ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ @ethioterkaa Channel on Telegram

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

@ethioterkaa


@ethioterkaa

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ (Amharic)

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ የቴሌግራም ክፍል ነው የተባለው። እርስዎ እስከ ሠንጋይ ምርጥ መፅሀፍት እና ትረካዎን በነፃ ይጠቀሙ። በትምህርት ቤት የሚፈላገለውን ብሄራዊ እና መረጃዎትን ለመረጃ ገጽ ላይ ሊለዩ ነው። ኢትዮጵያ በስብሰባችን በመልኩ ከምርጫ እኩል ወደ ምስራቅ እና የተነገረበት ከተማ ይወጣል። የወጣቶች በሙሉ የቴሌግራሙን በጣም ለመቀነስ ከስልክዎ ላይ በማንበብ በመላው እና የእንስሳቱን ለውጥ ያስተምሩ። ከሀገራችን በስብሰባችን በመተው ማህበረሰብና መምህር ዜናችንን ለመጠቀም የሚጠብቁትን አዳዲስ ቃልን እና መረጃዎትን ለመረጃ ወደ ባትዊ ገጽ በመምጣቱ እና በመረብ ቻናሲ ይከፈሉ።

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

14 Nov, 17:23


Live stream finished (24 days)

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

10 Nov, 18:08


#በአንበሳ የሚመሩ በጎች በበግ የሚመሩ አንበሰችን ያሸንፏቸዋል

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

23 Oct, 13:18


https://t.me/major/start?startapp=953703726

እንዳያመልጣቹ

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

23 Oct, 07:59


ይቅርታ
ሳይገባችሁ ውድ ልቤን ለሰጠዃችሁ
ይቅርታ
ስለኔ ግድ ሳይሰጣችሁ ውድ ጊዜየን ለሰዋሁላችሁ
ይቅርታ
ንፁህ የፍሴን በበደል እንድታቆሽሿት ለፈቀድኩላችሀ
ይቅርታ
የማይገባችሁን ቦታ ሰጥቸ ለተጨነቅኩላችሁ
ይቅርታ
ልቤን እንድትሰብሩ ለፈቀድኩላችሁ
ይቅርታ
አጉል ደግ ለሆንኩላችሁ
ይቅርታ
አሁንም ላልተቀየምኩዋችሁ
ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ ምክንያቱም እኔ እንዲ ነኝ
@ethioterkaa

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

23 Oct, 07:36


የቡርኪናፋሶዋ ገበሬ

ይህች ልጅ ስዋሚድዋ ሀቢዳዲ ትባላለች ሀገሯ የቶማስ ሳንካራዋ ቡርኪናፋሶ 🇧🇫🇧🇫

ገበሬ ነች ። ወላጆቿ ከሞቱ በኋላ በ16 ዓመቷ ግብርና ጀመረች።

ከትምህርት ይልቅ እርሻን መረጠች ፤ ከቤተሰቧ በውርስ ያገኘችውን 6 ሄክታር መሬት ''አሸሼ ገዳሜ ብላ አላጠፋችውም ''። 6 ሄክታር መሬቷን ለተለያዩ አዝርዕት እና ፍራፍሬ ከፋፍላ አሳረሰች ። ሩዝ፣ በቆሎ፣ ባቄላ፣ አኩሪ አተር እና ፍራፍሬ እና ሌሎችንም ዘራች ።

ከወላጆቿ የተረከበችውን 6 ሄክታር መሬት ለእርሻ ብቻ አዋለችው ። መሬቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ዋና የገቢ ምንጭዋ ሆነ ።

ስዋሚድዋ በዚህ አመት 10,000 ከረጢት በቆሎ፣ 8,000 ከረጢት ሩዝ እና 5,000 ከረጢት የተፈጨ ለውዝ ሰበሰበች።

ከ900 በላይ ከብቶች፣ 500 ፍየሎች አልዋት ። 20 ወንድ እና 20 ሴቶች ቀጥራ ታሰራለች ። በቀላሉ ለማልማት የሚያስችል ትራክተርም አላት።

