Institute of Technology-IoT, Hawassa University @iot_hu Channel on Telegram

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

@iot_hu


Ever to Excel- Official IoT Telegram Channel

Institute of Technology-IoT, Hawassa University (English)

Welcome to the official Telegram channel of the Institute of Technology at Hawassa University, also known as IoT HU! Here, we bring you the latest updates, news, and information about all things related to technology and innovation. Our channel is dedicated to bringing together students, faculty, alumni, and industry professionals to share knowledge, ideas, and opportunities in the field of technology. Whether you are a current student looking for internship opportunities, an alumna/alumnus wanting to stay connected with the tech community, or simply someone interested in the latest technological advancements, this channel is for you. Stay tuned for updates on workshops, seminars, job opportunities, and exciting projects happening at the Institute of Technology. Join us on this journey to excellence and innovation in the world of technology. Subscribe to our channel @iot_hu today and be part of the ever-growing IoT community at Hawassa University!

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

14 Feb, 20:10


UPCOMING EVENT @ HU

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

11 Feb, 14:54


መልካም ዜና ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል
**//***
 የመካንነት ችግር ፡ - የቱቦ መዘጋት እና የማህጸን ግርግዳ መጣበቅ መንስዔ ላለባቸው
 የቆየ የዳሌ ህመም (chronic pelvic pain)
 Endometriosis (ከማህጸን ጋር የተያያዘ የሕመም ስሜት )
 Sub-serosal myomas (በውጭኛው የማህፀን ግርግዳ ላይ ያለ የማህጸን እጢ)
 SUB-MUCOUS MYOMA (በውስጠኛው የማህፀን ግርግዳ ላይ ያለ የማህጸን እጢ)
 የዘር ፍሬ እጢ (Ovarian Cysts)

ከየካቲት 17 እስከ 20/2017 ዓ.ም ለማህፀን እና ተያያዥ ችግሮች የላፓራስኮፒ እና ሂስቴሮስኮፒ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ከፖላንድ በመጡ የሕክምና ቡድን እንደምናደርግ በደስታ እንገልፃለን።

 የላፓራስኮፒካል ቀዶ ጥገና ህክምና እጅግ ዘመናዊ ከመሆኑ የተነሳ ታካሚዎች በቶሎ ማገገም የሚችሉበት ዘዴ ነው ፡፡
 ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱት ህመመሞች ያለባችሁ ታካሚዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን

*ከየካቲት 6 እስከ 13, 2017 ዓ.ም በሆስፒታላችን በመገኘት ቅድመ ምርመራ እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

ቀድሞ የመጣ፣ ቀድሞ ይገለገላል ፡፡
መልዕክቱ ለሌሎች ይደርስ ዘንድ ያጋሩ !!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

06 Feb, 13:44


Today's Orientation for Freshman Students in Natural Science About Engineering.

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

04 Feb, 19:30


የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የደስታ መልዕክት
****//****
ውድ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ልዑካን:-

የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ውድድርን በአንደኝነት አሸናፊ ሆናችሁ በማጠናቀቃችሁ እጅግ አኩርታችሁናል እና እንኳን ደስ አላችሁ!
እንኳን ደስ አለን!

በነበራችሁ የአጭር ግዜ ዝግጅት ይሄንን የመሰለ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገብ በመቻላችሁ በጣም ልትመሰገኑ እና ልትኮሩ ይገባችኅዋል!

ለዚህ ድንቅ ውጤት ደግሞ በአስፈላጊው ነገር ሁሉ ከተማሪዎቻችን ጎን ሆናችሁ ስታሰለጥኑና ስታስተባብሩ ለነበራችሁት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህራን ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ!
በድጋሚ ለስፖርት ልዑካን እና ለመላው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ!

እንኳን ደስ አለን!

