Bole Community General Secondary School @genralschoole Channel on Telegram

Bole Community General Secondary School

@genralschoole


For notice

Bole Community General Secondary School (English)

Welcome to the Bole Community General Secondary School official Telegram channel - @genralschoole. This channel has been created for the students, parents, teachers, and community members of Bole Community General Secondary School to stay updated with important notices and announcements. Whether you are a student looking for information on upcoming exams, a parent wanting to know about school events, or a teacher needing to communicate with colleagues, this channel is the perfect place for you. Stay informed about school closures, extracurricular activities, academic achievements, and much more. Join us on @genralschoole and be part of our school community. For notice, updates, and everything related to Bole Community General Secondary School, this is the channel to follow!

Bole Community General Secondary School

14 Feb, 17:26


ቀን 7/06/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ፦
በሚቀጥለዉ እሁድ ማለትም በቀን 9/06/2017ዓ.ም የ2017ዓ.ም የስድስት ወር ስራ አፈጻጸም እና የተማሪዎች ዉጤት ትንተና ይቀርባል በመሆኑም ሁላችሁም ከጥዋቱ 2:00ስአት እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

12 Feb, 17:01


ቀን 05/06/2017ዓ.ም
ጥብቅ ማስታወቂያ
ለቦሌ ህብረተሰብ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ12ኛ ክፍል የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ወሳጅ ተማሪዎች በሙሉ ፦
በነገዉ እለት ማለትም በቀን 06/06/2017ዓ.ም በ CBT እና በPPBT ዙሪያ ከ ኢንፎርሜሺን ኮሚኒኬሺን ቴክኖሎጂ መምህራን ጋር በመሆን ስልጠና እንሰጣለን።
በመሆኑም በነገዉ እለት ስልጠና የማይሰለጥን ተማሪ ሀገር አቀፍ ፈተናዉን የማይወስድ መሆኑን ከወዲህዉ በጥብቅ እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

10 Feb, 14:18


ቀን 03/06/2017ዓ.ም
ጥብቅ ማስታወቂያ
ለቦሌ ህብረተሰብ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ተማሪዎች በሙሉ፦
እንደሚታወቀዉ የ2017ዓ.ም የሁለተኛዉ መንፈቅ አመት ትምህርት በዛሬዉ እለት በጥሩ ሁኔታ ተጀምሯል።
በመሆኑም በነገዉ እለት የዛሬዉ ጀማሮ በማስቀጠል ሙሉ በሙሉ የመማር ማስተማሩ ሂደት ይኖራል።
በመሆኑም፦
1.ዉድ ተማሪዎቻችን ወደ ትምህርት ቤት እንድትመጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
2.ዉድ የተማሪ ወላጆች ልጆቻችሁን በጥዋት እንድትልኳቸዉ ጥሪ እናስተላልፋለን።
3.ሀገር አቀፍ ፈተና ለምትወስዱ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች፦ ፈተና የምትወሰዱበትን PPBT እና CBT የአወሳሰድ ሂደቱን ለማሰልጠን ከነገ ጀምሮ ልየታ እናደርጋለን በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ከፍል ዉስጥ አየገባን ልየታ ስለምናደርግ ክፍል ዉስጥ እንደትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።ስልጠናዉን ያልወሰደ ተማሪ ፈተና ላይ አይቀመጥም።
4. የትምህርት ቤታችን የወ.ተ.መ.ህ
ተወካዮች በጥዋት ተገኝታችሁ እንድታስተባብሩ ጥሪ እናስተላልፋለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

09 Feb, 04:52


ዉድ ተማሪዎቻችን ከዚህ በላይ ያለዉን የ2016የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጥያቄዎችን ስሯቸዉ ይጠቅማችኋል።
ወድ ወላጆቾች ለጆች ይህን ጥያቄ መስራታቸዉን መስራታቸዉ ተከታተሏቸዉ። ምክንያቱም የ 2017ዓ.ም የሀገር ከቀፍ ፈተና መውሰጃ ቀን እየደረሰ ስለሆነ።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

08 Feb, 10:24


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 3/2017 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

(ጥር 30/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 3/2017 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡


ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacaebc

Bole Community General Secondary School

31 Jan, 18:28


ቀን 23/05/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህበረተሰብ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሙሉ ;
እንደሚታወቀዉ የ2017ዓ.ም
የመጀመሪያዉ መንፈቀ አመት የማጠቃላያ ፈተና በዛሬዉ እለት ማለትም በቀን23/05/2017ዓ.ም ያለምንም ችግር በሰላም ተጠናቋል።
በመሆኑም ዉድ ተማሪዎቻችን በሚቀጥለዉ ሰኞ ማለትም በቀን በ26/05/2017ዓ.ም ከጥዋቱ
2፡30 ጀምሮ መታወቂያችሁን በመያዝ እና ዩኒፎርም በመልበስ፦
1.የማጠቃላያ ፈተና ዉጤት ከመምህራኖቻችሁ ጋር እንድታዩ
2.ከመቶው(100%) ዉጤታችሁን እንድታዪ ጥሪያችን እናስተላልፋለንደ።
ከዚህ ቀን ዉጭ ለሚመጣ ተማሪ ሀላፊነት የማንወስድ መሆኑን ከወዲህዉ እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

25 Jan, 14:48


ቀን 17/05/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህበረተሰብ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሙሉ፦
እንደሚታወቀዉ የ2017ዓ.ም የመጀመሪያዉ መንፈቀ አመት የማጠቃላያ ፈተና የሚሰጠዉ ትምህርት ቢሮ ባወረደዉ የትምህረት ካላንደር መሰረት ከጥር 19 እስከ ጥር 23 መሆኑን በተደጋጋሚ በተለያዬ የመረጃ ምንጮት አሳወቀናችኋል። በመሆኑም ሰኞ በ19/05/2017ዓ.ም ለፈተና ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ ነገሮች፦

1. ሁሉም ተማሪ ፀጉሩን ተሰተካክሎ መምጣት የግድ ነዉ።
2. ሁሉም ተማሪ ፈተና ከመጀመሩ 30 ደቂቃ በፊት በት/ቤት ውስጥ መገኘት ይጠበቅባችኋል።
3.  በተመደባችሁበት ክፍል ፈታኙ በሚሰጣችሁ አቅጣጫ መሰረት ወደ ፈተና ክፍል በመግባት በቦታቸው መቀመጥ ይጠበቅባችኋል፡፡
4.ከእስክሪብቶ፣ እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ ውጪ ወደ መፈተኛ ክፍል ይዘው መግባት የተከለከለ ነዉ።
5.በፈተና ሰዓት መኮረጅ ወይም ማስኮረጅ ፈተና የሚያሰርዝ በመሆኑ በስርዓት የራሳችሁን ፈተና ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ መፈተን ይጠበቅባችኋል።
6.ለፈተናው የተሰጣችሁን ሰዓት በአግባቡ መጠቀም ይኖርባችኋል።ማለትም ፈተና ከተጀመረ 30 ደቂቃ ቀድሞ መዉጣትም ሆነ መግባት የተከለከለ ነዉ።
7.በፈተና ሰዓት ምንም አይነት ድምፅ ማሰማት፣ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ አላስፈላጊ ወረቀት(ደብተር) ይዞ መገኘት፣ ረብሻ መፍጠር ፣ወረቀት መወርወር በጥብቅ የተከለከለ ነዉ።
8.ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች አስፈላጊውን መረጃ፣ ስም፣ተራ ቁጥር፣ ፆታ ፣ክፍል እና ሴክሽን የመሳሰሉትን በአግባቡ መሙላትና የፈተናውን መልስ መሟላቱን በማረጋገጥ ለፈታኝ መምህሩ በጠየቀው ሰዓት መመለስ ይጠበቅባችኋል።
9. ሁሉም ተፈታኞች ማንኛውም ጥያቄ ሲጠየቁ በስርዓት እጅ በማውጣት መሆን ይኖርበታል።
10.ሁሉም ተፈታኞች አቴንዳንስ ላይ በዕለቱ በተፈተኑበት ትምህርት ስር መፈረም ይኖርባቸዋል።
11.የተለያዬ ጌጣጌጦች ይዞ መምጣት የተከለከለ ነወ።በተለይ ሴቶች
12.ሞባይል ይዞ መምጣት የተከለከለ ነዉ።
13.የተለያዪ ኤሌክትሮኒክስ ነገሮች፣ስለታማ ነገሮች፣ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተሮች ፣ዘመናዊ የ እጅ ስአቶች ይዞ መምጣት የተከለከለ ነዉ።
14.ዩኒፎርም ለብሶ መምጣት ይጠበቅባችኋል።
15.የ12 ኛ ክፍል ፈተና በሞዴል እስታንዳርድ በመሆኑ እርሳ ላፒስ እና መቅረጫ ይዞ መምጣት የግድ ነዉ።
16. ሁሉም ተፈታኞች ፈተና ከጨረሱ በኃላ የተፈተኑት የመልስ መስጫ ወረቀት ለፈታኙ በጥንቃቄ መስጠት ይናርባችኋል።
17.ሁሉም ተፈታኝ ፈተና ጨርሶ ከክፍል ከወጣ በኋላ ምንም አይነት ድምፅ ማሰማት የተከለከለ ነዉ።
18.የትኛዉም ተፈታኝ የጥያቄ ወረቀቱን ክፍል ውስጥ ወይም ከክፍል ዉጭ ጥሎ ወይም ቀዶ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ ነዉ።
19.የትኛዉም ተማሪ ለተለያዩ ጉደዮች ለማጠራት አስተባባሪዎ ወይም የፈተና ኮሚቴዎች ወይም ፈታኞች መታወቂያ ከጠየቁ ማሳየት የግድ ነዉ።
20.የትኛዉም ተማሪ ወደ ትምህርት ቤት ሲመጣ የትምህርት ቤት መታወቂያ ይዞ መምጣት የግድ ነዉ።
21.የትኛዉም ድምፅ የሚያወጡ ነጠላ ጫማ እና የመሳሰሉት ለብሶ መምጣት የተከለከለ ነዉ።
ማሳስቢያ፦
1. ዉድ የተማሪ ወላጆች ተማሪዎች ወደ ፈተና ስትልኩ በእናንተ በኩል ያላችሁ የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክር አገልግሎት ሰጥጣች ከጥር 19 እስከ ጥር 23 ለሚሰጠዉ የመጠቃላያ ፈተና እናንተም አንድ የትምህርት ባለድርሻ አካል ስለሆናችሁ የተማሪዎች ዉጤት የተሻለ እንዲሆን ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪ እያስተላለፍን።
2. ተማሪዎች በስአቱ ወደ ትምህርት ቤት እንድትልኳቸዉ በጥብቅ እናሳስባለን።
3.የትምህር ቤታችን የወላጅ ተወካዬች የፈተና ሰርአቱን ትምህርት ቤት በመገኘት እንድታስተባብሩ ጥሪ እናስተላልፋለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

