ልብ - ወለድ @lib_weled Channel on Telegram

ልብ - ወለድ

@lib_weled


ልብ - ወለድ (Amharic)

ልብ - ወለድ በአማርኛ እና በቀላሉ ቋንቋዎችን ማየት የሚፈልጉት ቴሌግራም ክላኦድ ነው። ይህ ትልቅ እና አውሮፕያይ ቴሌግራም ክላኦድ የተጠቃሚ ተጠቃሚ ሰልፍ ሆነን እየሞቀ አልፏል። እኛም በዚህ ቦታ መሠረት ከተማይቱ እንደተወለደ ይህን ሽልማድ እንደሚያከናውኑ አሁንም አማርኛ ሊንኩን ደምቀን በመረጃው ላይ ነን።

ልብ - ወለድ

09 Jan, 03:43


አዲስ ልብወለድ እንድንጀምር ቻናሉን ሼር በማድረግ ተባበሩን🙏

@Lib_Weled

ልብ - ወለድ

09 Dec, 03:55


ሚጠብቁ ገመተች፡፡ የሂባ ልጅ የመጣው ከወንድ ጋር ተኝታ ነው፡፡ የናርዶስም ስብራት የተፈጠረው ከወንድ ጋር ተኝታ ነው፡፡ ልዩነቱ ግን በጋብቻ እና በዝሙት መሀል ነው፡፡ ከጋብቻው ልጅ ….. ከዝሙቱ ደግሞ በሽታ! ጋብቻ ምንም ያህል የተመቻቸ ባይሆን እንኳ ፍሬው እንደዝሙት አይከፋም ስትል አሰበች፡፡ ጋብቻ ያስከተለው ህይወትን ….. ዝሙቷ የሸለማት ሞትን እንደሆነ ስታስብ እንባዋ ቀደማት፡፡
ናርዶስን የመረመረቻት ነርስ ከላብራቶሪ የመጣላትን ውጤት ከተመለከተች በኋላ ወደ ተረኛው የስነ ልቦና ባለሙያ ደወለች፡፡ ካፌ ውስጥ እያውደለደለ ነበር፡፡ እየሮጠ መጥቶ ወደ ቢሮው ገባ፡፡ ነርሷ ወደ ውጪ ወጥታ ናርዶስን ጠራቻት፡፡ ናርዶስ ቢሮው ውስጥ እንደገባች ነርሷ ቢሮውን ዘግታ ወጣች፡፡ ቀጫጫው የስነ ልቦና ባለሙያ እንድትቀመጥ ከጋበዛት በኋላ ለምን መመርመር እንደፈለገች ጠየቃት፡፡ ነገረችው፡፡ ከጅምሩ ምክር ማብዛት ሲጀምር ሰለቻት፡፡ ‹‹ቫይረሱ ቢኖርብሽ እንኳ በህይወት መኖር አትችይም ማለት አይደለም! ከቫይረሱ ጋር አብሮ መኖር ይቻላል …..›› ወሬው ሰለቻት፡፡
‹‹ይቅርታ …… የምትለውን ሁሉ አውቀዋለሁ፡፡ አሁን ውጤቴን ብቻ ንገረኝ!›› ተበሳጨች፡፡
‹‹ካልሽ መልካም ….. ውጤቱ የሚያሳየው ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ እንዳለ ነው ይህ ማለት ግን ….››
‹‹እልልልልልልልል›› የሚል የደስታ ጩኸት ጤና ጣቢያውን አናጋው፡፡ ሂባ በሰላም የመገላገሏን ብስራት የሰሙ ቤተሰቦቿ እና ጎረቤቶቿ ያወጡት ድምፅ ነበር፡፡ ናርዶስ የስነ ልቦና ባለሙያውን ሳታስጨርሰው ትታው ወጣች፡፡ የጠበቀችውን ውጤት መስማቷ ብዙም አላስደነገጣትም ነበር፡፡ ከመተላለፊያው ላይ ቆማ ማዋለጃ ክፍል በር ላይ እየተካሄደ ያለውን የደስታ ትዕይንት ተመልክታ ፈገግ አለች፡፡ ፈገግ ለሂባ ….. ፈገግ ለጓደኛዋ ደስታ …. ፈገግ ለአብሮአደጓ የአብራክ ክፋይ ….. ፈገግ! የቤተሰቡን …. የራሷንም እናት ደስታ ስታይ ለቤተሰቧ ውርደት መሆንን ፈራች፡፡ ከረፈደ በኋላ መንቃቷ እያመማት ቀስ ብላ በሌላኛው የፎቁ መውረጃ በኩል ወርዳ ወደ ውጪ ወጣች፡፡ ወዴት እንደምትሄድ አታውቅም …. ቦርሳዋን ብቻ እንደያዘች ….. ማንም ወደ ማያውቃት ….. ማንንም ወደማታሰድብበት ቦታ ለመሰደድ ወሰነች፡፡ ታክሲ ውስጥ ….. ከዛም መናኸሪያ …… ከዛም አንድ አባዱላ መኪና ውስጥ እንዱ ደላላ ጎትቶ ሲያስገባት …. መኪናው ወዴት እንደሚሄድ እንኳ አታውቅም! ብቻ ከአዲስ አበባ ውጪ መሆኑን ብቻ ነው የፈለገችው …… ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ ….. ናርዶስ አዲስ አበባን ለቅቃ ወደማታውቀው ስፍራ ተጓዘች፡፡
ሂባ ከሆስፒታል ከወጣች ጀምሮ ጥያቄ የሆነባት ናርዶስን አለማየቷ ነበር፡፡ ቤተሰቦቿ ተጨንቀው ስልክ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ….. ስልኳ ዝግ ነው፡፡ ሳምንት … ናርዶስ የሌለችበት ባዶ ቤት ውስጥ አለፈ፡፡ ዚያድ ልጁን ለማየት ብቅ ባለበት እግረ መንገዱን አባቷ ባዘዙት መሰረት ‹‹ፈትቼሻለሁ›› ብሏት አዲስ የሰርግ ጥሪ ካርድ ሰጥቷቸው ሄደ፡፡ ተፈላጊ ነኝ ለማለት ይመስላል፡፡ ገንዘብ አለው …… ሴት ለእርሱ የምትገዛ እቃ ናት፡፡
*
ቀመር የነበራት ተስፋ ሲሟጠጥ ለመጨረሻ ጊዜ ኢምራንን አገኘችው፡፡ ሻንጣዋን ይዛ ነበር፡፡ በጣም ደንግጧል፡፡
‹‹ወዴት ነው?››
‹‹ወደ ቤት …. በቃኝ ባክህ እዛው የግል እማራለሁ … ወንጀል ከለመድኩበት ቦታ ልሽሽ!››
‹‹እንዴ ቀመር ጎበዝ ተማሪ እኮ ነሽ …››
‹‹እሱን ተወው ለማንኛውም አሁን ላገኝህ የፈለግኩት ባለፈው ሂባ ያማከረችህ ጉዳይ ስለራሷ እንደሆነ ልንገርህ ብዬ ነው፡፡ ፈትታለች … ሲመስለኝ ልጅም አርግዛለች … አግባት››
‹‹ጓደኛዋ ደውላ ስትነግረኝ ወዲያው ነው የነገረችኝ ስለራሷ እንደነበር የገባኝ …. ግን ለእማማ ስነግራት የወለደች ሴት አታገባም … ያኔ እንደዛ አድርጋህ ምናምን አለች …. እዛው ደሴ ቤተሰብ የሚያመጣውን ለማግባት ወስኛለሁ ባክሽ!››
‹‹እሷ የወለደችው እኮ አግብታ ነው አይደል እንዴ ….. አንተ ሳታገባ በዝሙት የረከስክ መሆንህን እንደውም ለሂባ ንፅህና የማትመጥን መሆኑን አትነግራቸውም ነበር? …… ያው ለነገሩ ፍርዳችን ሁሌም ሚዛናዊ አይደለም፡፡ ወንድ እንዳሻው ቢቆሽሽ አይታወቅበትም …. አይታወቅበትም ብቻ ሳይሆን ቢታወቅም እሱ ወንድ ስለሆነ ችግር የለውም አይደል? …. ሴት አግብታ ስትወልድ ግን ….. ›› ንግግሯን መጨረስ ከበዳት፡፡
‹‹እንዴ ጥብቅና መቆም›› ሳቀ፡፡
‹‹በቃ ቻው የምትመጥንህን ይስጥህ ብያለሁ!››
‹‹ይቅርታ ለዚህ ውሳኔሽ ምክንያት ስለሆንኩ!››
የፌዝ ፈገግታ ፈገግ ብላ ሻንጣዋን እየጎተተች ትታው ሄደች፡፡ የዩኒቨርሲቲውን ግቢ ለቅቃ እስክትወጣ በአይኑ ሸኛት፡፡ የሂባን በደል ቀመር ላይ የተወጣ መሰለው፡፡ በልቡ ‹‹ሁሉም ዕድሉን ሲያገኝ በደለኛ ነው!›› ሲል አሰበ፡፡ ዋናው በር ላይ በእርሱ አነሳሽነት የተመሰረተው የሴቶች መብት ላይ የሚሰራው ቢሮ ክፍለ ሀገር ለሚኖሩ ሴት ተማሪዎች የሞዴስ ወጪያቸውን ለመሸፈን በማሰብ ላሰናዳው የባለድርሻ አካላት የተሳትፎ ምክረ ሀሳብ ማጎልበቻ ኮንፈረንስ የመጥሪያ ባነር ተሰቅሎ ነበር፡፡
*
ተፈፀመ፡፡

@Lib_Weled

ልብ - ወለድ

09 Dec, 03:54


የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል ሀያ
(ፉአድ ሙና)
.
ቀመር የኢምራን ነገር ተስፋ እያስቆረጣት የመጣ ይመስላል፡፡ ከሱ የጠበቀችውን ክብር እያገኘች አይደለም፡፡ ዶርም ውስጥ ተኝታ በደንብ ስታሰላስለው የነበረው ኢምራንን የምታስገድድበትን አዲስ መንገድ ነበር፡፡ ምንም አይነት አዲስ መንገድ አላገኘችም፡፡ ከዶርም ወጥታ በቀጥታ እየተንደረደረች ወደ ኢምራን ቢሮ ሄደች፡፡ ኢምራን ቢሮው ውስጥ ተቀምጦ እያነበበ ነበር፡፡ ሳታንኳኳ ቢሮውን በርግዳው ገባች፡፡ ኢምራን ሁኔታዋ በጣሙን አስደንግጦታል፡፡ ጠረጴዛውን አልፋ ሄዳ ጭኖቹ ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹ደህና ነሽ ግን?›› በግርምት እያየ ጠየቃት፡፡
‹‹ኢምሩ በአላህ ይሁንብህ አግባኝ! ካንተ ሌላ ጥብቅ የነበርኩ መሆኔን የሚያውቅ የለም! አዲስ ሰው መልመድ አልችልም እባክህ!››
‹‹ቀመር ይኼ እኮ በልመና የሚሆን አይደለም! ውስጤ ላይ ላንቺ ያለኝ ፍላጎት ተንኗል፡፡ ተረጂኝ!››
‹‹የመጨረሻ ውሳኔህ ነው?››
‹‹አዎ አዝናለሁ!››
‹‹በቃ መጥጠህ ወረወርከኝ? ስሜትህን አረካህብኝ በቃ?›› ቀመር ማልቀስ ጀመረች፡፡
ኢምራን ለቅሶዋ ሰልችቶታል፡፡ ‹‹ለሰራሽው ስራ ሀላፊነቱን ራስሽ ውሰጂ! አስገድደሽኝ እንጂ አስገድጄሽ ያደረግኩት ነገር የለም!››
ቀመር ተፈናጥራ ቢሮውን ለቅቃ ወጣች፡፡ ልቧ ውስጥ የነበረው ተስፋ ሙሉ ለሙሉ ሲተንን ተሰማት፡፡
*
ልክ እንደ ፅጌረዳ አበባ …. የፍካቷ ቀን በመጣ ጊዜ አይኖች እንደሚቃብዙባት …. ብዙዎች እንደሚመኟት ….. አዎን ልክ እንደ አበባዋ ፍካት አክሳሚ እጆች እንደሚሽቀዳደሙባት ….. የተቀጠፈች ቀን ከቀናት የዘለለ እድሜ እንደማይኖራት …. እንደምትሟሽሸው እንደሷ እንደአበባዋ ….. ናርዶስም ፈክታ ፣ ሂባም አብረቅርቃ ነበር፡፡ የሂባ ትዳር ጎርባጣ መሆን ሁለቱንም ሲያሳዝናቸው ፣ ማምለጫ ሲያስፈልጋቸው …. ስሜቱን እኩል ሲጋሩት ያኔ የመጀመሪያው ስብራታቸው ነበር፡፡ ዛሬ ግን ከብዶ የሚከብድ …. እንዲሁ በቃኝ ተብሎ የማይመለጥበት የጭንቀት አጥር ውስጥ ታጭቀዋል፡፡ ዛሬ ማንንም ለመውቀስ የማይመች ሁኔታ ላይ ወድቀዋል፡፡
‹‹እና ምርመራውን ምን አሰብሽ?›› ሂባ የናርዶስ አልጋ ላይ እግሮቿን በልቅጣ ትራሷን ተደግፋ አልጋው ላይ በፊቷ ተደፍታ የደነዘዘችውን ናርዶስን ጠየቀቻት፡፡
‹‹አላውቅም››
‹‹ናርዲዬ እንዲሁ ክፍልሽ ውስጥ ታሽገሽ ሳምንት ሊያልፍ እኮ ነው! ቢያንስ ለመፍትሄ ይረዳናል ተመርመሪ!››
‹‹ለየቱ መፍትሄ? ቀን ከሌት ክኒን ለመዋጥ? ንገሪኛ ለምኑ ነው የሚረዳን?›› ናርዶስ ለቅሶዋን ቀጠለች፡፡
የናርዶስ ፊት ጠውልጓል፡፡ በለቅሶ ብዛት አይኖቿ አባብጠዋል፡፡ ለቤተሰቦቿ ስራዋን እርግፍ አድርጋ ትታ መኝታ ቤቷ መታሸጓ ትልቅ ዱብዳ ሆኖባቸዋል፡፡ ምግብም በብዙ ልመና ጥቂት ብትወስድ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በአንድ ቀን ተገለባብጧል፡፡ ሳቂታዋ ናርዶስ ለቅሶ ቤት ሆናለች፡፡ ሂባ ሁኔታዋ እጅጉን እያሸበራት ነው፡፡ በዚህ ከቀጠለች አቅም አንሷት መሞቷ ነው፡፡ ሂባ ልመናዋን ቀጥላለች፡፡
‹‹ናርዲዬ አሁን እኮ እሱ ስላለበት ነው ይዞሽ ሊሆን ይችላል ብለን ያሰብነው! ምን ይታወቃል ይዞሽ ባይሆንስ? መመርመሩ ይሻላል ተይ!?››
‹‹ሂባ ለምን አጉል ተስፋ ትሰጪኛለሽ? በየቀኑ ያለምንም መከላከያ ነበር እኮ ስንፋተግ የነበረው! ……ምናለ ቢያንስ እንኳ ትንሽ ቢያስብልኝ? ደደብ! ….. ራስ ወዳድ ነው!››
ሂባ የናርዶስን ስልክ ከአጠገቧ አንስታ ልታስነሳው ሞከረች፡፡ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ሳምንቱን ሙሉ ተዘግቶ ነበር፡፡ ቻርጅ ከሰካችው በኋላ ድጋሚ አስነሳችው፡፡ ስልኩ በርቶ ትንሽ እንደቆየ በርካታ መልዕክቶች ገቡ፡፡ የኤርሚያስን መልዕክት ከፈተችው፡፡ ‹‹ለተፈጠረው ነገር አዝናለሁ፡፡ እኔም ለራሴ ማሰብ ስለነበረብኝ ነው፡፡ መከላከያ ለምን እንድንጠቀም አላደረግክም ላልሽኝ ….. ሎሊፖፕ ከነልጣጩ መምጠጥ እንደማለት ነው፡፡ ስሜት አይሰጠኝም! አዝናለሁ!›› ይላል፡፡ ሂባ ማንበብ የፈለገችውን ስላገኘች ስልኩን መልሳ አጠፋችው፡፡
‹‹እና ናርዲዬ እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምትቀጥይው?››
‹‹እስከምሞት ነዋ! ከዚህ የአታላዮች አለም እስክገላገል!›› ብላ ወደ ሂባ ፊቷን መለሰችና ንግግሯን ቀጠለች፡፡ ‹‹ሂባዬ ታውቂያለሽ አይደል? እኔ ያላንቺ … አንቺ ያለኔ ደካማ እንደሆንን? …. እ ሂቡ ታውቂያለሽ አይደል ከልጅነታችን ጀምሮ በሁሉም የህይወታችን ጉዳዮች ላይ በጋራ ተማክረን ስንወስን በራሳችን መወሰን እንዳልለመድን? ….. አየሽ ያኔ ሳይረፍድ በፊት ስለ ኤርሚያስ ላማክርሽ ስፈልግ አንቺ በዚያድ ምክንያት ጊዜ አልነበረሽም፡፡ ስንገናኝም ስለ ዚያድ በደል እንጂ ስለ አዲስ ፍቅር ለማውራት ሁኔታዎች ምቹ አልነበሩም፡፡ ያኔ አንቺን አማክሬሽ ቢሆን ኖሮ እንዲህ አልሆንም ነበር፡፡ …. ሂቡዬ ያኔ ብነግርሽ ኖሮ…›› ለቅሶዋ በርትቶ ከንግግሯ ገታት፡፡
ሂባ በናርዶስ ተስፋ መቁረጥ ውስጧ ተረበሸ፡፡ ዳግም ወደ ተወችው መነፋረቋ ተመለሰች፡፡
*
በእንባ እና በጭንቅ እንደተሞሉ በርካታ ቀናት ነጎዱ ….
ሂባ ለእርግዝና ክትትሏ ወደ ህክምና ተቋም በሚሄዱበት ጊዜ ሁሉ ናርዶስን እንድትመረመር ብትለምናትም ልትሰማት አልቻለችም፡፡ ምርመራ የሚባለው ቃል እጅጉን ቀፏታል፡፡ ስራዋን ትታ ቤቷ ውስጥ ከታሸገች ወር አለፈ፡፡ ቤተሰቦቿ መጨነቃቸው ሲበረታ ሂባ ‹‹ፍቅረኛዋ ከድቷት ነው›› በሚል ምክንያት ልባቸውን ለማሳረፍ ትሞክራለች፡፡ አሁን አሁን ግን እነሱም አልመስል እያላቸው ነው፡፡
የሚያዚያ ወር ገብቶ ጥቂት ቀናት ሄደዋል፡፡ ሂባ እና ናርዶስ የሂባ መኝታ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው ስለኢምራን እያወሩ ነበር፡፡ ናርዶስ ስልኳን አንስታ ኢምራን ጋር ደወለችለት፡፡
‹‹ምን እያደረግሽ ነው?›› ሂባ ደንግጣለች፡፡
‹‹አታካብጂ ባክሽ የምን መንቀጥቀጥ ነው!››
ስልኩ ተነሳ፡፡ ኢምራን የቀድሞ ጓደኛውን ስልክ ከረዥም ጊዜ በኋላ ሲያይ ተገርሟል፡፡
‹‹ናርዲ ቀውሷ!››
‹‹ትሰማለህ ኢምራን! ሂባ ከባሏ ጋር ተፋታለች፡፡ ከአንድ ልጇ ጋር ተቀብለህ ልታገባት ከፈለግክ ፈቃደኛ ስለሆነች ደውልላት! ቻው!›› ስልኩን ጆሮው ላይ ጠረቀመችው፡፡
‹‹ናርዲ ምንድነው ያደረግሽው?››
‹‹በቃ ከፈለገሽ ይደውላል፡፡ አለቀ!››
እየተጨዋወቱ ብዙም ሳይቆይ ሂባ ማቃሰት ጀመረች፡፡ ምጧ መጥቶ ነበር፡፡ ናርዶስ ሮጥ ብላ ወ/ሮ ዘምዘምን ጠራቻቸው፡፡ ጎረቤት ተሰበሰበ፡፡ እናቷ እንደደገፏት ናርዶስ የምታውቀው ባለላዳ ጋር ደውላ ይዘዋት ወደ ጤና ጣቢያ ሄዱ፡፡
ጤና ጣቢያ ደርሰው ሂባን ለነርሶቹ ካስረከቡ በኋላ ውጪ ላይ ቆመው እየተቁነጠነጡ የመውለዷን ብስራት መጠበቅ ጀመሩ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሂባ አባት ስለተደወለላቸው ከስራ ቦታቸው መጡ፡፡ ሁሉም በጉጉት የሚጠብቀው የሂባን ልጅ በሰላም ወደዚህ አለም መቀላቀል ነው፡፡ ናርዶስ በሩ ላይ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀከል ተነጥላ ወደ ፎቅ ወጣች፡፡ የላይኛው ፎቅ ከታች ወደ ላይ እስከጣራው ድረስ ደረጃው ዙሪያውን ክፍት ነው፡፡ ታች ሆና የላይኛው ፎቅ ላይ ያየችው ነገር አለ፡፡ ራመድ ….. ራመድ …. አንደኛ ፎቅ ….. ሁለተኛ ፎቅ ….. ሶስተኛ ፎቅ ….. አንድ ቀይ ቀለም የበዛበት ማስታወቂያ የተለጠፈበት ቢሮ ውስጥ ገባች፡፡ እጇን ከጠረጴዛው ወዲያ ተቀምጣ ስትቦዝን ለነበረችው ነርስ ዘረጋችላት፡፡ ደሟን ወስዳ ጥቂት ደቂቃዎችን እንድትታገሳት ጠየቀቻት፡፡ ናርዶስ ተስፋ መቁረጧ ፊቷ ላይ እየተነበበ ከቢሮው ወጥታ ወደ ታች ቁልቁል ተመለከተች፡፡ የማዋለጃ ክፍሉ በር ላይ ወላጆቿ እና ጎረቤቶቿ ሲቁነጠነጡ ተመለከተች፡፡ ሁሉም የሂባን መውለድ በተስፋ እ

