********************************
(የካቲት 11/2017ዓ.ም፡ የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተውጣጡ የቅርንጫ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች IFRS (INTERNATIONAL FINANCIAL REPORTING STANDARDS) አተገባበር ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ወ/ሮ አስቴር አዱኛ በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ የተቋማዊ አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ባስተላለፉት የመክፈቻ ንግግር አንደገለፁት የተቋሙን ሰራተኞች አቅም በመገንባት ለግብር ከፋዩ ጥራት ያለውና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ በመዘርጋት ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በብቃት መሰብሰብ እንደሚያስፈልግ እና በዚህም የሰራተኛውን አቅም መገንባት ትልቅ ድርሻ እንዳለው፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱም የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የራሱን ድርሻ እየተወጣ እንዳለ የዛሬው ስልጠናም የዚሁ አካል መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሰልጣኞችም የወሰዱትን ስልጠና ወደተግባር መቀየር እንደሚጠበቅባቸው እና ለሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው በማጋራት የእርስ በርስ አቅም ማጎልበት እንደሚያስፈልግ፤ በቀጣይም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተለያዩ ስልጠናዎችን ለሰራተኞቹ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
ስልጠናው ከታክስ ጋር በተገናኘ የIFRS አጠቃቀም ምን ይመስላል? ስራ ላይስ እንዴት ይውላል? በሚለው ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በአቶ አይተነው እንዳሌ የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ የተሰጠ ሲሆን በሰው ሀይል አመራርና ልማት የሥራ ሂደት ተዘጋጅቷል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ ከታክስ ጋር በተገናኛ የ IFRS አተገባበር ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን እና በስራ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመሙላት ሲሆን ከስራቸው ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ሰራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡
ግብር÷ ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2