ከጋዜጠኛው ጋር ቆም ብላ ስታወራ Vx hilux መኪናዋን ተደግፋ ነው ። ከዚህ ተሽከርካሪ ሌላ እንደ 4 BMW፣ 2 Mercedes Benz wagon እና 3 range Rover መኪኖች አሏት። ለእያንዳንዱ ሰራተኛ 40 ሞተር ሳይክል ገዝታለች ።

በአሁኑ ጊዜ በአካባቢዋ የበጎ አድራጎት በስፋት ትሳተፋለች ። መብራት ቧንቧ ውሃ ለአካባቢዋ አስገብታለች ። ለበርካቶች እንጀራ እንዲወጣላቸው ምክንያት ሆናለች ።

@ethioterkaa
@ethioterkaa

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

22 Oct, 19:18


መልካም ምሽት
ሰላም በምድራችን ይስፈን
@ethioterkaa
@ethioterkaa
@ethioterkaa

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

22 Oct, 16:16


#አይ_መርካቶ 😥😥

አገር ከየጎራው ወጥቶ
አንቺን ብሎ ነቅሎ መጥቶ
ግሳንግሱን ጓዙን ሞልቶ
ኁልቁ መሳፍርትሽ ፈልቶ
ባንቺ ባዝኖ ተከራትቶ
እንደባዘቶ ተባዝቶ
ተንጠራውዞ ዋትቶ ዋትቶ
አይ መርካቶ

የምድር አለም የእንጀራ እናት
ላንዱ ርካሽ ለሌላው እሳት
ላንዱ ፍትሃት ላንድ ምትሃት
ላንዱ ሲሳይ ላንድ ፍርሃት
ላንዱ ተስፋ ላንድ ስጋት
የግርግር የሆይታ ቋት

አይ መርካቶ

ያንዱን ወስዶ ላንዱ ሰጥቶ
ያንዱን ገፋፎ ላንዱ አብልቶ
አንዱን ነስቶ ላንዱ አድልቶ
ስንቱን ፈርቶ ስንቱን ሸሽቶ
ባፈ ጮሌ ተሸልቶ

ፀጋዬ ገብረ መድህን

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

22 Oct, 09:45


በማሌዥያ የአልጋ ቁራኛ የሆነውን ባለቤቷን ለስድስት ዓመታት ስታስታምም የነበረችው ግለሰብ ከበሽታው ካገገመ በኋላ ሌላ ትዳር መሰረተ

በደረሰባት የተሽከርካሪ አደጋ ለስድስት አመታት የአልጋ ቁራኛ የሆነውን ባሏን የተንከባከበችው ማሌዥያዊት ሴት ባሏ ከበሽታው ካገገመ በኃላ ሌላ ሴት ማግባቷን በቅርቡ አስታውቃለች።

ለዓመታት ኑሩል ስያዝዋኒ የዕለት ተዕለት ህይወቷ የባለቤቷ ጠባቂ በመሆን የምታሳልፈውን ጊዜ በማህበራዊ ድህረ-ገፆች ላይ በማሳየት ስራ የበዛበት ተግባሯን አጋርተች። ይህም ባለቤቷ ምግብ በእጁ ጎርሶ ስለማይወርድለት በናሶጋስቲክ ቱቦ መመገብ፣ ዳይፐር መቀየር እና እንዲታጠብ መርዳት የእርሷ የእለት ከእለት ስራ ነበር። የኑሩል ባል የመኪና አደጋ ከደረሰበት በኃላ እንደገና ለመራመድ ስድስት አመታት መጠበቅ የግድ ብሎት የነበረ ሲሆን በነዚህ ዓመታት ሁሉ ግን እሷ ከጎኑ ነበረች።

