የካምፓስ ህይወት_MAHIR @yecampas_hiwet Channel on Telegram

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

@yecampas_hiwet


*በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
# የካምፓስ ህይወት
# ፍቅር
# ምርጥ ምርጥ ታሪኮች
# ቀልዶች
# ቁም ነገሮችን ያገኙበታል
ይዝናኑበታል ....ይቀላቀሉን

አስተያየት ካለዎት ለቡቱ ከሆነ👉 @Abdumah_bot or
በዚህ ደግሞ 👉 @mahmahi_bot
በዚህ ደግሞ 👉 @mahmahi_bot
መስጠት ይቻላል

የካምፓስ ህይወት_MAHIR (Amharic)

የካምፓስ ህይወት_MAHIR በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሆነ፣ ስለ እናቶቻችን እና ባህላችን የብልሽጣኑ ፍቅር እና ስለ ምርጥ ምርጥ ታሪኮች የሚሆነውን ቀልዶች እና ቁም ነገሮችን ያገኙበታል። የእናቶችን እና ባህላችን ፍቅርን ለማስወገድና ለመንቀሳቀስ የሚሆኑ ምርጥ ታሪኮችን እና ስለ ቀልዶች ምን እንደሆነ መስጠት ይቻላል። በቡቱ ከሆነ @Abdumah_bot ወደ mahmahi_bot በማወቅ ይቅርብ።

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

02 May, 20:49


Coming soon

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

16 Aug, 14:02


የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ተአምር 1

ክፍል አንድ

ቅዱስ ቁርኣን፡-
ቅዱስ ቁርኣን ለነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ከተሰጣቸው ተአምራት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ አላህ ቁርኣንን በሳቸው ላይ ማውረዱ ብቻ ለነቢይነታቸው በቂ ማስረጃ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ቃሉም እንዲህ ይላል፡-

" أَوَلَمْ يَكْفِهِمْ أَنَّا أَنْزَلْنَا عَلَيْكَ الْكِتَابَ يُتْلَى عَلَيْهِمْ إِنَّ فِي ذَلِكَ لَرَحْمَةً وَذِكْرَى لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ " سورة العنكبوت 51
"እኛ መጽሐፉን በነሱ ላይ የሚነበብ ሆኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸውምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ችሮታና ግሣጼ አለበት።" (ሱረቱል ዐንከቡት 51)፡፡
የቅዱስ ቁርኣን ተአምራዊነት፡ ከቀደምት ነቢያት ተአምራት በሁለት መልኩ ይለያል፡-
- ‹‹መዕነዊይ›› መሆኑ፡- የቀደምት ነቢያት ተአምራት ‹‹ሒስሲይ›› ይባላል፡፡

‹‹ሒስሲይ›› ማለት፡- በአይን የሚታይ፣ በእጅ የሚዳሰስ ማለት ነው፡፡ በሙሳ በኩል፡- በትር ወደ እባብ ሲቀየር፣ ባህሩ ደርቆ መሻገሪያ መንገድ ሲሆን፣ እጅ መልኩ ተቀይሮ የሚያበራ ነጭ ሲሆን የሚታይና የሚዳሰስ ይባላል፡፡ በዒሳ በኩል፡- የሞቱት ሲነሱ፣ የዕውሮች አይን ሲበራ፣ ለምጽ የነበረባቸው ሲሽሩ የሚታይና የሚዳሰስ ተአምር ይባላል፡፡ ለነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይነት እንደ ማስረጃ የተሰጣቸው ቁርኣን ግን ‹‹መዕነዊይ›› ነው፡፡

‹‹መዕነዊይ›› ማለት፡- ህሊናን የሚያናግር፡ አእምሮን የሚቆጣጠርና ልብን የሚገዛ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ቀርኣን ሲቀራ በመስማት ብቻ የሰውን ልብ ይገዛል፡፡ በሚያስተላልፋቸው መልእክቱ፡ ሰዎችን ለለውጥ ይዳርጋል፡፡

- ‹‹አበዲይ›› መሆኑ፡- የቀደምት ነቢያት ተአምር ከነቢይነት ዘመናቸው ጋር ብቻ የተቆራኘ ነው፡፡ ከነሱ ሞት በኋላ ያበቃል፡፡ ሙሳ ከሞተ በኋላ በትር ወደ እባብ አይቀየርም፡ ባህር ደርቆ መንገድ አይሆንም፡፡ ዒሳ አላህ ወደ ራሱ ከወሰደው በኋላ፡ የሞተ አልተነሳም፡ የእውር አይን አልበራም፡፡ ቅዱስ ቁርኣን ግን ከነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ሞት በኋላ እንኳ ተአምራዊነቱ አላከተመም፡፡ እስከ ቂያማ ድረስ ድሮ በነበረው ተአምራዊነቱ ይቀጥላል፡፡ ስለዚህም ‹‹አበዲይ›› (ዘውታሪ) ይሰኛል፡፡ ከቅዱስ ቁርኣን ተአምራቶች መካከል የተወሰኑትን እንመልከት፡-

1. አምሳያው ፈጽሞ አለመገኘቱ፡- በቅዱስ ቁርኣን አምላካዊ ቃልነት ላይ ጥርጣሬ ያደረባቸው ሰዎች ካሉ፡ ጌታ አላህ አንድ ማጣሪያ ሰጣቸው፡፡ እሱም፡- ይህ ቁርኣን የሰው ድርሰት ነው፡ ብላችሁ ከተጠራጠራችሁ፡ እናንተም ሰው ናችሁና ያ ሰው የተጠቀመውን መንገድ በመጠቀም ቁርኣንን የሚመስል ነገር ጽፋችሁ አምጡ!! አላቸው፡፡ ቅዱስ ቁርኣን በአነጋገሩ ጠቅላላነት፡ በአረፍተ ነገሮቹ አሰካክ፡ ስድም ቅኔም ሳይሆን ለየአንቀጾቹ ዜማዊ ማሳረፊያዎች ያሉት፡ ትርጉሙን የተረዳውንም ሆነ ያልተረዳውን ሰው ቀልብ የሚገዛ በመሆኑ፡ እርሱን የሚመስል አነጋገርና አጻጻፍ ማን ማምጣት ይችላል? እያለ ነው፡፡ ቅዱስ ቁርኣን አምሳያዬን አምጡ ብሎ ሰዎችን በቀጣዮቹ መንገድ ተፎካክሯል፡-

1. ሙሉውን ቁርኣን ማምጣት፡-
"أَمْ يَقُولُونَ تَقَوَّلَهُ بَلْ لَا يُؤْمِنُونَ * فَلْيَأْتُوا بِحَدِيثٍ مِثْلِهِ إِنْ كَانُوا صَادِقِينَ " سورة الطور 34-33
“ወይም ቀጠፈው ይላሉን? አይደለም በውነቱ አያምኑም፡፡ እውነተኞችም ቢሆኑ መሰሉ የሆነን ንግግር ያምጡ” (ሱረቱ-ጡር 33-34)፡፡

2. ሙሉውን ካልቻሉ 10 ሱራ ብቻ
"أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ قُلْ فَأْتُوا بِعَشْرِ سُوَرٍ مِثْلِهِ مُفْتَرَيَاتٍ وَادْعُوا مَنِ اسْتَطَعْتُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ " سورة هود 13
“ይልቁንም (ቁርአንን) ቀጣጠፈው ይላሉን?፡- እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን አስር የተቀጣጠፉ ሱራዎች አምጡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን (ረዳት) ጥሩ በላቸው፡፡” (ሱረቱ ሁድ 13)፡፡

3. 10ሩን ካልቻሉ ደግሞ አንዲትን ሱራ ብቻ
"أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ قُلْ فَأْتُوا بِسُورَةٍ مِثْلِهِ وَادْعُوا مَنِ اسْتَطَعْتُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ " سورة يونس
“በውነትም (ሙሐመድ) ቀጣጠፈው ይላሉን? ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ እውነተኞች እንደሆናችሁም (ተጋግዛችሁ አምጡ) በላቸው፡፡” (ሱረቱ ዩኑስ 38)፡፡

"وَإِنْ كُنْتُمْ فِي رَيْبٍ مِمَّا نَزَّلْنَا عَلَى عَبْدِنَا فَأْتُوا بِسُورَةٍ مِنْ مِثْلِهِ وَادْعُوا شُهَدَاءَكُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ * فَإِنْ لَمْ تَفْعَلُوا وَلَنْ تَفْعَلُوا فَاتَّقُوا النَّارَ الَّتِي وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ أُعِدَّتْ لِلْكَافِرِينَ " سورة البقرة
“በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ ከቢጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ እውነተኞችም እንደሆናችሁም ከአላህ ሌላ መስካሪዎቻችሁን ጥሩ፡፡ (ይህንን) ባትሠሩ ፈጽሞም አትሠሩትምና ያችን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጊያዎች የሆነችውን እሳት ተጠበቁ ለከሓዲዎች ተደግሳለችና፡፡” (ሱረቱል በቀራህ 23-24)፡፡

በመጨረሻም ሰዎችም ጋኔኖችም በጋራ ቢሰባሰቡ፡ ቁርኣንን የሚመስል ለማምጣት ቢጥሩ፡ ፈጽሞ እንደማይሳካላቸው በመግለጽ ቁርጡን ነገራቸው፡-

"قُلْ لَئِنِ اجْتَمَعَتِ الْإِنْسُ وَالْجِنُّ عَلَى أَنْ يَأْتُوا بِمِثْلِ هَذَا الْقُرْآنِ لَا يَأْتُونَ بِمِثْلِهِ وَلَوْ كَانَ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ ظَهِيرًا " سورة الإسراء 88
“ሰዎችም ጋኔኖችም የዚህን ቁርአን ቢጤ በማምጣት ላይ ቢሰበሰቡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆንም እንኳ ብጤውን አያመጡም በላቸው፡፡” (ሱረቱል ኢስራዕ 88)፡፡

2. እርስ በርሱ ባለመጋጨቱ፡- ሌላው ቅዱስ ቁርኣን ከአላህ ዘንድ የመጣ የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተአምር መሆኑን የሚያመላክተው፡ በውስጡ የሰፈሩ ሀሳቦችና ቃላቶች ምንም አይነት መፋለስ፡ እርስ በርስ መጋጨት የማይታይባቸው መሆኑ ነው፡፡ ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-

"أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِنْدِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا " سورة النساء 82
“ቁርአንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡” (ሱረቱ-ኒሳእ 82)፡፡

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

16 Aug, 14:02


.

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

16 May, 09:06


ማሳሰቢያ!!!!!!!!!

ሰላም እንዴት ናችሁ የኔ ምርጦች ቤተሰቦቼ እና የኔ ተከታዮች የዘንድሮው ማለትም 2014 ማትሪክ ተፈትናችሁ ውጤት መቶላችሁ ሰመራ ዩንቨርስቲ የደረሳችሁ እና መምጣትም ሆነ ኢንፎሜሽን የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ ሙሉ መረጃ እና የሚያግዛችሁ አለ!!!!
@mahmahi_bot
@mahmahi_bot
@mahmahi_bot

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

04 May, 05:17


​​╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯


. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


#ክፍል_⓫



አባቷ ሀዩ በወሰነችው ውሳኔ እጅግ ተደሰቱ፤
የሚደርጉት ጠፋቸው፤ ግንባሯን ስመው ከመረቋት በኋላ ቶሎ እንደሚመለሱ ነጥረዋት ወጡ።
ሀዩ ትናንት አባቷ ላይ ያየችው የሀዘን ስሜት ዛሬ እንዲህ ባለ ደስታ ተቀይሮ ስታይ ውሳኔዋ ልክ እንደሆነ ገባት። አዎ ሉቅማንን ለማግባት ወስናለች።


የቤት ውስጥ ስራዋን እንደጨረሰች አባቷ ከአንዲት ሴት ጋር ወደቤት መጡ። ፊታቸው በፈገግታ ተሞልቷል። ሀያቴ ተዋወቂያት ዘይነብ ትባላለች ከዚ በኋላ ለቤት ውስጥ ስራ እሷ አለችልሽ አንቺ ትምህርትሽ ላን ነው በደንብ ማተኮር ያለብቅ
ሀዩ አባቷ ትናንት ለትምህርት ቤት የምከፍለው ገንዘብ አጣው እንዳላላት ዛሬየቤት ውስጥ ሰራተኛ
ይዞ መምጣቱ ግራ አጋባት።

እንዴ አባ አለት ዘይነብን ከተዋወቀቻት በኋላ በመገረም ስሜት አባቷን እያየችው። አባቷም የመገረሟ ምከንያት ስለገባቸው ወሬዋን እንኳን ሳያስጨርሷት ስለሆነው ነገር ነገሯት።

ሉቅማን ነው ያመጣት ሀያቴ ስለውሳኔሽ ስነግረው በጣም ነበር ደስ ያለው እሷም ለልጆቹ ትምህርት ቤትም የምከፍለውን እሱ ነው የሰጠኝ አንቺም ነገ ሄዳቹ እንደምትመዘገቢ
ነግሮኛል ደስ አይልም በአላህ ሉቅማን እኮ በጣም መልከም ሰው ነው
አዎ አባቴ አለች የሱ ደስታ ወደሷም ተጋብቶባታል።

