የግጥም መንፈሳውያን @yegetem_menfesawuyan Channel on Telegram

የግጥም መንፈሳውያን

@yegetem_menfesawuyan


መንፈሳዊ ግጥም ከ ገጣሚ ጸሃፊ ሄሮል

Username @Herol_17

የግጥም መንፈሳውያን ✍️
Join and share

@yegetem_menfesawuyan

የግጥም መንፈሳውያን (Amharic)

እንኳን ደህና መጣህ! ይህ የግጥም መንፈሳውያን በምሳሌ ከገጣሚ ጸሃፊ ሄሮል እናት @Herol_17 ጋር ተደሰትን ይህን ይመስላል። ነገር ግን የተመረጠው 'ሰላም እና መልቅ መንፈሳዊ ግጥም' በሚል ቀጥል ውስጥ መንፈሳዊ ምላሽን የሚዘረጋ ነው። እናትህ አንት ምን አለ? እናትህ በተለያዩ ቀጥሎች መንፈሳዊ የስልክ ጠቃሚውን ለመመልከት ለሚያደርግ በማንኛውም ላይ ምን እንከው? ይህን ምስጢር እናት @yegetem_menfesawuyan አድርገህ ይጫኑ።

የግጥም መንፈሳውያን

25 Apr, 15:39


be andand mekniyatoch getem letewesenu gizeyat alemelkeke yetawekal . enam kezih behuala betechalegn akm wede enante wede kidusan yemastelalef mehonun lasawukachu ewedalew



ጸጋ ይብዛላችሁ

የግጥም መንፈሳዉያን

የግጥም መንፈሳውያን

20 Mar, 16:14


የመርገምን ነገር አላወራም ከቶ
ብርሃን ሆኖልኛል ጨለማዬም ነግቶ ።
አስጨናቂዎቼ በባህር ተጥለው
የመከራዬም ቀናት ላያገኙኝ አልፈው
የእውነት ህይወት ኖሬ ታሪክ ተቀይሯል
ለዝማሬው ዜማ አዲስ ዘመን መጥቷል ።

የርሃብ የጥማቴ የርዛት የማጣቴ
የመገፋት ህይወት አንሼ መታየቴ
የጫንቃዬ ላይ ቀንበር ከላዬ ሲሰበር
ምስጋናዬን አምጥቼ ስላንተ ልናገር
ዘመን ጊዜው ደርሶ ሀዘኔ ተረስቶ
የደስታዬም ገመድ በእጅህ ተዘርግቶ
ሁሉን ተሻግሬ በድል በምስጋና
በገናዬን ይዤ ቆምኩን እንደገና።


@Yegetem_Menfesawuyan


ገጣሚ ጸሀፊ @Herol_17

የግጥም መንፈሳውያን

22 Feb, 07:22


ከጨለማው ዘመን ከመጨረሻው ሩጫ
ሰዎች ሲታገሉ ፈልገው ማምለጫ
ሳይሆንላቸው ቀርቶ ሲሆን ለቅሶ ዋይታ
እኔም በዚያ አንዳልገኝ እርዳኝ የኔ ጌታ።

አሁን አስመልጠኝ ከአለም መከራ
የነብሴን ጉዳይ ግን አምላኬ ሀደራ።🥹




ጸሀፊ @Herol_17

የግጥም መንፈሳውያን

18 Feb, 17:13


ፍለጋ በዋራ

የግጥም መንፈሳውያን

05 Feb, 17:57


#እኔን_ላከኝ


ማንን እልካለው ማንስ ይሄድልኛል
ሀሳቤን ጭንቀቴን ማን ያውጅልኛል
አትበል ኢየሱሴ እኔን መርጠህ ላከኝ
በእሾህ መሃልም ቢሆን ቀብተህ ስደደኝ።
በሞት ጥላ ውስጥ ለተዘፈቁ
አምላክነትህን ከቶ ስላላወቁ
በሲኦል አፋፍ ደጅ ለተቀመጡ
ለጨለማው ግዛት እጃቸውን ለሰጡ
ማምለጥ ተስኗቸው ተስፋ ለቆረጡ
መውጣትን ፈልገው አጋዥ ረዳት ላጡ

እኔን ላከኝ ዛሬ እኔ እሄዳለው
በእጅህ ብቻ ዳስሰኝ ብርቱ እሆናለሁ።

የቀደመችውን መንገድ ለሚፈልጉ
ጽድቅህን ተርበው መብል ላደረጉ
ግን ተስፋ ቆርጠው ለተቀመጡ
በአለም ብልጭልጭ ወድቀው ለተዋጡ
አፌን ሞልተህ ዛሬ በእሳትህ ነበልባል
አኔን ላከኝ ኢየሱስ ብርታትህ ይታያል።