ንደ

ልብ - ወለድ

08 Dec, 03:49


እንዴት ይኼን ያህል ራስ ወዳድ ትሆናለህ? ትንሽ እንኳ አላሳዝንህም?›› ተነፋረቀች፡፡
‹‹ናርዲዬ ምንድነው የምትዪው? የምን ራስ ወዳድነት ነው? ምን ሆንሽብኝ?››
‹‹ቢያንስ እንኳ ምናለ በኮንዶም እንድንወጣ ብታደረግ? እህት ባይኖርህ እንኳ እናት የለህም?››
‹‹ናርዲ እባክሽ ግራ አታጋቢኝ! ምንድነው አረገዝሽ እንዴ?››
‹‹እሱማ በምን እድሌ! ስማ! ዛሬ የሄድክበት ሀኪም ቤት እኔም ክትትል ስጀምር እንገናኝ ይሆናል! አንተ ግን ሰብዓዊነት የማይሰማህ …… ደደብ ነህ እሺ!›› ስልኩን ጆሮው ላይ ጠረቀመችበት፡፡
ትንሽ ካነባች በኋላ ሂባ ጋር ልትደውል እንደነበር ትዝ አላት፡፡ ሂባ ጋር ስትደውል ሜላት ወደ መቀመጫዋ እየተመለሰች ነበር፡፡ ሜላት ወንበሯ ላይ እንደተመቻቸች ስልኳን ጆሮዋ ላይ የለጠፈችውን ናርዶስን እየተመለከተች ‹‹ናርዲዬ ይኼ ማለት እኮ አንቺን ይዞሻል ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ አይታወቅም እኮ የፈጣሪ ነገር ላይዝሽ ይችላል ብዙ አትረበሺ!›› አለች፡፡
ናርዶስ የደወለችው ስልክ ተነስቶ ስለነበር ምላሽ ሳትሰጣት እያለቀሰች ‹‹ሂባዬ …. ›› አለች፡፡
‹‹ወዬ ናርዲዬ ምንድነው ድምፅሽ? ምን ሆነሻል?››
‹‹ጉድ ሆንኩልሽ ሂባዬ! ጉድ ሆንኩልሽ!››
‹‹የት ነሽ? ምን ተፈጠረ?›› ድንጋጤዋ ንግግሯን የመርበትበት ወዘና አልብሶታል፡፡ ያለችበትን ቦታ ነገረቻት፡፡ የአብሮ አደግ ጓደኛዋ ጭንቅ ላይ መሆን ሆዷ በጣሙን መግፋቱንና በታክሲ ለመሳፈር በጣሙን የሚከብዳት መሆኑን አስረስቷታል፡፡ ከቤቷ ወጥታ ታክሲ ጋር እስከምትደርስ የሆዷን መግፋት ረስታው ነበር፡፡ ሰዓቱ መምሸቱ ደግሞ ታክሲ እንደልብ እንደማታገኝ ሲያረዳት ኮንትራት ታክሲ አናገረች፡፡ የናርዶስ መስሪያ ቤት አቅራቢያ ስትደርስ ደወለችላት፡፡ ከካፌው በር ላይ ወጥታ ተቀበለቻት፡፡ ሜላት ናርዶስን ለሂባ አስረክባ በተደጋጋሚ ሲደውል ወደነበረው ባሏ ሄደች፡፡ ናርዶስ ሂባን ስታይ ለቅሶዋ ቅጥ አጣ፡፡ ክፉኛ አነባች፡፡ ከልብ ለማንባት ምቹ መደገፊያ ያሻል የሚባለው እውነት ለመሆኑ ምስክር ይመስላሉ፡፡ ሂባ ምን እንደሆነች እንኳ ሳታውቅ ደረቷ ላይ አስደግፋት አብራት ታለቅሳለች፡፡ በቃ ዝም ብሎ ማልቀስ! ዝም ብሎ ማንባት!
‹‹የኔ ቆንጆ ምንድነው የሆንሽብኝ?›› ሂባ ፊቷ በእንባ እንደታጠበ የናርዶስን እንባ ለመጥረግ እየሞከረች ጠየቀቻት፡፡
ከንፈሮቿ እየተንቀጠቀጡ ፣ ሳግ ባጎረበጠው ድምፅ ‹‹ኤርሚ ኤች አይ ቪ አለበት›› አለች፡፡ ሂባ የሰማችውን ለማመን አልቻለችም፡፡ በቀጥታ አዕምሮዋ ውስጥ የተፈጠረው ምስል የናርዶስ ሞት ነው፡፡ ለጥቂት ደቂቃ ከደነዘዘች በኋላ መንሰቅሰቅ ጀመረች፡፡ ለቅሶዋ ናርዶስን ይበልጥ እያስለቀሳት ነው፡፡ አፅናኝ የለም፡፡ ሁለቱም ህመሙን እኩል የቀመሱት ይመስላሉ፡፡ ያነባሉ …. እንባ ግን አይፈውስም፡፡
***
ይቀጥላል…

