✍ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር✍ @literature_for_god Channel on Telegram

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

@literature_for_god


የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው
ምሳ፩፥፯

ስነ-ፅሁፍን ለእግዚአብሄር አላማ መጠቀም

በስነ-ፅሁፍ የእግዚአብሄርን ክብር መግለጥ

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ

👉👉👉👉https://t.me/Heron_Beki

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር (Amharic)

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር እናመሰግናለን! ይህ በስነ-ጽሁፍ የእግዚአብሔርን የጥበብ መጽሐፍ ተመልከቱ፣ አታማኝ መጠቀምና የማንኛውም አስተያየት ጥያቄን ለመጠቀም እንደምንችልበት ማወቅ ነው። ስነ-ጽሁፍ ሉክ ላይ የሚሰራውን መረጃ እና መረጃ ይችላሉ: https://t.me/Heron_Beki

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

11 May, 02:30


The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 18 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The channel will remain accessible for all users.

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

09 Jun, 18:38


ተጻፈ በመቅደስ
#መቅደስ
🌿 @Literature_For_God🌿

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

06 Jun, 17:41


ገጣሚ አንቲ & ቤki
#አንቲ
🌿 @Literature_For_God 🌿

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

31 May, 18:19


ገጣሚ- አንቲ
# አንቲ

🌿 @Literature_For_God 🌿

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

28 May, 16:11


አንድ እድሜያቸው የጠና ማየት የማይችሉ ሽማግሌ ሁል ጊዜ
መንገድ ዳር ተቀምጠው ይለምኑ ነበር ፡፡ ሁሌም በሚለምኑበት
ወቅት አንድ የማይለያቸው ጽሑፍ የያዘ ካርቶን ነበር ፡፡ በካርቶኑ
ላይ " ማየት አልችልም እርዱኝ " ይላል ። አላፊው አግዳሚም
ሰው ጽሑፉን እያየ በአጠገባቸው ያልፋል ፡፡ አንዳንዱ ያለውን
ጣል ጣል ያረጋል የቀረው ደሞ ትቶ ያልፋል ፡፡

ነገር ግን አንድ ቀን በጠዋት ይህ ተከሰተ ፡፡ ከዚህ በፊት የማያውቁት ሰው ወደ እሳቸው ቀረብ ብሎ ጽሑፍ የያዘውን ካርቶን አንስቶ ጫር ጫር አድርጎ መልሶ ካስቀመጠው በኀላ ምንም ሳይሰጣቸው ጥሎ ሄደ ፡፡ ሽማግሌው በሚሰሙት ግራ
ተጋቡ ። ሰውየው አጠገባቸው መጥቶ ሲቆም ብዙ ብር
ሊሰጣቸው አልያሞ ችግራቸውን ሊጠይቃቸው መስሎቸው ነበር
ነገር ግን ምንም ሳይል ነበር ጥሎአቸው የሄደው ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን የሳቸውን ሁኔታ የሚቀይር ነገር ተፈጠረ ፡፡ አላፊ አግዳሚው ሁሉ ያለውን እያወጣ ይሰጣቸው ጀመረ ፡፡ ከሳንቲም አልፎ ብዙ ሰዎች ብር በእጃቸው ይሰጡአቸው ጀመር ። ሽማግልው ግራ ተጋቡ ቆይ ያ ሰውዬ ምን አርጎ ነው የሄደው ብለው ራሳቸውን ሲጠይቁና ግራ ሲጋቡ ዋሉ ፡፡ በዛች ሰአት ብቻ ሰዎች የረዱአቸው ወር ሙሉ ለምነው ካገኙት ይበልጥ ነበር ፡፡

በዚህ ግርምት ቆይተው ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ
ወደሳቸው ቀረበ ፡፡ እሳቸውም በጥርጣሬ "ቅድም አንተ ነህ
ጽሑፍ የጻፍከው ? ቆይ ምን ብለህ ነው የጻፍከው? " ልጄ
አሉት ። ሰውየውም በደስታ " አባቴ በእርግጥ በገንዘብ አልረዳሆትም ነገር ግን ጽሑፉን እንዳየሁ የተጻፈው ነገር ሰዎች እንዲረዱዎት ብዙ እንደማያስችል ስላወኩ የተጻፈውን ነው የለወጥኩት ፡፡ መጀመሪያ '
#ማየት_አልችልም_እርዱኝ ' ይል ነበር እኔ ደግሞ ከጀርባው '
#ዛሬ_ቀኑ_ደስ_ይላል_ግን_እኔ_አላየውም ' ብዬ አስተካከልኩት ፡፡ አዩ አባቴ ሰው ይህን ሲያነብ የእርሷን አለማየት ሳይሆን የራሱን ማየት ስለሚያስብ በደስታ ለእርሶ
ያለውን ይለግሳል ። " አላቸው ፡፡ ሽማግሌው እጁን ከያዙ በኀላ
እያመሰገኑት እጁን ይስሙ ጀመር ፡፡