ለባሏ ያሳየችው ትጋት እና ታታሪ አገልግሎት በፌስቡክ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን ብዙዎቹ የኑሩል ሲያዝዋኒ ባል ካገገመ በኋላ ፈትቷታል፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ሌላ ሴት ማግባቱን ሲሰሙ ደንግጠዋል። የእብደት ድርጊት ሲሉ በርካቶች የተደመጡ ሲሆን ኑሩል በፌስቡክ ገጿ የቀድሞ ባለቤቷን እና አዲሲቷን ሙሽሪት እንኳን ደስ አላችሁ ብላለች።ለባለቤቴ እንኳን ደስ አለህ ፤ በመረጥከው ህይወት ደስተኛ እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ። አዲሲቱ ሚስቱ አይፋ አይዛም እባካሽ ልክ እንደ እኔ ተንከባከቢው ፤አሁን ተራው የአንቺ ነው ስትል ኑሩል መልዕክቷን አጋርታለች። በጥቅምት 4 መጠናቀቁ የተነገረለት የኑሩል የፍቺ ዜና የማሌዢያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ማስደንገጡን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።

በርካታ ተጠቃሚዎች ደግነቷን ሊከፍላት ይችላል የሚለውን አባባል መቀበል አቅቷቸዋል። በህመሙ ወቅት ከባድ ጊዜን አሳልፌያለሁ በየቀኑ እንዲያገግም እረዳው ነበር፣ ቤተሰቦቼ በየቀኑ ሊረዱኝ ይመጡ ነበር፣ ለልጆቼና ለባለቤቴ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ብቻዬን ሳሟላ ቆይቻለሁ ስትል ተደምጣለች።ሆኖም ኑሩል የቀድሞ ባለቤቷ “ኃላፊነቱን በሚገባ እንደተወጣ” እንደሚሰማት ጠቁማ ሰዎች እሱን እና አዲሷን ሚስቱን ማስጨነቅ እንዲያቆሙ ጠይቃለች ። ሆኖም ደጋፊዎቿ በሀሳቧ አልተስማሙም። አንድ ሰው በሰነዘረው አስተያየት “እንዴት እንዲህ ያለው ምስጋና አልባ ሰው ሊኖር ይችላል? ልብ ያለው አይመስለኝም ሲል መደመጡን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

የቀድሞ ባሏን እና አዲሲቱን ሚስቱን ከብዙሃኑ ትችት ለማዳን ስትል ኑሩል ሲያዝዋኒ በፌስቡክ ላይ የደረሰባትን ያሰፈረችውን ፅሁፏን በማጥፋት ሰዎች ለተፈጠረው ነገር የቀድሞ ባሏን መወንጀል እንዲያቆሙ ደጋፊዎቿን ጠይቃለች።የቀድሞ ባለቤቴን፣ አዲሲቱን ሚስቱን እና ቤተሰቦቻቸውን በፌስ ቡክ ላይ ባጋራሁት መልዕከት ለደረሰባቸው ትችት ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ። የሆነው ሁሉ የእኔ ስህተት ነበር ሲል ኑሩል ጽፋለች።

በስምኦን ደረጄ
ዳጉ ጆርናል

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

21 Oct, 17:08


ቤት ስትገባ እናቴ ብለህ ተጣርተህ ምላሽ ከማግኘትህ በላይ እድለኛ ልትሆን አትችልም

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

20 Oct, 19:28


Live stream started

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

20 Oct, 20:00


Live stream scheduled for

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

20 Oct, 11:39


Live stream started

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

20 Oct, 11:38


የፍሪዳ ካህሎ ስም ደማቅ ምስል ይገለጣል፡ ደማቅ ቀለሞች፣ የሚዋጋ እይታ፣ በኃይለኛ ጥንካሬ የሚቃጠል መንፈስ። ህይወቷ በህመም፣ በስሜታዊነት እና እውነቷን ለመግለጽ በፅኑ ቁርጠኝነት የተሸመነ ካባ ነበር! ይህ እውነት ከሸራዋ ባሻገር በብዙዎች ዘንድ ያስተጋባ እውነት ነው።

