SDA የትንቢት ጹሑፎች @sdayetnbit Channel on Telegram

SDA የትንቢት ጹሑፎች

@sdayetnbit


“ዘመኑ ቀርቦአል፤ እንግዲህ ይህን የትንቢት ቃል የሚያነብ ብፁዕ ነው፤ የሚሰሙትና የተጻፈውንም የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው።”
— ራእይ 1፥3 (አዲሱ መ.ት)

SDA የትንቢት ጹሑፎች (Amharic)

በዚህ ልጅ መልኩ አርአያ ወጚት አንዴ ወጣቶች አለበት። እነዚህ ታሪኮች አምላክ እፈርዳለሁ፤ በመልካም ነገር አለው።nn"SDA የትንቢት ጹሑፎች" በዚህ ትንቢት ቃላቸውን አዲስ መልእክትን እንቅስፎ ለተመናው ትንቢት ሌሎችን ማህበረሰብ አዘንብለዋል። የሚደብቀውን በጣም ብዙ መረጃዎች በእንቅስቃሴ መልኩ አለን።nnየትንቢት ጹሑፎች ከተለያዩ ትንቢት በተለያዩ አፍላለጐ ፕሮግራሙ ማኅበረሰቦች በተያንነት አስተዋዛቸው።nnየትንቢት ጹሑፎች የሚለይበት ቅዳሜ መስማት መናገር ከሚቻሉበት ቀረበው ደግሞ በየጊዜ ልጆች ከቱዳን የሚኖሩ ጎበኛዎች በኋፍቆች የጥቅምት ማቆምና ለዶላር መሰብሰብ ነበር። አቶ እባብ ገርነትሽ በማየት ጊዜ ከምሽቱና እኔ በእኔ ላይ እንዲቆይ የባለቤትዎሽ የሆኖ ናት።nn"አቃቂ ምኞት ወይኒም ጌታ ነኝ፤ ከመኖር እኔ በላይ የለኝም፤ ከእኔም በላይ ስለ አንቺ እንጠይቃለን።" — እርሷ 12:7

SDA የትንቢት ጹሑፎች

17 Jan, 09:18


https://youtu.be/XqNuMt6UMV8?si=4SH1hhNcKDKsCRTq

SDA የትንቢት ጹሑፎች

16 Jan, 18:54


አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤
ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።

(ሰቆ ኤርምያስ 5 :21)
Coming soon

SDA የትንቢት ጹሑፎች

16 Jan, 08:10


የበጎ አድራጎት አገልግሎት

ምዕራፍ ሁለት ክፍል 2

ክርስቶስ የመጣው መከራን ሊያቃልል ነው- ይህ ዓለም ሰፊ የህመምተኞች ቤት ነው፣ ነገር ግን ክርስቶስ የታመሙትን ለመፈወስና ለሰይጣን ምርኮኞች ነጻነታቸውን ለማወጅ መጣ። እርሱ በራሱ ጤና እና ብርታት ነበር። እርሱ ለታመሙ፣ ለተቸገሩት፣ በአጋንንት ለተያዙት ህይወቱን ሰጠ። የፈውስ ኃይሉን ሊቀበል የመጣውን ማንንም አልመለሰም። እርሱን ለእርዳታ ይማጸኑት የነበሩ ሰዎች በራሳቸው ላይ በሽታ እንዳመጡ ያውቅ ነበር፤ ሆኖም ግን እነርሱን ከመፈወስ አሻፈረኝ አላለም። የክርስቶስ በጎነት በእነዚህ ምስኪን ነፍሳት ውስጥ በገባ ጊዜ፣ ኃጢአተኝነታቸው ተሰምቶአቸው ብዙዎች ከመንፈሳዊ ደዌያቸው፣ እንዲሁም ከሥጋዊ በሽታቸው ተፈወሱ። ወንጌል አሁንም ተመሳሳይ ኃይል አለው፤ ታድያ ዛሬ እንደነዚህ አይነት ውጤቶችን የማናየው ለምንድን ነው?

ክርስቶስ የእያንዳንዱ ሰው ስቃይ ይሰማዋል። እርኩሳን መናፍስት የሰውን አካል መዋቅር በኃይል ሲመነጭቁ፣ የዚህ እርግማን ውጤት ክርስቶስን ይሰማዋል። ትኩሳት የሕይወትን ጅረት ሲያነድድ ህመሙ ለእርሱ ይሰማዋል። እናም እርሱ በአካል በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ አሁንም የታመሙትን ለመፈወስ ፈቃደኛ ነው። የክርስቶስ አገልጋዮች የእርሱ ተወካዮች፣ የሥራው መስመሮች ናቸው። የፈውስ ኃይሉን በእነርሱ በኩል ለመጠቀም ይፈልጋል። -The Desire of Ages, 823, 824.

በሰው ልጆች ላይ በሚደርሱት ሀዘኖች እና ፈተናዎች ሁሉ ልምድ የነበረው ክርስቶስ ብቻ ነው። ከሴት የተወለደ ማንም እንዲህ ባለ ጽኑ ፈተና ከቶ አልተፈተነም ነበር፤ የዓለምን ኃጢአት እና ስቃይ ማንም ሰው በእርሱ ልክ አልተሸከመም። እንዲህ ያለ ስፊ ርህራሄ ወይም ሐዘኔታ ያለው ሌላ ማንም አልነበረም። በሁሉም የሰው ልጅ ልምምዶች ውስጥ ተካፋይ የሆነው እርሱ የእያንዳንዱን ሸክም፣ ፈተናና ትግል ከመረዳት ባሻገር አብሮ ይጋፈጣል። Education, 78.

ክርስቶስ ሃብታም እና ድሀን በተመሳሳይ ደረጃ ተደራሽ አድርጓቸዋል- ክርስቶስ በደረጃ ከድሆች ጋር ራሱን አስተካከለ፣ ይህን ያደረገው ከእርሱ ድህነት የተነሳ በባህሪ ውበት ባለ ጠጎች እና እንደ እርሱ የህይወት ሽታ እንሆን ዘንድ ነው። ድሀ በመሆኑ ለድሆች ሊራራላቸው ይችላል። የእርሱ ሰብአዊነት ሰብአዊነታቸውን ሊነካ እና ትክክለኛ ልማዶችን እና የተከበረ የባህሪ ፍጽምናን እንዲያገኙ ሊረዳቸው ይችላል። በሰማይ የማይጠፋ ሀብት ለራሳቸው እንዴት ማከማቸት እንደሚችሉ ሊያስተምራቸው ይችላል። ባሕርይውን በማሳየት እና እንከን በሌለው ንጽሕና የመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች ይሆኑ ዘንድ፣ በዓለም ካለው ከርኩሰት ምኞት አምልጠው የመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች እንዲሆኑ በሰማይ ቤት የነበረው አዛዥ፣ ከሰው ልጆች ጋር አንድ ሆነ፣ የመከራቸውና የችግራቸው ተካፋይም ሆነ። ክርስቶስ ለሀብታሞችም ደስታ ነበር፣ ምክንያቱም በስህተት ጨለማ ውስጥ የሚጠፉትን ነፍሳት ለማዳን ምድራዊ ንብረታቸውን እንዴት መስዋዕት ማድረግ እንደሚችሉ ያስተምራቸዋል። -Letter 150, 1899.

እንደ ክርስቶስ ያለ ሀዘኔታን እና ርኅራኄን አዳብሩ— ለወደቀው እና ለሚሰቃየው የሰው ልጅ የአዳኛችን የርኅራኄ ስሜት ተነሳስቷል። የእርሱ ተከታዮች ከሆናችሁ፣ ርኅራኄንና ለሌሎች ማስብን ማዳበር አለባችሁ። ለሰዎች መከራ ግድየለሽ መሆን የሌሎችን ሥቃይ ለመካፈል ፍላጎት ለማሳየት ቦታ መልቀቅ አለበት። መበለቲቱ፣ ወላጅ አልባው፣ የታመሙ እና በሞት አፋፍ ያሉ ሰዎች ሁልጊዜ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። የሰው ሁሉ ተስፋ እና መጽናኛ የሆነውን ኢየሱስን ከፍ አድርገው በማሳየት ወንጌልን ለማወጅ እድሉ ይህ ነው። የሚሰቃየው አካል እፎይታ ሲያገኝ እና ሰዎች ለተጎዱት ሰዎች ጥልቅ ፍላጎት ሲያሳዩ፣ ልብ ስለሚከፈት ሰማያዊውን የመድሃኒት ቅባት ወደ ውስጥ ማፍሰስ ይችላሉ። ኢየሱስን የምትመለከት ከሆነ እና ከእርሱ እውቀት፣ ብርታት እና ጸጋ እየተቀበልክ ከሆነ፣ የእርሱን አጽናኝነት ለሌሎች ማካፈል ትችላለህ፣ ምክንያቱም አጽናኙ ከአንተ ጋር ነውና። -The Medical Missionary, January, 1891.

ምዕራፍ ሦስት ይቀጥላል...
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

15 Jan, 14:38


የበጎ አድራጎት አገልግሎት

ምዕራፍ 2በመከራ ለሚሰቃየው ሰው የክርስቶስ ርህራሄ

ከሚሰቃየው ሰው ጋር ክርስቶስ ራሱ ይሰቃያል - የሰዎች ስቃይ የክርስቶስ ስቃይ ነው። ባልንጀሮቻቸው ላይ በሚያደርሱት በደል ምክንያት ህዝቡን ይወቅሳቸዋል። እጅግ ደካማ የሆኑትን፣ በጣም የተሳሳቱ አማኞችን ችላ ማለት ወይም ማጎሳቆል በራሱ ላይ እንደ ደረሰ ያህል እንደሚቆጥር ይናገራል። ሰዎች ለእነርሱ የሚያሳዩአቸውን በጎነት ለራሱ እንደተደረገ ይቆጥረዋል። የሚጠበቅብንን ግዴታ ሳያሳውቅ በጨለማ ውስጥ አልተወንም፤ ነገር ግን ዘወትር ተመሳሳይ ትምህርቶችን በተለያዩ ምስሎች እና በተለያዩ ብርሃኖች ደጋግሞ ያቀርባቸዋል። እርሱ ተዋናዮቹን ወደ መጨረሻው ታላቅ ቀን በማምጣት፣ ደካማ ለሆኑ ወንድሞቹ የሚደረገው አያያዝ በራሱ የተደረገ ያህል በምስጋና ወይም በውግዘት ምላሽ እንደሚያገኝ ይናገራል። እርሱ “ለእኔ አድርጋችሁታል” ወይም “አላደረጋችሁትም” ይላል።

እርሱ ምትካችን እና ዋስትናችን ነው። እርሱ እጅግ ደካማ ተከታዩ የሚጎዳውን ጉዳት ራሱ ለመቀበል ሲል ሰብአዊ ዘርን ተክቶ ቆመ። በልጆቹ ላይ ለሚደርሰው መከራ ግድየለሽ ተመልካች እንዲሆን ፈጽሞ የማይፈቅድለት የክርስቶስ ርኅራኄ እንደዚህ ነው። ለወደቀው ሰብአዊ ዘር ህይወቱን የሰጠውን የእርሱን ልብ የማይነካው ትንሽም ቁስል ቢሆን በቃል፣ በመንፈስ ወይም በድርጊት ሊፈጸም አይችልም። የክርስቶስ ደም ወደ እያንዳንዱ የአካል ክፍል የሚፈስበት ታላቅ ልብ መሆኑን እናስታውስ። እርሱ እያንዳንዱን ነርቭ ወደ ጥቃቅን እና ራቅ ወዳለው የሰውነት ክፍል የሚዘረጋበት ራስ ነው። ክርስቶስ በምስጢር የተያያዘበት አንድ የአካል ክፍል ሲሰቃይ አዳኛችንም ከፍተኛ ህመም ይሰማዋል።

ቤተ ክርስቲያን ትነቃለችን? በመንጋው ውስጥ ያሉ በጎችን እና ጠቦቶችን ሁሉ ማጽናናት ይችሉ ዘንድ አባላቱ ከክርስቶስ ጋር ርኅራኄ ይኖራቸዋልን? ለእነርሱ ሲል የሰማይ ባለ ግርማ የሆነው ጌታ የራሱን ዝና ተወ፤ ለእነርሱ ሲል ሙሉ በሙሉ በእርግማን ወደተበላሸ ዓለም መጣ፣ ለማስተማር፣ ከፍ ከፍ ለማድረግ እንዲሁም አመስጋኝ ላልሆኑ እና ለማይታዘዙ ሰዎች የዘላለም ደስታን ለመስጠት ቀንና ሌሊት ደከመ። በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ስለ እነርሱ ድሃ ሆነ። ስለ እነርሱ ራሱን ካደ። ስለ እነርሱ ብቸኝነትን፣ ንቀትን፣ ስድብን፣ መከራ እና ሞትን ተቀበለ። ስለ እነርሱም የባሪያን መልክ ያዘ። ይህ ለእኛ ምሳሌ ነው፤ ቅጂውን እንወስዳልንን? ለእግዚአብሔር ቅርስ እንክብካቤ እናደርጋለን? ለተሳሳቱ፣ ለተፈተኑ እና መከራ ውስጥ ላሉት ርኅራኄ ይኖረናልን? – Letter 45, 1894.

የድካማችን ስሜት ይሰማዋል— ምትካችን እና ዋስትናችን የሆነው ክርስቶስ የሃዘን ሰው እና ስቃይን የሚያውቅ ነበር። ሰብአዊ ህይወቱ ስፍር ቁጥር በሌለው ዋጋ ለሚዋጅ ውርስ የተከፈለ ረጅምና አዳጋች ጉዞ ነበር። አርሱ የድካማችን ስሜት ተሰማው። ለደሙ ዋጆ የሚሰጠውን ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ እንደ ልጆቹ አድርጎ ያሳድጋቸዋል፣ ርኅራኄው የተገባቸው ሰዎች ያደርጋቸዋል፣ ደግሞም ሥጋዊና መንፈሳዊ ፍላጎቶቻቸው እንዲሟሉላቸውም፣ “ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት” ሲል ለቤተ ክርስቲያኑ አደራ ይሰጣል። -Manuscript 40, 1899.

ምዕራፍ ሁለት (ክፍል 2) ይቀጥላል...
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

14 Jan, 04:37


ጌታ ለመስበክ ብቻ ሳይሆን ተስፋ የቆረጡትን ለማገልገል እና ተስፋ በሌላቸው ሰዎች ልብ ውስጥ ተስፋን ለማንሰራራት ራሱን ለስራ በሚሰጥ ነፍስ ሁሉ ይሰራል። የምድራዊ ህይወት መከራን በማቅለል እና በማለዘብ የበኩላችንን መወጣት አለብን። የምድራዊ ህይወት ጉስቁልና እና ምስጢሮች ከብዙ ሺህ አመታት በፊት እንደነበረው ሁሉ አሁንም ጨለማ እና ደመናማ ናቸው። ልንሰራ የሚገባ አንድ ነገር አለ፦ “ብርሃንሽ መጥቶአልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና፣ ተነሺ አብሪ።” በአቅራቢያችን ያሉ ችግረኞች አሉ፤ በመከራ ላይ ያሉ በአከባቢያችን አሉ። እነርሱን ለመርዳት መሞከር አለብን። በክርስቶስ ቸርነት፣ የታሸጉ የቅንነት እና ክርስቶስን የመምሰል ሥራ ምንጮች መከፈት አለባቸው። ሁሉንም ሥራ ብርታት ባለው በእርሱ ብርታት ከዚህ በፊት ሰርተን በማናውቀው አይነት ሁኔታ መሥራት አለብን። -Manuscript 65b, 1898.

