MEHON MEDIA @mehonmedia Channel on Telegram

MEHON MEDIA

@mehonmedia


MEHON MEDIA (English)

Welcome to MEHON MEDIA, the ultimate destination for all your digital content needs! Are you looking for captivating videos, stunning photography, or engaging social media content? Look no further than MEHON MEDIA. Our team of talented creatives is dedicated to providing you with top-notch content that will elevate your brand and leave a lasting impression on your audience. Whether you're a business looking to enhance your online presence or an individual seeking quality content for personal use, MEHON MEDIA has you covered. Join our channel @mehonmedia today to stay updated on our latest projects, behind-the-scenes footage, and exclusive offers. Don't miss out on the opportunity to take your digital content to the next level with MEHON MEDIA!

MEHON MEDIA

24 Oct, 13:48


የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ድረ-ገፅ: placement.ethernet.edu.et

ቴሌግራם: MoE Student Bot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@mehonmedia

MEHON MEDIA

01 Oct, 09:09


እንኳን ደስ አላችሁ
****
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛው፣ በተከታታይና በክረምት መርሀ-ግብር ያስተማራቸውን 3271 የ2016 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን መስከረም 25/2017 ዓ.ም ያስመርቃል።
በመሆኑም ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን እና የአካባቢያችን ማህበረሰብ እንዲሁም ለተመራቂ ተማሪዎቻችንና ለተማሪ ቤተሰቦቻቸው ከወዲሁ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
እንኳን ደስ ያላችሁ !
***
ለልህቀት እንተጋለን
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳሬክቶሬት
መስከረም 21/2016 ዓ.ም

@mehonmedia

MEHON MEDIA

21 Aug, 18:37


Live stream finished (44 minutes)

MEHON MEDIA

21 Aug, 17:53


Live stream started

MEHON MEDIA

21 Aug, 18:00


Live stream scheduled for

MEHON MEDIA

21 Aug, 14:26


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልጇን በግፍ ለተነጠቀቸው ሕጻን ሄቨን እናት የመኖሪያ ቤት አበረከተ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልጇን በግፍ ለተነጠቀቸው ሕጻን ሄቨን እናት የመንግስት መኖሪያ ቤት አበርክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ የሄቨንን እናት በማግኘት አጽናንተዋል::

ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትሕ ሳታገኝ ለቆየችው ሲስተር አበቅየለሽ የፍትሕ ሒደቱን ለመከታተል፣ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላትና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አስተዳደሩ አንድ የመንግስት መኖሪያ ቤት አበርክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሙያዋ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እንድትሰራ መመቻቸቱን ነው ከንቲባ አዳነች የገለጹት፡፡

የህጻን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትሕ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ከንቲባዋ አስገንዝበዋል፡፡

መሰል ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@mehonmedia

MEHON MEDIA

17 Aug, 19:14


#Ethiopia #ፍትሕ

በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ የተገደለችው የ7 ዓመቷ ህጻን ሔቨን ታሪክ የበርካቶችን ልብ የሰበረ ጉዳይ ሆኗል።

ይህ ድርጊት የተፈጸመው ከዛሬ #አንድ_ዓመት በፊት በባህርዳር ከተማ እንደሆነ ዛሬም ድረስ መሪር ሀዘን ውስጥ የምትገኘው እናት " ኢዮሃ " በተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቀርባ ተናግራለች።

ሕጻን ሔቨን የተደፈረችው ተከራይተው ይኖሩበት በነበረ ግቢ አከራይ ነው።

የተደፈረችበት መንገድም ወደ ሽንት ቤት በምትሔድበት ጊዜ ጠብቆ ወደ ቤት በማስገባት ነው። እጅግ በጣም አሰቃቂም ነበር።

ህጻን ሔቨንን የደፈረው ወንጀለኛ በምትደፈርበት ወቅት አንገቷን አንቆ ፤ አፏን አፍኖ ድርጊቱን የፈጸመ ሲሆን ወድቃ የሞተች ለማስመሰል ደሟን አንጠባጥቦ በር ላይ ጥሏት መሄዱን እናት ታስረዳለች።

እናት ልጇን ብቻ አይደለም ያጣችው ፤ ፍትህ ስትጠይቅ ይህንን ግፍ ሰምተው እንዳልሰማ የሆኑ ጎረቤት እና ቤተሰቦች ፤ በጥቅም ወንጀለኛውን ነጻ ለማስወጣት የሰሩ ፤ እናትን ጭምር ተባብረው ለማጥፋት ረጅም ርቀት የተጓዙ ፤ ማስፈራሪያ ደርሷቸው ቃላቸውን ከመስጠት የጠፉ ሁሉ ለእናት ፈተና ሆነውባታል።