13 Jan, 11:06


ቀን 05/05/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ 2ኛደረጃ ት/ቤት የ2017ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግብያ ተፈታኞች በሙሉ።እንደሚታወቀዉ
በከተማ ደረጃ የተዘጋጀዉ ሞዴል  ፈተና የሚጀምረዉ በ6/05/2017ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ለፈተና ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ ነገሮች
1.ሁሉም ተፈታኝ ጠዋቱ 2፡00 ሰአት መገኘት አለበት
2. ሁሉም ተማሪ እርሳስ ማጥፊያ እና መቅረጫ ይዞ መምጣት አለበት
3. ሁሉም ተማሪ ፀጉሩን አስተካክሎ መሞጣት ይጠበቅበታል
4.ሁሉም ተማሪ ዩኒፎርም ለብሶ መምጣት ይጠበቅበታል።
5.ሞባይል ይዞ መምጣት በጥብቅ የተከለከለ ነዉ።
6.የትኛዉንም ኤሌክትሮኒክስ ነገር ይዞ መምጣት የተከለከለ ነው።
7.የትኛዉንም ከቀላል ሂሳባዊ ማሰቢያ ማሽን እስከ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር ይዞ መምጣት የተከለከለ ነው።ዘመናዊ ስአቶችን ጨምሮ የተከለከ ነዉ።
8.የትኛዉንም የማሰቢያ ወረቀትም ይሁን አጫጭር ማስታወሻዎች ወደ ፈተና አዳራሺ ይዞ መግባት የተከለከለ ነዉ።
9.በየትኛም አጋጣሚ ወደ ፈተና ከገቡ በኋላ መኮረጂም ማስኮረጀም ዉጤቱን ሙሉ በሙ ያሰረዛል(በኮሚቴዉ ህግ እና ደንብ መሰረት
10.የትኛዉም ተፈታኝ ከተመደቡት ፈተኞች ጋር አምጓሮ ለመፍጠር የሞከረ ተማሪ ከፈተና ዉጭ ይሆናል።
11.ፈተና ከተጀረ ከ30ደቂቃ በኋላ የተኛዉም ተማሪ ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት አይችልም።
12.የትኛዉም ተፈታኝ ፈተናዉ ከተጀመረ በኋላ ከ30ደቂቃ ቀድሞ መዉጣት የተከለከለ ነዉ።
13.ማንኛዉ ተፈታኝ ፈተና ተፈትኖ ከጨረስ በኋላ የፈተና ወረቀቱን ክፍል ዉስጥ ጥሉ መሄድ ወይም መቅደድ የተከለከለ ነዉ።
ማሳስቢያ፦
በዚህ የሞዴል እና ማጠቃላያ ፈተና ላይ ያልተቀመጠ ተማሪ የመግቢያ ፈተናዉን የማይወስድ መሆኑን ከወዲህዉ እናሳዉቃል።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

