Ye Haybaw Mender @yehaybaw Channel on Telegram

Ye Haybaw Mender

@yehaybaw


اللهم صل عل سيدنا ونبينا وحبيبنا وشفيعنا محمد 💚💚💚

Ye Haybaw Mender (Arabic)

Ye Haybaw Mender هو قناة تيليجرام رائعة تهدف إلى نشر السلام والمحبة والتسامح. يمكنك الانضمام إلى هذه القناة لتلقي رسائل يومية تلهمك وتجلب لك السعادة والإيجابية. بفضل الرسائل والصور والفيديوهات التي تنشرها Ye Haybaw Mender، سوف تشعر بالطمأنينة والتأمل. ستجد في هذه القناة مجتمعاً ملهماً يشارك الحب والخير مع الآخرين. انضم اليوم إلى Ye Haybaw Mender لتكون جزءاً من هذه التجربة الرائعة وتعيش في جو من السلام والإيجابية والتفاؤل. اللهم صل عل سيدنا ونبينا وحبيبنا وشفيعنا محمد 💚💚💚

Ye Haybaw Mender

21 Feb, 17:44


﴿اِن ينصركُم الله فلا غالِب لكم...﴾

{If Allah helps you no one can defeat you}

[አላህ ቢረዳችሁ ለእናንተ አሸናፊ የለም]
ሱረቱል አል ዒምራን 160

ስለዚህ አላህን ያዙ አላህን ያገኘ ምን አጣ??

Ye Haybaw Mender

20 Feb, 17:29


አያልፉም ያልናቸው ቀናቶች በሰለዋት አልፈውልናል .....

እስቲ በነዛ አዛኙ ነቢያችን ላይ ሰለዋት እናውርድ ....

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد

መልካም ኸሚስ💚💚

Ye Haybaw Mender

15 Feb, 17:22


አላህ አንድን ነገር እንዲሰጣችሁ አልቅሳችሁ በለመናችሁበት ቦታ

ስለሰጣችሁ እያለቀሳችሁ ሀምድ ማቅረብ ያለው ስሜት .....

አላህ🤍🤍

ትንሽ ብቻ ታገሱ

Ye Haybaw Mender

14 Feb, 17:47


አላህ ሆይ ፍቅርህን❤️‍🩹❤️‍🩹

Ye Haybaw Mender

12 Feb, 17:29


የአላህ:-

በሰዎች ላይ የጠላነውን ወንጀል
በእኛ ላይ አታሳየን..

Ye Haybaw Mender

11 Feb, 03:54


አላህ ከፍራሽ እስከ አርሽ ድረስ የሚያህል ፀጋን ቢለግስህ :-

<<አንተን ነው የምፈልገው በለው>>

ሰይዲ በስጧሚ (ቀ.ሲ)

Ye Haybaw Mender

09 Feb, 04:33


لن يذهب لغيرك شيء
قد كتببه الله لك

አላህ ለአንተ የፃፈው ምንም ነገር
ወደ ሌላ ሊሄድ አይችልም


መልካም ቀን🌼🌼

Ye Haybaw Mender

04 Feb, 17:52


ለተዘጋብኝ በር አላማርረውም
የሚበጀኝ ቢሆን ፊትም አይዘጋውም
ሳለቅስ አልገኝም በምሬት ስኳትን
ከፍቶልኝ ስለሚያውቅ ያላንኳኳሁትን

አላማርረውም 🌸🌸

Ye Haybaw Mender

01 Feb, 17:46


የአዛውንቱ ታሪክ 📥

  📍  በአንድ ገጠራማ መንደር ውስጥ መስገጃ ቦታ ያልነበራቸው የአካባቢዋ ነዋሪዎች መስጂድ ለመስራት ይነሳሉ ,

  
📍እንጨት ያለው እንጨት ጣራ መሸፈኛ ያለው ያለውን ሁሉም ያላቸውን እየያዙ ወጡ መስገጃ ቦታዋም መሰራት ጀመረች በዛ ርብርብ መሀል ግን አንድ ልባቸው የተጨነቀ አዛውንት ነበሩ በእጃቸው ከሚይዟት ምርኩዝ ውጭ ምንም  አልበራቸውም
   