በቃ ሀዩ ለ2 አመት ስትኖር የነበረውን ህይወት ዛሬ ልታቆሥ ነው። ሰለራሷ ማሰብ ልትጀምር ምንም ቢሆን ዛሬን ኑር አይደል የሚባለው።

አይደለም የዛሬ እንደ አመት ከትንሽ ደቂቃ በኋላ እንኳን ምን እንደምንሆን አናውቀውም። አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው።

ሀዩም ትልቁ ፍርሀቷና ስጋቷ ወንድምና አህቶቿን ጥላ ሰለመሄድ ነበር። አሁን ግን በተወሰነ መልኩ ሀሳቧን ቀይራ ዛሬን ስለመኖር መርህ ውስጥ ገብታለች። 1 አመት ካምፓስ እስከምትገባ ድረስ እዚው ቤት ስለምትቀመጥ ሌላውን ሲደርስ አስብበታለሁ ብላለች።

ሀሰን ሳንፈልግ ለቤተሰቦቹ ሲል ዛሬ ትምህርት ቤት ሊሄድ ነው። ውስጡ ምንም ሰላም አይሰማውም። የሀዩ ፍቅር ከቀን ከቀን እየጨመረ ሄዶ ናፍቆት ሊያሳብደው ደርሷል።
ቢያንስ ሀዩ ለምን ትምህርት ቤት እንደቀረች፣ ምን ሆና እንደሆነ፣ አሁንም ስላለችበት ሂወት ቢያውቅ ኖሮ የተወሰነ ሊረጋጋ እንደሚችል ያስባል። አሁንም ሀዩ ትኑር፣ ትሙት ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።

ብዙ ቀን ከት/ቤት ስለቀረና ማስረጃ ማቅረብ ስለሚያስፈልግ ከ አባቱ ጋር ነበር ወደት/ቤት የሄዱት። ትምህርት ቤት ሳይመጣ ከመቆየቱ ዛሬ አዲስ አመት ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጣ ነበር የመሰለው።

አባቱ የትምህርት ቤቱን አስተዳደር ለማናገር ወደቢሮ ሲገቡ ሀሰን ወደክፍሉ ገባ። ሁሉም ተማሪዎች ከበው ምን ሆኖ እንደቀረ እየጠየቁ ያጨናንቁት ጅመር።
ትንሽ አሞኝ ነበር ለዛ ነው ብሎ እጭር መልስ ከሰጣቸው በኋላ ወደመቀመጫው ጋር ሄደ። ድንገት ግን አይኑ እንጅ ነገር ላይ አረፈ በጣም ነበር የደነገጠው። እራሱን ስቶ ሲወድቅ የክላስ ተማሪዎች አስተማሪ አቅፈው ወደክሊኒክ እየተሯሯጡ ይዘውት ወጡ

#ክፍል\አስራሁለት ⓬ ይቀጥላል

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

02 May, 10:48


​​╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯



. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


#ክፍል_አስር....⓾
⊱◈◈◈⊰──────



ልጅቷ ይባስ ብላ ሄዳ አቅፋ ሰላም አለችው። ሀዩ በድንጋጤ ውስጥ ሆና እንደቆመች ነው።
ተዋወቂያት እህቴ ናት... ሁለቱንም እያየ እንዲተዋወቁ ጋበዛቸው።
አሰላም አለይኩም...ኢማን እባላለሁ..ለሰላምታ እጇን ዘረጋችላት።
ወአለይኩም አሰላም...ሀያት.. እጇን እየጨበጠች ፈገግ ብላ መለሰችላት።

ምኑንም ሳታጣራ ሉቅማንን የገመተችበትን እያሰበች እየሳቀች ከክፍሉ ወጣች።
የሄደችበት ጉዳይ አልተሳካም። ይልቁንም ሌላ ሀሳብ ነው የጨመረባት። ስለራስሽ ህይወት በደንብ አስቢበት ያላት ደጋግሞ አእምሮዋ ላይ እየተመላለሰ አስቸገራት። እውነቱ ያ እንደሆነ እኮ ታውቃለች ፤ ግን መቀበል አትፈልግም።



ሀሰን ዛሬ ከሆስፒታል የሚወጣበት ቀን ነው። ተሽሎት ሳይሆን ትንሽ መለስ ስላለለት ነው እንዲወጣ የተደረገው። ለህመሙ ማስታገሻ እንጂ መድሀኒት ሳይገኝለት!
ጭንቀቱን አውቀው ሊያስደስቱት ይቅርና ሀሰን ከልቡ ፈገግ ካለ እንኳን ቀናት ተቆጥረዋል።

ሀሰን አሁን ሁሉም ነገር አስጠልቶታል። ትምህርት ቤት አልሄድም እያለ ከቤተሰቦቹ ጋርም ይከራከራል። እሷ የሌለችበት ት/ቤት አልሄድም በሚል ደረቅ ብሂል ልቡን አደንድኖታል።

ህይወት ሁሌ እንዳሰብነው አትሄድም። እኛ እንደፈለግነው ሳይሆን አላህ ባዘዛት መንገድ ብቻ ነው የምትጓዘው። ታድያ አንዳንዴ እኛ የፈለግነውና አላህ የመረጠልን የመንገድ አቅጣጫ የተለያየ ሲሆን እናማርራለን። ነገሮችን የምንቀበልበት መንገድም ልክ እንደአቅጣጫው የተለያየ ነው። ታድያ ሀሰንም ለውጦችን ፣ አጋጣሚዎችን በፀጋ ተቀብሎ ከመጋፈጥ ይልቅ መሸሽን ይመርጣል። ምናልባትም ማፈግፈግ ጀርባን እንደሚያስመታ አላወቀም ይሆናል።

ከስንት ክርክርና ሙግት በኋላ ይሄን ሁለት ቀን አርፎ ከዛ በዋላ ትምህርቱን እንዲጀምር ተስማሙ።



አቶ ጀማል ዛሬ ሳያመሹ በጊዜ ነበር ወደቤት የመጡት። ፊታቸው ላይ የድካም፣ ተስፋ የመቁረጥ ፣ የሀዘን ስሜት ይነበባል። ከዚ በፊት እንደዚ ሲሆን አይተውት አያውቁም። ዛሬ እንደከፋው ያስታውቃል። ሀዩ ወንድምና እህቶቿ እንዳይጨነቁ ብላ እነሱ ፊት ምንም አላለችውም። ከተኙ በኋላ ግን ምን እንደሆነ ቀርባ አዋራችው። እሱም ባንክ ያለው ገንዘብ እያለቀ እንደሆነና ለልጆቹ ት/ቤት የሚከፍለውን ገንዘብ እንዳጣ በሀዘን ተውጦ ነገራት።

የአባቷን ሀዘን ስታይ ሀዩም በጣም ከፋት። አቅፋው
አብሽር አላህ ያውቃል እያለች አፅናናችው። አሁን የመጣላትን ባል ለማግባት ፍቃደኛ ከሆነች የአባቷን እንባ ማበስ እንዲሁም ለወንድምና እህቶቿ የነገ ህይወት ዛሬ አሻራ መጣል ትችላለች።

ዛሬ ያየችው የሉቅማን መልካም ስብዕና እንዲሁም የአባቷ ሀዘን ሉቅማንን እንድታገባው የገፋፋት ይመስላል። ዛሬም ስለዚሁ ጉዳይ እያሰበች እስከመጨረሻው የማትወላውልበትን ውሳኔ ለመወሰን ቆርጣ ከራሷ ጋር ግብ ግብ ይዛለች። ግብ ግቡ ግን እንዲው በከንቱ አልቀረም። ውሳኔ እንድትወስን አድርጓታል።

ጠዋት ላይ ልጆቹ ትምህርት ቤት ከሄዱ በኋላ አባቷ ጋር ሄዳ ስለውሳኔዋ ነገረችው።

#ክፍል_አስራአንድ....⓫...ይቀጥላል
──────⊱◈◈◈⊰──────

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

25 Apr, 21:11


​​╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯


. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─

#ክፍል_ዘጠኝ....⓽
⊱◈◈◈⊰──────


ሀዩ የቢሮውን በር ከፍታ ወደውስጥ ገባች። ሉቅማን አንድ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ፊቱን ወደውጪ አዙሮ ቁጭ ብሏል። ፊቱን ወደበሩ አዙሮ ሀዩ መሆኗን ሲያይ በጣም ደነገጠ! ሀዩ ሰላምታ ከሰጠችው በኋላ የእንግዳ መቀበያ ወንበር ላይ ሄዳ ተቀመጠች። ከዛም ስለሁሉም ነገር ነግራው ማግባት እንደማትፈልግና ሌላ ሴት እንዲያገባ ጠየቀችው። ሉቅማን የሰጣት መልስ ግን ጭራሽ ያልጠበቀችው ነበር።


ሀሰኔ በመታከሚያ ክፍሉ ኩርምት ብሎ ተኝቷል። እጁ ላይ ግልኮስ ተደርጎለታል። ምግብ የሚባል ነገር ከቀመሰ ሁለት ቀን ሞላው። ምንም ቢሉት ፣ የምግብና የመጠጥ መዓት ቢደረድሩለትም እሺ ብሎ ሊበላ አልቻለም።

እናትና አባቱም ስለሚያስጨንቀው ነገር ለማወቅ ቀርበው ቢያናግሩትም እሱ ግን አንድም ቃል ሊተነፍስ ፍቃደኛ አልሆነም። በቃ ማልቀስ ፣ ዝምታን መርጧል። የሱ ህመም ፍቅር እንደሆነ ማን በተረዳለት። አዎ እሱ ሀዩን አጥቶ መኖር አይችልም። የመጀመሪያው እንደሆነች ሁላ የመጨረሻውም እንደሆነች ነው የሚያስበው። ልቡን ብቻ ሳይሆን እሱነቱንም በሀዩ ፍቅር ዘግቶታል።

ፍቅር ከሁለቱም ወገን ሆኖ ፣ በሀላል መንገድ ሳይመሰረት ቀርቶ ፣ ከአንዱ ወገን ብቻ ሲመጣ ስቃዩ ብዙ ነው። ለመቀበል መስጠት ግድ ነው። ታድያ ምንም ሳይቀበሉ ሁሌ መስጠት ብቻ ልብን ሊያደማ ይችላል። የሷ ናፍቆት ሁሉ ነገሩን ተቆጣጥሮታል። እሱ ያለሷ ባዶ ነው! ምን ያደርጋል እሷ ግን ይሄን አታውቅም! በሷ ምክንያት እንደታመመ አታውቅም! በሷ ፍቅር እንደሚሰቃይም አታውቅም!


ሉቅማን ሀዩ የምታወራውን ምንም ሳያቋርጣት በጥሞና ካዳመጣት በኋላ እንዲ አላት...
ይሀውልሽ ሀያት እኔ አንቺ እንዳሰብሽው ገንዘብ ወይም ሀብት አለኝ ብዬ አይደለም አንቺን ማግባት የፈለኩት። የእውነት ስለምታስፈልጊኝ ፣ ስለምወድሽ እንጂ.
አንድ ሰው ሽማግሌ ልኮ ላግባ ሲል በገንዘቡ ብቻ እሷን መግዛት እንደሚፈልግ ነው ብዙ ሰው የሚያስበው። እኔን ግን በፍፁም እንደዛ እንዳታስቢኝ። አንቺን በፊትም አውቅሽ ነበር...ሱቅ ስትመጪ ምናምን አይሽ ነበር...ልቤ ከከጀለሽ ቆይቷል፤ ነገር ግን አጋጣሚውን አግኝቼ ልነግርሽ አልቻልኩም። ለዛ ነው አባትሽን አንቺን እንዲድሩልኝ የጠየኳቸው። በእርግጥ መጀመሪያ አንቺን አናግሬ ፍላጎትሽን ልጠይቅሽ ይገባ ነበር። ለዚ ደሞ አውፍ በዩኝ!

ሀያት ላንቺ ያለኝን ፍቅር ለማሳየት የግድ የኔ ሁኚ ብዬ አልጫንሽም። ግን ካገባችኝ እንደዚ አደርግላታለው ያልኩትን ነገር ባታገቢኝም አደርግልሻለው። ለትምህርትሽ ያለሽን ቦታና ወደፊት ትልቅ ደረጃ መድረስ ትፈልጊ እንደነበር አባትሽ ነግረውኛል ፤ ስለዚ ትምህርትሽን እንድትቀጥዪ እፈልጋለው።

እድሜሽን ሙሉ ለውንድምና እህቶችሽ ብለሽ የራስሽን ህይወት እንድታጪም አልፈልግም። እነሱም እኮ ነገ የራሳቸው ሰው ሲመጣ አግብተው አንቺን ጥለውሽ መሄዳቸው አይቀርም ፤ እና ስለራስሽ ህይወት በደንብ አስቢበት!