ማንን እልካለሁ ለምንስ ትላለህ
ለይተህ የመረጥከው ትውልድ እያለህ
ማንስ ይሄድልኛል ለምንስ ትላለህ
ከፊትህ የቆመን ልጅህን እያየህ

ስደደኝ እወጣለሁ ከወገን ተለይቼ
ወደ ኋላ አልልም ክብርህን አይቼ
ድምፅህን አሰማኝ ይታዩኝ ሰማያት
እጅህ ሲነካኝ ነው ክብርህ የኔ ብርታት።

ተራራም ቢሆን እኔን ላከኝ
ሸለቆም ቢሆን እኔን ብቻ ላከኝ
ማንስ ይሄድልኛል አትበል እኔ ልጅህ እያለው
መርጠህ ብቻ ላከኝ የትም እሄዳለው።


@Yegetem_Menfesawuyan
@Yegetem_Menfesawuyan
@Yegetem_Menfesawuyan


ገጣሚ ጸሃፊ @Herol_17

የግጥም መንፈሳውያን

27 Jan, 16:02


የልብን ጩኸት ፈጥነህ ትሰማለህ
መላ ለጠፋበት ፈጥነህ ትደርሳለህ
ነብስን ከጨለማ ህይወትን ከፈተና
ሀዘንን በደስታ እምባን በምስጋና
ታሪክን በድል ጠላት በቁጣ ትመታለህ
አንተን ለታመነ ስምህን ለጠራ ፈጥነህ ትደርሳለህ።

የግጥም መንፈሳውያን

27 Jan, 15:51


ፍሬ የተሸከመ ዛፍና በእውቀት የተሞላ ሰው አንድ ናቸው
ሁለቱም ዝቅታን ይመርጣሉ።

የግጥም መንፈሳውያን

17 Jan, 13:15


ሲነጋ በጠዋት ስነቃ ከእንቅልፌ
ምስጋናህ ይሙላብኝ ዘውትር በአፌ
በሰላም ተኝቼ በሰላም ስነቃ
ስምህ ግርዶሽ ሆኖኝ ከለላ ጠበቃ
ከጉዞም ደክሜ ስመጣ በጤና
አጥንልሃለው የልቤን ምስጋና ።

ወድቄ ስላልቀረው ደግፈሄኝ ስለቆየሁ
የአባትነህን ፍቅር ቀምሼ ስላየሁ
ብርቱ ሰይፍ ስላለኝ ለጠላቴ ዛቻ
ጉልበት ስትሆነኝ ማምለጫ መበርቻ
ታምኜብህ ባንተ በእቅፍህ እኖራለው
ለውለታህ ምላሽ ከምስጋና በቀር ምንስ እከፍላለው ።

ፅድቅህን አይቼ መቆም ቢያቅተኝ
ክብርህ ውስጤን ሞልቶ በፊትህ ካቆመኝ
ዘምርልሃለው በህይወት ዘመኔ
ውሰድ ተጠቀመኝ ያንተው ነኝ እኔ


ገጣሚ ጸሃፊ ሔሮል

የግጥም መንፈሳውያን

የግጥም መንፈሳውያን

12 Jan, 08:26


የልጅነትህ መንፈስ ወዴት ነው?
ዛሬም አለ ወይስ አውጥተህ ጣልከው
ነበልባሉ እሳት በውስጥህ ይነዳል ?
አንደበትህ ደፍር ሊሳን ይናገራል ?

እስቲ ልጠይቅህ ዘይትህን ሞልተሃል
ከሀጢያት ርቀህ ለኢየሱስ ሞተሃል
እስቲ ልጠይቅህ ዘውትር ትሮጣለህ
ያኔ በልጅነት እንደምታደርገው ጉልበትህን ሰብረህ ትንበረከካለህ ?

ወይስ ስጋ ይዞሃል ወይስ ደካክመሃል
ወይስ ለሚጠፋው ነገር እጅህን ሰጥተሃል ?

ቅዱሱን ማደሪያ የጌታን ቤተመቅደስ
በሚጠፋው ምኞት ልብህን በማርከስ
እጅህ ደም እያለ ነብስህ ተራቁታ
ቅዱስ የሆነውን መከተልን ትታ
ድካሚ*2/ ብሏት ዛሬ እጇን ሰጥታ
በሚያልፈው አለም በስጋ ተረታ
ነው ያለችው ወይስ ይልቅ በርትተሃል
የልጅነትህን መንፈስ ወዴት ደብቀሃል ?