ምዕራፍ ሁለት ይቀጥላል...

@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

14 Jan, 04:37


የበጎ አድራጎት አገልግሎት

ምዕራፍ አንድ (ክፍል 2)

መግታት መንፈሣዊ እድገትን ያቀጭጫል:- በራስ ወዳድነት አና እራስን ብቻ መንከባከብ ከመሞላት የላቀ መንፈሳዊነትን ከነፍስ ውስጥ የሚያደርቅ ፈጣን ነገር የለም። የራሳቸውን ፍላጎት የሚያረኩ እና ክርስቶስ ነፍሱን የሰጣቸውን ሰዎች ከመንከባከብ ቸል የሚሉ ሰዎች የሕይወትን እንጀራ እየበሉ ወይም ከድነት የውኃ ጉድጓድ ውኃ እየጠጡ አይደለም። እነርሱ ፍሬ እንደማያፈራ ዛፍ ደረቅና የጠወለጉ ናቸው። እነርሱ ያላቸውን ገንዘብ በራሳቸው ጉዳይ ላይ ብቻ የሚፈጁ መንፈሳዊ ድንክዬዎች ናቸው። ሆኖም ግን “ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል። - The Review and Herald, d, January 15, 1895.

ባለጠጎች ይበልጥ የሚኩራሩት፣ የራስ ብቃት የሚሰማቸው፣ ፍላጎታቸውን ብቻ የሚያረኩት እና ልበ ደንዳኖች የሚሆኑት፤ ሀብታሞች ለድሆች እንዲሰሩ እግዚአብሔር የወጠነውን ሥራ ቸል በማለታቸው ነው። ድሆችን ድሆች ስለሆኑ ብቻ ከእነርሱ እንዲለዩ በማድረጋቸው ምቀኞች እና ቅናተኞች ይሆኑ ዘንድ እድል ይሰጧቸዋል። በመሆኑም ብዙዎች መራራ ይሆናሉ፣ እንዲሁም ምንም ነገር ሳይኖራቸው ሁሉም ነገር ባላቸው ሰዎች ላይ በጥላቻ ይሞላሉ።

እግዚአብሔር ተግባራትን ይመዝናል፣ በመሆኑም በመጋቢነቱ ታማኝ ያልሆነ፣ በራሱ አቅም ሊያርመው የሚችለውን ክፉ ነገር ማረም ያቃተው ሰው፣ በሰማይ ቤት ውስጥ ምንም ክብር አይኖረውም። ለችግረኞች ደንታ ቢስ የሆኑ ሰዎች ታማኝነት እንደ ጎደላቸው መጋቢዎች ይቆጠራሉ፣ የእግዚአብሔር እና የሰው ጠላቶች ሆነውም ይመዘገባሉ። የእነርሱ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለመርዳት እግዚአብሔር በአደራ የሰጣቸውን መንገድ አላግባብ የሚጠቀሙ ሰዎች ከክርስቶስ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው ያረጋግጣሉ፣ ምክንያቱም ከእነርሱ በታች ለሆኑ ችግረኞች የክርስቶስን ርኅራኄ ማሳየት ተስኗቸዋል። —The Review and Herald, December 10, 1895.

ባለጠጎች በክርስቶስ ፈለግ የሚሄዱ ቢሆን ኖሮ— ሀብታም ሰው የእግዚአብሔር መጋቢ ነው፣ በመሆኑም በትህትና እና አምላካዊ ሕይወትን እየኖረ የክርስቶስን ፈለግ የሚከተል ከሆነ፣ የባህሪ ለውጥ በማድረግ የዋህ እና በልቡ ትሑት ይሆናል። እርሱ ንብረቱ በአደራ የተሰጠው ሀብት ብቻ እንደሆነ ይገነዘባል፣ እናም በክርስቶስ ምትክ የተቸገሩትን እና መከራ ውስጥ ያሉትን ለመርዳት የተቀደሰ አደራ እንደተሰጠው ይሰማዋል። ይህ ሥራ በእግዚአብሔር ዙፋን አጠገብ ከተቀመጡት መክሊት እና ውድ ሀብቶች ሽልማትን ያስገኛል። በዚህ መሰረት ባለጠጋ ሰው የጌታው ንብረት ታማኝ መጋቢ በመሆን የመንፈሳዊ ህይወት ስኬት ሊያገኝ ይችላል። Manuscript 22, 1898.

መከራ ባህሪይ ወደ ፍጽምና የሚደርስበት አንዱ መንገድ— የአዳኝ ቃላቶች በመከራ ወይም በሀዘን ለሚሰቃዩት የማጽናኛ መልእክት አላቸው። ሀዘናችን እንዲሁ ከባዶ ሜዳ የመነጨ አይሆንም። እግዚአብሔር “ፈቅዶ የሰውን ልጆች አያሠቃይም ወይም እንዲያዝኑ አያደርግም። ፈተናዎች እና መከራዎች እንዲደርሱብን ሲፈቅድ፣ “የቅድስናው ተካፋዮች እንሆን ዘንድ ለጥቅማችን ነው።” በእምነት ከተቀበልን፣ መራራና ለመሽከም የሚከብድ ፈተና በረከት ያስገኝልናል። የምድርን ደስታ የሚያበላሸው የጭካኔ ምት ዓይኖቻችንን ወደ መንግሥተ ሰማያት የምናዞርበት መንገድ ይሆናል። የደረሰባቸው ሀዘን መጽናኛን እንዲፈልጉ ወደ እርሱ ባይመራቸው ኖሮ ፈጽሞ ኢየሱስን ሊያውቁት የማይችሉ ስንቶች ነበሩ!

የህይወት ፈተናዎች ከባህሪያችን ቆሻሻን እና ሸካራነትን ለማስወገድ የሚያገለግሉ የእግዚአብሔር ሰራተኞች ናቸው። የእነዚህ ፈተናዎች የመጥረብ፣ ቅርጽ የማስያዝ፣ የመወልወል እና የማስተካከል ሂደቱ በጣም የሚያሠቃይ ሂደት ነው። ወደሚፈጨው ወፍጮ ውስጥ መግባት ከባድ ነገር ነው። ነገር ግን ድንጋዩ በሰማያዊው ቤተ መቅደስ ውስጥ ለቦታው ብቁ ይሆን ዘንድ እየተዘጋጀ ይገኛል። ምንም ጥቅም በሌላቸው ዕቃዎች ላይ ጌታ እንዲህ ዓይነቱን ጥንቃቄ የተሞላበት እና ጥልቅ ስራ አይሰራም። በቤተ መንግሥት አምሳያ ተጠርበው የሚቀርቡ የከበሩ ድንጋዮች ብቻ ናቸው።

በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጌታ ይሠራል። ታማኞች አስገራሚ ድሎችን ያገኛሉ፤ ድንቅ ትምህርቶችን ይማራሉ፤ የተከበሩ ተሞክሮዎችን ያገኛሉ። -Thoughts from the Mount of Blessing, 10, 10, 11.

መከራና አ አደጋ የአምላክ ቁጣ ምልክት አይደሉም- “ኢየሱስም ሲያልፍ ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው አየ። ደቀ መዛሙርቱም፤ መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ነው ወይስ ወላጆቹ? ብለው ጠየቁት። ኢየሱስም መልሶ፡- የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ አልበደሉም” ሲል መለሰላቸው።

በአጠቃላይ፤ ሐጢአት በዚህ ሕይወት (በምድር ላይ) ቅጣት እንደሚቀበል አይሁዶች ያምኑ ነበር። ሰው በራሱም ሆነ በቤተሰቡ ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ስቃይ ለተፈጸሙ ስህተቶች መቀጮ እንደሆነ ይቆጠር ነበር። ሁሉም የአምላክን ሕግ በመጣስ መሆኑ እውነት ነው፤ ነገር ግን ይህ የኃጢያት እና የውጤቶቹ ሁሉ ባለቤት የሆነው ሰይጣን፣ ሰዎች በሽታን እና ሞትን ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጡ እንደሆነ ማለትም ኃጢአት በተሰራ ቁጥር የሚደርስ የጭካኔ ቅጣት አድርገው እንዲመለከቱ መርቷቸዋል። ስለዚህም አንድ ታላቅ መከራ ወይም መቅሰፍት የደረሰበት የደረሰበት ሰው፣ እንደ ታላቅ ኃጢአተኛ የመቆጠር ተጨማሪ ሸክም ነበረበት።...

እግዚአብሔር ይህን ለመከላከል የተዘጋጀ ትምህርት ሰጥቷል። የኢዮብ ታሪክ መከራ በሰይጣን እንደሚመጣ እና ለመልካም ዓላማ በእግዚአብሔር የሚለወጥ እንደሆነ አሳይቷል። እስራኤል ግን ትምህርቱን አልተረዳም። የኢዮብን ወዳጆች በእግዚአብሔር የተገሰጹበትን ተመሳሳይ ስህተት አይሁዶች ክርስቶስን በመቃወም ደግመውታል።

በኃጢአትና በመከራ መካከል ካለው ግንኙነት ጋር በተያያዘ አይሁዶች የነበራቸውን ያንኑ እምነት የክርስቶስ ደቀ መዛሙርትም ይዘው ነበር። ኢየሱስ ስህተታቸውን ቢያርምም እንኳ የሰውን የስቃይ መንስኤ ምን እንደሆነ አልገለጸም፣ ውጤቱ ምን እንደሚሆን ግን ነገሯቸዋል። በዚህም ሳቢያ የእግዚአብሔር ሥራ ይገለጣል። “በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን ነኝ” ሲል ኢየሱስ ተናገረ። በዚያን ጊዜ የዕውሩን ዓይኖች ቀባና በሰሊሆም መጠመቂያ ይታጠብ ዘንድ ላከው፥ ሰውየውም ማየት ቻለ። ስለዚህም ሰዎች ለማወቅ በመጓጓት የሚያቀርቡለትን ጥያቄዎች ኢየሱስ ዘወትር ይመልስ እንደ ነበረ ሁሉ የደቀ መዛሙርቱን ጥያቄ ተግባራዊ በሆነ መንገድ መለሰላቸው። ደቀ መዛሙርቱ ኃጢአቱን የሠራው ወይም ያልሠራ ማን ነው በሚለው ጥያቄ ላይ እንዲወያዩ ሳይሆን የዓይነ ስውሩን ዓይን ማየት እንዲችል በማድረግ ረገድ የእግዚአብሔርን ኃይልና ምሕረት እንዲረዱ አደረጋቸው። -The Desire of Ages, 470, 471

ክርስቶስ በእኛ በኩል መታየት እና መሰማት አለበት- የእግዚአብሔር ንድፍ የታመሙት፣ ችግረኞች፣ እርኩሳን መናፍስት ያደረባቸው፣ በእኛ በኩል ድምፁን እንዲሰሙ ነው። እርሱ በሰብዓዊ ወኪሎቹ በኩል ዓለም ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቀውን አጽናኝ ለመሆን ይፈልጋል። ቃሉ “ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ በእኔም ደግሞ እመኑ” እያለ በተከታዮቹ ሊስተጋባ ይገባል።

SDA የትንቢት ጹሑፎች

13 Jan, 03:38


የበጎ አድራጎት አገልግሎት

ምዕራፍ 1- ድህነትና ጭንቀት ለምን ኖረ?

የሚምሩ ብፁዓን ናቸው ጌታ ኢየሱስ “የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፣ ምሕረትን ያገኛሉና” ይላል። ከዛሬ የበለጠ የምሕረት ተግባር የሚፈለግበት ጊዜ አልነበረም። የሚጨነቁ፣ የተጎዱ፣ የሚሰቃዩ እና በእልቂት አፋፍ ላይ ያሉ ድሆች በዙሪያችን አሉ።

ሐብት ያፈሩ ሰዎች ያንን ሀብት ያካበቱት ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን መክሊት ተጠቅመው ነው፣ ሆኖም ይህ ሀብት የማግኛ መክሊት የተሰጣቸው በድህነት ውስጥ ያሉትን ስቃያቸውን ለማቃለል ሲባል ነው። እነዚህ መክሊቶች ለሰዎች የተሰጧቸው በምድር ፍሬያማነት ሰዎች በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ የተትረፈረፈ አቅርቦት እንዲያገኙ ፀሓዩን እንዲበራ ዝናቡንም በጻድቃንና በኃጢአተኞች ላይ እንዲዘንብ በሚያደርገው በእርሱ ነው። እርሻዎች በእግዚአብሔር ተባርከዋል፣ በመሆኑም “በቸርነቱ ለድሆች አዘጋጀ።" -The Signs of the Times, June 13, 1892

መከራ እና ስቃይ በእግዚአብሔር የታቀደ አይደለም ዓለም በችግር እና በመከራ የተሞላች በመሆኗ በእግዚአብሔር ላይ የሚያጉረመርሙ ብዙዎች ናቸው፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህ መከራ ይኖር ዘንድ ፈጽሞ ዕቅዱ አልነበረም። የአንድ ሰው ልጆች ለእንጀራ እያለቀሱ ሌላው ሰው ቅንጦት በተሞላ ህይወት እንዲኖር ዕቅዱ አልነበረም። ጌታ ቸር አምላክ ነው። -Testimonies for the Church 6:273

እግዚአብሔር ሰዎችን መጋቢዎቹ አድርጓቸዋል፣ ስለዚህ እሱ በሰው ልጆች ስቃይ፣ መከራ፣ ራቁትነት እና አጦት መከሰስ የለበትም። ጌታ ለሁሉም እንዲትረፈረፍ አድርጎ እዘጋጅቷል። የባልንጀሮቻቸውን እጦት የሚያቃልሉባቸውን እጅግ አያሌ አቅርቦቶች በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሰጥቷል። ነገር ግን እግዚአብሔር መጋቢዎች ያደረጋቸው ሰዎች ፈተናውን አላለፉም ምክንያቱም እነርሱ መከራ ውስጥ ያሉትን እና የችግረኞችን ስቃይ ማቃለል አልቻሉም።

ከሰማይ በብዙ ባለጸግነት የተባረኩ ሰዎች የእግዚአብሔርን እቅድ መፈጸም ሲሳናቸው፣ እና ድሆችን እና የተጨቆኑትን ከስቃያቸው ማሳረፍ ያልቻሉ ሲሆኑ፣ ጌታ ያዝናል እናም በእርግጥ ይጎበኛቸዋል። እነርሱ እግዚአብሔር በስልጣናቸው ቁጥጥር ሥር ያስቀመጠውን እርዳታ ከጎረቤቶቻቸው ለመከልከል ምንም ምክንያት የላቸውም እግዚአብሔር ተዋርዷል፣ ባህሪው በሰይጣን አማካይነት በተቃራኒ መልኩ ቀርቧል።።ደግሞም እሱ በፈጠራቸው ፍጥረታት ላይ መከራ እንዲደርስ በሚያደርግ ጨካኝ ዳኛ ተመስሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ባሕርይ በተሳሳተ መንገድ መግለጽ እንደ እውነት እንዲታይ ተደርጓል፣ እናም በጠላት ፈተና አማካኝነት የሰዎች ልብ በእግዚአብሔር ላይ ደነድኗል። ሰይጣን ሰዎች ገንዘባቸውን ችግር ላይ ለሚገኙት እንዳይሰጡ በማገድ ራሱ ያመጣውን ክፋት በእግዚአብሔር ላይ ያላክካል። የራሱን ባህሪያት የእግዚአብሔር መለዮ አድርጎ ያቀርባል። - The Review and Herald, June 26, 1894.

