🚶🏾♂➡️🚶🏾♂➡️
አብዛኛውን ጊዜ ወጣቱ ሃገሩን በመጥላት ተጠምዶ ያጋጥመኛል። ለምን የሚል ጥያቄ ስታነሳ ደግሞ የሚሰጥህ ምላሽ ከጤነኛ እና ከደህና ሰው የማይጠበቅ ሆኖ ይገኛል።
፦"ሀገሬን በጣም ነው ምጠላት!"
፦"ለምን"
፦" አንድ ቀን ደልቶኝ ያልኖርከባት ጦርነት የምሰማባት ለቅሶ የበዛባት ረሃብ የሰፈነባት ሰላም የማያቃትን ሃገር እንዴት ልወድ እችላለሁ?"
የአብዛኛው ወጣት ወጣትም ባይሆን የአብዛኛው ሃገር ጠል ምክኒያት ይህ ነው!!
እውነት ታዲያ ሃገር ነች ጦርነቱን ያወጀችውን? እውነት ኢትዮጵያ ትመስላቹሃለች የረሃባችሁ እና የረሃባችን ምንጭ?, እውነት ጦቢያ ነች ቤተሰብህን የቀጠፈችውን? እውነት እምዬ ነች እናት እና እህትህን ያስለቀሰችውን?? በአጠቃላይ ስመልሰው ኢትዮጵያ ምንም አላደረገችም እሷም አይደለችም 😑🚶🏾♂➡️
● መጥላት ከፈለጋችሁ እና ካለባችሁ
👉🏽 ህዝብ እየተራበ ሃገር የምታመርተውን ስንዴ ሽጦ ጦር መሳሪያ ሚገዛ አዋቂ ¡¡ መንግስት አለ።
መንግስት ማለት ሃገር አስተዳዳሪ እንጂ ሃገር አደለም ❕
👉🏽 ሲቀጥል ዜጎች አመታት ጥረው እና ለፍተው ካፈሩት ንብረት መንገድ የሚበልጥበት ምጡቅ ¡¡ መንግስት አለ።
ተጨምሮ ያየነው የመንገድ ላይ ተክል እና አምፖሎች ብቻ ነው።
👉🏽 ምንም በማያገባው እየገባ በየ ክልሉ መሃል ፀብ የሚፈጥር ትኩሽት አሮጊት የሆነ መንግስት አለን።
መንግስት ስራው ሃገርን ሰላም ማድረግ ቢሆንም !
ይሄንን የሚያደርገው መንግስት ሆኖ ሳለ ሃገር ምን ቦጣት በልጆቿ ትጠላ ??
እንዴት አረፈዳችሁ
መልካም ውሎ
መልካም ዕለተ ረብዕ