ስለትዳሩ ደሞ በጣም እንድትጨነቂበት አልፈልግም። የአሁኑን አመት ትምህርትሽን በስርዓቱ ተማሪ። አላህ ብሎ መቀራረባችን ለኔ ስሜት እንዲኖርሽ ካደረገሽ ታገቢኛለሽ። ካልሆነም ግን አልሆነም ነው። እኔ የምፈልገው አካልሽን ሳይሆን ልብሽን ነው!

ሀዩ በመለሰላት መልስ በጣም ደነገጠች። ልክ እሱ እንዳላት ገንዘብ ስላለው ብቻ ሊገዛት የመጣ አድርጋ ነበር ያሰበችው። ግን በተቃራኒው ሆኖ ጠበቃት። ምን እንደምትለው ግራ ገብቷት አንገቷን ደፍታ ቁጭ አለች። ሁለቱም ጋር ለደቂቃዎች ዝምታ ነገሰ።

ሀዩ ምንም መልስ ሳትሰጠው ለመሄድ አስባ ከተቀመጠችበት ስትነሳ አንዲት ሴት የቢሮውን በር ከፍታ ገባች።
ሀቢቤ ምንሆነህ ነው ቅድም ስደውልልህ ስልክ አታነሳም አለች ወደሉቅማን እየተጠጋች። ሁዩ የልጅቷ ማንነት ግራ አጋብቷት ባለችበት ቆመች። ምናልባትም ሉቅማን መጀመሪያ እንዳሰበችው አይነት ወንድ የሆነ መሰላት።

#ክፍል_አስር....⓾...ይቀጥላል
──────⊱◈◈◈⊰──────

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

24 Apr, 21:59


​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━



#ክፍል_ስምንት...⓼
∴━━━✿━━━∴


የሀሰን እናትና አባት የልጃቸውን የህክምና ውጤት ለመስማት ልባቸው ተንጠልጥሏል። ከምንም በላይ የዶክተሩ ፊት ላይ ጥሩ ነገር እያዩ ስላልሆነ በጣም አስፈርቷቸዋል። ዶክተሩ ሁለቱንም በትንሹ ካረጋጋ በኋላ ስለሀሰን የህክምና ውጤት መናገር ጀመረ።

ዶክተር፡ ቢስሚላሂ እንግዲ ስለልጃችሁ እናንተ በደንብ ታውቃላችሁ ብዬ አስባለው...እስኪ ንገሩኝ ልጃቹ የሚያስጨንቀው ነገር ምንድን ነው? መልስ ፍለጋ ሁለቱንም ተራ በተራ አያቸው።

አባት፡ ወይ ዶክተር! እሱን ብናውቅ ኖሮ ምናልባትም ዛሬ እዚ ባልተገኘን ነበር። እሱ ለኛም ጥያቄ ነው።
ሀሰኔ በጣም ዝምተኛ ልጅ ነው። ከኛ ጋር ኖረ እንጂ እኛ ስለሱ ምንም አናውቅም ማለት ይቻላል። ሁሉንም ነገር በሆዱ ነው የሚይዘው። ቢደሰትም ቢከፋም ለኛ አይነግረንም። ከሰዎች ጋር ብዙ አይግባባም። የትምህርት ቤት ጓደኞቹ እነማን እንደሆኑ እንኳን አናውቅም።
ይሄንን ጭምተኝነቱን እንዲተው ብዙ ነገር ሞክረን ነበር፤ ግን እያባሰበት ከመምጣቱ ውጪ ምንም መፍትሄ ማግኘት አልቻልንም።

ዶክተር፡ አዎ ሀቅ ነው...ይሄ በአንዳንድ ልጆች ላይ ይፈጠራል። የሀሰን ጭምት ወይም ዝምተኛ መሆን ተፈጥሮአዊ ባህሪው ነው። በግዳጅ ልናስለውጠው አንችልም። ምናልባት ግን በጣም የሚያስደስተውን ወይም በጣም ማግኘት የሚፈልገውን ነገር ካገኘ ቀስ በቀስ በራሱ ፍላጎት እየተወው ሊመጣ ይችላል። ከዚ ተፈጥራአዊ ባህሪው ሌላ በጣም የሚያስጨንቀው ነገር ግን አለ...

የምርመራ ውጤቱ እንደሚያሳየው ከሆነ ሀሰን የልብ ህመም heart case አለበት። ይሄ ደሞ የመጣው ከፍተኛ በሆነ stress ወይም ጭንቀት ምክንያት ነው። ለዛ ነው ቅድም ምንድን ነው የሚያስጨንቀው ብዬ የጠየኳችሁ። አሁን ያለበት የልብ ህመም ደረጃ ለክፋት ባይሰጠውም የሚያስጨንቀውን ነገር አውቀን ችግሩን ካልፈታንለት ግን ወደፊት ከፍተኛ ደረጃ በመድረስ ሊጎዳው ከዛም በላይ ለሞት ሊያደርሰው ይችላል።

ለ3 ቀን እዚው አልጋ ይዞ ህክምናውን መከታተል ይኖርበታል። አንዳንድ ማስተገሻዎችንም አዘንለታል። እናንተም የምትገዙለት መድሀኒት ይኖራል። ከሁሉም በላይ ግን ለሱ ትልቅ መድሀኒት ሊሆነው የሚችለው ደስታ ነው። ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ደስታ ይፈጥርለታል ብላቹ ያሰባችሁትን ነገር አድርጉለት። እኛ የምንችለውን እናደርጋለን። ሁሉም የሚሆነው አላህ ያለው ስለሆነ እናንተም ጠንከር ብላቹ በዱዓ በርቱ። በተረፈ አብሽሪ

የሀሰን እናት መሬት ላይ ወድቀው ማልቀስ ጀመሩ። እሳቸውን እንደምንም ካረጋጉ በኋላ ሀሰንን የሚያስጨንቀውን ጉዳይ ለማጣራት የቤት ስራ ተቀብለው ወጡ።


ሀዩ በድቅድቅ ጨለማ ብቻዋን ቁጭ ብላለች። እንቅልፍ የሚባል በአይኗ ሳይዞር ለሊቱ ተጋመሰ። ስለቀኑ ጉዳይ እያሰበች ነበር በድንገት ግን አንድ ሀሳብ በሀዩ አዕምሮ ላይ ብልጭ አለ።

<አዎ! አዎ! እንዴት ይሄን አላሰብኩትም ነበር? በቃ ይሄ ነው ምርጥ ሀሳብ ሳታውቀው ጮክ ብላ ማውራት ጀመረች። የደስታ ስሜት ውስጧን ሲያሰክረው ተሰማት። ገና ውጤቱን ሳታውቀው እንዲ የሆነችበትን ምክንያት አላህ ነው የሚያውቀው።

አሁን የመጣላት ሀሳብ ሉቅማንን ራሱ ሄዶ አታግባኝ ማለት ነው። ስላለችበት ህይወት ነግራው፣ ማግባት እንደማትፈልግ ነግራው ለማሳመን። እሱ እሺ ካላት ሁሉም ቀላል ነው። ለአባቷ ሀሳቡን እንደቀየረ ይናገራል እሷም ሰላሟን አግኝታ ወደበፊት ህይወቷ ትመለሳለች። ጠዋት የሱ ህንፃ ነው የተባለበት ቦታ ሄዳ ልታገኘውና ልታዋራው እቅድ ይዛ ተኛች። የከዳት እንቅልፍም ምላሽ ያገኘ ይመስል ጋደም እንዳለች ቶሎ ይዟት ሄደ።

ጠዋት እንደልማዷ ስራዋን በጊዜ ከጨራረሰች በኋላ አባቷ ሲወጡ ጠብቃ ለነፈቲ እቃ ልትገዛ እንደሆነ ነግራቸው ሄደች። አባቷ የሉቅማን
ነው ያላት ህንፃ ጋር እንደደረሰች ጥበቃዎቹን የሉቅማንን ቢሮ ካወቁ በማለት ጠየቀቻቸው። ሙሉ ህንፃው የሱ ስለሆነ እዚ ማንም የማያውቀው ሰው የለም። ጥበቃዎቹ በነገሯት አድራሻ ወደሉቅማን ቢሮ አመራች። የሉቅማን ቢሮ ጋር እንደደረሰች በሩን በቀስታ አንኳኳች።
ይግቡ ... አለ ከውስጥ ያለ አንድ ሰው። እሷም ቀስ ብላ የቢሮውን በር ከፈተችው።

#ክፍል_ዘጠኝ...⓽...ይቀጥላል
◈ ━━━━━━━ ⸙ ━━━━━━━ ◈

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

22 Apr, 04:25


​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ሶፊያ አህመድ

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


#ክፍል_ሰባት...⓻

ሉቅማን ዙሁር ሰላት ሊደርስ አከባቢ ስራ አለኝ ብሎ ሲወጣ አቶ ጀማልም ሊሸኙት አብረውት ወጡ። እነሱ ከሄዱ በኋላ ሀዩ ምንም እንዳልሰማች መስላ ከነፈቲ ጋር መጫወት ጀመረች። ውስጧ እያረረ ጥርሷ ግን ይስቃል። የውስጣችንን ሀዘን ጥርሳችን ባይሸፍነው ምን ይውጠን ነበር?


ሀሰን ከጠዋት ጀምሮ ሶፋ ላይ እንደተጋደመ ነው። ምንም እንኳን የራስ ምታት መድሀኒት ቢወስድም ሊሻለው አልቻለም። ቤተሰቦቹ እንዳይጨነቁ ከላይ ከላይ እንዳላመመው ለማስመሰል ቢሞክርም አልቻለም። ራሱ እንደእሳት ይለበልባል ፣ መተንፈስ እንከሚከብደው ድረስ ልቡ በሀይል ትመታለች ፣ ላብ ሰውነቱን አጥምቆታል...
በመጨረሻም እንደምንም ጨቅጭቀው ሆስፒታል እየወሰዱት ሳለ መንገድ ላይ እራሱን ስቶ ድንገተኛ ክፍል አስገቡት።

ቤተሰቦቹ በሀሰን ነገር እጅግ ተረብሸዋል። አባቱ አንድ አግዳሚ ወንበር ላይ ጭንቅላታን ይዘው ቁጭ ብለዋል። እናቱ እያለቀሱ ወደዚ ወደዛ ይንጎራደዳሉ።

ከሀሰን ጋር አብሮ ከመብላት ፣ አብሮ ከመጠጣት ፣ አብሮ ከመኖር ውጪ ስለሱ ህይወት ምንም ነገር አያውቁም። ምን እንደሚያስደስተው ፣ ምን እንደሚያስከፋው ፣ ጓደኞቹ እነማን እንደሆኑ...ምንም በቃ ምንም!

የሀሰን ከልክ በላይ ጭምት መሆን ትክክለኛ የቤተሰብ ህይወትን እንዳያሳልፉ አደረጋቸው። ዝምተኛነቱን በመቆጣት ሊያስተውት ቢሞክሩም ጭራሽ ሌላ ጭንቀት ውስጥ ስለሚገባባቸው ትተውታል። አንድም ቀን ግን ስለሱ ሳይጨነቁ ፣ ለባህሪው መፍትሄ ሳያፈላልጉ ውለውም አድረውም አያውቁም።


ሀዩ የመጣባትን የህይወት ፈተና ለመጋፈጥ ወስናለች። ቀኑን ሙሉ መፍትሄ ስትፈልግ ቆይታ በመጨረሻም ሁለት የአማራጭ ሀሳቦች ላይ ደርሳለች። የመጀመሪያው ሉቅማንን አግብቶ መኖር ነው። ግን በዚ ህይወት ውስጥ ሀዩ ራሷን ታጣለች። 2 አመት ከራሷ ቀንሳ ዋጋ የከፈለችላቸውን ሁሉ ገደል ታስገባዋለች። ከወንድምና ከእህቶቿ ተነጥላ ለማታውቀውና ለማትወደው ሰው ሚስት ሆና ትኖራለች።

ሁለተኛው አማራጭ ደሞ ወንድምና እህቶቿን ይዛ ከቤት መጥፋት ነው። በዚ ሀሳቧ ላይ ግን ብዙ ጥያቄዎች አሉ። ሀዩ ምንም ዘመድ የላትም። ገንዘብም እንደዛው። ይዛቸው የት ትሄዳለች? ምን ታበላቸዋለች? የት ታኖራቸዋለች? በምን ታስተምራቸዋለች? ይሄ ለሷም ጥያቄ ነው

አባቷ እንዳይድራት ብትጠይቀው ራሷን ከማስቆጣት ውጪ ምንም ምላሽ እንደማታገኝበት ታውቃለች። አባቷ አንዴ ስለወሰኑት ነገር ምንም ቢመጣ ሀሳባቸውን አይቀይሩም። አሁን ደሞ ገንዘብ በደንብ የሚያስፈልጋቸው ጊዜ ነው። ለዛ እሷን ከመዳር ወደኋላ አይሉም። እናም ሁዩም ይሄንን ሀሳቧን አስወጥታ በሁለቱ ሀሳቦች ላይ ለረጅም ሰአት መሟገት ጀመረች። አንድ መወሰን ግድ ነው። ሁለት ወዶ አይሆንም!


