WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ) @wcumsj2015 Channel on Telegram

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

@wcumsj2015


ይህ የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመአ ኦፊሲየል የቴሌግራም ቻናል ነው!!

This is the official channel of Wachemo University Muslim Students jamea.
በዚህ channel ላይ:-
① የሚቀሩ ቂርዓቶችን
② የሚደረጉ ሙሀደራዎችን ማዳረስ ፡፡
③ እንድሁም ሌሎች ዲናዊ ምክሮች ይላኩበታል

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ) (Amharic)

ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመአ ኦፊሲየል እናትህን ቋናው ነው! ይህ አንድ አማራኛ በላይ ቴሌግራም ቻናል ነው፡፡ ከዚህ ትግርኛ በተገኝበትምህ ቦታ:- ① አዋዛ አድርጎአል፡፡ ② አማን ፍራጁለን በስጦችህ እናጠቃለን፡፡ ③ የዲናዊ ምክርዳቸውን እንዲቋረጥ በእርስዎ የቻናሉን እያተመልኩህ እንነጋለን፡፡ ለማስጠበቅ ከቀጣሪት እንደገለጠ እንመለከታለን! @Wcumsj1_bot

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

19 Nov, 06:34


السلام عليكم ورحمة الله  وبركاته

🏝 በ2017 ምድባችሁ ዋቸሞ  ዩኒቨርሲቲ ለሆናችሁ አዲስ ገቢ(fresh)  ሙስሊም እህት እና ወንድሞቻችን

➩ በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን። ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ ለዚህ  እንድትበቁ ላስቻላችሁ ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን። እንደ አንድ አካል ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን!

🔎 በመቀጠል የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት እና ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።

🕋  ስለሆነም እናንተ እህት እና ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያዛምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እናሳውቃለን ‼️
    
👌 ፈድሉ ከድር  (main campus )
📲 +521937240724

👌ነስረዲን ሙሐመድ (main campus )
📲 +251961203437

👌 ሀብታሙ አብደላህ (Main campus )
+251996789829
...............................................
..................................................

👌Yunus ... (Durame campus)
📲 +251943740992

👌 nesredin ebrahim
           (Durame campus)
📲 +251912685088


✍️ የእህቶችን ስልክ ለማግኘት  
📲 +251937240724

📝 የዋቸሞ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት (ጀምዓ)

https://t.me/WCUMSJ2015

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

18 Nov, 19:11


የሙናፊቆች ጉድ
➫➫➫➬➬➬
🟢 ያመኑ መሳይ አጭበርባሪዎች

🟢 ሁለቱ ፈተናዎች

🟢 የጠፉ ህዝቦች ዜና አልደረሳቸሁም?

🟢 የዘመናችን ሙናፊቆች


🎤 ሸምሱ (አቡ ሀመዊያ) ሀፊዘሁሏህ

➻ "የሙዕሚኖች መታደል" በሚል ርዕስ የቀረበውን ትምህርት ለማግኘት
➷➷➷➴➴➴➘➘➘➘➘➘ https://t.me/AbuImranAselefy/3175

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

15 Nov, 13:38


ስለ ሞት

16 mb

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

15 Nov, 05:37


የፈለከዉን ስራ !!! አላህ ዘንድ  ለብቻህ የማይቀር የምትመረመርበት ቀጠሮ አለህ

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

14 Nov, 20:34


📚📚 قال ابن الجوزي – رحمه الله تعالى – :

" وَاعْلَمُوا رَحمكم اللهُ أََنَّ فِي الصَّلَاةِ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ صلى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم عَشرَ كَرامَاتٍ.

🍃 إِحْدَاهُنَّ صَلَاة الْمَلِكِ الْجَبَّار.
🍃  وَالثَّانيَِةُ شَفَاعَةُ النَّبِيِّ الْمُخْتَارِ.
🍃 وَالثَّالِثَةُ الِاقْتِدَاءُ بِالْمَلَائِكَةِ الْأَبْرَارِ.
🍃 وَالرَّابِعَةُ مُخَالفَةُ الْمُنَافِقِينِ وَالْكفَّارِ.
🍃وَالْخَامِسَةُ مَحوُ الْخَطَايَا وَالْأَوزارِ.
🍃 وَالسَّادِسَةُ قَضَاءُ الْحَوَائِجِ وَالْأَوْطارِ.
🍃وَالسَّابِعَةُ تَنوِيرُ الظَّوَاهِرِ والأَسرارِ.
🍃 وَالثَّامِنَةُ النَّجَاةُ مِن عَذَابِ دَارِ الْبَوَارِ.
🍃 والتاسعةُ دُخُولُ دَارِ الرَّاحَةِ والقرارِ.
🍃 وَالعاشرةُ سَلامُ الْمَلِكِ الْغَفَّارِ".
اهــــــــ [بستان العارفين ٢٩٧].


اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.

🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃

قَــال رَسُـــــولُ اللهِ
صلى الله عليه وسلم:
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹 "...وَالكَلِمَةُ الطَّيِّبَةُ صَدَقَةٌ" رواه مسلم🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በአሏህ ፍቃድ የተለያዩ ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ።👇👇👇👇👇👇👇👇


አቡ ኑዐይም - Sultan Hassen
ይህ የአቡ ኑዐይም ሱልጣን ሐሰን ቻናል ነው
https://t.me/abunueaymsultanhassen

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

14 Nov, 14:09


# አዲስ ማስታወቂያ

ለአዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

14 Nov, 05:34


👉 ቀን ጥሎኝ ብታየኝ

አንዳን ንግግሮች ባለቤታቸው ቦታ ሳይሰጣቸው ይናገራቸውና ዱንያውንም አኼራውንም የሚያበላሹ ይሆናሉ ። ከእንደነዚህ አይነት ንግግሮች ውስጥ ምን ታረገው ቀን ጥሎኝ አይተኸኝ የሚለው ሲሆን ሀብታም የነበረ ወይም በጀግንነቱ የሚታወቅ የነበረ ወይም ትልቅ ስልጣን የነበረውና በኋላ ሁኔታዎች የተቀየረበት ሰው የሚናገረው ይገኝበታል ። እንደዚሁ አንዳንድ እህቶች በተለይ ዐረብ ሀገር ያሉ ስራ ፈተው ለብዙ ጊዜ በመቀመጥ ሲቸገሩና ሲከሱ ሲጎሳቆሉ ይህን ንግግር ይጠቀማሉ ።
በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች የዚህን አይነት ንግግር መናገር ወንጀሉ በጣም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ከዐቂዳ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ነው ።
በመጀመሪያ አንድ ሙስሊም የሚናገረውን ንግግር አስቦና የሚያመጣውን ጥቅምና ጉዳት አመዛዝኖ መናግር ነው ያለበት ። የአላህ መልእክተኛ ሳያመዛዝን የሚናገር ሰው ንግግሩ የሚያመጣውን መዘዝ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ : –
عَنْ أَبي هُرَيْرَةَ أَنَّهُ سَمِعَ النَّبيَّ – ﷺ – يَقُولُ : 
" إنَّ الْعَبْد لَيَتَكَلَّمُ بِالكَلِمةِ مَا يَتَبيَّنُ فيهَا يَزِلُّ بهَا إِلَى النَّارِ أبْعَدَ مِمَّا بيْنَ المشْرِقِ والمغْرِبِ ".
متفقٌ عليهِ
" አንድ ሰው አንዲትን ንግግር የሚያስከትለውን ሳያውቅ ይናገርና ከፀሀይ መውጫ እስከ ፀሀይ መግቢያ ርቀት ወዳለው እሳት ይወድቃል " ።

