University of Gondar / UoG @universityofgondar Channel on Telegram

University of Gondar / UoG

@universityofgondar


The University of Gondar is one of the first generation universities in Ethiopia. In the 2016 and 2017 academic year UoG was ranked the number 1 university

MORE INFO
http://www.uog.edu.et

Call 058 114 1232

University of Gondar / UoG (English)

Are you interested in pursuing higher education in Ethiopia? Look no further than the University of Gondar (UoG)! As one of the first generation universities in the country, UoG has a long-standing reputation for academic excellence and innovation. In fact, in the 2016 and 2017 academic year, UoG was ranked as the number 1 university in Ethiopia.

At UoG, students have access to a wide range of programs and resources to help them succeed in their academic and professional goals. Whether you're interested in pursuing a degree in business, science, engineering, or the humanities, UoG has something to offer everyone.

To learn more about the University of Gondar and the programs they offer, visit their website at http://www.uog.edu.et. You can also contact them directly at 058 114 1232 for more information. Don't miss out on the opportunity to be a part of this prestigious institution and take your education to the next level with UoG!

University of Gondar / UoG

05 Jan, 09:43


#MoE‼️
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ማለፊያ ነጥብ ማምጣት ላልቻሉ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት (Remedial) ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኗል።

በሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የማካካሻ ትምህርት ለሚሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ፤ የማካካሻ ትምህርቱ ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰጥ ያዛል።

በዚህም ተቋማቱ ከጥር 1 ጀምሮ በቀሩት ወራት ትምህርቱን ውጤታማ በሆነ መንገድ መስጠት እንዳለባቸው ተገልጿል።

#join👇 #ተቀላቀሉ👇 #share
┏•••♡••❀━••🍃•••♡••❀━••┓
👉 @universityofGondar 👈

University of Gondar / UoG

05 Jan, 09:40


የተማሪዎች ጥሪ‼️‼️
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል‼️
በዚህም የነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2016 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥር 2 እና 3/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለአንደኛ ዓመት እና ለሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ እሰከሚደረግ በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል:: #DebreTaborUniversity
=================

#join👇 #ተቀላቀሉ👇 #share
┏•••♡••❀━••🍃•••♡••❀━••┓
👉 @universityofGondar 👈

University of Gondar / UoG

01 Jan, 09:01


PhD Viva
***********************
Misganaw Tilahun defended his PhD successfully on December 28, 2023 at the University of Gondar.
Dissertation title: Effects of Scaffolding Instruction on EFL Students' Awareness of Metacognitive Reading Strategies and Reading Comprehension
Congratulations!
************************
Devoted for Excellence!
Public and International Relations Directorate
December 28, 2023


#join👇 #ተቀላቀሉ👇 #share
┏•••♡••❀━••🍃•••♡••❀━••┓
👉 @universityofGondar 👈

University of Gondar / UoG

08 Jul, 14:11


የምርምር ስነ-ምግባር መርሆወችን የተመለከተ የአሰልጣኞች ስልጠና በጎንደር ከተማ ኦሎምፒክ ሆቴል ከዛሬ ሐምሌ 1/2013 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል። ስልጠናው እየተሰጠ የሚገኘው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ የድህረ-ምረቃ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት እና በ"ኢንስቲትዩት ኦቭ ትሮፒካል ሜዲሲን" ትብብር ነው።
*************
ለልህቀት እንተጋለን!
ሐምሌ1/2013 ዓ.ም