አንድ ጠቆር ያለ ዶክተር እጁ ላይ አድርጎት የነበረውን የእጅ ጓንት እያወለቀ ከሁለት ነርሶች ጋር ሀሰን ከሚታከምበት ክፍል ወጣ። እናትና አባቱም እየሮጡ በመሄድ ስለሀሰን ሁኔታ ጠየቁት።

እናት ፡ ዶክተር ሀሰኔ እንዴት ነው በአላህ እንባ አንቋቸው የሚሉትም በደንብ አይሰማም

ዶክተር፡ ይቅርታ እናንተ ለሀሰን ምኑ ናቹ? በግርምት እያየ ጠየቃቸው።

አባት፡ ወላጆቹ ነን ምንድን ነው ዶክተር በአላህ አታስጨንቀን ልጃችን ምን ሆኖ ነው?

ዶክተር፡ ታድያ እንዴት እዚ እድሜ ድረስ ለማንኛውም ውስጥ ገብተን እንነጋገራለን በማለት ወደሱ ቢሮ እንዲሄዱ ጋበዛቸው።

#ክፍል_ስምንት...⓼...ይቀጥላል

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

20 Apr, 06:25


​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


.ክፍልስድስት...⓺
「✿」────❮✿



አባታቸው አቶ ጀማል ወደውስጥ እንደገባ ከኋላው አንድ በወጣቶች የእድሜ ክልል ውስጥ ያለ ፣ የተስተካከለ ቁመትና ሰውነት ያለው ቀላ ያለ ልጅ ተከትሎት ገባ። አልይን አቅፎ ሰላም ካለው በኋላ መርየምን ፣ ፈቲንና ሀዩን በርቀት ሰላምታ ሰቷቸው ከአባትየው አጠገብ ሄዶ ቁጭ አለ።

ሉቅማን ይባላል...እዚ እኛው ሰፈር እኮ ነው ያለው...ወደአስፓልቱ መውጫ ጋር ያለው ትልቅ ህንፃ የሱ ነው...እንዴት ያለ መልካም ሰው መሰላቹ...በማለት አባትየው ስለወጣቱ በአጭሩ ገለፀላቸው።
ስለሉቅማን ሲያወራ በጣም ደስ እያለው ነው። ሉቅማንም ስለሱ ጥሩ ነገር ሲወራ እንደሚሽኮረመም ሰው አንገቱን ደፋ ያደርጋል።

ሀዩና ፈቲ ተነስተው ምግብ ማቀራረብ ጀመሩ። ሉቅማንና አቶ ጀማልም የቀለጠ ወሬ ይዘዋል። ስለንግድ ፣ ስለትዳር እያነሱ ተጫዋወቱ። ምግብ ቀርቦ አንድ ሁለት ከጎረሱ በኋላ ሉቅማን
በጣም ይጣፍጣል ቆንጆ ምግብ ነው...እያለ በቀስታ ወደሀዩ ተመለከተ።
ታድያስ እንዴ ልጄ እኮ ባለሙያ ነው... ሀዩ ናት የሰራችው...በምግብማ አትታማም! የሉቅማንን ትከሻ መታ መታ አደረጉት!

ምግብ በልተው ከጨረሱ በኋላ
በሉ ልጆች ወደጓዳ ገብታቹ ተጫወቱ በቃ ...እኔና ሉቅማን ትንሽ የምንጨዋወተው ነገር አለ... ብሎ ሁሉም እንዲገቡ ነገራቸው። ሀዩም ልጆቹን ይዛ ወደክፍላቸው ገባች።

*

ሀሰን እራሱን አሞት ሶፋ ላይ ተኝቷል። የሀዩን ስልክ በመጠበቅ እንቅልፍን ስለከዳ እየቀጣው ይመስላል።
ሀሰንዬ አሁንስ እንዴት ነህ ትንሽ አልተሻለህም? አለች የሀሰን እናት ልቧ እየተንሰፈሰፈ መጥታ አጠገቡ ቁጭ አለች።
ወይ ካልሆነ ሆስፒታል እንሂድ.. ሰውነቱን በእጇ ስትዳብሰው በጣም ያተኩሳል።
አይ ኡሚ እዚው ብሆን ይሻለኛል... አለመሄዱን ለማረጋገጥ አተኛኘቱን አመቻቸ።
ከትምህት ቤት ደውለው ነበር...አሞት ነው የቀረው ብያቸዋለው...
ሌላስ ምን አሉ?
ምንም...ሌላ ምን ይላሉ ልጄ?
አዲስ ተማሪ ገብቷል አላሉሽም? ሀሳቡ ሁሉ ሀዩ ጋር ስለሆነ እንጂ ከመች ጀምሮ ነው አዲስ ተማሪ ሲገባ ለወላጅ የሚነገረው። እናቱ በግርምት አፍጥጣ ስታየው ነው ምን እንዳላት ትዝ ያለው። ደነገጠ!
በቃ ኡሚ ልተኛ...ብተኛበት ይሻላል..አትጨነቂ አንቺ... ምንም እንዳትጠይቀው ፊቱን አዙሮ እንደሚተኛ ሰው አስመሰለ።

ሰው እንዴት አንድ ሰውን ለረጅም ጊዜ ከዛ ሰው ምንም አይነት የፍቅር ምላሽ ሳያገኝ ሊያፈቅር ይችላል? ያውም በዚ ጊዜ...ትናንት ተዋውቀው ዛሬ የሚጣሉ ሰዎች በበዙበት ዘመን.. ፍቅር ቃሉ ብቻ የቀረ በሚመስል ብዙዎቹ በፍቅር በሚቀልዱበት ዘመን...

ሀሰን እኮ የእውነት አፍቃሪ ነው። እሷን ያፈቀራት ገንዘብ አላት ብሎ ፣ ከሷ ጥቅምን ፈልጎ ወይም እሷ ትወደኛለች ብሎ አይደለም። በቃ ፍቅር የሚባለው ነገር በትክክል በልቡ ስለገባ ነው።
ሀሰን አሁንም ቢሆን ተስፋ አልቆረጠም። ስልኳ ካርድ ስለሌለው ይሆናል ወይም አልተመቻትም ይሆናል እያለ ዛሬም የሀዩን የስልክ ጥሪ እየጠበቀ ነው። ያልደወለችበትን መጥፎ ጎን ጭራሽ ማሰብ አልፈለገም።

*

ሀዩ አባታቸው ውስጥ ግቡ ብሏቸው ብትገባም ተረጋግታ ልትቀመጥ ግን አልቻለችም። ይሄን ያህል ስለምን ሊያወሩ ቢሆን ነው እንድንገባ ያደረጉን? በዛ ላይ ዛሬ ያለወትሮው የአባቷ ሙገሳ ፣ ፈገግታ ብቻ ብዙ ነገር ለየት ብሎባታል።
ልጆቹን ክፍል ካስገባች በኋላ ለሳሎኑ የምግብ መስሪያ ቤቱ ስለሚቀርብ እቃ እንደምታስቀምጥ መስላ ገብታ ጆሮዋን ወደሳሎኑ አስጠግታ ስለምን እንደሚያወሩ መስማት ጀመረች።

አባት፡ እቺት እንግዲ ...ቆንጆዋ የመጀመሪያ ልጄ ሀዩ ማለት እሷ ናት..

ሉቅማን፡ ማሻአላህ ቆንጅዬ ልጅ አለቾት...እና እሷስ ስለነገሩ ታውቃለች?

አባት፡ ኧረ አታውቅም... ዛሬ ጠዋት ነው እንደምትመጣ ብቻ የነገርኳቸው...ግን ልጄ አርቆ አሳቢ ናት...ቀድማ እንደምታስብ አልጠራጠርም...

አሁን ይባስ ለመስማማት ወደግድግዳው ተጠጋች። ስለምን እንደሚያወሩ ምንም ሊመጣላት አልቻለም።

ሉቅማን፡ ያው እንዳልኮት ነው...ካምፓስ እስከምትገባ ድረስ እዚው ሆና መማር ትችላለች...እኔ እሷን ጨምሮ ሁሉንም ልጆች አስተምራለሁ... ይሄ አመት አልቆ 12ተኛ ክፍልን ከጨረሰች በኋላ ግን ከእኔ ጋር እንድትኖር ነው የምፈልገው...

አባት፡ ኧረ ችግር የለውም...ሀያቴን እኔ አንድ ነገር ብያት እንቢ አትለኝም...በዛ ላይ የሚጠቅማትን በደንብ የምታውቅ ልጅ ናት...

አሁን ሁሉም ነገር ገባት። አባቷ ለሉቅማን ሊድራት እንደሆነ...በጣም ደነገጠች። ከወንድምና እህቶቿ ላለመነጠል ብላ ብዙ መስዋትነት ከፍላ ነበር እኮ። አሁንም ቢሆን እሷ ማግባት አትፈልግም።

ሉቅማን፡ እስከዛው ግን አደራዎትን እርሶ ሊጠብቋት ይገባል.. እስከነክብረንፅህናዋ ነው ላገባት የምፈልገው..

አባት፡ ኧረ ሀያቴ ወንድ ራሱ ጭራሽ አታውቅም እኮ...ለዚስ ጭራሽ አታስብ...

ሉቅማን፡ መርሀባ ያው ትምህርት ከተጀመረ ገና 1 ወር እንኳን ስላልሞላው ትምህርቷን አሁን መጀመር ትችላለች...

ሀዩ የምትገባበት ቀዳዳ ጠፋት። የምትይዝ የምትጨብጠውን አጣች። ለማታውቀና ለማትፈልገው ሰው ልትዳር ነው...መቀበል አትፈልግም።
በጭራሽ! በጭራሽ አላገባም! እልህ በተናነቀው የሲቃ ድምፅ ከሷ ውጪ ማንም በማይሰማ መልኩ ዝቅ አርጋ እየደጋገመች ተናገረች።
ያአላህ ስቃዬን አታብዛው...እኔ ደካማ ባርያህ ነኝ...ምንም ነገር ለመጋፈጥ አቅሙ የለኝም..ያ አላህ የልቤን አንተ ነህ የምታውቀው...በማልችለው ነገር አትፈትነኝ...እያለቀሰች እጇን ከፍ አርጋ ስሞታዋን ለአላህ አቀረበች።
ወይ ዱንያ ቀጣይስ ምን ይፈጠር ይሆን? አለች በልቧ ጭራሽ ያልጠበቀችው ነገር በመፈጠሩ ግራ እየተጋባች።

#ክፍል\ሰባት...⓻...ይቀጥላል
✿❯────「✿」─

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

18 Apr, 19:55


​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


#ክፍል_አምስት. . .⓹
❦•⊰❂⊱• ════ ❦


ሀሰን እስከ ምሽት 5 ሰአት ድረስ የሀዩን የስልክ ጥሪ እየጠበቀ የስልኩ ስክሪን ላይ አፍጥጧል። መሀል መሀል ላይ እንቅልፍ እያዳፋው ከስልኩ ጋር ሲጋጭ ብድግ ይልና ፊቱን በውሀ አርሶ መልሶ ይቀመጣል።

የእሷን ስልክ ምን ያህል በጉጉት እየጠበቀ እንደሆነ ብታውቅ ኖሮ ምናልባት ለመደወል ደቂቃዎችን ባላባከነች ነበር። በህይወታችን ምዕራፍ ውስጥ ስለኛ ደስታ ብለው እኛ ሳናውቀው በድብቅ ብዙ ዋጋ የሚከፍሉልን ሰዎች ይኖራሉ። አንዳንዴ ግን እኛ ለነሱ የምንሰጠው ምላሽ በተቃራኒው ሲሆን እጅግ ያማል!

ሀሰን ከሁለት አመት በላይ በሀዩ ፍቅር መሰቃየቱ ፣ በናፍቆት ተቃጥሎ ህመሙን ለሌላ ሰው አለማሰማቱን ከራሱና ከአላህ ውጪ ማንም አያውቀውም። እንደሌሎቹ ወንዶች ፍቅሩን ገልፆ ሀዩን የራሱ ሊያደርጋት የሚችልበት ድፍረት የለውም። ይሄንን ባህሪውንም የተረዳችው ሀዩ ብቻ ነበረች። ግን እሷም ዛሬ ከልቡ እንጂ ከእይታው ጠፍታ ስቃይ ሆናበታለች።

በእያንዳንዱ ዱዓው መሀል አላህን ሁዩን እንዲሰጠው ሳይለምነው ቀርቶ አያውቅም። ፅናቱ ፣ ተስፋ አለመቁረጡ ከምንም በላይ ጀግንነቱን ያሳያል! ሀዩ ጋር ስላለው ስሜት ፈፅሞ አያውቅም፤ ግን እሱ ጋር የሷ ፍቅር ልቡን ሞልቶታል። በቃ ተስፋው አላህና ፍቅሩ ብቻ ናቸው!

