ከመፃህፍት አለም @kanebebekutelakafelachu Channel on Telegram

ከመፃህፍት አለም

@kanebebekutelakafelachu


በ ቻነላችን ስለ ጤና፣ግጥም፣ቀልዶች፣ወጎች፣አስተማሪ ታሪኮች እና ስለ ፍቅር እንወያዪበታለን

ከመፃህፍት አለም (Amharic)

ከመፃህፍት አለም ከምንም ህዝብ አስተማሪ ታሪኮች እና ምንም አስተማሪ አለም፣ 'kanebebekutelakafelachu' እንደሚከነዛበት መፍትሄ ነው። በ ቻነላችን ስለ ጤና፣ ግጥም፣ ቀልዶች፣ ወጎች፣ አስተማሪ ታሪኮች እና ስለ ፍቅር እንበያያቸዋል። በዚህ ታሪከች ለሁሉም ህዝብ በመመረጧ ለጤና፣ ለግጥም፣ ለቀልዶች፣ ለወጎች፣ ለአስተማሪ ታሪኮች እና ለፍቅር ብንወያያን አደረጋችን። ትብብር የሆነች ቢስ እና የታተሙት ፅሁፍ እና አስተሳሰብ ቋንቋዎችን እባኮት፣ መምህር ወዳለሁኔ በምርምር ያለፈባት ኃላፊነት ለክስ እና ትግሉ መነሻ ለማስቀመጥ ያሳያል።

ከመፃህፍት አለም

02 May, 02:46


Hy

ከመፃህፍት አለም

05 Feb, 09:14


የውበት ወጥመድ Married for her Beauty

ደራሲ - Berta Clay

ተርጓሚ - ዮሀንስ ገብረፃዲቅ

ዘውግ - ልብወለድ

የህትመት ዘመን - 1977

የገፅ ብዛት - 311

ከመፃህፍት አለም

03 Feb, 06:32


ደራሲው - በዓሉ ግርማ

ከመፃህፍት አለም

02 Feb, 12:09


የሚፈልጉትን የሀገራችን ልብወለድ መፅሀፍቶች አነስ አነስ ባሉ size በ PDF ለሞባይል ስልክ የተዘጋጁ 📔📔 ከናንተ የሚጠበቀው ደውለው ወይም በ ቴሌግራም ማዘዝ ብቻ ነው። ደግሞ በነፃ ነው (ማንበብ ሙሉ ሰው ያረጋል)