University of Gondar / UoG

08 Jul, 14:11


ለ220 የዩኒቨርሲቲ መምህራን በከፍተኛ ዲፕሎማ የማስተማር ስነ-ዘዴ ለ10 ወራት የተሰጠው ስልጠና ተጠናቀቀ !!
***********************************************************
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ዓመታት በሚሰጠው የከፍተኛ ዲፕሎማ በማስተማር ስነ-ዘዴ ስልጠና በ2013 ዓ.ም 220 ሰልጣኝ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ከሰኔ 28-30/2013 ዓ.ም. የተግባር ተኮር የምርምር ስራቸውን በማቅረብ ማጠናቀቃቸው ታወቀ ፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር የማታው ወንዴ እንደገለፁት “የትምህርትን ጥራት ለመጠበቅና ውጤታማ ተግባራትን ለመፈፀም ዩኒቨርሲቲው የከፍተኛ ዲፕሎማ በማስተማር ስነ-ዘዴ መርሃ-ግብርን ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ዋና ዓለማውም ተግባር ተኮር፣ ችግር ፈችና አሳታፊ የመማር ማስተማር መርህን በመከተል ብቃት ያለው መምህር ማፋራት ነው” ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የከፍተኛ ዲፕሎማ በማስተማር ስነ-ዘዴ መርሃ-ግብር በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ላሉ መምህራን የሚሠጥ ሲሆን ስልጠናው አምስት ሞጁዩሎችን ለ10 ወራት ያህል ያስተምራል፡፡ እስከ 2013 ዓ.ም. ድረስ 1,500 ያህል መምህራን ስልጠናውን መውሰዳቸውን መረጃዎች ያሳያሉ ፡፡
*********** **************
ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት!
ሐምሌ 01/2013 ዓ.ም

University of Gondar / UoG

08 Jul, 14:11


በስነ-ምግብ( Nutrition) የዶክትሬት ዲግሪ ስርዓተ-ትምህርት ለመክፈት የውጭ ግምገማ ተካሄደ
****************************************************************
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ የስነ-ምግብ ትምህርት ክፍል በስነ-ምግብ (Nutrition) የዶክትሬት ዲግሪ ስርአተ- ትምህርት ለመክፈት የውጭ ገምጋሚዎችን ያሳተፈ አውደጥናት ሰኔ 30/2013 ዓ.ም በኮሌጁ ምንትዋብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡
በአውደጥናቱ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ምሁራን በተጨማሪ የተለያዩ የመስኩ ምሁራን ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በበይነ-መረብ በመሳተፍ ያላቸውን ሙያዊና ሳይንሳዊ ሀሳብ አጋርተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲያችን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በሰው ኃይልና በትምህርት ፕሮግራሞች እየሰፋ መምጣቱን በመክፈቻ ንግግራቸው የገለጹት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ ብቁ ምሁራን እንዲኖረን በስታንዳርዱ መሰረት ጥራቱን የጠበቀ የፒ ኤች ዲ ስርአተ ትምህርት እና ምርምር ሊኖር እንደሚገባ ጠቁመዋል፤ የዩኒቨርሲቲው የወደፊት አቅጣጫም ጥራት ያለው ትምህርትን ችግር ፈች ከሆነ የምርምር ስራ ጋር ማቀናጀት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ካሳሁን አለሙ በበኩላቸው በሀገራችን ያሉ የጤና ችግሮች በብዛት ከአመጋገብ ጋር እንደሚያያዙ አንስተዋል ፤ለእነዚህ ችግሮች መፍትሄ ለመፈለግ ደግሞ በሳይንስና በምርምር ብቁ የሆኑ የጤና ስርአትን መምራት የሚችሉ ምሁራን ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡ ጤናማ ትውልድ የሚገነባው በጤናማ አመጋብ ነው፡፡ስለሆነም በዩኒቨርሲቲያችን በስነ ምግብ/ Nutrition / የሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም መሰጠቱ ከምግብና ከአመጋጋብ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በምርምር ለመፍታት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው አክለው የገለጹት ዶ/ር ካሳሁን አለሙ ይህ አውደጥናት መካሄዱ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገኙ የመስኩ ምሁራን /ኤክስፐርቶች/ አስፈላጊ እና ገንቢ ምክረ-ሀሳቦችን ለማካተት ታስቦ መሆኑንም ተናግረዋል፤አያይዘውም በስርዓተ-ትምህርቱ ዝግጅትና ግምገማ ሂደት የበኩላቸውን ሚና ለተወጡ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ያሳተፈ የውስጥ የስርአተ ትምህርት ግምገማ ከዚህ በፊት መካሄዱ ይታወሳል፡፡
*********************************************************************
ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 30/2013 ዓ.ም