በፊት የነበረው ዝምተኝነት ተፈጥሮአዊ ቢሆንም ሀዩን ካጣት በኋላ ግን እየባሰ መምጣቱ ቤተሰቦቹን በጣም አስጨንቋቸዋል። እሱን ለማስደሰት ምንም ነገር ቢያረጉለትም የሱ ባህሪ ግን ሊቀየር አልቻለም። ደስታውን ሀዩ ስትሄድ አብራ ይዛው ሳትሄድ አትቀርም።


ሀዩ እንቅልፍ እንቢ ሲላት ፈቲን ቀስቅሳ ልታማክራት አሰበች። ግን ፈቲ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ስለወሰዳት ልትሰማት አልቻለችም።
ለሀሰን ለትደውልለት ስልኳን ታነሳና መልሳ ደሞ ታስቀምጠዋለች። ለምን መደወል እንደፈራች ግልፅ ነው። በዚ ሰዓት ጊዜዋን መስጠት የምትፈልገው ለቤተሰቦቿ ብቻ ነው። ከዚ በኋላም ሀሳቧን እንዳትቀይር ሀሰን የሰጣትን ደብዳቤ ከነስልክ ቁጥሩ ቀዳዳ ጣለችው። አበቃ!

ጠዋት ሀዩ በጊዜ ስለምትነሳ ሁሉንም ቀስቅሳ የሱብሂን ሰላት በጋራ ሰገዱ። አባታቸው አቶ ጀማል አንድ ስልክ ተወድሎላቸው ለማውራት ወጡ። ልክ አናግረው እንደተመለሱ

<< ሀዩ እስኪ ቤቱን ፏ አድርጉት! ትልቅ እንግዳ እየመጣ ነው... ብሎ ከኪሱ የተወሰነ ብር አውጥቶ ሰጣት።
ማነው እሱ? አለች ከእናቷ ሞት በኋላ እነሱ ቤት ሌላ ሰው መጥቶ ስለማያውቅ ግራ እየተጋባች።
እሱን በኋላ ታዪዋለሽ...ቶሎ በሉ እሱን ይዤው እስከምመጣ ተዘገጃጁ..ደሞ ቆንጆ ሆነሽ ጠብቂኝ! ብሏት እየተጣደፈ ከቤት ወጣ።

ቆንጆ ሆነሽ ጠብቂኝ ያላት ጆሮዋ ውስጥ ገብቶ ቀረ። ይሄን ያህል ማን ሊመጣ ነው ብላ ግራ ተጋባች።
በተሰጣቸው ብር አንዳንድ ነገር ገዝተው ምግብ ማዘገጃጀት ጀመሩ። ቤቱንም አፀዳድተው አሰማመሩት። ስራ እንደጨረሱ ሁሉንም ልጆች አጣጥባ ቆንጆ አደረገቻቸው። 3 ሰአት ላይ አባቷ ደውሎ ሰፈር እንደደረሱና ለባብሳ እንድትጠብቃቸው ነገራት።

ሀዩም የአባቷ ነገር ግራ ቢያጋባትም ቃሉን ማክበር ስላለባት መስተካከል ጀመረች። ከሁለት አመት በኋላ እራሷን ለማሰማመር ፊቷን በመስታወት አየችው። ትንሽ ከመጥቆርና ሰውነቷ ከመቀነሱ ውጪ ልክ እንደትናንቱ በጣም ቆንጆ ናት። ከሁለት አመት በፊት ትምህርት ቤት አንደኛ ስትወጣ እናቷ የገዛችላትን ቀይ ረጅም ቀሚስ ለብሳ እንዳማረባት ለመጠየቅ ወደነፈቲ ጋር ሄደች። ልክ ሳሎን እንደገባች አባቷ
አሰላም አለይኩም ልጆች... እያለ ወደውስጥ ገባ። ሁሉም ለአባታቸው መልስ እንኳን ሳይሰጡት ከሱ በኋላ ያለውን እንደዚ የተካበደለትን እንግዳ ለማየት አይናቸውን ወደበሩ ወረወሩት።

#ክፍል_ስድስት. ⓺. ይቀጥላል
❦ ════ •⊰❂⊱• ════ ❦

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

16 Apr, 21:12


​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


ክፍልአራት...(⓸)
∴━━━✿━━━∴

የሀዩ የልብ ምት በጣም ጨመረ! ካሁን አሁን አየው እያለች መረጋጋት አቃታት። አባቷ በሩን በውስጥ በኩል ከቆለፈ በኋላ ወደቤት ገባ።
<< ኡፍ አልሀምዱሊላህ >> አለች በልቧ። እሱ እንደገባ እየሮጠች ሄዳ ደብዳቤውን አነሳችው።

አሁን ለማንበብ ስለማይመቻት ማታ ልተኛ ስትል ለማንበብ ወስኗ የልብሷ ኪስ ውስጥ ከታው ወደቤት ገባች።

የተኙትን ቀስቅሳ ሁሉንም ከሰበሰበች በኋላ እራት አበላቻቸው። ከነሱ ጋር ቁጭ ብትልም ልቧ ግን እዛ ደብዳቤው ላይ ነው ያለው።በልተው ከጨረሱ በኋላ እቃዎችን አስገባባች። አባቷ ለመተኛት ሲገባ እሷም ወንድምና እህቶቿን ይዛ ወደክፍል ገባች። በዛ ያረጀ ፍራሽ ላይ ሁሉም ጎናቸውን ለማሳረፍ ጋደም አሉ።

<< ዛሬስ የማንን ታሪክ ነው የምትነግሪን?? >> አለ አልይ ሁሌ ሊተኙ ሲሉ የምታውቀውን የነብያቶች ወይም የሰሀባዎችን ታሪክ ስለምትነግራቸው ለመስማት ጓጉቶ።

<< ኢንሻአላህ ዛሬ ታሪክ ሳይሆን የምነግራችሁ ከዚ በፊት ስለነገርኳችሁ ታሪኮች ጥያቄና መልስ ነው የሚኖረን...>> አለች አቀማመጧን እያስተካከለች።
ሁሉም ዝግጁ መሆናቸውን ካረጋገጠች በኋላ ተራ በተራ መጠየቅ ጀመረች...

ሀዩ፡ << ነብያችን ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ የት ተወለዱ? >>

አልይ፡ << መካ >>

ሀዩ፡ << ነብያችን ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ < ምላስ ላይ ቀላል አላህ ጋር ግን ሚዛን ደፊ የሆነ ዚክር > ያሉት ቃል ምንድን ነው? >>

መርየም፡ << ሱብሀነላህ ወቢሀምዲሂ ሱብሀን አላህ አልአዚም >>

ሀዩ፡ << 4ቱ ትልልቅ ኪታቦች እነማን ናቸው? የወረዱትስ ለማን ነበር? >>
ፈቲ፡ << 1) ዘቡር ለዳውድ (ዐ.ሰ)
2) ተውራት ለሙሳ (ዐ.ሰ)
3) ኢንጂል ለኢሳ ( ዐ.ሰ)
4) ቁርዓን ለነብዬ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ)

ሀዩ አንዳንድ ጊዜ ከጠየቀቻቸው በኋላ ልቧ የቅድሙን ደብዳቤ ለማንበብ ስለተንጠለጠለ እንዲተኙ አደረገቻቸው።

ሁሉም እንቅልፍ እንደወሰዳቸው ስታረጋግጥ ደብዳቤውን አውጥታ ማንበብ ጀመረች።

<< አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ... ሰላም ነሽ ሀዩ... ስለናፈቅሽኝ ነበር ላገኝሽ የመጣውት...አንቺም ከናፈኩሽ በዚ ደውዪልኝ...>> ብሎ ከስር ስልክ ቁጥር አስቀምጧል።

ሀዩ አንብባው እንደጨረሰች በጣም ሳቀች። እሷ የጠበቀችው እንደዚ አልነበረም። ለነገሩ ልጁ እኮ ሀሰን ነው። ደብዳቤውን መላኩ ራሱ ለሱ ትልቅ ነገር ነው።

እሷም ሀሰን ናፍቋት እንደነበር የገባት ግን አሁን ነው። ስለሱ ስታስብ ፈገግ ማለት ታበዛለች። አሁንም ሁለት ሀሳብ ውስጥ ገብታ ከራሷ ጋር መከራከር ጀመረች። መደወል ወይም አለመደወል...

<< ደውዪለት ሀዩ...ሀሰን እኮ ወንድምሽ ነው... ይሄ ሁላ ጊዜ ሳታገኚው አልናፈቀሽም? ደሞ አንቺን ብሎ መጥቶ ...ደውዪና አግኚው ሀዩ..>>

<< ከዛስ ደውለሽለትስ? ልታወሩ? ከዛስ አውራቹ? ከዛ ያላቹ ግንኙነት ወደየት ሊሄድ ነው? አንቺ አሁን ከወንድ ጋር የምትጃጃዪበት ጊዜ አይደለም.. ትምህርት እንኳን ያቆምሽው ለነሱ ብለሽ ነው.. አሁንም ከነሱ ውጪ ምንም ነገር ማሰብ የለብሽም! >>

ውስጧ ለሁለት የተከፈለ ያህል በተቃራኒ ሀሳቦች መሟገቱን ቀጠለ...ሀዩ የምትወስነው ነገር ግራ ገባት። ብታገኘው ደስ እንደሚላት ብታውቅም እሱን ማግኘቷ ግን አሁን ካለችበት መንገድ እንዳያሰናክላትም ፈርታለች

በዚ ጊዜ ፍቅር ፣ ትዳር ለሀዩ ትርጉም የለውም። ሁሉ ነገሮቿ ወንድምና እህቶቿ ናቸው። ለነሱ ስትል የራሷን ህይወት ሰውታለች።
ከረጅም ሰአት ክርክር በኋላ አንዱን ለማድረግ ወሰነች።

#ክፍል\አምስት..⓹...ይቀጥላል
❯────────────

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

15 Apr, 11:54


​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


.#ክፍል_ሶስት...( ⓷ )
┗•━•━•━ ◎ ━•━•━•┛

ሀዩ መወሰን አቅቷት ለረጅም ደቂቃ በሩ ላይ ቆማ ማሰብ ጀመረች። ሀሰን አንገቱን እንደደፋ የግቢውን በር ማንኳኳት ቀጥሏል። በውስጡ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ሲመጣ በዛው ልክ የግቢውንም በር በቀስታ ማንኳኳት ጀመረ። በመጨረሻም በሩ እንደማይከፈት ስላሰበ አንድ ደብዳቤ በበሩ ስር ከቶ ሄደ።ሀዩ ግን ያንን ደብዳቤ አላየችውም ነበር።

ሀሰን ሳያገኛት በመመለሱ በጣም ከፋው። ከቤት ሲወጣ ምን ብሎ እንደሚያናግራት ተለማምዶ ነበር የወጣው። የሀዩ ናፍቆት አላስችል ብሎት ነበር የመጣው ግን አልተሳካም።

<< ሀዩ ማን መጥቶ ነው ቆየሽ እኮ..>> አለች ፈቲያ ከቤት እየወጣች።
<< አይ መጣው ፈቲ ግቢ መጣው...>>

ሀሰን መሄዱን ካረጋገጠች በኋላ ወደቤት ገባች። ሀሰንን ማግኘት ፈልጋ የነበረ ቢሆንም ለሚጠይቃት ጥያቄ ግን በቂ ምላሽ እንደማታገኝ ስላወቀች ጨከነችበት።

እንደተከዘች ወደሳሎን ሄዳ ቁጭ አለች። ፈቲ ትንሽ አሟት ስለነበር ለመተኛት ወደመኝታ ስትሄድ ሁዩም ባለችበት ቁጭ ብላ የድሮ ትውስታዎቿን ታውጠነጥን ጀመር።

የመጀመሪያ ቀን ከሀሰን ጋር የተግባቡት አማርኛ የቡድን ስራ ተሰቷቸው እሷና ሀሰን እንዲሁም ሌሎች ልጆች በጋራ ሲሰሩ ነበር። ታድያ ያኔ ሀሰን በጣም አስቸግሯት ነበር። እያስረዳች እንደገባቸው ለማረጋገጥ ሁሉንም በተራ ስትጠይቅ ሀሰን ግን አንገቱን ደፍቶ ቁጭ ከማለት ውጪ ምንም መልስ አይሰጣትም። ያኔ በጣም ተናዳበት << ግሩፕ ውስጥ ምንም እየሰራ አይደለም ብዬ ነው ለመምህሩ የምነግረው >> ብላ ስታስፈራራው ነበር ለምኖ ያስተዋትና ስለራሱ በደንብ የነገራት።

ሀሰን ሌሎች ሴቶችን ቀና ብሎ የማያይ ልጅ ያኔ ለሷ ስለህይወቱ መናገሩ ለራሱም ጥያቄ ሆኖበት ነበር። በዛ ተዋውቀው ጥሩ የእህትና ወንድም ትስስር ፈጠሩ። ሀዩ በትንሹም ቢሆን ከሰዎች ጋር እንዲግባባ አደረገችው።

ስለሀሰን መቼም የማትረሳው ነገር ሌሎች ወንዶች ሊያዋሩአት ፈልገው እሷ ጋር ሲመጡ << አስተማሪ እየጠራሽ ነው >> እያለ ከልጆቹ የሚለያት ነገር ነው። ሀሳቡ እውነት ይመስል ፈገግ አለች።