13 Jan, 07:39


" ያልተመዘገበ ተማሪ አይፈተንም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2ዐ17 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ / የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ መጪ ማክሰኞ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገቡ ካሉ በእነዚህ ቀሪ ሁለት ቀናት ላይ ብቻ እንዲመዘገቡ ያሳሰበ ሲሆን " ያልተመዘገበ አይፈተንም " ብሏል።

@tikvahethiopia

Bole Community General Secondary School

13 Jan, 07:25


ዉድ የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን የነገዉ ሞዴል ፈተና ማጥቆር ስለሆነ፦
1.እርሳስ
2.ማጥፊያ
3.መቅረጫ
ይዛችሁ እንድትመጡ ከወዲህዉ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

12 Jan, 13:18


ቀን 04/05/2017ዓ.ም
በድጋሜ የወጣ ማስታወቂያ
ለቦሌ ህብረተሰብ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2017ዓ.ም
በከተማ ደረጃ የሚስጠው ሞዴል ከቀን 06/05/2017- 08/05/2017ዓ.ም
መሆኑን አዉቃችሁ እራሳችሁን እንድታዘጋጁ በጥብቅ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

10 Jan, 08:01


ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት የሌሎችን በትክክል ያሟሉ ተማሪዎችን መረጃም ሪፖርት ለማድረግ ተቸግረናል።

Bole Community General Secondary School

10 Jan, 07:54


በጣም አሰቸኳይ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞላችሁትን ፎርም መጥታችሁ እንድታስተካክሉ እና እንድትፈርሙ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግም መጥታችሁ የሚጠበቅባችሁን ግዴታ አላሟላችሁም። ሰለሆነም ያልፈረማችሁ ተማሪዎች ዛሬውኑ እንድትፈርሙ በጥብቅ እያሳሰብን ከዚህ በታች ስማችሁ የተጠቀሳችሁ ደግሞ ፎቶ ያልተነሳችሁ 1.አሸናፌ ጌቱ 2. ፍሬህይወት ግርማ 3. ወርቅነሽ ሞላ

Bole Community General Secondary School

09 Jan, 11:13


የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና መስጫ መርሀ ግብር


(ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም)



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!



https://linktr.ee/aacaebc

Bole Community General Secondary School

07 Jan, 13:04


ሰላም ለት/ ቤተችን የ12ኛ ክፍል  ተፈታኝ ተማሪዎች  በሙሉ  በቅድሚያ እንኳን ለጌታችን   ለእየሱስ ክርሰቶስ የልደት በዓል በሠለም አደረሳችሁ እያልሁኝ  የሞላችሁትን ፎርም   ትክክል መሆን አለመሆኑን በ30/04/17 ዓ.ም በማረጋገጥ እንድትፈርሙ  እያሳሰቡብሁ በተባለው ጊዜ መጥቶ ያለረጋገጠ እና ያል ፈረመ ተማሪ ለሚፈጠረው ማንኛውም ስህተት ት/ ቤቱ ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑን  እንገልፃለን።               ላልሰሙ መረጃውን በማጋራት  ትብብር  እንድታደርጉ  አንጠይቃለን።                                                              ት/ ቤቱ

Bole Community General Secondary School

01 Jan, 12:51


ጥብቅ ማሳሰቢያ ለትምህርት ቤታችን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና ወላጆች በሙሉ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ድረስ ፎርም ያልሞላችሁ በአስቸኳይ ማለትም እስከ 25/04/17 ዓም ድሰስ ብቻ መጥታችሁ የማትሞሉ ከሆነ ለሚፈጠረው ማንኛውንም ችግር ሃላፊነት ት/ቤቱ የማይወስድ መሆኑን በድጋሚ እንገልጻለን። ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

26 Dec, 18:14


የ2017 ዓ.ም የ1ኛ መንፈቅ ዓመት ሞዴል ፈተና መረጃ ለ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች

1️⃣6ኛ ክፍል በተመለከተ

በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
👉አማርኛ
👉እንግሊዘኛ
👉ሒሳብ
👉አካ/ሳይንስ  እና
👉ግብረ ገብ  ሲሆኑ 

✍️ የ1ኛ መንፈቅ ዓመት ሞዴል ፈተና የሚዘጋጀው ከ6ኛ ክፋል first semester (5ኛ ክፍልን first semester  ይጨምራል)

የ1ኛ መንፈቅ ዓመት ሞዴል ፈተና የሚዘጋጀው ከ8ኛ ክፍል  first semester   (ከ7ኛ ክፋልን first semester ይጨምራል)

በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
👉አማርኛ
👉እንግሊዘኛ
👉ሒሳብ
👉ሶሻል ሳይንስ
👉አጠ/ሳይንስ
👉የዜግነት ት/ት

12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በተመለከተ

👉በ2017 ዓ.ም ለፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን  በሁለቱም ዘርፎች ስድስት፡ ስድስት የትምህርት አይነቶች ናቸው::   እነሱም :-

ሀ/የተፈጥሮ ሣይንስ
✍️እንግሊዝኛ
✍️ሒሳብ
✍️ባዮሎጅ
✍️ፊዚክስ
✍️ኬሚስትሪ
✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት

ለ/የማህበራዊ ሣይንስ
✍️እንግሊዝኛ
✍️ሒሳብ
✍️ታሪክ
✍️ኢኮኖሚክስ
✍️ጅኦግራፊ
✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት


የ1ኛ መንፈቅ ዓመት ሞዴል የፈተና ዝግጅትም:-

1.  12ኛ ክፍል first semester ብቻ
2. ከ9ኛ ክፋል በአሮጌው ስርአተ ትምህርት  ያጠቃልላል::
3. ከ11ኛ ክፋል first semester ብቻ  ::
4. 10ኛ ክፋልን አያካትትም

👉በመሆኑም የፈተና ወቅት እየተቃረበ በመሆኑ ተማሪዎች በዚህ መረጃ መሰረት በአግባቡ ማጥናት ይጠበቅባቸዋል::
👉ሁሉም ሞዴል ፈተናዎች  ከጥር 7--9  ይሰጣሉ ።
በዚህ መረጃ መሠረት ሁሉም  የመንግስትና የግል ት/ቤቶች ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

Bole Community General Secondary School

17 Dec, 17:32


ቀን 08/04/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከነገ እሮብ ጀምሮ በየክፍሉ እየገባን የወሰዳችሁን መጽሀፍ በአግባቡ እየተጠቀማችሁበት መሆኑን እናረጋግጣለን ።
በመሆኑም ሁላችሁም ከእሮብ ጀምሮ ክፍል ውስጥ ይዛችሁ መገኝት ይጠበቅባችኋል። ይዞ በማይመጣ ተማሪ ህጋዊ እርምጃ የምንወሰድ መሆኑን ከወዲህዉ እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

09 Dec, 14:08


ቀን 30/03/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከቀጣይ ማክሰኞ ጀምሮ በየክፍሉ እየገባን የወሰዳችሁን መጽሀፍ በአግባቡ እየተጠቀማችሁበት መሆኑን እናረጋግጣለን ።
በመሆኑም ሁላችሁም ከማክሰኞ ጀምሮ ክፍል ውስጥ ይዛችሁ መገኝት ይጠበቅባችኋል። ይዞ በማይመጣ ተማሪ ህጋዊ እርምጃ የምንወሰድ መሆኑን ከወዲህዉ እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

07 Dec, 15:11


ቀን 28/03/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል  ተማሪዎች በሙሉ  ነገ እንደተመደዉ የጥናት ፕሮግራሙ ይቀጥላል ። በመሆኑም በተለመደዉ ስአት ጥዋት 2:30 በስአቱ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።
የማይመጣ ተማሪ ቀጣይ ሰኞ ት/ቤት የማናስገባ መሆኑን  ከወዲህዉ እናሳስባለን።
      ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

06 Dec, 12:59


ቀን 27/03/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ነገ እንደተመደዉ የጥናት ፕሮግራሙ ይቀጥላል ። በመሆኑም በተለመደዉ ስአት ጥዋት 2:30 በስአቱ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።
የማይመጣ ተማሪ ቀጣይ ሰኞ ት/ቤት የማናስገባ መሆኑን ከወዲህዉ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