ጥር 27 ቀን 2017 ዓም
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

04 Feb, 19:30


የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
**
27/5/17
ላለፉት አስር ቀናት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ ሲጠናቀቅ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቡድን ከተወዳደሩት 49 ዩኒቨርሲቲዎች የአጠቃላይ ውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።

በትምህርት ሚኒስትር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የስፖርት ውድድሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ያለውን መስተጋብር ከሚያሳድጉ መንገዶች አንዱ መሆኑ በመታመኑ ከዘጠኝ አመታት ቆይታ በኃላ መጀመሩ ግቡን ያሳካ መሆኑን ገልፀዋል።

የአዲስአበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ደረጄ እንግዳ በበኩላቸው በአጠረ ጊዜ ዝግጅት ነገር ግን በደመቀ መልክ በተዘጋጀው ውድድር ላይ የበኩላቸውን ለተወጡ ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበው በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑና ለተሳተፉ ዩኒቨርሲቲዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ስፖርት ልዑክ መሪ ዶ/ር ንጉሱ ተገኔ ዩኒቨርሲቲው በዚህ ፌስቲቫል ላይ በአምስት የስፖርት ዓይነቶች ማለትም በእግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ፣ በቴኳንዶ፣ በቼዝ እና በባህል ስፖርቶች የተወዳደረ ሲሆን በቴኳንዶ እና በገበጣ የባህል ስፖርት ጨዋታ የወርቅ፣ እንዲሁም በቼዝና በገበጣ ጨዋታ ሌላ የብር ሜዳሊያ በማግኘት የአጠቃላይ ውድድሩ አሸናፊ የሆነበትን ዋንጫ መረከቡን ተናግረዋል።

በዕለቱ በሁሉም ውድድሮች አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች የተሸለሙ ሲሆን የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ማህበር ፕሬዚደንት ዶ/ር አባይ በላይሁን ፈስቲቫሉ በቀጣይ በአምስት ክላስተሮች ተከፋፍሎ በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

24 Jan, 11:03


በስፖርት ውድድሩ ተሳታፊዎችና ድጋፍ ላደረጉ አካላት የምሥጋና መርሃ-ግብር ተደረገ።
***
ጥር 16/2017 ዓም
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በዘንድሮው የስፖርት ውድድር ላይ ኢንስቲትዩቱን ወክለው ለተሳተፉ ተጫዋቾችና ስፖርቱን በልዩ ልዩ መልኩ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን የተመለከተ የምሥጋና መርሃ-ግብር አደረገ።
የምሥጋና መርሃ-ግብሩ በትናንትናው ዕለት የተደረገ ሲሆን፤ በውድድሩ ተሳትፎ ያደረጉ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና የስፖርት ቡድኑን ለመሩ እንዲሁም ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ የምሥጋና ወረቀት ከኢንስቲትዩቱ ተበርክቶላቸዋል። በሌላ በኩል ኢንስቲትዩቱን ወክለው በመጫዎት የዋንጫ ሽልማት አሸናፊ ሆነው የተመለሱ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች የተገኘውን ዋንጫ ለኢንስቲትዩቱ በክብር አስረክበዋል። የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይ/ዳይሬክተር ዶ/ር ኢ/ር ፋሲካ ቤተ እና የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ለስፖርተኞችና ስፖርቱን ሲደግፉ ለቆዩ ሁሉም ተሳታፊዎች ምሥጋና አቅርበዋል።

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

09 Jan, 18:55


ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የኮሌጅ አመራሮች የአፈፃፀም ውል ኮንትራት ተፈራረሙ::
*//*
ጥር 1 ቀን 2017 ዓም
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ከኮሌጅ ዲኖች: የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር: የህ/ጤ/ሣ/ኮ ቺፍ ኤግዘኪዩቲቭ ዳይሬክተር እና ከዳዬ ካምፓስ ኤግዘኪዩቲቭ ዳይሬክተር ጋር ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾችን የያዘውን የአፈፃፀም ውል ኮንትራት ዛሬ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት በተገኙበት ተፈራርመዋል::

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ስለ ውሉ አስፈላጊነት ባስረዱበት ንግግራቸው ሁሉም የሥራ ክፍሎች የየድርሻቸውን ኃላፊነት ቆጥረው ተረክበው ውጤቱንም እንዲያመጡ የወረደና ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን ገልፀዋል::

በዚህም መሰረት ዛሬ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ውል የገቡት የየኮሌጁ አመራሮች በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ በተዋረድ ከየትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ጋር ውል ገብተው አፈፃፀሙን የመምራት ግዴታ እንደተጣለባቸው እንዲረዱ መመሪያ የሰጡት ፕሬዝዳንቱ ከፍተኛ አመራሩም ሁሉንም የሥራ ሂደቶች የመከታተልና አስፈላጊውን ሁሉ አስተዳደራዊ ድጋፍ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ተናግረዋል::

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!
           