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

ሰውን በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በሃሳብም መርዳት ይቻላል።

🌿 @Literature_For_God 🌿

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

26 May, 07:22


Channel name was changed to «ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር»

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

26 May, 07:21


ስነ- ጽሁፍ ለ እንግዚአብሔር

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት መኪኖች ብዛት 1 ሚልየን አይደርስም። በሚገርም ሁኔታ ግን በአማካይ በአመት 5,000 ከዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያልፋል።

👉 ግራ እጃቸውን የሚጠቀሙ ሰዎች ብዙ ግዜ ስሜታዊ ናቸው። የፀባይ ችግርም ሊኖርባቸው ይችላል።

👉 አንድ ሰው እድሜው 35 ካለፈ በቀን 7,000 የአዕምሮ ሴሎችን ማጣት ይጀምራል።

👉 አቮካዶ ለውሾች እጅግ መርዛማ ምግብ ነው።

👉 ዝሆኖች በየቀኑ ለሁለት ሰዓታት ብቻ ይተኛሉ።

👉 ዶሮዎች ከሰዎች የበለጠ ቀለሞች ማየት ይችላሉ ።

👉 ሙሉ ጨረቃ ከግማሽ ጨረቃ በ 9 እጥፍ የበለጠ ብሩህ አላት።

#ቅምሻ

🌿 @Literature_For_God 🌿

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

26 May, 07:16


#አንቲ
🌿 @Literature_For_God 🌿

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

23 May, 18:23


#አንቲ
🌿 @Literature_For_God 🌿

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

23 May, 18:19


ውድ የስነ-ጽሁፍ ለእግዚአብሔር ቻናል ቤተሰቦች የተለያዩ አስተማሪ ትረካዎች ግጥሞች ስነ-ጽሁፍ ነክ የሆኑ ጽሁፎችን በማንበብ እንዳትሰላቹ በድምጽ ልናቀርብላችሁ አስበናል በመሆኑም አብሮነታችሁ አይለየን ተባረኩ

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

19 Apr, 10:59


👏 ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ 👏


@Literature_For_God

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

19 Apr, 10:57


" እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።" (ኢሳ 53: 5)

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

14 Apr, 17:09


……የኢየሱስ ልጅ

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

19 Mar, 19:52


አሁን ላይ ካለው ክፉ የሞት መቅሰፍት ሊያስመልጠን የሚችለው ብርቱ የእግዚአብሔር ክንድ ነው ለምድራችን እንጸልይ ቅዱሳን!

ነነዌ ትምጣልን!

ሀጢያታችን በዝቶ መስመር ብንስትም
ቁጣህ በኛ በዝቶ ቅጣት ብትመርጥም
እባክህ አባት ሆይ በምህረት አስበን
በፊትህ እንውደቅ ነነዌ ትምጣልን

(ትንቢተ ዮናስ 3 )
------------
1፤ የእግዚአብሔርም ቃል ሁለተኛ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ።
2፤ ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ የምነግርህንም ስብከት ስበክላት አለው።
3፤ ዮናስም ተነሥቶ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም የሦስት ቀን መንገድ ያህል እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች።
4፤ ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም። በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ።
5፤ የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።
6፤ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ።
7፤ አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥ እንዲህም አለ። ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፤
8፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።
9፤ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?
10፤ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።
ቤki