መከራ እና እጦት አይኖርም ነበር ሰዎች የጌታቸው ንብረት ታማኝ መጋቢዎች የመሆን ግዴታቸውን ቢወጡ ኖሮ፣ ለዳቦ የሚያለቅስ፣ በድህነት የሚሰቃይ፣ የተራቆተ እና የተቸገረ አንድም ሰው ባልኖረ ነበር። የሰው ልጅ የተዘፈቀበትን ስቃይ ያስከትለው የሰዎች ታማኝ አለመሆን ነው። እግዚአብሔር መጋቢዎች አድርጎ የሾማቸው ሰዎች የጌታቸውን ንብረት አርሱ በሰጠው ዓላማ ላይ ቢያውሉ ኖሮ እንዲህ አይነቱ መከራ ባልኖረ ነበር። በተጠቀሰው ምሳሌው ጌታ ባለጠጋውን ሰው እንደፈተነው ሁሉ ብዙ መልካም ነገሮችን በመስጠት ሰዎችን ይፈትናል። በዚህ አለም ሀብት ታማኞች ካልሆንን እውነተኛውን ሀብት ማን አደራ ይሰጠናል? ከጌታ አፍ “በጎና ታማኝ አገልጋይ፣ መልካም አድርገሃል” የሚለውን ቃል የሚሰሙት በምድር ላይ ተፈትነው ያለፋ፣ ታማኝ ሆነው የተገኙት፣ ለሌሎች በመራራት እና ገንዘባቸውን ለመንግሥቱ መስፋፋት በመጠቀም የጌታን ቃል የታዘዙት ናቸው። —Ibid.

አንዳንዶች ሀብታሞች፣ አንዳንዶች ድሆች :- ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት እስካልፈጠሩ እና የራስ ወዳድነት ሃሳቦቻቸውን ከመተግበር ይልቅ አቅዱን እስካልፈጸሙ ድረስ እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎች ሀብታም አንዳንዶቹም ድሆች እንዲሆኑ የፈቀደበት ምክንያት ለሰው ልጆች ለዘላለም ምስጢር ሆኖ ይቆያል። Testimonies to Ministers and Gospel Workers, 280.

ፍቅርን እና ምህረትን ለማበረታታት:- በሰው ልብ ውስጥ የምሕረት እና የፍቅር ባህሪያት የማያቋርጥ ልምምድ እንዲኖር ሲባል በእግዚአብሔር መመሪያ ድሆች ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር እንዲሆኑ ተደርገዋል። ሰው የክርስቶስን ምህረት እና ርህራሄ ማካበት አለበት፤ ካዘነው፣ ከተጨነቀው፣ ከተቸገረውና ስቃይ ውስጥ ካለው ሰው ራሱን መለየት የለበትም። -The Signs of the Times, June 13, 1892.

በሰው ውስጥ እግዚአብሔርን የመምሰልን ባሕርይ ማጎልበት:— ዓለም ርኅራኄን ሲፈልግ፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ ጸሎትና እርዳታ ሲፈልግ፣ ክርስቶስን በተከታዮቹ ሕይወት ውስጥ ማየት እንዲችል፣ የእግዚአብሔር ሕዝብም በተመሳሳይ ሁኔታ ርህራሄያቸው ይገለጥ ዘንድ፣ ለጸሎታቸው ተግባራዊነ፣ እና በውስጣቸው መለኮታዊ ባህሪይ ይዳብር ዘንድ የሚያደርጉ ዕድሎችን መሻት አለባቸው።

እግዚአብሔር በእኛ መካከል ድሆችን፣ ምስኪኖችን፣ ሕሙማንን እና ችግረኞችን ያስቀመጠው እነዚህን እድሎች ለማቅረብ ነው። እነርሱ ለቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ሐብት በመሆናቸው እርሱ እንደሚንከባከባቸው ሁሉ እነርሱም ሊንከባከቧቸው ይገባል። በዚህ መንገድ እግዚአብሔር ቆሻሻውን አስወግዶ ወርቁን በማንጻት እኛ የሚያስፈልገንን የልብና የባህርይ እሴት ይሰጠናል።

ጌታ ያለ እኛ ትብብር ስራውን ማከናወን ይችላል። እርሱ በገንዘባችን፣ በጊዜአችን ወይም በጉልበታችን አይደገፍም። ቤተ ክርስቲያን ግን በእርሱ ፊት እጅግ የከበረች ናት። እርሷ ዕንቁዎቹን የያዘች ዕቃ፣ መንጋውን አቅፋ የያዘች በረት በመሆኗ፣ ያለ ነቁጣ እና እድፍ ወይም ከሌሎች መሰል ነገሮች ነጻ ሆና ለማየት ይጓጓል። ይህን ሊነገር በማይችል ሁኔታ እጅግ ይናፍቃል። ለእርሱ እንድንሠራ እድሎችን የሰጠን ለዚህ ነው፣ በመሆኑም ጥረታችንን የፍቅር እና የታማኝነት ምልክቶች አድርጎ ይቀበላል። -Testimonies for the Church 6:261.

የእግዚአብሔርን ምሕረት እንረዳ ዘንድ— ድሃውም ሆነ ባለጠጋው የእግዚአብሔር ልዩ እንክብካቤ እና ትኩረት አካል ናቸው። ድህነት ባይኖር ኖሮ፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እና ፍቅር የምንረዳበት፣ ሩህሩህ እና አዛኝ የሆነውን የሰማይ አባት የምናውቅበት መንገድ ሊኖር አይችልም። : -Letter 83, 1902.

እግዚአብሔር የሰጠን ለሌሎች እንድንሰጥ ነው— እግዚአብሔር በረከቱን የሚሰጠን እኛም ለሌሎች እናካፍል ዘንድ ነው። የዕለት እንጀራችንን ስንጠይቀው ከራሳችን በላይ ለተቸገሩት ያንኑ እናካፍል እንደሆነ ለማየት ልባችንን ይመለከታል። “እግዚአብሔር እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ” ብለን ስንጸልይ ለምንገናኛቸው ሁሉ ርኅራኄ እንድናሳይ ይጠባበቃል። ይህ የሰማይ አባታችን መሐሪ እንደሆነ እኛም መሐሪ መሆናችንን እና ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ማስረጃ ነው። -Testimonies for the Church 6:283, 284.

ምዕራፍ አንድ ክፍል 2 ይቀጥላል...

@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

12 Jan, 11:54


https://youtu.be/izFuUg7X87Q?si=Tq_LmyLPy3EaCc2b

SDA የትንቢት ጹሑፎች

10 Jan, 07:57


https://youtu.be/7UBxtY9YE9Y?si=WbrEn5J0xHduFKwu

አዲስ መዝሙር ነው ሰምታችሁ ተባረኩ ሌሎች አዳዲስ መዝሙሮች በብዛት ስለሚለቀቁ YouTube ቻናሌን Subscribe አድርጉ ለሌሎችም ያጋሩ እናመሰግናለን!🙏

SDA የትንቢት ጹሑፎች

08 Jan, 14:53


https://youtu.be/7wP9o7nSlhk?si=36hrqdkQZey2CbN0

SDA የትንቢት ጹሑፎች

07 Jan, 07:17


https://youtu.be/QwzTN-hDo7w?si=m0fPB0r55GJsIMA0

SDA የትንቢት ጹሑፎች

05 Jan, 12:12


የበጎ አድራጎት አገልግሎት

እውነተኛ ሚስዮናውያን የሆኑ እና የሦስተኛውን መልአክ መልእክት የሚያምኑት ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን አባላት፣ እግራቸውን ከሰንበት የመለሱትን ሁሉ፣ የኢሳይያስ አምሳ ስምንተኛውን ምዕራፍ መልእክት እንዲያጤኑ እንዴት አጥብቄ እንደማሳስባቸው አላውቅም። በዚህ ምዕራፍ የተደነገገው የበጎነት ሥራ እግዚአብሔር በዚህ ጊዜ ሕዝቡ እንዲሠራው የሚፈልገው ሥራ ነው። Testimonies for the Church 6:265-267.

ክርስቶስ እንዴት ያለ ሥራ የበዛበት ሕይወት ነበር የመራው! ቀን በቀን ወደ ችግረኞች እና ሐዘንተኞች የተዋረዱ መኖሪያዎች ሲገባ ፣ ለተጣሉት ተስፋን እና ለተጨነቁት ሰላምን ሲናገር ይታይ ነበር። ድሆች እና ችግረኞች የእርሱን ትኩረት ትልቁን ድርሻ አግኝተዋል። ልጆች እርሱን ወደውት ነበር። ሁሌም ዝግጁ ወደ ነበረው ርኀራኄው ይሳቡ ነበር። በቀላል እና በፍቅር ቃላቱ ብዙ ችግሮችን በመካከላቸው ይፈታላቸው ነበር። Manuscript 115, 1902.

ምንጭ:- ከጀርባ ሽፋን ላይ

@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

01 Jan, 06:06


የዘማሪ በረከት ዮሐንስ የFacebook ገጹ Hack ስለተደረገ ገጹ ወደነበረበት ቦታ እስክመለስ ለጊዜው ማንኛውም ፖስት የሚደረጉ ነገሮች እሱን (በረከት ዮሐንስን) አይወክሉም!

ለሁሉም እንድደርስ ሼር አድርጉት🙏

SDA የትንቢት ጹሑፎች

29 Dec, 10:05


የበጎ አድራጎት አገልግሎት

ክፍል 1:- የመከራ እና ድህነት መለኮታዊ ፍልስፍና

ዕንቁ ከስተሳሰብ

ኃጢአት እግዚአብሔር በሰው ልብ ውስጥ ያስቀመጠውን ፍቅር አጥፍቶታል። የቤተ ክርስቲያን ሥራ ይህ ፍቅር እንደገና እንዲቀጣጠል ማድረግ ነው። ራስ ወዳድነትን ከሰው ልብ በመንቀል እና በእርሱም ፋንታ በሰው ልብ ውስጥ ያለውን ቸርነት ቀድሞ በነበረው ፍጽምና በማስቀመጥ ረገድ ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር አለባት። -Letter 134, 1902.

ድሆች ከምድሪቱ ላይ አያልቁምና ስለዚህ እኔ፦ በአገርህ ውስጥ ላለው ድሀ ለተቸገረውም ወንድምህ እጅህን ትከፍታለህ ብዬ አዝዝሃለሁ።
(ዘዳግም 15፡11)

ምዕራፍ አንድ ይቀጥላል...

@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

28 Dec, 08:53


https://www.facebook.com/share/v/15xCGhE9Qn/
የ13ኛ ሰንበት ትምህርት ፕሮግራም፣የተማሪዎች ምረቃ እና የቃል ኪዳን ሥነሥርዓት በኢትዮ- ዳርባን 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን (ደቡብ አፍሪካ)

SDA የትንቢት ጹሑፎች

23 Dec, 11:12


ክርስቲያን፣በጌታ ቤት ያደጋችሁ አልፎ ተርፎም አገልጋዮች ከሆናችሁ በተለይ ደግሞ አድቬንቲስት ሆናችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ መልክ ተማምናችሁ አሻንጉሊት ሳትመስሉ ልክ እንደነዚህ የሠርግ ፕሮግራማችሁን አድርጉ!

እናመሰግናለን!

SDA የትንቢት ጹሑፎች

22 Dec, 13:01


https://youtu.be/qEmKDPAF-Xk?si=37QD8SlhfCev2n0P

SDA የትንቢት ጹሑፎች

18 Dec, 15:24


https://youtu.be/omvwRlMeBLk?si=qFNHFC903GZTf66G

SDA የትንቢት ጹሑፎች

17 Dec, 08:55


ሙሉ መጽሐፍ

SDA የትንቢት ጹሑፎች

13 Dec, 06:57


እንደፈለግነው አልታሸገም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:- “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም
(ኤርምያስ 29:11)

ስዩም ከዩኒቨርሲቲ ለመመረቅ በዝግጅት ላይ ነው፤ ለብዙ ወራት አንድ እጅግ የሚያምር የስፖርት መወዳደርያ ሚመስል መኪና በመኪና መሸጫ ቦታ ቆሞ ተመልክቶት ሲመኘው ቆይቷል። አባቱም ያንን ለመግዛት አቅም እንዳለው ስለሚያውቅ ሁሉ ነገር ቀርቶበት ይህንን መኪና ብቻ እንደሚፈልግ ነግሮታል። የምርቃት ቀኑ እየተቃረበ ሲመጣ ይህ ወጣት አባቱ ያንን መኪና መግዛቱን የሚያሳዩ ምልክቶችን መፈለግ ጀመረ። በመጨረሻ የምርቃቱ ቀን ማለዳ አባቱ ወደ ጥናት ክፍሉ ጠራው። ምን ያህል እንደኮራበትና እንዳስደሰተው የእርሱ ልጅ በመሆኑም ደስተኛ እንደሆነ እና እጅግ እንደሚወደው ከነገረው በኋላ በሚያምር ማሸግያ የታሸገ አነስተኛ የካርቶን ሳጥን ሰጠው። በጉጉት፣ ነገር ግን በጥቂቱም ቢሆን እየከፋው ሲከፍተው፤ ... የሚያምር በቆዳ የተለበደና የልጁ ስም በወርቃማ የተጻፈበት መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ አገኘ። በጣም ተናደደ፤ እየተቆጣም አባቱ ላይ ጮኸበት:- “እጅግ ብዙ ገንዘብ እያለህ ይህንን መጽሐፍ ቅዱስ ነው ምትሰጠኝ?" ብሎ መጽሐፍ ቅዱሱን ትቶ በሩጫ ከቤት ወጥቶ ሄደ።

ብዙ አመታት አለፉ ይህ ወጣት የተዋጣለት የንግድ ሰው ሆነ፤ የሚያምር ቤት እና መኪና ግሩም ቤተሰብንም አፈራ። ነገር ግን አባቱ እጅግ ማርጀቱን በማሰብ እርሱን ሄዶ ማየት እንዳለበት ተሰማው። ከምርቃቱ ቀን በኋላ አባቱን አይቶት አያውቅም ነበር። ነገሮችን አስተካክሎ ከመጓዙ በፊት አባቱ እንዳረፈ እና ሙሉ ንብረቱን ለእርሱ ማውረሱን የሚገልጽ መልዕክት ደረሰው። በፍጥነት ወደቤቱ ገብቶ እቃውን ሰብስቦ ወደ አባቱ ቤት ለመሄድ ተነሳ። አባቱ ቤት ሲደርስ ልቡ በድንገት በሃዘንና በጸጸት ተሞላ፤ አርፍዷል በጣምም ዘግይቷል። የአባቱን አስፈላጊ ሚባሉ ዶክመንቶች ሁሉ መፈታተሽ ጀመረ፤ እስካሁን ድረስ አዲስነቱን ያለቀቀውን መጽሐፍ ቅዱስ ከአመታት በፊት እንደተወው አገኘው። በእንባ አይኖቹ እያነባ መጽሐፉን መግለጥ ጀመረ። ምንም እንኳን ጥሩ ትዝታም ባይሆን አባቱን ሊያስታውስ የሚችልበት ብቸኛው ማስታወሻ እርሱ ነበር። ማንበቡን ሲጀምር ከመጽሐፍ ቅዱሱ የኋላ ገፅ አንድ ቁልፍ ወደቀ፤ የመኪና ቁልፍ፤ በላዩ ላይ የተንጠለጠለው ማንጠልጠያ ያ ሲመኘው የነበረውን የስፖርት መኪና መሸጫ ቤት ስም ተጽፎበታል። በዚያው ማንጠልጠያ ላይ የምርቃቱ ቀን እና “ሙሉ በሙሉ ተከፍሏል" የሚል ጽሁፍ ነበረበት።

እኛስ፣ ምን ያህል ጊዜ ነው እኛ እንደምንፈልገው ያልታሸጉ ስጦታዎቻችንን አልፈናቸው የሄድነው? እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:- “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም” (ኤር 29:11)

👉 በማስተዋል አንብቡ በዚህ ታሪክ ውስጥ ማን ነው ተጎጂው? አባት ወይስ ስዩም?
👉 የስዩም ችኮላ ምን አስከተለው?
👉 ከዚህ ታሪክ ምን ተማርን?

