DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA @dtu_pr1 Channel on Telegram

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

@dtu_pr1


DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA (English)

Welcome to the official Telegram channel of Debre Tabor University in Ethiopia, where excellence meets opportunity! Our channel, @dtu_pr1, is dedicated to keeping our students, alumni, and the general public informed about news, events, and updates related to our prestigious university. Debre Tabor University is a leading institution of higher learning in Ethiopia, known for its quality education, innovative research, and commitment to community development. Founded with the mission of providing students with a transformative educational experience, DTU offers a wide range of undergraduate and postgraduate programs across various disciplines. Whether you're a current student looking for important announcements, an alumnus wanting to stay connected with your alma mater, or simply interested in learning more about our university, our Telegram channel is the perfect place for you. Stay up to date with the latest campus news, academic achievements, and upcoming events by joining @dtu_pr1 today. Experience the rich academic tradition and vibrant campus life of Debre Tabor University, where you can unlock your full potential and shape a brighter future. Connect with us on Telegram and be a part of our growing community of scholars, researchers, and changemakers. Join us on this exciting journey of learning, discovery, and innovation at Debre Tabor University, Ethiopia!

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

17 Dec, 22:33


የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የጋፋት ህዋ ምህንድስና ልማት ማእከል በአቪየሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ 2016 ባቀረበው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራ 2ኛ ደረጃ አሸናፊ ሆነ።፨፨፨የአቬየሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ "ፈጠራ ለኢኖቬሽን ልህቀት" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ሲቪል አቬየሽን ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ጋር በጋራ አዘጋጅነት ከታህሳስ 1 እስከ ታህሳስ 6 2016 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የአቪየሽን ኤክስፖ ላይ በመስኩ የተለያዩ የፈጠራ ስራቸውን ያቀረቡ በርካታ ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ይገኙበታል። ለአምስት ቀናት በሳይንስ ሙዚየም በተካሄደው በዚህ ታላቅ ኤክስፖ ላይ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የጋፋት ህዋ ምህንድስና ልማት ማእከል የተሰራው ሮኬት ለእይታ የቀረበ ሲሆን በአቪየሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ 2016 የ2ኛ ደረጃን በማግኘት ተሸላሚ ሆኗል። እስከ 20 ሺህ ጫማ ከፍታ መወንጨፍ እንደሚችል በሙከራ የተረጋገጠው ይህ ሮኬት በዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተማሪወች የተሰራ የምርምር ውጤት ነው። በኤክስፖው ላይ በዩኒቨርሲቲው ተማሪወች የተሰሩ የድሮን እና የራዳር የፈጠራ ስራወች የቀረቡ ሲሆን በጎብኝወች እና ተሳታፊወች ከፍተኛ አድናቆት ተችሯቸዋል።የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶር አነጋግረኝ ጋሻው እና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው መንግስቴ በኤክስፖው የማጠናቀቂያ ቀን ላይ በሳይንስ ሙዚየም በመገኘት 2ኛ ደረጃን በማግኘት አሸናፊ የሆነውን የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የጋፋት ህዋ ምህንድስና ልማት ማእከል ቡድን ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና በማቅረብ አበረታተዋቸዋል። በደብረታቦር ዩንቨርስቲ የጋፋት ህዋ ምህንድስና ልማት ማዕከል የተሠራው "አጼ ቴዎድሮስ 2015" ተብሎ የተሰየመው ሮኬት ከሀያ ሺ ጫማ ከፍታ በላይ የተሳካ የማስወንጨፍ ሙከራውን ሚያዚያ 28/2015 በፋርጣ ወረዳ መደብ ጉብዳ ቀበሌ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ፣ዲኖች ፣ዳይሬክተሮች እና ተማሪዎች በተገኙበት ማድረጉ ይታወሳል።👇https://ift.tt/V8Rko6Xየደብረ ታቦር ዩኒቨርሲተ የጋፋት የህዋ ምህንድስና ልማት ማእከል የሮኬት ሙከራ ሙሉ ታሪክ፣ ህልም፣ ውጥን፣ ጥረት፣ ስኬት፣ አላማ እና ራእይን እዚህ ላይ ይመልከቱ።👇https://youtu.be/zG3oPu4HCL0?si=kFGT6qP_W0NawY7F
December 18, 2023 at 01:21AM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