በ1907 በሜክሲኮ ሲቲ የተወለደችው የፍሪዳ ሕይወት እንደማንኛውም ሰው ነበር። መንፈሷ፣ ለ ስዕሎቿ እንደተጠቀመችባቸው ቀለማት ደመቅ ያለ፣ በውበትም በችግርም በተሰየመ ግርግር ውስጥ የልጅነት ጊዜዋ ተቀርጾ ነበር። ባህሏ፣ ጥበቧን እና የበለጸገ ታሪኳን በመቀበል በሜክሲኮ ባሕል በደመቀ ዓለም ውስጥ ፈካች። ነገር ግን በዚህ ደማቅ ዳራ ውስጥ እንኳን የፍሪዳ ህይወት በአሳዛኝ ሁኔታ ተነካ።

ገና በ18 ዓመቷ አሰቃቂ የሆነ የአውቶብስ አደጋ ሰውነቷን እና መንፈሷን ሰባበረው። ውጤቱም በቀሪው ሕይወቷ የሚሰቃያትን ሥር የሰደደ ሕመምን ይዞባት መጣ። አልጋ ላይ እንደተኛች ሰውነቷ ተሰባብሮ አእምሮዋ በአሰቃቂ ህመም ሲሞላ የጥበብ መንፈሷ ተቀጣጠለ። ፍሪዳ ሰውነቷን በካስት ውስጥ በመሳል ሥዕሏን ሥቃዩን ለመቋቋም፣የራሷን ስሜት ጥልቀት ለመፈተሽ እና በዙሪያዋ ስላለው ዓለም ግንዛቤ ለመፍጠር እንደ መንገድ በመጠቀም ሸራዋን ማቅለም ጀመረች።

የፍሪዳ የራስ-ገፅ ስዕሎቿ ፊርማዋ ሆኑ። በእያንዳንዷ የነፍሷ መስኮት ውስጥ በፍጹም ሐቀኝነት እና በማይለዋወጥ ፅናት ብቅ አለች። ትግሏን፣ ህመሟን፣ ጽናቷን፣ እና እምቢተኝነቷን በቀለሞቿ ውስጥ አሳየች። ጥበቧን የህብረተሰቡን ፍላጎቶች ለመቃወም፣ ጠንካራ የሴትነት ሀሳቦቿን ለመግለጽ እና የሰውን መንፈስ ሀይል ለማጠንከር ተጠቅማለች።

እሷ አንድ ሰዓሊ ብቻ አልነበረችም; እሷ ሹም ሽር የሌለበት የተፈጥሮ ኃይል ነበረች። መንፈሷ በጣም እንደምትወዳት የሜክሲኮ መልክዓ ምድሮች የማይበገር ነበር። ህይወቷ፣ ማዕበል የተሞላበት ጉዞ፣ በስሜታዊነት፣ በልብ ስብራት እና በማያወላውል ራስን የመግለጽ ፍላጎት ተሞልቷል። ፍቅርን አገኘች፣ፍቅርን አጣች እና ህይወትን በኪነጥበብዋ ደምቆ በሚያቃጥል አስፈሪ ጥንካሬ ተቀበልች።

የፍሪዳ ካህሎ ሕይወት መከራን የመቋቋም ኃይል እና በሥነ ጥበብ እና በፈውስ መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት የሚያሳይ ነበር። ሊታሰብ በማይቻል ህመም ውስጥ እንኳን የሰው መንፈስ ውበትን ለመፍጠር ፣እውነትን የሚገልጽ እና የማይጠፋ አሻራ በአለም ላይ የሚጥልበትን መንገድ እንደሚያገኝ አሳይታናለች።

የእሷ ታሪክ በጣም በጨለማ ጊዜ ውስጥ እንኳን ሁልጊዜ የፈጠራ ብልጭታ፣ በእያንዳንዳችን ውስጥ የጥንካሬ ምንጭ እንዳለ ያስታውሳል። ፍሪዳ ካህሎ ከአመድ ላይ እንደምትነሳ ፊኒክስ፣ ህመሟን ወደ ጥበብ፣ አቅም ማጣቷን ወደ ድምፅ፣ ህይወቷን ወደ ድንቅ ስራ ቀይራለች።

ከእንግዲህ መከራን እየተጋፈጣችሁ እንደሆነ ስታስቡ ፍሪዳን አስታውሱ። ልብ በሉ በህመም መካከል እንኳን; ውበት አለ፣ ጥንካሬ አለ፣ እና ሁልጊዜ አንድ የሚነገር ታሪክ አለ።

✍️ዮናታን በጋሻው (ቀዳማዊ)

#መታሰቢያነቱ: ህይወት ለደቆሰቻቸው ሁሉ ይሁንልኝ። እይዞኝ!

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

20 Oct, 08:48


Live stream finished (4 minutes)

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

20 Oct, 08:44


Live stream started

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

19 Oct, 16:43


_ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ_

ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተገልሎ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ-ሰው ተደብቆ
መሽቶ፥ የማታ ማታ ነው፥ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው፡፡ . . .
ብቻውን ነው የሚረታው፡፡ . . .
ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ተማምጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ . . .
መሽቶ፥ ረፍዶ፥ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ፥ በዝምታ ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር . . .

የኋላ የኋላ፥ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
ዓይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ ዓይኑ የሚረጥብ
የብቻ፥ እንባ ወዙ እሚነጥብ፡፡
ብቻውን ነው፥ ብቻውን ነው . . .

የእንባ ጭለማ ለብሶ ነው
ወንድ ልጅ ወዙ እሚነጥበው፡፡
ዕጣውን ለብቻው ቆርሶ
ብቻውን ሰቀቀን ጐርሶ
ብቻውን ጭለማ ለብሶ
ገበናውን ሣግ ሸፍኖ
ክብሩን በሰቆቃ አፍኖ
ሌሊት፥ የማታ ማታ ነው
ሕቅ እንቁን እሚነጥበው
ኤሎሄውን እሚረግፈው . . .
ከዓይኑ ብሌን ጣር ተመጦ
ከአንጀቱ ሲቃ ተቆርጦ
ደም አልሞ ፍም አምጦ
ከአፅመ-ወዙ እቶን ተፈልጦ
ከአንጀቱ ሲቃ ቆርጦ
ደም አልሞ ፍም አምጦ
ከአፅሙ ወዙ እቶን ተፈልጦ
እንደጠፍር-ብራቅ እምብርት
እንደእሳተ ገሞራ ግት
‘ርቅ ነው ወንድ ልጅ እንባው
ደም ነው፥ ፍም ነው እሚያነባው፤
ንጥረ ሕዋስ ነው ሰቆቃው
ረቂቅ ነው ምሥጢር ነው ጣሩ፥__ብቻውን ነው የሚፈታው፥
ብቻውን ነው የሚረታው፡፡

ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ሰቀቀኑን በሆዱ አጥሮ
በአንጀቱ ገበና ቀብሮ
ውሎ ጭጭ እፍን ብሎ፥ እንደደመና ተቋጥሮ
ጣሩን ውጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተሰትሮ፥ . . .
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
ከቤተ-ሰው ተደብቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ፥
ተሸሽጎ ተከናንቦ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ . . .
የብቻ ብቸኝነቱ፥ የጭለማ ልብሱ እስኪደርስ
በዓይን አዋጅ ሃሞቱ እንዳይረክስ
ቅስሙ በገበያ እንዳይፈስ
ተገልሎ በእኩለ-ሌት፥ ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ፡፡

_ ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
ርዕስ - እሳት ወይ አበባ
(፲፱፻፶፭ - አምቦ - ኮልፌ)

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

19 Oct, 11:19


~ይፈለጣል ፈላጭ በተፈላጭ ~

በእንጨት ተፈልጦ
መጥረቢያ ያነባል ፤
እዬዬ ..... ያሰማል፤

ለቅሶውን ሰምቶ እጅጉን ያዘነው
አንድ ቁራጭ ብረት ዝገት ያበለዘው
..." ምን ብርቱ ገጥሞህ ነው
እንዲህ ምታለቅሰው? " ሲለዉ

ህቅ ስቅ እያለ አይኑን እያበሰ
.....እንዲህ ሲል መለሰ :-
"እንቁላል ላይ ድንጋይ እንደሚፈጠፈጥ፣
እንደሚፈርስ ዐለት ፣ ሲፈነከት በጥጥ ፤
ያለ ጉድ ገጠመኝ ፣ ላልቅስበት ተወኝ፣
እምፈልጠው ፍልጥ ፣ መልሶ ፈለጠኝ!
ወይኔ.. ምሳር .. እኔ
ብርቱ የነበርኩ ..ያኔ
ምፈልጥ ፥ ማልፈለጥ ፤
ብረት ፥ የብረት ልጥ ፤
በእንጨት ስፈለጥ!
እንዴት እኔ አላልቅስ
አዬ . .. አዬ. ..አዬ!
~ተወኝ ተወኝ ላልቅስ !

አዬ ... አዬ ... አዬ ፤ "

ቁራጭ የማይጠቅም ፣
ያበለዘው ዝገት ፥
አፈር የሚቅመው ፣ ያ -የተጣለ ብረት
ቀና ብሎ አይቶት፣ ስሩ ካለው መሬት
" ወዳጄ አይዞህ ... " አለ
አንጋጦ እንዲህ ሲል ቀጠለ፤
"የኔ ከዚህ ይከፋል ፤
ያንተን ጉድ ያስንቃል፤
ባወጋህ ብትሰማኝ ፣ ትጽናና ይሆናል።
ከእንጨት ይበረታል ፣
ዉኃ ብርቱ ይፈልጣል ፣ ቢባል ማንስ ያምናል፤
እኔ ምስክር ነኝ ፣
ምን ይገርማል የእንጨት ፣ ዉኃም ቆርጧል ብረት ።
ውሃ ቆርጦኝ ስጣል ፣
እንጨት ፈልጦህ ይዞሃል፤
አንተ ታድለሃል ፤
ተጥለህ ለመኖር ብዙ ቀርቶልሃል ።
ይቀጠቅጡሃል ፤
ምሳርነት በቅቶ ምላጭ ያደርጉሃል ፤
ተ-ጠ -ቅ-መ-ው-ብ-ህ ከዛ ይጥሉሃል።

አትዘን ወዳጄ ባይቀርልህ መጣል ፤
ሚበላህ ዝገት ነው ገፋ ቢል ፤
አፈር ብትቅም ነው ከፋም ሲል ፤
ሀሩር ብርዱ እንደሆን ፣ 'ያደር ይለመዳል፤
ይሄው ነው አትዘን ፣ ምን ያስለቅስሃል።
ምሳር ተመከረኝ
አስተውለህ ስማኝ ፤
አንተ ስትፈልጠው ሲወድቅልህ ከርሞ፣
መልሶህ ፈለጠህ ፣ ዛሬ ሳይወድቅ ቆሞ።
ሊፈለጥ ከስርህ
ነው እንጂ ቢጋደም ፣
ያንተ ስትፈልጥ መክረም ፣ በብርታትህ አልነበረም ።
እና ወዳጄ፥
በወደቀልህ ...አትውደቅ ~ ከፍ ያደረገህን አትናቅ
ፈርቶ የሸሸን...አታሳድ ~ ያከበረህን አታዋርድ። "
~ 153

1,436

subscribers

154

photos

1

videos