1. ከፃእረ ሞት ጋር ትንቅንቅ(ሲድኒ ሼልደን)
2. ይስማከ ወርቁ(ክቡር ዲንጋይ)
3. ይስማከ .... (ዴርቶጋዳ)
4. ይስማከ .... (ራማቶሀራ)
5. ይስማከ .... (ዣንቶዛራ)
6. ይስማከ .... (ሜሎስ)
7. ሮሜዎና ዡልየት (ከበደ ሚካኤል)
8. ወንጀል እና ቅጣት (ፊዮደር ዶቶቭስኪ)
9. ብርቅርታ (አብይ ደምሴ)
10. የልምዣት (ሀዲስ አለማየሁ)
11. ትዝታ (ሀዲስ አለማየሁ)
12. 5-6-7 (በስብሀት ገ/እግዛብሄር)
13. ሰባተኛው መልአክ ( በስብሀት ...)
14. ኦሮማይ (በአሉ ግርማ)
15. ሌሎች አለማት
16. ታላላቅ ሰዎች
17. ደራሲው (በአሉ ግርማ)
18. የኢትዮጲያ ታሪክ
19. የኦጋዴን ድመቶች
20. የስንብት ቀለም (አዳም ረታ)
21. አጥቢያ
22. ጎረቤት ፈልጌ ነበር
23. ብርሀን ህሊና (ኦሾ)
24. የህሊና ደውል (በአሉ ግርማ)
25. የተቆለፈበት ቁልፍ
26. ታላቁ ሀይል
27. የሰርቆ አደሮች ስብሰባ
28. ሦስቱ ማጣርያዎች
29. መርበብት
30. ዙቤይዳ
31. የፍቅር ኬሚስትሪ
32. ገመና
33. መግባትና መውጣት (በውቀቱ ስዩም)
34. the prophet
35. Poverty of philosophy
36. Meditation (osho)
37. The god consipercy
38. the great philosophers
39. A new Earth
40. Emotional intelligence
41. How to get the Truth
42. Leader ship skill
43. War and peace
44. The monk who sold his Ferrari
45. The alchemist
46. የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች
47. የሳቅ ምንጭ በአለም ዙሪያ
48. የሁለት ሀውልቶች ወግ (ዲ/ን ዳንኤል)
49. በቀለኛው ሰላይ
50. ዮራቶራድ
51. የእሳት ዳር ወጎች (በውቀቱ ስዩም)
52. እመጒ (ዓለማየሁ ዋሴ)
53. ተልሚድ
54. የቡርቃ ዝምታ
55. ውስጠት (ሰይፉ መታፈሪያ)
56. የሸገር ወጎች
57. ጠበሳ
58. ሀኪም በሌለበት
59. ፍትህን በራሴ
60. ሼህ ሁሴን ጅብሪል
61. ሁቱ ቱትሲ
62. እንጉርጉሮ
63. መሰዋትነትና ፅናት
64. የሞሳድ ተልዕኮ
65. የአለም መስታወት
66. ምርኮኛ
67. ባድመ እንደ ምክንያት!
68. ከሞናሊዛ ጀርባ
69. ኢትዮጲያዊ ጃንደረባ
70. የእስራት ዘመን በአበሻ አገር
71. ኑ ሀገሬን እናዋልዳት
72. ራስን መለወጥ
73. የሰው ልጅ የጥበበኛነት መንገድ
74. የገንዘብ ነፃነት
75. መድሎት
76. ኢቫንጋዲ
77. የውበት ወጥመድ
78. ኢትዮጲያዊው ጃንደረባ
79. ፓፒዮ
80. ታላቁ የወያኔ ሴራ ሲጋለጥ
81. ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር( የግጥም መድብል)

📔📔ደውለው ይዘዙን 📔📔
{0916817004} or text ያርጉልን
Be safe pls stay home.

ከመፃህፍት አለም

27 Nov, 04:29


Channel photo updated

ከመፃህፍት አለም

27 Nov, 04:05


አስተማሪ ሐሳብ!!
እናቴ ጎረቤታችንን ጨው እንዲያውሷት ስትጠይቅ ሰማኋት፡፡ እኔም በመገረም
"እናቴ በቤታችን እኮ በቂ ጨው አለ፤ ታድያ ለምን ጠየቅሻቸው"
አልኳት፡፡ እናቴም እንዲህ አለችኝ
"እነሱ ሁሌም የተለያዩ ነገሮችን ከኛ ይጠይቁናል፤ እንደምታውቀውም ድሀ ናቸው፡፡ ስለዚህ
እኔም እነሱን ብዙ የማይጎዳ ነገር ለመጠየቅ አስቤ የመጣልኝ ነገር ጨው ነው፡፡
ይህን ያደረኩት እነሱ ላይ ጫና ለመፍጠር ሳይሆን፤ እኛም እንደምንፈልጋቸው
እንዲሰማቸው ብዬ ነው፡፡ በዚህም የፈለጉትን ነገር እኛን ያለ ሀፍረት በቀላሉ መጠየቅ
እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ብዬ በማሰብ ነው፡፡"አለችኝ