የዕለት እንጀራ (ገጽ 166)
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

11 Dec, 00:34


https://youtu.be/LQaj3LGVMuo?si=snznGNx4bZTYP-59

SDA የትንቢት ጹሑፎች

09 Dec, 11:58


ጃኬቴን ልደርብልሽ !

“ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል”
(ምሳሌ 17:17)

እውነተኛ ፍቅር ጊዜና ሁኔታ አይለውጠውም። ዛሬ ወይም በአንድ ወቅት ነፍስ እስከማይቀርልን ድረስ የወደድናቸውን ሰዎች እጃችን ከገቡ በኋላ ፍቅራችን መቀዝቀዝ የለበትም። እውነተኛ ፍቅር ጊዜ አይለውጠውም፡፡

በእጮኝነት ዘመናቸው በጣም የሚዋደዱ ፍቅረኛሞች ነበሩ። ወንዱ ነፍሱ እስከትወጣ ይወዳታል። አብረው እየሄዱ ከበረዳት የኔ ፍቅር ጃኬቴን ልደርብልሽ ይልና ይደርብላታል፤ እንቅፋት ከመታትም እኔን ይድፋኝ እኔ ልደፋ' ይላል ። እንዲህ እንዲህ እያለ ተጋብተው አንድ አስር አመት ከቆዩ በኋላ ሁኔታዎች እየተለወጡ መጡ። ያ የድሮ እንስፍስፍነቱ ቀዘቀዘና ከእለታት አንድ ቀን ወዳጅ ዘመድ ለመጠየቅ አብረው ሲሄዱ በርዷት “በረደኝ ስትለው በጎርናና ድምፁ:- ደርበሽ አትመጭም ነበር? ይላታል። እንቅፋት ሲያደናቅፋትም:- “ እያየሽ አትሄጂም? ” ይላታል። አጃኢብ ነው ጎበዝ! ለምን ብትሉ “ የቀደመውን ፍቅር ትቷልና ”። ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና” ብለን ይህን ሰው እንገስፀዋለን።

ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳልና '' ብሎ ይመክራል ጠቢቡ። እውነት ለመናገር በጣም የሚዋደዱ ወዳጆች አሁንም አሉ፣ ባይበዙም ቅሉ፤ በማይቀዘቅዝ ፍቅር የሚዋደዱ ጥንዶች አሉ፤ በንፁህ ፍቅር የሚዋደዱ አብሮ አደጎች ጓደኞች አሉ። ይሄም ይበል የሚያሰኝ እና ልንከተለው የሚገባ ግብር ነው፤ ምንም እንኳን አንዳንዶች “ ፍቅር ድሮ ቀረ ” ቢሉም።

አንድ ሰው ነበረ ይባላል፤ ስለ ትምህርት ሲነሳ “ውይ ትምህርት እኮ ድሮ ቀረ” ይላል። ስለ አገልግሎት ሲነሳ ውይ እሱማ ድሮ በእኛ ጊዜ ቀረ” ይላል። ብቻ ምን አለፋችሁ በሱ ቤት ሁሉ ነገር ድሮ የቀረ ነው። አንድ ቀን እንደ ልማዱ ከወጣቶች ጋር እያወራ ሳለ አንዱ ጎበዝ ለጓደኞቹ “የሚገርም ኮምፒዩተር ተገዛልኝ” አለ። ይሄኔ ያ ሰውዬ ቀበል አድርጎ “ውይ ኮምፒዩተር ድሮ ቀረ” አለ። ይገርማል ለመሆኑ ኮምፒዩተር ድሮ ነበር ግን? መልሱን ለእናንተ ትቻለሁ። አንድ ልብ ማለት ያለብን ነገር ዛሬም እንደ ድሮው መሆን እንደምንችል መዘንጋት የለብንም ። ለምሳሌ ድሮ የሰፈሩ ሰው በአንድ ላይ ቡና ይጠጣ ነበር ፤ አረም በደቦ ያርም ነበር ፤ ከብት ተራ በተራ ይጠብቅ ነበር። ይህ የፍቅሩ መገለጫ ሁነኛ ማሳያ ነው። ስለዚህም የድሮ ቀረ” መፈክርን ትተን ይልቁንስ “ ዘመኑን ዋጁት ” የሚለውን አስታውሰን ይሄን የጥላቻ ዘመን በፍቅር እንድንፈውሰው ያስፈልገናል። ልብ ማለት ያለብን፣ የፍቅር መገለጫ ሁሌ ደቦ ብቻ፣ ተራ ቡና መጠራራት ብቻ መገለጫው ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ወረት ያልነካው ፍቅር ጊዜው የሚሻው ነው፤ ምክንያቱም ይህ ዘመን በዘረኝነት ጥላቻ የቆረፈደ የፍቅርን ሸማ ገፎ የጣለ ጉደኛ ዘመን ነው። ስለዚህ ዘመናችንን፤ እንደ ጓደኛ፣ እንደ ቤተሰብ፣ እንደ ፍቅር አጋር፣ እንደ ክርስቲያን፣ በእውነተኛ ፍቅር እንድንጨርሰው ፈጣሪ ይርዳን አሜን! ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል ። እጸልያለሁ፡፡ ይህንንም በማድረግ እለት እለት አንተን በማምለክ እንዳድግ እርዳኝ። አሜን!

የዕለት እንጀራ (ገጽ 290)
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

09 Dec, 01:11


https://youtu.be/xww_k4E1YK4?si=X1KzyW2DRkKBb7kj

SDA የትንቢት ጹሑፎች

04 Dec, 13:02


የጽጌረዳዋ ምሳሌ

ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ
(1ኛ ተሰሎንቄ 4:3-5)

አንድ ወጣት ከዕለታት አንድ ቀን የአጎቱን የአበባ እርሻ ለመጎብኘት ወደዚያ አመራ። የአበባ እርሻው በተለያዩ የሚያማምሩ ጽጌረዳ አበቦች ተሞልቷል። ከዛም እየዞረ መጎብኘት ጀመረ፤ ሁሉም በጣም ያምሩ ነበር። ከዛ መሀል ግን አንዲት ጽጌረዳ ቀልቡን ሳበችው፤ እጅግ በጣም ታምራለች። ነገር ግን አልፈነዳችም፤ ገና እንቡጥ ነበረች። ፈንድታ መዓዛዋን እስኪያሸት ጓጓ፤ ነገር ግን መታገስ ስላልቻለ ጉብኝቱን ቀጠለ። ሌሎች የማረኩትን ጽጌረዳዎች እየዞረ ማሸተት ጀመረ። እጅግ ብዙ ጽጌረዳዎችን ጎንበስ ብሎ መዓዛቸውን አሸተተ። እንዳንዶቹንም እንዲያውም በቸልታ እየቀጠፈ ይጥል ነበር። በዚህ መሀል ዞር ሲል ቅድም ያያት እንቡጥ ጽጌረዳ ፈንድታለች። በደስታ እየሮጠ ሄደና ለማሽተት ሞከረ፤ ነገር ግን ምንም ልዩ መዓዛዋን ማሽተት አልቻለም፤ ምክንያቱም ቀድሞ ሌሎች ብዙ ጽጌረዳዎችን በማሽተት የማሽተት ስሜቱን ገድሎት ነበር፤ ወይም ሽታውን ተላምዶት ነበረ። በመሆኑም ምንም ማድረግ ስላልቻለ አዘነ።

ይህን ምሳሌ ወደ እኛ ሕይወት ስናመጣው እግዚአብሔር ባዘዘው የጋብቻ ሕይወት የተከለለ የግብረ ስጋ ግንኙነት ታግሶ ከመጠበቅ ይልቅ ከጋብቻ በፊት ብዙዎች ልክ እንደ ባለጽጌረዳው ወጣት የእነርሱ ያልሆኑትን ያልተፈቀደውን ግንኙነት በማድረግ እግዚአብሔር በጋብቻ የከለለውን ልዩ መዓዛ የመደሰት እድላቸውን ያባክናሉ። ስለዚህ ሰሪው እግዚአብሔር የሆነውን ተግባር 100% መደሰት ከፈለግክ/ሽ እርሱ እንዳዘዘው የራሳችሁን ጽጌረዳ የሆነ ወንድ ወይም ሴት በጋብቻ ብቻ እስክታገኙ መታገስ ጥቅሙ ለራስ ነው። አስቀድመን በምሳሌ እንዳነሳነው ወጣት አይነት ሕይወት ውስጥ ያላችሁም ጊዜው አልረፈደምና አቁማችሁ ወደ ጌታ መንገድ መመለስ ያዋጣል።

ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤” (1ኛ. ተሰ. 4:3-5 )

የዕለት እንጀራ (ገጽ 251)
@MesayD

👉 በተለይ ትዳር ሕይወት ውስጥ ያልገባን ወይም ለመግባት እየተዘጋጀን ያለን ወጣቶች ልብ ልንል የሚገባን ነገር ነውና በደንብ እናስብበት!!! (በትዳር ሕይወት ውስጥ ያላችሁም ብትሆኑ አስቡበት)

SDA የትንቢት ጹሑፎች

02 Dec, 11:14


https://youtu.be/UuZfvH86gx4?si=aFwZ409Qe-oqYnJY

SDA የትንቢት ጹሑፎች

28 Nov, 14:11


https://youtu.be/pPY9yl1tBqM?si=PECsgmYdDc-WRqli

SDA የትንቢት ጹሑፎች

27 Nov, 13:59


እንዳያመልጣችሁ!
ማህበራዊ ሚዲያን ለቀልድ ሳይሆን ለወንጌል

SDA የትንቢት ጹሑፎች

26 Nov, 13:34


አስገራሚ ጥያቄ

"...የእምነታችንን ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን..."
(ዕብራውያን 12:1)

አንዲት ጠና ያለች ሴት የቤተክርስቲያኑ ፓስተር ጋር በመሄድ “ከዛሬ ጀምሮ ለአምልኮ ወደ ቸርች አልመጣም አለችው። ፓስተሩም ደንገጥ ብሎ “ለም?" ብሎ ጠየቃት። እርሷም እንዲ አለች “ለአምልኮ የሚመጡት ሰዎች በስብከት ሰዓት ስልካቸው ላይ አፍጠው ፌስቡክና ሌሎች ሶሻል ሚድያዎችን ያያሉ፣ አንዳንዶቹ አፍ ለአፍ ገጥመው ያንሾካሽካሉ፣ ሰውን ያማሉ፣ ሌሎቹ በሃሳብ ሄደዋል። ሁሉም አሰመሳዮች ናቸው፤ ስለዚህ ሁለተኛ አልመጣም አለች። ፓስተሩ ዝም እለ። ከዚያ ትንሽ ቆይቶ "ውሳኔ ላይ ከመድረስሽ በፊት ላንቺ የሚሆን አንድ ጥያቄ አለኝ አላት ። አርሷም " ጠይቀኝ " አለችው። “አንድ ብርጭቆ ሙሉ ውሃ ይዘሸ ምንም ጠብ ሳይል በጉባኤው መሐል አቋርጥሽ መምጣት ትችያለሽ? እርሷም "በሚገባ እችላለው!" አለች ከዚያም በቀጣዩ የጉባኤ ቀን እንዳለችው አደረገች።

ፓስተሩም ጥያቄ አቀረበላት ዛሬ ጉባኤ ውሰጥ ስልክ የሚመለከት ወይም የሚያንሾካሽክ ሰው አይተሻል ወይ? አላት ሴትየዋም “አረ በፍፁም አላየሁም የብርጭቆው ውሃ እንዳይፈስ ሃሳቤን በሙሉ እዛ ላይ አድርጌ ነበር" አለች ፓስተሩም እንዲህ አለ:- "አየሸ መሉ ትኩረትሽ ብርጭቆው ላይ ሰለነበር ማንንም አላየሸም። ወደ ቤተከርስቲያን ስትመጪ ማድረግ ያለብሽ ነገር ይህ ነው፤ ሙሉ ትኩረትሽ እግዚአብሔር ላይ መሆን አለበት፥ ያለበለዝያ ትወድቂያለሽ። አይኖችሽን ከሰዎች ላይ አንስተሽ ክርስቶስ ላይ አድርጊ። ኢየሱስ እኔን ተከተሉኝ አለ እንጂ ክርስቲያኖችን ተከተሉ አላለም። አእምሮአችን ክርስቶስ የተናገረውን፣ ያደረገውን፣ ያሰበውን ምን አንደነበር እንዲያሰላስል እናድርግ፤ ከሰው ላይ ዓይናችን ይነሳ" አላት።

እኛም አይናችንን በሰዎች ላይ ከማድረግ ይልቅ በኢየሱስ ላይ አድርገን ጉዟችንን እስከመጨረሻው መቀጠል እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን።


የዕለት እንጀራ (ገጽ 159)
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

21 Nov, 12:35


ሰላም ውድ ወዳጆች!

ዛሬ ቀን ላይ በነበረን ስብሰባ የተገኛችሁ ፣ በተለያዩ መንገዶች አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ በተለያዩ ምክንያቶችም ልትገቡ ያልቻላችሁ ሁሉ ተባረኩ!

የውይይታችን የቪዲዮም ሆነ ምናልባት ለማውረድ ለምትቸገሩ ባነሰ file size የድምጽ ብቻ ፋይሎች ቀጥሎ ተያይዘዋል።

እንደ እኔ የግል እይታ የውይይቱ ዋና ዋና ዓላማዎች እና መልዕክቶች የሚከተሉት ነበሩ፦

የመተግበሪያው ግንባታ (application development) ሂደት በጥሩ ሁኔታ እየቀጠለ ነው። ጌታ ቢፈቅድ እጀግ ቢዘገይ ከ 1 ወር ያልበለጠ ስራ ነው የሚቀረው። ያውም በዋናነት የሚሰጧቸውን ዝማሬዎች የማስገባት ስራ!