  
📍 ወጡ  ወረዱ ለመስጂዳቸው ምንም ማረግ ባለመቻላቸው ልባቸው ተሰበረ ያቺ ያለቻቸውን ብትር እየተሰራ ባለው እንጨት መሀል አቁመዋት  ልባቸው እንደተነካ በጉልበታቸው ምንም ማረግ ባለመቻላቸው እያዘኑ ተመለሱ

🔖 እኚህ አዛውንት ያላቸውን በሙሉ ነው የሰጡት        እኛስ🤔
  🔖 አላህ ሊፈትነን ቢሆንስ ያለንን ሁሉ የሰጠን

   📍 አሁንም ጊዜ አለን


📌ንግድ ባንክ 1000666086458
📌ንብ ባንክ
   206
                 7000009165555
📌አቢሲኒያ 212115282

ለበለጠ መረጃ 📥 ኮሚቴ 🔽

0962515143 ዶክተር  ሙሳ
0913483618 ኢንጂነር  አልዩ በደዊ
0913425461 ፈድሉ ኡመር
0920242782 ሀምዱ ሸምሱ
0917949168 መሀመድ ይልማ

Ye Haybaw Mender

31 Jan, 07:27


አለሙ በሞላ ወርቅ ቢሆን
እንደኔው ነቢዬ ማንም አይሆን

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد 💚💚

መልካም ጁመዐ

Ye Haybaw Mender

30 Jan, 17:39


اللهم صل وسلم على سيدنا محمد
اللهم صل وسلم على شفيعنا محمد
اللهم صل وسلم على حبيبنا محمد

መልካም ኸሚስ

Ye Haybaw Mender

30 Jan, 03:36


አላህን ከማውሳት ከሚያርቅህ ምቾት ይልቅ ......
ወደ አላህ የሚመልስህ ችግር ይሻላል

Ye Haybaw Mender

26 Jan, 18:08


ዛሬ ለሊቱ ረጀብ 27 እንደመሆኑ
በዒባዳ ለማሳለፍ እንሞክር

ነገ ለመፆም ኒያ እናድርግ

መልካም ምሽት 🤍🤍

Ye Haybaw Mender

19 Jan, 17:44


ልብ እንደ ድስት በያዘው ነገር ይንተከተካል...ምላስ ጭልፋው ነው

አንድ ሰው ሲናገር አድምጠው ልቡ ውስጥ ካለው እየጨለፈ ነው

መልካም ምሽት 🫠

Ye Haybaw Mender

19 Jan, 11:35


{تنسى كانك لم تكن }

ጭራሽ እንዳልነበርክ ተደርገህ ትረሳለህ!!

Ye Haybaw Mender

18 Jan, 20:59


የስልክ ቁጥራቹ መጨረሻ ስንት ነው?

Ye Haybaw Mender

18 Jan, 20:38


🧕 ኢምሀል ልብ እንጠልጣይ ታሪክ 🧕

ታሪክ ማንበብ ይወደሉ ?

እንግዲያው ይቀላቀሉን ምርጥ ምርጥ የተመረጡ ታሪክ የሚለቀቅበትን channel ልጋብዛቹ 🥰

Join ብቻ በሉ 🙂
👇👇👇👇👇👇👇👇

Ye Haybaw Mender

18 Jan, 19:54


የሴት_ምላስ🤭
ሸይኹ በሚያስተምርበት መስጂድ ውስጥ ሰዎች የሚሰጡትን ክብር እንድትመለከት ሚስቱን አስከትሎ ሄደ። በምላሷ ትወጋው ስለነበር አዛዋን ለማስቆም መሆኑ ነው።…
:
መስጂድ ውስጥ ሚንበር ላይ ቆሞ ሲያስተምር ዋለ። እቤት ሲመለሱ ሃሳቧን ጠየቃት።
«.
.
.
.ሙሉውን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇
join

Ye Haybaw Mender

18 Jan, 18:34


📣 sponsored Fx_Squad 📌

‼️important message ☄️

🕯ስለ Forex trading ብዙ ቦታ ሰምታችሁ ይሆናል ግን አስካሁን በነፃ የሚያስተምር አታችሁ ተቀምጣችሁ ይሆናል 🤔

✏️ዛሬ ግን አሪፍ መረጃ ይዤላችሁ መጥቻለሁ በጣም አሪፍ አሪፍ የሆኑ አስተማሪኦች course 💯💯 በነፃ የሚያቀርብ channale ላስተዋውቃችሁ

🩸🩸 🩸🩸🅰️🩸🩸🩸🩸🩸

💧ብዙ ቦታ በ ብር የሚሸጡ course በነፃ አቅርቦላቹሃል  ግቡ እና እዩት🔘

Joined 👇👇👇👇👇👇

🔗 https://t.me/fx_squad2

Ye Haybaw Mender

18 Jan, 04:17


በጤና በተያዝን ጊዜ ኮርተን በበሽታ በተያዝን ጊዜ ወዳንተ ብንመለስም...