University of Gondar / UoG

08 Jul, 14:10


የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅና አጠ/ስ/ሆስፒታል "Clinical Trial Center" የምርምር ማዕከል አስጀመረ
*****************************************
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅና አጠ/ስ/ሆስፒታል የክሊኒካል ትሪያል /clinical trial center/ የምርምር ማዕከል ለማስጀመር የሚያስችል አውደ ጥናት ሰኔ 29/2013 ዓ.ም በሳይንስ አምባ አዳራሽ ተካሄደ። አውደ ጥናቱ የተለያዩ የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊወች፣መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል።
የመድሀኒቶች ውጤታማነት መሞከሪያ የምርምር ማዕከሉን /ክሊኒካል ትሪያል/ ለማስጀመር ሆስፒታሉ መዘግየቱን ያነሱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ቢኒያም ጫቅሉ፣ አሁን ላይ የማዕከሉን መዘጋጀት አድንቀዋል። አፍሪካ ውስጥ ካሉት 20 የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ቢኒያም፣ በሀገራችን ትልቅ ጉዳት በሚያስከትሉ በሽታዎች ላይ ለምሳሌ:- ወባ፣ ቲቢ፣ ካላዛርና የመሳሰሉት በሽታወች ላይ ይህን የመድሀኒቶች ውጤታማነት መሞከሪያ ማዕከል ተግባራዊ ማድረግ የተለያዩ ምርምሮችን ለመስራት ጭምር እንደሚያግዝም ም/ፕሬዚዳንቱ አክለው ገልፀዋል።
በአውደጥናቱ ስለ ክሊኒካል ትሪያል /clinical trial/ ታሪካዊ አመጣጥ፣ አስፈላጊነት እና በመሳሰሉት ርዕሰ ጉዳዩች ዙሪያ የህ/ጤ/ሳ/ኮ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር በሆኑት በፕ/ር ታደሰ አወቀ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት በዶ/ር መዝገቡ ሰላምሰው ገለጻ እና ማብራሪያ ከቀረበ በኋላ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፤ የተለያዩ የመፍትሄ ሃሳቦችም ከተጋባዥ እንግዶች ተነስተዋል ፡፡
*****************************************

University of Gondar / UoG

01 Jul, 08:07


በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሚካሄደው የድህር ምረቃ የስርዓተ ትምህርት ግምገማ እንደቀጠለ ነው፡፡
*******************
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተለያዩ የምህንድስና ዘርፎች ማለትም በኤሌክትሪካልና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ ት/ት ክፍል (PhD in Electrical & Power Engineering) ፣ እና በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ት/ት ክፍል (PhD in Process Engineering, MSc in process Engineering, MSc in Eniviromental Engineering and also MSc in Industrial Pollution Control Engineering) የስርአተ-ትምህርት ግምገማ አውደ ጥናት ሰኔ 23/2013 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ አካሂዷል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሰቲ ሁኖ መለየቱን ተከትሎ በድህር ምረቃ ትምህርቶች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የዩኒቨርሰቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተለያዩ የምህንድሰና ድህረ ምረቃ ዘርፎች በ3ኛ ድግሪ- ብዛት 3 እንዲሁም በ2ኛ ዲግሪ- ብዛት 8፣ በአጠቃላይ 11 የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን በሚቀጥለው የትምርህርት ዘመን ለመክፈት የስራዓተ ትምህርት ግምገማዎችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
***********
ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት!
ሰኔ 22/2013 ዓ.ም

University of Gondar / UoG

01 Jul, 08:07


ለክረምት ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ማሻሻያ
************************************

University of Gondar / UoG

01 Jul, 08:07


በ 2013 ዓ.ም ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
እንኳን ወደ ሰላሙ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና ወደ ጥንታዊና ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በሰላም መጣችሁ!!!
*********************************************
ለልህቀት እንተጋለን
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 23/2013 ዓ.ም
New undergraduate students assigned to the University of Gondar in 2021 are entering our many campuses. Welcome to University of Peace UoG and to the ancient and historic city of Gondar !!!


#join👇 #ተቀላቀሉ👇 #share
┏•••♡••❀━••🍃•••♡••❀━••┓
👉 @universityofGondar 👈

University of Gondar / UoG

01 Jul, 08:07



#join👇 #ተቀላቀሉ👇 #share
┏•••♡••❀━••🍃•••♡••❀━••┓
👉 @universityofGondar 👈