̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥ @kedibntebrahim Channel on Telegram

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

@kedibntebrahim


وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? https://t.me/joinchat/AAAAAERWlA0-JcdyhgSXoQ

መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) (Amharic)

መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) የእናቴን ህጻን መኖ ማየትን ለማድረግ ለሚያስችል እና ለሚለያይ ጥቅም እንዲሁም የሚመከራበት የሙያችንን ስጋ ለማድረግ በማሳያ ያስፈልገናል። ስንዴን መሆኑ ቢሆንም ከተለዋዋጭ ምልክቶች ሽልሞቻልና፣ ፈጥና በሉ አሳልፎ እንዲሰለፍ እናገልጻለን። ከእነዚህ እስከ አላህ አረንጓዴ ድምፅ ማንኛውም የሚደርስ የእኔ ቅዱስ መንፈሳዊ ንቅናቄ ነው። እናንተ ወደ አላህ ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም አማርኛ ወላለብን ከሆኑ ሰራነቶች። ሌሎቹ ትምህርቶችን መለየት ማቅረብ እና የስልካችንን ብርሃነቱ ከበሻና ማስገኝ በጣም ወንድምም እና ሴታችን ከበሻ ትማግበ እያሉ ነን። ስለዚህ አገልግሎትን በመንፈሳዊ ፍቅሩን የመስራቱን ህብረተሰብና ሥርዓተ መኖራዎቹ ለመስተር እና ለመጥፋት እንጠቀማለን።

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

25 Feb, 13:03


ማስታወሻ
========
    ለረመዿን ወር የቀረው ጊዜ አጭር በመሆኑ ካለፈው የረመዿን ወር በተለያዪ ምክንያቶች ቀዿ ያለብንን ቀን ያልፆምን ወይም ጀምረን ያልጨረስን ሰዎች ካለን የቀሩትን ጊዜያቶች ተጠቅመን ቀዿችንን ልናወጣ ይገባል።

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

22 Jan, 09:18


https://t.me/Xaaliburidallah

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

07 Nov, 08:46


•════•••🌺🍃•••════•
የተከበረው ቅዱስ የአላህ ቃል ሰላሳ ጁዝ ቁርዓን በተለያየ ቃሪዎች!!!

📚 የምትፈልጉት የቁርዓን ቃሪዓ ሼህ ስም በመጫን ሰላሳ ጁዝ ቁርዓን ማውረድ ትችላላቹ በቀላሉ ቦታውን ለማግኘት የምትፈልጉትን ቃሪዕ ብቻ ተጫኑ!!