ተመልከቱ እንደቀልድ በተናከርነው አንድ ንግግር የሚመጣው ውጤት ። ቀን ጥሎኝ የሚለው ንግግር ደግሞ በጣም አደገኛና ዱንያንም አኼራንም የሚያጠፋ ነው ። አንድ ሰው ይህን ንግግር ሲናገር ቀን መጣልና ማንሳት ( ማበልፀግና ማደህየት ) ይችላል የሚል እምነት ኖሮት ከሆነ ይከፍራል ከእስልምናም ይወጣል ። ነገር ግን ይህ እምነት ሳይኖረው እንደቀልድ ከሆነ የተናገረው ትንሹ ሽርክ ነው ። ይህ ማለት ከከባባድ ወንጀሎች ይመደባል ። ምክንያቱም ቃሉ ቀን መጣል ይችላል የሚል መልእክት ስለያዘ ።
በመሆኑም ሙስሊም የሆነ ሰው ከመናገሩ በፊት ስለሚናገረው ነገር ማወቅና ማመዛዘን ይኖርበታል ። ከዚህ በተጨማሪ ቀኑን በመኮነን መልኩ ከሆነ ሌላ ጥፋት ነው ። ምክንያቱም ቀን ምንም ነገር ማድረግ አይችልም ። የአላህ ስራ የሚያርፍበት ብቻ ነው ። ይህ ከሆነ የምንኮንነው አላህን ነው ማለት ነው ። ቀን ይነጋል ይመሻል የሚያመሸውና የሚያነጋው አላህ ነው ። ለዚህ ነው ዘመንን አትስደቡ የተባለው ። ምክንያቱም ዘመን የአላህ ስራ ማረፊያ ከሆነና በቀኑ ውስጥ የሚከሰቱ ነገሮች የሚያስከስታቸው እሱ ከሆነ የምንሰድበው አላህን ነው ማለት ነው ። !!! ይሄ ደግሞ ዱንያንም አኼራንም የሚያጠፋ ወንጀል ነው ።
አንድ ሰው በየትኛውም ጊዜ ምንም ነገር ቢደርስበት ይህ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው የደረሰው ብሎ ማመን አለበት ። ይህ በቀደር ማመን ይባላል ። በቀደር ማመን ደግሞ የኢማናችን አስኳል ነው ። በሌላ አባባል አሁንም ቀን ጥሎኝ የሚለው ንግግር ከቀደር ጋር ያጋጨናል ማለት ነው ። ምክንያቱም በአላህ ውሳኔ ያመነ ሰው በማንም በምንም አያማርም ። ይልቁንም አላህ ወስኖ ያሻውን ሰራ ነው የሚለው ። በዚህም ወደ አላህ ይቃረባል የአላህንም ውዴታ ያገኛል ። በቀን ማማረር ትርፉ ኪሳራ ነው ።
ሌላው መከራም ይሁን ችግር የሚያገኘን በሰራነው ወንጀል መሆኑን ማመን ይኖርብናል ። የበሽታና የርዝቅ እጥረት መንስኤ የራሳችን ወንጀል ነው ። በተለይ ዐረብ ሀገር ያላችሁ እህቶች መጀመሪያ ከሀገር ያለ መሕረም ስትወጡ ጀምሮ ወንጀል ላይ ወድቃችኋል ። እዛ ሆናችሁ አላህን ፈርታችሁ ላለፈው ተፀፅታችሁ ወደ አላህ መቅረብ ይኖርባችኋል ። በተለይ ኢጃዛ በምትወጡ ጊዜ አላህ ካዘነላት ውጪ አብዛኛዎች እህቶች ወንጀል ላይ ነው የሚዘፈቁት ። ከአጅ ነብይ ወንድ ጋር አብረው ነው የሚሆኑት የዝሙትና የተለያዩ ወንጀል አይነቶች ይፈፀማሉ ።
አላህን ፈርተናል የሚሉ እህቶችም ቢሆን በራሳቸው ቤት መከራየት ስለማይችሉ አንድ ወንድ ከ20 – 30 ሴቶችን ይሰበስብና ያችንም እቺንም አገባሻለሁ እያለ እየበዘበዘ አላህን ካመፀ በኋላ እነርሱንም አይናችሁ ላፈር ይላል ። በአብዛኛው እንደነዚህ አይነት ወንዶች የሚፈልጉዋቸውን እህቶች በተለያየ የኢጃዛ ጊዜ እንዲመጡ በማድረግ ነው የሚፈልጉትን የሚሰሩት ። ያቺም ከኔ ጋር ነው ትላለች እቺም ከኔ ጋር ነው ትላለች እሱ ግን ከማናቸውም ጋር አይደለም ከገንዘባቸውና ከሸህዋው ጋር ነው ። የዚህ ወንጀል መጨረሻ እህቶችን ቀን ጥሎኝ ነው ብለው ሌላ ወንጀል ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል ።
ለማንኛውም አላህን ፈርተን ቀንን ከመተቸትና አላህን ከሚያስቆጣ ወንጀል እንውጣ ።

https://t.me/bahruteka

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

13 Nov, 08:52


السلام عليكم ورحمة الله  وبركاته

በ2017 ምድባችሁ ዋቸሞ  ዩኒቨርሲቲ ለሆናችሁ አዲስ ገቢ(fresh) ሙስሊም እህት እና ወንድሞቻችን:-

    በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ ለእዚህ እንድትበቁ ላስቻላችሁ ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ አካል ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን !!

   በመቀጠል የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት እና ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን ::
🕋  ስለሆነም እናንተ እህት እና ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያዛምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንዳ  እናሳውቃለን ‼️
    

👌ፈድሉ ከድር ........0937240724(main campus )


👌ነስረዲን ሙሐመድ ....ዐ961203437(main campus )

..................................................
..................................................

👌Yunus .............094 374 0992 ( Durame campus )

👌0912685088 .........nesredn ebrahim (Durame campus )





✍️የእህቶችን ስልክ ለማግኘት   0937240724


የዋቸሞ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት (ጀምዓ)


https://t.me/WCUMSJ1

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

11 Nov, 19:01


የሱብሂን ሶላት መተው እንዲሁም የሱብሂን ወቅት በእንቅልፍ ማሳለፍ ከታላላቅ እርም ከተደረጉ ወንጀሎችና ከሙናፊቆች ባህሪም ነው !

" [ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ]

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

08 Nov, 21:57


የስነ-ምግባር ብልሽት
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯


🏝 በዚህ ዘመን ወጣቶች በተለያዩ ተፅዕኖዎች ምክንያት የስነ-ምግባር ቀውስ ውስጥ ገብተናል። አዎ በሽታችንን ለመደበቅ መሞከር የለብንም። ‟በሽታውን የደበቀ ሞቱ ግልፅ ያደርግለታል„ ከሚባሉት መሆን የለብንም። እንደውም ከራሳችን ጋር ተሳስበን ወደ አላህ መመለስ እና የፀባይ ለውጥ ማድረግ አለብን።

በዚህ ዘመን አንድ ወንድም እንደ አይን ብሌን የሚሳሳላት የእናትቱ ልጅ ትንሽ እህቱ ❝ወንድሜ ሆይ! ጥሩ ባል ፈልግልኝ❞ ብትለው «እሽ እህቴዋ ኢንሻአላህ» ለማለት ይሳቀቃል። ምክንያቱም ወጣቱ በሀይለኛው በምግባር ብልሽት ወረርሽኝ ተለክፏል። ለአቂዳችን ጤነኝነት ለመንሃጃችን መስተካከል የምንጓጓውን ያክል ስነ-ምግባራዊ ለውጥ ለማምጣትም ጥረቶችን ማድረግ አለብን።

👌 በዚህ ጉዳይ ብዙ ከማለት የሚያብቃቃኝ የሚቀጥለው የኡስታዝ ባህሩ ተካ ምክር ነው።

👌 በዚህ ጉዳይ ብዙ ከማለት የሚያብቃቃኝ የሚቀጥለው የኡስታዝ ባህሩ ተካ ምክር ነው።
👉 የሰለፍይ ስነ-ምግባር
➪➩➪➩➪➩➪➩➧

የተከበራችሁ ውድ ሰለፍይ ወንድምና እህቶች አብዛኞቻችን የሰለፍያ ዐቂዳን የተረዳንበት መንገድ ትክክል ነው ለማለት የሚያስደፍር ስለማይመስል ለግንዛቤ ይሆን ዘንድ ስነ-ምግባርና ተያያዥ ባህርያቶች ከዐቂዳችን ጋር ያላቸው ግንኙነት ለመግለፅ ወደድኩኝ

➜ የሰለፍያ ዐቂዳ ለዋዚሞችና ፍሬዎች እንዳሉት ማወቅ በሁላችንም ላይ ግዴታ ነው። አንድ ሰው ዐቂዳው የተስተካከለ ከሆነ ይህ የተስተካከለ ዐቂዳ ግድ የሚላቸውና የሚያፈራቸው ፍሬዎች ይኖራሉ። የተስተካከለ ዐቂዳ ግድ ከሚላቸው ባህሪያቶች ውስጥ ጥቂቶቹን ለማየት፦
➩ ከውሸት፣
➪ ከማታለል፣
➩ ከሌብነት፣
➪ ወሬ ከማቀበል፣
➩ ሰው ከማጣላት፣
➪ ከሀሜት፣
➩ እምነት ከማጉደል፣
➪ ቃል ከማጠፍ፣
➩ ቀጠሮ ከማፍረስ፣
➪ የወላጆችን ሀቅ ካለመጠበቅ፣
➩ ጎረቤትን አዛ ከማድረግ፣
➪ ጓደኛን ከማስቀየም፣
➩ ከምቀኝነትና
ከመሳሰሉ ተግባሮች መራቅ ይገኙበታል።

የተስተካከለ ዐቂዳ ከሚያፈራቸው ፍሬዎች ጥቂቶቹን ለማየት
➫ መልካም ስነምግባር፣
➬ አዛኝነት፣
➫ ሰውንማክበር፣
➬ በትንሹ መብቃቃት፣
➫ እውነተኝነት፣
➫ ታማኝነት፣ እንዲሁም ከላይ የጠቀስናቸው ባህሪያት ተቃራኒያቸውን ማስገኘት ይገኙበታል።
በመሆኑም አሁን የምናያው የአብዛኛውዎች ሰለፍዮች ስነምግባር ከዚህ በእጅጉ የራቀ መሆኑ ትክክለኛ ዐቂዳ ምን እንደሆነ ካለመረዳት የመነጨ እንደሆነ ያመለክታል። ትክክለኛ ዐቂዳ ሙሉ እንዲሆን እየጨመረ እንዲሄድ እነዚህ ስነ-ምግባሮች ጉልህ ሚና ይጫወታሉ። በተቃራኒው የእነዚህ ስነ-ምግባሮች አለመስተካከል ዐቂዳች ሩሕ የሌለው በነዘሪያት (ከተግባር ባገለለ እይታ) ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያደርገዋል። ትክክለኛ ዐቂዳ መልካም ስነምግባር ቅባቱ ነው። ይህ ካልሆነ ዐቂዳችን ጎምዛዛ በሰዎች ላይ ተፅኖ የማይፈጥር ይልቁንም ሰዎችን ከትክክለኛ ዐቂዳ እንዲርቁ የሚያደርግ ሊሆን ይችላል። ለዚህ ነው መልካም ስነምግባ በእስልምና በጣም ትልቅ ቦታ የተሰጠው። አንድ ሰው በምንም ነገር ሊደርሰው የማይችለውን የኢማን ማማ ላይ እንዲደርስ የሚያስችለው መልካም ስነምግባር ነው የተባለው። በመሆኑም አብዛኞቻችን ራሳችንን መፈተሽ ይገባናል።

➨ ሰለፍይነት በሙኻሊፍ ላይ መልስ መስጠት፣ ከእነርሱ ማስጠንቀቅ፣ እነርሱን መጥላት ብቻ አይደለም። ይህ በጣም ተፈላጊ ከመሆኑ ጋር ስነምግባራችን እንደ አባጨጓሬ የሚኮሰኩስ ከሆነ ለሰዎች ሂዳያ ሰበብ ልንሆን አንችልም። ይልቁንም ሰዎች የሰለፍያን ዳዕዋ እንዲጠሉ ሊያደርጋቸው ይችላል። ከዚህ የከፋው ደግሞ በእጃችን ላይ ያሉ ወንድሞች በከፊሎቻችን ያልተገባ ስነምግባር ከእጃችን ሊወጡ ይችላሉ ይህ ደግሞ ካፒታልን ማጣት ማለት ነው።