በዚህ ይከታተሉን:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

06 Jan, 16:53


እንኳን ለልደት በዓል/የገና በዓል አደረሳችሁ!
የክርስትና እምነት ተከታይ የኢንስቲትዩታችን ማህበረሰብ እንዲሁም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለልደት በዓል/የገና በዓል አደረሳችሁ።
የደስታ በዓል ይሁንላችሁ!
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

03 Jan, 14:37


ባለፉት ሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው ኢንስቲትዩት-አቀፍ ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል።
ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም
***
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው ኢንስቲትዩት-አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል። የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በዘንድሮው ዓመት በዩኒቨርሲቲ-አቀፍ ሊካሄድ የታሰበውን የተማሪዎች የስፖርት ውድድር ኢንስቲትዩቱን ብሎም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን ወክለው ሊወዳደሩ የሚችሉ ተማሪዎችን ለመምረጥ በየዘርፉ ውድድሮችን እያደረገ ቆይቷል። የዚህ ተወዳዳሪዎችን የመምረጥ ሂደት የተጀመረው ፋኩልቲዎችን በማወዳደር ሲሆን፤ ለፍፃሜ ጨዋታ የደረሱት የሲቪልና የተገነባ አካባቢ ምህንድስና ፋኩልቲ ከኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ ጋር ተጫውተው የሲቪልና የተገነባ አካባቢ ምህንድስና ፋኩልቲ 1፡0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የኢንተር-ፋኩልቲ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
በሌላ በኩል በኢንስቲትዩት ደረጃ በተካሄደው የ400ሜ እና የ1500ሜ የወንዶች ሩጫ ውድድሮች ተደርገዋል። በዚህ የሩጫ ውድድርም በ400ሜ አምስት ተወዳዳሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ዳናኤል ማህተሜ፣ አንተነህ ፍስሃ እና አብዱራሂም ሬድዋን ተከታትለው በመግባት በደረጃ አጠናቀዋል። በ1500ሜ ደግሞ ስድስት ተወዳዳሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ቢንያም ፍስሃ፣ ወንድማገኝ ስለሽ እና አዲሴ ቢራራ ተከታትለው በመግባት በደረጃ ውድድሩን አሸንፈዋል።
የኢንስቲትዩቱ ሰራተኛን በስፖርቱ ለማነቃቃትና ተሳትፎ እንዲደረግ በማለም የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች የተሳተፉበት በአካዳሚክ ስታፍ እና አስተዳደር ስታፍ የተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር ሲሆን የአስተዳደር ስታፍ 3፡2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የውድድሩ ማጠቃለያም ለአሸናፊዎች የሜዳሊያ እና ዋንጫ ሽልማት በማበርከት ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን፤ ለዚህ ውድድር መሳካት ተሳትፎ ላደረጉ የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች እና አጋር አካላትም የምስጋና ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል። በዚህ የመርሃ-ግብር መዝጊያ ላይ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የቴ/ኢ/ሳይ/ዳይሬክተር ዶ/ር ኢ/ር ፋሲካ ቤተ ለስፖርት ውድድሩ እንዲካሄድ ለሜዳ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወስደው ለሠሩ እና ጥረት ላደረጉ የኮሚቴ አባላት፤ ልዩ ልዩ ድርሻ ወስደው ሲሰሩ ለቆዩ በሁሉም ዘርፍ የሚችሉትን አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። ኢንስቲትዩቱን ወክለው ለኢንተር- ካምፓስ ውድድር የተመረጡትን ተማሪዎችም ምክረ-ሃሳባቸውን በማቅረብ በሚወዳደሩበት የስፖርት ዘርፍ ሁሉ ጥሩ ውጤት እንደሚያስገኙ ተስፋ በማድረግ መልካም ምኞታቸውን ከወዲሁ ገልጸዋል። የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በእግር ኳስ ውድድር፣ ሩጫ ውድድር፣ ቴኳንዶ ውድድርና የገበጣ ጨዋታ ውድድር እንደሚሳተፍ ታውቋል።