ከመፃህፍት አለም

01 Oct, 10:18


የሚፈልጉትን የሀገራችን ልብወለድ መፅሀፍቶች አነስ አነስ ባሉ size በ PDF ለሞባይል ስልክ የተዘጋጁ 📔📔 10 ብር ብቻ።

1. ከፃእረ ሞት ጋር ትንቅንቅ(ሲድኒ ሼልደን)
2. ይስማከ ወርቁ(ክቡር ዲንጋይ)
3. ይስማከ .... (ዴርቶጋዳ)
4. ይስማከ .... (ራማቶሀራ)
5. ይስማከ .... (ዣንቶዛራ)
6. ይስማከ .... (ሜሎስ)
7. ሮሜዎና ዡልየት (ከበደ ሚካኤል)
8. ወንጀል እና ቅጣት (ፊዮደር ዶቶቭስኪ)
9. ብርቅርታ (አብይ ደምሴ)
10. የልምዣት (ሀዲስ አለማየሁ)
11. ትዝታ (ሀዲስ አለማየሁ)
12. 5-6-7 (በስብሀት ገ/እግዛብሄር)
13. ሰባተኛው መልአክ ( በስብሀት ...)
14. ኦሮማይ (በአሉ ግርማ)
15. ሌሎች አለማት
16. ታላላቅ ሰዎች
17. ደራሲው (በአሉ ግርማ)
18. የኢትዮጲያ ታሪክ
19. የኦጋዴን ድመቶች
20. የስንብት ቀለም (አዳም ረታ)
21. አጥቢያ
22. ጎረቤት ፈልጌ ነበር
23. ብርሀን ህሊና (ኦሾ)
24. የህሊና ደውል (በአሉ ግርማ)
25. የተቆለፈበት ቁልፍ
26. ታላቁ ሀይል
27. የሰርቆ አደሮች ስብሰባ
28. ሦስቱ ማጣርያዎች
29. መርበብት
30. ዙቤይዳ
31. የፍቅር ኬሚስትሪ
32. ገመና
33. መግባትና መውጣት (በውቀቱ ስዩም)
34. the prophet
35. Poverty of philosophy
36. Meditation (osho)
37. The god consipercy
38. the great philosophers
39. A new Earth
40. Emotional intelligence
41. How to get the Truth
42. Leader ship skill
43. War and peace
44. The monk who sold his Ferrari
45. The alchemist
46. የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች
47. የሳቅ ምንጭ በአለም ዙሪያ
48. የሁለት ሀውልቶች ወግ (ዲ/ን ዳንኤል)
49. በቀለኛው ሰላይ
50. ዮራቶራድ
51. የእሳት ዳር ወጎች (በውቀቱ ስዩም)
52. እመጒ (ዓለማየሁ ዋሴ)
53. ተልሚድ
54. የቡርቃ ዝምታ
55. ውስጠት (ሰይፉ መታፈሪያ)
56. የሸገር ወጎች
57. ጠበሳ
58. ሀኪም በሌለበት
59. ፍትህን በራሴ
60. ሼህ ሁሴን ጅብሪል
61. ሁቱ ቱትሲ
62. እንጉርጉሮ
63. መሰዋትነትና ፅናት
64. የሞሳድ ተልዕኮ
65. የአለም መስታወት
66. ምርኮኛ
67. ባድመ እንደ ምክንያት!
68. ከሞናሊዛ ጀርባ
69. ኢትዮጲያዊ ጃንደረባ
70. የእስራት ዘመን በአበሻ አገር
71. ኑ ሀገሬን እናዋልዳት
72. ራስን መለወጥ
73. የሰው ልጅ የጥበበኛነት መንገድ
74. የገንዘብ ነፃነት
75. መድሎት

📔📔ደውለው ይዘዙን 📔📔
{0916817004} or text ያርጉልን
Be safe pls stay home.

ከመፃህፍት አለም

27 Sep, 14:09


የኔ የምትለው ቅርብ ሰው ሲያስቸግርህ ርቀትህን ጠብቅ። በተወሰነ ክልል ርቀትን መጠበቅ
ጥላቻ ሳይሆን ልብህ ክፉኛ በስቃይ አለንጋ እንዳይገረፍ እፎይታ ለማግኘት የሚያስችል
ዕድል መፍጠር ማለት ነው።


ሰውዬው የቱንም ያህል ብርሃን የሚለግስህ ቢሆን እንኳ ርቀትህን ጠብቅ። የእሳት እራት
ብርሃን የሚለግሳትን አምፖል አለቀጥ የምትቀርብ ከሆነ ያነዳታልና። በዙሪያው ያለውን
ውኃ ቸር ሆኖ በመስጠት ጥምህን በሚቆርጥልህ ባሕር ውስጥ ጠልቀህ ከገባህ
ያሰጥመሃል።