ጥያቄ ነው መርምረው
አቅቶህም ከሆነ ራስህን ጠይቀው
ጠፍቶብህም ከሆን ከእጅህ ከወደቀ
የተጎናፀፍከው የለበስከው ካባ ድንገት ከወለቀ
ተመልከት ራስህን እስከመጨረሻ
የት ይሆን ዕድልህ ያንተ መዳረሻ

የልጅነትህ መንፈስ ካልነካህ በድንገት
ፈጥኖ ካላራቀህ ከሀጢያት ከርኩሰት
ራስህን ጠይቀህ ታገልና በርታ
በሚጠፋው ነገር ከቶ እንዳትረታ

የልጅነትህን መንፈስ መልስ ወደ ቤትህ
ዘመኑ ተቃርቧል ሊመጣ አባትህ ።


የግጥም መንፈሳውያን

ገጣሚ ጸሃፊ @Herol_17

የግጥም መንፈሳውያን

11 Jan, 15:02


የመዝሙር ግጥም ማፃፍ የምትፈልጉ ወንድሞችና እህቶች ካላችሁ በውስጥ መስመር አናግሩኝ

የግጥም መንፈሳውያን

11 Jan, 12:20


ብዙ ጊዜ ከዚህ ቻናል ኮፒ ተደርገው በተለያዩ ሌሎች ቻናሎች ላይ የገጣሚውን ስም ሁሉ በመቀየር የሚለቀቁ የዚህ ቻናል መንፈሳዊ ግጥሞች አሉ ምንጩ ግን ይሄ ቻናል ነው ። ከዚህ በፊትም እንደምለው ሁሉ ይሄ ቻናል ከማንኛውም ዓይነት ኮፒና ፣ ሼር ነፃ የሆነ በ @Herol_17 ብቻ የሚፃፉ መንፈሳዊ ግጥሞች የሚቀርቡበት ቻናል ነው ።

የግጥም መንፈሳውያን

07 Jan, 19:17


የልብ ዓይኔን አብራው እባክህ ጌታዬ
እስቲ ልመልከተው የት ይሆን መድረሻዬ
የፊቴን አሳየኝ የሗላው ይቅርና
በመንፈስህ ምራኝ እጆቼን ያዝና ።

አሳየኝ የቤትህን የህግህን ስርዓት
በፍቅርህ ቀስቅሰኝ በለሊት በጠዋት
የልቤን ሸለፈት ግረዝልኝ ጌታ
በጭፍን በጨለማ እንዳልንገላታ ።

አለው ስትለኝ ድምፅህን ልስማ
የቃልህን ምንጮች ዘውትር ልጠማ
ጠጥቼ እንድረካ ከምድረ በዳው መንገድ
መንፈስህን ላክልኝ በሚጠፋው ነገር እንዳልንገዳገድ ።

ተመሳስሎ መኖር ለእኔስ ይበቃኛል
በቀናችው መንገድ መቆም ይሻለኛል
ክርስትናን በፅድቅ ልምሰለው በሞቴ
ላንተ ብቻ ልኑር በቀረው ህይወቴ

የልቤን ዓይኖች ግለጥልኝ በቃ
ካንቀላፋሁበት ልቤን ነቃ ነቃ
ዳስሰኝ በእጆችህ ንገረኝ በቃሎችህ
ከቤትህ ሳልጠፋ ልኑር በደጆችህ ።

ያላሰፍኩት ዘመን አንተን ባለማክበር
ሀጢያትን እየሰራው በፅድቅ በማፈር
እሱ ቀርቶ ዛሬ እንደ አዲስ ቀይረኝ
ህይወቴን ለክብርህ እንካ ተጠቀመኝ።


የግጥም መንፈሳውያን

ገጣሚ ጸሃፊ @Herol_17

የግጥም መንፈሳውያን

06 Jan, 18:35


ኢየሱስ ተወልዶ ባይሰብር ቀንበር
በድቅድቅ ጨለማ ተውጠን ነበር
በዳዊት ከተማ ባይገለጥ ኖሮ
ጠፍተን ቀርተን ነበር ገና ያኔ ድሮ።

ነገር ግን ተወልዶ የምስራች መጣ
በሞት ጥላ ላሉት የፅድቅ ፀሐይ ወጣ
አማኑኤል በስጋ ሆነልን መበርቻ
እኛም ይዘን መጣን የወርቁን መባቻ
ወርቅም ወርቅ አይደል እጅግ የረቀቀ
ለእኛስ ክብር አለን ልቆ የደመቀ
ደስ አያሰኘው ብር ነሃስ ወርቁ
ኑና በእልልታ የሱስን አድንቁ።


@Yegetem_Menfesawuyan

ገጣሚ ጸሃፊ @Herol_17