@Lib_Weled

ልብ - ወለድ

08 Dec, 03:48


የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አስራዘጠኝ
(ፉአድ ሙና)
.
ናርዶስ ከቢሮዋ ወጥታ በፍጥነት ደረጃውን ስትወርድ የኤርሚያስ ባልደረባ ተከተለቻት፡፡ ባለፈው ሰፈር ውስጥ አብረው አግኝታቸው ነበር፡፡ ናርዶስ ዛሬ ኤርሚያስ ለስብሰባ ወደ ሰበታ ሄጃለሁ ስላላት ከነጋ አላገኘችውም፡፡ እድሜዋ ከሀያ አራት የማይበልጠው አጠር ያለችው የኤርሚያስ ባልደረባ እየተፍለቀለቀች ቀረበቻት፡፡
‹‹hey ናርዲ እንዴት ነሽ?››
‹‹አለሁልሽ ሜላትዬ ሁሉ አማን ነው!››
‹‹ኤርሚ ዛሬ የለም ብቻሽን ነሽ!››
‹‹አዎ ስብሰባ ነው አይደል? እናንተም ዛሬ ብቻችሁን ዋላችሁ!››
‹‹ስብሰባ? የምን ስብሰባ?››
‹‹የቀረው ስብሰባ ሄዶ አይደለም እንዴ?››
‹‹ምናልባት አዲስ ነገር መጥቶ በዛው ከላኩት አላውቅም እንጂ ዛሬ የቀረው ለህክምና አስፈቅዶ ነው!››
‹‹የምን ህክምና ነው? አሞታል እንዴ?››
‹‹ ናርዲ ግር እያልሽኝ ነው! ይቅርታና ፍቅረኛው ነሽ አይደል?››
‹‹አዎ እንደዛ ነገር ነኝ፡፡ ምነው?››
‹‹ምንም አይነት የሚከታተለው ህክምና እንዳለ አታውቂም?››
‹‹እኔ አንድም ቀን አሞት አይቼው አላውቅም!››
ሜላት ነገሩ ግራ ስለገባት ረጋ ብላ ልታወራት ፈለገች፡፡ ደረጃውን ወርደው ወደ ውጪ ከወጡ በኋላ ወደ ቀኝ ታጥፈው ትንሽ እንደተራመዱ ያገኟት ትንሽዬ ካፌ ገብተው ተቀመጡ፡፡ አስተናጋጁ ከመቅፅበት ከፊታቸው መጥቶ ተገተረ፡፡ ማስተናገድ ናፍቆት የነበረ ይመስላል፡፡ ትኩስ ነገር ካዘዙ በኋላ ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡
‹‹ናርዲዬ ከኤርሚ ጋር ምን ያህል ጊዜ ሆናችኋል?››
‹‹በቃ እዚህ ከተቀጠርኩ በኋላ ነው እንደ ጓደኛ ቀረበኝ ቀስ በቀስ ወደዛ ቀየርነው፡፡››
‹‹እኔ እኮ ከዛም በፊት የምትተዋወቁ ነበር የሚመስለኝ! እንደውም በሱ ጥረት ነው የተቀጠረችው ምናምን ይባል ነበር እኮ!››
‹‹አጎቴ ነው ያስቀጠረኝ! ኤርሚያስን ከመቀጠሬ በፊት እንኳን ልግባባው አይቼውም አላውቅም!››
ሜላት አቀረቀረች፡፡ እንባ አይኗን ታገለው፡፡ በውሸት ፈገግታ እንባዋን ለማባረር እየሞከረች ቀና አለች፡፡
‹‹መስሪያ ቤት ውስጥ ስለናንተ የሚወራውን ሰምተሽ አታውቂም?››
‹‹ስለኛ ይወራል?›› ናርዶስ ቢሮ ውስጥ ያደረጉት ነገር የታወቀ መስሏት ልቧ በፍርሀት ራደ፡፡
‹‹በጣም ነው የሚወራው!››
‹‹ምን ተብሎ?››
‹‹በብዛት የሚወራው ከድሮም እንደምትተዋወቁ ፣ በጣም ራሳችሁን ስለምትጠብቁ እንደማያስታውቅባችሁ ምናምን ነው፡፡››
‹‹ምኑ ነው የማያስታውቅብን? ፍቅረኛ መሆናችን?››
ሜላት ራሷን ለማደፋፈር ሞከረችና ቀጠለች፡፡ ‹‹የእድሜ ማራዘሚያ ትወስጂያለሽ አይደል?››
‹‹ፈጣሪ ራሱ ያርዝምልኝ እንጂ እኔ ምን እወስዳለሁ?›› ካለች በኋላ ሳቋን ለቀቀችው፡፡
‹‹ግልፅ አድርጌ ልጠይቅሽ! አንቺ ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ እንዳለ ካወቅሽ ምን ያህል ጊዜ ነው?››
‹‹የምን ቫይረስ?›› ናርዶስ ሳታስበው ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡
‹‹አረ ቁጭ በይ ተረጋግተን እናውራ! እኔም ይሄን ስለገመትኩ እኮ ነው ላወራሽ የፈለግኩት!››
ናርዶስ በዝግታ ተመልሳ ተቀመጠች፡፡
‹‹ይኸውልሽ ናርዶስ ታውቂ ይሆን አይሆን ለማረጋገጥ ነበር ዙሪያ ጥምጥም እየሄድኩ ጥያቄዎችን ስጠይቅሽ የነበረው፡፡ አሁን እንደገባኝ ከሆነ ምንም የምታውቂው ነገር የለም፡፡ በአጭሩ ልልሽ የፈለግኩት ኤርሚያስ HIV career ነው፡፡ ይኼን ሳታውቂ ከሆነ የገባሽበት ከአሁኑ መንገድሽን እንድታስተካክዪ ነው፡፡ ያው ግንኙነታችሁ የአጭር ጊዜ ስለሆነ ሌላ ነገር ውስጥ የገባችሁ አይመስለኝም፡፡››
‹‹ቆይ ግን አንቺ እንዴት አወቅሽ? ማለቴ እሱ እንደዛ እንደሆነ!››
‹‹ይኸውልሽ እሱ እዚህ መስሪያ ቤት ወጣት ሆና የገባች ሴት አንድም አታልፈውም ነበር፡፡ ሲበዛ ሴሰኛ ነገር ነው፡፡ እኔም ስቀጠር እንደዚሁ ሊያሰምጠኝ ሞክሮ ነበር፡፡ ግን እኔ የዛኔም ቀለበት አስሬ ለማግባት የቀረኝ ጥቂት ቀን ስለነበር ፊት አልሰጠሁትም፡፡ እሱም ቀለበት እንዳሰርኩ ሲያውቅ ተፋታኝ! እና የገባውን ሰራተኛ ሁሉ በአጉል ጀብደኝነት ካልቀመስኩ ሲል ውጪም ጠጥቶ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር ሲልከሰከስ ነው የያዘው! አንዷን ከኔ በፊት የገባች ፋይናንስ ክፍል የምትሰራ ልጅ እንደዚሁ አሰማምጦ ቤቱ ወስዷት ቤቱ ውስጥ የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት ምናምን አየች፡፡ ከዛ ደግሞ ስትበረብር የኤች አይ ቪ ህሙማን ማህበር የአባልነት መታወቂያውን አገኘች፡፡ ከዛ መታወቂያውን ፎቶ አነሳችና ለግቢው ሰራተኞች ለምታውቃቸው ላከችላቸው፡፡ እያለ እያለ ሙሉ ግቢው አወቀ፡፡ እሱም ከዛ በኋላ በግልጽ የኤች አይ ቪ ቀን እዚህ ግቢ ሲከበር ምናምን ያስተምራል ነገር! አሁን አሁን እየቆየ ሲመጣ ሰዉ ተላመደውና ተረሳ እንጂ የገባ ሰራተኛ ቀድሞ የሚነገረው ይኼ ነበር፡፡ ያንቺን ግን ገና እንደገባሽ ፍቅረኛዬን አስቀጠርኳት ብሎ ቀድሞ ነበር ያስወራው፡፡ ደግሞም ትመስሉ ነበር፡፡››
ናርዶስ ሰማይ ከአናቷ ላይ የተደፋባት ያህል አዘመመች፡፡ ዝም ፣ ጭጭ! አስር ደቂቃ ፣ አስራ አምስት ደቂቃ ፣ ሀያ ደቂቃ! ዝም እንዳሉ ነጎደ፡፡ በእነዚህ ደቂቃዎች ላለፉት ስድስት ወራት የተካሄደውን ሁሉ እየተመለከተችው ነበር፡፡ ሜላት ትዕግስቷ ሲያልቅ ዝምታውን ለመስበር ሞከረች፡፡ ወንበሯን ወደ ናርዶስ በደንብ አስጠግታ አይኖቿን እያየች ማውራት ጀመረች፡፡
‹‹ናርዲዬ አብራችሁ ተኝታችኋል እንዴ?››
‹‹በጣም ብዙ ጊዜ!›› ናርዶስ ፊቷ ፍም መስሏል፡፡ እንባ እንኳን ማፍሰስ አልቻለችም፡፡
‹‹በጣም ቸኮልሽ ናርዲዬ! Whatever ግን በኮንዶም ነበር የምትወጡት አይደል?››
‹‹አይደለም ሁሉንም ቀን በባዶ ነበር ያደረግነው!›› አሁን ፊቷ በእንባ መራስ ሰውነቷ መንዘፍዘፍ ጀምሯል፡፡ ሜላትም አቅፋት ማንባት ጀመረች፡፡
‹‹አንቺ የተማርሽ አይደለሽ እንዴ ናርዲዬ እንዴት ሳትመረመሩ ያለኮንዶም አብረሽው ትወጪያለሽ?››
‹‹እኔ …… (ተንሰቀሰቀች) ….. HIV? …. የጠፋ ነበር የሚመስለኝ! አንድም ቀን ትዝ ብሎኝ አያውቅም!››
‹‹ከሚዲያ ላይ ጠፋ እንጂ እኮ ሀገራችን ውስጥ ወረርሽኝ በሚመስል መልኩ እየተስፋፋ ነው፡፡ ለማንኛውም ቶሎ ብትመረመሪ ነው የሚሻለው!››
‹‹እና ምን በድዬው ነው እኔን ማስያዝ የፈለገው? እንዴት ያለ ራስወዳድነት ነው ይኼ?››
ረዥም ሰዓት ናርዶስ እየተንሰቀሰቀች ሜላት ስታባብላት ከቆየች በኋላ ናርዶስ አልቅሳ ሲደክማት ጥያቄ መጠየቅ ጀመረች፡፡
‹‹እናንተ ታዲያ ለምን እስካሁን አልነገራችሁኝም?››
‹‹አንቺም እንዳለብሽ ነው የነገረን ደግሞ ገና መቀጠርሽን ሳናውቅ ማውራት ስለጀመረ አመንነው፡፡ እንጂ እንዲሁ ከገበያ ጥናት ክፍል ተነስቶ ኢንጅነሪንግ ሴክሽን ድረስ የሄደ አልመሰለንም ነበር፡፡››
‹‹እና አሁን ምንድነው የሚሻለኝ?›› እንባዋን በመዳፏ በጠረገችበት ቅፅበት ተመልሶ ይፈስሳል፡፡
‹‹መተኛት ከጀመራችሁ ሶስት ወር ይሆናል?››
ናርዶስ ጥቂት እንደማሰብ ካለች በኋላ ‹‹ይሆናል!›› አለች፡፡
‹‹ይኼን ያህል ጊዜ ከሆነው ብትመረመሪ ጥሩ ነው፡፡ ከጅምሩ የሆነ እርምጃ መውሰድ ትችያለሽ!››
ሜላት ስልኳ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡ ‹‹ባሌ ጋ ልደውልለት አንዴ!›› አለችና ስልኳን አንስታ እየደወለች ወደ ውጪ ወጣች፡፡ ናርዶስ ይኼን ጭንቅ ለማን እንደምታዋየው ግራ ገብቷት ስታሰላስል ብትቆይም ከሂባ ውጪ የመጣላት ሰው አልነበረም፡፡ እንባዋን ለመጥረግ እየሞከረች ሂባ ጋር ለመደወል ስልኳን ስታነሳ ኤርሚያስ ደወለ፡፡ ውስጧ እልህ እየተንቀለቀለ ስልኩን አነሳችው፡፡
‹‹ሄሎ የኔ ማር ሰላም ዋልሽልኝ?›› ኤርሚያስ እንደሁሌው እየተቅለሰለሰ ንግግሩን ጀመረ፡፡
‹‹ምን በድዬህ ነው ግን ኤርሚ?

ልብ - ወለድ

07 Dec, 05:54


ርታ! ግን አሁን የተሻለ ነገር እንገንባ! ተረዳኝ! አፈቅርሀለሁ!››
‹‹ብረዳሽ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም!››
‹‹ማለት?›› ከእቅፉ ተመንጭቃ ወጣችና አፈጠጠችበት፡፡
‹‹ማለት ማለት?››
‹‹አታገባኝም?››
‹‹ውስጤ አልተረጋጋም በዚህ ሰዓት ምንም ልልሽ አልችልም!››
ቀመር እንባዋ ፊቷ ላይ እየተንዠቀዠቀ ቀጠለች፡፡ ‹‹ወንድ ሁሉ አንድ ነው ሲባል ውሸት ይመስለኝ ነበር፡፡ አንተም ከሌሎቹ በምንም አትሻልም፡፡ ስሜትህን ካረካህብኝ በኋላ ልትወረውረኝ ነው ፍላጎትህ!››
‹‹እኔ ከጅምሩ ስሜቴን ላረካ አልቀረብኩሽም! ከገባሽ አንቺው ነሽ የደፈርሽኝ! ማልቀስ ደግሞ መፍትሄ አይሆንም!››
‹‹በጣም ጥሩ ስህተታችንን እንድናርም ፈቃደኛ ካልሆንክ ሌላ ስህተት እንቀጥላለን! አየህ አይደል በፍቅር እጅ አትሰጥም ሀይል ብቻ ነው የሚገዛህ! እኔማ የፍቅር ሰው ትመስለኝ ነበር፡፡››
‹‹እሱን ለመመስከር ካንቺ ይልቅ ሂባ ትሻላለች! ሳፈቅር የምታውቀኝ እሷ ናት!››
የተፈጠረውን የመካረር ስሜት ለማብረድ ፈለገች፡፡ ተመልሳ ወደ እቅፉ ገባች፡፡ ‹‹ስለማፈቅርህ እኮ ነው! እሺ በለኝ እና ደስተኛ ሆነን እንኑር!››
‹‹ቀመር እኔ አብረን እንድንተኛ እንኳ አልፈልግም እኮ! ግን አንቺ ስትመጪ እምቢ ማለት አይሆንልኝም! ራሴን እንደዚህ ያለ ቆሻሻ ቦታ አገኘዋለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም! ለዚህ ደግሞ ምክንያቷ አንቺ ነሽ! ልንገርሽ አይደል እንደውም ከዚህ በኋላ ቤቴ እንድትመጪ አልፈልግም! ከዚህ በላይ መቆሸሽ አልፈልግም በቃኝ! በቃኝ!››
ለመጀመሪያ ጊዜ ስትስመውም ሆነ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ስትገፋፋው ወዲያው ተፀፅቶ ያገባኛል የሚል እሳቤ ነበራት፡፡ ነገሩ ግን የተገላቢጦሽ እየሆነ ፣ ኢምራን ትዳርን እየሸሸ ፣ ለሷ የነበረው መውደድ እንኳ ተሸርሽሮ ቤቴ ድርሽ እንዳትይ ማለት ጀመረ፡፡ በፈጣሪዋ ዘንድ ድንበር አልፋ ልታገኝ ያሰበችው የደስታ ህይወት ገና ከጅምሩ እየራቃት ነው፡፡ እቅፉ ውስጥ እንዳለች ከዚህ ቀደም የሰማችው የነብዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) ንግግር ትዝ አላት፡፡ ‹‹አላህ አንድን ባሪያውን ሲወደው ለጅብሪል ጅብሪል ሆይ እኔ ይኼን ባሪያዬን ወድጄዋለሁ አንተም ውደደው ይለዋል፡፡ ጅብሪል ደግሞ ለመልዓክቱ ጌታችሁ ይኼን ባሪያ ወዶታል እናንተም ውደዱት ይላል፡፡ ከዚያም አላህ በምድር ያሉ ሁሉ እንዲወዱት ያደርጋል፡፡ ሲጠላም በተመሳሳዩ ነው›› እናም ምናልባት በነበረችበት ጌታዋን የማስደሰትና ወንጀልን የመራቅ መንገድ ላይ ቀጥላ ቢሆን ለሷ ያለውን ጊዜው ሲደርስ ታገኝ ነበር፡፡ ጌታዋን አስከፍታ ከኢምራን ልታገኝ የፈለገችው ፍቅር በጌታዋ ይሁንታን ያገኘ አይመስልም!
‹‹እሺ ጥሩ …. (እንባዋ አይኗን እየሞላ ይፈሳል) … እስኪ ኢምሩ ንገረኝ ከኔ ምኔን ነው የጠላኸው?›› ውስጧ ላይ የርካሽነት ንፋስ ይነፍሳል፡፡
‹‹አንቺን በአንቺነትሽ አልጠላሽም፡፡ አንቺን የምጠላሽ የወንጀለኛው እኔነቴ አካል በመሆንሽ ብቻ ነው፡፡››
‹‹አተርፍ ባይ አጉዳይ ነዋ የሆንኩት!›› እንባዋ ፊቷን ማርጠቡን ቀጠለ፡፡ ድሮ ገና ፊቷ ሲቀየር እንኳ ይደነግጥ ነበር፡፡ አሁን ግን እንባዋ ሲንዠቀዠቅ እንኳ ግድ አይሰጠው ጀምሯል፡፡
***
ይቀጥላል…