አሁን ላይ የዝማሬ ማሰባሰቡ ሂደቱን / ፍጥነቱን የሚወስን ስራ ሆኖ ነው የሚገኘው። በመሆኑም ይህ ስራ በየቋንቋው በጥሩ ከሄደ ጥሩ መተግበሪያ በአጭር ጊዜ ውስጥ እናገኛለን። ያ ግን ካልሆነ ጊዜው ይረዝምብናል ተያያዥ ችግሮችም ይገጥሙናል ማለት ነው።

በመሆኑም የሚከተሉትን ነጥቦች እንደ ጋራ አቋም ወስደናል። ምናልባት የተለየ ሀሳብ / አስተያየት ካለ ሊቃኙ የሚችሉ ነጥቦች ናቸው።

ጌታ ቢፈቅድ ዛሬ ህዳር 12 / 2017 ነው እስከ ሳምንት (ህዳር 19 / 2017) ድረስ የዝማሬ ማስባሰቡ ፣ ዝማሬዎቹም ብበተጨማሪ ሰዎች ታይተው (የአርትኦት - editing) ስራቸው ተጠናቅቆ ለእኔ ወይንም ለመተግበሪያ ገንቢዎቹ (ወንድም ተግባቡ እና ወንድም ሚኪ) እንዲደርሱ። ምናልባት ጊዜ የሚጠብብ ከሆነ ሌላ 1 ሳምንት የሚሰጥ ሲሆን ይህም ዝም ብሎ ሳይሆን “እየሰራን ነው ጊዜ ይጨመርልን” የሚል ጥያቄ ከመጣ ብቻ የሚጨመር ይሆናል።

ዝማሬዎቹ የሚላኩት ባለፈው በተገለጸው መልኩ አንድ አዝማች ወይንም አንድ ቁጥር በአንድ excel cell ውስጥ ሆነው በደንብ ተሰርተው ይሆናል።

እነዚህ መዝሙሮች በሙሉ ከደረሷቸው በኋላ መተግበሪያ ገንቢ ወገኖቻችን ቢቻል በ 2 ሳምንት ካልሆነም ቢበዛ በ 1 ወር ውስጥ በየስልካችን ላይ ጭነን የምንመለከተው አስተያየትም ካለን የምንሰጥበት የመጀመሪያ ዕትም ሊባል የሚችል መተግበሪያ ይልኩልናል።

በዚያ ላይ ያለንን ሀሳብ በ 3 ቀናት ውስጥ እናቀርብና እነርሱም የሚሻለውን እና የሚቻለውን አካትተው በሳምንቱ ሁሉም ሂደት ግን ተጠናቅቆ ቢበዛ የዛሬ 2 ወር ለምዕመናን የሚለቀቅ ተጨማሪ የመዝሙር መተግበሪያ ይኖረናል!

ከሁሉም አስተያየት ሊመጣ የሚችልባቸው ነጥቦች፦

የመተግበሪያው ስያሜ (እስካሁን ውዳሴ እና ሀገርኛ የሚሉ መተግበሪያዎች ያሉን ሲሆን እነዚሁኑ modify በማድረግም ሆነ አዲስ ስያሜን መጠቆም ይቻላል።

መተግበሪያው በማን ስም ይውጣ እንበልና የማንን ስልክ / ኢሜይል ይያዝ? እዚህ ላይ በቤ/ክ ባለቤትነት ይሁን ለአንድ ሰበካ / ዩኒየን ይቅረብና ከተባለ ለኮሚቴ እየቀረበ የተለያዩ ሀሳቦች እየተሰጡበት . . . ሊጓተት በመጨረሻ ሳይሰራጭ ሊቀርም ይችላል። በእኔ ውሳኔም የአትክልት ወይንም የትንቢት ቃል / የኢትዮ አጋፔ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስራ አድርጎ መልቀቁንም አላመንኩበትም። ስለዚህ እዚህ ላይ ሀሳብ ካላችሁ ብታዋጡ!

እዚህ ውስጥ እስካሁን አልታየም - ቢታይ የምትሉት ሀሳብ ካለም መጠቆም ይቻላል።

ጌታ ሁላችሁንም ይባርክ!

ወንድም አትክልት

SDA የትንቢት ጹሑፎች

21 Nov, 08:32


https://youtu.be/eg9oDFiUZ2M?si=qSReni5ufbNyYNG6

አድሜ ተባረክ አሁንም ጸጋው ይብዛልህ 🙏

እንዲህ አይነት ፀጋ ያላቸውን አገልጋዮቻችንን በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ማበረታታት አለብን ይህ ዘማሪ በአንድ Single Track ብቻ መቅረት የለበትም 20 ሰዎች 5ሺህ ብር እያንዳንዳችን ቢናዋጣ 100,000 ብር ሆኖ ኮራ ብሎ አንድ ሙሉ አልበም እንዲያወጣ ያደርጋል ስለዚህ ይህንን ሥራ እንስራ እኔም አንዱ ነኝ ብቻ በጹሑፍ ማበረታታት አይደለም በሀሳቡ የምትስማሙ በውስጥ መስማር አናግሩኝ🙏 ይህም ከወንጌል ሥራዎች አንዱ ነውና!

SDA የትንቢት ጹሑፎች

21 Nov, 05:22


👋ሰላም ውድ የ አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ወጣቶች

👉በአድቬንቲስት የመጀመሪያው የወጣቶች የውይይት እና የትምህርት መድረክ በ ኤ ዋይ የደቀመዝሙርነት ትምህርት ቤት!!!


🌼ከህዳር 12 ጀምሮ በ https://t.me/AYBCLUB ቴሌግራም ግሩፕ በቀጥታ ስርጭት በ ተመረጡ ርዕሶች የትምህርት እና የጥያቄ እና የውይይት ፕሮግራም ይኖረናል።

👉ግሩፑን በመቀላቀል በብዙ ይጠቀሙ።

📚ህዳር 12 እና 16 በመጽሐፍ ቅዱስ እና በትንቢት መንፈስ ዙርያ ጥልቅ ጥናት እና ውይይት ይኖረናል።

📅ህዳር 12
🕐ከምሽቱ 3:00-4:00
በቀጥታ ስርጭት( Live stream)

🔖  ያላችሁን መንፈሳዊ ጥያቄዎች ሁሉ ጻፉልን!! 👉@Kidist_Desalegn

👉ቀጠሯችሁ ከእኛ ጋር ይሁን

https://t.me/AYBCLUB

ተባረኩ!!!
ለአድቬንቲስት ወጣቶች ብቻ!!

SDA የትንቢት ጹሑፎች

20 Nov, 15:10


ጭንቀታችን ለምን ይሁን?

ለየትኛው ዓለም ነው ሁልጊዜ የምንጨነቀው? መጽሐፍ ቅዱስ ("ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ"። ፊል 4:4) እያለን የኛ ጭንቀት ለምንድነው? ተጨንቀን በቁመታችን ላይ ስንዝር እንጨምር ይሁንን? ቃሉ እንደምለው... (ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? ማቴ. 6:27 እና ሉቃ. 12:25) እናም ጌታ አምላካችን የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእኔ ላይ ጣሉ እያለን የእኛ የጭንቀትን መዓት ተሸክመን የምንገዳገደው ለምን ይሁን? (እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1ጴጥ. 5:7) እንዲሁም (ትካዜህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል እርሱ ይደግፍሃል ለጻድቁም ለዘላለም ሁከትን አይሰጠውም። መዝ. 55:22)

ሌላው ደግሞ በምድር ላይ ምን ያክል እንደምንኖር እኛ አናውቅም ግን በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ("የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው"... መዝ. 90:10) ።

ስለዚህ ለየትኛው ዓለም ነው ጭንቀታችን????

መልዕክቴ እግዚአብሔር በሰጠን በዚህች በጥቂት ጊዜ ደስተኞች ሆነን እንኑር! ከዚያም መልካም መልካሙን እንስራ! የጌታን ዱካ እንከተል! የሚያስፈልገንን ሁሉ እርሱ ያውቃልና በእርሱ እንታመን!

እርሱን አስከብረን ማለፍ እንድንችል ጌታ አምላክ በጸጋው ይርዳን!

ወንድማችሁ @MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

17 Nov, 12:03


በአባታችን መተማመን

አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ እነርሱም አልጎዱኝም"
(ዳንኤል 6፡22)

በጣም ከሚደንቁኝ የሃይማኖት አባቶች ታሪክ አንዱ የዳንኤል ወደ አንበሳ አስኪጣል ድረስ የነበረው እምነት ነው። ዳንኤል በባቢሎን ከዚያም በሜዶንና ፋርስ መግንስት ጊዜ ትልቅ ስልጣ ነበረው። ስልጣን ቢኖረውም በእግዚአብሐር ላይ ሙሉ በሙሉ በመታመን እስከሞት ድረስ ታማኝ ሆነ። እንዲህ አይነት የእምነት ታሪኮች ሊያበታቱንና እኛም በምናልፈው ችግርና መከራ ሁሉ ድል እንድናገኝ፣ በእግዚአብሔርም ላይ ሙሉ በሙሉ የምንታመን እንድንህን ያደፋፍሩናል። ያኔ ከነ ዳንኤል ጋር የነበረው አምላክ አሁንም ከእኛ ጋር ነው። እግዚአብሔር ሳያውቅ በሕይወታችን የሚሆን ነገር እንደሌለ እርግጠኞች ልንሆን ይገባናል። ዳንኤልን በሰማይ አባቱ ሙሉ በሙሉ እንዲታመን ያደረገው አምላኩን በሚገባ ለለሚያውቀው ነበር። ዳንኤል በቀን ሶስት ጊዜ በመንበርከክ ራሱን ዝቅ በማድረግ ከልብ የሆነውን ጸሎቱን ወደ ሰማይ አባቱ ያቀርብ ነበር። ዳንኤል የሰማይ አባቱን ሳያነጋግር ቀኑን አይጀምርም ነበር።

አንድ ፓስተር ወደ እሩቅ አገር በአይሮፕላን ሲጓዝ ሳለ ፓይለቱ አስደንጋጭ የሆን መልዕክት አስተላለፈ። በዚያን ጊዜ በአውሮፕላን ውስጥ የነበሩት በሙሉ በድንጋጤ ሲርበደበዱ፤ እንድ ትንሽ ልጅ ግን በተረጋጋ መንፈስ ተኝታ ነበር። ይህ ፓስተር በጣም በመገረም ወደዚህች ልጅ ጠጋ ብሎ እየሆነ ያለውን ነገር ሲነግራት የመለሰችለት መልስ በጣም የሚያስደንቅ ነበር:- ፓይለቱ አባቴ ነው ፤ ዛሬ እቤታችን እንደሚወስደኝ ነግሮኛል ብላ ለዚህ ፓስተር መለሰችለት ፤ ከዚያም ወደ መኝታዋ ተመለሰች። እኛስ ዛሬ ምድርን በቃሉ የፈጠረና ለእኛ እስትንፋስን ካለማቋረጥ ለሚሰጠን ለታላቁ እግዚአብሔር ያለን አምነት እንዴት ነው? በነገሮች ሁሉ ልባችን በተስፋው ቃል ላይ ያርፋል? ልክ እንደትንሽዋ ልጅ አይሮፕላኑ በችግር ላይ ቢሆንም ፓይለቱ አባትዋ ስለነበረ ተረጋግታ እንደነበረ እኛም ሁሉን ቻይ በሆነው አምላካችን ላይ ተስፋችንን እንድናደርግና በአርሱ ብቻ እንድንታመን እንደ ዳንኤል በጸሎት መትጋት አለብን።

እግዚአብሔር የቃሉን እውነታነትና የተስፋውን እርግጠኝነት ራሳችን ሞክረን እንድንለማመደው አንዲህ በማለት ያድመናል:- “ እግዚአብሔር ቸር አንደሆነ ቅመሱ እዩም (መዝ. 34:8)። " ጠይቁ ይሰጣችኋል " በማለትም ያደፋፍረናል (ዮሐንስ 16:24)። የተስፋው ቃሎች ይፈጸማሉ። ሳይፈጸሙ የቀሩበት ጊዜ የለም፣ ለወደፊትም አይኖርም። ወደ ኢየሱስ ስንቀርብና በፍቅሩ ሙላት ስንደሰት ጥርጣሬያችንና ጨለማችን ሁሉ በመገኘቱ ብርሃን ይገፈፋሉ። (ወደ ከርስቶስ የሚያደርስ መንገድ ገጽ 108)

ልክ ህጻን ልጅ በአባቱ እንደሚተማመን፣ እኛም በሰማይ አባታችን በሁሉ ነገር ልንተማመንበት ይገባናል



የዕለት እንጀራ (ገጽ 186)
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

15 Nov, 08:13


https://www.youtube.com/live/JECG0ExsL9A?si=g8OM9_0KOim-xSNw

SDA የትንቢት ጹሑፎች

14 Nov, 14:06


https://youtu.be/2IpgWhAFqjU?si=arMjImFvU6mz7OzT

SDA የትንቢት ጹሑፎች

13 Nov, 19:55


እግዚአብሔር እውነቱን ከሰዎች ደብቆ አያውቅም ። ሰዎች ግን በራሳቸው ድርጊት ቃሉ ግልጽ እንዳይሆንላቸው ያደርጋሉ። ክርስቶስ መሲሕ ስለመሆኑ ለአይሁድ በቂ ማስረጃ ተሰጥቷቸው ነበር፤ ሆኖም ትምህርቱ ወሳኝ የሕይወት ለውጥ የሚጠይቅ ነበር። በመሆኑም ክርስቶስን ከተቀበሉ ለዘመናት ሲደሰቱበት የነበረውን ወግ፣ ሥርዓት ራስ ወዳድና አምላካዊ ያልሆኑ ልምምዶችን በሙሉ መተው እንዳለባቸው ተረዱ። የማይለወጠውን ዘላለማዊ እውነት ለመቀበል መስዋዕትነት ይጠይቃል። በመሆኑም በክርስቶስ እምነት ለመመሥረት እግዚአብሔር በማያዳግም መልኩ የሰጠውን ማስረጃ ለመቀበል አልወደዱም። በብሉይ ኪዳን የተጻፈውን እንደሚያምኑ ሲናገሩ የነበረ ቢሆንም በዚያ ውስጥ ግን ስለ ክርስቶስ ሕይወትና ባህሪይ የተነገረውን ምስክርነት ተቃወሙ። ከተለወጡ አስቀድመው ያከማቹትን አመለካከትና ሃሰብ ለመተው ስለሚገደዱ ለመለወጥ ፈሩ። መንገድ፣ እውነትና ሕይወት የሆነውን የወንጌል ሃብት ከእነርሱ ጋር የነበረ ቢሆንም ከሰማይ ሊሰጥ የሚችለውን ታላቁን ስጦታ እምቢ አሉ” (ኤለን ጂ ዋይት፣ የክርስቶስ ምሳሌያዊ ትምህርቶች፣ ገጽ 55)።

SDA የትንቢት ጹሑፎች

12 Nov, 20:24


ሀይማኖቱን ብሎ በ 22 አመቱ ጫማውን የሰቀለው ተጨዋች

ስዊዘርላንዳዊው እግርኳስ ተጨዋች ሲልቫን ዋልነር ሃይማኖቴ ቅዳሜ እንድጫወት አይፈቅድም በሚል ገና በ22 አመቱ ጫማውን መስቀሉን አስታውቋል::

ተጨዋቹ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታይ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በሚከተለው እምነት ቅዳሜ ሰዎች ምንም ስራ እንዲሰሩ አይፈቀድም ብሏል::

''እኔ የእየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ነኝ ሀይማኖታዊ የበዓል ቀናት ለእኔ ከምንም በላይ ነው ስለዚህ ቅዳሜ አልጫወትም እግርኳስ ለማቆም ወስኛለሁ '' ብሏል ተጨዋቹ::