ይህም ሆኖ ጥቂት የሚባሉ (የሴቶች እና ህጻናት ወንጀል መሪማሪ ፖሊሷ፤ የሴቶችና ህጻናት ቢሮ) አንዳንዶቹ ማስፈራሪያ ጭምር እየደረሳቸው አግዘዋት ከብዙ መከራ በኋላ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ይፈረድበታል።

እናት ግን ዛሬም ትኩስ ሀዘን ላይ ነች።

ሥራ እየሰራች መኖር አልቻለችም።

ነገ ከእስር ሲለቀቅ እሷንም ጭምር ለመግደል እንደሚፈልግ ፤ ለዚህም ደግሞ ዳግም ሥራ ከጀመረችበት ቦታ ቤተሰቦቹ ተከታትለዋት ጥላ መውጣቷን እናት አስረድታለች።

ዛሬም እውነተኛ ፍትሕ አጥታ ትንከራተታለች።

ግፍ ላይ ግፍ !

በመሰረቱ በዚህች ምስኪን አንድ ፍሬ ፤ ክፉ ደግ በማታውቅ ህጻን ላይ አሰቃቂ የመድፈር እና ኃሏም ህይወቷን ያሳጣ የወንጀል ድርጊት የፈጸመ ሰው እንዴት 25 ዓመት ይፈረድበታል ? እውነት ይህ ማስተማሪያ ነው ? ወይስ ሌላ ነው ዓላማው ?

የሔቨን ታሪክ የብዙ ህጻናት ታሪክ ጭምር ነው።

ከዚህ በፊት ሴቶች፣ ህጻናት ጭምር ሲደፈሩ የሚተላለፉ የፍርድ ውሳኔዎች ህዝቡን እያስቆጣ መሆኑን አሳውቀን ነበር።

ዛሬም ፍትሕ ተጓድሏል። ፍትሕ ይስፈን።

ዛሬ አጋጣሚ ይህ ጉዳይ አደባባይ ወጣ እንጂ ስንቷ እናት ቤቷ ዘግያ እያለቀሰች ይሆን ? ስንት ሴቶች በግፍ ሰለባ ሆነው እያነቡ ይሆን ?

@mehonmedia

MEHON MEDIA

17 Aug, 19:10


የ7 አመት ህፃን ደፍሮ ከዛም በጭካኔ የገደለው ወንጀለኛ ይግባኝ የማለት መብት ለምን ተሰጠው በሚል እየሞገተ መሆኑን የአማራ ክልል የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ

በትናንትናው እለት በእዮሃ ሚድያ የተላለፈ የአንድ ህፃን መደፈር እና በጭካኔ መገደል መረጃ ከወጣ በኋላ በርካቶችን ማሳዘኑ እና ማነጋገሩን ቀጥሏል።

ድርጊቱ ከተፈፀመበት ከ2014 መጨረሻ ወራት ጀምሮ ጉዳዩን ሲከታተሉ ከነበሩ የመንግስት አካላት አንዱ የሆነውን የአማራ ክልል የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊን መሠረት ሚድያ አነጋግሯል።

የቢሮው ሀላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ "የ25 አመት ፍርድ ያገኘ ጉዳይ እንዴት ይግባኝ ተፈቀደበት ብለን ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ጋር በጋራ እየሰራንበት ነው" ብለው ማብራርያ ሰጥተዋል።

"ግለሰቡ 25 አመት ተፈርዶበት እስር ላይ ቢገኝም በህግ ይግባኝ ተፈቅዶበታል፣ ፍርድ ቤት ያስቀርባል ብሎታል። አሁን እኛ ይግባኝ መባሉ እንዴት ተቻለ ብለን እየሞገትን ነው" ብለው መረጃ ሰጥተዋል።

ሀላፊዋ ግለሰቡ የፍርድ ውሳኔ እንዲያገኝ ክልሉ ካለበት አሁናዊ ሁኔታ አንፃር ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ እንደተፈረደበት ገልፀው "ይሄ እንዴት ይግባኝ ያስቀርባል?" ብለው ለራሳቸው ጥያቄ እንደሆነባቸውም ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በህፃን ሄቨን ላይ በተፈፀመው ወንጀል በተሰጠው ውሳኔ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር እሰራለሁ ብሏል።

ሚኒስቴሩ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በህፃኗ ላይ በተፈፀመው ዘግናኝ የሆነ ኢ ሰብአዊ ወንጀል የተሰጠው ዉሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚኬድበት አግባብ ባለመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰራ አስታውቋል።

@mehonmedia

MEHON MEDIA

10 Aug, 09:30


#Ethiopia

በማራቶን ውድድር ላይ " ተጠባባቂ ነህ " ተብሎ የተያዘውና ለውድድሩ የተመረጠ ሌላ አትሌት መጎዳቱን ተከትሎ ሀገሩን ወክሎ የተሳተፈው ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ወርቅ ማምጣት ብቻ ሳይሆን በሚደንቅ ብቃት የኦሎምፒክ ሪከርድም ጭምር ነው የሰበረው።