«መራቅ» ሁሌም ኪሳራ ሳይሆን ነፍስን በማቃናት ለፍቅር ፣ ለወዳጅነትና ለጓደኝነት የሚሆን
ግልጽ መስመር በማስመር አስተማማኝ ስፍራ ላይ የምትቆምበት ሁኔታ ነው። የልብህን
ሚዛን እና የነፍስህን ሰላም ለመመለስ በሁሉም ግንኙነቶችህ አስተማማኝ ርቀት ወሳኝ
ነው። የኮቪድ -19ኝ ስርጭትን ለመግታት እንኳ አካላዊ ርቀትህን ጠብቀሃል

ከመፃህፍት አለም

23 Sep, 06:06


..

ከመፃህፍት አለም

23 Sep, 06:05


https://t.me/joinchat/AAAAAFShSZulixUKyIzTDQ

ከመፃህፍት አለም

23 Sep, 06:03


🔵ነጸብራቅ /Reflection/

በሚስጥረ አደራው)

🔷ኑሮን በአጭሩ ከሚገልጹ ቃላቶች ውስጥ “ነጸብራቅ” አንደኛው ነው ልበል? አንዴንዴ ዞር ብለን መንገዳችንን ስናጤነው፤ ተመሳሳይ ኩነቶችን ( Similar Patterns) ማየታችን የማይቀር ነው፤ ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸውን ሰዎች ማግኘት ወይም መጎዳኘት፤ ተመሳሳይ ስህተቶችን መስራት፤ ተመሳሳይ መልካም ዕድሎችን መሰብሰብ፤ ብቻ ተቀራራቢ የሆኑ ነገሮችን በምናሳልፈው ህይወት ውስጥ ማየታችን የተለመደ ነው።

🔶ይህ መመሳሰል ዝም ተብሎ እንደአጋጣሚ የሚታለፍ ነገር አይደለም። ምክንያቱም አጋጣሚ አይደለምና። ለመቀበል ቢከብድም፤ እውነታው ግን በኑሮ ሂደት ውስጥ የሚገጥሙን ነገሮች ሊያሳዩን የሚሞክሩት የራሳችንን የእምነትና የአስተሳሰብ ነጸብራቅ ነው። ይህን “ በዙሪያችን የምናየው የራሳችንን ነጸብራቅ ነው” የሚለውን አስተሳሰብ፤ መንፈሳዊ መጽሃፍቶች፤ የስነ ልቦና ትምህርቶች እንዲሁም ባህላዊ አባባሎች ሲያሰምሩበት የኖሩት ነገር ነው።

🔷ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ስነሳ በመጀመሪያ የራሴን ኑሮ ለመቃኘት ሞከርኩኝ፤ እውነትም ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸውን ሰዎች ስስብ፤ ተመሳሳይ ስህተቶችን ስስራ፤ ተመሳሳይ መንገዶችን ስመርጥ እንደነበር ለመረዳት ጊዜ አልፈጀብኝም። ለምን? ምክንያቱም ሳናውቀው በሰዎች ውስጥ የምንፈልገው (የምንስበው) የራሳችንን ባህሪ ስለሆነ፤ ተቃራኒ ቢመስልም እንኳን።

🟣ነገር መቼም በምሳሌ ይበልጥ ወደ ህሊና ይዘልቃልና ፤ከአንድ የግጥም መድብል (Coleman Barks- Chinese Art and Greek Art) ላይ ያገኘሁትን በግጥም መልክ የተጻፈ የሱፊ ታሪክ ላካፍላችሁ።

