ሰገነት ሚዲያ @segenetmedia1 Channel on Telegram

ሰገነት ሚዲያ

@segenetmedia1


ሰገነት ሚዲያ (Amharic)

ሰገነት ሚዲያ አለቃዎች እና ተማሪዎች መሰረት አራት በጣም የተጠቀሱ አባልነት በመሆን ለመበተን አንደምትመለከቷል። ለምን እንነኚ፡፡ ለምን አካሉ አስፈጻሚ ስፍራ አለ። በባህል ቆይቻለሁ፡፡

ሰገነት ሚዲያ

27 Jun, 18:26


ስለ ሃምስተር ኮምባት | Hamster Combat የአል-አይን መረጃ!

#ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ እየተዘዋወረ ያለው  “ሃምስተር ኮምባት” ምንድነው ?

“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካቶች ዘንድ እየተዘወተረ የመጣ በቴሌግም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ተጫዋቾቹ በየቀኑ ስክሪናቸውን በጣታቸው መታ መታ (ታፕ ታፕ) ሲያደርጉ ክሪፕቶ ሳንቲሞችን የሚያገኙበት ነው።

“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ በበርካቶች እየተዘወተረ የመጣ ጨዋታም ሆኗል።

በቴሌግራም ላይ የተመሰረተው ሃምስተር ኮምባት በአለም አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ተጫዋቾችን በማፍራት ከፍተኛ ተወዳጅነትን አግኝቷል።

ሃመስትር ኮምባት በቴልግራም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ኤር ድሮፕ ሊሆኑ የሚችሉ ሳንቲሞችን (ኮይን) ተጫዋቾችን የሚሸልም የቴሌግራም ጨዋታ ነው። እንዲሁም ሰዎች በቴሌግራም ለይ ጓኞቻውን እየጋበዙ በርከት ያለ የክሪፕቶ ሳንቲሞችን ለመሰብሰብ በጋራ የሚጫወቱት ጨዋታ እንደሆነም ይነገራል።

ሃመስትር ኮምባት በቴልግራም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ኤር ድሮፕ ሊሆኑ የሚችሉ ሳንቲሞችን (ኮይን) ተጫዋቾችን የሚሸልም የቴሌግራም ጨዋታ ነው። እንዲሁም ሰዎች በቴሌግራም ለይ ጓኞቻውን እየጋበዙ በርከት ያለ የክሪፕቶ ሳንቲሞችን ለመሰብሰብ በጋራ የሚጫወቱት ጨዋታ እንደሆነም ይነገራል።

ምናልባት ጨዋታ ብቻ ስለሆነ ዋናው ጥቅሙ ምንድነው? የሚል ጥያቄ ሊያስከትል ይችላል፤ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ ጨዋታ ቢሆንም፣ በሃመስተር ኮምባት የሰበሰብናቸው ሳንቲች (ኮይኖች) ኤርድሮፕ የመሆን ዝግጅት እንዳለ ነው የሚነገረው።

ይህ ማለትም በዚህ ጨዋታ ሳንቲሞችን (ኮይን) የሰበሰቡ ተጫዋቾች በቲ.ጂ.ኢ (ቶከን ጄኔሬሽን ኢቨንት) ወቅት ለኤር ድሮፕ ብቁ የመሆን እንደል አላቸው። ሳንቲሞቹ አስተዳዳሪዎች ያዋጣል ብለው ያመኑትን ማንኛውንም ተመን በመጠቀም ወደ ቶከን ይቀየራሉ፤ ስለዚህ “ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) መጫወት ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ነው የተባለው።

ሃምስተር ኮምባት ህጋዊ ወይስ ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው?

“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) በክሪፕቶ ገንዘብ ተፈጥሮ ምክንያት ህጋዊ ወይም ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ምንም መንገድ የለም። ነገር ግን ሃምስተር ኮምባት ጠቃሚ ነገር ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ ምልክቶች አሉ የተባለ ሲሆን፤ ከእነዚህም አንዱ ማሳያዎ እንደ “BingX” ካሉ ልውውጦች ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት መፍጠሩ ነው።

ይህ ማለት ወደፊት በ”BingX” ልውውጥ ላይ የሃምተርን ተመዝግቦ ልናይ እንችላል፤ ነገርግን አሁን ማድረግ ያለብን ማመን እና ጨዋታውን መጫወት ብቻ ነው። ተለዋዋጭ በሆነው እና ተገማች ባልሆነው በክሪፕቶ ዓለም ውስጥ ማድረግ የምንችለው እንድ ነገር ወይ አምኖ መጫወት አሊያም መተው ብቻ ነው።