06 Dec, 12:52


ቀን 27/03/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ በየክፍሉ እየገባን የወሰዳችሁን መጽሀፍ በአግባቡ እየተጠቀማችሁበት መሆኑን እናረጋግጣለን ።
በመሆኑም ሁላችሁም ከሰኞ ጀምሮ ክፍል ውስጥ ይዛችሁ መገኝት ይጠበቅባችኋል። ይዞ በማይመጣ ተማሪ ህጋዊ እርምጃ የምንወሰድ መሆኑን ከወዲህዉ እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

10 Nov, 18:14


ቀን 01/03/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሙሉ ከነገ ጀምሮ በየክፍሉ እየገባን የወሰዳችሁን መጽሀፍ በአግባቡ እየተጠቀማችሁበት መሆኑን እናረጋግጣለን ።
በመሆኑም ሁላችሁም ከነገ ጀምሮ ክፍል ውስጥ ይዛችሁ መገኝት ይጠበቅባችኋል። ይዞ በማይመጣ ተማሪ ህጋዊ እርምጃ የምንወሰድ መሆኑን ከወዲህዉ እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

07 Nov, 17:10


ቀን 28/02/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሙሉ ከነገ ጀምሮ በየክፍሉ እየገባን የወሰዳችሁን መጽሀፍ በአግባቡ እየተጠቀማችሁበት መሆኑን እናረጋግጣለን ።
በመሆኑም ሁላችሁም ከነገ ጀምሮ ክፍል ውስጥ ይዛችሁ መገኝት ይጠበቅባችኋል። ይዞ በማይመጣ ተማሪ ህጋዊ እርምጃ የምንወሰድ መሆኑን ከወዲህዉ እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

01 Nov, 16:45


ቀን 22/02/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ
ት/ቤት ለ12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች በሙሉ፦
የ 2017 ዓ.ም የማጠናከሪያ ትምህርት ነገ ቅዳሜ በ 23/02/2017ዓ.ም ሙሉ በሙሉ እንጀምራለን ።
በመሆኑም ሁላችሁም ተማሪዎችን ለቅዳሜዉ ዝግጁ እንድታደርጓቸዉ እና በጠዋት 2:30 እንድትልኳቸዉ።
ከወዲህዉ በጥብቅ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

29 Oct, 14:09


ቀን 19/02/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ
ት/ቤት ለ12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች በሙሉ፦
የ 2017 ዓ.ም የማጠናከሪያ ትምህርት በሚቀጥለዉ ቅዳሜ ሙሉ በሙሉ እንጀምራለን ።
በመሆኑም ሁላችሁም ተማሪዎችን ለቅዳሜዉ ዝግጁ እንድታደርጓቸዉ እና በጠዋት እንድትልኳቸዉ።
ከወዲህዉ በጥብቅ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

29 Oct, 07:56


🔥 Maths entrance exam ጉዱ ፈላ😱

📘አንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የ Maths ፎርሙላዎች

👉Arithmetic

1. Basic Operations:

   • Addition:  a + b

   • Subtraction:  a - b

   • Multiplication:  a × b  or  ab

   • Division:  a/b

2. Percentage:

Percentage = Part / Whol} × 100

👉Algebra

1. Quadratic Formula:

x = -b ± √(b² - 4ac) / 2a

for  ax² + bx + c = 0 .

2. Factoring Formulas:

   • Difference of Squares:  a² - b² = (a - b)(a + b)

   • Perfect Square Trinomial:  a² + 2ab + b² = (a + b)²

3. Exponents:

   •  aᵐ × aⁿ = aᵐ⁺ⁿ

   •  aᵐ/aⁿ = aᵐ⁻ⁿ

   •  (aᵐ)ⁿ = aᵐⁿ

4. Logarithms:

   • Change of Base:  logᵦ a = (logₖ a)/(logₖ b)

   •  logᵦ (xy) = logᵦ x + logᵦ y

   •  logᵦ ((x/y)) = logᵦ x - logᵦ y

👉Geometry

1. Area Formulas:

   • Rectangle:  A = l × w

   • Triangle:  A = ½ b h

   • Circle:  A = π r²

2. Perimeter Formulas:

   • Rectangle:  P = 2(l + w)

   • Triangle:  P = a + b + c

   • Circle (Circumference):  C = 2π r

3. Volume Formulas:

   • Cube:  V = s³

   • Rectangular Prism:  V = lwh

   • Cylinder:  V = π r² h

   • Sphere:  V = 4/3 π r³

4. Pythagorean Theorem:

a² + b² = c²

for a right triangle.