😭 @Literature_For_God 😭

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

17 Mar, 13:16


የልብ ቀለበት
አስቤያት በማላውቃት በአንዲት ቅዱስ ቀን በጥልቅ ፍቅር ውስጥ ወደኩኝ እንዴት እንደሆነ ያልገባኝ አንዳች ሀይል ልቤን ሲንጠው ተሰምቶኛል መኖሬን እንድናፍቅ ሆኛለሁኝ ለካ ፍቅር በመኖር የተገመደ ግማድ ነው ፍቅር ውስጥ ስንሆን እንደ አዲስ እንወለዳለን ልንገልፀው የማንችለው ሀሴት ልባችንን ይሞላል ነፍሳችን በውሀ ላይ እንደ ተንሳፈፈች ያህል እንሆናለን የሚታየን ሁሉ መልካም ነገር ነው በዙሪያችን ድቅድቅ ጨለማ ቢሆንም ብርሀናማው ፍቅር ግን የልባችን ፋና ነው በፅልመቱ ላይ እሱ ታላቅ ነው የነገሰብን ጨለማ በፍቅር ብርሀን ፊት ክብሩ ይገፈፋል እናም በቅፅበት በፍቅሩ ለጣለኝ የልቤ ንጉስ ለሆነው እንካ ልቤን ቀለበት ይሁንህ አልኩት ልቤን ከማንነቱ'ጋ አቆላልፌ ትዳሩ ሆንኩለት ልታመንለት ዘመኔን ልሰጠው በክብር ዙፋኑ ስር ተንበርክኬ ቃል ገባሁለት ይቺ ከንቱ አለም ለክፉ ምኞቷ ልትድረኝ ቀን ስትቆርጥልኝ የልብ ሙሽራዬ ሳይታሰብ ከተፍ አለ
ሆ....ሙሽራዬ....የልብ ቃልኪዳኔ...የሂወቴ ጌታ....የዘመኔ አለቃ.... እንካ...ልቤን...
ቃልኪዳኔ እንዲሆን ሰጠሁህ አልኩት ክፉ አይኖች የማያዩት ሌቦች ሊሰርቁት በማይቋምጡለት የልቤ ማህደር ላይ በምህረትህና በፍቅርህ ገምጄ የቃልኪዳን ቀለበቴን አጠለኩኝ ሰማያት በእልፍ ደስታ አሸበሸቡ ንፋሳት በእልፍ በምስጋና አፋጩ ነፍሴም ከከፍታው በላይ ተቀመጠች እሱ የኔ የዘመኔ ሚስጢር ነው በጠላሁት በዛ ክፉ ዘመን ቀራንዮ መድረክ ላይ በትኩስ ደም በተለወሰ መስቀሉ ፍቅሩን ነገረኝ ለእጅ መንሻም እንዲሆን በባዶ ዋሻው ውስጥ ስጋውን ለኔ ስጦታ አድርጎ ሰጠኝ ለኔ ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ በብዙ ተንገላታ ቆሰለ የህማም ሰው ሆነ ያ እርህራሄ በጉልህ የሚስተዋልበት ደግ ፊቱ የደም ጎርፍ ለበሰ የፍቅር ጥግ ምን ያህል እንደሆነ ነግሮኝ ሳይሆን ሆኖ አሳየኝ ከበዛ ፍቅር የተነሳ ትንሿ ልቤ ለትልቅ ፍቅሩ ተንበረከከች ለሱ ልትሆንለት ለሱ ልትኖርለት የዘላለም ቀለበትን አጠለቀኝ በታማኝነት እድሜ ዘመኗን ልትኖርለት በአባቱ ፊት ዘላለማዊ በሆነው ዙፋኑ ፊት ማንነቷን አስቀምጣ አለች
"፤ እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በመድኃኒትህ ደስ ይለዋል። "
(መዝሙረ ዳዊት 13: 5)

ቤki

🌿 @Literature_For_God 🌿

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

15 Mar, 13:07


#ቅምሻ_Facts

እስከ 1800 ዓ.ም ድረስ በጃፓን ነጭ ጥርስ የአስቀያሚነት ምልክት ተደርጎ ይወሰድ ስለነበር የጃፓን ሰዎች ጥርሳቸውን ለማሳመር ጥቁር ቀለም ይቀቡ ነበር😁

👉ምንጭ ቅምሻ

🌿 @Literature_For_God 🌿

ስነ-ጽሁፍ ለ እግዚአብሔር

15 Mar, 07:08


🌿መንፈሳዊ ጽሁፎች
🌿 አስተማሪ ልብ-ወለዶች
🌿ግጥሞች
🌿አስገራሚ መረጃዎች
🌿 ድንቅ ድንቅ ዝማሬዎች
😊በእርሶ ቻናል😊

https://t.me/Literature_For_God