"የት ከረማችሁ ሂዱ ከዚህ !
አትለንም

አላህ 🤍

Ye Haybaw Mender

17 Jan, 04:05


በሰለዋት ያሸበረቀ ጁመዐ ይሁንላችሁ

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد 💚💚

Ye Haybaw Mender

14 Jan, 09:32


By the way

ስታጡም አልሃምዱሊላህ በሉ
በማጣት ውስጥ ማግኘት አለ

መልካም ቀን🌸🌸

Ye Haybaw Mender

11 Jan, 18:42


ከአላህ ጋር ሁላችንም ደህና ነን


መልካም ምሽት 🫠🫠

Ye Haybaw Mender

09 Jan, 17:02


በመጨረሻም ቃሉን የሚጠብቀው አላህ ብቻ መሆኑን ታረጋግጣለህ

መልካም ኸሚስ 🫠🫠
ሰለዋት እንዳትረሱ

Ye Haybaw Mender

07 Jan, 14:08


ሙዕሚንን:-

ካልጠቀምክ አትጉዳው
ካላስደሰትከው አታስከፋው
ማወደስ ካልቻልክ አታዋርደው

Ye Haybaw Mender

06 Jan, 18:19


ሙስሊም ሆናችሁ ሰላት የማትሰግዱ ሰዎች አንድ ጥያቄ ብቻ ልጠይቃችሁ ??

ለምንድነው ሰላት የማትሰግዱት ?
አላህ ምን ቢያደርጋችሁ ሰላት አንሰግድም ያላችሁት ?

አላህ ሌሎችን ፈትኗቸው ለጣዖትና ለተለያዩ ነገሮች በሚሰግዱበት ሰዐት እናንተን መርጦ ሙስሊም አደረጋችሁ ፤ ሙስሊም ካደረጋችሁም በኋላ ሰላት እንድትሰግዱ አዘዛችሁ እና ሰላት የማትሰግዱበት አንድ ምክንያት ንገሩን እስቲ ...

አንድ ሰው ሰላትን ከተወ ስሜቱን መከተል ይጀምራል ስሜቱን መከተል ከጀመረ በሁሉም ወንጀል ውስጥ መገኘት ይጀምራል

ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ...<<ሞኝ ብሎ ማለት ስሜቱን ያለውን በሙሉ ተከትሎ ወንጀል ፈፅሞ ጀነት የሚመኝ ነው>> ብለዋል

አንድ ሰው ሰላትን በተወ ጊዜ የነቢያችንን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አደራ ይበላል ምክናያቱም የመጨረሻ ንግግራቸው ሰላታቹን አደራ ነበርና!!

mame hz

Ye Haybaw Mender

05 Jan, 16:31


የልብህን መፅዳት እና መብራት ሶስት ነገር ጋር ፈልገው

1 ቁርዐን እያስተነተኑ እና ቀስ ብሎ በመቅራት

2 አዝካር በማብዛት

3 በተሰበረ ልብና በፈራ ሰውነት ለይል በመቆም

መልካም ምሽት 🫠🫠

Ye Haybaw Mender

04 Jan, 03:54


በአላህ ብቻ ተሻገል!!

መልካም ቀን🤗🤗

Ye Haybaw Mender

26 Dec, 17:43


አላህን የፈራ ማንም አይጎዳውም
አላህን ያልፈራ ማንም አይጠቅመውም


መልካም ኸሚስ 🫠🫠

Ye Haybaw Mender

19 Dec, 17:31


ሀጃ ያለባችሁ ያሳሰባችሁ ነገር ካለ
በሉ ሰለዋት እናውርድ ...