ሲልቫን ዋልነር የስዊዘርላንድ ከ 21 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተጨዋችም ነበር::

SDA የትንቢት ጹሑፎች

10 Nov, 12:43


https://www.youtube.com/live/zv2847kJvnc?si=oVpl65LmMfqsz_ce

SDA የትንቢት ጹሑፎች

10 Nov, 09:21


ከፀሐይ በታች

“... ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው”
(መክብብ 1:14)

ጠቢቡ ሰለሞን “ስኬት ናቸው” ተብለው የሚታሰቡትን ብዙ ነገሮች በመክብብ ምዕራፍ 2 ውስጥ ከዘረዘረ በኋላ ሁሉንም አንድ ላይ ሰብስቦ “ ከንቱ ናቸው ” በማለት ይደመድማል። ምንድነው ከንቱ ያደረጋቸው? የሚለውን ሲገልጽ “ ከፀሐይ በታች " መሆናቸው ነው ይለናል። ይህንንም በመክብብ መጽሐፍ ብቻ 29 ጊዜ ጠቅሶታል። እውነትም ከፀሐይ ማዶ ያለውን ነገር ታሳቢ ያላደረገ ማንኛውም ነገር ከንቱ ነው። ከሰማያዊ ነገር የተለየ ሁሉ ከንቱ ነው። ከዘለዓለማዊነት የተለየ ጉዳይ ከንቱ ነው። ከእግዚአብሔር የተለየ ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።

ብዙ ፈላስፋዎች እና ሳይንቲስቶች “ እግዚአብሔርን ገድለናል” በማለት ተናግረዋል፤ በመጽሐፍም ጽፈውታል። ይህንን መስማትም ሆነ ማንበብ በእጅጉ ያስደነግጣል። እነዚህ ሰዎች የተሳካላቸው እና ደስተኞች ይመስላሉ። ነገር ግን ሕይወታቸው ትርጉም የለውም። ምክንያቱም ከፀሐይ በታች ናቸው። በእርግጥ እግዚአብሔር ሟች ባይሆንም፣ እነርሱ ግን ከጥበባቸው ውስጥ ገድለውታል፤ ከስኬታቸው ውስጥ ገድለውታል፤ ከሕይወታቸው ውስጥም እንዲሁ።

ውድ አንባቢ ፡- ነገሮችህ “ ከፀሐይ በታች " ከሆኑብህ የእግዚአብሔር ነገር ከውስጥህ እየሞተ ይሄዳል። ከፀሐይ ማዶ ያለው ከውስጥህ እየሞተ ይሄዳል። ያ ደግሞ ከንቱ ነው፤ የከንቱ ከንቱ። “ ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ፣ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል? ” ይለናል በማርቆስ 8፡36 ላይ። አብዛኛውን ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን የምናባክነው ከንቱ በሆነው የዚህ ምድር ኑሮ ላይ ነው። ዛሬ ግን ቆም ብለን ልናስብ ይገባል። የምናደርጋቸው ማናቸውም ነገሮች ከፀሐይ ማዶ ያለውን ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት።

ከከንቱ ነገር ተላቀን የዘለዓለም ሕይወትን ያማከለ ኑሮ መኖር እንድንችል ፈጣሪ ራሱ ይርዳን

የዕለት እንጀራ (ገጽ 239)

@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

08 Nov, 13:28


https://www.youtube.com/live/coUeZvKhkRA?si=bDY2_2zHiwxdMj69

SDA የትንቢት ጹሑፎች

08 Nov, 08:55


https://www.youtube.com/live/_c4dGo01o00?si=2oLUA_IIncCEj9l1

SDA የትንቢት ጹሑፎች

07 Nov, 12:05


https://www.youtube.com/live/lt6Fx2Zsl5E?si=mQqID2maR7Z-jIuP

SDA የትንቢት ጹሑፎች

07 Nov, 07:09


የምላስ ጉልበት

አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ ''
(መዝሙር 141:3)

በዚህ ምድር ሰውን ከሚያሰናክሉ በርካታ ነገሮች አንዱ ምላስ ነው ። ጌታ ኢየሱስ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል ብሎአል (ማቴ. 12:36–37)። ጠቢቡ ሰለሞንም ስለ ምላስ ጉልበት እንዲህ ብሎአል: “ የለዘበች ምላስ ቁጣን ትመልሳለች፣ ሸካራ ቃል ግን ቁጣን ታነሳለች ' (ምሳሌ 15:1)። " ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፣ ጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል ” (ምሳሌ 15:4)።

ምላስ መጠኑ ትንሽ ይሁን እንጂ መገንባት ይሁን ማፍረስ የሚችል ጉልበት አለው። ያዕቆብ ከፈረሶች ልጓም፣ ከመርከቦች መቅዘፊያ፣ እንዲሁም ከእሳት ጋር ያነፃፅረዋል። ምላስ መጠኑ ትንሽ ቢሆንም በሰው ሕይወት ውስጥ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው መቅዘፊያ በግዙፉ መርከብ፣ ልጓም በትልቁ ፈረስ፣ እንዲሁም ትንሽ እሳት በትልቁ ጫካ ላይ የሚጫወቱትን አይነት ሚና ይጫወታል። በምላስ ምክንያት በሁለት አገሮች መካከል ግጭት ሊፈጠር በሺህዎች የሚቆጠሩ ሊሞቱ ይችላሉ። በምላስ ምክንያት ወህኒ ቤቶች ሙሉ ናቸው። በምላስ ምክንያት ትዳራቸው የፈረሰ ብዙ ናቸው። ያዕቆብ “ምላስ መጥፎ ጉዳት ስለሚያስከትል ዝም በሉ' እያለን አይደለም፤ ነገር ግን ትክክለኝውን ነገር በትክክለኛ ጊዜ ተናገሩ” እያለን ነው

ምላስ የሚያስከትለው ጉዳት በጫካ ውስጥ ከሚነሳው እሳት ጋር ተመሳሳይ ነው። የእሳትን አጥፊነት ማንም ሰው ያውቀዋል። እሳትና ምላስን ከሚያመሳስሏቸው ነገሮች አንዱ ፍጥነታቸው ነው። ምላስ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችን ተጉዞ ሊጎዳ ይችላል። አንድ በአገሪቱ በምስራቅ አቅጣጫ ከብዙ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተለቀቀ የቃል ሚሳኤል በአጭር ጊዜ በሌላኛው ጥግ በሚኖሩ ላይ ትልቅ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ምላስ እጅ የለውም፣ ነገር ግን እጅ እንደሚገል ምላስም ይገድላል። እጅ በቅርብ ያለውን ሲገድል ምላስ ግን በሩቅ የሚኖረውንም ሊገድል ይችላል። ዳዊት ስለ ምላስ ከተናገረው አንዱን ልጥቀስላችሁ:- አፋቸውን በሰማይ አኖሩ፣ አንዳበታቸው በምድር ውስጥ ተመላለሰ ” (መዝ. 73:9)።

ምላስ በምድር ሁሉ የመመላለስ ኃይል አለው። ከዚያም አልፎ ወደ ሰማይም ይደርሳል። በአጠገቡ ያለውን ብቻ ሳይሆን የማያውቀውን እንግዳ ጭምር ሊያጠቃ ይችላል። ያዕቆብ ምላስን hመፀኛ አለም' ብሎ ይጠራዋል (ያዕቆብ 3:6)። አመፀኛ አለም ማለት ለእግዚአብሔር የማይታዘዝ አለም' ማለት ነው። ያልተቆጣጠሩት ምላስ ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳማይታዘዝ አለም ነው። አንድ የማይታዘዝ አመፀኛ አለም በውስጣችን አለ ማለት ነው። ምላስን ለመቆጣጠር ከሰው ውጪ የሆነ ኃይል ያስፈልጋል: " አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ ” (መዝሙር 141:3)

የዕለት እንጀራ (ገጽ 137)
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

06 Nov, 13:00


https://www.youtube.com/live/LiC5pEW1jG8?si=hw9fAU5nio_r7UmH

SDA የትንቢት ጹሑፎች

05 Nov, 14:58


https://www.youtube.com/live/cH0II8XN8Zo?si=Y9dRr3apSHTkn9ky

እስራኤል በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ክፍል 1

SDA የትንቢት ጹሑፎች

04 Nov, 17:01


https://youtu.be/2eeiA81GXt4?si=lwwU43GI7mWhNz0g

SDA የትንቢት ጹሑፎች

03 Nov, 08:07


የፈተና ደስታ

ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት
(ያዕቆብ 1፡2)

ብዙዎቻችን በፈተና ወይም በመከራ ምክንያት የሚገኝ ደስታን ለማጣጣም አልታደልንም። የዚህ ምክንያቱ ብዙ ነው። ከብዙ በጥቂቱ:-

1 . የሚደርሱብን ፈተናዎች ያዕቆብ እንዳለው በእምነታችን ምክንያት ሳይሆን በሥጋዊ ምኞታችን ምክንያት የሚመጡ ስለሆኑ ነው። *አመጋገብ ላይ ባለመጠንቀቅ በሽታዎች፣ ኑሮ ላይ ባለመጠንቀቅ እዳዎችና ሌሎች ብዙ ችግሮች ይመጣሉ* ።

2 . ብዙ ጊዜ ችግርና መከራ ሲመጣ ክፉ ሰዎች፣ ኃጢአተኞች ስለሆንን የመጣብን ስለሚመስለን በጥፋተኛነት እየተቸገርን የመከራውን መንፈሳዊ በረከት ማጣጣም አንችልም።

3 . የሚደርስብን ችግር ለመንፈሳዊ እድገታችን የሚበጅ ሳይሆን “ *ሰይጣን እኛን ለመጉዳት ያመጣብን ነው* ” ብለን በማሰብ በአምላካችን ላይ ያለው እምነታችን ይሸረሸራል። የመከራ እሳቱ እኛን ለማጥፋት ሳይሆን ለማጽዳት የመጣ መሆኑን ማመን ይከብደናል። በዚህ ምክንያት የፈተናን ደስታ አናውቀውም።

4 . ለፈተና የሚበቃም እምነት ስለማይኖረን በትንሹ ኮሽታ በመደንገጥ ጸሎትን እግዚአብሔርን ለመምሰል ሳይሆን ከፈተናና ከችግር ማምለጫ መንገድ እናደርገዋለን።

በእምነታችን ምክንያት ግን በሥራ፣ በትምህርት፣ በትዳር እና በተለያዩ የኑሮአችን ክፍሎች እንፈተናለን!! ይህን አይነት ፈተና የተፈተነ ሰው በትእግስት የሚበልጥ በረከትን መቀበሉ አይቀርም። አንዳንዶቻችን በትምህርት ቤት በሰንበት ምክንያት እሳት ውስጥ ገብተን እናውቃለን። በእምነታችን በቤተሰብ ውስጥ ችግር ውስጥ ገብተን እናውቅ ይሆናል። ከወዳጅ ዘመድ መሳደድ ይመጣብን ይሆናል። ይህ መከራ መጨረሻው በረከት ነው። ጌታን የሰቀሉት እኛን ቢደበድቡን ስለስሙ ስለሆነ ደስ ይበለን!!

የመከራ በረከቶች ብዙ ናቸው። ከሁሉ በላይ ግን ጠንካራ የሆነ ሕይወት፣ የእግዚአብሔርን እጅ ያየ እምነት ይኖረናል!!

የዕለት እንጀራ (ገጽ 134)
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

02 Nov, 17:27


https://www.youtube.com/live/mFqPxlZj4F4?si=Es_MW3uKRH6mLnot

ተጽፏል የቀጥታ ስርጭት

SDA የትንቢት ጹሑፎች

01 Nov, 08:10


https://www.youtube.com/live/AVRjLXrQfJ0?si=yXBW3X2uAcpXsFmI

5ኛ ሰንበት ትምህርት

SDA የትንቢት ጹሑፎች

01 Nov, 06:40


https://youtube.com/@alamurasdachurch?si=weWY7I5wKlTCapoF

ይህንን የአላሙራ SDA YouTube ቻናል Subscribe አድርጉ ሌላው ደግሞ በጣም ግሩም የሆኑ ዝማሬዎች አሉ ሰምታችሁ ተባረኩበት ለሌሎችም ሼር አድርጉ የበረከቱ ተካፋዮች ይሁኑ🙏

SDA የትንቢት ጹሑፎች

31 Oct, 16:03


ስምንቱ ሐኪሞች

"ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ"
3ኛ ዮሐንስ 1:2

1.ምግብ

ነገ የሚናገረው፤ የሚሰራው፤ የሚራመደው ዛሬ የተመገብነው ምግብ ነው። ስለዚህ ገንቢ ገንቢውን ብላው! የሚጎዳውን ሁሉ ተወው።

2.እንቅስቃሴ

የአካል እንቅስቃሴ ከሚታሰበው የበለጠ አስፈላጊ ነው፤ ስለዚህ ለነፍስህ ድረስ፣ ተነሳ! ተንቀሳቀስ!

3.ውኃ

አካላችን ከመቶ ሰባ ውኃ ነው። ሲነጋ በውኃ ጀምር፤ ቀኑን ሙሉ ቀጥል። ውኃ ለደፈረው መድኃኒት ነው።

4.ጸሐይ

በአግባቡ ከተጠቀሙበት ጸሐይ ፈውስና በረከት ናት። የጸሐይ ሙቀትና ብርሃን ባይኖር ኖሮ ምን ይውጠን ነበር!!