@Lib_Weled

ልብ - ወለድ

07 Dec, 05:53


የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አስራስምንት
(ፉአድ ሙና)
.
ናርዶስ የወሲብ ፊልም የማየት ሱሷን ለመግታት እጅጉን ከራሷ ጋር ትግል እየገጠመች ነው፡፡ ሂባ ፊልም በፍላሽ የሚጭኑ ቤቶች እየሄደች የሆሊዉድ ኮሜዲ ፊልሞችን እያስጫነች ታመጣላታለች፡፡ ናርዶስ ብትጨክን ብትጨክን በሳቅ አትጨክንምና የወሲብ ቪዲዮ በምታይባቸው ጊዜዎች ኮሜዲ ፊልሞችን ማየት ጀምራለች፡፡ ግን እንዲሁ በአንዴ እርግፍ አድርጋ ልትተወው ከብዷታል፡፡ ሂባ ሁሉንም ነገር ችላ ብላ ናርዶስን መልሶ በመስራቱ ጉዳይ ላይ ትኩረቷን አድርጋለች፡፡ የናርዶስ ስልክ እና ላፕቶፕ ላይ የነበሩትን የወሲብ ፊልሞች ሂባ ሙሉ ለሙሉ ስላጠፋቻቸውና በየቀኑም ስልኳን ስለምትፈትሽባት ማየት ብትፈልግ እንኳ ቢሮ ስትሄድ በኤርሚያስ ስልክ የማየት እድል ብቻ ነው ያላት፡፡ እጅጉን ከብዶ የከበዳት ከኤርሚያስ ጋር ያላትን የአልጋ ግንኙነት የመቋጨቱ ጉዳይ ነው፡፡ ልትጠላው አልቻለችም፡፡ ወንዳ ወንድ ቁመናውን ….. ያስለመዳትን አጓጉል ነገር … ብቻ በቃኸኝ ለማለት ብትፈልግም አልቻለችም፡፡ ቢሮ እየመጣ ከአንገት በላይ ሰርቷት ይሄዳል፡፡ በእርግጥ እንደድሮው ፊልሞችን አያመጣላትም፡፡ ምክንያቱም ፊልሞቹ እንዲያደርሷት የፈለገበት ቦታ ደርሳለታለች፡፡ እንደቀድሞው በየቀኑ ባይሆንም በሳምንት ሁለት ቀን እሱ ቤት ሄዳ የለመዱትን ይፈፅማሉ፡፡ ለሂባ ግን እሱ ቤት እንደምትሄድ አትነግራትም፡፡ ዛሬ ከስራ እንደወጣች ከኤርሚያስ ጋር ተያይዘው እሱ ቤት ሄዱ፡፡ ሰዓቱ መሸት ወደማለቱ እየተጠጋ ነበር፡፡ መንፈራገጡ ሲያበቃ አልጋው ላይ እንደተጋደሙ ማውራታቸውን ቀጠሉ፡፡ እሷ በጊዜ መሄድ አለባት፡፡
‹‹ስማ postpill አላለቀም አይደል?››
‹‹እስኪ እሱ መሳቢያ ውስጥ ፈልጊ!››
ማርገዝን እጅጉን ትፈራዋለች፡፡ አረገዘች ማለት ጉዷ ሁሉ ተዘረገፈ ማለት ነው፡፡ የአልጋውን ኮመዲኖ ስትከፍተው ብዙ አይነት ክኒኖች ተመለከተች፡፡ ጫፍ ላይ pospill ስላገኘች ኮመዲኖውን ዘጋችና የመኝታ ክፍሉ በር አካባቢ መሬት ላይ ከተቀመጡት የታሸጉ ውሀዎች አንዱን አንስታ ክኒኑን ዋጠች፡፡
‹‹አንተም የወሊድ መቆጣጠሪያ ትወስዳለህ እንዴ? ምንድነው ይሄ ሁሉ ክኒን?››
‹‹ባክሽ የቆዩ ናቸው፡፡ ዛሬ ለምን እዚህ አታድሪም?››
‹‹ያምሀል እንዴ! አሁን ራሱ ላመሸሁበት ሰበብ መፈለግ አለብኝ!››
‹‹አንቺ ደግሞ ስታካብጂ ነው እንጂ አሁን እኮ ብዙ አልቆየሽም፡፡ ሰበብ የሚያስፈልገው አይነት አይደለም፡፡››
ልብሷን ለባብሳ ስትጨርስ ሊሸኛት ተከትሏት ወጣ፡፡ የውስጥ ለውስጥ መንገዱን ጨርሰው ሜክሲኮ ጋር ሲደርሱ አንድ የስራ ባልደረባቸውን አገኙ፡፡ የኤርሚያስ ቢሮ ውስጥ ነው የምትሰራው፡፡ ከልጅቷ ጋር ሰላም ተባብለው ከተሰነባበቱ በኋላ የፒያሳ ታክሲ ተሰለፉ፡፡ ሰልፉ ረዥም ነበር፡፡ ግን ማለቁ አይቀርም፡፡ ህይወትም እንደዛው ናት፡፡ ረዥም ብትመስልም ማለቋ አይቀርም፡፡
*
ሂባ የናርዶስ ነገር ራስምታት እየሆነባት ነው፡፡ ቀን ከሌት የቀድሞዋ ናርዶስን ለመገንባት የሚያስችሏትን መንገዶች ታሰላስላለች፡፡ ናርዶስ አብዛኛውን ሰዓቷን መስሪያ ቤት ማሳለፏ ደግሞ ለሂባ ትልቅ እንቅፋት እየሆነባት ነው፡፡ በሂባ እጅ ትነፃና እዛ ሄዳ በኤርሚያስ እጅ ትጨቀያለች፡፡ ሂባ ቤት ተቀምጣ ቴሌቪዥን እያየች ነበር፡፡ ከእነርሱ ቤት ፊት ለፊት ያለው ቤት የሚኖሩት ጎረቤታቸው ወ/ሮ ገነት መጡ፡፡ የሂባን ለመፋታት መንገድ ላይ መሆን ከራሷ እና ከናርዶስ ቤተሰቦች በቀር የሚያውቅ አልነበረም፡፡ ገና እንደገቡ ሰላምታ እንኳ ሳያስቀድሙ ‹‹ወይኔ ሂባዬ ለካ ከባልሽ ጋር ተጣልተሽ ነው የመጣሽው! እኔ እኮ ስለደረስሽ ልትታረሺ መስሎኝ ነበር፡፡›› አሉ፡፡ ሂባ ከየት እንደሰሙ ግራ ገባት፡፡
‹‹ማነው እንደዛ ያለው?››
‹‹ውይ አሁንማ ሁሉም አውቆ የለ እንዴ! አንቺ ግን ምነው ከኛ ይደበቃል ይኼ? እኔስ ብሆን እናትሽ አይደለሁ!››
‹‹ይኼ እኮ ደስ የሚል ነገር አይደለም! ደግሞ ጊዜው ሲደርስ ማወቅዎ አይቀርም ነበር፡፡››
‹‹ይሁን እስኪ! እና መች ነው የፍርድ ቤት ቀጠሮው? ያለውን ንብረት ሙሉ ለሙሉ ነው አይደል የሚያካፍሏችሁ?››
‹‹ኧረ ገንዬ የምን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ፣ የምን ንብረት ነው?››
‹‹እንዴ የሰፈሩ ሴት ሁሉ ቤተሰቦቿን ልታስከብራቸው ነው ስላረገዘች የመኪና መሸጫው ለሷ ሊፈረድ ይችላል እያለ አይደል እንዴ?››
‹‹እንደሱ ብሎ ነገር የለም፡፡ ወሬ ነው፡፡›› ሂባ ውስጧ እያረረ ነው፡፡
‹‹አዪ ተይው ተይው! ገና ለገና የሆነ ገንዘብ ትጠይቀኛለች ብለሽ ነው አይደል? ድሮም ሰው እኮ ገንዘብ ሲያገኝ መቀየሩ አዲስ አይደለም!›› ወ/ሮ ገነት ከተቀመጡበት ተነስተው ቤቱን ለቀው ወጡ፡፡
ሂባ የወሬው መናፈስ ግርም እያላት ትኩረቷን እየተመለከተችው ወደነበረው የቴሌቪዥን ዝግጅት ለመመለስ ሞከረች ግን አልቻለችም፡፡ ገንዘቡን ፈልጋ ተፋታች ይሉኛል የሚለው ስጋት ውስጧን ይረብሸው ነበር፡፡ ሰው የራሱን ህይወት ትቶ በሌሎች ሰዎች ህይወት ዙሪያ የማያውቀውን ሲቀባጥር ስትመለከት ቀፈፋት፡፡
*
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሁለተኛው መንፈቅ አመት የትምህርት መርሀ ግብር ተጀምሯል፡፡ ቀመር ቀደም ብላ ለኢምራን ገብታው በነበረው ቃል መሰረት civil engeenering ከመግባት ተቆጥባ biomedical engeeneringን መርጣ ተመድባለች፡፡ የየካቲት ወር ተጠናቆ የመጋቢት ወር ስለተጋመሰ ትምህርቱም በአግባቡ እየተሰጠ ነው፡፡ ቀመር እና ኢምራን ሳያስቡት የወደቁበት የስሜት አረር በዘላቂነት እየተንቀለቀለ ነው፡፡ አብረው ከተኙ በኋላ በጣሙን ተፀፅቶ ነበር፡፡ እሷም ያጠፋችው ጥፋት አሟታል፡፡ ግን ሁለቱም ሲገናኙ ፀፀታቸውን ረስተው ድጋሚ ስሜታቸውን ይከተላሉ፡፡ ኢምራን የማያውቀውን መጥፎ ነገር ለምዶ ያቅበጠብጠዋል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ፀፀቱ መፈጠሩን እስኪጠላ ድረስ ያይልበታል፡፡ ከመጀመሪያዋ መንፈራገጥ ወዲያ ቀመር አብዛኛውን ቀን እሱ ጋር ማደር ጀምራለች፡፡ ዛሬም ምሽቱን አብረው ናቸው፡፡ ትግሉ በሁለቱም አሸናፊነት ሲጠናቀቅ እቅፉ ውስጥ እንዳለች አንሾካሾከች፡፡
‹‹ኢምሩዬ!››
‹‹ወዬ››
‹‹ትወደኛለህ?››
‹‹እኔንጃ! ይመስለኛል!››
‹‹ጉረኛ እኮ ነህ!››
‹‹አይመስለኝም!››
‹‹እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምንቀጥለው? ለምን ኒካህ አናስርም?››
‹‹ለምንድነው የምናስረው?››
‹‹እንዴ! እኔ የማውቀው ኢምራን እንደዚህ አይልም! አሁን የምንሰራው እኮ ወንጀል ሆኖ ይመዘገብብናል፡፡ ሚስትህ ስሆን ግን እንደውም ምንዳ እናገኝበታለን፡፡ ደግሞ ልጅም እወልድልሀለሁ፡፡››
‹‹ተይ ይሄ ባንቺ አፍ አያምርም፡፡ ራሴን ከዝሙት በብዙ ርቀት ጠብቄ የነበርኩትን ልጅ ገፍትረሽ ካሰመጥሽኝ በኋላ እጅሽን ተጣጥበሽ ልትሰብኪኝ አትሞክሪ!››
‹‹ለምን ተስፋ ትቆርጣለህ? ተፀፅተን መንገዳችንን ካረምን እኮ አላህ ይቅር ይለናል!››
‹‹ወንጀል ውስጥ ሆነ ብለሽ እንድንገባ ካደረግሽ በኋላ ይምረናል ስትዪ ትንሽ አይሸክክሽም? ይምረኛል ብሎ ወንጀል መስራት በጣም ያስቃል፡፡››
‹‹ከዚህ በፊት ለነበረው እኔ ተጠያቂ ልሆን እችላለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ላለው ግን ተጠያቂው አንተ ነህ! ህጋዊ እንድናደርገው እየለመንኩህ ነው፡፡››
‹‹ታውቂያለሽ ….. ድሮ እንደ ትዳር የሚያጓጓኝ ነገር አልነበረም፡፡ አሁን ግን ያስፈራኛል፡፡ ደግሞ …….. መሰረቱ ወንጀል የሆነ ትዳር እንዲኖረኝ አልፈልግም፡፡››
‹‹ገብቶኛል የትም መሄጃ እንደሌለኝ ስለምታውቅ ነው እንደዚህ የምትንጠባረርብኝ! …………. አዎ አጥፍቻለሁ አልኩኝ እኮ! …… የኔ ላደርግህ ጓጉቼ መሄድ ባልነበረብኝ መንገድ ሄጃለሁ! ለሱ

ይቅ

ልብ - ወለድ

06 Dec, 17:44


ላ አንስታ ለበሰች፡፡ ሙሉ ለሙሉ ራቁቷን ነበረች፡፡ አንሶላውን ተጋራት፡፡ ዝም እንዳሉ መሸ፡፡ አስር የለ፣ መግሪብ የለ ፣ ኢሻ የለ ….. ዝም! ሁለቱም ልብ ውስጥ በዚህ ሁኔታ ፈጣሪ ፊት የመቆም ድፍረት የለም፡፡ ዝምታው ሲደክማት ተጠግታ ተለጠፈችበት፡፡ አቀፋት፡፡
‹‹ኢምሩዬ አፈቅርሀለሁ እሺ!››
‹‹እኔም እወድሻለሁ!››
‹‹የምርህን ነው?››
‹‹ይመስለኛል! ባልወድሽ ይህን ያህል አልቀርብሽም ነበር፡፡››
ፊቷ ላይ የደስታ ብርሀን በራ፡፡ እንዳታልፈው እስኪሰጋ ድረስ ተለጠፈችበት፡፡ የወደደችውን ስላገኘች ….. ህይወቷን ልትሰጠው የምትፈልገው ሰው ስለተቀበላት ….. ደስ ብሏታል፡፡
‹‹ግን ቀሙ ትክክል ያልሆነ ነገር አለ አይደል?››
‹‹የቱ?››
‹‹አሁን ካንቺ ጋር መተኛቴ!››
‹‹በጣም ይቅርታ ኢምሩዬ! አማራጭ የነበረኝ አልመሰለኝም!››
ቀና ብላ ከንፈሩን ሳመችው፡፡ መፀፀት የጀመረው ያገኘው እርካታ አልቆበት ከሆነ ብላ ማደንዘዣዋን ደገመችው ….. ሳመችው፡፡ በጣም ደካማ ነበር፡፡ ስትስመው ተመልሶ ስሜቱ ውስጥ ሰጠመ፡፡ የፍራሿ ስቃይ ቀጠለ፡፡ እሱም ሆነ እሷ በፍፁም ራሳቸውን በዚህ አይነት ወራዳ ተግባር ውስጥ እናገኛለን ብለው አስበው አያውቁም፡፡ ጭንቅላቷን ተጠቅማ እያሸነፈች ነበር፡፡ አሁን ግን በአቋራጭ ለማሸነፍ ብላ ሴትነቷን ተጠቀመች፡፡ ሴት ልጅ መሸነፍ የምትጀምረው ሴትነቷን መጠቀም ስትጀምር ነው፡፡ ዛሬ ኢምራን ተደፈረ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ መድፈር በጉልበት ማነቅ ብቻ አይደለም፡፡ እንዲህ በውበት ሀይል …. እንዲህ በስሜት ሀይል አስገድዶ እጅ እንዲሰጥ ማድረግም መድፈር ነው፡፡
ጠዋቱን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ሁለት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ ቀመር የወር አበባ ላይ ሆና ሰላት የማትሰግድባቸው ቀናትን እንኳ ልምድ ሆኖባት በንጋት ስግደት ሰዓት ትባንን ነበር፡፡ ኢምራንም የሷው ቢጤ ነው፡፡ ወንጀል ፤ ሰሪውን ከመልካም ስራ እንደምትከለክል ለመረዳት የሻ ሰው ሁለቱን መመልከት ይበቃዋል፡፡ የትናንትናው ወንጀላቸው ከስግደት ሲከለክላቸው … ደነገጡ፡፡
‹‹ሁለት ሰዓት ሆኖ ነው?›› ቀመር ሰውነቷን በአንሶላው እንደጠቀለለች ስልኳን ፈልጋ ስትመለከት ማመን ከብዷት የጠየቀችው ነበር፡፡
‹‹ማለት ነዋ እንግዲህ! ምነው ደነገጥሽ?››
‹‹ፈጅር ሳንሰግድ ብዬ ነዋ!›› ፈጅር ጎህ ሲቀድ የሚሰገደው የንጋት ስግደት መሆኑ ነው፡፡
‹‹ትናንት አስር ፣ መግሪብ እና ኢሻም አልሰገድንም ከረሳሽው ላስታውስሽ!››
ቅስሟ ስብር እንዳለ ወደ ፍራሹ ተመለሰች፡፡ ገና ለስግደት ብቁ ለመሆን ጀናባ ማውረድ የሚባለው መስፈርት ይቀራቸዋል፡፡ ገላቸውን መታጠብ አለባቸው፡፡ ያኔ ጀናባቸው ወረደ ይባላል፡፡ ኢምራን ከወ/ሮ አርሴ መዘፍዘፊያ ተውሶ ቀመር ቤቱ ውስጥ ገላዋን እንድትታጠብ እሱ ደግሞ ግቢው ውስጥ እንደነገሩ በቆርቆሮ የታጠረችው ክፍል ውሀ ይዞ ሄዶ ለመታጠብ አሰበ፡፡ ቱታውን ለብሶ ወደ ወ/ሮ አርሴ ቤት ሲሄድ ወ/ሮ አርሴ እና ሌሎች ተከራዮች ቤቱ ውስጥ ሲሰራ የነበረውን ወንጀል ያወቁ ፣ ያወቁ እየመሰለው ያፍር ነበር …. እነሱ ግድ ይሰጣቸው ይመስል ይጠራጠራቸዋል! የሚመለከተው ….. ከመመልከት ምንም የማይጋርደው ጌታው ግን ያልተፈቀደለትን ቀለበት በማህተሙ ሲዘጋ እየተመለከተው ነበር፡፡ እሱ ያውቃል …. እሱ ተወንጅሏል ….. ግን ምንም አላለም! አይቸኩልማ!
.
ይቀጥላል …