ሀሰን ቤት ከገባ በኋላ ምንም አርፎ መቀመጥ አልቻለም። ትምህርት ቤት አትመጣም፣ ስልክ አይደውልላት ነገር ስልኳ የለውም። እሷን የማግኛ የመጨረሻ እድሉ ቤቷ መሄድ ነበር እሱም አልተሳካም።

<< ቆይ ለምንድን ነው የምትናፍቀኝ? ከመች ጀምሮ ነው እኔ ስለሴት ማሰብ የጀመርኩት? ጭራሽ የሴት ቤት እስከመሄድ ድረስ? ፍቅር ማለት ይሄ ነው እንዴ? ወድጃት ነው እንዴ? >> እራሱን በጥያቆዎች ማፋጠጥ ጀመረ።

እሱም በተራው የመኝታ ክፍሉ አልጋ ላይ ጋደም ብሎ ከሷ ጋር የነበረውን የማይረሳ ትውስታ በማሰብ በሀሳብ ጭልጥ አለ።
አንድ ጊዜ ትምህርት ቤት ውስጥ ሀዩ ተደብቃ ስትሰግድ ሀሰን ያያታል። የትምህርት ቤቱ ባለቤቶች ሙስሊም ስላልነበሩ እዛ መስገድን አይፈቅዱም። እሱ ብዙ ጊዜ ብቻውን መሆን ስለሚፈልግ አንድ ባዶ ክፍል ለመቀመጥ ሲሄድ ነበር ክፍል ውስጥ ጥግ ላይ ስትሰግድ ያያት።

ለሀይማኖቷ ያላት ጥንካሬ ፣ ድፍረቷ ፣ ጀግንነቷ ቀልቡ ውስጥ የገባው ከዛ ቀን ጀምሮ ነው። ሀዩ ለሱ ከሌሎች ሴቶች ትለይበታለች። ታድያ ምንም ያህል ወዷት ቢሆን እንኳን ያንን ጊዜ ሁሉ ፍቅሩን አልገለፀላትም ነበር። 2 አመት ሙሉ በናፍቆቷ ሲቃጠል ፣ ከዛሬ ነገ ትመጣለች እያለ ሲጠብቅ እሷ ግን የውሀ ሽታ ሆና ቀረችበት። እስካሁንም ልቡን ለሷ ዘግቶ እሷን እየጠበቃት ነው።



አመሻሹ ላይ የነሀዩ አባት ወደቤት መጣ። ለሱ በሩን ለመክፈት ልትሄድ ስትል አልይ ቀድሟት እሮጦ ከፈተለት። ልክ አባቷ እግሩን ወደግቢው ሲያስገባ ነበር ደብዳቤውን መሬት ላይ ያየችው። ቅድም ሀሰን መጥቶ ስለነበር ከሱ እንደሆነ ለማወቅ ጊዜ አልፈጀባትም።

በጣም ደነገጠች! አባቷ እግሩ ያለው ደብዳቤው ጋር ነው። ጎንበስ ካለ ማየቱ የማይቀር ነው። አየው ማለት ደሞ ለሀዩ ጥሩ አይመጣም። ልቧ በሀይለኛው መምታት ጀመረ!
<< ያረቢ ደብዳቤውን እንዳያየው አይኑን ሸፍንልኝ ! >> እያለች በልቧ ዱዓ ማድረግ ጀመረች።
ቅድም እንዴት እንዳላየችው ግራ ገብቷታል። ብቻ ግን አባቷ ይሄን ሰሞን አሪፍ ሁኔታ ላይ ስለሌለ ደብዳቤው ምንም ይሁን ምንም ከወንድ እንደተላከ ካወቀ ሁዩን እንዲው አይተዋትም።
አባቷ የግቢውን በር አልፎ ወደውስጥ ገባ....

ክፍልአራት..⓸ ይቀጥላል....
┍──━──━──┙◆┕──━──━──

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

14 Apr, 20:50


...┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ ).
.╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝

በ @tibebislam_nw የቀረበ
ልብ አንጠልጣይ ታሪክ

ክፍል ሁለት (❷)
❃•❃ ════ ❁

አይኑን ወደአንድ ቦታ ተክሎ እየተመለከተ ይንሰቀሰቅ ጀመር። ምክንያቱን ባታውቀውም የሱ ለቅሶ ተጋብቶባት አብራው አለቀሰች። ምላሹን እየፈለገች አይኗን የአልይ አይን ላይ አንከራተተች። ትንሽ ካለቀሰ በኋላ
<< እማ...እማ ናፈቀችኝ! >> አለ እንባ በተናነቀው ድምፅ።

ሀዩ አሁን ይባስ ደነገጠች።
<< እንዴት ዛሬ ትዝ አለችህ ? >> የሷን ስሜት እሱም መጋራቱ አስገርሟታል።
<< በህልሜ አየዋት ..>> አለ። አሁንም ለቅሶውን አላቆመም። እልቅሻው ልቧን ነካው። የታደፈነውን ቁስሏን ሲነካው ተሰማት። አቅፋ ወደራሳ ካስጠጋችው በኋላ አብራው አነባች።

ዛሬ ውሎዋ በትዝታ ጀመረ። አልይን ካረጋጋችው በኋላ ሱብሂ ሰላትን ለመስገድ ስትነሳ እሱም አብሯት ተነሳ። ከሰላት በፊት የሚደረገውን ትጥበት ( ኦዱ ) አብረው ካደረጉ በኋላ አንድ ላይ ሰገዱ። እሱም ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ሰላት ውስጥ ስለሚባለው ነገር በትንሹም ቢሆን ያውቃል። አብሯት ጎንበስ ቀና እያለ የሱብሂን ሰላት ሰግደው ጨረሱ።

በስስት አይን እያየች ግንባሩን ሳመችው። ነገ እሱ ከፊት ሆኖ እንደሚያሰግዳት ታምናለች። ቁርስ ለማዘጋጀት ኩሽና ውስጥ ጉድ ጉድ ስትል እሱም ከኋላ ቀሚሷን ይዞ ይከተላታል። አልፎ አልፎ እቃ ያቀብላታል። አልይ ለሀያት ልዩ ፍቅር አለው። እሷም ልክ እንደእናት ሆና ነው የምታሳድገው።

ወፎች መንጫጫት ፣ ጎህ መቅደድ ሲጀምር የሀዩ ታናናሽ እህቶቿና አባቷ ከእንቅልፋቸው ተነሱ። መርየምና አባቷ ለመስገድ ሲሄዱ ፈቲያ ወደሀዩ ጋር መጣች።

<< ምነው አትሰግጂም እንዴ ፈቲ..>> አለቻት። ስራ ልታግዛት የመጣች ስለመሰላት...
<< አይ ሰላት የለኝም እህቴ ...>> አለች በሀፍረት አንገቷን እየደፋች። ሰላት የላኝም ማለት ሀይድ ላይ ወይም የወርአበባ ላይ ናት ማለት ነው። በዚ ጊዜ ሰላት ሰለማይሰግዱ
<< ሰላት የለኝም >> በሚለው ቋንቋ ነው የሚግባቡት። አሪፍ መግባቢያ ነው...

ከፈቲያ ጋር ሆነው ቆንጆ ቁርስ ካዘጋጁ በኋላ ተሰብስበው በሉ። ሀዩ አልይን እያጎረሰችው ለራሷ አልበላችም ማለት ይቻላል። እነሱ ሲጠግቡ ነው እሷም የምትጠግበው። አጁብ ፍቅር!

አባታቸው እንደልማዱ ትንሽ ገንዘብ አስቀምጦላቸው ወጣ። ዛሬ እሁድ ነው። ትምህርት ስለሌለ ከምትወዳቸው ወንድምና እህቶቿ ጋር ቀኑን ስለምታሳልፍ ደስ ብሏታል። ከፈቲያ ጋር እስከ 4 ሰአት ድረስ የቤቱን ስራ ሰርተው ጨረሱ። ከዛ ሰብሰብ ብለው ቁጭ አሉ። ቆንጆ ጊዜ ለማሳለፍ...

ልክ እንደሌላው ቀን መጀመሪያ የሁሉንም ደብተር check ካደረገችላቸው በኋላ የቤት ስራቸውን አሰራቻቸው። የዛሬን አያርገውና ያኔ ተማሪ እያለች ክፍል ውስጥ የሚፎካከራት ተማሪ አልነበረም። ታድያ ወንድምና እህቶቿም ከዲናቸው ቀጥሎ በትምህርታቸውም ቀልድ እንዳያውቁ አድርጋ ነው እያነፀቻቸው ያለችው።

የቤት ስራቸውን ከጨረሱ በኋላ የተለያዩ ጨዋታዎችን በመጫወት ጊዜውን ማሳለፍ ጀመሩ።

ፍቅራቸው በጣም ያስቀናል። ሀዩ እነሱን ለማሳቅ ፣ ለማዝናናት የምታደርጋቸው ነገሮች ለነሱ ያላት ፍቅር ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ አንዱ ማሳያ ነው። ሀዩ ለነሱ እንጂ ለራሷ እንደማትኖር በአንድ ቀን ያያት ሰው ራሱ መገመት ይችላል።

ከዙሁር ሰላት በኋላ 8 ሰአት አከባቢ ሀዩ አልይንና መርየምን አስተኝታ ከፈቲያ ጋር ቁጭ ብላ እየተጨዋወተች ባለችበት ሰአት የቤታቸው የግቢ በር ተንኳኳ። ሀዩም በሩን ለመክፈት ተነስታ ወጣች። የግቢው በር ጋር ደርሳ ከውስጥ ወደውጪ በሚያሳይ ትንሽዬ ቀዳዳ የሰውዬውን ማንነት ለማወቅ አጮለቀች።

ሀሰን ነበር በሩን እያንኳኳ ያለው። ሀሰን ማለት ትምህርት ቤት እያለች እንደወንድም ትቀርበው የነበረ ልጅ ነው። ሀሰን በጣም ዝምተኛና ከሰዎች ጋር ብዙ የማይቀራረብ አይነት ልጅ ነው። ከሀዩ ጋርም አንድ ጊዜ አማርኛ መምህራቸው በሰጣቸው የቡድን ስራ ምክንያት ነው መግባባት የቻሉት። ሀሰን አይደለም እንደዛሬ ሴት ቤት ሊመጣ ቀርቶ ሴት እንኳን ቀና ብሎ ለማየት በጣም የሚያፍር ልጅ ነበር።

ዛሬ ግን ሀዩን ፍለጋ ቤቷ መጥቷል። ምናልባት ከትምህርት ቤት መቅረቷ አሳስቦት ይሆናል። ሀዩ ልክ ስታየው በጣም ደነገጠች። ከተማሪዎች ጋር መገናኘት አትፈልግም። ደሞ እንደወንድም የምትቀርበው ሀሰን የሷ መቅረት አስጨንቆት እፍረቱን ለሷ ሰውቶ ሊጠይቃት በመምጣቱ አሳዘናት። ልክፈት ወይስ አልከፈት በሚል ሁለት አሳብ ውስጥ ገብታ መታገል ጀመረች።

#ክፍል_ሶስት..⓷.....ይቀጥላል....

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

13 Apr, 20:33


​​ .┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ ).
.╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝

በ @tibebislam_nw የቀረበ
ልብ አንጠልጣይ ታሪክ

ክፍል አንድ ( ⓵ )
❃•❃ ════ ❁

ሀዩ በትዝታ ማዕበል ውስጥ ሰምጣ በአሮጌው የእንጨት መስኮታቸው በኩል አሻግራ ወደውጪ ትመለከታለች። የእናቷ ነገር ትዝ ቢላት፣ የናፍቆት ጅራፍ ክፉኛ ቢወግራት ከነዛ ውብ ክብ አይኖቿ መሀል የእንባ ዘለላዎች መንጠባጠብ ጀመሩ። ትናንት ልክ እንደዛሬ ሳይሆን በፊት ጠዋት 12 ሰአት ላይ ከእናቷ ቀድማ ተነስታ ኩሽና ውስጥ ትንጎዳጎድ ነበር። ትናንት እናቷ በስራ እንዳትደክም በደንብ ታግዛት ነበር። ትናንት በዚ መስኮት አሻግራ ስትመለከት እናቷ ከኋላ መጥታ ትኮረኩራትና እየተሳሳቁ ይጫወቱ ነበር።

ግን ትናንት ነው። ነበር ተብሎ የሚወራ ከልብ እንጂ ከእይታ የጠፋ ታሪክ። የማይመለስ ትውስታ... ሀያት ገና 16 አመቷ እያለች ነበር እናቷ ወደአኼራ የሄደችው። ከ3 ታናናሽ ውንድምና እህቶቿ እንዲሁም ከአባቷ ጋር ጥላቸው ላትመለስ ካሸለበች ድፍን ሁለት አመት ተቆጠረ።

ይሀው ዛሬም የሱብሂ ሰላትን ለመስገድና በዛውም የቤት ውስጥ ስራዎችን በጊዜ ለመጀመር ስትነሳ የእናቷ ትዝታ ገረፍ አርጓት ነው ከዚ መስኮት የከተመችው። ድምፅዋ እንዳይሰማ እጇን በአፏ ይዛ ተነሰቀሰቀች!!