5.ራስን መግዛት

ራሱን የሚገዛ አገርን ከሚገዛ ይበልጣል። ለሰውነትህ የማይስማማውን እምቢ በል፣ ጠቃሚውን በልክ ተጠቀምበት"

6.አየር

መስኮቱን ከፈት ከፈት አድርገው አየር ይግባ፡፡ ክክርስቶስ ጸጋ ቀጥሎ ታላቁ ስጦታ አየር መሆኑን አትርሳ።

7.ዕረፍት

የዛሬ ዓመት ወይም ጡረታ ስገባ አርፋለሁ አትበል። በየቀኑ እፎይ በል፤ ተዝናና። ለሚያልፍ ዓለም ይህን ያህል አትጨነቅ።

8.እምነት በመለኮት

ባለቤቷን የምታምን በግ ላቷን ከውጭ ታሳድራለች። እግዚአብሔርን እመነው፤ አትጠራጠረው። ከእናት የበለጠ ያፈቅርሃል ፤ከእረኛም የበለጠ ይጠነቀቅልሃል።

“አንተ የእምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ በፊቱም የሚበጀውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ።" ዘጸ 15:26

የዕለት እንጀራ (ገጽ 272)
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

30 Oct, 14:52


https://www.youtube.com/live/Zth7QxHhnBE?si=OkL9ZbSoSaIyiHs4

5ኛ ሰንበት ትምህርት

SDA የትንቢት ጹሑፎች

30 Oct, 13:41


የዕለት እንጀራ (ገጽ 279)



                ክፉ ለማድረግ ጊዜ የለም

"ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኮላችሁ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደምን ልትሆኑ ይገባችኋል”
               (2 ጴጥሮስ 3፡11-12)

የጽድቅ ጠላት ከሆነው ጋር እየሰሩ ያሉ፣ ሳያውቁም የእርሱን ሥራ የሚሠሩ እንዲሁም ከክርስቶስ ጋር ሆነው የእርሱን ሥራ እየሠሩ ያሉ ሁሉ ነፍሳቸውን የከበበው ከባቢ አየር ወደ ምን እየወሰዳቸው እንደሆነ ሊያውቁ ይገባል።

ሰይጣን እውነቱን ባመኑት መካከል አለመስማማትን የሚያመጡትን፤ በወንድማማቾች መካከል መተማመን እንዲሳሳ ከሚያደርጉት ከማናቸውም ጋር በመተባበር ይደሰታል።

ይህ ለጌታ የምንዘጋጅበት ቀን ነው። አለማመንን ለመነጋገርና የሰይጣንን ስራ ለመስራት አሁን ጊዜ የለንም ። እየንዳንዱ የቅናትን፤የምቀኝነትንና የመከፋፈልን ዘር በመዝራት የሌሎችን እምነት እንዳይንድ ይጠንቀቅ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ቃሎቻችንን ስለሚሰማና ሲፈርድም አንድ ድርጊት ባመጣቸው ውጤቶች ልክም ጭምር ስለሚፈርድ ነው።

ደግሞም እራቱ ነፋሳት ሳይለቀቁ የተያዙት የእግዚአብሔር ባርያዎች ግንባሮች እስኪታተሙ ድረስ ነው። ከዚያ የምድር ኃይላት ወደ መጨረሻውና ታላቁ ጦርነት ኃይላቸውን ያሰፋሉ። በምህረት የተሰጠንን ጊዜ በጥንቃቄ ልናሻሽለው ይገባል፤ ተግተን ራሳችንን ልንመረምር ይገባናል።

የሚያስፈልገን የተገራ መንፈስ፣ የነፃ ልብና ሃሳብ ነው። ይህ ከችሎታ፣ ከብልሃት ወይም ከእውቀት የበለጠ ዋጋ ያለው ነው። ችሎታው ኖሯቸው በትክክል ከማይተገብሩት ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” *የሚለውን ለመታዘዝ የሰለጠነ ብዙም ችሎታ የሌለው ሰው አእምሮ ለእግዚአብሔር ሥራ በተሻለ ብቁ ነው። ሰዎች ዓለማዊ ነገሮችን በማወቃቸው ሊኩራሩ ይችላሉ። ነገር ግን እውነት፣ ሕይወትና መንገድ የሆነውን ክርስቶስን ካላውቁ አላዋቂዎች ሆነው እውቀታቸውም ከእነርሱ ጋር አብሮ የሚጠፋ ይሆናል። አለማዊ እውቀት ኃይል ቢሆንም እዕምሮን መለወጥ የሚችለውን ቃል ማወቅ ግን የማይጠፋ ነው።

              📝 ኤለን ኋይት፥ማራናታ 53

       @MesayD                     

SDA የትንቢት ጹሑፎች

28 Oct, 07:30


https://www.youtube.com/live/58IWegkfXnU?si=rKAtH00hSDi_NSyQ

ታላቁ ተጋድሎ
ምዕራፍ ሁለት

SDA የትንቢት ጹሑፎች

27 Oct, 12:20


https://www.youtube.com/live/vjCR6hGfw14?si=RBJhIkzJQWMF_c1N

ታላቁ ተጋድሎ

SDA የትንቢት ጹሑፎች

25 Oct, 14:37


Happy Sabbath መልካም ሰንበት

SDA የትንቢት ጹሑፎች

25 Oct, 06:22


https://www.youtube.com/live/mkhaV7-cflM?si=42DaS3NldOyNOJsi

4ኛ ሰንበት ትምህርት

SDA የትንቢት ጹሑፎች

24 Oct, 06:49


https://www.youtube.com/live/bWDjCyUm7zQ?si=c_539QNLHlx3MZVs

SDA የትንቢት ጹሑፎች

23 Oct, 15:32


https://www.facebook.com/share/v/gedhewn7YTU7V6G1/

የቀጥታ ስርጭት ከሀላባ ቁሊቶ

የመጨረሻ ዘመን መልዕክት

SDA የትንቢት ጹሑፎች

23 Oct, 08:04


በYouTube

https://www.youtube.com/live/hsgSkmLuelk?si=a1s2juSkUpZUZxNb

SDA የትንቢት ጹሑፎች

23 Oct, 07:58


የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት
በዘማሪ ማሞ ጴጥሮስ

https://www.facebook.com/share/v/C9WtvpuC6E2UkKNq/

SDA የትንቢት ጹሑፎች

21 Oct, 17:16


ከማክሰኞ ጀምሮ በሀላባ ቁሊቶ የሚደረገውን ታላቅ መንፈሳዊ ኮንፈረንስ ከቦታው በቀጥታ ስርጭት በFacebook እና በYouTube ቻናል ከHope Channel Ethiopia በተጨማሪ ለማስተላለፍ ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ! መልካም የበረከት ጊዜ እንደሚሆን ተስፋ አድርጋለሁ።

እስከዛው Facebookን follow እና YouTubeን Subscribe አድርጉ 🙏

Facebook Link 👇👇

https://www.facebook.com/dubushe?mibextid=ZbWKwL

YouTube👇👇

https://youtube.com/@mesayadventist1984?si=xDYXn5-fDvI_OHJb

SDA የትንቢት ጹሑፎች

20 Oct, 14:39


https://youtu.be/SBG1sWE0lwg?si=UGFJEvsdkRooaA10

SDA የትንቢት ጹሑፎች

20 Oct, 09:21


https://www.facebook.com/share/v/URj8UeDARaVKPY7T/

ተጽፏል Live መከታተል ትችላላችሁ🙏

SDA የትንቢት ጹሑፎች

15 Oct, 06:25


ሠላም ለእናንተ ይሁን ውድ የጌታ ልጆች 🤝

አንድ ሀሳብ በጥምቀት ዙሪያ በአዕምሮዬ ስመላለስ ነበር ያውም ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት የተጠመቀው ወደ 30 ዓመት ሆኖት እንደሆነ የሚታወቅ ነው። አሁን ላይ ግን እንደ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አባል እንደመሆኔም:-

1. ጥምቀት እየተካሄደበት ያለበት ሁኔታ ትክክል ነው ብለን እናስባለን?

2.ከዕድሜ አንፃር ስንመለከት?

3. ወይስ ወንጌላውያን /ፓስተሮች ለዩኒየን ሪፖርት ለማቅረብ ብቻ ነው ጥምቀት እየተካሄደ ያለው?

ምክንያቱም በጥምቀት ወቅት ቃል ኪዳን አለ ይህንን ቃል ኪዳን በደንብ ተረድተው አይደሉም ቃል የሚገቡት ለምሳሌ እኔ እራሴን ስመለከት ስጠመቅ 10ቱን ትዕዛዛት በቃል መጥራት ስለቻልኩ ብቻ ነው የተጠመቁት ለዛውም ቤተሰቦቼ ሳያውቁ እናም ቃል ኪዳን ሲገባም ምን ምን እንደተባለም ሳልረዳ ነው የገባሁት። ከዚህም አንፃር መታሰብ አለበት።

ስለዚህ ከጥምቀት በፊት ልጆች ምን እንደሚጎዳቸውና እንደማይጎዳቸው ለይተው እንዲያውቁ መደረግ አለባቸው ለሪፖርት ብላችሁ ያለዕድሜያቸው እንድጠመቁ አታድርጉ🙏

ሀሳባችሁን በጨዋነት አጋሩ...

ወንድማችሁ መሳይ ነኝ

SDA የትንቢት ጹሑፎች

12 Oct, 10:49


https://t.me/Nehemiahchristian

SDA የትንቢት ጹሑፎች

10 Oct, 14:17


https://youtu.be/7trZuSV3deE?si=yO4bdipK6h6Sjyv0

SDA የትንቢት ጹሑፎች

09 Oct, 02:58


📖 መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር 📖

40ኛ ትምህርት

ጠቅላላ ድግግም

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ጥቅሱን በሙሉ ወይም በከፊል ያጥኑ፤

1. የሱስ ስለ ፀሎት ምን ምክር ይሰጣል?
2. ስንት ጊዜ ልንፀልይ ይገባል?
3. ስንፀልይ ማን ይረዳናል?
4. በማን ስም ልንፀልይ ይገባል?
5. ከፀሎት ጋር ምን ሊኖር ይገባል?
6. ትፀልያለህን?
7. እግዚአብሔርን እንዳንበድል በልባችን ውስጥ ምን ሊኖረን ያሻል?
8. ለክርስቲያን እድገት ምን ያስፈልጋል?
9. ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ መጽሐፉን ለማጥናት ምን ምክር ሰጠው?
10. የእግዚአብሔርን ቃል ከማጥናት ሌላ ምን ያሻል?
11. የሰው ሁለንተናው ምንድር ነው ተባለ?
12. የሱስ ወደ ዘላለም ሕይወት ለመግባት ምን ያስፈልጋል አለ?
13. ከእግዚአብሔር ሕግ ስንቱን መጠበቅ ያስፈልጋል?
14. ኃይማኖት ሕግን ምን ታደርጋለች?
15. የመጀመሪያዎቹን አራቱን ትእዛዛት በቃልዎ ይደጋግሙ፤
16. የመጨረሻዎቹን አራት ትዕዛዛት በቃልዎ ይደጋግሙ፤
17. ሰንበት ተብሎ የተጠራው የትኛው ቀን ነው?
18. ሰንበት ለማን ተፈጠረ?
19. የሱስ በሰንበት ቀን ምን አደረገ?
20. ጳውሎስ በሰንበት ቀን ምን አደረገ?
21. ከሰንበት ትዕዛዝ መጀመሪያው መስመር ምንድር ነው የሚለው?
22. ከሰንበት ቀን በፊት ያለው ቀን ምን ይባላል?
23. በሰንበት ቀን ምን ልናደርግ አይገባም?
24. ክርስቲያኖች አሁንም ሰንበትን ሊጠብቁ ይገባልን?
25. ዓለምና በውስጥዋ ያሉ ሁሉ የማን ናቸው?
26. ሀብት እንድናገኝ ኃይል የሚሰጠን ማን ነው?
27. እግዚአብሔር ከገንዘባችን ሁሉ ምን ያህሉን እንድንመልስለት ይሻል?
28. ሚልክያስ 3፡8-9 በቃል ደጋግም?
29. ሰው አሥራት ሳይመልስ እውነተኛ ሊሆን ይችላልን?
30. ሰውነታችን የማነው?
31. ሰውነታችንን ብናበላሸው ምን እንሆናለን?
32. እግዚአብሔር ለሰው ጥንት ምን ዓይነት ምግብ ሰጠው?
33. የሥጋ ምግብ ከተፈቀደ በኋላ በእንስሳዎች መካከል ምን ልዩነት ተደረገ?
34. ንጹሕ ያልሆኑትን እንስሳዎችና አሳዎችን ለመለየት ምን ሕግ ተሰጠ?
35. ለምግብነት የማይሆኑ ወፎች ስም ተናገር:-
36. 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡30ን በቃልዎ ይደጋግሙ
37. እግዚአብሔር ስለ ትዕቢተኛ ምን ይላል?
38. ክርስቲያኖች እንቁ ወይም ጌጣ ጌጥ እንዳይለብሱ የሚያሳይ አንድ ወይም ብዙ ጥቅሶችን በቃል ተናገር:-
39. የክርስቲያን ጌጥ ምን ሊሆን ይገባል?
40. የሱስ እነማን ናቸው እግዚአብሔርን የሚያዩ አለ?
41. ጥንት ከተደረገ የእርክስና ነገር ምን ምሳሌ ለኛ ምክር እንዲሆን ተሰጠን?
42. መንግሥተ ሰማያት ከመግባት የሚከለከሉን የሥጋ ሥራዎች ምንድን ናቸው?
43. ዋና ልናስብበት የሚገባ ነገር ምንድር ነው?
44. ሰው ከምን ተፈጠረ? ሕይወትስ እንደምን ተሰጠው?
45. ሰው በኤድን ገነት ለዘላለም እንዲኖር የተሰጠው ምንድን ነው?
46. ሞት ወደ ዓለም እንደምን መጣ?
47. ሰው ሟች ነው ወይስ የማይሞት?
48. ሰው እንደምን ብቻ ነው የዘላለም ሕይወት የሚያገኝ?
49. የሰው አሟሟት የፍጥረቱ ተቃዋሚ መሆኑን እንደምን ያሳያል?
50. ሰው ሲሞት ምን ያውቃል?
51. በመጽሐፍ ቅዱስ ሞት ምን ይባላል?
52. ጻድቃኖች እንኳ ሲሞቱ ወደ ሰማይ እንደማይሄዱ ምን ማስረጃ አለ?
53. ሙታን ሕይወታቸውን የሚያገኙት መቼ ነው?
54. ርኩሳን መናፍስት ምንድር ናቸው?
55. ወደ ርኩሳን መናፍስት እንዳንሄድ ምን ተመከርን?
56. እግዚአብሔር ስለ ጠንቋይ እና ስለ ርኩሳን መናፍስት ምን አለ?
57. እግዚአብሔር አስማተኞችን ምን አደርጋለሁ አለ?
58. የእግዚአብሔር ልጆች ለምን ጠንቋይ መፍራት አይገባቸውም?
59. እግዚአብሔር ልጆቹን ለመጠበቅ ማንን ይሰጣቸዋል?
60. የእግዚአብሔር ልጆችን መላእክቶች እንዳዳኑዋቸው ሁለት ምሳሌ ስጥ:-
61. መላእክት ምን ይባላሉ?

፠፠፠፠ ክፍል 1 THE END ፠፠፠፠

መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር ክፍል 2 በቅርቡ...

፨፨፨፨፨፨፨@MesayD፨፨፨፨፨፨፨

SDA የትንቢት ጹሑፎች

08 Oct, 20:06


Live stream finished (2 minutes)

SDA የትንቢት ጹሑፎች

08 Oct, 20:03


Live stream started

SDA የትንቢት ጹሑፎች

08 Oct, 03:50


📖 መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር 📖

39ኛ ትምህርት

ጠቅላላ ክለሳ

የሚከተሉት ጥቅሶች የት ይገኛሉ ?