@Lib_Weled

ልብ - ወለድ

06 Dec, 17:43


የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አስራሰባት
(ፉአድ ሙና)
.
ቀመር ለአስራ አምስት ቀናት ያህል የትውልድ ከተማዋ ሀላባ ላይ ከቤተሰቦቿ ጋር ከቆየች በኋላ ውዷን ለማግኘት በናፍቆት እየተሳከረች ወደ ሀዋሳ አቀናች፡፡ ኢምራን ለአንድ ሳምንት ያህል ደሴ ደረስ ብሎ እንደተመለሰ መጀመሪያ ያሳወቃት ለቀመር ነበር፡፡ እሷም በተነጋገሩት መሰረት ይኸው ከተፍ አለች፡፡ ለሁለተኛው የትምህርት መንፈቅ አመት የሚያስፈልጓትን እንደ በሶ እና ሌሎች መሰል ግብዓቶችን ሳትይዝ ነበር የመጣችው፡፡ ገና በመጀመሪያው ሴሚስተር የፍሬሽነት ካባው ሙሉ ለሙሉ ከላይዋ ላይ ተገሽልጦ ሳይወርድ አልቀረም፡፡ ልጅቷ በጣም ፈጣን ናት፡፡ አውቶብስ ተራ ስትደርስ ኢምራን ቀድሞ ደርሶ መምጣቷን እየተጠባበቀ ነበር፡፡ ለኢምራን የራሱ ለውጥ በጣም እየገረመው ነው፡፡ በቻለው መጠን ይገፋት እንዳልነበር አሁን በሷ የፍጥነት መጠን እሱም እየተጠጋት ያለ እየመሰለው ነው፡፡ አውቶብስ ተራው ጋ ያለች ትንሽዬ ሻይ ቤት ውስጥ ተቀምጦ ቡና እየጠጣ ደሴ ሲሄድ እናቱ የተማፀኑት ተማፅኖ አይኑ ላይ ድቅን አለበት፡፡ የሂባ ክህደት በጣም እንደጎዳው ያውቃሉና ቢያንስ እሷን የምታስረሳ ሴት ፈልጎ እንዲያገባ ካልሆነም እሳቸው የሚያመጡለትን እንዲቀበል ተማፅነውት ነበር፡፡ እንደምንም ‹‹እኔው ያሰብኳት አለች!›› ብሎ ተፋታቸው እንጂ በእርሳቸው አያያዝ እዛው ተድሮ መምጣቱ ነበር፡፡
ከሚኒባሱ እንደወረደች ደወለችለት፡፡ ሂሳቡን ከፍሎ ፈጠን ፈጠን እያለ ወደ መናኸሪያው ገባ፡፡ ወደሷ ሲመጣ ስታየው ፊቷ በብርሀን ፈገግታ ተሞላ፡፡ ወገቧ ላይ የተሸከመችው ተለቅ ያለ ቦርሳ ፣ በእጇ ያንጠለጠለችውን ፌስታል ሲያይ … እንዲሁ በብርሀን እንደተጠመቀች ወደ ህዋ ልትመጥቅ መሰለው፡፡ ፈገግ ለማለት ሞከረ፡፡ ወደሷ ተጠግቶ በእጇ የያዘችውን ፌስታል ተቀበላትና ቦርሳዋን ከወገቧ ላይ አንስቶ አዘለው፡፡
‹‹ቢያንስ ፌስታሉን እኔ ልያዘው!››
‹‹ቀላል ነው እኮ! ቦርሳውም ፌስታሉም አይከብድም! ይኼ ብቻ ነው ልብስሽ?››
‹‹ውይ አንተ ደግሞ ልብሴማ ዶርም ነው ያለው! ይህቺ ለአስራአምስት ቀን ይበቃኛል ብዬ ይዣት የሄድኩት ናት!››
‹‹በለው አሰብኩት እኮ ዶርም ያለው ሻንጣ ደግሞ ምን እንደሚያክል!››
ከመናኸሪያው ከወጡ በኋላ ኢምራን ሰረቅ አድርጎ አያትና ‹‹አሁን የት ነው የምንሄደው?›› አለ፡፡
‹‹ኮተቴን ዶርም ላስቀምጥ እና ምሳ እንብላ!››
‹‹ምሳ አሪፍ ድንች ወጥ ሰርቻለሁ ቤት እንበላለና?››
‹‹መችስ ድንቹ ተበጥብጧል አይደል?›› ተሳሳቁ፡፡
እየተቀላለዱ የቴክኖ ግቢ በር ጋ ሲደርሱ ኮተቷን ይዛ ገባች፡፡ ዶርም አስገብታ እስክትመለስ እሱ በር ጋር ቆሞ ጠበቃት፡፡ ከዶርሟ ልጆች ውስጥ ማንም የተመለሰ አልነበረም፡፡ ገና ለምዝገባ አንድ ሳምንት ይቀራል፡፡ ኮተቷን አስቀምጣ ከተመለሰች በኋላ ተያይዘው ወደ እሱ ቤት አቀኑ፡፡
ቤት ደርሰው ወጡን እያሞቀ ‹‹ታውቂያለሻ ግን እኔ ድሮ ረጋ ያለች ሴት ነበር የምወደው!›› አለ፡፡
ቀመር እየሳቀች አየችው፡፡ ‹‹እና አሁን ምን አይነት ሴት ወደድክ?››
‹‹ማለቴ አሁን እንዳንቺ ፈጠን ፈጠን የሚሉ ሴቶች አልወድም ነበር፡፡ የሆነ ዱርዬ ምናምን ነበር የሚመስሉኝ!››
‹‹እና አሁንስ?››
‹‹አሁንማ ላይሆኑ እንደሚችሉ ባንቺ እያየሁ ነው፡፡››
‹‹ታውቃለህ ቤት በጣም ነው የሚፈሩኝ! ከሰው ጋር መቀራረብ ስለማበዛ ምናምን በተለይ ከወንድ ጋር ስለምቀራረብ መጥፎ ነገር ላይ እንዳልወድቅ ይፈራሉ፡፡ ለዛ ነው ሁሌ ሊድሩኝ የሚፈልጉት፡፡ አሁን ራሱ ለክረምት ስመለስ ወይ እኔ ያመጣሁትን ወይ እነሱ የመረጡትን ለማግባት ቃል አስገብተውኝ ነው የመጣሁት!››
‹‹እና ክረምቱን ሰርግ ልታበይኝ ነዋ!››
‹‹ታዋጣለህ እንጂ አዎ!›› ሳቀች፡፡
‹‹ስሚ ደግሞ ሳልነግርሽ ሂባዬ ደውላ ረዥም ሰዓት አወራን እኮ!››
‹‹ከባለፈው በኋላ?›› ውስጧ እየተቃጠለ ነው፡፡
‹‹አዎ!››
‹‹እና ስለልጇ ምን አለችህ? ባሏ ነው ወይስ አንተ ስም የምታወጡለት?››
‹‹ስለሱ እንኳ አላወራንም ግን ለጓደኛዋ ምክር ቢጤ ፈልጋ አማከርኳት!››
‹‹ጓደኛዋ ምን ገጥሟት?››
ሂባ የነገረችውን አንድም ሳያዛንፍ ነገራት፡፡ ፊቷ ተቀያየረ፡፡ የነገረችው የሁለቱን ታሪክ እንደሆነ ለመረዳት ቅፅበት አልወሰደባትም፡፡
‹‹ምነው ቀመር? አመመሽ እንዴ?›› የፊቷ መቀያየር አስደንግጦታል፡፡
‹‹አይ ደህና ነኝ! እና እጮኛ ይዘሀል ወይ አላለችህም?››
‹‹ብላኛለች እንዴት አወቅሽ?››
‹‹ያው ሴት አይደለሁ! ልትልህ የምትችለው አይጠፋኝም!››
‹‹በለው ጉራ!››
‹‹ከዛ በኋላ ሌላ ምንም ነገር አልነገረችህም አይደል?››
‹‹አዎ በቃ የነገርኩሽን ብቻ ነው ያወራነው፡፡››
ወጡን ጨልፎ ያዘጋጀውን ምሳ አቀረበ፡፡ ቀመር በልቧ ሂባን እንዴት መቅደም እንዳለባት ታሰላስላለች፡፡ ምግብ የመብላት ፍላጎቷ ትቷት ተነነ፡፡
‹‹ቀሙ ሰላም ነሽ ግን? እየበላሽ እኮ አይደለም!››
‹‹ሰላም ነኝ …. አንተ ግን ለኔ ….›› የጀመረችውን መጨረስ አቃታት፡፡ ጭንቅላቷ ውስጥ የሊዲያ ምክር አቃጨለ፡፡ ‹‹እወድሀለሁ እንዳትይው ዝም ብለሽ ከንፈሩን ሳሚው!›› የሷ እቅድ በዚህ መልኩ የነበረ ባይሆንም የሂባ ፍጥነት እጅጉን ስላስፈራት የማታምንበትን ነገር ለማድረግ አሰበች፡፡ ‹‹ብስመው ምን ይለኛል? ከቤት ያባርረኛል? ወይስ መልሶ ይስመኛል?›› ከራሷ ጋር ሙግት ገጠመች፡፡
‹‹ቀሙ የተፈጠረ ነገር ካለ ንገሪኝ አታስጨንቂኝ! ምግቡ አልተመቸሽም?››
‹‹አጉርሰኝ!›› ቁጣ የቀላቀለ ትዕዛዝ ነበር፡፡ ኢምራን ደንግጧል፡፡ እጁ ላይ ይዞት የነበረውን አጎረሳት፡፡
እያጎረሳት ለራሱም እየጎረሰ ምግቡን በልተው ሲጨርሱ እጇን አስታጥቧት እቃውን አነሳሳና ፍራሹ ላይ ከጎኗ ተቀመጠ፡፡ ከዚህ በፊት እንዲህ ከጎኗ ተቀምጦ አያውቅም፡፡ ልቧ በፍጥነት መምታቱን ቀጥሏል፡፡ ‹‹ልሳመው ፣ አልሳመው›› አመነታች፡፡
‹‹ቀሙ ዝም አልሽ እኮ! ዝም ስትዪ በጣም ነው የምትጨንቂው!››
ሳታስበው እንባዋ ከአይኖቿ ሞልቶ ፈሰሰ፡፡ ‹‹ቀሙ!›› ኢምራን ደነገጠ፡፡ እንዴት እንደሚያባብላት ግራ ገባው፡፡ ደረቱ ላይ ተለጥፋ ማልቀስ ጀመረች፡፡ እንባዋን ለመጥረግ እጁን ወደ ፊቷ ሲልክ ያዘችውና ቀና አለች፡፡ በፊቶቻቸው መካከል የህጻን ልጅ ስንዝር ያህል እንኳ ርቀት የለም፡፡ የኢምራን ልብ ቀጥ አለ፡፡ አይኗን ጨፍና ተጠጋችው፡፡ አንዴ ስትስመው የተፈጥሮ ህግ ትዝ አለው፡፡ እሱ ወንድ ነው፡፡ ራሱን ያጠረባቸውን የመርህ ሰንሰለቶች ሁሉ ዘነጋቸው፡፡ ደገመችው፡፡ ንዝረቱ ጋመ፡፡ ደጋገመችው፡፡ ወንድ ሆነ፡፡ መሳሙ ወደ መሳሳም ተቀየረ፡፡
የኢምራን ጾመኛ ቤት ሳታስበው አፈጠረች፡፡ ባልታሰበ ….. ፀጋ ለማለት በሚከብድ መና ጾሟን ገደፈች፡፡ ይህቺን እሳት በአግባቡ ካልሞቋት ማቃጠሏ እንደማይቀር ግልፅ ነበር፡፡ የአሟሟቁ አግባብ በትዳር መተሳሰር ብቻ ነው፡፡ ሁለቱም የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው፡፡ አቅላቸውን ስተው ደመ ነፍሳቸው የሰጣቸውን ፈረስ ቼ ቼ ቼ እያሉ ጋለቡ፡፡ ትንሿ ቤት ሰምታው የማታውቀውን የሲቃ ድምፅ ሰማች …. ፍራሿም ተጭኗት የማያውቅ ሀይል ሲፈትጋት ተጨንቃለች፡፡ የእሳቱ ማጥፊያ የነበረው እሷ ጋ ነው፡፡ እሳት አደጋ መከላከያ የለኮሰውን እሳት ደግሞ መብራት ሀይል ሊያባብሰው እንጂ ሊያጠፋው አይችልም፡፡ የተፈጥሮን ሚዛን እንድትጠብቅበት የተሰጣትን አደራ በላች፡፡ ደካማውን ፍጥረት አስጎነበሰችው፡፡
ከዛ ደግሞ ድካም አለ …. ፍራሹ ላይ ጎን ለጎን ተዘረሩ፡፡ ሀፍረት ሁለቱንም ከመተያየት ቆጥቧቸዋል፡፡ ቀመር ከፍራሹ ራስጌ የቆሻሻ ልብስ ማስቀመጫ ቅርጫቱ ላይ የተቀመጠውን አንሶ

ልብ - ወለድ

05 Dec, 04:45


በቡ ያህል ዘመዶቿ ቤት ጎራ ካለች በኋላ ወደ ኤርሚያስ ቤት ታመራለች፡፡ ሂባ ለኢምራን ያለችበትን ሁኔታ ለመንገር ስለፈራች ናርዶስን ለማማከር እጅጉን ብትፈልግም ሊሳካላት አልቻለም፡፡
ዛሬ በጠዋቱ ሂባ ወደነናርዶስ ቤት ገባች፡፡ ቤተሰቡን ሰላም ብላ ወደ ናርዶስ ክፍል ስትገባ ናርዶስ ከአልጋዋ ላይ በርግጋ ተነሳች፡፡ ከላይ በጡት ማስያዣ ብቻ ነበረች፡፡ ከታች ብርድ ልብስ ለብሳለች፡፡ ጆሮዋ ላይ የሰካችውን የጆሮ ማዳመጫ አውልቃ በፍጥነት የጀመረችውን የወሲብ ቪዲዮ ዘጋችው፡፡ ሂባ በናርዶስ ሁኔታ ግራ ተጋብታለች፡፡
‹‹ምነው ናርዲዬ አስደነገጥኩሽ እንዴ?››
‹‹አይ አስላደነገጥሽኝም! ድንገት በሩ ሲከፈት ነው …. ነይ ተቀመጭ!›› እግሯን ሰብስባ ለሂባ ቦታ አመቻቸች፡፡ የሂባ ሆድ በጣሙን ገፍቷልና እግሯን ከፍታ ቀስ ብላ ተቀመጠች፡፡ ናርዶስ መደገፊያ ትራስ አመቻቸችላት፡፡
‹‹wow ጡት ማስያዣሽ የሌለ sexy ናት፡፡››
‹‹እምም ስጦታ ናት›› ያላሰበችው መልስ ነበር፡፡
‹‹ስ … ጦ …. ታ? ከማን?››
‹‹የአክስቴ ልጅ ናት የሰጠችኝ!››
‹‹የአክስትሽ ልጅ እንደዚህ አይነት ጡት ማስያዣ? የማይመስል ወሬ አታውሪ! ይልቅ ንገሪኝ ማነው?››
‹‹አንድ የስራ ባልደረባዬ ነው፡፡ እዛ ለነበርነው ሴቶች የሰጠን!››
‹‹ናርዶስ!›› ሂባ ተቆጣች፡፡
‹‹ምነው?››
‹‹ከመች ጀምሮ ነው እኔና አንቺ መደባበቅ የጀመርነው?››
‹‹እንደሱ አስቤ አይደለም እኮ! ...... ግን ላወራሽ ስፈልግ አጠገቤ አልነበርሽም ነበር!››
‹‹ይኸው አሁን አጠገብሽ ነኝ! ንገሪኝ! የማላውቀውን ሁሉ ንገሪኝ!›› የሁለቱም አይን እንባ አቅርሯል፡፡
‹‹አሁን ሁሉም ነገር ተቀይሯል ሂባዬ! ያንቺዋ ናርዶስ ሞታለች›› ከአይኖቿ የእንባ ዘለላዎች ተሽቀዳደሙ፡፡ የሂባም አይን ተሸነፈ፡፡ አይኖቿ በእንባ እንደራሱ ጠየቀቻት፡፡
‹‹ንገሪኝ ናርዲዬ! የተቀየረውን ንገሪኝ!››
ናርዶስ በእንባ እየተጠመቀች ከመነሻው አንስቶ እስካሁን ያለውን ሂደት አረዳቻት፡፡ ሂባ የምትሰማውን በፍፁም ለማመን አልቻለችም፡፡ ያቺ ፍቅረኛዋን አብረን እንተኛ ስላላት የተፋታችው ናርዶስ …. ያቺ የወንድ ጓደኛ እንኳ ማብዛት የማይመቻት ናርዶስ …. ከስራ ባልደረባዋ ጋር በዚህ መልኩ ለመርከስ ትፈቅዳለች ብላ ለማመን ተቸገረች፡፡ ሂባ አልቅሳ ጋብ ሲልላት የምታለቅሰውን ናርዶስን ደረቷ ላይ አቅፋ እንባዋን እየጠረገችላት ጥያቄዋን ቀጠለች፡፡
‹‹ናርዲዬ ልጁን ወደሽው ይሆናል ግን መጀመሪያ ላይ እንዴት እንደዚህ እንዲያደርግሽ ፈቀድሽ?››
‹‹የሚሰጠኝ Pornography ፊልሞች ሙሉ ለሙሉ ለውጠውኝ ነበር፡፡ ገና እሱ አንዱን step ሲጀምር እኔ ባየሁት መልኩ በጭንቅላቴ ሁሉንም ስቴፖች አለፍኩና በአንዴ ውሀ ሆንኩ፡፡ ከዛ በኋላ እምቢ የምልበት አቅም አልነበረኝም፡፡ የመጀመሪያው ቀን ከተከሰተ በኋላ በቃ እኔም ፍላጎት እያደረብኝ መጣ! ምን ልበልሽ ሱስ ሆነብኝ! ትክክል እንዳልሆነ አውቃለሁ ግን መመለሱ ከበደኝ! አሁንም ስትመጪ እሱ የሰጠኝን እያየሁ ነበር፡፡ ለዛ ነው የደነገጥኩት! ሌላ አይነት ፊልም የሚባል ማየት አስጠልቶኛል፡፡››
‹‹እና የጠፋሽው ሁሌ ይህን እያደረጋችሁ ነበር?››
‹‹ላታምኚኝ ትችያለሽ ግን ቀን በቀን አንድም ቀን ሳንዘል!››
‹‹እና እንዴት ዛሬ ቤት ተገኘሽ?››
‹‹ፔሬድ ላይ ሆኜ ነው! ደበረኝ››
‹‹ናርዲዬ ከዚህ በኋላ በፍፁም ሰውየውን አታገኚውም እሺ! በቃ የPornography ሱሱንም ቢሆን ገና ብዙ ስላልሄድሽበት በቀላሉ ይቆማል፡፡››
‹‹ልጁ እኮ ደስ ይለኛል! እንዲያገባኝ ብናደርግ ይሻላል!››
‹‹እንደዚህ አይነት ርካሽ ስብዕና ያለው ሰው በፍፁም ያንቺ ባል ሊሆን አይገባም! ይኼኔ በጎን ሌላም ሴት ያጫውት ይሆናል!››
‹‹እንደሱ እንኳ አያደርግም ጥሩ ልጅ እኮ ነው!››
ሂባ አለመሳቅ አልቻለችም፡፡ እንባዋ ከፊቷ ላይ ሳይደርቅ ሳቋን ለቀቀችው፡፡
‹‹ናርዲዬ እሱን ሳታገኚ ረጋ ብለሽ ቢያንስ ለሳምንት አስቢበት! ከዛ ውሳኔሽን ትነግሪኛለሽ! በሀሳቤ ከተስማማሽ ሁሉንም ነገር አብረን እንወጣዋለን!››
ናርዶስ እስከዛሬ አፍና የያዘችውን ጭንቀቷን በመተንፈሷ ቀለል አላት፡፡ የልቧ ፍላጎት ግን አሁንም ገና ወደ ቀድሞው አቋሙ አልተመለሰም! ዝሙትን የምትጠየፈው ናርዶስ ጠንክራ አዲሷን ሴሰኛ ናርዶስ ገና አላፈረሰቻትም፡፡ ትወላውላለች፡፡ መቁረጥ እጅጉን ከብዷታል!
.
ይቀጥላል…