👉Trigonometry

1. Basic Trigonometric Ratios:

   • Sine:  sin(θ) = Opposite/Hypotenuse

   • Cosine:  cos(θ) = Adjacent/Hypotenuse

   • Tangent:  tan(θ) = Opposite/Adjacent

2. Pythagorean Identity:

sin²(θ) + cos²(θ) = 1

3. Angle Sum and Difference Formulas:

   • Sine:

     •  sin(a + b) = sin a cos b + cos a sin b

     •  sin(a - b) = sin a cos b - cos a sin b

   • Cosine:

     •  cos(a + b) = cos a cos b - sin a sin b

     •  cos(a - b) = cos a cos b + sin a sin b

👉Calculus

1. Derivatives:

   • Power Rule:  f'(x) = nxⁿ⁻¹

   • Sum Rule:  (f + g)' = f' + g'

   • Product Rule:  (fg)' = f'g + fg'

   • Quotient Rule:  ((f/g))' = (f'g - fg')/g²

2. Integrals:

   • Indefinite Integral:

∫xⁿ dx = xⁿ⁺¹ / n+1 + C, n ≠ -1

• Definite Integral:

A = ∫ₐᵇ f(x) dx

👉Statistics

1. Mean (Average):

Mean = ∑ xᵢ / n

2. Median:

   • Middle value when data is ordered.

3. Mode:

   • Most frequently occurring value.

4. Standard Deviation:
   For population:

σ = √((∑ (xᵢ - μ)²)N)/(``)
For sample:

👉ማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት ለመስጠት👇  comments

Bole Community General Secondary School

22 Oct, 18:45


ቀን 12/02/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ቤት መታወቂያ ላልወሰዳች ተማሪዎች
በሙሉ ፦
1.ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመያዝ
2. የመታወቂያ ክፍያ በመያዝ
ሁላችሁም እንድትወስዱ ከወዲህዉ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ
ማሳሰቢያ፦
ከቀጣይ ሰኞ ጀምርን የትኛዉንም ተማሪ ያለመታወቂያ የማናስገባ መሆኑን ከወዲህዉ እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

19 Oct, 08:20


ቀን 9/ 02/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህበረተሰብ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የ 2017 ዓ.ም የ 12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች በሙሉ፦
በነገዉ እለት ማለትም በቀን 10/02/2017ዓ.ም
1.በተማሪዎች ወጤት እና ስነ ምግባር ማሻሻያ ዙሪያ
2.በተማሪዎች ማጠናከሪያ ትምህርት ዙሪያ
3.በ እንግሊዘኛ እና ሂሳብ የትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ
የ 2015 እና የ 2016 የተማሪ ዉጤት መነሻ በማድርግ እና ከ እናንተ በሚመጡ አጀንዳዎች ዉይይት እናደርጋለን።
በመሆኑም ሁሉም ወላጆች ከ ጠዋቱ 2:30 ላይ በመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ማሳሰቢያ፦
መቅረትም ሆነ ማስፈቀድ የተከለከለ ነዉ።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

12 Oct, 17:39


Part of the body in English

Bole Community General Secondary School

12 Oct, 17:33


for 2017 EC Freshman Students

Bole Community General Secondary School

08 Oct, 16:40


ማስታወቂያ
የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫን ይመለከታል
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2017