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد


መልካም ኸሚስ

Ye Haybaw Mender

07 Dec, 20:30


የስልክ ቁጥራቹ መጨረሻ ስንት ነው?

Ye Haybaw Mender

07 Dec, 20:02


የሴት_ምላስ🤭
ሸይኹ በሚያስተምርበት መስጂድ ውስጥ ሰዎች የሚሰጡትን ክብር እንድትመለከት ሚስቱን አስከትሎ ሄደ። በምላሷ ትወጋው ስለነበር አዛዋን ለማስቆም መሆኑ ነው።…
:
መስጂድ ውስጥ ሚንበር ላይ ቆሞ ሲያስተምር ዋለ። እቤት ሲመለሱ ሃሳቧን ጠየቃት።
«.
.
.
.ሙሉውን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇
join

Ye Haybaw Mender

07 Dec, 19:31


💔'#ሙሽሪትን_ማን_ገደላት?' 💔
 
...ዛሬ ለየት ያለ ቀን ነበር ሰርግ'ማይደል! ሁሉም ተሰብስበው ጨዋታ እያፈኩ፣ ልጆች እየጨፈሩ ሰፈሩ ድምቅ ብላል።   ምሽት 1 ሰአት ተኩል ገደማ "እርርርርርርርይ" የሚል ድምጽ ተሰማ። ከርቀት ነበር። ጩኸቱ እየቀረበ መጣ፤ ሁሉም እየሮጠ ወጣ አንዲት ወጣት ቀሚሷ በደም እርሷል መሬት ላይ ተዘርራለች ሁሉም የሚያዩትን ማመን አቃታቸው። አንገቷ ላይ ያለው ደም መሬቱን ሞልቶታል። ሁሉም የሚያደርገውን አያቅም። እሪታው እየሞቀ ቀለጠ.......See More

ሙሉውን ለማግኘት #OPEN ይበሉ 👇👇

Wave - @semutiyeee

Ye Haybaw Mender

05 Dec, 03:52


Ye Haybaw Mender pinned «ሁለት ዶሮዎች የነበሩት ሰዉዬ ነበር አንዷ ዶሮ በጣም ሷሊህ ናት አታስቸግርም አትረብሽም አንዷ ዶሮ ግን በጣም አስቸጋሪ ናት ...ሰውየው ምግብ ሚሰጣቸው በእኩል ሰዐትና እኩል መጠን ነው ፤ ሷሊኋ ዶሮ የተሰጣትን ቀስ ብላ በልታ ወደ ቤታ ተመልሳ ትገባለች አስቸጋሪዋ ዶሮ ግን በፍጥነት ትበላና ከሰውየው ኋላ እየተከተለች ታስቸግረዋለች ...ከዛም ሰውየው በጣም ሲቸገር ለሷሊኋ ዶሮ እዛው ቤቷ ላይ ምግቧን በአንድ…»

Ye Haybaw Mender

05 Dec, 03:43


ሁለት ዶሮዎች የነበሩት ሰዉዬ ነበር አንዷ ዶሮ በጣም ሷሊህ ናት አታስቸግርም አትረብሽም አንዷ ዶሮ ግን በጣም አስቸጋሪ ናት ...ሰውየው ምግብ ሚሰጣቸው በእኩል ሰዐትና እኩል መጠን ነው ፤ ሷሊኋ ዶሮ የተሰጣትን ቀስ ብላ በልታ ወደ ቤታ ተመልሳ ትገባለች አስቸጋሪዋ ዶሮ ግን በፍጥነት ትበላና ከሰውየው ኋላ እየተከተለች ታስቸግረዋለች ...ከዛም ሰውየው በጣም ሲቸገር ለሷሊኋ ዶሮ እዛው ቤቷ ላይ ምግቧን በአንድ እቃ ይሰጣታል እናም ሳትደክም እዛው ባለችበት ትበላለች ለአስቸጋሪዋ ዶሮ ግን መጠኑ እኩል ሆኖ ግቢው ሙሉ ውስጥ ይበትነዉና እሷም እሱም ስትለቅም ትውላለች እሱንም አታስቸግረውም ። አያችሁ ሷሊህ መሆን በእንስሳት እንኳ ያለውን ጥቅም ....