@Lib_Weled

ልብ - ወለድ

05 Dec, 04:44


የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አስራስድስት
(ፉአድ ሙና)
.
አርብ ከከሰዓት በኋላ ኤርሚያስ እና ናርዶስ የመስሪያ ቤቱ ክበብ ውስጥ ተቀምጠው ስለፊልሞቹ እየተወያዩ ነው፡፡
‹‹የመጀመሪያው አሪፍ ነበር ያው ታሪኩን ወድጄዋለሁ! ሁለተኛው እስከዚህም ነው ግን እሱም ደስ የሚል ነገር አለው፡፡ those pornography videos ግን …. ለምናባህ ነው የላክልኝ?!››
ኤርሚያስ እየሳቀ ወደ አፉ ያስጠጋውን ማኪያቶ ፉት ብሎ ወደ ጠረጴዛው መለሰና ቀጠለ፡፡ ‹‹ያው ለወደፊቱ እውቀት ይሆንሻል ብዬ ነዋ! ግን አሪፍ ናቸው እኮ አልወደድሻቸውም?››
‹‹ሂድ እዛ ሙት እሺ! ዘጊ!››
‹‹ቆይ እንደውም ላሳይሽ አዲስ የተቀበልኩትን!›› ስልኩን አውጥቶ መነካካት ጀመረ፡፡
‹‹እንዴ አንተ እብድ! ሰው አለ እኮ!›› ጨነቃት፡፡
‹‹ነይ እሺ አንቺ ቢሮ እንሂድ!›› ስልኩን እየነካካ ተነሳ፡፡ ተከተለችው፡፡ ሂሳብ ከፍለው ወደ ቢሮዋ ሄዱ፡፡ ቪዲዮውን የማየት ፍላጎቱ ቢኖራትም ከሱ ጋር ለማየት ፈቃደኛ መሆኗ ርካሽ እንዳያስብላት ፈርታለች፡፡ በሩን ከውስጥ ከቆለፈው በኋላ ቀድሟት ወንበሯ ላይ ተቀመጠ እና ጎትቶ ጭኑ ላይ አስቀመጣት፡፡ የጆሮ ማዳመጫውን ካደረጉ በኋላ ቪዲዮውን ከፈተው፡፡ ከእስከዛሬዎቹ እጅጉን የከፋ ነበር፡፡ የናርዶስ ሰውነት መንዘፍዘፍ ጀመረ፡፡ እግሯ እግሩን ሲታከከው ይታወቀዋል፡፡ እሱ ላይ ቪዲዮው ብዙም ተፅዕኖ አያሳድርበትም ፣ የለመደው ነው፡፡ የናርዶስን መቅለጥ ሲመለከት እጆቹን ወደ ሰውነቷ ልኮ ይደባብሳት ጀመር፡፡ እጅግ ቀስቃሽ የሆኑ የሰውነት ክፍሎቿን በእጆቹ አዋራቸው፡፡ ናርዶስ አቅሏን ለመሳት እየተቃረበች ነው፡፡ ስልኩን ጠረጴዛው ላይ ወርውሮ ወደ ራሱ አዞራት፡፡ ከዛማ … የሚቆራረጥ ትንፋሽ! ከዛማ …. የሚወዛወዝ ጠረጴዛ! ስልኩ ከጠረጴዛው ስር መሬት ላይ ወድቆ ተሰበረ፡፡ ከጠረጴዛው በላይም የተሰበረ ውድ ነገር ነበር፡፡
ሁሉም ነገር ማብቂያ አለውና መንፈራገጡ ሲያበቃ ተፋፈሩ፡፡ ናርዶስ ጭንቅላት ውስጥ ብዙ ጥያቄ ይመላለሳል፡፡ ክብሯን በዚህ መልኩ ማጣቷ ፣ ነገስ የሚለው ጥያቄ ፣ ብዙ ብዙ ታስባለች፡፡
‹‹ሁሉ ነገርሽ ምርጥ …. ጣፋጭ ነሽ!›› የወለቀውን ቀሚሷን እየለበሰች ያለችውን ናርዶስን እያየ ቀጠለ ‹‹ዛሬ ነው አይደል እራት የምትጋብዢኝ?›› እሱ ሱሪውን ለብሶ ከረባቱን እያስተካከለ ነበር፡፡
‹‹አንተ ውጪ ሰምተውን ይሆን እንዴ? በጣም ጮህኩ?›› ከቢሮ ስትወጣ ቀና ብሎ የመሄድ ድፍረት ውስጧ ላይ የለም፡፡
‹‹ይኼ እኮ አርማታ ነው ድምፅ አያስወጣም! ፈታ በይ ባክሽ!››
‹‹ባረግዝስ?››
‹‹አሁን የሚወሰድ ክኒን አለ ቆይ ስንወጣ እገዛልሻለሁ!››
‹‹አውቀዋለሁ እሺ! አሁን እንሂድ በቃ ከዚህ እንጥፋ!›› የምትናገረው ለራሷም ግራ እየገባት ነው፡፡ ተያይዘው ግቢውን ለቀው ወጡ፡፡
*
ሂባ ቅዳሜ ከሰዓቱን ናርዶስ ጋር ስልክ ስትደውል አይነሳም፡፡ በአካል ከተገናኙ ሶስት ቀን ሊያልፍ ነው፡፡ ከሰዓቱን ስራ ስለሌላት በጊዜ ትመጣለች ብላ ብትጠብቃት በጣም ዘገየች፡፡ ደጋግማ የሞከረችው ስልክ ተስፋ ሲያስቆርጣት አልጋ ላይ ጋደም እንዳለች ኢምራን ጋር ስለመደወል አሰበች፡፡ ‹‹ደውዬ ምን እለዋለሁ?›› ፈራች፡፡ ልትተወው ስትል ባለፈው ‹‹የምታማክሪኝ ነገር ሲኖር ከጎንሽ ነኝ!›› ማለቱ ትዝ አላት፡፡ ደወለች፡፡ ጥቂት ከጠራ በኋላ ተነሳ፡፡ ኢምራን ቶሎ ለመመለስ ብላ ፈተና እንዳለቀ የሄደችውን ቀመርን አውቶብስ ተራ ሸኝቶ መመለሱ ነበር፡፡ ስልኩ ላይ የሂባን ስልክ ሲመለከት ውስጡ በደስታ ተሳከረ፡፡
‹‹ሂባዬ!››
‹‹ኢምሩ እንዴት ነህ?››
‹‹አለሁልሽ አንቺ እንዴት ነሽ?››
‹‹አለሁ አልሀምዱሊላህ!››
ሰላምታቸውን እንደቋጩ የተፈጠረ አዲስ ነገር ካለ ከተጠያየቁና እሱ ከነገራት እሷ ከደበቀችው በኋላ ወደ ደወለችበት ጉዳይ ገቡ፡፡
‹‹አንድ ነገር ላማክርህ ብዬ እኮ ነው!››
‹‹ምን?››
‹‹አንድ ጓደኛዬ ናት እና አንድ ወዳጇ በጣም ቤቷን ወዶት ቤቷ ውስጥ አንድ ክፍል ልትሰጠው ተስማምተው ነበር፡፡ ኋላ ላይ እሷ ቤት ለመኖር እቃውን ሸክፎ ሲመጣ የቤተሰቦቼ ዘመዶች ስለመጡ እነሱ ሊያርፉበት ነው ብላ ከለከለችው፡፡ እሱም እንደሷ ቤት ልቡ ወዶ የሚያርፍበት ቦታ ስላልነበረው በጣም ተጉላላ፡፡ ኋላ ላይ እሱ ተጉላልቶ ተጉላልቶ ሲረጋጋ ፣ የቤተሰቦቿ ዘመዶች ሁሌ እየረበሹ አስቸገሯትና አባረረቻቸው፡፡ እነሱ ሲኖሩበት የሰጠቻቸውን ክፍል በር ሰብረውት ነበር፡፡ ኮርኒሱም ውሀ አዝሎ ጠቁሯል፡፡ አሁን ያንን ወዳጇን ጠርታ ቤቱን ልትሰጠው ትፈልጋለች ግን አዲስ እያለ ቃሏን አጥፋ ስለነበር አሁን በሩ ከተሰበረ እና ኮርኒሱ ውሀ ካዘለ በኋላ ብጠራው ሌላ የተሻለ ቤት እንዳያገኝ መመቅኘት ይሆናል ብላ ፈራች፡፡ እና ምን ልበላት?››
‹‹እሱ ቆይ አቅም የለውም ነው? ለምን እሷ ቤት ማረፍ ፈለገ?››
‹‹ቤቷን ስለወደደው ነው እንጂ አቅም እንኳ አለው!››
‹‹ታዲያ አቅም ካለው በሩንም ፣ ኮርኒሱንም አሰርቶ መኖር ይችላል አይደል! ያለውን ሁኔታ ለምን አትነግረውም?››
‹‹በሩም ሆነ ኮርኒሱ የተሰሩት በጣም ድሮ ከውጪ ሀገር በመጡ ግብዓቶች ነበር፡፡ አሁን ምርቱ ስለቆመ ገበያ ላይ የሚገኙ አይነት አይደሉም!››
‹‹ታዲያ የዘመኑን አዲስ በር እና ኮርኒስ ያስገጥማ ምንድነው እንዲህ መጨናነቅ?››
‹‹እንደዛ መሆን አይችልም! እቃው ላይቀየር ከአያቶቿ አደራ አለባት፡፡››
‹‹በቃ ወይ አሁን እሱ ያለበትን ሁኔታ ታጣራና የተሻለ ቤት ካገኘ ትተወው! ካላገኘ ደግሞ ትንገረውና እሱ የፈለገውን ይምረጥ! አይታወቅም እኮ ቤቱን ከወደደው በሩ ቢሰበርም ሊኖርበት ሊፈልግ ይችላል››
‹‹እሺ ይኼ ጥሩ አማራጭ ነው!››
‹‹አዲስ አበባ ቤት እንዲህ ችግር ሆነ ማለት ነው? የሚወደድ ቤት እንዲህ ጥቂት እስኪሆን?››
‹‹አይገርምህም!››
የምታወራው ወሬ ምንም እንዳልገባው በመረዳቷ በጣም ደስ ብሏታል፡፡ እንደልቧ የማውራት ነፃነት አግኝታለች፡፡ የመከራትን ምክር ዛሬውኑ ተግባራዊ ለማድረግ አሰበች፡፡
‹‹በቃ የጓደኛዬን ጉዳይ ያልከኝን እነግራታለሁ፡፡ እስኪ ወደራሳችን እንመለስ ኢምሩዬ ግን እስካሁን እንዴት አላገባህም?››
‹‹እንዴ ገና እኮ ስምንት ወር አልሞላም ቁርጤን ካወቅኩ፡፡ በዚህ ጊዜ ሌላ ከየት ይመጣል?››
‹‹ፍቅረኛም አልያዝክም? እንደው ያሰብካትም የለችም?››
‹‹አንቺ ደግሞ ኧረ ማንም የለም ባክሽ!›› የቀመርን ጉዳይ ሊነግራት አስቦ ነበር ግን በቅጡ መስመር ውስጥ ያልገባ ጉዳይ ማውራት ከበደውና ተወው፡፡
‹‹ማስተማሩ busy አድርጎሀል ማለት ነው፡፡››
‹‹በይው››
ሂባ በሱ ምክር መሰረት ቀጣዩ ስራ የተፈጠረውን ሁሉ ነግራ ምርጫውን ለሱ መስጠት መሆኑን አውቃለች ግን ደግሞ ከየት ድፍረት አምጥታ እንደምትነግረው ግራ ገብቷታል፡፡
*
ቀናት የጊዜ ጓዛቸውን እየጠቀለሉ ከመጓዝ አልቦዘኑም፡፡ እሽጉ ከተፈታ ወዲያ ኤርሚያስ ቤት ጎራ ተብሎ በቪዲዮ የተመለከቱትን መተግበር የናርዶስ ቋሚ ስራ ሆኗል፡፡ ከሂባ ጋር በቅጡ ተገናኝተው የሚያወሩበት ፣ እንደድሮው ስለሁሉም ነገር የሚማከሩበት ጊዜ ጠፍቷል፡፡ አምሽታ ትመጣለች ….. ቤተሰቦቿም ‹‹ወይኔ ይኼ ስራ ልጃችንን አደከማት›› እያሉ በምክንያት ያጅቧታል፡፡ እሷ ሌላ ቋሚ ስራ መጀመሯን በፍፁም የጠረጠረ ሰው የለም፡፡ ከሂባ ጋር በቅጡ በአካል ከተገናኙ አስራአምስት ቀን ሊሆን ነው፡፡ ናርዶስ ከኤርሚያስ ጋር መተኛት ከጀመረች በኋላ ሂባንም ሆነ ቤተሰቦቿን በቅጡ ደፍራ ለማየት እንደድሮው አብራ ተቀምጣ ለመጫወት ትፈራለች፡፡ እሁድን እንኳ ሳይቀር ሰበብ ፈልጋ በጠዋቱ ትወጣለች፡፡

ለሰ

ልብ - ወለድ

04 Dec, 07:39


ግሽው ይቀራል!›› አሉ፡፡
ምንም ከብዙ መስዋዕትነት በኋላ ቢሆንም አባቷ ስለተረዷት ደስ አላት፡፡ ግን ከዚህ በኋላ ዳሩኝ ብላ የምታመጣው ሰው ያለ አልመስል አላት፡፡ ኢምራን ነበር! እሱን አሁን ላይ ለማግባት የምትመጥን አይመስላትም! ‹‹ጠምቶት ሲማፀነኝ ከልክዬው ፣ ያልደፈረሰውን ለሌላ ሰጥቼ ፣ ያጠጣሁት ሲገፋኝ ጠርቼ ፣ ቅራሪዬን ጠጣ አልለውም!›› ትላለች፡፡ የኢምራን መሆን ብትፈልግም አሁን ላይ ያንተ ልሁን ማለት ለሱ አለማሰብ ይመስላታል፡፡
***
‹‹አራቱንም ፈተና የነገርከኝ ቦታዎችን ነበር focus አድርጌ ያጠናሁት! እንዳለ የመጣውም እሱ part ነው፡፡›› ቀመር ፍራሹ ላይ ተቀምጣ ከስራ መጥቶ ጃኬቱን የሚያወልቀውን ኢምራንን እያየች ቀጠለች ‹‹እና አሪፍ ውጤት እንደሚኖረኝ አትጠራጠር!››
‹‹እሱን ሲመጣ እናየው የለ የምን ፕሮፖጋንዳ ማብዛት ነው?!››
‹‹እኔማ ላመስግንህ ብዬ ነው!››
‹‹እና አሁን ስንት ፈተና ቀራችሁ?››
‹‹ሁለት መሰለኝ! በዚህ ሳምንት እንጨርሳለን!››
‹‹ከዛስ?››
‹‹ከዛማ ጉዞ ወደ ቁሌታሟ ሀላባ ነዋ!›› ተሳሳቁ!
‹‹የማጥኛ ክፍልሽ አትናፍቅሽም?›› ለማለት የፈለገውን ተረዳችና ፈገግ አለች፡፡
‹‹በጣም ትናፍቀኛለህ ኢምሩዬ! አንተ ወደ ደሴ አትሄድም እንዴ?››
‹‹ለሳምንት ደርሼ መምጣቴ አይቀርም!››
‹‹በቃ ታዲያ ስትመለስ ደውልልኝና እመጣለኋ!››
‹‹የምርሽን ነው?››
‹‹አዎ እኛ ቶሎ ስለምንሄድ አንተ ውጤት አስገብተህ ከመሄድህ በፊት ራሱ እኔ እዛ ሄጄ ሳምንት አሳልፋለሁ፡፡ ከዛ አንተ ሄደህ አንድ ሳምንት! በድምሩ አስራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ ቤት ደግሞ ከዚህ በላይ የምናርፍ ስለማይመስላቸው አይባንኑም! so ከች እላለሁ፡፡ ታዲያ ፈታ የምታደርገኝ ከሆነ ነው! ታስደብረኝና አለቀልህ!››
‹‹ውይ እኔ ፈታ ማድረግ አልችልበትም! ያው ባይሆን አንቺ እንሂድ የምትይው ቦታ ለመሄድ ከተስማማሁ አይበቃም?››
‹‹ይበቃል! የምልህን ሁሉ እሺ ካልክማ በቃ የሚገርም ጊዜ ነው የምናሳልፈው!›› ተሳሳቁ፡፡ ለማለት የፈለገችውን እሱም ተረድቶታል፡፡ በፊት በፊት ቶሎ አይገባውም ነበር፡፡
ሰዓቱ ለመምሸት እየቀረበ ስለነበር ጓደኞቿ መደወል አበዙ፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ለመሄድ ተነሳች፡፡ ሁሌም ልትሄድ ስትል ደስ አይለውም፡፡ ከብቸኝነቱ የሚያተርፈው ትዝታ ነው፡፡ ትዝታው ደግሞ መሪር ነው፡፡ በቀመር ውስጥ ትዝታውን ለመርሳት ይታገላል፡፡ የሀይማኖቱን ክልከላ ይዘነጋው ጀምሯል፡፡ በራሱ በጣም ተማመነ መሰል ቤት ውስጥ ብቻቸውን መቀመጣቸው የሚያመጣው መዘዝ መኖሩን ረስቷል፡፡ ግን ባትሄድ ደስ ይለዋል፡፡ ለሊቱንም አብራው ሆና ከትዝታው ብታስጥለው ይመኛል፡፡ ምኞት ብቻ! ሊሸኛት ተከትሏት ወጣ! እግረ መንገዱን የቆይታቸውን ጊዜ ሊያራዝም! ግቢ መግባቷ ላይቀር!
.
ይቀጥላል …