እንደሚታወቀው ካፒታልን መጠበቅ ትርፍ ከመፈለግ ቅድሜያ የሚሰጠው ተግባር ነው። እየአንዳንዱ ሰለፍይ ሌላውን የመጠበቅ ሀላፊነት አለበት። ክፍተት ሲኖር ክፈተቱን መዝጋት፣ ድክመቱን ለማስወገድ መጣር በጣም አስፈላጊ ነው። በኛ አላስፈላጊ ስነምግባር የሰለፍያ ገፅታ መበላሸት የለበትም ለዚህ ሰበብ ከመሆን መጠንቀቅ አለብን አላህ ይርዳን።

📝 በኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ አላህ ይጠብቀው @bahruteka

ወዳጄ ሆይ! ሰለፎቻችንን መከተል ማለት በሁሉም ነገራችን እንጂ በከፊሉ ማንነታቸው ጠንካራ ሆነን ልንኮፈስ አይደለም። የሰለፎችን ህይወት 100% ማሟላት እንደማንችል ግልፅ ነው። ነገር ግን በሁሉም የህይወት እንቅስቃሴዎቻቸው ለመመሳሰል መሞከር አለብን። እራሳችንን እንተሳሰብ! እስኪ ማንነታችንን እንፈትሽ! ወደ አላህ እንመለስ! ስነ-ምግባርን ማስተካከል የማይቻል ተፈጥሯዊ ችግር አይደለም። ልክ እንደአቂዳህ እንደመንሃጅህ የምታስተካክለው ጉዳይ ነው። አብሽር ወደ አላህ እንቅረብ እንጂ እንስተካከላለን።

📝 ያንተንም የሱንም መስተካከል የሚመኘው ወንድምህ አቡ ዒምራን!

በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

07 Nov, 12:20


ጌታችን አሏህ ሆይ

ህመማቸው ባንተ እንጂ የማይታወቁ
ነፍሶችን ሁሉ ፈውሣቸው።


https://t.me/menhaj_Aselefiya

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

07 Nov, 09:07


السلام عليكم ورحمة الله  وبركاته

🏝 በ2017 ምድባችሁ ዋቸሞ  ዩኒቨርሲቲ ለሆናችሁ አዲስ ገቢ(fresh)  ሙስሊም እህት እና ወንድሞቻችን

➩ በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን። ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ ለዚህ  እንድትበቁ ላስቻላችሁ ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን። እንደ አንድ አካል ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን!

🔎 በመቀጠል የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት እና ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።

🕋  ስለሆነም እናንተ እህት እና ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያዛምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እናሳውቃለን ‼️
    
👌 ፈድሉ ከድር (main campus )
📲 +521937240724

👌ነስረዲን ሙሐመድ (main campus )
📲 +251961203437

..................................................
..................................................

👌Yunus ... (Durame campus)
📲 +251943740992

👌 nesredin ebrahim
(Durame campus)
📲 +251912685088


✍️ የእህቶችን ስልክ ለማግኘት  
📲 +251937240724

📝 የዋቸሞ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት (ጀምዓ)

https://t.me/WCUMSJ2015

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

03 Nov, 03:41


👉 ሸይኽ አልባኒን ያስለቀሰ ታሪክ

ዒሳም ሃዲይ የተባለ ተማሪ ሸይኽ አልባኒን በተኽሪጅ ያግዛቸው ነበር ። ከሳቸው ጋር ወደ አምስት አመት አካባቢ አሳልፏል ። የኢብኑ ሒባንና ኢብኑ አሳኪርን ኪታቦች ተኽሪጅ እየሰራ በነበረበት ጊዜ ሸይኽ አልባኒ በእነዚህ ኪታቦች ውስጥ ለየት ያለ ጠቃሚ ነገር ስታገኝ ንገረኝ አሉኝ ይላል ።
የሲቃት ኢብኑ ሒባንን ኪታብ እያነበብኩ ሳለ የአቡ ቂላባን ታሪክ በአምስተኛው ሙጀለድ መጀመሪያ ላይ ለሸይኻችን ማንበብ ጀመርኩ ። በጣም አስገራሚ ሶብሩን ይናገራል ወደ መጨረሻ አካባቢ ደርሼ ቀና ብዬ ሳይ ሸይኻችን በእንባ ታበዋል ። የለቅሶ ሀይል ከውስጣቸው ገንፍሎ ድምፃቸው እንዲወጣ ስላደረገው ተነስተው ወደ ቤት ገቡ ። ከቆይታ በኋላ ተመልሰው መጥተው በጎረነነ ድምፅ ሰላም ብለውኝ ስራቸውን ቀጠሉ ። ታሪኩ ጠቃሚ ስለሆነ ላቅርብላችሁ ይላል የሸይኽ አልባኒው ተማሪ ዒሳም ታሪኩ እንዲህ ነው ።
ኢብኑ ሒባን ከዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ይዞ እንዲህ ይላል : –
" አንድ ጊዜ ወደ ዳርቻ ሄጄ ዒባዳ ለማድረግ ወጣሁ ። ዳርቻ ላይ ማረፊያችን ከቅጠላቅጠል የተሰራ ዳስ ቢጤ ነው ። ወደ ዳርቻ ስደር አሸዋማ በሆነው በባሕር ዳር ባለው ዳርቻ ላይ የሆነ ድንኳን አየሁ ። ወደ ድንኳንኩ ጠጋ አልኩኝ ። በውስጡ የሆነ ሰው አለ ይህ ሰው ሁለቱም እጅና እግሮቹ የሉም ። አይኑም ተይዟል ፣ ጆሮውም ያስቸግሯል ፣ ከአካሉ ሙሉ ጤነኛው ምላሱ ብቻ ነው ። ጠጋ ስል እንዲህ እያለ ዱዓእ ያደርጋል : –
" አላህ ሆይ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋና ከብዙ ፍጥረታቶችህ ለማስበለጥህ የማሸኩርበት ምስጋና እንዳመሰግንህ አድርገኝ " ።!!!
ዐብዱላህም በአላህ ይሁንብኝ ይህን ሰው ቀርቤ መጠየቅ አለብኝ የትኛው ፀጋ ነው አላህ ከሌሎች አስበልጦ የሰጠው ? ፈህም ነው ወይስ እውቀት ወይስ ኢልሃም ነው አላህ በልቡ ላይ የጣለለት አለ ። ዐብዱላሂ ሄደና ሰላም ካለው በኋላ ስታደርገው የነበረውን ዱዓእና ምስጋና ሰምቻለሁ ከአላህ ፀጋዎች የትኛውን ነው የምታመሰግነው አልኩት ይላል ። እንዲህ ብሎ መለሰልኝ : –
" አላህ በኔ ላይ የዋለውን ፀጋ አታይምን አላህ ሰማይን እሳት እንድታዘንብብኝ አዞ ቢያቃጥለኝ ፣ ተራራን አዞ ቢያጠፋኝ ፣ ባሕርን አዞ ቢያሰምጠኝ ፣ ምድርን አዞ ቢውጠኝ አሁን ካለሁበት ምስጋና አልወገድም ነበር ። እሱን የማመሰግንበት ምላስ እስከሰጠኝ ድረስ !!!!! ነገር ግን እስከመጣህ ድረስ ካንተ አንድ ሀጃ አለኝ ። እንደምታየኝ እኔ ራሴን መጥቀም አልችልም አንድ ልጅ ነበረኝ የሶላት ሳአት ሲደርስ ውዱእ የሚያስደርገኝ ፣ ሲርበኝ የሚያበላኝ ፣ ሲጠማኝ የሚያጠጣኝ, ነገር ግን ከሶስት ቀን ጀምሮ አጣሁት እኔ እንደምታየኝ ነኝና እስኪ ፈልግልኝ አለኝ ። በአላህ ይሁንብኝ አንድም ሰው በሰው ሀጃ አይሄድም በምንዳ የላቀ በሆነ ባንተ ሀጃ ከመሄድ የበለጠ ብዬው ፍለጋ ቀጠልኩ ።
ብዙም ሳልቆይ በሁለት ኮረብታዎች መካከል አሸዋማ በሆነ ደለል ላይ አውሬ በልቶት አየሁ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ብዬ በምን መልኩ ነው ቀርቤ የሆነውን የምነግረው ብዬ ጭንቀት ውስጥ ገባሁ ። የተወሰነ ጊዜ በሀሳብ ከተሰወርኩ በኋላ መመለስ ጀመርኩ ።
መንገድ ላይ እያለሁ የነብዩላሂ አዩብ ታሪክ ትዝ አለኝ ። ከዛም ደርሼ ሰላም አልኩት መለሰልኝ ቀጥሎም አንተ ጓደኛዬ ነህ አይደል አለኝ አው አልኩት ። ጉዳዬን ምን አደረከው አለኝ ።
እኔም አላህ ዘንድ አንተ ነህ ወይስ አዩብ ነው የበለጠ ቦታ ያለው አልኩት ።
እሱም አዩብ አለኝ ።
እሺ ጌታው ምን እንዳደረሰበት ታውቃለህ አይደል በአፍያው ፣ በልጆቹና በሀብቱ ፈትኖታል አይደል አልኩት ።
እሱም አው አለኝ ።
ታዲያ ጌታው እንዴት አገኘው አልኩት ።
እሱም ታጋሽ ፣ አመስጋኝ ሆኖ አገኘው አለኝ ።
አዩብ ጌታው በሱ ላይ ያደረሰበትን ቤተሰቦቹንና ጓደኞቹን እስከሚያስገርም ወዶ ተቀብሏል አይደል አልኩት ።
እሱም አው አለኝና አሳጥረው አላህ ይዘንል አለኝ ።
ልፈልገው የላክኸኝ ልጅ አውሬ በልቶታል አላህ አጅርህን ያብዛልህ ትእግስቱንም ይስጥህ አልኩት ።
የመከራው ባለቤትም እንዲህ አለ " ምስጋና ለዚያ ከዘሬ ውስጥ እሱን አምፆ በእሳት የሚቀጣው ያልፈጠረ ለሆነው ጌታዬ የተገባ ይሁን " ብሎ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን አለና የማቃሰት ድምፅ አውጥቶ ሩሑ ወጣ ። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ብዬ ትካዜ ውስጥ ገባሁ ።
ትቼው ከሄድኩኝ አውሬ ይበላዋል ቁጭ ካልኩም ምን እንደማደርግ አላውቅም ብዬ በላዩ ላይ በነበረው ፎጣ ሸፍኜው ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ። ብዙም ሳይቆይ አራት ሰዎች ሲያልፉ አዩኝና መጡ ። ምንድነው ነገርህ አሉኝ ታሪኩን ነገርኳቸው ። እስኪ ክፈተው አሉኝ ከፈትኩት ። ተንበርክከው በአይኖቹ መካከል ይስሙት ጀመር ሐራም ያላየ አይን ይላሉ ። እጅና እግሮቹን እየሳሙ ሰው ሲተኛ ለጌታቸው በመስገድ ያልተኙ አካሎች ይላሉ ። አላህ ይዘንላችሁ ለመሆኑ ይህ ሰው ማን ነው አልኳቸው ። እነርሱም አላህና ነብዩን በጣም ይወድ የነበረው አቡ ቂላባ የኢብኑ ዐባስ ባልደረባ ነው አሉኝ ።
አጥበን እኛ ጋር በነበረ ልብስ ከፍነን ቀበርነው ። ሰዎቹም ሄዱ እኔም ወደ ዒባዳ ቦታዬ ሄድኩ ። ማታ ላይ ጋደም አልኩኝ የተኛ ሰው እንደሚያየው ያን የአላህ ባሪያ በጀነት ጨፌ ላይ የጀነት ልብስ ለብሶ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ ሲቀራ አየሁት :–

«سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ»
الرعد ( 24)
«ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)፡፡

አንተ ያ ጓደኛዬ አይደለህምን አልኩት ። አው አለኝ ። ታዲያ ይህን ደረጃ እንዴት አገኘኸው አልኩ ። አላህ ደረጃዎች አሉት በመከራ በመታገስ ፣ በደስታ በማመስገን ፣ አላህን በድብቅም በግልፅም በመፍራት እንጂ የማይገኝ አለኝ " ።

አስሲቃት ሊብኒ ሒባን የአምስተኛው ሙጀለድ መጀመሪያ የአቡ ቂላባ ታሪክ

https://t.me/bahruteka

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

31 Oct, 10:18


ባጢል ቢውለበለብ ይደበዝዛልና አትሸወድበት !

ባጢልን ይዞ ስሜትን ተከትሎ መዝለቅ አይቻልም ከስሜታዊነት ወጥቶ ሀቅን ቁርዓንና ሀዲስን መመሪያችን ስናደርግ ብዙ ያጣናቸውን ነገሮች አግኝተን በሀቅ ላይ ሆነን ከፍ ማለት ይቻላል ።

በባጢል ግን መቼም አትሸወድ ሜዳ ላይ ጥሎህ ላሽ ይላል ።

* وقل جاء الحق وزحق الباطل إن الباطل كان زحوقا

ባጢል ጠፊ ነው እመን ግድ የለሀም ሀቅ ምንም ቀጭን መስላ ብትታይህ ታዛልቃልችና ያዛት ።

قال ابن أبي حاتم: «سمعت أبا زرعة يقول كتب إليَّ إسحاق ابن راهويه: لا يهولنك الباطل؛ فإن للباطل جولة ثم يتلاشى».

«الجرح والتعديل» ٣٤٢/١.

~ ባጢል ምንም እንዳያስፈራህ ባጢል ሲጀምር ዙር መዞር እና መዳረስ አለው ከዛ በኃላ ይደበዝዛል ይላሉ ።

https://t.me/abuabdurahmen

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

31 Oct, 06:49


ኒቃብ አውልቂ አለ...?
▰▱▰▱▰▱⁉️

🏝 ሰውነታቸውን ለሸፋፈኑ የምድራችን ከዋክብት ለሆኑት ኒቃቢስቶች መነቃቃት የሚሰጥ በተቃራኒው በኒቃብ ጥላቻ የሰከሩ ሰዎችን ልክ ልካቸውን የሚናገር አስፈላጊ መልዕክት ከእህታችን ተላልፏል
ይሄው ➴➴➴➴➴
እንደው ግርም ይላል
               የሰው ልጅ አህዋሉ
ሀላልን ሀርሞ ሀራም መሀለሉ

🌄 በነጋ በጠባው በላ እየዘነበ
ለምን ይሆን ግን ተውበት ያላሰበ
📝
ሱናን ማጥበቅ ትቶ
               ለወንጀል ይሮጣል
ሰለፍያ አትበሉ አትለዩን ይላል

የነብዩን መንገድ ቀናውን ጎዳና
እርቆት ይጓዛል ወንበርን ልመና

➩➩➩
ጊዜ የማይፈታው የሴት ልጅ ሰቆቃ
እኔስ ግራ ገባኝ መቼ ነው ሚያበቃ
🚥 አላህ ያዘዛትን ኒቃቧን ጠብቃ
👉 ልማር በማለቷ ደረሰባት ሲቃ

⁉️
ምንድን ነው ጥፋቷ ምንድን ነው በደሏ
ትዕዛዝ አትፈፅሚም አትለብሽም መባሏ
የትምህርት  ቤቱ  አላማ እና ግቡ
ትውልዶችን ማነፅ አይደል ወይ ባግባቡ
🏖
ኒቃብ የለበሰች የሱናዋ እንስት
አተረፈች እንጂ መች አመጣች ክስረት

ጌታዋንም ታዛ ፊቷን ስትሸፍነው
ባይገባህ ነውጂ
             ጥቅሙ ላንተ እኮ ነው

👌
አላህን ያልፈራ ያንተ ብጤ ርካሽ
አይጎነትላትም ያንቺን ኒቃብ ለባሽ
ላንተም ጠቀመችህ ወንጀልህ ላይበዛ
🎞 አለፍ ገደም ስትል ላታደርጋት አዛ
🔦
ባለኒቃቧ እንስት ታዳጊ ወጣቷ
ንግግሯ ቁጥብ ሂጃብ ነው ውበቷ

ብታንገላታትም መጥተህ በትምህርቷ
🔩🔩 እምነቷ ፅኑ ነው አይታይም ፊቷ
🎙
ደግሞ ነግራሃለች በጣፋጭ ቃላቷ
ፈርታህ እንዳልሆነ አንገቷን መድፋቷ

እንባዋን ማፍሰሷ ብሶቷን ማውራቷ
ሰበብ ለማድረስ ነው ይከበር መብቷ

ኒቃቧን ዝቅ አርጋ ፀጉሯን ብታለብስ
💡ያእምሮዋ ስፋት አይምሰልህ ቅንስ
ያንተ ራስ ነው እንጂ ጠቦ የጠበበው
💡 ትርፍና ኪሳራ መለየት ያቃተው
እባክህ ተመለስ ጭንቄህን ሸቅለው
እባክህ አትድከም  ወንጀል አታደልብ

ትምህርት ይቅር እንጂ ይቀጥላል ሂጃብ
አንተ ብትለፈልፍ ላንቃህ እስኪበጠስ
ጥንታዊ ትዕዛዝ ነው የለም የዲን አዲስ

🌐
ብታሳዝኚኝም በዚህ እንግልትሽ
እርግጠኛ ሆኜ አንድ ቃል ልንገሽ

ግርማ ሞገስሽ ነው በኒቃብ መፅናትሽ
ይህ አለባበስሽ ሰውን ያስጨነቀው
አላህ የወደደው ደስ የሚያሰኝ ነው
🔆
የሱ ስይጥንና ያ ስድ አደግነት
ከውርደት ያለፈ አላሳየም ስኬት

ሴትና ወንዶቹ አይለዩም በቅጡ
አንድ አይነት ሀረካት ለብሰው እየወጡ
እሱ እየጠረገ አስባልቱን በሱሪ
ሴቷን ደግሞ ይላል ኒቃብ አትሰሪ
አእምሮው የዞረ ቀን የጨለመበት
ኒቃብ አውልቂ አለ በከረፋ አንደበት
🟰
ነስሩ ከአላህ ነው የኔ ውድ በርቺ
ጀነት ነው አላማሽ
                ሙስሊም ነሽኮ አንቺ
አርአያዎችሽን ቀደምቶችን አርገሽ
የመጣም ቢመጣ በዲንሽ ላይ ታገሽ
🕋
ዛሬ ያንገላታሽ ያ የሰው ሰይጣኑ
አይቀርም አንድ ቀን
                   እንደ ጨው መትነኑ
ትምህርት ምናባቱ ይቅርብሽ ካልሆነ
     ዲንን ከተጋጨ ትውልድ ካመከነ
ከትርፉ ኪሳራው በልጦ ካመዘነ
ትምህርትን መራቁ ላንቺ ኸይር ሆነ
🖼
ኒቃቧን ጠብቃ ትምህርቷን ተምራ
በዱንያ ስትኖር ሆና የሴት አውራ

🎁ስትነግስ ያሳየን ነገም በአኼራ

📥
ያንተም ውድቅ ሀሳብ ላሽቆ የዘቀጠው
ከአንገት መሀል ቆሞ ልሳንክን ይነቀው
እህቴ ከፍ በይ ይፅናልሽ እምነትሽ
ፈላህ መውጫ ይሁን ይህ አለባበስሽ
ዛሬ ያንገላታሽ ትምህርት ሚኒስተር
በጀሀነም ገመድ ሰንሰለት ይታሰር

📝እህታችን ሰሚራ ኡሙ ማሂር
አላህ ይጠብቃት!