ጀግናው አትሌት ታምራት ከአትሌት ገዛኸኝ አበራ በኋላ (ከ24 ዓመታት በኃላ) ነው የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ለሀገራችን ያስገኘው።

ሌላው አንጋፋው ኢትዮጵያ ሁል ጊዜ በስራው የምታመሰግነው የ42 ዓመቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 39ኛ ደረጃ ይዞ እጅግ ከባድ የነበረውን የፓሪስ ማራቶን አጠናቋል።

አትሌት ደሬሳ ገለታም 5ተኛ ደረጃ በመውጣት እጅግ በጣም አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤት አስመዝግቧል።

ምንም እንኳን ዛሬ በወንዶች ማራቶን የተገኘው ውጤት አስደሳችንና የሚያኮራ ቢሆንም በፓሪስ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ኢትዮጵያን የሚመጥናት አይደለም።

በጭቅጭቅና ንትርክ በተሞላው በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ ያገኘችው እስካሁን 3 ሜዳሊያ ብቻ ነው። 1 ወርቅ እና 2 ብር ብቻ።

የአትሌቲክሱ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ ያሉ ችግሮች እና ኢትዮጵያን ዝቅ ያደረጉ ነገሮች ሁሉ ተፈትሸው መለወጥ እንዳለባቸው የፓሪስ ኦሎምፒክ በግልጽ አመላክቷል።

ከሚዲያ በዘለለ ስለዚህ ሀገር አትሌቲክስ ሁሉም " የሀገር ክብር ያሳስበኛል " የሚል ቁጭ ብሎ ተነጋግሮ በአስቸኳይ ለውጥ ማምጣት አለበት። እንዲህ ከቀጠለ በዓለም ደረጃ የነበረን ክብር የማናጣበት ምክንያት የለም።

@mehonmedia

MEHON MEDIA

10 Aug, 09:29


#Ethiopia

በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የሐዋሳ ቅርንጫፍ በመደበኛው የፓይለት ስልጠና ልምምድ ላይ የነበረ ቀላል የተማሪዎች መለማመጃ አውሮፕላን (Dimond DA40NG) አየር ላይ ሳለ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አርሲ ነጌሌ አካባቢ ለማረፍ መገደዱን የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ ገልጿል።

" ይህንን ተከትሎ በመደበኛ ስልጠናው ላይ የነበሩት አስተማሪውና ተማሪው የመለማመጃ አውሮፕላኑ ሕብረተሰቡ ላይ አደጋ በማያደርስ ሁኔታ ለማሳረፍ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም ለማረፍ በተደረገው ጥረት መሬት ላይ በነበረች አንዲት ታዳጊ ላይ ጉዳት ደርሷል " ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ፥ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ በሚመለከታቸው አካላት በመጣራት ላይ መሆኑን አሳውቋል።

@mehonmedia

MEHON MEDIA

09 Aug, 09:07


#Tigray #TPLF

"ሊካሄድ በታቀደው ጉባኤ አልሳተፍም ! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዜዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ ዛሬ ዓርብ ነሀሴ 3/2016 ዓ.ም ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፣ ለድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ተኽለብርሃን ኣርኣያ በፃፉት ደብዳቤ በጉባኤው እንደማይሳተፉ አረጋግጠዋል።

ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች ውሳኔ በጣሰው ጉባኤና የምዝገባ ሂደት እንደማይሳተፉ በመግለፅ " ህወሓት መዳን የሚችለው አባላቱና አመራሩ በሚያካሂዱት ጤናማ እንቅሰቃሴ ነው " ሲሉ አስታውቀዋል። 

@mehonmedia
@mehonpodcast1

MEHON MEDIA

08 Aug, 14:17


የደመወዝ ማሻሻይ ይፋ ተደርጓል ?

እስካሁን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ / ጭማሪ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በቴሌግራም ፣ በፌስቡክ እየተዘዋወረ ያለው " የፌዴራል መንግሥት ሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ " የሚለው መረጃ ምንም ምንጩ የማይታወቅ ነው።

የተሰራጨው የደመወዝ ማሻሻያ ሰንጠረዥ ፤ የፅሁፍ ስህተቶች ጎልተው የሚታዩበት፣ የአጻጻፉ ግድፈት ያለበት፣ የድምር ጭምር ግልጽ እና ቀላል ስህተት ያለበት ነው።

ሲቀጥል ማን ይፋ እንዳደረገው አይታወቀም።

ማህተም አላፈረበትም ፤ መረጃውን ያወጣው መ/ቤትም አይታወቅውም።

እስካሁን በይፋ ለህዝብ የተሰራጨ የደመወዝ ጭማሪ ዝርዝር መረጃ የለም።

መንግሥት በቅርቡ የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ማሳወቁ ይታወሳል።

@mehonmedia
@mehonpodcast1