እና የኛንም ርዝቅ እንደሷሊኋ ዶሮ በአንድ ቦታ የተሰበሰበ ፣ ሩቅ ማያስጉዘን፣ ትንሽ ለፍተን ብዙ የምናገኝበት ያድርግልን

መልካም ቀን

Ye Haybaw Mender

03 Dec, 05:25


ዞሮ ዞሮ ሁላችንም ከመሬት በታች ነን !!

Ye Haybaw Mender

27 Nov, 04:44


የሙስሊም ባንኩ ሰደቃው ነው
ለአኼራው ያስቀምጣል

ሸይኽ ሰዒድ ረሂመሁላህ

Ye Haybaw Mender

22 Nov, 03:15


በተዘናጋንበት ሰዐት አላህ እንዳይወስደን እንጠንቀቅ

ዛሬ ጁመዐ ነው በሰለዋት እንበራታ
اللهم صل وسلم عليه سيدنا محمد 💚💚

Ye Haybaw Mender

20 Nov, 03:09


አልሃምዱሊላህ
ስለሁሉም አልሃምዱሊላህ
አላህን ለማመስገን ግዴታ ማስነጠስ አለብን እንዴ??

መልካም ቀን🌸🌸

Ye Haybaw Mender

18 Nov, 20:31


ሩሃችን ደስታን ትፈልጋለች🥰
ደስታ የሚገኘው ደሞ አላህን በመገዛት
ሀላልን በመፈለግ  እና ከሀራም
በመራቅ ነው😍

የመሳሰሉ የሀላል ምክሮች ከፈለጉ👇👇👇

Ye Haybaw Mender

17 Nov, 17:18


አህዋላችን ሲታይ ሞት ያለብን አይመስልም

እስቲ ሞት እንዳለበት ፣ሲራጥ እንዳለበት ፣የቀብር ፊትና እንደሚጠብቀው ሰው እናስብ እስቲ በዚህ መልክ እንንቀሳቀስ ..

መልካም ምሽት

Ye Haybaw Mender

16 Nov, 04:46


አላህን እንደምታየው ሆነህ ተገዛው
አንተ ባታየውም እርሱ ያይሀልና

መልካም ቀን👑👑

Ye Haybaw Mender

15 Nov, 20:34


Ye Haybaw Mender pinned «ሰባህ የየቲሞች ድርጅት በሥሩ አባት አልባ ልጆችን እንዲሁም እናቶቻቸው ለመደገፍ እየሰራ ያለ ጀምአ ነው እናቶቹ የጤና እክል ያለባቸው ዲያሊሲስ ሚያደርግ ጆሮቸው መስማት የተሳንቸው እንዲሁም እራሳቸው ችለው የገቢ ምንጭ ማገኘት ያልቻሉ ቤተሰቦች ናቸው እኛም ከ አላህ ጋ ቆሚ የገቢ ምንጭ ሚያገኙበትን ሥራ አማራጭ ለማስጀመር መንገድ ላይ ነን እናንተም ይሄ ያአላህን ትዛዝ እንዲሁም የነቢን አደራ አንድ ላይ…»

Ye Haybaw Mender

15 Nov, 18:34


ሰባህ የየቲሞች ድርጅት
በሥሩ አባት አልባ ልጆችን እንዲሁም እናቶቻቸው ለመደገፍ እየሰራ ያለ ጀምአ ነው እናቶቹ የጤና እክል ያለባቸው ዲያሊሲስ ሚያደርግ ጆሮቸው መስማት የተሳንቸው እንዲሁም እራሳቸው ችለው የገቢ ምንጭ ማገኘት ያልቻሉ ቤተሰቦች ናቸው እኛም ከ አላህ ጋ ቆሚ የገቢ ምንጭ ሚያገኙበትን ሥራ አማራጭ ለማስጀመር መንገድ ላይ ነን እናንተም ይሄ ያአላህን ትዛዝ እንዲሁም የነቢን አደራ አንድ ላይ በመዋጣት ከሰይዳችን ጋር ጎረቤት ለመሆን ሰበቡን እናድርስ እንላለን
የኛ ሃብት ማለት ኪሳችን ውስጥ ያለው ሳይሆን ትክክለኛው ሃብት በሰው ሀጃ ቆመን ለነገ ያሻገርነው ነው
1000596989504
sebah islamawi dirijit
Screenshot በመላክ ተባበሩን

