በፌዴራል መንግስት እና በህወሃት አመራሮች መካከል የሚደረገዉን የሰላም ዉይይት የአላማጣ የኮረም እና ጨርጨር ከተማ ነዋሪዎች አደነቁ።
በፌዴራል መንግስት እና በህወሃት አመራሮች መካከል እየተደረገ ያለዉን የሰላም ዉይይት ተከትሎ በሰፈነው አንፃራዊ ሰላም በተለያዩ ዕለታዊ ፍጆታዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ እና መረጋጋት በመታየቱ መደሰታቸውን ነዉ የአላማጣ የኮረም እና ጨርጨር ከተማ ነዋሪዎች የተናገሩት።
ነዋሪዎቹ እጅግ ባጠረ ጊዜ የመብራት እና የስልክ አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውም ለዕለት ተዕለት ኑሯቸው እገዛ እንዳደረገላቸዉ ገልፀዋል።
በግጭት ወቅት በተከሰተው የሠላም እጦት ምክንያት ሰላም እርቋቸዉ መረጋጋት ተስኗቸዉ ህይወታቸዉን አንድ ቦታ ላይ ሆነዉ መምራት ያልቻሉ መሆናቸዉን ያወሱት ነዋሪዎቹ ከጦርነት ኪሳራ እንጅ ትርፍ አይገኝም በማለት ትዝባታቸዉን ለመከላከያ ሚዲያ ገልፀዋል።
አሁን ላይ መንግስት በእነኝህ አካባቢዎች እና የጦርነት ቀጠና በነበሩ አካባቢዎች አስፈላጊ ድጋፎችን ለህብረተሰቡ ከማደረስ ጀምሮ እንደቴሌ መብራት እና ዉሃ የመሰሰሉ መሰረታዊ እና ለሰዉ ልጅ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት እየገነባ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ስለሆነም ነዋሪዎቹ በፌዴራል መንግስት እና በህወሃት አመራሮች መካከል የሚደረገዉን የሰላም ዉይይት አድንቀዉ በህብረት የኢትዮጵን የዕደገት ግስጋሴ ለማፋጠን ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
የኃላሸት ሶረሳ
ፎቶግራፍ በየኃላሸት ሶርሳ