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

30 Nov, 20:19


The programme was based on the different stages of Design Thinking. All participants selected potential customer groups, analysed their problems and needs and formulated a specific design challenge. This was followed by a creative process where different ideas were generated and evaluated, which then led to an initial prototype. At the end of the week, all participants tested this prototype with potential customers in order to receive feedback for further development.
In addition to working in mixed Swiss-Ethiopian teams on their own idea, all participants were attending input sessions and workshops on topics such as:
•Different phases of Design Thinking
•Customer centered design: definition of a persona
•Storytelling
•Smart method for goal setting
•Business model canvas
•Presentation Skills
•Minimal viable product approach (MVP)
Finally, Institute Scientific Director Dr.-Ing. Fasika Bête Georgise gives a certificate for Participant and closing remark for the Entrepreneurship week.

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

30 Nov, 20:18


YEEP Entrepreneurship Week, 24 November – 30 November 2024
The Young Entrepreneur Exchange Project (YEEP) is a Swiss-Ethiopian non-profit initiative that promotes entrepreneurial thinking among young people and fosters technology know-how transfer and international exposure and intercultural learning. The YEEP Entrepreneurship Week was carried out with 40 participants from Hawassa University (HU), Höhere Fachschule für Technik Mittelland (hftm), Höhere Fachschule für Wirtschaft Bern (HFW) and Eidgenössische Technische Hochschule Zürich (ETHZ).

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

19 Nov, 13:41


Welcome to the Magnificent Hawassa University Main Campus & IOT Campus

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

13 Nov, 11:06


የ2017 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
ህዳር 4/2017 ዓም
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የ2017 በጀት ዓመት አንደኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የገመገመበት መድረክ አካሂዷል::

የዩኒቨርሲቲው ተ/ፕሬዚደንት ዶ/ር ችሮታው አየለ መድረኩን ባስጀመሩበት ንግግራቸው ዘንድሮ የግምገማ መድረኩን ለየት የሚያደርገው በቅርቡ በማኔጅመንት ውሳኔ ካውንስሉ ከዚህ ዓመት ጀምሮ በነበረው የአባላት ስብጥር ላይ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችን ማካተቱ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ሩብ ዓመት ግዜ ውስጥ በየኮሌጆችና ትምህርት ክፍሎች ደረጃ ምን ታቅዶ ምን እንደተከናወነ እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና በቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቅጣጫ ለመያዝ መድረኩ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ተ/ፕሬዝዳንቱ አክለዋል።

በግምገማ መድረኩ ከስምንት ኮሌጆች: የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና በንሳ ዳዬ ካምፓስ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ካውንስሉ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል::

ውይይቱን የመሩት ሶስቱም ምክትል ፕሬዝዳንቶች ዩኒቨርሲቲው አሁን በሚጠበቅበት የራስገዝነት እና የምርምር ዩኒቨርሲቲ የመሆን የሽግግር ወቅት ላይ እንደመሆኑ በየዘርፋቸው በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ያላቸውን ግብረመልስ ሲሰጡ አስሩም የዩኒቨርሲቲው ቅርንጫፎች በቀሪዎቹ የዓመቱ ወራት ውስጥ በአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው መፃኢ ዕድል ላይ ወሳኝ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል::

በአካዳሚክ ዘርፍ ላይ ድጅታላይዜሽን: የድህረምረቃ ፕሮግራሞችን ማጠናከር: የፕሮግራሞች ክለሳና አለማቀፍ እውቅና ማግኘት: ፕሮግራሞችን ከዩኒቨርሲቲው ልዩ የትኩረት መስክ ጋር ማጣጣም: ቤተሙከራዎችንና ቤተመፃህፍትን በቴክኖሎጂ ግብዓቶች ማሳደግ እንዲሁም የተማሪዎች ተግባር-ተኮር ትምህርትና ክህሎት