17 Dec, 22:33


December 18, 2023 at 12:52AM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

27 Nov, 17:33


November 27, 2023 at 08:13PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

23 Nov, 11:33


November 23, 2023 at 02:29PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

04 Sep, 11:33


To all DTU staff,As #Debre_Tabor_University is both a founding member institution (in 2020) and an active member (for 2023) of the #Africa_UniNet, we are glad to inform you that the #4th_Africa_UniNet_call for research cooperation projects is open from 1 September – 30 November 2023.Africa-UniNet funds international research cooperation projects with at least one Austrian and at least one African university / university of applied sciences / research institution. Please note that applications should be submitted via the Africa-UniNet representative and therefore DTU staff can send proposals to [email protected]. We kindly ask you to distribute this information among your departments, units, and colleges at DTU to make them aware about it.Detailed information on the 4th Africa-UniNet call including all necessary application documents, the selection process and the reporting guidelines can be found on: https://ift.tt/UdOtTGR
September 04, 2023 at 02:06PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

15 Aug, 08:33


August 15, 2023 at 11:08AM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

31 Jul, 18:34


በሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና አሰጣጥ ሂደት ዙሪያ ገለጻ (Orientation) ተደረገላቸው። ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 24 /2015 ዓ.ም በሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና አሰጣጥ ሂደት እና ፈተናውን በስኬት ለማጠናቀቅ የሚያግዙ ሁኔታዎች ዙሪያ የትምህርት ሚኒስቴርና የፈተናወች ድርጅት የፈተና አስፈፃሚዎች፣ የዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሃላፊ እና የደብረ ታቦር ከተማ ሀገር ሽማግሌዎች ተወካይ በተገኙበት ገለጻ ተደርጓል።ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል ካደረገው የመጨረሻው ቅድመ ዝግጅት ስራ ለተማሪዎች ገለፃ (Orientation) ማድረግ ሲሆን በዚህም በተማሪዎች ምግብ ቤትና መኝታ ቤት አጠቃም፣በግቢ ቆይታቸው ሊፈፅሟቸው የሚገቡ መብትና ግዴታዎች፣ በፈተና ወቅት የተከለከሉ ተግባራት በተመለከተ፣የዩኒቨርሲው አመራሮች እና የስራ ሃላፊዎች በየዘርፍ ለተማሪወች ጠቃሚ መረጃወችን እና መመሪያዎች አስረድተዋቸዋል።የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው የዛሬው መድረክ መመሪያዎችንና ደንቦችን ባለማወቅ ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮች እንዳይኖሩ ለማድረግ እና ተማሪዎች የመጡበትን ዋና አላማ እንዲወጡ ለማድረግ የተዘጋጀ የመጨረሻው የቅድመ ዝግጅት ስራችን ነው ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ አክለውም ተፈታኝ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲውን እንዲላመዱት በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው በመለየታቸው የብቸኝነት እና የመደናገጥ ስሜት እንዳይሰማቸው በማድረግ ተቋሙን እንደቤታቸው እንዲቆጥሩት ለማስቻል የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀው ተፈታኝ ተማሪዎች ቆይታቸው የተሳካ እንዲሆን የሚጠቅሙ መልዕክቶችን በመግለፅ ለተማሪዎች ጥሩ የፈተና ጊዜ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።ተማሪዎቹ ፈተናውን ተረጋግተው እንዲፈተኑም የተፈታኝ ተማሪዎች ወላጆችን በመወከል አቶ በፍርዱ ወጨፎ ሥነ ልቦናዊ ዝግጅትን የሚያጠናክሩ አባታዊ ምክሮችን አስተላልፈዋል።የብሄራዊ ፈተና አስፈፃሚወች እና አስተባባሪዎች የፈተና ቅድመ ዝግጅት፣ የተማሪዎች የስነ ልቦና ዝግጅት፣በፈተና ሰዓት ያሉ መብትና ግዴታዎች፣ የመልስ መስጫ ወረቀት አጠቋቆር እና ሌሎች ተያያዥ የፈተና መመሪያና ደንቦችን በተመለከተ ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል።ዩኒቨርስቲው ባለፉት ሁለት የቅበላ ቀኖች ወንድ 3ሺ121፣ ሴት 3ሺ 508 በድምሩ 6ሺ 629 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን ዝግጅቱን አጠናቋል።የሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ከሃምሌ 25 እስከ 28/2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ # መልካም ፈተና!! #ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ
July 31, 2023 at 09:25PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