Ye Haybaw Mender

14 Nov, 16:49


አጠገባችን ማንም ሰው ባልነበረን ጊዜ ሰለዋት ጓደኛችን ነበር🥰🥰

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد

መልካም ኸሚስ

Ye Haybaw Mender

13 Nov, 17:08


لا تعبدوه ليعطي  بل أعبده ليرضي ...
فإذا رضي أدهشكم بعطائه


إمام الشعراوي


"  አሏህን ሊሰጣችሁ ዘንዳ አትገዙት
  ስትገዙት ለፍቅሩ  ብላችሁ ይሁን!
እርሱ አሏህ የወደዳችሁ እንደሆነ  (ያለጥያቄ) በሥጦታው ያንበሻብሻችኋል!

     
   👳‍♂ ኢማም ሙተወሊይ አሻእራዊይ

Ye Haybaw Mender

10 Nov, 17:29


እሱ ስንት ባሪያ ኖሮት ለአፍታ የማይረሳን

እኛ አንድ ጌታ ኖሮን ስንቴ ረሳነው??

😔😔😔

Ye Haybaw Mender

09 Nov, 05:01


ስለቸኮላችሁ አታገኙትም
ስለዘገያችሁ አያመልጣችሁም

ሁሉም የአላህ ፍላጎት እና ውሳኔ ነው..
ስለዚህ አብሽሩ ያ ቀን እስኪደርስ በሰብር ጠብቁ😊😊


መልካም ቀን🦋🦋

Ye Haybaw Mender

08 Nov, 09:21


መልካም ጁመዐ
በሰለዋት በርቱ
اللهم صل وسلم على سيدنا محمد

Ye Haybaw Mender

07 Nov, 17:52


ባይወለዱ ኖሮ ባይመጡ ወደአለም
መሽቶ መምሸት እንጂ መንጋት አይታለም

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد 💚💚

Ye Haybaw Mender

05 Nov, 18:30


በወጣትነታችን እስቲግፋር እናብዛ
ምናልባት እርጅና ላይኖረን ይችላል

መልካም ምሽት 🫠🫠

Ye Haybaw Mender

31 Oct, 17:48


ይሰምራል ሀሳቡ ይሽራል ህመሙ
ያያቸው እንደሆን ነቢን በመናሙ

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد 💚💚

Ye Haybaw Mender

29 Oct, 16:55


ሞኝ ማለት ምንድነው ተብሎ ተጠየቁ:-

{{ሊጠቅምህ እንኳን ቢያስብ ይጎዳሀል ብለው መለሱ}}

መልካም ምሽት 🫠🫠

Ye Haybaw Mender

25 Oct, 17:56


እንደ እጅና አይን ያለ ቁርኝት አይታችሁ ታውቃላችሁ ??

እጅ ሲቆስል አይን ያለቅሳል አይን እንባ ሲያፈስ እጅ ይጠርግለታል ...
እንደዚህ አይነት ሷሂብ ብናገኝ አስቡት

መልካም ምሽት 🫠🫠

Ye Haybaw Mender

20 Oct, 10:17


እንደው በጣም ብንጨናነቅ ምንም እንኳን ሰዐት ብናጣ ሶስት ጊዜ ሱረቱል ኢኽላስን (ቁል ሁወላሁ አሀድ) የመቅራት ጊዝ ያጥረናል ??


ሶስት ጊዜ መቅራት ቁርዐን እንደማክተም ነው እና ይህን ሳናደርስ ማደር ጅልነት አይደለምን ??

ከዛሬ ጀምሮ እንጀምራለን ኢንሻአላህ

Ye Haybaw Mender

19 Oct, 17:51


5 ቀናቶች ብቻ ቀርተውታል!
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
👇👇
@darul_hijreteyni
@darul_hijreteyni

Ye Haybaw Mender

17 Oct, 18:27


በሰለዋት ጠንክሩ
اللهم صل وسلم على سيدنا محمد 💚💚

Ye Haybaw Mender

16 Oct, 18:37


አኼራ እንደ ዱኒያ አይደለም ...መላዒካዎች የአላህን ትዕዛዝ ለመፈፀም አያመነቱም አንድ ሀሰና አጥተን ጀሀነም ልንገባ እንችላለን ያኔ ጉቦ ከፍለን ጀነት ልንገባ ግን አንችልም ..ስለዚህ ኸይር ስራ በመስራት ላይ እንበራታ የኸይር ስራ ትንሽ የለውም ፤ የመጥፎ ስራም እንደዛው ....