@Lib_Weled

ልብ - ወለድ

04 Dec, 07:39


የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አስራአምስት
(ፉአድ ሙና)
.
በእግሮቿ መንፈራገጥ የአልጋው አንሶላ ተሰብስቦ ከአልጋው መሀል ላይ ደርሷል፡፡ ልክ ምጥ ላይ ያለች እናት ህመሟን ለመቋቋም ፍራሹን አሊያም ትራሱን ጨምድዳ እንደምትይዘው የግራ እጇ ከላይ የለበሰችውን ብርድ ልብስ በሀይል እየጨመደደ ይለቃል፡፡ ከንፈሮቿ ይንቀጠቀጣሉ፡፡ የመኝታ ክፍሏ ጭልም ብሎ ከስልኳ የሚወጣው ጨረር ብቻውን ይንቦገቦግበታል፡፡ የስልኳ ስክሪን ላይ ሁለት ራቁታቸውን ያሉ ሴቶች ከአንድ በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ካለ ወንድ ጋር የተለያየ መጠሪያ ያላቸውን የወሲብ አይነቶች ሲፈፅሙ ይታያል፡፡ የድርጊቱ አካል የሆነች እስኪመስል ገፅታዋ ላይ ተፅዕኖው እየታየ ኤርሚያስ የሰጣትን ተከታታይ የወሲብ ፊልም ተመልከታ ጨረሰች፡፡ ሌላ አይነት ፊልም የማየት ፍላጎቷ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሞቷል፡፡
በነጋታው ቢሮ ስትገባ ኤርሚያስን የህንፃው ደረጃ ላይ አገኘችው፡፡ ተያይዘው ወደ እሷ ቢሮ ገቡ፡፡ ኤርሚያስ እንደተለመደው ሱፉን ግጥም አድርጎ ለብሷል፡፡
‹‹ሱፍ ላንተ ነው! የሌለ እኮ ነው የሚያምርብህ!›› ቢሮ ገብተው ወንበሯ ላይ እየተቀመጠች ነበር፡፡
‹‹እንዳንቺ ሁሉም ነገር አያምርብኝም እንጂ በሱፍ አልታማም!›› ተሟዘዘ፡፡
በልቧ የሰጣትን ፊልም ተመልክታ እንደጨረሰችና ቀጣዩን ክፍል እንዲልክላት ለመጠየቅ ፈልጋለች ግን አፈረች፡፡ እሱ ስለፊልሙ እንዲያስታውስ ለማድረግ መላ ዘየደች፡፡
‹‹የአማርኛ ፊልሞች ግን አይደብሩም? ታሪካቸው ሁሉ ተመሳሳይ ነው እኮ!››
ፈገግ አለ፡፡ ስለላከላት ፊልም ለማውራት ፈልጋ እንጂ ስለአማርኛ ፊልም የሚያስቀባጥር ምንም ምክንያት እንደሌላት ገብቶታል፡፡ ሀፍረቷን ጠብቆ ፍላጎቱ የሆነውን ፍላጎቷን ሊሰጣት ፈለገ፡፡
‹‹እንዴ ረስቼው የሰጠሁሽን ፊልም ጨረስሽው?››
‹‹አዎ ጨረስኩት እኮ ትንሽ ግን ይደብራል ነገር!›› ወደደች ላለመባል መታገሏ ነው፡፡
‹‹እሱን ለመፍረድ አጨራረሱን ማየት ያስፈልጋል! የመጨረሻው ክፍል ተልኮልኛል፡፡ እዪው እና እናወራበታለን፡፡››
የተከታታዩን የወሲብ ፊልም የመጨረሻ ክፍል እና ሌላ ምንም ታሪክ የሌላቸው የወሲብ ቪዲዮዎችን አብሮ ላከላት፡፡
‹‹እና ደሞ ስሚ እራቱን አልረሳሁትም! በዚህ ሳምንት ትጋብዢኛለሽ!››
‹‹ውይ ስፕራይት ምናምን እሽኮለሌ ስትል አልነበር እንዴ ባለፈው?››
‹‹አይ እንግዲህ ሰበብ አትፈልጊ! ትጋብዢኝ እንደው መጋበዝ ነው!››
‹‹አታለቃቅስ በቃ እጋብዝሀለሁ!››
ተሰናብቷት ወደ ቢሮው ሄደ፡፡ ፊልሞቹ ላይ እንዳየችው ቢነካካት ፣ ቢስማት …. ውስጧ ይመኝ ነበር፡፡ መልሳ በራሷ ታፍራለች፡፡ የቀድሞዋን ናርዶስ ውስጧ ላይ እያጣቻት መሆኑ ያስፈራታል፡፡ ‹‹ይሄን ነገር ልተው? አልተው?›› በሀሳብ ትዋልላለች፡፡
ገና ከቢሮዋ እግሩ ሲወጣ በሩን ቆልፋ የሰጣትን ፊልም መመልከት ጀመረች፡፡ ጠዋቱን ለወጉ ስራ ገባች እንጂ የምትሰራው ስራ አልነበረም፡፡
ከገፀ-ባህሪያቱ ጋር አብራ በስሜት ነደደች፡፡ ከሁሉም የምትጠላው የፊልሙን ማለቅ ነው፡፡ ፊልሙ ሲያልቅ የሷን ንዳድ የሚያበርድ ምንም ነገር አጠገቧ አለመኖሩ ያማታል፡፡ ተስፋ የመቁረጥ ፣ አንዳንዴም በራስ የማፈር ስሜት ይሰማታል፡፡ የራሷን ስሜት ራሷ ስለማብረድ ታስባለች፡፡ ሀይማኖቷ ትዝ ይላትና ሌላ ወንጀል መጨመርን ትፈራለች፡፡ በዚህ ከቀጠለች ሰው መሆኗ እየጠበበ ሴት ብቻ እንደምትሆን ታውቀዋለች፡፡ አካሏ ሁሉ ቀርቶ ሀፍረተ ስጋ ብቻ ወደ መሆን ስነ ልቦና እንደምትሸጋገር ትረዳለች፡፡ መፍትሄው ግን ማወቅ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚህ ጉድ ጎትቶ የሚያወጣ ጠንካራ አቋም ይፈልጋል፡፡ አሁንም ፊቷ በላብ እየተጠመቀ ፣ እግሮቿ መሬቱን እያስቸገሩ ነው፡፡ ቆንጅዬዋ እና በስነ ምግባሯ የማትታማው ናርዶስ የወሲብ ፊልም እያየች ነው፡፡
***
ዚያድ ሂባ ከቤት ከወጣች ከአራት ቀናት በኋላ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት መጣ፡፡ እጅ መንሻ የሚሆን ኮተት አስከትሏል፡፡ አመሻሽ ላይ ስለነበር ጋሽ ጀሚልም ወደ ቤት ተመልሰው ነበር፡፡ ሂባ ወንድሟ የዚያድን መምጣት ሲነግራት የእናትና አባቷ መኝታ ክፍል ገብታ በሩን ቆለፈችው፡፡ አስገድዶ ይዟት የሚሄድ ይመስል ትፈራለች፡፡ ያንን የጨለማ ጊዜ መድገም አትፈልግም፡፡
በስነ ስርዓቱ ቤት ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ጋሽ ጀሚል ቁጣቸው እጅጉን ጣራ ቢነካም ዋጥ ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡፡ ወ/ሮ ዘምዘም የእጅ ውሀ ይዘው ብቅ አሉ፡፡ መብላት እንደማይፈልግ ደጋግሞ ማለ፡፡
‹‹እሺ ጋሼ ዛሬ ያው በዚህ ሰዓት የመጣሁት ለእርቅ ነው፡፡ ሰው ነን አለመስማማት ያለ ነው፡፡ ግን ትዳርን ያክል ነገር ትቶ መውጣት እጅጉን አሳፋሪ ነው፡፡ እኔም ያው ልጅነቷ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ነው እናንተ የሚበጀውን እንድታሳይዩዋት ለመጠየቅ መምጣቴ!››
ሂባ የሚለውን ሁሉ ግድግዳው ላይ ተለጥፋ እያደመጠች ነው፡፡ ጋሽ ጀሚል ቁጣቸው ገነፈለ፡፡ ‹‹ልጄን አክብሬ ስሰጥህ ዘር እንድታስቀጥሉ ፣ ተሳስባችሁ እንድትኖሩ እንጂ! እንደ ባሪያ እንድትደበድባት ፣ እንድታስራት ነበር እንዴ!?››
‹‹እንዴ ጋሼ የምን መደባደብ ፣ የምን እስር ነው? እንዴት ተንከባክቤ እንደያዝኳት እማማ ሲመጡ ተመልክተዋል እኮ! ይኼ እልም ያለ ቅጥፈት ነው፡፡››
ሂባ ምን ያህል የመዋሸት ድፍረት እንዳለው እየታዘበች ውስጧ በብስጭት አረረ፡፡
‹‹ስማ ዚያድ ከምንም በላይ ደሜ ያንገበግበኛል፡፡ ስጋዬን ቆርጬ ስሰጥህ እሷን አስገድደን እንጂ ወዳ አልነበረም! ከድሮም ስርዓት ያላት ልጅ ስለሆነች ፍላጎቷ ሳይሆን እንኳ ፣ ሌላ የምትወደውን ሰው ትታ ፣ የአባቷን ትዕዛዝ አክብራ ፣ ፍላጎቷን ተጭና ነው የዳርኩልህ! ይህን ሁሉ አድርጋ ስታበቃ በፍፁም ባለፈው ደውለህ ያልከውን መሸርሞጥም ሆነ አንተን አለመታዘዝ የምታስብ ልጅ ናት ብትለኝ ልሰማህ አልችልም!››
ሂባ አንጀቷ ራሰ፡፡
‹‹እንዴ ጋሼ እኔም እኮ ልጅዎት ነኝ! በዛ ላይ ልጃችንን አርግዛለች፡፡ የሚበጀው ተስማምተን ብንኖር ነው፡፡››
‹‹ከሽምግልናው በፊት ተገናኝተን ስናወራ ጫት አልቅምም ብለኸኝ ነበር እኮ! አንተ ግን በየቀኑ ተጥደህበት ነው የምትውለው! ስለሷ ሳይሆን ስለጫት ብቻ ነው የምታስበው! ጫት እኔም እቅማለሁ ግን እኔ አልቅምም ብዬ አልቀጥፍም! ያመጣብኝንም ጉዳት እኔ አውቀዋለሁ!››
‹‹ጋሼ እንዲህማ ጥሩ ነገር የሌለኝ አያስመስሉ! እኔ ለሷም ለቤተሰቡም ጥሩ ለመሆን ሞክሬያለሁ!››
ስለከፈለላቸው ገንዘብ ማስታወሱ እንደሆነ ገብቷቸዋል፡፡ ‹‹የዋልከውን የዋልከው በፍላጎትህ እንጂ ማንም አስገድዶህ አይደለም! ለማንኛውም አሁን በሰላሙ የምልህ ልጁ ከተወለደ በኋላ አርፈህ ኒካህን አውርድ! ከዚህ በኋላ ልጄን ድጋሚ አስገድጄ ህይወቷን አላበላሽም!››
‹‹ኧረ እማማ የሆነ ነገር በሉ!›› ወደ ወ/ሮ ዘምዘም ዞሮ በአይኑ ተለማመጠ፡፡ ወ/ሮ ዘምዘም ከዝምታ በቀር ሌላ ምላሽ አልነበራቸውም፡፡
ሂባ የአባቷ ይህን ያህል መቆጣትና ለሷ ዘብ መቆም ፍፁም ያልጠበቀችው ነበር፡፡ ያለፉት ምሽቶች ላይ ያወሩት ያሳለፈችው መከራ እጅጉን እንደቆረቆራቸው ገባት፡፡ በሳቸው አስገዳጅነት መዳሯ ደግሞ የስቃይዋ ምንጭ እንደሆኑ እንዲያስቡ ሳያደርጋቸው አይቀርም፡፡
ዚያድ ሲወጣ ሂባ የመኝታ ክፍሉን በር ከፍታ እየሮጠች አባቷ ላይ ተጠምጥማ ማልቀስ ጀመረች፡፡ በአባቷ እንደዛሬ የተደሰተችበት ቀን በህይወቷ ገጥሟት የሚያውቅ አልመሰላትም፡፡ አባቷም እንባ ተናነቃቸው፡፡ ግንባሯን ሳሟት እና ‹‹ልጄ አላህ ያክብርሽ እስከዛሬ አንድም ቀን አስከፍተሸኝ አታውቂም! ከዚህ በኋላ አንቺ የምትፈልጊውን ሰው አምጪ አይተን ጥሩ ከሆነ እንድርሻለን! እኛም የምናመጣውን ካልፈለ