30 Jul, 18:33


በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡት የ12ኛ ክፍል ፈተና አስተባባሪዎችና ፈታኞች የጉብኝትና መስተንግዶ መርሃ ግብር ተደረገ።ዛሬ ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ለማስፈፀም ለተመደቡ አስተባባሪዎች እና ፈታኞች ዩኒቨርስቲው ከደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር፣ ደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የትምህርት መምሪያ እና የቱሪዝም መመሪያ ጋር በመተባበር ፕሮግራሙን ያዘጋጀ ሲሆን በዛሬው ውሎ ከቱሪስት መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን የውቅሮ መድሃኒያለም ቤተ ክርስቲያንን ጉብኝት ተካሂዷል።ጉብኝቱን የመሩት የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአለቃ ገብረሃና ባህል ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የታሪክ መምህሩ መሰረት ወርቁ እንደተናገሩት ደቡብ ጎንደር ዞን በርካታ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ያሉት ሲሆን ከነዚህም በጉና በጌምድር ወረዳ የሚገኘው የውቅሮ መድሃኒያለም ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ገልፀው በቅዱስ ንጉስ ላሊበላ ዘመን እንደተጀመረ የሚነገርና በኋላም በ14ኛው ክፍለ ዘመን በአቡነ ተክለ ፀዴቅ እንተጠናቀቀ የሚነገር በአንድ ግዙፍ ሰንሰለታማ ድንጋይ ተፈልፋሎ የተሰራ መሆኑን አብራርተው በውስጡ ቅድስት፣ቅኔ ማህሌት፣የተለያዩ ዋሻዎች ፣የቅዱሳን የቀብር ቦታዎች የሚገኙበት ታሪካዊና ጥንታዊ ቦታ መሆኑን ለጎብኝዎች ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።ዳይሬክተሩ አክለውም በዞኑ የሚገኙ የቱሪዝም ቦታዎቹን ለቱሪስት ምቹ በማድረግ በኩል በተለይም ዩኒቨርስቲው፣ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ ባለ ድርሻ አካላት በጋራ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል ። በጉብኝት መርሃ ግብሩ የተሳተፉ አስተባባሪዎች እና ፈታኝ መምህራን ባደረጉት ጉብኝት እጅግ መደሰታቸውን ገልፀው በጉብኝቱ ወቅት የጉና በጌምድር ወረዳ አስተዳደር እና ህብረተሰብ ለእንግዶቹ ላደረጉላቸው አቀባበል እና ባህላዊ መስተንገግዶ (ድንች በተልባ) መደሰታቸውን በመግለጽ አመስግነዋል።ከጉብኝት መልስ በደብረ ታቦር ከተማ በቀጠለው ፕሮግራም የሀገር ሽማግሌዎች እና የዩኒቨርስቲው ማኔጅመንት በተገኙበት የመስተንግዶ እና የመዝናኛ ዝግጅት ተደርጓል።የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው በፕሮግራሙ ተገኝተው እንደተናገሩት ከመላው ኢትዮጵያ የብሄራዊ ፈተናን ለማስፈፀም የተመደቡ ፈታኞች እና አስተባባሪወች በተዘጋጀው የደብረ ታቦርን እና ደቡብ ጎንደር አካባቢ ትውውቅ እና ጉብኝት የአካባቢውን ህብረተሰብ ባህልና ታሪክ ለማወቅ እድል እንደፈጠረላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ በማለት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የፈተና መርሃ ግብር ያለምንም ችግር በስኬት እንዲጠናቀቅ የፈተና ሀላፊዎች፣ፈታኞች፣ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት እና የፈተና ግብረ ሀይል አባላት ከከተማው ማህበረሰብ፣ የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር እና የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ጋር በጋራ እና በቅንጅት በመስራት ሁሉም አካላት ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው በሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪወች ፈተናም በቅንጅት እና በትብብር አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።የሀገር ሽማግሌ ተወካዮች በበኩላቸው መምህራን በመጀመሪያው ዙር የፈተና ሂደት በሰላም መጠናቀቅ ያደረጉትን አስተዋፅኦ አመስግነው የፈተና አስፈፃሚዎች፣የከተማው ነዋሪዎች እና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ተሳትፎ በአካባቢው ማህበረሰብ ስም አመስግነዋል።ታዋቂው የጉና ባንድ በፕሮግራሙ ወቅት ባህላዊ ጥዑመ ዜማወችን ለእንግዶቹ አቀርቧል።በመጨረሻም የፈተና ፈፃሚዎች እና አስተባባሪወች በተደረገላቸው አቀባበልና መስተንግዶ መደሰታቸውን ገልፀው ለዩኒቨርሲቲው እና ለአካባቢው ማህበረሰብ በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።
July 30, 2023 at 09:32PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