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

30 Oct, 11:06


መገላለጥ መሰልጠን ነው ወይስ መሰይጠን!!?

ቆይ ግን ኒቃብ በመልበሷ በመሸፈኗ ምኑ ጋ ነው ጥፋቷ!!! መሸፋፈን ኋላ ቀርነት ነውን!!!?
ስትገላለጥ ግን ሰለጠነች አይደል!!? አሏሁል'ሙስተዓን!!ነገር ግን መገላለጣ መሰይጠን ነው እንጂ መሰልጠን አይባልም!!? ወሏሂ ግልፅ የወጣ ሰይጣንነት ነው:: መገላለጥ የእንስሶች ባህሪ እንጂ የሰው ልጅ ባህሪ አይደለም!
መገላለጥ ስልጣኔ ከሆነማ ቀድመው እንስሳቶች እነ ዝንጀሮ ጦጣ ስልጡን ናቸው ማለት ነው!! ጉድ'እኮነው! አሉ ሸይኹ!!:: ከአርሽ በላይ ያለው አምላካችን ሴት ልጅ እንድትሸፈን ሒጃቧን አጥብቃ እንድንይዝ ነው ያዘዘው! እንጂ እንደ እንስሳቶች እንድትገላለጥ አላዘዘም!! ይሄን መንገድ የሚቃረን የሆነ አካል ሰለጠነ ሳይሆን ሰየጠነ ነው የሚባለው!!!

https://t.me/Mehfuza_os99

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

30 Oct, 08:07


የኒቃቢስቶች ብቻ
🔎🔎🔎🔎🔎

🏝 አንዳንድ ተቋማት ላይ እንደዚህ ልብህን በደስታ የሚሞላ መልዕክት ታያለህ!!! ሀገራችን ጤንነቷ እየተመለሰ ነው ብለህ ታስባለህ

🚥 በሌላ በኩል የተለያዩ የመንግስት ተቋሞች ኒቃቢስቶችን ለማግለል ሲሞክሩ ደግሞ በጣም ያማል። እውነትም ሀገራችን ጤነኞችም በሽተኞችም ያሉባት ነች

አዎ ራቁቷን የምትሄድ ሴት ምንም ሳትባል ሰውነቷን በሰተረች ከተወቀሰች ይህ በሽታ ለመሆኑ አልጠራጠርም።

ሴት ልጅ የፈለገችውን ትልበስ የሚለው ቃል ኒቃብ የፈለገች ለምን ለምን አይፈቅድላትም? ወይስ ለመራቆት ብቻ ነው መብቱ? አይ

👌 የሚያሳዝነው የሙስሊሙ ተወካዮች ነን ብለው ይህንን በማስከበር ፈንታ በተቃራኒው ችግር የሌለው በማስመሰል የሚጥሩ ዱዓት ተብየወች መብዛታቸው ነው።

🤲 አላህ የተሻሻለውን ሁሉ ይምረጥልን!

https://t.me/AbuImranAselefy/9319

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

30 Oct, 08:06


ምኑ ላይ ነው ነውሩ!
⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️

የእምነቷን ትዕዛዝ
አደቡን አክብራ
ትምህርቷን ብትማር
ኒቃብ ከራሷ አስራ
➴➴➴➴➴➴
ምኑ ላይ ነው ነውሩ!
ምንድነው ችግሩ?

በሷ ኒቃብ ማጥለቅ
ተማሪው ታወከ?

ወይስ መምህሩ?
እስኪ የሚያሳምን
❶ አንድ ምክንያት ጥሩ!
⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️

ምክንያት ከሌላችሁ
ሌላ ሴራና እቅድ
ኒቃቡ ብቻውን
በፍፁም አይችልም
ትምህርትን ሊያሳግድ።
🚦🚦🚦🚦🚦🚦🚦🚦🚦

ለኒቃብ ጥላቶች
➴➴➴➴➴➴

በኒቃብ አትምጣ አንደራደርም
በኒቃቡዋ እንጂ በሱሪ አትኖርም

ኢስላማችን ውብ ነው አክብሮ ይዟታል
በኒቃብ ሸፍኖ ከሀራም  ጠብቋታል።
🏝
ሀይማኖትን መርጦ የሚሰራ ስልጣን
እንደመር ተብሎ ሰላም ሚያሳጣን
ስለዚህ   ነቃ   በል  ሀጂ ከብልግና
ኒቃብ እየነካህ የለም ብልፅግና

📝 የተለቃቀሙ

https://t.me/AbuImranAselefy/9320

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

29 Oct, 06:28


ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም!

ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦

‹‹ ከእሳት ሰዎች መካከል ሁለት አይነት ሰዎች አሉ። እኔ ያላየኋቸው ወደፊት የሚመጡ!

አንደኛቸው ለብሰው ያለበሱ (የለበሱት ልብስ ሰውነታቸውን የማይሸፍን) አካሄዳቸው እና እንቅስቃሲያቸው ወደ ፀያፍ ተግባር ያዘነበለ፤ ሌሎችንም የሚያሳስቱ ፀጉራቸው ልክ እንደ ግመል ሻኛ የተከመረ ሴቶች ናቸው። እንደነዚህ አይነቶቹ ሴቶቺ ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም፡፡››

ሙስሊም ዘግበውታል

ሙስሊሙዋ እህቴ እስቲ እራስሽን ከዚህ ሐዲስ አንፃር ቆም ብለሽ ተመልከቺ

~

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

29 Oct, 06:22


የማይካድ ሀቅ

السلفي يدور حيث دار الدليل .


والإخواني يدور حيث دار
الكرسي

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

28 Oct, 12:23


👉 ለፈገግታ

በመፋቂያ ነው ሚስቴን የመታሁት !!!

ባልና ሚስት ተጣልተው ሚስት ሽማግሌ ሰበሰበች ። ሽማግሌዎቹ ከሁለቱም በኩል የተውጣጡ ነበሩ ። ቁጭ ብለው ነገሩን ማየት ጀመሩ ። ባል ሚስቱን ለምን እንደሚመታት ተጠየቀ ። ባልም ሚስቴን የመታኋት በመፈቂያ ነው አለ ። ሽማግሌዎቹም ሚስትን እውነት በመፋቂያ ነው ወይ የመታሽ ብለው ጠየቋት ሚስትም እስኪ መፋቂያውን አምጣው በሉት አለቻቸው ። እስኪ መፋቂያውን አምጣው ተባለ ሲያመጣው ለካስ ዱላ ነው ።


https://t.me/bahruteka

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

28 Oct, 03:31


👉 የአንድን ሰው ሕይወት ለማዳን ሰበብ መሆን የሰውን ልጅ ሕይወት ሁሉ እንደማዳን ነው ።

ውድ ቤተሰቦቻችን በየጊዜው የሚያጋጥሙ የህመም አይነቶች አንዱ ሌላውን እያስረሳ ውስጥን በሐዘን የሚሞላ አእምሮን የሚረብሽ ነው ። የተለያዩ ሰዎች በተለያየ በሽታ ይሰቃያሉ ። ከበሽታ ሁሉ አስከፊውና በአሁኑ ጊዜ እንደወረርሽኝ እየተዛመተ ያለው የካንሰ በሽታ ነው ። በዚህ በሽታ ሰበብ ብዙ ሰዎች ወደ አኼራ ይሄዳሉ ። የአላህ ውሳኔ እንዳለ ሆኖ ቤተሰብ በአቅም ማነስ ምክንያት ማሳከም ባለመቻሌ ነው በሚል ፀፀት ይሰቃያል ። ከእንደነዚህ አይነት ገጠመኞች አንዱ የሆነውን ዛሬ ወደናንተ ለማድረስ ወደድኩ ።
ይኸውም ወንድማችን ሙሀጅር አሕመድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በደም ካንሰር ተይዞ በአሁኑ ሰአት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይገኛል ። ይህ ወንድማችን የኬሞ መድሀኒት የጀመረ ሲሆን ያለበት ሁኔታ ሐኪሞች ተስፋ ሰጪ ነው ይላሉ ። ነገር ግን የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጅ በመሆኑ ለሕክምናው የሚያስፈልጉ ወጪዮችን መሸፈን የማይችሉ መሆኑን ሆስፒታሉ አረጋግጦ ፅፎለታል ።
ከሱ ጋር ያለው አርሶ አደር ወንድሙ በደረሰው ነገር ቅስሙ ከመሰበሩ ባሻገር የወንድሙም ህይወት በሱ ድጋፍ የነበሩ ቤተሰቦቹም ችግር ረፍት ነስቶት የይድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ነው ። ተስፋ የነበረውን ወንድሜ ሰበብ ሆናችሁ አድኑልኝ ይላል ። አይኑ ብቻ ሳይሆን ሁለመናው እያለቀሰ የደረሰበትን ሲናገር ማየት በጣም ይከብዳል ። በጣም ብዙ ጉዳዮች የሚመጡ ሲሆን ወደናንተ የማደርሰው በጣም አሳዛኝና ምንም ሰበብ ከሌላቸው ውስጥ ጥቂቶቹን ነው ። ስለዚህ በአላህ ፈቃድ ከተባበርን አላህ ካልቀደረበት ወንድማችንን ሰበብ ሆነን ማዳን እንችላለን ።
የአንድን ሰው ሕይወት ለማዳን ሰበብ መሆን የሰውን ልጅ ሁሉ ህይወት እንደማዳን ነው ። በመሆኑም ውድ እህትና ወንድሞች ለወንድማችን ጥሪ ምላሽ ሰጥተን ታማሚውን ለማዳን ሰበብ ሆነን የወንድሙን እንባ እንጥረግለት እላለሁ ። በምንም መልኩ አንብበን እንዳናልፈው የምንችለውን እናበርክት ።
የሆስፒታሉ የድጋፍ ደብዳቤ ላይ አካውንትና ስልክ አለ አብሬ አያይዘዋለሁ ።

https://t.me/bahruteka/5492

https://t.me/bahruteka

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

27 Oct, 17:25


🔷 የሰለፍያን ዳዕዋ ለምን ይፈሩታል ?