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

13 Nov, 11:06


ክህሎት ማሻሻያ እድሎች ላይ የበለጠ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ም/ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ኢ/ር ፍስሃ ጌታቸው ተናግረዋል::

በተመሳሳይ በምርምር: የማህበረሰብ አገልግሎትና ዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ዘርፎች ላይ የበለጠ መስራት የሚጠበቀው በጭብጥ-ተኮር ምርምሮችና የድህረምረቃ ተማሪዎችን ያካተቱ ፕሮጀክቶች ላይ ማትኮር: በዓለምአቀፍ ጆርናሎች ላይ ያለውን ህትመት መጨመር: የተጀመሩ ጆርናሎችን እውቅና እንዲያገኙ ማጠናከር: ራስን ለመቻል የሚረዱ ጠንካራ የትብብር ፕሮጀክቶችን ማምጣት: ከኢንዱስትሪው ጋር ጠንካራ ትስስር መፍጠር: የምርምርና ልህቀት ማዕከላትን ማዘመንና አለማቀፍ ስታንዳርድ ማሰጠት: ከማህበረሰቡ ጋር ትርጉም ያለው ትስስርና ትብብር መፍጠር: ያለንን ተፈጥሯዊና አካባቢያዊ ፀጋ ለይቶ ፈጠራ የታከለበት ችግር ፈቺ ምርምር መስራት እንደሚገኙበት ም/ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ ገልፀዋል::

በመጨረሻም በአስተዳደርና ልማት ዘርፉ ዩኒቨርሲቲው ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው በሰው ኃይልና የመሰረተ ልማት አቅም ግንባታ ላይ ሆኖ ከዚህ በኃላ እንደበፊቱ ወደጎን መስፋት ሳይሆን ጥራትና አግባብነት ላይ የበለጠ እንደሚሰራ: ካለው የበጀትና የገበያ ሁኔታ ጋር የተናበበ ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚገባቸው ጉዳዮች ልየታ ላይ የተመሰረተ የግዥ: የጥገናና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ሥራዎች ላይ ብሎም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ተጠቅሞ አገልግሎቶችን በሙሉ አውቶሜት ማድረግ ላይ መሆኑን ም/ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ አብራርተዋል::
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

በዚህ ይከታተሉን:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

09 Nov, 17:48


የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከል በተማሪዎች የቀረቡ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር አካሄደ።
ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም
*****
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከል በየዓመቱ የሚያካሂደውን የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር አካሄደ። ውድድሩ የተካሄደው ቀደም ብሎ ለተማሪዎች የሥራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ ከቆዬ በኋላ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎ በሥልጠናው የተሳተፉ ተማሪዎች በጋራ በመሆን የተለያዩ የቢዝነስ ሃሳቦቻቸውን ለተመረጡ ዳኞች አቅርበው ከተገመገመ በኋላ ከነዚህ አጠቃላይ ለውድድር ከቀረቡት አሥራ ሦስት የቢዝነስ ሃሳቦች መካከል አሸናፊ የሆኑት አሥሩ በውድድሩ ተመርጠው ወደ ማበልፀጊያ ማዕከሉ እንዲገቡ እድል አግኝተዋል።