30 Jul, 10:33


ሀምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ምየተፈጥሮ ሳይንስ ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች በምሳ ሰአት ላይ፤
July 30, 2023 at 01:17PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

29 Jul, 17:34


ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።===============ዛሬ ሃምሌ 22/2015 ዓ.ም ከተለያዩ ወረዳዎች የመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ወንድ 2ሺ ሰላሳ፣ ሴት 2ሺ 528፣ በድምሩ 4ሺ 558 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ተቀብሏል። በወጣው የመግቢያ መርሃ ግብር መሰረት ቀሪወቹ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪወች ነገ ሃምሌ 23/2015 ዓ.ም የሚገቡ ይሆናል። #ተማሪዎቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ!!! #መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ!!
July 29, 2023 at 07:49PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

28 Jul, 17:33


በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ በሰላም ተጠናቋል።የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው የመጀመሪያው ዙር ፈተና በሰላም መጠናቀቅ አስመልክቶ እንደተናገሩት ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን ካደረገው ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በፈተና አሰጣጥ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ቀድሞ በመለየት ቅድመ ገለፃ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ (orientation) ለተፈታኞች በመስጠት የጀመረ መሆኑን ጠቁመው ፈተናውን ለማስፈፀም በተቋቋመው ግብረ ሃይል እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር የነበረው የተቀናጀ እና የተናበበ ስራ ለፈተናው በስኬት መጠናቀቅ ዋና ምክንያቶች ናቸው ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ አክለውም ፈተናውን ለማስፈፀም የተሳተፍ የፈተና ሀላፊወች፣ ፈታኞች፣ የተቋቋሙ የፈተና ግብረ ሀይሎች፣ የትምህርት ሚንስቴር፣ የፈተናወች ድርጅት፣ የክልል፣ የደቡብ ጎንደር ዞንና የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የትምህርት መምሪያ ሃላፊዎች እና ሌሎች የስራ ሀላፊወች፣ በተለይም ሰላማዊ የፈተና ከባቢ እንዲኖር ከመላው የፈተና አስፈፃሚ ግብረሀይል ጋር በብቃት ሙያዊ ሀላፊነታቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙት የፀጥታ እና ደህንነት አካላት እና አመራሩ እንዲሁም ለተፈታኝ ተማሪወቻችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የመኝታ፣ የምግብ፣ እና የህክምና አገልግሎት በተሟላ ሁኔታ እንዲቀርብ ያደረጉት የተማሪወች አገልግሎት ዳይሬክተር ጽ/ቤት አመራሮች እና መላው የስራ ባልደረቦች በአጠቃላይ በፈተና ሂደቱ ውስጥ ለተሳተፉ አካላት ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።በመጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ወንድ 3ሺ 502 ሴት 4ሺ 332 በድምሩ 7ሺ 837 ተማሪዎች ፈተናውን እንደወሰዱ ተገልጿል ። የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ከደብረታቦር ከተማ እና አቅራቢያ ትምህርት ቤቶች የመጡ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው በሰላም የተሸኙ ሲሆን በነገው እለት ቀሪወቹ በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት ወደቤተሰቦቻቸው የሚመለሱ ይሆናል።የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ሃምሌ 22-23/2015 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርስቲው ይገባሉ።
July 28, 2023 at 08:33PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

27 Jul, 17:33


July 27, 2023 at 08:29PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

27 Jul, 17:33


#ማስታወቂያ ለክረምት ትምህርት መርሃ -ግብር ተከታታይ ተማሪዎች በሙሉ
July 27, 2023 at 08:29PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