1. እውነተኛ እግዚአብሔር የተባለ ማነው?
2. እውነተኛ እግዚአብሔር ከጣኦት በምን ይለያል??
3. እግዚአብሔር እስከ መቼ ይኖራል?
4. ሐሰተኛ አምላኮች ምን ይሆናሉ?
5. አምስት የእግዚአብሔርን ጠባይ ግለጽ
6. መጽሐፍ ቅዱስ እንደምን ተሰጠ?
7. መጻሕፍት ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?
8. የእግዚአብሔር ቃል ምንድን ነው ተባለ?
9. የሱስ ሰው በምን ሊኖር ይገባዋል አለ?
10. እግዚአብሔር ማንን ነው ልጄ የሚለው?
11. የእግዚአብሔር ልጅ በማን መልክ ነው?
12. አብና ልጅ እንደምን ይቀራረባሉ?
13. እግዚአብሔርና ክርስቶስ በምን ታላቅ ሥራ አብረው ነበሩ?
14. ሰይጣን ከየት ወደቀ?
15. ሰይጣን ለምን እንዲጣል አስፈለገ?
16. ከሰይጣን ጋር እነማን ተጣሉ?
17. ስለ ሰይጣን ምን ተመከርን?
18. ሰይጣን መጨረሻው ምን ይሆናል?
19. ዓለም እንደምን ተፈጠረ?
20. በፍጥረት ሣምንት በያንዳንዱ ቀን ምን ተፈጠረ?
21. እግዚአብሔር በዓለም ላይ እንዲገዛ ለማን ሥልጣን ሰጠ?
22. ሰው በማን መልክ ተፈጠረ?
23. ሰው እንደምን ተፈጠረ?
24. እግዚአብሔር በፍጥረት መጨረሻ በሰባተኛው ቀን ምን አደረገ?
25. እግዚአብሔር አዳምንና ሔዋንን የት አኖራቸው?
26. ሰው እንደምን በኃጢአት ወደቀ?
27. በአዳም ኃጢአት ምክንያት በሰው ሁሉ ላይ ምን መጣበት?
28. ስለ ኃጢአት ምን ተባለ?
29. ስንት ናቸው ኃጢአት የሠሩት?
30. ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት የሚከለከሉን የሥጋ ሥራዎች ምንድር ናቸው?
31. ኃጢአት ምንድር ነው?
32. የዓለም መድኃኒት ማን ነው?
33. ሌላ መድኃኒት አለን?
34. ዮሐንስ 3፡16ን በቃል ደጋግም?
35. የሱስ ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ የማንን መልክ ወሰደ?
36. የሱስ የት ተወለደ?
37. ስሙን ማን ብለው ጠሩት? ትርጓሜውስ ምን ነበረ?
38. የሱስ ምን ዓይነት ሞት እንዲሞት አስፈላጊ ሆነ?
39. ለማን ኃጢአት መከራ ተቀበለ?
40. የሱስ ለማን ሞተ?
41. የሱስን እንደ መድሐኒትህ አድርገህ ተቀብለኸዋልን?
42. የሱስ በመቃብር ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ቆየ?
43. የሱስ ሞትን ስላሸነፈ አሁን ምን አለው?
44. የሱስ ስለ ሞት ራሱ ምን አለ?
45. የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ያሻል?
46. የሱስ አጽናኝ እንዲሆን ማንን እልክላችኋለሁ አለ?
47. መንፈስ ቅዱስ ምን ሊያደርግ ይችላል?
48. መንፈስ ቅዱስን ምን ልናደርግ አይገባንም?
49. መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ምን ያስፈልጋል?
50. ሰው ኃጢአቱ እንዲጠፋለት ምን ማድረግ ይገባዋል?
51. ሰዎችን በድለን እንደሆን ምን ልናደርግ ይገባናል?
52. ኃጢአታችንን ብንናዘዝ እግዚአብሔር ምን ያደርግልናል?
53. ኃጢአታችንን እስከ የት ድረስ ያርቀዋል?
54. ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንድንገባ ምን መለወጥ ያሻል?
55. የሱስ ይህን መለወጥ ምን ይለዋል?
56. የሱስ እንደገና መወለድን እንደምን ይገልጸዋል?
57. ዳግም ተወልደዋልን?
58. ንስሐ ከመግባትና ከመመለስ በኋላ ቀጥሎ ምን ያስፈልጋል?
59. ከጥምቀት በኋላ እንደምን ያለ ኑሮ ሊኖር ይገባል?
60. የሕግ ጽድቅ በማን ይፈፀማል?

40ኛ ትምህርት ይቀጥላል...
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

07 Oct, 17:10


ኢየሱስ:-

“ልቡ እስኪሰነጠቅ፣ ሕይወቱም እስክትደቅ ድረስ የመተላለፍን ኩነኔና የአባቱን ፊት መሰወር ተሸከመ። ይህ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለው ኃጢአተኞች እንዲድኑ ነበር ” (ኤለን ጂ ዋይት፣ ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 617)።

SDA የትንቢት ጹሑፎች

07 Oct, 03:31


📖 መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር 📖

38ኛ ትምህርት

ክለሳ

1. ሰው ኃጢአት ከሠራ በኋላ እግዚአብሔር ምን እርምጃ ወሰደበት?

መልስ ፡ ከኤደን ገነት አስወጣው።

«ከዚያም እግዚአብሔር አምላክ «ሰው መልካምንና ክፉውን ለይቶ በማወቅ ረገድ አሁን ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል፤ አሁን ደግሞ እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ቀጥፎ እንዳይበላ፣ ለዘላለምም እንዳይኖር ይከልከል አለ። ስለዚህ የተገኘበትን ምድር እንዲያርስ፣እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከዔደን የአትክልት ስፍራ አስወጣው፤ሰውንም ካስወጣው በኋላ፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በየአቅጣጫው የምትገለባብጥ ነበልባላዊ ሠይፍ ከዔደን በስተምስራቅ አኖረ።›› ዘፍ. 3:22-24

2. የሰው ተፈጥሮ ምንድን ነው?

መልስ ፡— ወደ ኃጢአት ማዘንበል።

«ሥጋ ለባሽ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን? ሰውስ ከፈጣሪው ይልቅ ንጹህ ሊሆን ይችላልን?›› ኢዮብ 4፡17።

3. ማን ብቻ ነው የማይሞት?

መልስ ፡ እግዚአብሔር።

«እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ሊቀረብ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፤ እርሱን ያየ ማንም የለም፤ ሊያየውም የሚችል የለም። ለእርሱ ክብርና ኃይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤አሜን።» 1 ጢሞቴ. 6፡16።

4. ሰው እንዴት ነው የዘላለም ሕይወት የሚያገኘው?

መልስ :— በየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ።

ሀ. ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንደይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤» ዮሐ. 3፡16

ለ. «ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሰጠን፤ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም፡፡ በእግዚአብሔር ልጅ ስም የምታምኑ እናንተ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ ይህን እጽፍላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ ማንኛውንም ነገር እንደፈቃዱ ብንለምን እርሱ ይሰማናል፤›› 1 ዮሐ. 5፡11-2።

5. ሰው ከሞተ በኋላ ሊያውቅ ይችላልን?

መልስ ፡—ምንም አያውቅም።

«ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁምና፤ መታሰቢያቸው ይረሳል፤ ምንም ዋጋ የላቸውም። ፍቅራቸው፣ ጥላቻቸው፣ ቅናታቸውም ከጠፋ ቆይቶአል፤ ከፀሐይ በታች በሚሆነው ነገር ሁሉ፣ ፈጽሞ ዕጣ ፈንታ አይኖራቸውም። መክ. 9:5-6።

6. ሞት ምን ይባላል?

መልስ ፡—በአበባና በእንቅልፍ ተመስሎአል።

ሀ. «እንደ አበባ ይፈካል፤ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላ ይፈጥናል፤ አይጸናምም።›› ኢዮብ 14፡12።

ለ. ይህን ከነገራቸው በኋላ፣ «ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤እኔም ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ» አላቸው። ዮሐ.11፡11-14

7. ሙታን ሕያው የሚሆኑት መቼ ነው?

መልስ ፡—በትንሣኤ ጠዋት።

በዚህ አትደነቁ፤ መቃብር ውስጥ ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።›› ዮሐ. 5:28:29።

8. ክፉ መናፍስት እነማን ናቸው?

መልስ ፡ የሰይጣን መልዕክተኞች ናቸው፡፡

ሀ. ታላቁ ዘንዶ፣ የጥንቱ እባብ ተጣለ፤ እርሱም ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው፣ ዓለምን ሁሉ የሚያስተው ነው፤ እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላዕክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።» ዮሐ ራዕይ 12፡9።

ለ. ‹‹ከዚያም ከዘንዶው አፍ፣ ከአውሬው አፍና ከሐሰተኛው ነቢይ አፍ እንቁራሪት የሚመስሉ ስሦስት ርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ። እነርሱም ምልክቶች የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲሰበስቧቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይሄዳሉ።› ራዕ. 16፡13:14።

9. እግዚአብሔር ስለ ጠንቋዮችና አስማተኞች የሰጠው ማስጠንቀቂያ ምንድን ነው?

መልስ ፡— ተጠንቀቁ እንዳትረክሱባቸው አለ።

ሀ. «እንዳትረክሱባቸው ወደ ሙታን ጠሪዎች ዘወር አትበሉ፤ መናፍስት ጠሪዎችንም አትፈልጉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።›› ዘሌዋ 19፡31

ለ. «በመካከልህ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሰዋ ሟርተኛ፣ ወይም መተተኛ፣ ሞራ ገላጭ፣ ጠንቋይ ወይም በድግምት የሚጠነቁል፤ መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከልህ ከቶ አይገኝ፡፡›› ዘዳ. 18፡10-12።

10. የእግዚአብሔር ልጆች ጠንቋይን ሊፈሩ ይገባቸዋልን?

መልስ : አይገባቸውም አለ።

በያዕቆብ ላይ የሚሠራ አስማት የለም፤ በእስራኤል ላይ የሚሠራ ሟርት አይኖርም፤ ለያዕቆብና ለእስራኤል እግዚአብሔር ያደረገውን እዩ! ይባልላቸዋል።›› ዘኁ.23፡23።

11. ጠንቋይ ትፈራለህን? እፈራለሁ / አልፈራም

12. እግዚአብሔር ሰዎችን እንዲጠብቁ ማንን ያዝላቸዋል?

መልስ ፡—ቅዱሳን መላእክትን፡፡

«የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።›› መዝ. 34፡7።

13. መላእክት ምን ይባላሉ?

መልስ :—አገልጋይ መናፍስት ይባላሉ፡፡

‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና መዝ. 91፡11››

‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።›› መዝ.34፡7

14. የሱስ ሲመጣ ሳለ መላእክት ምን ያደርጋሉ?

መልስ ፡—በየስፍራው ያሉትን ቅዱሳን ሁሉ ይሰበስባሉ፡፡

‹‹የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤ መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።›› ማቴ 24፡30-31።

39ኛ ትምህርት ይቀጥላል...
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

06 Oct, 18:42


ሥጋዊ ሕይወታችን የሚኖረው በምግብ ኃይል እንደሆነ ሁሉ መንፈሳዊ ሕይወታችንም የሚኖረው በእግዚአብሔር ቃል ነው ። እያንዳንዱ ሰው በግሉ ሕይወትን ከእግዚአብሔር ቃል ማግኘት አለበት። ከምግብ የሚገኘውን ድጋፍ ለማግኘት እያንዳንዳችን በግል መመገብ እንዳለብን ሁሉ ልክ በዚያው ዓይነት የእግዚአብሔርን ቃል መመገብ አለብን ። ቃሉን በሌላ ሰው አማካይነት ብቻ ማግኘት የለብንም። ቃሉን ለማስተዋል እንድንችል የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ ለማግኘት እግዚአብሔርን እየጠየቅን መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ማጥናት ይገባናል ” (የዘመናት ምኞት፣ ኤለን ጂ ዋይት፣ ገጽ 396)።

SDA የትንቢት ጹሑፎች

06 Oct, 03:36


📖 መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር 📖

37ኛ ትምህርት

የመላዕክት አገልግሎት

1. እግዚአብሔር ሰዎቹን ለመጠበቅ በማን ይጠቀማል?

መልስ ፡—በመላእክቶቹ ይጠቀማል።

ሀ. ‹‹ክፉ ነገር አያገኝህም፤ መቅሰፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋልና።›› መዝ 91፡10-11

ለ.‹‹እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ የእግዚአብሔር መልአክ ይሰፍራል፤ ያድናቸውማል።›› መዝ 34፡7

2. መላእክት ሊቆጠሩ ይችላሉን?

መልስ ፡—ሊቆጠሩ አይችሉም፡፡

ሀ. «ከዚያም ተመለከትሁ፤ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቁጥራቸውም ሺህ ጊዜ ሺህና እልፍ ጊዜ እልፍ ነበር፤ እነርሱም በዙፋኑና በሕያዋን ፍጡራኑ፣ በሽማግሌዎቹም ዙሪያ ከብበው ነበር›› ራዕይ 5፡11።

ለ. «እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ፣ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ መጥታችኋል፤ በደስታ ወደተሰበሰቡት ወደ አዕላፋት መላዕክት፣›› ዕብ 12፡22።

3. መላእክት ኃያል ናቸውን?

መልስ ፡—ብርቱዎችና ኃያላን ናቸው፡፡

«እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክቱ፤ ትዕዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኃያላን፤ እግዚአብሔርን ባርኩ›› መዝ. 103፡20

4. የእግዚአብሔርን ሰዎች ለማዳን አንድ መልአክ ምን አደረገ?

መልስ :- ጠላቶቻቸውን ፈጀ።

በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ከአሦራውያን ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰው ገደለ። በማግስቱም ሰዎቹ ሲነቁ ቦታው ሬሳ በሬሳ ሆኖ ተገኘ።›› 2 ነገሥ.19፡35።

5. እግዚአብሔር ሲድራቅና ሚሣቅን አብደናጎንና ዳንኤልን እንዴት አዳናቸው?

መልስ ፡ መላእክትን ልኮ።

ሀ. ከዚያም ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፤ ‹‹መልአኩን ልኮ አገልጋዮቹን ያዳነ፣ የሲድራቅ፣ የሚሳቅና የአብድናጎ አምላክ ይባረክ፤ በእርሱ በመታመን የንጉሡን ትዕዛዝ ጥሰው፣ ከአምላካቸው በቀር ሌላ አምላክ ለማገልገልም ሆነ ለእርሱ ለመስገድ ፈቃደኛ ባለመሆን ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጥተዋልና።›› ዳን. 3:28።

ለ. ይህም የሆነው ጥንታዌ ጥንቱ እስኪመጣና ለልዑል ቅዱሳን እስኪፈርድላቸው ድረስ ነበር፤ ከዚያም የልዑል ቅዱሳን መንግሥቱን የሚወርሱበት ዘመን መጣ።›› ዳን.7፡22

6. ጴጥሮስ ታስሮ ሳለ ማን አዳነው?

መልስ ፡ አንድ የእግዚአብሔር መልአክ አዳነው።

«የጌታ መልአክም ድንገት ታየ፤ በከፍሉም ውስጥ ብርሃን በራ፤መልአኩም የጴጥሮስን ጎን መታ አድርጎ ቀሰቀሰውና፣ ‹‹ቶሎ ተነሳ! አለው፤ በዚህ ጊዜ ሰንሰለቶቹ ከእጆቹ ወደቁ።›› ሐዋ. 12፡7።

7. መላእክት ማን ተብለው ይጠራሉ?

መልስ ፡ አገልጋይ መናፍስት።

መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?›› ዕብራ 1፡14።

8. ክርስቶስ ዳግመኛ ሲመጣ የተመረጡትን ሕዝብ ማን ይሰበስባቸዋል?

መልስ ፡ መላእክት ይሰበስቡዋቸዋል።

በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፤ የምድር ወገኖች ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የሰው ልጅም በሰማይ ደመና ሆኖ በኃይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፤ መላእክቱንም ከታላቅ የመለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ እነርሱም ምርጦቹን ከአራቱም ነፋሳት፣ ከሰማያት ከእንዱ ዳርቻ ወደ ሌላው ዳርቻ ይሰበሰባሉ።›› ማቴ. 24:30-31

38ኛ ትምህርት ይቀጥላል...
@MesayD

SDA የትንቢት ጹሑፎች

04 Oct, 08:22


የዚህ መጽሐፍ ሁኔታ ምን ሆነ?

1,678

subscribers

178

photos

12

videos