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

09 Nov, 06:03


በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጽዳት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሰራተኞች ሥልጠና ተሰጠ
ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም
****
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለተቋሙ የጽዳት ሠራተኞች በጽዳት ሥራ ክህሎት፣ ግብዓት አጠቃቀምና የንብረት አያያዝ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ።
በሥልጠናው መርሃ ግብር መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የቴ/ኢ/ዳይ/ዳይሬክተር ዶ/ር ኢ/ር ፋሲካ ቤተ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ሁሉም የድርሻውን ኃላፊነት እና ሥራ ማከናወን እንደሚገባው የሚታወቅ በመሆኑ፤ የእናንተም አስተዋፅኦ የግቢውን ፅዳት በማስጠበቅ በተለይም በተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች፣ ካፍቴሪያ፣ የመማሪያ ክፍሎች እና በተቋሙ ውስጥ ባሉት መጸዳጃ ቤቶች ላይ በየዕለቱ ትኩረት ሰጥታችሁ በመስራት እና ንጽህናው የተጠበቀ የሥራ ከባቢን በመፍጠር በኩል ጉልህ አስተዋፅኦ ማድረግ የሚጠበቅ እና ማድረግ የሚቻል ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የቴ/ኢ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ከበደ በሥልጠና መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ለሠልጣኝ ሠራተኞች ባስተላለፉት መልዕክት ሥልጠናው አስፈላጊነቱ በጽዳት ሥራ ላይ ክህሎትን ለማሳደግ እና የኢንስቲትዩቱን ንብረት እና ግብዓቶች አጠቃቀም ላይ ግንዛቤን ለመፍጠር በመሆኑ፤ በተለይም ከዚህ ሥልጠና በምታገኙት ግንዛቤ ተጠቅማችሁ የግቢውን አጠቃላይ የጽዳት ሥራን በማከናውን በኩል ከምንጊዜውም የተሻለ አፈጻጸም የምታሳዩበት እና ከአደራ ጭምር የተሰጠ ኃላፊነት መሆኑን አስታውሰዋል።
ሥልጠናውን የሰጡት በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የብ/ሰ/ሀ/አ/ልማ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ደምሴ ዳንሳሞ እና የቴ/ኢ/ን/አስተዳደር ቡድን መሪ ወ/ሮ አመለወርቅ ሽብሩ ሲሆኑ ሥልጠናው ለሁለት ቀን ያህል ተሰጥቷል።

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

22 Oct, 10:53


የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2017 አንደኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም
****
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ። የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው የተካሄደው የሥራ ክፍሎች በዳይሬክተር ደረጃ በቀረበ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ መሠረት በማድረግ ሲሆን፤ በዚህም የኢንስቲትዩቱ አካ/ጉ/ም/ዳይሬክተር፣ የም/ቴክ/ሽግ/ም/ዳይሬክተር እና የማኔጂንግ ዳይሬክተር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።
በግምገማ መድረኩም ከተሳታፊዎች በኩል ጥያቄ እና አስተያየቶች ቀርበው ምላሽ ተሠጥቶባቸዋል። የግምገማ መድረኩን የመሩት የቴ/ኢ/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ኢ/ር ፋሲካ ቤተ ሲሆኑ፤ የግምገማ መድረኩ ለተሻለ የሥራ አፈፃፀምና ውጤታማነት አስፈላጊ በመሆኑ እንደ ኢንስቲትዩት ከኛ የሚጠበቀውን የሥራ ድርሻ ሁሉ አቅማችንን ተጠቅመን ከግብ ማድረስ የሚጠበቅ ጉዳይ ነው። በመሆኑም ሁሉም ክፍሎች እንደየ ዘርፋችሁ የሥራ ባለቤቶች መሆኑን አውቃችሁ በውይይቱ ላይ የተገኙ ሃሳቦችን እንደ ግብዓት በመውሰድ ለተሻለ የሥራ አፈፃፀም እና ውጤት ለመብቃት በኃላፊነት መስራት የሚጠበቅ መሆኑን በመልዕክታቸው የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