ከስር ባለው ሊንክ በመግባት ሳንቲሞችን ይሰብስቡ!👇
https://t.me/hamSter_kombat_bot/start?startapp=kentId1680622844

ሰገነት ሚዲያ

16 Mar, 08:39


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞኛል አለ

በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል።

አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ በመሆኑ ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን እየጠየቅን፣ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን።

ሰገነት ሚዲያ

22 May, 12:10


መምህር ብርሃኑ

  የሀገሬ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅ  መምህር ብርሃኑ አድማስ ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓም "ለጥያቄ ትፈለጋለህ" በሚል በፀጥታ ኃይሎች ከቢሯቸው ተወስደው ነበር።ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ተለቀዋል።

ሰገነት ሚዲያ

21 May, 12:04


የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በአዲስ አበባ ንፋስ ሥልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

የትራፊክ አደጋው የደረሰው በወረዳ 11 ልዩ ሥሙ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡በተጨማሪ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና በህክምና ክትትል ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

ሰገነት ሚዲያ

21 May, 12:01


ተመስርቷል!

የአማራ ሕዝባዊ ግንባር በትላንትናው ዕለት ምሽት መምስረቱን ይፋ አድርጓል። የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የአገር ውስጥ መሪና ከአገር ውጭ ላለው ማህበረሰብ አስተባባሪ መሰየማቸውን እንዲሁ ታውቋል። በዚህ ተቋም ውስጥ ጠንካራ የአማራ ልጆች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል።

ሰገነት ሚዲያ

15 May, 16:40


ብርጋዴየ ጄነራል ተፈራ ማሞ እንደ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በህክምና እጦት እንዲሞት ተፈርዶበታል!

ጉዳዩ፡- ለህክምና ከአገር እንዳልወጣ መከልክሌን ይመለከታል!

እኔ ብርጋዴየ ጄነራል ተፈራ ማሞ ጨርቆስ በኢሕአዴግ ትግል ከተራ ታጋይነት ጀምሮ እስከ ከፍለ ጦር ድረስ በመምራት ለድል አብቅቻለሁ፡፡በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም የክ/ጦር አዛዥ ሆኞ በወጊያው ለተገኘው የበላይነት ክቡድ አስተዋጽኦ ማድረጌ በመንግሥት ታምኖበት የሜዲያና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶልኛል፡፡ ከ1997ቱ ምርጫ በኋላም በመከላከያ ሠራዊቱና በሌሎች ተቋማት የሚያገለግሉ የዐማራ ተወላጆች ታድነው መታሰራቸውና ከሥራ መባረራቸውን ተከትሎ፣ ከጓዶቼ ጋር ሥርዐቱን ለመቀየር ያደረግነው ሙከራ ከሽፎ ከዘጠኝ ዓመት በላይ በአስከፊ እስር ማቅቄያለሁ፡፡ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ትግራይ በነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተከፈተበትን ጥቃት ተከትሎ፣ እንደ አገር የተላለፈውን ጥሪ ተቀብዬ የዐማራ ልዩ ኃይልን በዋና አዛዥነት እየመራሁ እና ከመከላከያ ኃላፊዎች ጋር እየተናበብን አገሪቷን ገጥሟት ከነበረው ከባድ አደጋ ታድጌያለሁ፡፡

ክቡራትና ክቡራን፡- ይህንን መግለጫ እንድሰጥ የተገደድኩበትን ምክንያት በተጋድሎ ታሪኬ የጀመርኩት፣ እኔ ለአገሬ ታማኝ ወታደር እንጂ፤ አጥፊዋ ወይም ክፉ ከሚያስቡባት ጋር የመዋል ልማድ እንደሌለኝ ለማስገንዘብ ነው፡፡  ከዚህ ቀጥሎ ፍትሕ የተነፈኩበትን ጉዳይ አብራራለሁ፡፡ በትግሉ ዘመን በደረሰብኝ የፈንጂ አደጋ ከስምንት ያላነሱ ፍንጥርጣሪዎች በቀኝ እግሬ ውስጥ ተሰግስገው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ፍንጥርጣሪዎች በተለይ ዕድሜዬ እየገፋ ከመሄዱ ጋ ተያይዞ ነው መሰለኝ ወደ አደገኛ ደረጃ መድረሳቸውንና ወደ ካንሰር የመቀየር እድል እንዳላቸው በመረጋገጡ፣ የባሕር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል የሐኪሞች ቦርድ በአስቸኳያ ውጭ አገር ሄጄ እንድታከም ወስኗል፡፡