25 Jul, 18:33


የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ ገለጻ (Orientation) ተደረገላቸው። ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 18 /2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ የትምህርት ሚኒስቲር የፈተና ሀላፊዎች፣ የዩኒቨርስቲው አመራሮች፣የሀገር ሽማግሌዎች ተወካይ፣የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሃላፊ በተገኙበት ገለጻ ተደርጎላቸዋል።የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት፣ በተማሪዎች ምግብ ቤትና መኝታ ቤት አጠቃም እንዲሁም ሌሎች በቆይታቸው ሊፈፅሟቸው የሚገባ ደንቦችንና የተከለከሉ ተግባራትን በተመለከተ በዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች እና የስራ ሃላፊዎች በየዘርፍ መመሪያዎችን ገለፃ አድርገዋል።የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው የዛሬው መድረክ መመሪያዎችንና ደንቦችን ባለማወቅ ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮች እንዳይኖሩ ለማድረግ እና ተፈታኝ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲውን ተላምደው እንደቤታቸው እንዲቆጥሩት ለማስቻል መሆኑን ገልፀው ቆይታቸው የተሳካ እንዲሆን የሚጠቅሙ መልዕክቶችን በሰፊው ገለፃ አድርገዋል።ተማሪዎቹ ፈተናውን ተረጋግተው እንዲፈተኑም ሥነ ልቦናዊ ዝግጅትን የሚያጠናክሩ ምክሮችም ተሰጥተዋል።በትምህርት ሚኒስቴር በተወከሉ አስተባባሪዎች የፈተና ቅድመ ዝግጅት፣ የተማሪዎች የስነ ልቦና ዝግጅት፣በፈተና ሰዓት ያሉ መብትና ግዴታዎች ፣ የመልስ መስጫ ወረቀት አጠቋቆር እና ሌሎች ተያያዥ የፈተና መመሪያና ደንቦችን በተመለከተ ማብራሪያ ተሰቷል።የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21/ 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ # መልካም ፈተና!! #ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ
July 25, 2023 at 09:28PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

25 Jul, 13:33


በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ፈታኝ መምህራን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትና በፈተና ሂደቶችች ዙሪያ"ኦረንቴሽን" ተሰጠ።========ሀምሌ17/2015 ዓ.ም የፈተና ጣቢያ ሀላፊዎች፣ሱፐርቫይዘሮች የትምህርት ሚኒስቲር የፈተና ሀላፊዎች፣የደብረ ታቦር ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች እና የወጣቶች ተወካይ፣ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት እና የሎጅስቲክ አስተባባሪዎች በተገኙበት ለፈታኝ መምህራን በፈተና አሰጣጥ ሂደቶች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዩች ዙሪያ ወይይት ተደርጓል።የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉ እንደተናገሩት ፈተናው ከኩረጃ የፀዳና የተሳካ የፈተና ሂደት እንዲኖር የመጀመሪያ ግባችን መሆኑን ገልፀውለፈታኝ መምህራን ቆይታቸው የተሳካ እንዲሆን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በርካታ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን አመላክተዋል። ፈታኝ መምህራን ቆይታቸው መልካም እንዲሆንና ተልዕኮአቸው የተሳካ እንዲሆንም ተመኝተዋል።የደብረ ታቦር ከተማ ማህበረሰብን በመወከል የተገኙት አቶ በፍርዱ ወጨፎ ፈታኝ እንግዶቻችን ደብረ ታቦር ከተማ ከገቡበት ቀን ጀምሮ በቆይታቸው ጊዜ ሁሉ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከከተማው ወጣቶች ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው መልካም የስራ ጊዜ እና ቆይታ ተመኝተዋል።የዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ የስራ ሀላፊወች እና ከትምህርት ሚኒስቴር እና ፈተናወች ኤጀንሲ የፈተና ክፍል ሀላፊወች በልዩ ልዩ ጉዳዮች በተለይ በፈተና ስርጭትና ሂደት፣በሎጂስቲክ ፣በሰው ሃይል እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዩች ዙሪያ ገለፃ ተደርጓል።በመጨረሻ ከትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና የፈተናወች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶር እሸቱን ጨምሮ የስራ ሀላፊወች እና የፈተና ባለሞያወች የተሰጠውን የበይነ መረብ (on line) "ኦረንቴሽን" በጋራ በመካፈል ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
July 25, 2023 at 03:52PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