10 Oct, 10:03


ዶ/ር ችሮታው በማጠቃለያው በሰጡት የስራ መመሪያ ዩኒቨርሲቲዎች በአሁኑ ሰዓት ወደ ጎን ከመስፋት ይልቅ ወደ ውስጣዊ ጥራት ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው: የትምህርትም ሆነ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማረጋገጥ ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትም ሆነ ሌሎች ኮሌጆች የምርምርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶቻቸውን ወደ ገቢ ማመንጫነት መቀየርና የውስጥ አቅማቸውን ማጠናከር ቅድሚያ ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት: በተለይም ደግሞ ህንፃዎችና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ከተሰሩ በኃላ የአገልግሎት ዘመናቸውን እያሳጠረ ያለውን የፍሳሽ ማስወገጃ ሲስተም እንደ ሀገር ራሱ በሰፊው የሚታይ ችግር መሆኑን የታዘቡት እንደሆነ አንስተው የምህንድስና ባለሙያዎቹ በዚህ ችግር ላይ መፍትሄ ለማምጣት ምርምር እንዲሰሩ ጭምር አመላክተዋል:: በሌላው ምልከታቸው ደግሞ እንደባህል በሚመስል መልኩ በፅዳት ላይ አናሳ አመለካከት እንደሚስተዋል የገለፁት ተ/ፕሬዝዳንቱ ይሄ በማስተማርም: የንፅህና መጠበቂያ ግብዓቶችን በማቅረብም: ቁጥጥርና ክትትል አድርጎ በማስፈፀም ትኩረት የሚሻ ነው ብለዋል::

እዚህ ካምፓስ ያለው ከራሱ አልፎ ለከተማው ብሎም ለሀገርም የሚተርፍ እውቀትና አቅም ያለው የተማረ ኃይል እንዳለ እረዳለሁ ያሉት ዶ/ር ችሮታው ሁሉም እንደአዲስ ወደ ውስጡ እንዲያይና በራሱ አቅም መፍታት የሚችለውን ችግር ግዜ ሳይሰጥ መፍታት እንዳለበት አደራ ብለዋል:: የአካዳሚክ በተለይ ደግሞ የአስተዳደር ሰራተኞች ሕግና ኃላፊነታቸውን በሚጠበቀው ልክ ያለመረዳት ሁኔታዎች መኖራቸውን የገለፁት ተ/ፕሬዝዳንቱ ይሄንን ክፍተት ለመሙላት ሥራ መስራት በኃላም ግዴታውን በአግባቡ ያልተወጣውን አካል ተጠያቂ ወደ ማድረግ እንሄዳለን ሲሉ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል::
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

ሊያገኙን ቢፈልጉ:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice

Institute of Technology-IoT, Hawassa University

10 Oct, 10:03


የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
**//****
በዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚደንት ዶ/ር ችሮታው አየለ የተመራው የከፍተኛ አመራር ቡድን መስከረም 29/2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት የተለያዩ ምልከታዎችንና ውይይት አድርጓል።

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ኢ/ር ፋሲካ ቤተ ለአመራሮቹ ስለ ኢንስቲትዩቱ አመሰራረትና አሁናዊ ቁመና ብሎም ስለትኩረት አቅጣጫዎቹ አጠቃላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን አመራሩ ከኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎችና መምህራን ጋር በመሆን ጠቅላላውን ምድረግቢና ህንፃዎች፣ ቤተሙከራዎች፣ የሜካኒካል ምህንድስና ማምረቻና የተግባር ትምህርት ማዕከል፣ ቤተ መፃሕፍት፣ የቴክኖሎጂ ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል፣ የተማሪዎች ማደሪያና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ወደ ግብረመልስና ውይይት ተመልሰዋል::

ኢንስቲትዩቱ በሙሉ አቅሙ እንዲሰራና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ የኮምፒውተርና የኢንተርኔት ዝርጋታን በተለያዩ ህንጻዎች ላይ ማስፋፋት፣ የመምህራን አቅም ለመገንባትና ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት እንዲሁም ሶስተኛ ዲግሪ ያላቸው መምህራን ቁጥር በማሳደግ የምርምር ተሳትፎን መጨመር እንዲቻል ከፍተኛ አመራሮቹ ድጋፍ እንዲያደርጉ በኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ጥያቄና አስተያየት ቀርቧል።

ተ/ፕሬዝዳንቱና ም/ፕሬዝዳንቶች በውይይቱ ማጠቃለያ ወቅት ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል የቴክኖሎጂና ምህንድስና ዘርፉ የመንግስትም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ እንደመሆኑ ኢንስቲትዩቱ በተቀመጡለት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በማተኮር ሀገራዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንዲችል ሁሉም በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ህጋዊ አሰራርን ተከትለው በልዩ ትኩረት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልጸዋል።