላ ዲጂታል የሲቪል ምዝገባ ስርዓት የሚተካ፣ለነዋሪዎች ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚስችል ለሀገራችን ሞዴል የሆነ ስራ እየሰራን እንገኛለን።
የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ ምዝገባን፤ የነዋሪነት መታወቂያ አሰጣጥን፤ ሰነድ ማመሳከር እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ ዲጂታል አገልግሎት በመተካትና ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ 132 የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በካሜራ ቁጥጥር ስርዓት የተሸፈኑ በማድረግ የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ፣ የመታወቂያ፣ ሰነድ ማመሳከር እና ተያያዥ የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶች በየእለቱ በየወረዳው በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት፣ ከማዕከል አገልግሎት አሰጣጡን መከታተል እና በየሰአቱ እና በየዕለቱ ምን ያህል አገልግሎት እንደተሰጠ ወዲያዉ ያለምንም ሪፓርት ማወቅ የተቻለበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።
የተቋሙን ሰራተኞች የተቋሙ ሰራተኛ በመምሰል ከሚያጭበረብሩ እና ከደላላዎች መለየት እንዲቻል ሁሉም የደንብ ልብስ እና መለያ ባጅ እንዲኖራቸው በማድረግ ከአሰራር በተጨማሪ ሰራተኛዉን መለየት እንዲቻል ግልፅነትን ጨምረናል።
ለነዋሪዎቻችን በማዕከሉ ከሚሰጡ አገልግሎቶች በተጨማሪ የሰርግና የልደት ፕሮግራሞቻቸውን በጊቢው ውስጥ እንዲያከናውኑ የቀድሞው ሸገር መናፈሻ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ተደርጓል። በትላልቅ ፓርኮች እና የመዝናኛ ቦታዎች ከፍለው ይህን አገልግሎት ማግኘት የማይችሉ ነዋሪዎቻችን በዚህ ጊቢ እና በቅርንጫፎቹ በተዘጋጁ የሰርግና የልደት ማክበሪያ ቦታዎች ፣ የቁሳቁሶች እና የፎቶግራፍ ግልጋሎት ጭምር እንዲያገኙ በማድረግ ፍትሃዊነትን እያረጋገጥን እንገኛለን።
በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎትን በዋና መስሪያ ቤትም ሆነ በየቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ እና ሰፋፊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ተቋማት ነዋሪዎችን በመመዝገብ ላይ እንገኛለን። በዚህ አጋጣሚ የብሄራዊ መታወቂያ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ሁላችሁም ምዝገባችሁን እንድታጠናክሩ ጥሪ አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን
ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et
የፌስቡክ (facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686
ቴሌግራም (telegram): https://t.me/addisvaitalpress
ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320