     ሰለፍያ ማለት ትክክለኛው እስልምና ማለት ነው ። የሰለፍያ ዳዕዋ ሲባል ወደ ትክክለኛው ኢስላም  ነብዩ ፣ ሶሓቦች ፣ ታቢዒዮች ፣ አትባዑ ታቢዒዮችና እነርሱን በመልካም የተከተሉ የኢስላም ሊቃውንቶች ያስተማሩት ኢስላም  ማለት ነው ። ሰለፍያ ዳዕዋው ሲሆን ዳዒው ( ወደዛ ተጣሪው)  ሰለፍይ ይባላል ። ቃሉ የተወሰደው ሰለፍ ( ቀደምት)  ከሚለው ሲሆን ሰለፎች የሚባሉት የመጀመሪያወቹ ኢስላምን በቁርኣንና ሐዲስ አስተምረው ተግብረው ያሳዩት ናቸው ።
      ከዚህ የምንረዳው የሰለፍያ ዳዕዋ ማለት የመጀመሪያው ወደ ትክክለኛ ኢስላም በነብዩና ሶሓቦቻቸው የተደረገው ዳዕዋ ማለት ነው ። ታዲያ ለምን ይሆን ዛሬ የሙስሊም መሪዮች ነን እያሉ ይህን ዳዕዋ የሚፈሩትና የሚጠሉት ? ለምን ይሆን ሁሉም ሙስሊም ነን የሚሉ አንጃዎች ይህን ዳዕዋ ማሰናከል የመጀመሪያ ግባቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱት ? ለእስልምና ታስቦ ወይስ ለሙስሊሙ ? ሁለቱም አይደለም ነው መልሱ ። ምክንያቱም እስልምና ማለት ከሰባት ሰማይ በላይ በጅብሪል አማካይነት በነብዩ ላይ ወርዶ ለተከታዮቻቸው በንግግርና በተግባር ያስተማሩት ስለሆነና የሰለፍያም ጥሪ ወደዛው በመሆኑ ። ለሙስሊሞች ታስቦ ነው የሚለው ውድቅ የሚሆነው ሙስሊሞች በቅርቢቱም ሆነ በመጪው ዐለም ስኬት የሚጎናፀፉት የመልእክተኛውን ፈለግ ተከትለው አላህን በብቸኝነት ሲያመልኩ ነውና ።
     ስለዚህ የትኞቹም የኢስላም አንጃዎች የሰለፍያን ዳዕዋ የሚፈሩትና የሚዋጉት ዝንባሌያቸውንና ጥቅማቸውን ስለሚነካ ነው ። እነዚህ አካላት ለእስልምናና ለሙስሊሙ ነው የምንሰራው የሚሉት ለሽፋን መሆኑ ይፋ የሚወጣው በኢስላም ስም ቀብር ሲመለክ ፣ በኢስላም ስም መውሊድ ሲደለቅ ፣ በኢስላም ስም ሽርክና ቢዳዓ ሲስፋፋ መብት ነው እያሉ የተውሒድን ዳዕዋ ማሰናከል ግብ አድርገው ሲሰሩና ለዚህም ዋጋ ሲከፍሉ ነው ።
     በኢስላማዊ ዳዕዋ ስም ህዝብ ተሰብስቦ ጫት በአይሱዙ በሰለፍ ሲራገፍ እያዩ ምንም ሳይመስላቸው ሰዎችን ከፉጡራን ጋር ሳይሆን ከፈጣሪ ጋር የሚያስተሳስረውን የተውሒድ ዳዕዋን ማጨናገፍን ለኢስላምና ለሙስሊሞች ብለን ነው ማለት ምን የከፋ ቅጥፈት ነው ?
      የተውሒድን ዳዕዋ ለማስቆም መሞከር ፀሀይን በእጅ መዳፍ ብርሃኗን ለመጋረድ እንደመሞከር ነው ። የተውሒድ ዳዕዋ ተቀናቃኞቹ በበዙ ቁጥር እያበበ ይሄዳል ። በደቆሱት ልክ እየጠነከረ ይሄዳል ። ስለዚህ የሰለፍያን ዳዕዋ መዋጋት ትርፉ የሁለት ሀገር ክስረት ነውና ከፍርሃትና ጠላትነት ወጥታችሁ ወደ ሰፉ ግቡ ለበላይነቱ ስሩ እንላችኋለን ።

https://t.me/bahruteka

https://t.me/WCUMSJ2015

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

27 Oct, 11:29


🌾አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ🍀

ኪታብ :-📝ኪታቡ ተውሂድ እና
📝ሹሩጡ ላዒላህ ኢለላህ

ሱቅ ስለሚገኝ መውሰድ ትችላላችሁ ።

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

27 Oct, 09:25


🔷  ሱፍይና አሕባሾች የዼንጤ ድልድዮች

      በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ዼንጤዮች ጌታዋን የተማመነች ጊደር ጅራትዋን ውጪ ታሳድራለች እንደሚባለው የልብ ልብ ተሰምቷቸው እየዘመቱ ነው ። የአክፍሮት ዘመቻቸው በዋነኝነት ቀብር አምላኪዮችን ትኩረት ያደረገ ነው ።
      ኢስላም ከጅምሩ የተዋጋው ኩፍር ቢኖር ቀብር አምልኮትን ነው ። የሚያሳዝነው ግን አሕባሽና ሱፍዮች ቀብር አምልኮትን ኢስላም አድርገው ለማህበረሰቡ በማቅረብ ዘጠና ከመቶ የሚሆነው ሙስሊም ቀብር አምላኪ እንዲሆን አድርገውታል ።
     አሕባሽና ሱፍዮች ይህን ቀብር አምልኮ የሚቃወምን ከእስልምና የሚያስወጣ ተግባርና ክልክል መሆኑን የሚያስተምሩ የተውሒድ ሰዎችን ካፊር ይላሉ ። ማህበረሰቡ የዚህ አይነቱን አስተምሮ እንዳይሰማ በዚህ የተውሒድ ዳዕዋ የተሰማሩ የነብያት ወራሾችን ወሀብዮች በማለት እንደጭራቅ እንዲታዩ ያደርጋሉ ። ከዚህ አልፎ ተርፎ የተለያዩ አጋጣሚዮችን በመጠቀም እድሉን ሲያገኙ በማሳሰር በማስገረፍ የቻሉትን ይሰራሉ ።
     የሱፍይና የአሕባሽ መሪዮች ወሀብዮች ከአባታችሁ የወረሳችሁትን እምነት ሊያስለቅቁዋችሁ ነው በምትችሉት ታገሏቸው ብለው የተውሒድ ሰዎችን እንዲገሉ ያበረታቱዋቸዋል ። ሞራል ይሰጡዋቸዋል ። ምስኪኖቹ የቀብር አምላኪዮች እስልምናችንን ሊያጠፉብን ነው ብለው የህይወት ዋጋ እስከመክፈል ራሳቸውን ያዘጋጃሉ ።
    አላህን በብቸኝነት ተገዙ የሚሉ ዱዓቶችን ከከሀዲያን የበለጠ ይጠላሉ ። የሚሉትን ለመስማት ቀርቶ ማየት አይፈልጉም ። 124 ሺህ ነብያት ሊዋጉት የተላኩበትን ቀብር አምልኮ ኢስላም ነው ብለው የነብያት ተከታዮችን ይዋጋሉ ። ነብዩ የተወጉለትን ፣ ደማቸው የፈሰሰለትን ፣ የተራቡለትና የተጠሙለትን ፣ የተሰደዱለትን ፣ ሶሓቦች የሞቱለትን ፣ ሰባ ሰማኒያ ቦታቸው የተወጉለትንና የተሰየፉለትን ተውሒድ ኩፍር ነው ይላሉ ።
    በተቃራኒው ያወገዙትና ኩፍር ነው ያሉትን ቀብር አምልኮ ኢስላም ነው ይላሉ ።
     ይህ የሱፍይና የአሕባሽ መሪዮች አስተምሮና ተግባር ለዼንጤዮች ወርቃማ እድል ሆኖላቸዋል ። ይህን ክፍተት ተጠቅመው ቀብር አምላኪ ምስኪኖች ጋር ቀርበው እናንተ ሞቶ የበሰበሰን ከምታመልኩ ዒሳ ጌታ ነው ብላችሁ ለምን አትድኑም ቀናቶችን ከፋፍላችሁ ቁጭ ብላችሁ ጫት በመቃም እድሜያችሁን ከምትጨርሱ የሙታን መንፈስ እያመለካችሁ የሲኦል ከምትሆኑ እየሱስ ጌታ ነው ብላችሁ ለምን አትድኑም ይሏቸዋል ።
    ምስኪኖቹ አንድ ቀን ተውበት አድርገው ወደ አላህ ተመልሰው ዘላለማዊ ሕይወት የሚወርሱበትን እድል ትተው የዘላለማዊ ጀሀነም መሆንን ይመርጣሉ ።
     ዒሳ ሁሉን ቻይ የሆነው ጌታ ኣደምን ያለ አባትና እናት ፣ ሓዋን ያለ እናት እንደፈጠረው ሁሉ ያለ አባት ከእናት ብቻ ሁን በሚለው ቃሉ ፈጥሮ ነብይ ያደረጋቸው መሆኑን የሚያስተምረውን ኢስላም ትተው በመርየም ማህፀን ውስጥ ማንኛውም ህፃን የሚያልፈውን ሂደት አልፈው ተረግዘው የተወለዱትን ዒሳን ፈጣሪ ብለው ይከፍራሉ ።
    እነዚህ ምስኪኖች ዒሳ በመርየም ማህፀን ውስጥ ከረጋ ደም ጀምሮ የነበሩ ሂደቶችን አለረፈው ደሙ ስጋ ሆኖ ፣ ስጋው አጥንት ለብሶ ፣ ስጋና አጥንቱ ቅርፅ ይዞ የተለያየ የሰውነት ክፍል እንደ ልብ ፣ ሳንባ ፣ ጉበት ፣ ኩላሊት ፣ ዐይን ፣ ጆሮ ፣ አፍና አፍንጫ ፣ ጭንቅላትና አእምሮ ፣ እጅና እግር ፣ ሴልና ነርቭ ፣ የውስጥ ሜካኒካል ክፍልና የአእምሮ ኤሌክትሪካል ክፍል ተሟልቶለት ሙሉ ሰው እስኪሆኑ ፍጥረተ ዓለሙን ማን ነበር የሚያስተናብረው ?
    ብለው መጠየቅ አልቻሉም ። እየሱስ ጌታ ነው ሲባሉ እሺ ብለው ተቀበሉ ። ለዚህ የዳረጋቸው ከሱፍያና አሕባሽ የወረሱት የሙታን መንፈስ አምልኮት ነው ።
     እነዚህ የሱፍይና አሕባሽ መሪዮች ወሀብዮችን በሚያስጠቁቁበት ልክ ከዼንጤ አያስጠነቅቁም ። ዼንጤ ልጆቻቸውን ሲከፍር ዱላ ይዘው አይወጡም ። እምነታችሁ ተነጠቀ አይሉም ። ዐቂዳችሁ ተነካ አይሉም ። በምትችሉት ታገሏቸው አይሉም ። የእነርሱ ወኔ በነብያት ወራሽ የተውሒድ ሰዎች ላይ ነው ።
     ለዘህ ነው እነዚህ አካላት የዼንጤዮች ድልድዮች ናቸው ያልኩት ። የአሕባሽና ሱፍዮች የኩፍር ተግባር ነው ምስኪን ቀብር አምላኪያንን ወደ ከፋ ኩፍር ይዟቸው የሚሄደው ።
      በጣም የሚያሳዝነው ነሲሓዎች ከእነዚህ ጋር ነው አንድ ነን ብለው ከኢኽዋንና ሱፍይ እንዲሁም አሕባሽ ጋር አንድነት በመፍጠር እኛ የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ነን ያሉት ።
     በየአካባቢያችሁ ያሉትን የነሲሓ ዱዓቶችን ዳዕዋ አዳምጡ የቀብር አፈር በጥብጦ መጠጣት ፣ በአንዬ ፣ ዳንዬ ፣ አልከስዬ ፣ ቃጥባርዬ ፣ አብሬትዬ ፣ አባድርዬ ፣ ሾንክዬ ፣ ሸከና ሑሰይንዬ ፣ ጀማ ንጉስዬ ፣ ከረምዬ ቀብር ላይ ጠዋፍ ማድረግ ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ ነው የሚል የለውም ።
     ይህን ካሉ ከሱፍይና አሕባሽ እንዲሁም ኢኽዋን ጋር ስለሚጣሉ ። እየአንዳንዱን ወልይ ተብለው የሚመለኩ መሻኢኾችን ስም ጠርተው እዱኝ ፣ አክብሩኝ ፣ አሽሩኝ ፣ እጄን ያዙኝ ዋስ ጠበቃ ሁኑኝ ማለት ኩፍር ነው አይሉም ። የአንድነት  ስምምነቱን ስለሚያፈርስ ። በጥቅሉ ሽርክ ከባድ ወንጀል ነው ይላሉ ። ተውሒድ የነብያት ዳዕዋ ነው ይላሉ ። በዚህም ተከታዮቻቸውን ይሸውዳሉ ። የቱ ምን አይነቱ ተግባር ሽርክ እንደሆነ በዝርዝር አይናገሩም ።
     በመሆኑም ሰለፍዮች ሆይ ኡማውን ከቀብር አምልኮና ከአክፍሮት ሀይላት ለማዳን ያለባችሁ ሀላፊነት ከምን ጊዜውም የከበደ ነው ። ከዚህ ጎን ለጎን ይህን የነብያት ተልእኮ ለዱንያዊ ጥቅም ብለው በመተው በኢስላም የሚነግዱትን ነሲሓዎችንና የእንጀራ አባታቸው ኢኽዋኖችን እንዲሁን እንባ ጠባቂዮቻቸው የሙነወር ልጅና ግብረአበሮቹ ማንነት ለሱናው ማህበረሰብ ግልፅ ማድረግ ሌላው ትልቅ ሀላፊነት መሆኑን መዘንጋት የለባችሁም ።
       አላህ ዲኑን ይረዳል ተውሒድም የበላይ ይሆናል ።

ጠቃሚ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ ።

https://t.me/bahruteka

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

27 Oct, 07:36


Live stream started

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

27 Oct, 06:20


Live stream scheduled for

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

23 Oct, 07:22


ጅልባብም ሆነ ኒቃብ  የምትለብስ እህቶች ጃኬትም ሆነ ሌላ የሂጃቡን መስፈርት የሚያሳጣ ልብስ መደረብ እንደማይቻል ልትገነዘቡ ይገባል....የብርድ ወቅት በሚሆንበት ግዜ ከውስጥ ሙቀት በሚሰጠን መልኩ መደራረብ እንችላለን

የአላህ ሰላም እና እዝነት በዕነዛህ , ጭቆና እና ትችት  ሙቀት እና ብርድ ሳይበግራቸው  የአላህን ትዕዛዝ ምንም ሳያጓድሉ ለመፈፀም በሚታክሩት ላይ ይሁን ።

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

21 Oct, 05:55


የታላቁ ሸይኽ ዐብዱል_ሐሚድ አል_ለተሚይ (ሀፊዘሁሏህ) ሙሉ የቁርዓን ተፍሲር አውርደው ይጠቀሙበት።

#ክፍል
ከሱረቱል
#ፋቲሓ እስከ ሱረቱል #አንዓም መጨረሻ

ለሞባይል በሚመች መልኩ ቁርዓን እየታየ እንዲቀራ ተስተካክሎ የቀረበ

በታላቁ ዓሊም
#ሸይኽ_ዐብዱልሐሚድ አል-ለተሚይ ሀፊዘሁላህ

@Abdul_halim_ibnu_shayk

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

21 Oct, 03:26


ኸዋሪጆች ቁርአን ቀን ና ማታ ይቀራሉ ይስግዳሉ ይቀራሉ ነግር ግን እነሱ ዘንድ ሚዛን የለም
https://t.me/+VgzWTJOEeEVkNDNk

https://t.me/WCUMSJ2015

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

19 Oct, 06:00


🌸የህይወት እንቅፋቶችን አትጥላቸው። 
እነርሱ ላንተ ብለው የተፈጠሩ ናቸው።
የህይወትን ጥፍጥና የምትገነዘበው በነርሱ ውስጥ ነው።

እንቅፋቶች ባይኖሩ የህይወትን ምንነት መረዳት ይከብድህ ነበር።
አስተውል ጨለማ ባይኖር ኖሮ የብርሃንን ጥቅም በቅጡ ባል ተረዳህ ነበር !!

🍃መልካም ውሎ 🎀

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

18 Oct, 18:20


«ኒቃብ ለብሳ መጥፎ የምትሰራ አውቃለሁ» .........ካለህ
....
«ሙናፊቅ ሆኖ ከነብዩ ጀርባ ሶፈል አወል የሚሰግድ ሰው አውቃለሁ»  በለው ።

በሙናፊቁ ምክንያት ሶላትን እንደማንቃወመው ሁሉ በሴቷ ምክንያት ኒቃብን አንከለክልም። በህክምና ስም የሚያጭበረብር ዶክተር ካለ ዶክተሩን እናስወግዳለን እንጅ ህክምናና ሆስፒታልን አንዘጋም።

ጉድለት ያለው ሰዎቹ ጋር እንጂ ዲናችን ላይ አይደለም። የአላህ ዲን ሙሉ ነው።ሰዎች በሚሰሩት ጥፋት የሚወቀሱት ሰዎቹ እንጅ የተደበቁበት ውብ የዲን ድንጋጌ አይደለም።

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

18 Oct, 18:15


ሴኩላር መሆን ማለት ሰው ከጦጣ ነው የሚለውን የዳርዊን ፍልስፍና ተቀብሎ ሰዎችን እንደ ጦጣ እንዲራቆቱ ማድረግ ከሆነ..... እኛ ገላችን ክብራችን እንደሆነና ከጦጣ በተለየ ሰው የሰው ልጅ እንደሆን የምናምን አማኞች እንደሆን ይረዱልን!

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

18 Oct, 10:35


👉ርዕስ--ሒጃብ

ሒጃብ ምንድነው?
ስለሒጃብ ያለን የተሳሳተ ግንዛቤ ምንድነው?
ስለ ሂጃብ ቁርኣን ምን ይላል?ሀዲስስ የሰለፎችስ አቋም ምን ነበር? የመሣሠሉት በቂ ማብራሪያ የተሠጠበት ምክር ነውና ያድምጡና ለሌሎችም
ያስደምጡ



🕌ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ(ዳሩል ሂጅረተይን) መሥጅድ

📆ጥቅምት 8/2016

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

18 Oct, 03:41


ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ያልተጨነቀ አይደሰትም፣ ያልታገሰ አይጣፍጠውም፣ ያልተቸገረ አይደላውም፣ ያልለፋ አያርፍም። ይልቁንስ ባሪያ ትንሽ ከለፋ ረጂም ጊዜ ያርፋል፣ የሰአታት ትዕግስት ለዘላለማዊ ህይወት ትመራዋለች። የዘውታሪ ፀጋ ባለቤቶች ያሉበት ሁሉ የጥቂት ሰአት ትዕግስት ውጤት እንጅ ሌላ አይደለም።»

ጌታችን ሆይ በዲንህ ላይ እንድንፀና ሰብር ስጠን 🤲

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
🩵 ውሏችን ሰብር የተሞላበት፣ በሀቢባችን ላይ የበዛ ሰለዋት የምናወርድበት በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን 🤲🤲🤲

https://t.me/WCUMSJ2015
https://t.me/WCUMSJ2015

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

17 Oct, 07:26


★彡 የማይቀረው ጉዞ 彡★
彡彡彡彡彡彡

🏝አንዱ ከፊት ሆኖ ሌላው ቢዘገይም፣
ወደዛኛው አለም መጓዝ ግን አይቀርም፣
📝
ስራችንም ከፋ ፈሳዱም ተስፋፋ፣
በወንጀልም ሳቢያ ስራችን ከረፋ

በዚህ ዘረኝነት እዚያ ማዶ ክፋት፣
በዚያምጋ ኢሬቻ ከዚህምጋ ልደት፣

የሽርኩ ወላፈን ሲጋረፍ በርቀት፣
ሱናን ነክሶ መያዝ ሆኖባቸው  ውድቀት፣
🏖
ከበር ላይ ቆሞ ሞት የሚባል ነገር፣
እንዲህ መጨካከን ሰውንም ማስቸገር፣
🚥
የኑሮ እንግልቱ ውጣ ውረድ በዝቶ፣
በችግር ሲቆስል የሚበላ ጠፍቶ፣
🚦
መቋቋም ተስኖት የዱንያን ፈተና፣

አንዱን ሲሰበስብ ሌላው ሲሆን መና
የኔ ያለው ሆነ እንደጉም ዳመና፣
➹➷
ሂሳብ ሲያወራርድ የኑሮውን ማትስ፣
ሲያባዛ ሲያካፍል ሲደምር ሲቀንስ፣

🔍
ለአንዲት አፍታ እንኳን ተውሂድ ሳይረዳ፣
በመውሊድ ኢሬቻ ከአሏህ ውጭ ኢባዳ።
♻️
ጎንበስ ቀና እያለ ሳያገኘው ውሉን፣
እድሜም ገሰገሰ ቀርቧል ሰአታችን፣

📐
ከሁለቱም አለም ከዱንያም ከአኼራ፣
ምንም ሳንጠቀም አንድ ውል ሳንሰራ፣
↘️
እንደ ደራሽ ውሀ ወሰደን ጠምዝዞ፣
ያ ዝንጉ እንግዳ የማይቀረው ጉዞ፣

እንደ ቅጠል ሲረግፍ ወጣት አዛውንቱ፣
ለስንት ሚጠበቀው ያ የነብር ጣቱ፣
እጥፍጥፍ አለና ከለህድ ውስጥ ገባ፣
ወገን ዘመድ ሸኘው ሆዱም እየባባ፣
🔘
ጥርሱንም መጠጠ እንባም ፈሰሰለት፣
ልብም አዘነና ፊቶች ገረጡለት፣
በሀዘን ቅላፄ ከንፈርም አፏጨ፣
መራራውን ፅዋ ሁሉም ተጎነጨ

🚦🚥
ያም ሆነ ይህ ሆነ ሁሉም አያዋጣም፣
ይልቅ እንዘጋጅ ሌላ እድል አይመጣም፣
የማይቀረው ጉዞ ሞት ከፊት አለና፣
እንዘጋጅለት እስኪ በተውሂድ በሱና።

📝 በወንድማችን አቡ ሳራህ አላህ ይጠብቀው!

https://t.me/AbuImranAselefy/9272

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

16 Oct, 18:46


ማን አዞሽ ነው ኒቃብ የለበስሽው?" ካሉሽ የአንተም ሆነ የእኔ ፈጣሪ የሆነው ረበልዐለሚን በይው:: "ከላይኮ እንዳትለብሱ ትዕዛዝ መጥቷል!" ካለ ደግሞ "እኔ ከአርሽ በላይ ባለው ፈጣሪ ታዝዣለሁ እያልኩህ እኮ ነው::" በማለት ንገሪው

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

16 Oct, 18:36


ኒቃብ ራስን እንጂ አዕምሮን አይሸፍንም!

ኒቃብ ፊትን እንጂ እይታን አይጋርድም!



أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَأْتِكُم مَّثَلُ الَّذِينَ خَلَوْا مِن قَبْلِكُم ۖ مَّسَّتْهُمُ الْبَأْسَاءُ وَالضَّرَّاءُ وَزُلْزِلُوا حَتَّىٰ يَقُولَ الرَّسُولُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ مَتَىٰ نَصْرُ اللَّهِ ۗ أَلَا إِنَّ نَصْرَ اللَّهِ قَرِيبٌ

"(እናንተ በአላህ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ!) በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት ምዕመናንን ያጋጠመ መከራ የመሰለ ሳይመጣባችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልዕክተኛውና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት 'የአላህ እርዳታ መቼ ነው?' እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ደረሰባቸው። ተርበደበዱም። አስተውሉ የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው ተባሉም።" (አል-በቀራህ 214)

ስኬትና ድል በቀላሉ ያለ ትግል አይገኙም፤ ጀነት በቀላሉ አትገኘም፤ መታገልና መታገስን ትጠይቃለች። አሏህን ምዕመና 'የአላህ እርዳታ መቼ ነው?' እስከሚሉ ድረስ ይፈትናቸዋል።

መብታችን ለማስከበር በምናደርገው ትግል ላይ ስኬት እንቀዳጅ ዘንድ ልክ ከኛ በፊት የነበሩት ምዕመናን እንዳደረጉት ሁሉ ወደአሏህ ልንመለስ ይገባል

https://t.me/WCUMSJ2015

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

16 Oct, 07:11


በአላህ ፈቃድ በመንሀጅ ዙሪያ ለመጠቀምና ከሙመይዓዎች ተንኮል ለመጠበቅ እነኝህ ሙሀዶራዎችንና ምላሾችን አድምጧቸው።

1. በዱክቱር ሸይኹ ሁሰይን ሙሐመድ
👇
t.me/Abdurhman_oumer/6299


2. ድጋሜ በዱክቱር ሸይኽ ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
👇
t.me/Abdurhman_oumer/6322

3. ድጋሜ በሸይኽ ሁሰይን ሙሐመድ (ሰለፍዮችን መድኸልይ የሚሉት እነ ማን ናቸው)
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6817


4. አሁንም ዱክቱር ሸይኽ ሁሰይን ሙሐመድ (ለኢብኑ ሙነወር ምክርና ምላሽ)
   👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/9170


5. በሸይኽ አቡዘር አቡ ጦለሀ
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6300


6. ድጋሜ በሸይኽ አቡዘር አቡ ጦለሀ
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6301


7. በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዘሁላህ
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6314


8. በሸይኽ ዓብዱልሀሚድ ያሲን አልተሚይ ሀፊዘሁላህ
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6320



9. ሸይኽ ዓብዱልሀሚድ ያሲን አልተሚይ ሀፊዘሁላህ (ክፍል ሁለት)
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6321


10. በኡስታዝ ባህሩ ተካ
👇
t.me/Abdurhman_oumer/6449



11. በኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን
   👇
t.me/Abdurhman_oumer/6450

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

15 Oct, 15:06


👉 ከጭንቅ መውጫው መንገድ

ኢብኑል ጀውዚ ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-

" ነገሩ ከብዶኝ ተጠበብኩኝ የማይላቀቅ የሆነ ጭንቀት ያዘኝ , በምችለው ዘዴና አቅም ከዚህ ጭንቅ ለመውጣት የምችለውን ሁሉ ማሰብ ጀመርኩ ። ምንም መውጫ እንደሌለ አየሁ ። በዚህን ጊዜ እንዲህ የሚለው የአላህ ቃል መጣልኝ :–
" አላህን የፈራ ሰው ከጭንቅ ሁሉ መውጫ ያደርግለታል " 
ከዚያም አላህን መፍራት የጭንቅ ሁሉ መውጫ መሆኑን አወቁኝ ። በምችለው ሁሉ አላህን መፍራት ጀመርኩ ። ከጭንቄም መውጫ አገኘሁ ። ለሰው ልጅ ማሰብም ሆነ መመካት ያለበት የአላህን ትእዛዝ በመፈፀም ላይ ነው
ይህ ለሱ የተዘጋን ሁሉ ለማስከፈት ሰበቡ ነው "

ሰይዱል ኻጢር ገፅ ( 63 )

https://t.me/bahruteka

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

15 Oct, 13:47


📍ثناء العلماء على الشيخ ربيع حفظه الله من العلماء الكبار
📍የኡለማዎች ውዳሴ በ ኢማሙ ረቢእ አል መድኸሊይ ላይ ከ ኪባረል ኡለማእ
🎙العلامة ابن باز
🎙አል አላማህ ኢብኑ ባዝ
🎙العلامة زيد المدخلي
🎙አል አላማህ ዘይድ አል መድኸሊይ
🎙العلامة أحمد النجمي
🎙አል አላማህ አህመድ አን ነጅሚይ
🎙العلامة صالح اللحيدان
🎙አል አላማህ ሷሊህ አል ሉሀይዳን
🎙العلامة مقبل الوادعي
🎙አል አላማህ ሙቅቢል አልዋዲኢይ
🎙العلامة الألباني
🎙አል አላማህ አል አልባኒይ
🎙العلامة محمد بن عبد الوهاب البنا
🎙አል አላማህ አል በና
🎙العلامة محمد العثيمين
🎙 አል አላማህ ኢብኑ ኡሰይሚን
🎙العلامة صالح الفوزان
🎙አል አላማህ ሷሊህ አል ፈውዛን
🎙العلامة عبيد الجابري
🎙አል አላማህ ኡበይድ አል ጃቢሪይ
🎙العلامة عبد المحسن العباد
🎙አል አላማህ አል አባድ

💥ሀዳድዮች እና ሙመይኦች የሚያስከፋ ቢሆንም ለሱኒዬች ደስታ ነው

📍ልብ ይበሉ ኢማሙ ረቢእ አልመድኸሊይ መእሱም ነው አላልንም ድንበር ማለፍ እንዳይመስላችሁ

📚ማስረጃውን ነው ምናየው📚

t.me/mubarekabulbukhary
t.me/mubarekabulbukhary

https://t.me/WCUMSJ2015

1,366

subscribers

230

photos

26

videos