በዚህም መሰረት፣ በእስራኤል የሚኖሩ አገር ወዳድ የዐማራ ተወላጆች ህክምናውን አመቻችተውልኝ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ቦሌ አየር መንገድ ከደረስኩ በኋላ፣ በደህንነት ሠራተኞች እንዳልጓዝ ተከልክዬ ተመልሻለሁ፡፡ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች ችሎት ወስጄ፣ ግራ-ቀኙን ለአንድ ወር ያህል ካከራከረ በኋላ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም መከልከሌ ሕገ-ወጥ እንደሆነ ጠቅሶ፣ ከአገር ወጥቼ እንድታከም ተወስኗል፡፡ የውሳኔው ግልባጭም ለኢሚግሬሽንና ለብሔራዊ መረጃ ተልኳል፡፡ ነገር ግን፣ በዛሬው ዕለት ግንቦት 7 2015 ዓ.ም ከኢሚግሬሽን ከአገር እንዳልወጣ መታገዴ ተነግሮኛል፡፡ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሳጣራ፣ የፌደራል ፖሊስ ባለፈው ዓመት በ“ፍትሕ መጽሔት” የሰጠሁትን ቃለ-መጠይቅ ጠቅሶ በሁከትና ብጥብጥ እንደሚፈልገኝ ሚያዚያ 30/2015 ዓ.ም የጻፈውን አቤቱታ የተመለከተው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ አራዳ ፍርድ ቤት ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የዛኑ ቀን የእግድ ትዕዛዝ በማስተላለፉ እንደሆነ ነገሩኝ፡፡
 
መቼም አንድ ዓመት ባለፈው ቃለ-መጠይቅ ከአገር ወጥቼ እንዳልታከም የተከለከልኩት ፈልጌና መርጬ ባልተወለድኩበት ብሔር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህም በዚህች አገር ላይ ዐማራ መሆን አደጋ እንደሚያስከትል በስፋት ተመልክተናል፡፡ በእኔም የደረሰው ይህ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም “ዐማራ ለምን ይፈናቀላል? በማንነቱ ለምን ይጠቃል?” ብለው በዐደባባይ የተሟገቱት ፕሮፌሰር አስራት ወ/ደየስን አገዛዙ ህክምና በመከልክል ሕይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ የዐማራ ክልል ገዥ ፓርቲ የነበረው ብአዴንም የወንጀሉ ተባባሪ እንደሆነ አንዘነጋውም፡፡ 

ጥያቄው፣ አሁንስ በሥልጣን ላይ ያለው የዐማራ ብልጽግና በዚህ ጉዳይ አቋሙ ምንድን ነው? “እወክለዋሁ” የሚለው ማኀበረሰብ አንድ በአንድ እየታደነ እንዲጠፋ ተስማምቷል ወይስ “እጃችሁን ከሕዝቤ ላይ አንሱ?” የማለት ዐቅም የለውም? የሚል ነው፡፡ ፍርዱን ለታሪክና ለሕዝብ ብተወውም፤ ፍትሕን ለማግኘት በሕጋዊ መንገድ የማደርገውን ጥረት እቀጥልበታለሁ፡፡

በመጨረሻም፣ ዘመኔን ሙሉ ደረቱን ለጥይት ሰጥቶ ሕዝብንና አገርን በሚያገለግል ሙያ ላይ ያሳለፍኩ ብሆንም፤ ባለቅኔው ዮፍታዬ ንጉሤ፡-
“ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!” ያሉበትን ዐውድ በሚያስታውስ መልኩ፣ ሆን ተብሎ ህክምና በመከልከል ህይወቴ እንዲያልፍ የሚደረገው አሻጥር ያሳዝነኝ ይሆናል እንጂ፤ ለሕዝቤ ያለኝን ውዴታና ግዴታ ስንጥር ታህል እንደማይሸርፈው ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡
                                                                                                         ከሰላምታጋር!                                      

ብ/ጄ ተፈራ ማሞ   

ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣
ለዐማራ ሕዝብ፣
ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣
ለሚዲያዎች፣
ለማኀበረሰብ አንቂዎች

ሰገነት ሚዲያ

15 May, 11:44


መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ በማምጣት በፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

እስካሁን የተያዙበት ምክንያት ያልታወቀ ሲሆን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውም ታውቋል። መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ በቦሩ ሜዳ ጉባኤ ቤት ጉባኤ በመዘርጋት በርካታ ሊቃውንት ያፈሩ በአሁኑ ሰዓትም ከአገልግሎታቸው በተጨማሪ በወሎ ዩኒቨርስቲ የግእዝ መምህር ናቸው።

ዝርዝር መረጃዎች እንዳገኘን የምናደርስ ይሆናል።

ምንጭ:-EOTC TV

ሰገነት ሚዲያ

15 May, 11:42


ባህርዳር‼️

በአሁኑ ሰዓት የባህርዳር ዙሪያ አርሶ አደሮች የማዳበሪያ አቅርቦት ባለመኗሩ በርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ ናቸው።

የፀጥታ አካላት ሰልፈኞቹን ለመበተን ጥረት እያደረጉ ነው። የሰልፉ ዓላማ መጪው የእርሻ እና የአዝመራ ወቅት በመሆኑ የግብርና አቅርቦት እንዲሟላላቸው ለመጠየቅ ያለመ ነው።

ሰገነት ሚዲያ

15 May, 10:28


ሰበር ዜና!

የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ የነበሩት አሕመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) የአማራ ክልል ብልጽግና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው በዶ/ር ዐብይ አሕመድ መሾማቸው ተገልጿል።

ዶክተር አሕመዲን የአቶ ግርማ የሺጥላ ሥልጣን እና ቦታ ተክተው የሚሰሩ ይሆናሉም ተብሏል። ዶ/ር አህመዲን የመከላከያ ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታም ሆነው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አገልግለዋል።

ሰገነት ሚዲያ

13 May, 07:21


ቦርዱ የህወሓትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው " ይነሣልኝ " ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

ለቦርዱ ውሳኔ ምክንያት የሆነው ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመፅ ተግባር አሁን ላይ ባይኖርም እንደገና ህጋዊ ሰውነቱን ለፓርቲው ለመመለስ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ 1162/2011 ተደንግጎ አይገኝም ሲል ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በዚህም የህጋዊ ሰውነት ጥያቄ የማስመለስ ጉዳይ በህግ የተደገፈ ሆኖ እንዳላገኘው ቦርዱ አመልክቷል።

ፓርቲው ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በአዋጅ 1162/2011 አንቀፅ 66 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ህጉን መሰረት አደርጎ ሲፈቅድ መሆኑን ቦርዱ ወስኗል።

የፓርቲው አመራሮች እና ንብረትን በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ፓርቲው ላይ የሰጠው የስረዛ ውሳኔ ውጤቶች በመሆናቸው እንደአዲስ ሊጠየቁ የሚችሉ አይደሉም ያለው ምርጫ ቦርድ በዚህ በኩልም የተጠየቀውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

ሰገነት ሚዲያ

13 May, 06:51


ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች፤ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በአፋጣኝ እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ (CPJ) ጥሪ አቀረበ። መቀመጫውን በአሜሪካ ኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ትላንት አርብ ባወጣው መግለጫ “በአገር ውስጥና በውጪ ያሉ የፕሬስ አባላትን ማዋከብ እንዲያቆሙ” ለኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጥሪ አስተላልፏል።

“የአማራ ድምጽ” የተባለው በዩቲዩብ የሚተላለፍ የግል መገናኛ ብዙኃን መስራች እና አርታኢ የሆነው ጎበዜ፤ ሚያዝያ 28፤ 2015 በጅቡቲ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ይፋ እንዳደረጉ ሲፒጄ በመግለጫው ጠቅሷል። የጋዜጠኛው ጠበቃ አዲሱ አልማው፤ ጎበዜ ከጅቡቲ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱን እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ለሲፒጄ ተናግረዋል።

“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ዝም ለማሰኘት እና ለመበቀል በድፍረት ድንበር ተሻግረዋል” ያሉት ከሰሃራ በረሃ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት የሲፒጄ ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ፤ እስሩ “በስደት ደህንነት ፈልገው ከሀገራቸው በሄዱ ጋዜጠኞች ላይ ስጋት ይፈጥራል” ብለዋል። “ጎበዜ ያለመዘግየት ሊፈታ ይገባል” ያሉት የሲፒጄ ተወካይ የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ስለዋለበት እና ተላልፎ ስለተሰጠበት ሁኔታ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

ሰገነት ሚዲያ

13 May, 06:38


የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ቺፒግ ግብዣ ከሰሞኑ ወደ ቤጂግ ሊያቀኑ ነው። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በተለያዩ ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሏል።

ሰገነት ሚዲያ

12 May, 13:36


#Update

" ግድያውን የፈፀመው የፖሊስ አባል ነው " - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባቸው አሞኜ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ #በፖሊስ አባል መገደላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳወቀ።

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል መሆኑን ፓሊስ ገልጿል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ግድያውን የፈፀመው ግለሰብ ፤ የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ያመለክታል፡፡

ወረዳው ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም " ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ " በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ ገድሏቸዋል።

ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ለፈጣንና ታማኝ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/SegenetMedia1
https://t.me/SegenetMedia1