🌴1 - ሼህ መሀመድ አዩብ
ሀፍስ አን አሲም

🌴2 - ሼህ ፋሪስ አባድ
ሀፍስ አን አሲም

🌴3 - ሼህ አህመድ አልአጀሚይ
ሀፍስ አን አሲም

🌴4 - ሼህ ሰአደል ጋሚዲን
ሀፍስ አን አሲም

🌴5 - ሼኽ አብደሏህ ካሚል
ሀፍስ አን አሲም

🌴6 - ሼህ ሀኒ አልራፊኢይ
ሀፍስ አን አሲም

🌴7 - ሼህ ሙሃመድ አልሙሃይሲኒ
ሀፍስ አን አሲም

🌴8 - ሼህ ማሂር አልሙአይቂሊ
ሀፍስ አን አሲም

🌴9 - ሼህ አብዱራህማን አልሱዲየስ
ሀፍስ አን አሲም

🌴10 - ሼህ ያሲር አዱሰሪ
ሀፍስ አን አሲም


🌴11 - ሼህ ሚንሻሪ አልአፋሲ
ሀፍስ አን አሲም

🌴12 - ሼህ አብዱልወዱድ ሀኒፍ
ሀፍስ አን አሲም

🌴13 - ሼህ ኻሊድ አልጀሊሊ
ሀፍስ አን አሲም

🌴14 - ሼይህ ሙሃመድ አልሚንሻዊ
ማስተማሪያ ከህፃን ጋር
ሀፍስ አን አሲም

🌴15 - ሼህ ሙሃመድ አልሚንሻዊ
ሀፍስ አን አሲም ሙረተል

🌴16 -ሼህ ማህሙድ አልሀስሪይ
ሀፍስ አን አሲም ሙረተል

🌴17 - ሼህ አብዱልባሲጥ አብዱሰመድ
ሀፍስ አን አሲም ሙጀዊድ

🌴18 - ሼህ ወዲዕ አልየመኒ
ሀፍስ አን አሲም

🌴19 - ሼህ ማህሙድ አልበና
ሀፍስ አን አሲም ሙጀዊድ


🌴20 - ሼህ ሙሃመድ አልልሂዳን
ሀፍስ አን አሲም

🌴21 - ሼህ አይመን ሰኡዲይ
ማስተማሪ
ሀፍስ አን አሲም


🌴22 - ሼህ ኢድሪስ አብከር
ሀፍስ አን አሲም


🌴23 - ሼህ አብዱራህማን አልአውሲ
ሀፍስ አን አሲም

🌴24 - ሼህ አብዱልዚዝ አልዘህራኒ
ሀፍስ አን አሲም

🌴25 - ሼህ ሙሃመድ ጅብሪል
ሀፍስ አን አሲም


🌴26 - ሼህ ሙሃመድ አልሚንሻዊ
ሀፍስ አን አሲም ሙጀዊድ


🌴27 - ሼህ አቡበከር አሻጢሪይ
ሀፍስ አን አሲም

🌴28 - ኻሊድ አልቀህጣሚ
ሀፍስ አን አሲም

🌴29 - ሼህ ስኡድ ሹረይም
ሀፍስ አን አሲም

🌴30 - ሼህ ሙሃመድ አጠብላዊ
ሀፍስ አን አሲም ሙጀዊድ


🌴31 - ሼህ ሰላህ አቡኻጥር
ሀፍስ አን አሲም


🌴32 - ሼህ አብደሏህ በስፈር
ሀፍስ አን አሲም


🌴33 - ሼህ አብዱል አዚዝ አልአህመድ
ሀፍስ አን አሲም


🌴34 - ሼህ ናሲር አልቃጣሚ
ሀፍስ አን አሲም


🌴35 - ሼህ ቢንደር በሊሊህ
ሀፍስ አን አሲም


🌴36 - ሼህ ኢብራሂም አልአኽደር
ሀፍስ አን አሲም

🌴37 - ሼህ ካሚል አልሙሩሺ
ቃሉን አን ናፊዕ

🌴38 -ሼህ ኒዕመሁ አልሃሳን
ሀፍስ አን አሲም

🌴39 - ሼህ ሙስጠፋ ገርቢ
ወርሽ አን ናፊዕ

🌴40 - ሼህ አልይ አልሁዘይፊይ
ሀፍስ አን አሲም

🌴41 - ሼህ አብዱረሺድ አሱፊ
ሺዕበት አን አሲም

🌴42 - ሼህ አልኡዩኒልኮሺ
ወርሽ አን ናፊዕ


🌴43 - ሼህ ተውፊቅ አሳኢግ
ሀፍስ አን አሲም


🌴44 - ሼህ አብደሏህ መጥሩድ
ሀፍስ አን አሲም


🌴45 - ሼህ ሃቲም አልዋኢሪ
ሀፍስ አን አሲም


🌴46 - ሼህ ሙሀመድ አብዱል ከሪም
ወርሽ አን ናፊዕ አን ጠሪቅ አልኡስቡሃኒ


🌴47 -ሼህ ዩሱፍ አህመድ
አልሱሲ አን አቢ አምር

🌴48 - ሼህ ሷሊህ ሷሊህ
አልደውሪ አን አቢ አምር


🌴49 -ሼህ ዩሱፍ አህመድ
ሒሻም አን ኢብኑ አሚር


🌴 50- ሼህ አብደሏህ አልጁሐኒ
ሀፍስ አን አሲም

🌴 51- ሼህ ካሚል አል ሙሩሺ
ወርሽ አን ናፊዕይ

📮 @AlQuranulKerim

👇👇👇📡👇👇👇
t.me/AlQuranulKerim

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

22 Oct, 04:09


#Umma_Life_ምንድነው_ማነው_የሰራው_ዓላማውስ_ምንድነው?