Ye Haybaw Mender

15 Oct, 19:01


{ በዚህ ዘመን ይህን ኡመት የሚያስፈልገው መሰባሰብ ሳይሆን መግባባት ነው! የመግባቢያው ሂደት ደግሞ ቀደምት ሶሓበቶች በተግባቡበት መንገድ ነው። ሶሀበቶች የተግባቡት ደግሞ ሁላቸውም የግል ፍላጎታቸውን በመተው ለአላህና ለሰይዳችንﷺ ፍላጎትና እና ትዕዛዝ <<ሰሚዕና ወዓጣዕና>> በማለት ተገዢ በመሆን ነበር ...

"ከአላህ እና ሰዪዳችን ፍላጎት እና ትእዛዝ ውስጥ ደግሞ ዋነኛው ዳእዋ ማድረግ እና ኢጅቲማእ ናቸው" 

      ይሄንን ፍላጎት እና ትእዛዝ ለመፈፀም ከጥቅምት 14/17 ድረስ በቡታጅራ ከተማ ኢጅቲማእ አድርገን ደዓዋ ለማድረግ እንዘጋጅ 🙌

  መውላና ሸይኽ ኢንዓሙል ሐሰን (ራህመቱላሂ ዓለይህ)❤️

Ye Haybaw Mender

13 Oct, 04:45


በቀደር ላይ ምንም ስህተት የለም
ስለዚህ አትጨነቁ🤗🤗

Ye Haybaw Mender

11 Oct, 07:20


اللهم صل وسلم على سيدنا محمد 💚💚

ዱዐቹ ተቀባይነት የሚያገኝበት ፣
ከጭንቀታችሁ ነጃ የምትወጡበት ፣
ፏ ያለ ጁመዐ ይሁንላችሁ

Ye Haybaw Mender

09 Oct, 11:03


🎁ያያችሁት ሁሉ ለሌላው ሼር አድርጉት እስቲ እናጥለቅልቀው ፕሮፋይል እናድርገው ።😊 #ሀበሻ_ኢጅቲማዕ🥰

Ye Haybaw Mender

07 Oct, 16:29


ሰውነትህን ዒባዳ ለመፈፀም ሲከብደውና (ለአሏህ)ትዕዛዝ ሲሰላች ካየከው እወቅ ማያገባክ (ማላየዕኒ)ውስጥ ገብተክ ነበር ማለት ነው።

Ye Haybaw Mender

04 Oct, 05:27


አስቡት በዛ በጭንቁ ቀን ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፈገግ ብለው የምታወርዱት ሰለዋት እኮ ይደርሰኝ ነበር ሲሉ.....

እንግዲህ በሰለዋት ጠንክሩ ይህን ለመባልም ያብቃን


ጁመዐ ሙባረክ 🥰🥰

Ye Haybaw Mender

02 Oct, 16:20


ሁልጊዜ የማይለይህ ..ቤትህም እያለህ ,ጉዞ ላይም ስትሆን ,ስትተኛም ስትነቃም ,ስታገኝም ስታጣም ,ስትደሰትም ስታዝንም ...አላህ እንጂ ማንም አይደለም ያ አላህ እኮ አኗኗሪህ ነው...ልክ እንዳለው {{انا جليس من ذكرني }}

አላህን ካወቁት ሰዎች ያድርገን

Ye Haybaw Mender

27 Sep, 06:56


በሰለዋት የደመቀ ጁመዐ ይሁንላችሁ 🍀🍀

Ye Haybaw Mender

23 Sep, 17:28


ስለራስህ አትናገር
ስራህ ይናገርልህ

ሸይኽ አዲል ....