እናቷ ሰፈር ውስጥ በጣም ተግባቢ ፣ ሁሉም ሰው የሚወዳትና ለሰዎች በጣም አዛኝ ሴት ነበረች። በእናቷ ምክንያት ሀዩም ሰፈር ውስጥ ብዙ ሰው ያውቃታል። ታድያ እናቷን የሚያውቁ ሁላ እሷ ከሞተች ውዲ ትምህርት ቤት አለመሄዷና ቤት ውስጥ እንደሰራተኛ ሆኗ መቀመጧ ያሳሰባቸው ይመስላል። ለዚም ነው ሁሉም << አግቢ አግቢ >> እያሉ የሚጨቀጭቋት። << ሀብታም ወንድ አግብተሽ ታናናሾችሽንም ትረጃለሽ >> ይሏታል። እሷ ግን << እነሱን ጥዬ የትም አልሄድም።የኔ ህልም እናቴ የሰጠችኝን አማና ( አደራ ) መወጣት፣ ታናናሾቼን አስተምሬ ለወግ ለማዕረግ ማብቃት ነው! የኔ ቀስ ብሎ ይደርሳል።>> ብላ አሻፈረኝ ብላለች።

አባቷ አይደለም ዛሬ ሚስቱ ሞታ ድሮውንም ፀባዩ አስቸጋሪ ነበር። ግን ቢያንስ እሷ ስትኖር አደብ ይገዛ ነበር። አሁን ግን በሷ ሞት አሳቦ ቤተሰቡን ከረሳ ሰንበትበት ብሏል። አዎ ጠዋት ወጥቶ ማታ ከመመለስና አልፎ አልፎ ለአስቤዛ ብሎ ከሚሰጣቸው ጥቂት ገንዘብ ውጪ እንደድሮ ለነሱ መሳሳቱ ፣ አብሮ መጫወቱ ፣ ሁሉም ቀርቷል። የአባትነትን ፍቅር ያኔ እናታቸው ስትቀበር አብሮ ተቀብሯል።

ሀያትም ከቀን ወደ ቀን ውበቷ እየቀነሰ ፣ ሰውነቷ እየመነመነና ተስፋዋ እየተሟጠጠ መቷል። የሰዎች << አግቢ >> የሚለው ጭቅጨቃና የጓደኞቿ << ለምን ትምህርት ቤት አትመጪም? >> የሚሉ ጥያቄዎች ስለሰለቿት ከሰዎች እራቃ ከታናናሾቿ ጋር ብቻ ማሰላፍ ጀምራለች።

<< ሀዩ..ሀዩ...>> አለ የ7 አመቱና የቤቱ የመጨረሻው ልጅ አልይ... ከእንቅልፉ ቀድሞ መነሳት ልማዱ ነው። እጁንና እግሩን ለማፍታታት እየተንጠራራ ከታኛበት ፍራሽ ብድግ አለ።

ፊቷ ላይ እየተንሸራተተ ወደመሬት የሚወርደውን እንባ አይቶ እንዳይረበሽ በማለት እንባውን ከአይኗ ጠራርጋ ወደአልይ ጋር ዞረች። መሬት ላይ የተነጠፉ ሁለት ያረጁ ፍራሾች ይስተዋላሉ። በአንዱ አልይና በቅርቡ 11 አመቷን የያዘችው ታናሽ እህቷ መርየም ተኝተውበታል። በአንዱ ፍራሽ ላይ ደሞ እሷን በደንብ የምትቀርባት ፣ በእድሜም ከእሷ በ2 አመት ብቻ የምታንሰው ሌላኛዋ ትናሽ እህቷ ፈቲያ ተኝታለች።

<< አባቴ ተነሳህ እንዴ?? >> እያለች ወደ አልይ ጋር ሄደች። አጠገቡ ሄዳ እንደተቀመጠች አልይ ማልቀስ ጀመረ። ሀያት በጣም ደነገጠች። አሁን ሲጠራት እኮ ምንም አልሆነም ነበር። አልይ ሲያለቅስ የሷ ውስጥ አብሮ ያለቅሳል። ታናናሾቿ አንድ ቀንም ቢሆን እንዲከፉና እንዲያዝኑ አትፈልግም። ለዛ ነው ይሄን ሁላ መስዋትነት ከፍላ ፣ ከጓደኞቿ በታች ሆና እየኖረች ያለችው።

<< ምነው አባቴ ምን ሆንክብኝ? >> አለች ከአይኑ የሚፈሱትን የሚያሳሱ እንባዎችን በእጇ እየጠረገች።

#ክፍል_❷....ይቀጥላል....

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

09 Apr, 10:56


#ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ


#ክፍል10_የመጨረሻው_ክፍል


አብዱ ከክፍሉ ይዞኝ ወጣና ቦታዬ አስቀምጦኝ ቤቱን ለቆ ወጣ ጀማል መጣና ይዞኝ ወጣ ሰርግ ቤት ሳይሆን ለቅሶ ቤት ነበር የሚመስለው አባም እማም መጡ አይኔን ግን አላዩም ነበር በስራቸው ተፀፅተው ይመስለኛል እያለቀሱ ከቤት ወጣን።

እነሱ ቤት ስንደርስም ሰው በሽ ነው ምንም የቀረ ነገር የለም የታሰበበት ነው የሚመስለው።እኔ ግን ምንም ፊቴ አልተፈታም ተበላ ተጨፈረ ይዞኝ ወደራሱ ቤት አቀናን የኔ ሚዜዎች የለበስከለትን ቬሎ ቀያይረዉልኝ ሄዱ። ሽማግሌ ከተላከበት ቀን አንስቶ እስአ አሁን እንቅልፍ የሚባል አልተኛሁም አልጋው ላይ በተቀመጥኩበት እንቅልፍ ሸለብ አደረገኝ ትንሽ እንደተኛው ነቃ ስል አጠገቤ ጀማል ተቀምጧል ወደኔ ጠጋ ሲል አበድኩ ምን ያላልኩትት ነገር አለ ክፍሉን ለቆ እንዲወጣ ነገርኩት ምንም አላለኝም ወጣ በሩን ከዉስጥ ቆልፌ የሆንኩትን እያስታወስኩ አነባው ከማልቀሴ የተነሳ ፊቴ ፍም መስሏል ራስ ምታት ሊለቀኝ አልቻለም በዛው እንቅልፍ ወሰደኝ.......በማግስቱም ተመሳሳይ ነገር ነበር የተፈጠረው።

በ ሶስተኛው ቀን መልስ ተጠራን በጣም ነበር ደስ ያለኝ እንደዛ ቀን የተደሰትኩበትን ቀን ሁላ አላስታውስም ወላሂ...መልስ ሲባል ያሰብኩት መመለሴን እቤት የምቀር ነገር ነበር ግን አይደለም ሄድን አሪፍ ዝግጅት አድርገው ነበር። 5 ሰአት አካባቢ የተሰጠኝን ስጦታ ጭነን መጣን ትዳር ሲባል የራስን ስሜት ማዳመጥ ብቻ አይደለም የባል ሀቅ የሚባለውም ነገር አለ ምንም ማድረግ አልችልም ላያስችል አይሰጥም አይደል የሚባለው..ወላሂ በዛን ሰአት ጀማልን ቀና ብዬ ሳየው ራሱ ይቀፈኛል ራሴን ጠላዋለው ቢሆንም ግን ምንም አማራጭ አልነበረኝም ቢጃማዬን ቀይሬ አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ እንዳልኩ ጀማል መጣ ሰውነቴን እንደ እሾህ ይወጋኝ ጀመር ከዛን ሰአት በኋላ ምን ይፈጠር ምን ልሁን የማውቀው ታሪክ የለም ብቻ ስነቃ ያስተዋልኩት ማማ ግርግዳውን ተደግፋ ታለቅሳለች ሳሎን ላይ ተዘርሬ ብርድ ልብስ አልብሰውኛል ሁለት ሼኽዎች በግራና በቀኝ ቁርአን ይቀሩብኛል ዙሪያዬ በቤተሰቦቼ ተከብቤያለሁ።.....ከዛን ጊዜ በኋላ ተለከፍኩ ጊዜ እየጠበቀ ህመሜ ይነሳብኛል ቁርአንም ቤት እመላለሳለው።

አንድ ቀን እንደ ወትሮ ቁርአን ሲቀራብኝ እለፈልፍ ጀመር ለካስ የዚ ሁሉ መንስኤ ሀምዛ እና እናቱ ነበሩ ሱብሀንአላህ😔 እኔ በህይወቴ በትዳሬ ደስተኛ እንዳልሆን አስደግመውብኛል ወላሂ ይሄንን ሳውቅ ሀምዛን ከልቤ እርግፍ አድርጌ አወጥቼ ጣልኩት ሀምዛንኮ ሌላ ባገባ ብወልድ ራሱ አልረሳውም ነበር...ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ በህይወቴ ምንም ደስታ አልነበረኝም 2 ልጆች አሉኝ ደስታዬ ግን አልነበረም አልሀምዱሊላህ ይሄን ስራቸውን ካወኩኝ በኋላ ቁርአንም መከታተል ስቀጥል ደስታ ወደ ቤቴ ገባ። ጀማል ይሄን ሁሉ ታገሰኝ ሁሌ ያዘነች ሚስት ቤት ውስጥ እያየ ሁሌ ያኮረፈች ሴት እያየ ኖሯል ሆኖም ግን አንድ ቀን እንዲህ ሆኜ ብሎኝ አያውቅም ታገሰኝ ይህንን ሳስብ እሱን ይበልጥ እንድወደውና እንዳከብረው አደረገኝ።

አልሀምዱሊላህ ከዛን ጊዜ በኋላ ደስተኛ ነኝ አሁን ላይ ትምህርቴን ጨርሼ ተመርቄ በተመረኩበት ሞያ ላይ እየሠራው ነው ሶስተኛ ልጄን ወልጃለው ለሁሉም ግን አልሀምዱሊላህ...........


#ተፈፀመ....

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

06 Apr, 20:59


#ኢማን

#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ


#ክፍል9

ወደ 7 ሰአት ገደማ ሰርገኛ መጣ በእልልታም ተቀበሉት። ምሳ ተበላ ተጨፈረ ኒካም ታሰረ ብናይ አይወጡም ብናይ አይወጡም። የሆነ የሰፈር ህፃን ልጅ መጣና በጆሮዬ " ልክ ቀለበቱን እጅሽ ላይ ሲያጠልቅ እኔን ከልብሽ አውጥተሽ አትጣይኝ ሁሌም አኑሪኝ" የሚል ከ ሀምዛ የተላከ መልእክት ነበር ውስጤ ተረበሸ ግራ ገባኝ እያለቀስኩ ሳለ የ አባ ወንድም አጎቴ መጣ
"እ ኢሙ ተበላ ተጠጣ መዝናኛ እንሂድ እየተባለ ነው ፎቶ ተነስታቹ አመሻሽ ላይ ትመለሳላቹ" ምን ትዝ አለኝ አንዷን ጓደኛችን እንዲህ ብለው ማይሆን ነገር ሰርተዋታል ማለት ወሰዷት እቤታቸው የሷ በቤተሰብ ቢሆንም ወዳዋለች ግን እኔስ?? ሃሃሃሃ በጣም ትሸውዱ የለም እንዴ በል ንገራቸው እንዳልተስማማው
"አረ እንደሱ አያደርጉም ካደረጉማ 20,000 አስይዘናል ይቀጣሉ" ታድያ ለኔ ምን ያደርግልኛል ከሄድኩ በኋላ እናንተ ትበሉበታላቹ ትጠጡበታላቹ በቃ🤷‍♀ ሲያቅተው አብዱን ጠራው ያው ቀረቤታዬም ከሱ ጋር ስለሆነ ምንም ቢለኝም አምነዋለዋ።
እ አብዱ የሚለው እውነቱን ነው?
"አዎ እውነቱን ነው" አለኝ አይ እንደሱ ከሆነማ እሺ ብዬ ስነሳ ዘወር ብሎ በምልክት እንቢ በይ አለኝ አረ አልፈልግም አልሄድም አልኩ ድጋሜ አጎት ተብዬው ተናዶብኛል ከፈለጋቹ እነሱ ከሄዱ በኋላ እኛ ሄደን እንዝናናለን አልኩት።