🔷በድሮ ጊዜ የቻይና እና የግሪክ ጠቢባን ማንኛቸው የተሻለ የስዕል ጥበብ እንዳላቸው ለማስመስከር ክርክር ይጀምራሉ። ክርክሩ ሲጧጧፍ ከቃላት ጦርነት በበለጠ ስዕሎቻቸውን በተግባር እንዲያሳዩ ተወሰነ። ቻይናዎቹ ብዙ ቀለማት እንዲሰጧቸው ሲጠይቁ ግሪኮቹ ግን ምንም ቀለም እንደማይፈልጉ አሳወቁ። በመጋረጃ በተከፈለ ክፍል ውስጥ፤ ለየብቻ ተቀምጠው የሚወዳደሩበትን የስዕል ስራ እንዲጀምሩ ተደረገ። ቻይናዎቹ ከመቶ በላይ ቀለማትን ተጠቅመው ስዕላቸውን መሳል ተያያዙ። ግሪኮቹ ግን ስዕል በመሳል ፋንታ ዝም ብለው ግድግዳውን ማጽዳት ጀመሩ። በየቀኑ ቻይናዎቹ መዓት ቀለማትን እየተጠቀሙ ስዕላቸውን ሲስሉ፤ ግሪኮቹ ግን ዝም ብለው ግድግዳቸው ሰማይ እስኪመስል ድረስ ማጽዳታቸውን ቀጠሉ።
♦️ በመጨረሻ ቻይናዎቹ ስራቸውን መጨረሳቸውን በደስታ አበሰሩ። የሚዳኛቸው ንጉስም በቅድሚያ የቻይናዎቹን ስራ ገብቶ ሲመለከት በቀለማቱ ድምቀት ተደነቀ፤ ቀጥሎ የግሪኮቹን ለመመልከት መጋረጃውን ሲያስገልጥ፤ ቻይናዎቹ የሰሩት የስዕል ነጸብራቅ ግሪኮቹ ባጸዱት ንጹህ ግድግዳ ላይ ተንጸባርቆ ታየ፣

🔷 እንደውም ከተፈጥሮ ብርሃን ጋር ተዋህዶ ከቻይናዎቹ በላይ ልብን የሚሰርቅ ጥበብ ሆነ። ገጣሚው ግጥሙን ሲያጠቃልል የግሪኮቹን ስራ “የሱፊ ጥበብ” ሲል ይገልጸዋል፤ በመጽሃፍትና በፍልስፍና ሳይሆን፤ ልባቸውን (ፍቅራቸውን- Make their loving clearer and clearer ነው የሚለው) እንደመስታወት በማጽዳት እያንዳንዷን ቅጽበት ያያሉ፤ መልሰውም ያንጸባርቃሉ፤ እራሳቸውን በሌላ ውስጥ ይመለከታሉ፤ ሌሎችም እራሳቸውን በእነሱ ውስጥ እንዲመለከቱ ያደርጋሉ ሲል ያሞግሳቸዋል።

🔶የእኛ ኑሮ ከቻይናዎቹ እና ከግሪኮቹ የስዕል ፉክክር የተለየ አይደለም። እኔን እንደገባኝ፤ በእኛ ኑሮ ውስጥ በመጋረጃ የተከፈሉት አስተሳሰባችን እና በተግባር የሚገጥሙን ነገሮች ናቸው። በአንደኛው ክፍል አስተሳሰባችን ሲገኝ፤ በሌላው ክፍል ኑሮዋችን ይገኛል። አስተሳሰባችን የሳለውን ስዕል፤ ኑሮዋችን ያንጸባርቀዋል። የቻይናዎቹ ስራ አስተሳሰባችን ሲሆን፤ የግሪኮቹ ነጸብራቅ ደግሞ በእውን የሚገጥሙን ነገሮች ናቸው። ማጽዳቱ የሚያመላክተው ደግሞ፤ ንቃትን ወይም Awareness ይመስለኛል።
🔹 የበለጠ ግድግዳው ሲጸዳ፤ ስለራሳችን ያለን እውቀት ይጨምራል፤ ሁሉም ነገር የማንነታችን ነጸብራቅ መሆኑ በተሻለ መልኩ ይገባናል። ዓለምን በሌላ መነጽር እንድናይ የሚያስችለን አንዱ ጥብብ ፤ የሚገጥሙንን ነገሮችን እንደ እራሳችን ነጸብራቅ መመልከቱ ነው (Viewing our experiences as the reflection of our thoughts and deepest emotions) ።