2.   ማስታወቂያ
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2017

Bole Community General Secondary School

03 Oct, 19:01


ቀን 23/01/2017ዓ.ም
ጥብቅ ማስታወቂያ
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህረት ቤት ተማሪዎች በሙሉ :
ወደ ትምህርት ቤት ስትመጡ መያዝ ወይም መሆን ያለባችሁ ወይም ማደረግ ያለባችሁ፦
1.ከጠዋቱ 2:00 ስአት በፊት መገኘት ይኖርባችኋል።
2.ሁሉም ተማሪ ፀጉሩን ተስተካክሎ ወይም ኖርማል ቁርጥ መስተካከል ይኖርባችኋል።
3. ከ 9ኛ ክፍል ዉጭ ዩኒፎርም ለብሶ መምጣት ይጠበቅባችኋል። 9ኛ ክፍል ደግሞ የ 8ኛ ክፍል ዬኒፎርም መልበስ ይጠበቅባችኋል።ከሌላችሁ ደግሞ የተማሪ አለባበስ መልበስ ይኖርባችኋል።
4.ማንኛዉም ተማሪ ሞባይል ይዞ መምጣት የተከለከለ ነዉ።
5.ለሴት ተማሪዎች ;የትኛዉንም አላስፈላጊ የሆነ ጌጣጌጥ ለብሶ ይዞ መምጣት የተከለከለ ነዉ።
6.ዲጅታል የሆነ ስአት ወይም ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር ይዞ መምጣት የተከለከለ ነዉ::(እንደ አስፈላጊነቱ)
7.መጽሀፍ ይዞ መምጣት ግድ ነዉ።
(ከ አንድ ተማሪ በስተቀር)
8.መጽፍ ላልወሰዳችሁ 9ኛ ክፍል ተማሪን አይመለከትም።ነገር ግን በዚህ ሳምንት እንስጣለን
9.የ ግል ንጽህናን ጠብቆ መምጣት ግድ ነዉ።
10.የትኛዉም ተማሪ ወደ ት/ቤት ሲመጣ የተማሪ ስነ ምግባር ተላብሶ መምጣት ይኖርባችኋል።
ማሳስቢያ፦
ዉድ እና የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆቻችን  ልጆቻችሁን ወደ ትምህርት ቤት ስትልኩ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን አሟልታችሁ እንድትልኳቸዉ እና ግንዛቤ እንድትሰጧቸዉ  ከወዲህዉ እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

02 Oct, 16:13


ቀን 22/01/2017ዓ.ም
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች:
1.የ 10ኛ ፣የ 11ኛ እና የ12ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ ስለመጣ ያልወሰዳችሁ መውስድ ትችላላችሁ።
2.ዘግይታችሁ የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ወይም ደብተር ያልወሰዳችሁ መዉሰድ ትችላላችሁ።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

01 Oct, 14:33


ቀን 21/01/2017ዓ.ም
ጥብቅ ማስታወቂያ
ለቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህረት ቤት ተማሪዎች በሙሉ :
ወደ ትምህርት ቤት ስትመጡ መያዝ ወይም መሆን ያለባችሁ ወይም ማደረግ ያለባችሁ፦
1.ከጠዋቱ 2:00 ስአት በፊት መገኘት ይኖርባችኋል።
2.ሁሉም ተማሪ ፀጉሩን ተስተካክሎ ወይም ኖርማል ቁርጥ መስተካከል ይኖርባችኋል።
3. ከ 9ኛ ክፍል ዉጭ ዩኒፎርም ለብሶ መምጣት ይጠበቅባችኋል። 9ኛ ክፍል ደግሞ የ 8ኛ ክፍል ዬኒፎርም መልበስ ይጠበቅባችኋል።ከሌላችሁ ደግሞ የተማሪ አለባበስ መልበስ ይኖርባችኋል።
4.ማንኛዉም ተማሪ ሞባይል ይዞ መምጣት የተከለከለ ነዉ።
5.ለሴት ተማሪዎች ;የትኛዉንም አላስፈላጊ የሆነ ጌጣጌጥ ለብሶ ይዞ መምጣት የተከለከለ ነዉ።
6.ዲጅታል የሆነ ስአት ወይም ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር ይዞ መምጣት የተከለከለ ነዉ::(እንደ አስፈላጊነቱ)
7.መጽሀፍ ይዞ መምጣት ግድ ነዉ።
(ከ አንድ ተማሪ በስተቀር)
8.መጽፍ ላልወሰዳችሁ 9ኛ ክፍል ተማሪን አይመለከትም።ነገር ግን በዚህ ሳምንት እንስጣለን
9.የ ግል ንጽህናን ጠብቆ መምጣት ግድ ነዉ።
10.የትኛዉም ተማሪ ወደ ት/ቤት ሲመጣ የተማሪ ስነ ምግባር ተላብሶ መምጣት ይኖርባችኋል።
ማሳስቢያ፦
ዉድ እና የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆቻችን ልጆቻችሁን ወደ ትምህርት ቤት ስትልኩ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን አሟልታችሁ እንድትልኳቸዉ እና ግንዛቤ እንድትሰጧቸዉ ከወዲህዉ እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ

Bole Community General Secondary School

21 Sep, 06:30


በድጋሜ የተላላፈ የስብሰባ ጥሪ የቦሌ ህብረተሰብ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች በሙሉ በቀን 12/01/17 ዓም 2 : 00 ጠቅላላ የወላጆች ጉባኤ ስላለ በዕለቱ ስዓት አክብራችሁ እንድትገኙ እያሳሰብን በማትገኙት ወላጆች ላይ ግን አስፈላጊውን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን አስቀድመን እናሣስባለን ። ት/ቤቱ