24 Jul, 19:33


የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ የሪሚዲያል ውጤት ይፋ ሆነ፡፡ተማሪዎች ከዚህ በታች ባለው ሊንክ በመጠቀም ውጤታችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳወቀለን፡፡ 👉 ID NO ያስገቡ በሚለው ቦታ ላይ DTU16R በማስቀደም ቁጥራችሁን በመጻፍ ሙሉ ውጤታችሁን ማየት ትችላለችሁ፡፡https://ift.tt/swb4YMt
July 24, 2023 at 10:32PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

24 Jul, 19:33


በደብረ ታቦር ዩኒበርሲቲ የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበሉን ቀጥሏል።=============== ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በ2ኛ ቀን የቅበላ መርሃ ግብር ከተለያዩ ወረዳዎች የመጡ ተፈታኝ ተማሪዎችን በተሳካ ሁኔታ ሲቀበል ውሏል።በዛሬው ዕለት ወንድ 1ሺ 150፣ሴት 1ሺ 557 በድምሩ 2ሺ 707 ተማሪዎችን ተቀብሏል። በአጠቃላይ በመጀመሪያው ዙር በሁለቱም ቀናት ወንድ 3ሺ 355፣ ሴት 4ሺ 240 በአጠቃላይ 7ሺ 593 የማህበራዊ ሳይንስ የመጀመሪያ ተፈታኝ ተማሪዎችን ተቀብሏል። #ተማሪዎቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ!!! #መልካም ፈተና!!
July 24, 2023 at 09:40PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

23 Jul, 18:33


ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።===============በ2015 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ተፈታኞቹን በመቀበል ላይ ይገኛል። ዛሬ ሃምሌ 16/2015 ዓ.ም ከደቡብ ጎንደር ዞን ወረዳዎች የመጡ ደራ፣አንዳቤት፣ስማዳ፣ሰዴ ሙጃ እና ፋርጣ ወረዳ የመጡ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወንድ 2203 ፣ሴት 2683 በድምሩ 4886 ተፈታኝ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ተቀብሏል። ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ቀናትን በወጣላቸው የመግቢያ መርሃ ግብር መሰረት ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበሉን ይቀጥላል። #ተማሪዎቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ!!!
July 23, 2023 at 09:28PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

20 Jul, 13:33


የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 1ሺ 202 ተማሪዎችን አስመረቀ።ሃምሌ 13/2015 ዓ.ም በመደበኛና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር እንዲሁም በክረምትና በኤክስቴሽን 1ሺ 202 ተማሪዎችን ለ10ኛ ጊዜ አስመርቋል።ዩኒቨርሲቲው ከ2004 ዓ.ም ስራ የጀመረና ቀደም ሲል በትምህርት ክፍልና ፍኩሊቲ ይጠቀሱ የነበሩትን ወደ ትምህርት ቤትና ኮሌጅ አሳድጎ በአሁኑ ሰዓት በ5 ኮሌጆችና በ1 ኢንስቲትዩቱ እና ሁለት ትምህርት ቤቶች የተዋቀረ ነው።የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው በእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸው "የዛሬዎቹ ተመራቂዎች ለየት የሚያደርጋችሁ በዩኒቨርስቲው ብቻ ሳይሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የመውጫ ፈተና ሚዛን ተመዝናችሁ ለመመረቅ መብቃታችሁ ነው "የዕለቱ ተመራቂዎች የቀጣዩን ዘመን መልካም የህይወት ምዕራፍ እንዲሆንላቸው እመኛለሁ" ብለዋልየዕለቱ የክብር እንግዳ ዶክተር ሳሌ አያሌው የአማራ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር "እናንተ ተማሪዎች ሙሉ አቅማችሁንና ትኩረታችሁን አላማ ላይ በማድረግ ለዚህ ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።ከሂሳብ ትምህርት ክፍል ተማሪ አወቀ ቢያዝን በላይ 3.97 በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
July 20, 2023 at 04:26PM

DEBRE TABOR UNIVERSITY, ETHIOPIA

20 Jul, 00:33


To 2015 Graduates at DTU:“You’ll always remember this day and so will all of us who were here cheering you on. Best of luck to you always!”
July 20, 2023 at 02:59AM