Ye Haybaw Mender

19 Sep, 17:22


በሰለዋት በርቱ

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد 🥰🥰

ፏ ያለ ኸሚስ ይሁንላችሁ

Ye Haybaw Mender

15 Sep, 02:53


ከዉኑ ተንተግትጎ በኑር ሲጥበረበር፤
አሚነት ስታምጥ ተስኗት መሶበር፤
አላህ ማዝለቅ ቢሻ የሹኡኑን ኸበር፤
ሰኞ ወለደችዉ አብርቶ እንደጀንበር፤

السلام عليك يا نبي الله
السلام عليك يا حبيب الله
السلام عليك يا أمين الله
السلام عليك يا صفوة الله
السلام عليك يا خيرة الله
السلام عليك يا شفيع المذنبين
السلام عليك يا إمام المتقين
السلام عليك يا سيدي محمد
السلام عليك يا سيدي أحمد
السلام عليك يا سيدي محمود
السلام عليك يا أبا القاسم
السلام عليك يا بشير السلام
السلام عليك يا نذير السلام
السلام عليك يا شاهد السلام
السلام عليك يا طاهر
السلام عليك يا ماحي
السلام عليك يا سيد المرسلين
السلام عليك يا أشرف خلق الله
السلام عليك يا خاتم النبيين
السلام عليك يا قائد الغر المحجلين
السلام عليك يا رسول رب العالمين
السلام عليك يا أفضل رسل الله
السلام عليك وعلى أصحابك أجمعين
السلام عليك وعلى أهل بيتك الذين أذهب الله عنهم الرجس وطهرهم تطهيراً
السلام عليك وعلى سائر الأنبياء والمرسلين وعلى عباد الله الصالحين
السلام عليك وعلى أزواجك الطـاهرات أمهـات المؤمنين
وجزاك الله عنا يا سيدي يا رسول الله أفضل ما جزي الله نبيا عن قـومه ورسولا عـن أمته وأشهـد أنك يا سيدي يا رسول الله قـد بلغت الرسـالة وأديت الأمـانة ونصحـت الأمـة وأوضحت الحجة وجاهدت في الله حق جهـاده وعبدت ربك حتى أتـاك اليقـين
وصـلى الله عليك كلما ذكرك الـذاكرون وكلمـا غفـل عـن ذكـرك الـغافلون .

#مرحباً_ربيع_النور
#صلوا_عليه_وسلموا_تسليماً
#صدقة_جارية
#مدد
#المولد_النبوي_الشريف

Ye Haybaw Mender

14 Sep, 19:37


( መርሀበን ረሡሉላህ )


#ربيع الأنوا ر

Ye Haybaw Mender

13 Sep, 04:00


ኢማመል ገዛሊ ቢዳየቱል ሂዳያ በተሰኘው ኪታባቸው ላይ ስለ ጀመዐ አዳብ ሲናገሩ :-
<<አንድ አማኝ ጁመዐን ከሰገደ በኋላ ከማንም ጋር ንግግር ከማድረጉ በፊት :-ሰባት ጊዜ ሱረቱል ፋቲሀን ሰባት ጊዜ ሱረቱል ኢህላስን ሰባት ሰባት ጊዜ ሙዐዊዘተይንን ይቅራ ይህን ማድረጉ ከሸይጣን ተንኮሎች መጠበቂያ ይሆኑለታል ።


መልካም ጁመዐ🌸🌸

Ye Haybaw Mender

10 Sep, 17:43


ትክክለኛ እውቀት ብሎ ማለት :-

1 የአላህን ፍቅር የሚጨምርልህ
2 የሸይጣን ተንኮሎችን የሚያሳውቅህ
3 የአላህን ፍራቻ የሚጨምርልህ
4 የሌላ ሙስሊምን ጥላቻ የማያሳድርብህ ነው።

Ye Haybaw Mender

06 Sep, 03:34


ጁመዐ+ረቢዕ 💚💚

ይህን ወር ከሌላው ወር ለየት አድርገን ሰለዋት በማለት እንበራታ የማይረቡ ወሬዎችን በማውራት እንዳያልፍብን ....በዚህ ወር ነበር የኛ ትልቅ ነቢይ የኛ አለኝታ የኛ ተፈቃሪ ነቢይ ወደዚች ዓለም ብቅ ያሉት ለዛም እኛም ደስታችንን እሳቸው ላይ ሰለዋት በማውረድ ኸይር ስራ በመስራት እንግለጽ ....

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد

Ye Haybaw Mender

03 Sep, 03:21


አላህ አላህ በል
ከአፍህ አላህ የሚለው ቃል አይጥፋ

4,173

subscribers

119

photos

2

videos