እንደዚህ እየተከራከርን 12 ሰአት ሆነ እነ ሀምዛ ቤት ተረብሸዋል ይሄ ነገር የምር እዚህ የሚደርስ አልመሰላቸውም ነበር ማዘርየው አልመጡም መረጃ የሚያመላልስ አለ ከኔ ወደነሱ ከነሱ ወደ እኔ መጨረሻ ላይ ጀማልን ጥሩልኝ ብዬ መጣ።
ቆይ ግን ያምሀል ምን ብላቹ ነበር መጀመሪያ እእእእ
"አንቺ ራሱ ምንድነው የምትይው እኔ ትምህርትሽን ስትጨርሺ እና የማስተካክላቸው ነገሮች አሉ ስጨርስ ብዬሽ አልነበር በአንዴው ምን ተለውጦ ነው ካልወሰድከኝ የምትይው"??
በጣም ደነገጥኩ ምን እንደሚያወራ ራሱ ግራ ገብቶኛል በሰአቱ ለካ ይሄን ሁሉ የሚጠነስሱት የኔ አጎት እና የሱ አባት ነበሩ። አባ እና እማ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም የሱ አባት ልጅቷን ይዘን ካልሄድን ከዚህ ንቅንቅ አንልም አሉ አማም አባም ግራ ተጋብተዋል እኔን ተነሽ ሂጂ እንዳይሉ እጎዳባቸዋለው የመጣውንስ ሽማግሌ እንግዳውን ምን ብለው ተነስታቹ ውጡ ይላሉ? ተያይዘው ወጥተው መስጊድ ሄደው ማልቀስ ጀመሩ። ህዝብም ደሞ መጨረሻውን ሳናይ ንቅንቅ አንልም ብለዋል መሰለኝ የሚወጣም የለም በቆሙበት እርስ በእርሳቸው ይንሾካሸካሉ ትወጣለች አትወጣም የሚለውን በመሀል አባን ጥሩልኝ ስል ነው እንደሌሉ ያስተዋልኩት
ቆይ በአላህ ከኔ ከልጃቸው ሽማግሌ በልጦባቸው ነው የሸሹት? እ ለምንድነው መተው ማያባርሩልኝ ሁሉም እኔን እያየ የሚያለቅስ እንጂ ምንም የሚለኝ ጠፋ።

ማንም ከጎኔ ሊቆም አልቻለም ነበር መጨረሻ ላይ ተሸነፍኩ የተሸነፍኩትም አብዱ መጣና ይዞኝ ባዶ ክፍል ገብተን እንዲህ አለኝ
"በቃ ኢሙ አልቻልኩም ወላሂ ብዙ ጣርኩ አቃተኝ ከዚህ በላይ ምን ላርግልሽ እእ "ስቅስቅ እያለ ነበር የሚያለቅሰው
በቃ አብዱ አንተም ተሸነፍክ ምንም ተስፋ የለኝም ማለት ነው ከጎቴ በሩን እየቀጠቀጠ አንተ ነህ ልጅቷን የምትመክራት ተዋት ትሂድበት ይለዋል
"ኢሙ ሰማሽ አይደል ሁሉም እኔን እየወቀሱኝ ነው ኢሙዬ ከዚህ በላይ መታገል አልችልም ይቅርታ"እያለ እግሬ ስር ወደቀ
የኔ የ ኢማን ህይወት እዚህ ጋር አበቃ ማለት ነው እንጫወታለን ብለን ተጫወቱብን አይደል? አቅፌው መንሰቅሰቅ ጀመርን።


#የመጨረሻው_ክፍል10_.........

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

05 Apr, 07:11


#ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ


#ክፍል8

ቤት ሁሉም ለ ሰርጉ ሽር ጉድ ማለቱን ተያይዘውታል የቀረ ሰው ያለ አይመስለኝም ከ ክፍለ ሀገር የ እማም የአባም ቤተሰቦች መተዋል። አንድ የ እማዬ ወንድም አለ በጣም ነው ምወደው ሚወደኝ ምንም ብነግረው ይረዳኛል እሱ የመሰለው ፍቃደኛ ሆኜ እንደማገባ ነው ነገሩን ሲሰማ ግን የተገላቢጦሽ ነው
"ያልገባኝ ነገር ለምንድነው ይሄን ያህል ጀማልን የምትጠይው?"
ምን ብዬ የምወደው ሰው ስላለ ልበለው የቱንም ያህል ብቀርበው ይሄንን ማውራት ግን አልቻልኩም
በቃ ቀልቤም አይወደውም በዛ ላይ ተማሪ ነኝ.....
"እህ እሱ ታዲያ መች ልውሰድሽ አለ ኢሙ ትምህርትሽን ጨርሰሽ ነውኮ ምትገቢው"
አብዱ እንዴት ነው በአላህ የምጠላውን ሰው አግብቼ ምኖረው?
" እሱ ከሆነ ቀላል ነው የምትጠይውን ሰው መውደድ ትችያለሽ ዋናው ነገር ጊዜ ነው በጊዜ ሂደት ማይለወጥ ነገር የለም ም/ቱም ኒካህ ነው ሚታሰርልሽ በጊዜ ሂደት ስትገናኙ ትወጂዋለሽ"
አይ አልወደውም አይ አልወደውም እያልኩ እንባ ተናነቀኝ
" እሺ ኢሙ እንደሱ ከሆነ አብረን መፍትሄ እንፈልጋለን እቃ ስትገዛዢ አታብዢ ትንሽ ትንሽ ግዢ በጊዜ ሂደት ካልወደድሽው ኒካሽ ይወርድልሻል የገዛውንም እቃ ታስቦ እኔ አመልስለታለው"


አልሀምዱሊላህ የሆነ ነገር ቅልል አለኝ።አብዱ እንዳለኝም ወርቅ የእጅ እና የጆሮ ብቻ ገዛው ልብስም ሁለት ቅያሬ ሂጃብም እንደዛው ገዝተን ተመለስን እነ ማሚ ሲያዩት በጣም ነበር የተናደዱብኝ " ምንድነው ቁንጥር ቁንጥር ያለ እቃ ምትገዢው" እያሉ ተራ በተራ ጮሁብኝ ያሰብኩትን ማውቀው እኔ ነኝና ያሉትን ከምንም አልቆጠርኩትም

የኒካው ቀን ደረሰ የሰው ጫጫታ ሽር ጉዱ ሲታይ ግን ኒካ አይመስልም ነበር መቆሚያ ቦታ ራሱ የለም።የሰፈር ሰው ሁሉ ተጠርቷል ማንም አልቀረም።የመጀመሪያ ሚዜ ሰሚራ ናት ሁለቸኛ የ አክስቴ ልጅ ሀያት ሶስተኛም ዘመዴ ናት ሰአዳ። ከ ሚዜዎቹ ጋር አንድ ሀሳብ መጣልን " ሲታይ ገንዘብ ሚያወጣ አይመስልም ለምን ተናዶ እንዲተው ወጪ አናበዛበትም?"ሀያት ነበረች "እውነቷን ነው ቬሎ ተከራይ እንበለው" አለች ሰአዳ ደወልንለትና መከራየት እንደምንፈልግ ነገርነው አሺ ወደ ማታ ላግኝሽ ብሎኝ ጨረስን ማታ አካባቢ ከ ሀዩ ጋር ሄደን ተቀብለን በማግስቱ ሄደን ተከራየን መልካም ጋብቻ የሚል ፅሁፍ አፅፈን መጣን። በኛ ቤትኮ። እቃ እቃ መጫወታችን ነው አይ ልጅነት ሌላ ነገር አናስብምኮ በቃ የኒካው ቀን ደረሰና ለብሼ ተቀምጫለው ቤቱ ፏ ብሏል ሰው መምጣት ጀምሯል አጎት ተብዬው መጣ ሲያይ ቬሎ ለብሻለው ሲያይ መልካም ጋብቻ ይላል ጠራኝና
"አንቺ ግን እብድ ነሽ ወላሂ ብልጥ ትመስይኝ ነበርኮ ከመች ጀምሮ ነው ለ ኒካህ ቬሎ ሚለበሰው ምንድነውስ ጋብቻ ማናምን ያላቹት"!!!!
አረ አብዱ እኛኮ ምንም አስበን አይደለም አልኩት
"ምን ለነገሩ ቬሎ ስለለበስሽ ይወስድሻል ማለት አይደለም ፏ በይበት እንደውም" ብሎኝ ነገሩን ቀለል አደረገው።

#ክፍል9....ይቀጥላል......

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

04 Apr, 09:23


#ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ


#ክፍል7

እንደዛ እየባለ ህይወት ቀጠለች። አሁን ላይ ትምህርትም ስለተጀመረ ሀምዛን አየዋለው በማናገር ደረጃስ ብትሉኝ አናወራም እሱም ለኔ የተጨነቀ ይመስላል በአይን ብቻ ነበር ምናወራው ከ 7 ወር በኋላ ግን ህይወቴ ምስቅልቅሉ ወጣ አባ ጫማ ቤት ሲሰራ ምሳ እኔ ነበር ምወስድለት ጀማልም እዛው አጠገብ ሱቅ ነበረው ስመላለስ ያየኛል ለ አባም ሊያገባኝ እንደሚፈልግ ይነግረዋል አባና እማ ተነጋግረው ጨርሰዋል ፍቃደኛነታቸውን ገልፀውለታል አባ ከ 7 ወር በፊት ልጅ ናት አሁን አልድራትም ያለው አሁን ተቀየረ በትውውቅ ይሁን በሼም ወላሁ አእለም የሚገረረመው ደሞ የኔ ፍላጎት ሁላ አልተጠየቀም ምንም አላውቅም ሰጀምር like እንደ ክፍለ ሀገር ነው ሚያስቡት የኛ ቤተሰብ ደሞ ወግ ያጠብቃሉ አባም ከ ሀምዛ ጉዳይ በኋላ የኔ ነገር ሳያሳስበው አልቀረም መንገድ ላይ ስንሄድ ሁላ ለምን ወንዶች አዪሽ ብሎ ነበር ሚቀያየረው ትኩረት መስጠት ጀመረ። ማሚን የሰፈር ወንዶች "እቺን ልጅሽንማ ጠልፈን ነው ምንወስዳት" ይሏታል የዛኔ ልጅነትም አለ ቀይ ቀጠን ረዘም ያልኩ ስትስቂ ደስ ትያለሽ እባላለው ይመስለኛል ስስቅ ጉንጮቼ ላይ የሚወጣው ስርጉድ ውበቴን አግዝፎ ያወጣዋል አባ አሁን ሀሳብ የሆነበትን ጉዳይ ሊገላገል ነው....ተነገረኝ ያው ምንም ማድረግ አልችልም ዝም ነበር ያልኩት ጀማል ከ ትምህርት ቤት ስወጣ ይጠብቀኛል የሁል ጊዜ መልሴ ተማሪ ነኝ ነበር ሌላ ምንም አልለውም አይደለም እሱን አግብቼ መኖር ይቅርና እሱን ማየት ራሱ አልወድም ነበር ሆኖም የኔ ፍላጎት መች ተጠበቀ ጀማልን ባገኘሁት በ ወሩ ሽማግሌ ተላከ ለሀምዛ ማን እንደሚነግረው አላውቅም ብቻ ግን ይሰማ ነበር ከዛ በኋላ ነው አራስ ነብር የሆነው።

የሆነ ቀን ከ ት/ቤት ስወጣ ጠበቀኝ ሳየው ደስ አለኝ ዘለሽ ተጠምጠሚበት ይለኛል ውስጤ ሀይማኖቴ አይፈቅደውም እንጂ "ሰላም አለይኪ" አለኝ በቀዘቀዘ ድምፅ ወአለይከ ሰላም አንገቴን ደፍቼ ነበር ማወራው "ኢሙ አስችሎሽ ነው ግን ከኔ መለየቱ....እእእ ለነገሩ አንቺ መች ፈለግሺኝ አንቺ የያዝሽው ምርጫ ነው አይደል እስከ አሁንም እየጠበቅሽ ያለሽው ገንዘብ ሀብት ያለውን ነው" እንዲ ሲለኝ በጣም ነበር የተናደድኩት እኔ ነኝ ያለሁበትን ጭንቀት የማውቀው ማንምም ሊረዳኝ አልቻለም ...ምንም አይነት መፍትሄ የለኝም! ምን እንድሆን ነው ምትጀየፈልገው እእእ!! ሁለታችንም ተረብሸናል እሱም እንድንጠፋ ጠየቀኝ ምንም ያህል ባስበው አንድም ቀን ይሄ ሀሳብ መቶልኝ አያውቅም ሀምዛ ትዳር ማለት የ ሁለት ሰዎች ህይወት ብቻ አይደለም እነሱ ደስተኛ ካልሆኑ እኛም ጋ ደስታ አይኖርም። " ልክ ነሽ ኢሙ ሀራም ላይ እንወድቃለን"ወላሂ እንዲህ ሲያስብ ይበልጥ እንድወደው አደረገኝ አንዳንዴ የማትጠብቁትን ነገር በማትጠብቁት ቦታ ታገኙታላቹ ዱርዬ ነው ብዬ ያሰብኩት አስተሳሰቡ ግን ማሻ አላህ...ተያይዘን እነሱ ቤት ሄድን ለ እናታቸውም ነገርናቸው "ልጄ አንቺን ከልጅነትሽ ነበር ለልጄ ምከጅልሽ ቢሆንም ግን ቤተሰቦችሽ ሳይፈቅዱ ምንም የሚሆን ነገር የለም አላህ አንድ ላይ ትሆናላቹ ካላቹ ትሆናላቹ ካላለውም አላለውም ነው"....

#ክፍል8_ይቀጥላል........

5,681

subscribers

209

photos

6

videos