🔷ሌላው ቢቀር ሌሎች ሰዎች ላይ የምንጠላው ባህሪ በራሱ፤ እኛ ውስጥ ያለውን ድብቅ ነገር እያሳየን ነው። ለሰዎች እና ለአጋጣሚዎች የምንሰጠው ምላሽ፤ ውስጣችንን እንደ ግሪኮቹ ግድግዳ አንጸባርቆ ያሳያል።

♦️ የምንናደድባቸው፤ የምንደሰትባቸው፤ የምንጨቆንባቸው፤ የምንመሰገንባቸው ነገሮች በሙሉ የሚያንጸባርቁት ውስጣዊ ባህሪ አለ። እርግጥ ነው ነጸብራቁን በቀላሉ ማየት ከባድ ነው ምክንያቱም የተደበቁ ባህሪያቶቻችንን በቀላሉ ማየት ስለሚከብደን።ለዛም ነው ብዙ ስራና እውቀትን ሳይሆን ብዙ ጽዳትን የሚጠይቀው። እንዲህ የሚሰማኝ ለምንድን ነው ብለን፤ በስሜቶች ውስጥ ሁሉ ባህሪያችንን እና አስተሳሰባችን እንድንጠይቅ ያስገድደናል። ያኔ የሆነው ሁሉ ለምን እንደሆነ በትንሹም ቢሆን መረዳት ይቻለናል።

ከመፃህፍት አለም

29 Jun, 06:23


‼️ረጋ ብላችሁ አንብቡት‼️

በአንድ መንደር ውስጥ ስዕል እየሳለ በውድ ዋጋ በመሸጥ የሚተዳደር ሽማግሌ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን አንድ የመንደሩ ነዋሪ የሆነ የኔ ቢጤ መጣና
"አንተ ሰዓሊ ነህ። ስዕል እየሳልክ ብዙ ስለምታገኝ ሀብተም ሆነሀል፤
ግን ለድሆች አትሰጥም፤ ባለ ልኳንዳ ቤቱ እንኳ ሁሌ ስጋ
ለድሀች በነጻ ያድላል።" አለው……
ሽማግሌው ሰዓሊም ፈገግ
ከማለት ውጪ ምንም መልስ አልሰጠውም ……ድሀው ሰውዬም
በመንደሩ እየዞረ ሽማግሌው ሀብታም እንደሆነና ግን ስስታም
እንደሆነ አናፈሰ። የመንደሩ ሰዎች አዛውንቱን ጠሉት……
ከጊዚያት በኃላ አዛውንቱ ታመመ። አንድ እንኳ የሚያስታምመው
ሰው አጥቶ ሞተ ……ከዚያን ቀን በኃላ ባለ ልኳንዳው ስጋ ማደሉን አቆመ።
ለምን እንዳቆመ የመንደሩ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁት……
"እስከ ዛሬ የማድላችሁ እኮ ሰዓሊው ስለሚከፍለኝ ነው" ብሎ መለሰላቸው።
👌👇👇👇👇👇👇👇👇
አንዳንዴ ነገሮችን ሳናረጋግጥ ለውሳኔ አንቸኩል። የሰውን ማንነት ሳንረዳ ለፍርድ አንቸኩል።

ከመፃህፍት አለም

29 Jun, 06:22


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራቹ !!!
"ላለመርዳት ኪስህን ሰበብ አታድርግ። ባዶ ኪስ ነህ ማለት የምትሰጠው ምንም ነገር የለህም ማለት አይደለም፤ ቢያንስ የምትሰጠው ባዶ ኪስ የሆነ ሱሪ አለክ ማለት እንጂ።

ባዶ ኪስ የሆነ ሱሪ መስጠት ቢያቅትህ፥ በባዶ ኪስህ እጁን እንዲያስገባ ፍቀድለት። ቢያንስ አንድ እጁን ከብርድ ትከላከላለህ።"

#እያዩ_ፈንገስ -ተዉኔት
#በረከት_በላይነህ -ደራሲ
#ግሩም_ዘነበ -ተዋናይ