ይህ Umma Life(ኡማ ላይፍ) የተሰኘው አፕልኬሽን ልክ እንደ ፌስቡክ አካውንት ከፍተን የራሳችንን ፅሁፎች፣ ምስሎች እና ቪድዮዎች ጭምር ማጋራት የምንችልበት ፕላትፎርም ሲሆን ከፌስቡክ የሚለየው እያንዳንዱ የምንለቃቸው ነገሮች ከሸሪዐ አስተምህሮ ጋር የሚጋጭ መሆን የለበትም።

የዚህ ፕላትፎርም መስራችና ስራ አስኪያጅ "ዒሳ ዳገስታኒ(Isa Dagestani) ሲባል በዜግነት ቱርካዊ ነው።

ይህን ፕላትፎርም ለማዘጋጀት እንደምክንያት ሆኖ ያነሳሳቸው በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሀሳቡን ሲያንፀባርቅ ሀሳቡን/ፅሁፉን ከማገድ አልፈው አካውንቱን እስከመዝጋት በመድረሳቸው ነው።

Non-ሙስሊም የሆኑ ሰዎች የፕላትፎርሙን ህገ_ደንብ ካከበሩ መቀላቀል እንደሚችሉ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

እኔ ያየሁዋቸው መስተካከል ያለባቸው የተወሰኑ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ የኮሜንት ሴክሽኑ ክፍት ቢሆንም ሀሳብ ማስፈር አንችልም። በተጨማሪ አንድ ጊዜ ፖስት ካደረግን በኋላ Edit ማድረግ አንችልም።

አሁን ቨርዥን 2.4.15 ላይ ደርሷል።

አፕልኬሽኑን ለማግኘት ተቸግረናል ላላችሁኝ በሚከተለው የቴሌግራም ሊንክ ገብታችሁ ማውረድ ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇
Follow me
https://ummalife.com/umma1697909821

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

07 Oct, 14:56


የአቢዘር ቤተሰቦች ከጎናቸው ያለ ዘመድ ጓደኛ ወደ አቢዘር ዛሬም አምጥትዋል።
ባለፉት በ24 ሰአት ውስጥ 7 አዲስ ቤተሰብ ወደ አቢዘር ተቀላቅለዋል።
ከአዲስ አበባ 3
ከቤኒ ሻንጉል 1
ከጅዳ 1
ከሪያድ 1
ከጅቡቲ 1
አላህ ይቀበላችሁ አላህ ይጨምርላችሁ ።

ሁላችንም የአቢዘር ቤተሰቦች በየቀኑ ለውጥ ለመፍጠር በወር ከ100 ብር ጀምሮ እንደ አቅሙ በመደገፍ ሁሉም ማህበረሰብ የቲሞችን ወደ ራሱ እንዲያስጠጋ ባላችሁበት አስተባብሩ ፍቃደኛ ሲሆኑ በታች ባለው ሊንክ መዝግቧቸው።
https://bit.ly/2TeUor3

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

24 Sep, 17:39


ሰኞ እና መውሊድ?

መውሊድ አክባሪዎች “ነብዩ ﷺ ሰኞን የተወለዱበት ቀን ስለሆነ ፆመዋል፡፡ ይህም መውሊድን (ልደታቸውን) ለማክበር ማስረጃ ነው፡፡” ይላሉ፡፡
በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ማስረጃ ብለው ያቀረቡት፣ ማስረጃ መሆን እንደማይችል በሰፊው እንየው፡፡
ነብዩ (ﷺ) ሰኞን ቀን እንደሚፆሙ በትክክለኛ ሀዲሶች ተረጋግጧል፡፡ የሚከተሉትን ሀዲሶች እንይ

የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ሰኞን ለምን እንደሚፆሙ ተጠየቁ፣ እሳቸውም “በዛ ቀን ተወለድኩ፣ እናም መለኮታዊ ራእይም በዛው ቀን መጣልኝ” ሰሂህ ሙስሊም 1162
በሌላ ዘገባ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ አሉ “ስራዎች ሰኞ እና ሀሙስ (ወደ አላህ) ይወጣሉ፡፡ ስራዬ ፆመኛ ሆኜ እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ” ቲርሚዚ 747

ከነዚህ ሁለት ሀዲሶች የምንማራቸው ትምህርቶች እንደሚከተለው ይቀርባሉ
1.) የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ሰኞን የፆሙት ለሶስት ምክንያቶች ነው
a. የተወለዱበት ቀን ስለሆነ፣
b. ቁርኣን ለእሳቸው የወረደበት ቀን ነው፣
c. ስራዎችም ወደ አላህ የሚወጡበት ቀን ስለሆነ እና እሳቸው ስራቸው ፆመኛ ሆነው እንዲወጣላቸው ስለፈለጉ፡፡
የአላህ መልክተኛ (ﷺ) የፆሙት ከላይ በተጠቀሱት ሶስት ምክንያቶች እንጂ ሰኞን ስለተወለዱበት ብቻ አልነበረም፡፡

2.) ከዚህ ሀዲስ ሰሃባዎች አመት ጠብቀው በረቢአል አወል የነብዩን (ﷺ) ልደት ማክበርን አልተረዱም፡፡ ሰሃባዎች ደግሞ ለኢስላም በጣም ቅርብ፣ ኢስላምን ጠንቅቀው አዋቂዎች እና ኢስላምን ከማንም በላይ የተረዱ ከመሆናቸውም ጋር “መውሊድ” የሚባል በአል አያከብሩም ነበር፡፡

3.) ታቢኢን በመባል የሚታወቁት የሰሃባ ተማሪዎች ከዚህ ሀዲስ መውሊድ የሚባል በአል አለ ብለው አልተረዱም፡፡

4.) አራቱ ታላላቅ የፊቂህ ኢማሞች አቡ ሀኒፋ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማሙ ሻፊኢ እና ኢማሙ አህመድ ይህን ሀዲስ እያወቁ፣ ሀዲሱን መውሊድ (የነብዩን ልደት) ማክበር ይቻላል ለሚል ማስረጃ አልተጠቀሙትም ፡፡

5.) በዚህ ሀዲስ የተገደበው አምልኮ ፆም ነው፡፡ ስለዚህ ፁሙ፡፡ ከዚህም አትለፉ፡፡ ዲኑ ገር ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) የሰሩትን እንስራ ያልሰሩትን አንስራ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ይገርማሉ ሀዲስን ትርጉሙን ያዛባሉ፣ ይጠመዝዙታል ለምን ሲባል ቢድኣን ለማንገስ፡፡ እኛ ከሰሃባዎች በላይ አላህን አዋቂ፣ ፈሪም፣ አላህ ዘንድ እውነተኞችም አይደለንም፡፡ እኛ ከሰሃባዎች በላይ ነብዩ (ﷺ) አንወድም፣ አናከብርም፣ መስዋትም አልሆንም፡፡ ስለዚህ አደብ አድርገን እንቀመጥ፡፡
እንዲህ አይነት ጥፋቶችን ስናጋልጥ እናንተ በእድሜ ከጠገቡት ታላላቅ ኡለማዎች፣ ሙፍቲዎች፣ ዶክተሮች፣ ኡስታዞች ትበልጣላችሁን? ሲሉ ይጠይቃሉ
መልሱም ቀላል ነው
እነዚህ እናንተ ኡለማ ብላችሁ የምትከተሏቸው ሶዎች ከሰሃባዎች አላህን በመፍራት፣ አላህ እና መልክተኛውን በመውደድ፣ በእውቀት ይበልጣሉን?
አይበልጡም
ስለዚህ ሙፍቲም፣ ዶክተርም፣ ኡስታዝም፣ ሙነሺድም፣ ድቤ መቼም አርፈው ይቀመጡ፣ ዲን አይበጥብጡ፡፡
ኡማውን አይከፋፍሉ፡፡ ሺርክ እና ቢድኣን አያንግሱ፡፡
አላህ ከሺርክ፣ ከቢድኣ፣ ከዘረኝነት የፀዳ እውነተኛ አንድነት ይስጠን፡፡

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

05 Jun, 21:25


የኢትዮጵያውያን ሑጃጆች ከትናንት ሌሊት ጀምሮ ጉዞ መጀመራቸውን አንብቢያለሁ።

የተጓዛችሁና የምትጓዙ ይሄንን በከለር ምስሎች የተደገፈ የሐጅና ዑምራህ ማብራሪያ አንብቡት።

ደግሞ ለኡማው ዱዓእ አድርጉ።

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

03 Jun, 15:18


አንተ ሩቅ የሆነን ተመልካች ነህ
አንተ  የውስጥን አዋቂ ነህ
አንተ  አዛኝም ሩህሩህም ነህ
አንተ ታጋሽ እና ሀያል ነህ ጌታዬ
አንተ  መሀሪም ይቅር ባይም ነህ 

በዲናችን እና በሙስሊም ወንድም እህቶቸ ላይ እየሆነ ላለው በደል  እና ጭቆና በበደለኞች ላይ መቀጣጫ ይሆናቸው ዘንድ የቆጣ ብትርህን አሳርፍባቸው::

ለዲናቸው መስዋዕትነት የከፈሉትንም  በጀነትን ሞሽራቸው

ዱአ ሸህድ ለሆኑት :-
#اللهم ارحم موتانا وموتى المسلمين برحمتك يا ارحم الراحمين
#اللهم اطعمهم من الجنة واسقهم من الجنة و ارهم مكانهم من الجنة وقل لهم أدخلوا من أي باب تشاؤون
#اللهم في ذمتك وحبل جوارك فقهم من فتنة القبر وعذاب النار وانت اهل الوفاء والحق فاغفر لهم وارحمهم انك انت الغفور الرحيم

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

20 Apr, 16:46


]

تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

13 Apr, 18:40


ወቅታዊ መልዕክት
==============
(ለሌሎችም አሰራጩት! ከምንዳው ተቋዳሽ ትሆናላችሁ!)
||
ዛሬ ሐሙስ ከመጝሪብ ሶላት በኋላ አሁን ይሄ ምሽቱ የጁሙዓህ ቀን ሌሊት ነው። በተጨማሪም የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ከሆኑት መካከል አንዱ ነው። በተጨማሪም ለይተ-ል-ቀድር ይበልጥ ከምትጠበቅባቸው ነጠላ ቀናት (ዊትር) መካከል አንዱ የሆነው 23ኛው ሌሊት ነው።
ታዲያ ይሄን ቀን ከሌሎቹ ምን ይለየዋል?

የጁሙዓህ ሌሊት ከዐሽረ-ል-አዋኺር መካከል ከነጠላዎቹ ቀናት ከአንዱ ጋር ከገጠመ ለይለተ-ል-ቀድር ከሌላው በበለጠ መልኩ ትጠበቃለች።



*بعد مغرب اليوم الخميس  .. ستكون ليلة الثالث والعشرين وتوافق ليلة الجمعة، فتوافقت ليلة وتر وليلة جمعة*
وقد نقل ابن رجب في لطائف المعارف عن ابن هبيرة أنه قال :
ኢብኑ ረጀብ አል-ሃንበሊ ለጧኢፉ-ል-መዓሪፍ በተባለው ዕውቅ ኪታቡ ላይ ከአቡ ሁበይራህ የሚከተለውን አስተላልፏል፦

«
*إذا وافقت ليلة الجمعة ليلة وتر فهي أرجى من غيرها في أن تكون ليلة القدر .*
«የጁሙዓህ ሌሊት ከነጠላዎቹ (የዐሽረ-ል-አዋኺር) ሌሊት ጋር ከተገጣጠመች፤ ከሌሎች (ሌሊቶች) ይበልጥ ለይለተ-ል-ቀድር ትሆናለች ተብሎ ይከጀላል።»


*ويقول شيخ الاسلام ابن تيمية :
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ሸይኹ-ል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚይተም እንዲህ ይላል፦
إذا وافقت ليلة الجمعة احدى ليالي الوتر من العشر الأواخر فهي أحرى أن تكون ليلة القدر بإذن الله.*
«የጁሙዓህ ሌሊት ከመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ከነጠላዎቹ ሌሊቶች ጋር ከገጠመች፤ በአላህ ፈቃድ ይበልጥ ለይተ-ል-ቀድር ትሆናለች ተብሎ ትጓጓለች (ትጠበቃለች)!»

*وفي حديث المساء للشيخ عبدالعزيز بن باز رحمه الله(239) قال بعض أهل العلم: إن كان في الأوتار ليلة الجمعة كانت آكد وأقرب أن تكون ليلة القدر، لذا ينبغي لنا أن نعني بهذه الليالي ولاسیما هذه الليلة وأن يكون لنا فيها حظ ونصيب من الإجتهاد  في الخير.*

በአጭሩ የጁሙዓህ ሌሊት ከነጠላዎቹ የመጨረሻዎቹ አስሮች ሌሊቶች ጋር ከገጠመች ያቺ ሌሊት ለይለተ-ል-ቀድር የመሆን እድሏ በጣም ትልቅ ነው። ለለይለተ-ል-ቀድርን ይበልጥ የቀረበች ናትና ሌሊቷን ቁርኣን በመቅራት፣ በተሃጁድና መሰል ዒባዳዎች ሕያው ማድረግ ላይ እንበርታ። ይህ ሌሊት ደግሞ አሁን ያለንበት ሌሊት ስለሆነ እኛም እንበርታ፤ ሌሎችንም እናበርታ፤ መልዕክቱንም እናድርስ።

አላህ ለሁላችንም ይወፍቀን!

وفقني الله وأياكم لقيام ليلة القدر إيمانا وإحتسابا..!!.

||
t.me/MuradTadesse

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

03 Jan, 20:31


ስለ ሰሞኑን ከባድ ብርድ እስልምና ምን ይላል?

የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ
ኢስላም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሀይለኛ ሙቀት እና በሀይለኛ ብርድ ሰው ተቸግሯል፡፡ ይህም ከመሆኑ ጋር ለአላህ ካጠፋነው ጥፋቶች ንሰሀ ከመግባት ይልቅ በየዜና አውታሩ “የአለም በረዶ ስለቀለጠ ነው፣ ዛፎች በመቆረጣቸው ነው፣ ኦዞን በመሳሳቱ ነው…..” እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች ናቸው እየተባለ ይለፈፋል፡፡

እስቲ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምን እንደሚሉ እንይ
አቡ ሁረይራ (ረድየላሁ አንሁ) ባስተላለፉት፣ ኡማሙ አል-ቡኻሪ በዘገቡት ትክክለኛ ሀዲስ ላይ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ

“ጀሀነም (እሳት) ወደ ጌታዋ ስሞታ አቀረበች፡፡ ከፊሌ ከፊሌን በላው አለች፡፡ አላህ ሁለት ጊዜ እስትንፋስን ፈቀደላት፡፡ አንደኛው በቀዝቃዜ ወራት ሌላኛው ጊዜ በሙቀት ወራት፡፡ በሙቀት ጊዜ የምታገኙት ከባድ ሙቀት እና በቅዝቃዜ ጊዜ የምታገኙት ከባድ ውርጭ (ቅዝቃዜ፣ ቀቅ) (ናቸው)፡፡”

حَدَّثَنَا أَبُو الْيَمَانِ، أَخْبَرَنَا شُعَيْبٌ، عَنِ الزُّهْرِيِّ، قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو سَلَمَةَ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ، أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا، فَقَالَتْ رَبِّ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا، فَأَذِنَ لَهَا بِنَفَسَيْنِ نَفَسٍ فِي الشِّتَاءِ وَنَفَسٍ فِي الصَّيْفِ، فَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ فِي الْحَرِّ، وَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الزَّمْهَرِيرِ ‏"‌‏.‏
ልብ እንበል ከባዱም ሙቀት እና ከባዱም ብርድ የአዋቂዎች ሁሉ አዋቂ፣ የአላህን ፈሪዎች ሁሉ ፈሪ፣ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ እንደነገሩን የጀሃነም እሳት የምትተነፍሰው ሁለት ትንፋሽ ምክንያት ነው፡፡
ሌላው መገንዘብ ያለብን ነገር እስልምና ሙሉ መሆኑን ለማንኛውም አለም ላይ ላለ ክስተት በል እንዲያውም ለሚቀጥለው አለም ጉዳዩች፣ የሚቀጥለው አለም ላይ ምን እንደሚከሰት በዝርዝር እና በጥቅል የተናገር ዉድ፣ ልዩ፣ የማይበረዝ፣ የማይሰረዝ፣ የማይደለዝ፣ ዘመን የማያልፍበት ሀይማኖት ነውና አጥብቀን እንያዘው፡፡ ይሀው ተመልከቱ አለም “Econmic Crisese” ኢኮኖሚክ ክራይስስ ብለው ሲያወሩ አላህ ጥንትም የወለድ መጨረሻው ይህ መሆኑን ነግሮን ነበር፡፡
ትዳር እንዲመሰረት እና ከዝሙት እንድንታቀብ ከጥንትም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት መክሮ ነበር፡፡ ግን ይህን አልሰማ ብለው አሁን አለም ላለችበት ከባባድ በሽታዎች ተዳርገዋል፡፡

በሁሉም የህይወት ዘርፍ ላይ የጥንት የጠዋቱ ኢስላም (ሰለፍያ) በሄደበት መንገድ መሄድ ብቻና ብቻ ነው ዋስትናው፡፡ ሁለት ሃቅ የለም፡፡ ሁሉም ሙስሊም ከጥመት ቡድኖች እርቆ ወደ ብቸኛዋ አማራጭ እና ሁለተኛ ወደሌላት ሃቅ ጎዳና፣ ሰለፉነ ሷሊሂን የተጓዙባት ጎዳና መመለስ ግድ ይለዋል፡፡ አለበለዚያ በሙስሊሙ አለም ላይ እንዳየነው አሁንም ከባድ ኪሳራ ይከሰታል፡፡
ታድያ ምን ይበጀን?

አማኞች ወደ ጌታቸው በንሰሃ ሊመለሱ፣ ያችን “ጭማሪ አለን?” ብላ የምትጠይቀውን ጀሀነም ከሷ ጌታችን እንዲጠብቀን እሱን ዘውትር መለመን ግድ ይለናል፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ፡፡ አላህ እነዚህን ሁሉ ተዓምራት የሚያሳየን በሰጠን አእምሮ የሱን ጌትነት፣ በቸኛ ተመላኪነት አውቀን ወደሱ እንድንመለስ ነው፡፡
አላህ ሆይ! ሁሌ ወዳንተ በጸጸት ከሚመለሱት አድርገን፡፡

Via SadatKemalAbuMeryem

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

12 Nov, 14:20


ሸኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

«المسبحة من شعار الصوفية، وأنت أصابعك تكفي»

«ሙሰቢሀ የሱፍዮች መገለጫ ምልክት ነው። እጅህ ይበቃሀልና በሱ ዘክር።»

شرح إغاثة اللهفان 8/11/1436

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

02 Nov, 13:22


ነጃሳው የበዛበት የቲክ ቶክ ግቢ ውስጥ የረባ ያልረባውን የምትሰሙና የምትመለከቱ ወንድሞችና እህቶች አሏህን ፍሩ ! ሁሉም ነገር አልፎ የቀብርን አፈር መንተራስ ይመጣል ፣ ይሄ ሁሉ አክትሞለት አሏህ ፊት መቆም ይከሰታል !

አሏህ ነገራችንን ሁሉ ተመልካች ነው !

እዚህ መንደር እውነተኛን ደስታ ማግኘት የሚታሰብ አይደለም ። የረከሱ እርኩሳንን መመልከትና መከታተል ከአማኞች ክብር ጋር የማይሄድ ምግባር ነው ።  ነፍስን የሚያረክስ ጎጂ ልማድ ነው !

እናንተ አማኞች ሆይ ፣ የተከበራችሁ ናችሁና የረከሰውን ለሚገባው ተውት !

ወደ እምነታችን ፣ ወደ ክብራችን እንመለስ !

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

13 Oct, 19:37


Live stream finished (9 minutes)

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

13 Oct, 19:31


https://t.me/kedibntebrahim?livestream=bd06ef0143d4065817

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

13 Oct, 19:27


Live stream started

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

13 Oct, 19:26


Channel photo updated

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

14 Aug, 05:19


#Turullee #dhugatuu #irra #aana

🥦🥦🥦🥦🥦🥦
#Kutaa #33ffaa
🥦🥦🥦🥦🥦🥦

Gilgaala; Hubannoo yaada sammuu keessaa qabnuu fi ragaa jiru wol bira qabuun ittiin madaallu;

Amaloota asii gadii keessaa, amala Waaqa ta'uun isa kan yaaddamu yookaa shakkamu, amala isa kami jettu?

A. #Maatewos 26:67-68
Yommus #fuula #isaatti #tufanii, isa abootan; #warri #kaanis #kakkabalanii, Ati, #Kristos! #Eenyutu #si #rukute? Raajii keetiin nutti himi!" jedhaniin. በዚያን ጊዜ #በፊቱ #ተፉበት፤ #ጐሰሙትም፥ ሌሎችም #በጥፊ #መትተው። #ክርስቶስ #ሆይ፥ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን አሉ። Kanaafuu, Yesuusitti itti tufame, itti biifame, ni kabalame, garuu Rabbiin amala kana hundaan himamuun gonkumaa hin malu.

B. #Luqaas 4:1-2
Yesus hafuura qulqulluudhaan erga guutamee booddee Yordaanosii deebi'ee, hafuuruma sanaan lafa onaa keessa #guyyaa #afurtama geggeeffame, #Seexanaanis #qoramaa #ture. Guyyaa sana hundaa homaa iyyuu hin nyaanne, dhuma guyyoota sanaattis in #beela'e. #የሉቃስ #ወንጌል 4:1 ኢየሱስም መንፈስ ቅዱስ መልቶበት ከዮርዳኖስ ተመለሰ፥ በመንፈስም ወደ ምድረ በዳ ተመርቶ:#አርባ #ቀን #ከዲያብሎስ #ተፈተነ። በነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፥ ከተጨረሱም በኋላ #ተራበ። Kanaafuu, Yesuus lafa onaa keessa ture, akkasumas seexanaan qorame, garuu kun hunduu amala Rabbiitii miti.

🥦🥦🥦🥦🥦🥦🥦🥦

Qabxiiwwan ijoon nuti argannu:

1ffaa- #Yesuus itti #tufame akkasumas itti #biifamuun, #Yesuus #nama #ta'uu fi aangoo Rabbuma akka #hin #qabne waan beekkamuuf, namootaan tuffatamuu fi aangoo dhuunfaa miidhaa ofi oolchuun waan hin qabneef, #tuftoo fi #biifaan namoota fuula irratti ta'uu isaa.

2ffaa- Yesuus tuftoo fi biifaa bira dabranii yeroo namoonni #kaballaassaniiyyuu,
Waaqummaa mitii, hafuurri Waaqummatuu waan harka isaa keessa hin jirreef, miidhaa isa irratti raawatamu yoo Rabbiin isa tisse malee inni ofi tissuu gonkumaa akka #hin #dandeenne mudhisa. Kun ammoo, amala Waaqumma Yesuus ni qaba jedhamuu mitii, yaaduunuu nama sammuun waa yaaduf akka hin malle, ifatti mirkaneessaa jechuudha.

3ffaa- #Yesuus osoma #hafuura #qulqulluudhaan #guutame jedhamee kitaaba kessatti ibsamu, #Yesuus amala Waaqummaa ni qaba jedhamee namoota tokko tokkoon osoma himamuu, aangoon hafuura qulqulluudhaan guuttamuu fi amalli ni qaba jedhame hundi, #rakkoo #jalaa #baraaruu #hin #dandeenne. Maqaa fi ragaan Yesuus ittin himamaa ture (#worrota #Kiristaanaatiin jechuudhaa) #guutuun isaa (Yesuus #gooftaadha, Yesuus #ilma #Waaqaati, Yesuus #fayyisaadhaa kkf), ragaa foorjidii ta'ee hafuun, akka wonti Yesuusiin hin qabne kamuu, gaafa Rabbiin ifa baasuu, Yesuusiin sobaan faarsuun gonkumaa isaaf aangoo guyyaa takkaallee hin daballe, kitaabuma Yesuus amala Waaqummaalle ni qaba jedhamu keessaatti, oduun biroo ta dhugaa maalummaa Yesuus mudhiftu, #Yesuus #bultii #40 #guutuuf, #lafa #onaa #keessa jiraataa akka turee fi dabrees #seexanaan #akka #qorame, gurraan dhageenne, dhagahuu bira kutnee ragaa isaa kitaaba irraa dubbisnee jechuudha. Kun hundi maal mudhisa yoo jenne, #Yesuus #garbicha #Rabbii, ka Rabbiin isa filate, #Nabiyyii #Rabbiin ummata #Israa'elitti #ergate malee, haasofni amala Waaqumma qoodaa fi gahee isaa #gonkumaa akka #hin #taane, akka aduu samii gubbaa, guyyaa duumessi hin jirre iftutti, dhugaa maalummaa Yesuus ibsu ta'uu mirkaneefanna.

4ffaa- Wolumaa galatti, #mootiin #ofi #danda’aan, #Rabbii #tokko malee akka #hin #jirre, wonti Rabbiin alatti argamu kamuu, Rabbii tokkichatti, Yesuusiinille dabalatee hajamuu ta'uu, #uumamni fedhii Rabbiitin ala #ofi #fayyaduu yookaa #miidhaa #ofi #irraa #dhoorguu #danda'u tokkoo akka #hin #jirre ifatti hubannaa jechuudh.

Worroota Amanti Kiristaanaatiif;
1 #Tasaloniiqee 5:21
" Garuu waan hundumaa qoraa, #isa #gaarii #jabeessaatii #qabadhaa! "
dhaamsa jedhu isinii dhaamaa.

Hawaasni keenna ammoo, "sababa keetiin namni "tokko "qajeeluun, #gaala #diddiimaa karaa Rabbii keessatti kennatu siif caala, ka Nabiyyiin Rabbii (nagahaa fi Rahmanni Rabbii isaan irratti haa jiraatu), jedhanii Aliyyiif dhaaman siif dhaama. Sheer taasisuun sin kafalchiisu, lammiiwwan keenna beektu hundaa ergii, toltuu guyyaa boruutti si fayyaddu guduunfadhu.

♻️♻️♻️♻️By:XR ♻️♻️♻️
https://t.me/Xaalibu6504

̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ መልካም ሥነ-ምግባር (حُسْنُ الخُلُق) ̥̥̥

05 Jul, 17:41


የፊታችን የጁሙዓህ ቀንና የዐረፋ ቀን መገጣጠሙ ልዩ የሚያደርገው ነገር‼️

በኡስታዝ ዐብዱስሰላም አሕመድ

Credit: ኹበይብ መስጅድ