ልብ - ወለድ

03 Dec, 04:41


ያስብ አደራውን ለሌላ ሰው የሰጠችበት ይመስለዋል፡፡ ‹‹በሄደችበት ለመደች በቃ?!›› ብሎ በክህደቷ ይታመማል፡፡ ባልየው ሊተኛት ሲመጣ ‹‹የኢምራን ነው እንዳትነካኝ!›› እንደምትል ገምቶ ነበር፡፡ እሱን ‹‹እወድሀለሁ›› ባለችበት ከናፍሯ ሌላ ትስማለች ብሎ አስቦ አያውቅም፡፡ ‹‹ደሞ በቤተሰቧ ታሳብባለች!›› ይላል፡፡ ‹‹ቤተሰቧን እምቢ ብላ ለኔ እንዲድሯት ለማድረግ ያልደፈረችው ሀላፊነቱን ላለመውሰድ አይደል! የሆነች ጥገኛ!›› ይበሳጫል፡፡ ‹‹ግን እኮ እሷ ግድ ባይሆንባት አትተወኝም!›› እራሱ ይከላከልላታል፡፡ ያለቅሳል መከዳቱ …. ባቀረበ መገፋቱ ያመዋል፡፡
ጣራው ላይ ትዝታውን ካነበበ በኋላ በቅርቡ የተደወለለት ስልክ ትዝ አለው፡፡ ስልኩን ከአጠገቡ አንስቶ ደወለ፡፡ ሂባ የቤተሰቦቿ ቤት ውስጥ ጋደም ብላ ነበር፡፡ ስልኳ ሲንጫረር ከሰጠመችበት የሀሳብ ባህር አባነናት፡፡ ስልኩን ስታየው ደነገጠች፡፡ ከባሏ ጋር መጣላታቸውን እና ወደ ፍቺ እየተንደረደሩ መሆኑን የሰማ መሰላት፡፡ ስልኩን ለማንሳት ፈራች፡፡ ጠርቶ ጠርቶ ዘጋ፡፡ እሁድ ስለሆነ ሌላ ስራ አልነበረውም፡፡ ደግሞ ደወለ፡፡ አነሳችው፡፡ ፈራ ተባ እያለች ‹‹ሄሎ›› አለች፡፡ ኢምራን የሚሰማውን ማመን ከበደው፡፡
‹‹ሂባ?››
‹‹አዎ ነኝ! ኢምራኔ ደህና ነህ?›› ሳግ ንግግሯን አነቀው፡፡
ኢምራን ህልም እየመሰለው ነው፡፡ ‹‹ሂባዬ የኔ?››
‹‹አዎ ኢምራኔ ሂባ ያንተው ከሀዲ!›› ተንሰቀሰቀች፡፡
‹‹የምን ክህደት! ለምን ታለቅሻለሽ ችግር አለ እንዴ?››
‹‹እንዲሁ ኢምሩዬ እንዲሁ!››
‹‹እንዴት ነሽ ግን በአላህ?››
‹‹ደህና ነኝ ኢምሩዬ! ደህና ነኝ››
‹‹ባልሽ ደህና ነው?››
‹‹ደህና ነው፡፡››
‹‹ፅንሱስ ሂባዬ?››
‹‹አልሀምዱሊላህ ደህና ነው፡፡ አንተ ጋ ስራ ምናምን ጥሩ እየሄደ ነው?››
‹‹አዎ እሱማ አሪፍ እየሄደ ነው፡፡ ወይኔ በአላህ ድምፅሽን ስለሰማሁ በጣም ነው ደስ ያለኝ!››
ስልኩን ከአፏ አርቃ ተንሰቀሰቀች፡፡ ለክህደቷ የጠበቀችውን ስድብ ስታጣው በራሷ አፈረች፡፡
‹‹ሄሎ ሂባ!››
‹‹ወዬ አለሁ ኢምራኔ››
‹‹እንዴት ደወልሽልኝ ግን? እኔ እኮ በዛኛው ስልክ ብዙ ጊዜ ስሞክር አይሰራም!››
‹‹አዎ ስልክ ስለቀየርኩ ነው፡፡ ሰላም ልበልህ ብዬ ነበር የደወልኩት ከዛ ፈራሁና ዘጋሁት፡፡››
‹‹እንዴ ምን ያስፈራሻል? please ሁሌ ደውዪልኝ እሺ! እኔም እደውላለሁ! የምታማክሪኝ ነገር ሲኖር ከጎንሽ ነኝ!››
‹‹እሺ ኢምራኔ አልፈራም እደውልልሀለሁ፡፡››
ተሰነባብተው ስልኩ ተዘጋ፡፡ ኢምራን በደስታ ከፍራሹ አልፎ ወለሉ ላይ ተንከባለለ፡፡ ‹‹ሂባዬ ደህና ናት!›› ‹‹የኔ ውድ ደህና ናት!›› ደህና በመሆኗ ደህንነት ተሰማው፡፡ ሂባ ስልኩን እንደዘጋች ተንሰቀሰቀች፡፡ ይቅርታው አመማት፡፡
ኢምራን ቤቱ ውስጥ በደስታ ተጠምቆ እየተደሰተ ባለበት ሰዓት የቤቱ በር ተንኳኳ፡፡ በቁምጣ ነበር፡፡ ቤቱ ከነጋ በቅጡ እንኳ አልተከፈተም፡፡ ታፍኗል፡፡ በሩን ሲከፍተው ቀመር በሩ ላይ ቆማ አበራች፡፡ እጅጉን አምሮባታል፡፡ ፈገግ አለች፡፡ ፈገግ ለማለት ሞከረ፡፡
‹‹እንቅልፎ! በቁምጣም ታምራለህ የኔ ቀጫጫ!›› ሳቀች፡፡
ተሽኮረመመ፡፡ በሩን ከፍቶ ትቶት ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ጫማዋን አውልቃ ተከተለችው፡፡
ቤት ውስጥ የነበረውን ሲሊፐር ጫማ ወረወረላትና ‹‹እንዳይቀዘቅዝሽ አድርጊው!›› አላት፡፡
ፈገግ እንዳለች ‹‹አንተ እያለህማ አይቀዘቅዘኝም!›› አለች፡፡ ተሳሳቁ፡፡
በጋራ ቤቱን ካፀዳዱ በኋላ ቁርስ ለመስራት መንደፋደፍ ጀመረች፡፡ ከፊት ለፊቱ እንዳጎነበሰች ‹‹ሂባ እኮ ደወለች!›› አለ፡፡
ዞር ብላ ተመለከተችውና ፈገግ ለማለት ሞከረች፡፡ ‹‹እና ደስ አለህ? ማለቴ ደስ የሚል ነገር አወራችህ?››
‹‹እሷ ካወራችው እኮ ሁሉም ደስ ይላል!››
‹‹ሌላ ላገባ ነው የሚለውም?››
‹‹ሂጂ እዛ አዝግ!››
ቀመር የጀመረችውን ጉዞ በከፊል ወደ ኋላ የሚመልስ ነገር እንደተከሰተ ተሰምቷታል፡፡ ከዚህ በኋላ የሚኖሩት እርምጃዎቿን ከታሰበው በላይ ለማፍጠን አሰበች፡፡
‹‹እና የልጇ የአይን አባት አታደርግህም?›› ሳቀች!
‹‹ወንድ መሆኑን በምን አወቅሽ?››
‹‹በአባቱ!››
ፈገግ ለማለት ሞከረ፡፡ ባል እንዳላት ስላስታወሰችው ደበረው፡፡ እሷ አላማዋ ስለተሳካ ደስ አላት፡፡ ውዷን ቁርስ ለማብላት መንደፋደፏን ቀጠለች፡፡ ሰዓቱ ወደ አራት ሰዓት እየተጠጋ ነበር!
.
ይቀጥላል…

@Lib_Weled

ልብ - ወለድ

03 Dec, 04:40


የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አስራአራት
(ፉአድ ሙና)
.
ቀመር ከኢምራን ቢሮ እንደወጣች ያመራችው ወደ ዶርም ነበር፡፡ የዶርም ጓደኞቿ ምሳ ለመብላት ሲወጡ መንገድ ላይ ተገናኙ፡፡ ደብተሯን አስቀምጣ ተመለሰችና ተያይዘው ምግብ ወደሚበሉባት ትንሿ ምግብ ቤት ሄዱ፡፡ ምሳቸውን በልተው እንደጨረሱ አራቱም የዶርሟ ልጆች በአይናቸው ሲያወሩ አየች፡፡ ቡና እና ሻያቸውን ካዘዙ በኋላ በአንድነት አፈጠጡባት፡፡
‹‹ሰዎች ምንድነው አፈጠጣችሁብኝ እኮ!››
ሊዲያ የያዘችውን የሻይ ብርጭቆ ከመሀላቸው የተቀመጠው መደገፊያ አልባ ወንበር ላይ እያስቀመጠች ሳቀችና ‹‹this girl is on fire›› የሚለውን ዘፈን መዝፈን ጀመረች፡፡ ኢማን ፣ ሀያት እና ሀይማኖት ያጨበጭባሉ፡፡
‹‹ኧረ አየር አትያዟ! ምን ተገኝቶ ነው?››
ሊዲያ መዝፈኗን አቁማ አፍጥጣ እያየቻት ‹‹you know what? You are in love with our mechanics teacher! Yeaaaa›› አለች፡፡
‹‹ምንድነው ምትሉት?››
ሀያት፡- ‹‹ልተርጉምልሽ እንዴ? መካኒክስ ቲቸርን አፍቅረሽዋል እያልን ነው!››
‹‹ውይ እናንተ ደግሞ! እስኪ የማይመስል ወሬ አታውሩ!››
ኢማን፡- ‹‹come on ቀሙ! ማፍቀር እኮ normal ነው፡፡ ባይሆን አሁን ያለሽበትን ሁኔታ አስረጂንና እናግዝሽ!››
ለቀመር ኢምራንን አፈቀርኩ ብሎ መናገር ምንም ሀፍረት የለውም፡፡ ለሱ ያላትን ስሜትም ሆነ ግንኙነታቸውን የምትደብቀው እሱ ላይ የሚፈጥረው ችግር ይኖራል በሚል ስጋት ነው፡፡ ልናገር አልናገር በሚሉ የሀሳብ አፅናፎች መሀል ተመላለሰች፡፡
ሀይማኖት፡- ‹‹የሆነ ቦታ እያልሽ ስትሄጂ እኮ ገብቶናል፡፡ እሺ ብሎሻል ማለት ነው?››
‹‹ኧረ አልጠየቅኩትም ገና!›› ሳታስበው አመለጣት፡፡
ሊዲያ፡- ‹‹እና እስካሁን kiss አላደረገሽም?››
‹‹መሬት ያዢ ባክሽ እኔ እሱን ለእንደዚህ አይነት ነገር አይደለም የማስበው››
ኢማን፡- ‹‹እና እንዲያስጠናሽ ነው ያፈቀርሽው?›› ሁሉም ሳቁ፡፡
ሀያት ፈገግ እንዳለች ‹‹እስኪ የተፈጠረውን ሁሉ ንገሪን! እናንተ ደሞ ዝም በሉ!›› አለች፡፡ ከመጀመሪያው አሁን እስከደረሱበት ያለውን ነገረቻቸው፡፡ ተገረሙ፡፡
‹‹እና አንድ ቤት ውስጥ the king and the queen ብቻችሁን ሆናችሁ ሊያውም ፍራሽ ላይ he even didn’t kissed you? ስልብ ነው እንዴ!?›› ሊዲያ ማመን ከብዷታል፡፡
ኢማን፡- ‹‹እና ለምን አትነግሪውም? ከዛ እሺ ካለ አሪፍ ካልሆነ ደግሞ ቶሎ መገላገል አይሻልም?››
‹‹ምን ብዬ ነው የምነግረው?››
ሊዲያ፡- ‹‹owu owu yea yeahi I love you more can I say emruye ብለሽ ነዋ!›› ተሳሳቁ፡፡
ሀያት፡- ‹‹ቀሙዬ በቃ ቶሎ ንገሪው እና ተገላገይ!››
ሊዲያ፡- ‹‹እወድሀለሁ ምናምን እንዳትዪው እሺ! በቃ ከንፈሩን ሳሚው የዛኔ ይገባዋል፡፡››
ቀመር ምክራቸው ምንም አልተዋጠላትም፡፡ እራሷ እየሄደችበት ያለውን መንገድ ወዳዋች፡፡
‹‹አደራ ማንም እንዳይሰማ እሺ!›› አስጠነቀቀቻቸው፡፡
*
ሂባ እና ናርዶስ ቤት እንደደረሱ ሂባ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት በቀጥታ እንድትገባ አልፈለጉም፡፡ መጀመሪያ የተፈጠረውን ክስተት በሙሉ ቤተሰቦቿ ሊረዱና የሚያስፈልጋትን ከለላ ለማድረግ የሚያስችል ስነ ልቦና ሊኖራቸው እንደሚገባ ተረድተዋል፡፡ የናርዶስ መኝታ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው ትንሽ አረፍ እንዳሉ ዚያድ ደወለ፡፡ አላነሳችለትም፡፡ መሸትሸት ሲል በተደጋጋሚ መደወል ጀመረ፡፡ ከጫቱ ላይ ተነስቶ ሲፈልጋት እንዳጣት ገባት፡፡
አልጋው ላይ ተጋድመው የተፈጠረውን በምን መልኩ ለቤተሰቦቿ መንገር እንዳለባቸው እየተወያዩ ነበር፡፡ ወ/ሮ ዘርፌ ሂባ ሰውየውን ትታ በመምጣቷ ደስ ብሏቸዋል፡፡ ከጅምሩም ለሱ መዳሯ ሲያንገበግባቸው ነበር፡፡
‹‹እስኪ አንሺለት ምናባቱ ሊል ነው?››
ስልኩን አንስታ ስፒከር ላይ አደረገችው፡፡ ‹‹ስሚ አንቺ የት ሄደሽ ነው?››
‹‹የሆነ ቦታ! … ሚስቱን የሚደበድብ … ሚስት ባሪያ እንደሆነች የሚያስብ ሰው የሌለበት ቦታ!››
‹‹መሸርሞጥ አማረኝ አትዪም!››
‹‹አልልም!››
‹‹ልጄን አታንገላቺው! አሁኑኑ ተመለሽ!››
‹‹የኔም ልጅ ነው ባክህ ልጄ ልጄ አትበል!››
‹‹እና አትመለሺም? ጠገብሽ በቃ? አዋራሽ ቦነነ አይደል!››
‹‹መቼም አልመለስም! ደግመህ እንዳትደውል!›› ስልኩን ጠረቀመችው፡፡
ናርዶስ ንግግሩን በግርምት እያዳመጠች ነበር፡፡ ‹‹ከዚህ ድንጋይ ራስ ጋር ነው አምስት ወር ምናምን የኖርሽው? ማርያምን እኔ አንድ ሳምንት እንኳ አልታገስም ነበር!››
ሂባ የምፀት ፈገግታ ፈገገች፡፡ ‹‹አይ ናርዲ ይኼ አስተሳሰብ እኮ የኔም ነበር፡፡ ቦታው ላይ ስትሆኚ ግን ብዙ ነገሮች ያስሩሻል! ለማንኛውም ቤት ሂጂና የተፈጠረውን በደምብ አብራርተሸ ንገሪያቸው!››
ናርዶስ ከወ/ሮ ዘርፌ ጋር አብራ ሄዳ የተፈጠረውን በሙሉ ለቤተሰቦቿ አስረዳቻቸው፡፡ ዚያድ ደውሎላቸው ከጎረምሳ ጋር እየፈነጨች እንደሆነ ነግሯቸው ነበር፡፡ ናርዶስ የምትለውን ፍፁም ማመን ከበዳቸው፡፡ ጋሽ ጀሚል እና ወ/ሮ ዘምዘም ዱብዳ የወደቀባቸው ያህል ደንግጠዋል፡፡ እየሰሙ ያሉት ሁሉ ፍፁም ካሰቡት በተቃራኒ ነበር፡፡ በመጨረሻም እነሱ ቤት እንዳለች ሲነግሯቸው እጅግ ደነገጡ፡፡ ተጠርታ መጥታ የተፈጠረውን በራሷ አንደበት አስረዳቻቸው፡፡ ወ/ሮ ዘምዘም ተንሰቀሰቁ፡፡ ስለሱ ለልጇ በተናገሩት ነገር ሁሉ አፈሩ፡፡
*
ኢምራን ከትንሿ ቤቱ ሚስኪን ፍራሽ ላይ እንደተጋደመ ጣራ ጣራውን እያየ ያስባል፡፡ በቀመር ወደ ህይወቱ መምጣት ልቡ ትንሽ እንኳ ቢሆን ተረጋግቷል፡፡ ስለሂባ ብቻ በሚያስብበት ጊዜው በፈረቃ የቀመርን ድርጊቶች መዘከር ጀምሯል፡፡ ዛሬ ሂባ እየናፈቀችው ነው፡፡ ከስራ አረፍ ካለና ብቻውን ከሆነ ትዝታ መልህቁን ይጥልበታል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሂባ ለየት ያለ ስሜት እንዳለው አስረግጦ የተረዳበትን ጊዜ አስታወሰ፡፡ ቤተ መፅሀፍ ውስጥ በጋራ የተሰጣቸውን የቡድን ስራ እየሰሩ …. ከጎኑ ተቀምጣ ሀሳቧን ስትሰጥ …. የተናገረችውን መፃፍ አቅቶት እጆቹ ሲንቀጠቀጡ …. ያመመው መስሏት ቀኝ እጁን በግራ እጇ ስትይዘው ….. ‹‹ምነው አመመህ እንዴ?›› ብላ አይን አይኑን በስስት ስታየው …. ሰውነቱ በሙሉ ውሀ የሆነ ሲመስለው ….. ‹‹አላመመኝም›› ብሎ ሲያቀረቅር ….. አረጋግታው የቡድን ስራውን ሰርተው ሲጨርሱ የጋበዘችው ሻይ ….. ለብሳው የነበረው ነጭ ሂጃብ ፣ ጥቁር አባያ እና ጥቁር ሰማያዊ ክፍት ጫማ …. ከፊት ለፊቱ ቆማ እያየችው ያለ ይመስል ወለል ብለው ታዩት፡፡ የዛኔ ሂባን ሰው የሚያገባት …. ከሰው ጋር የምትተኛ …. እንደሰው ደካማነት ያለባት አይመስለውም ነበር፡፡ የሚያፈቅራት እንጂ የሚያገኛት ….. ፍቅረኛው የምትሆን መስሎት አያውቅም፡፡ እጮኛው ከሆነች በኋላም ሲጋቡ የሆነ መቅደስ አዘጋጅቶ ጠዋት ማታ እየመጣ የሚያያት እንጂ እንደሰዉ የሚተኛት አይመስለውም ነበር፡፡ ስለ ልጅ ስታወራለት …. ስለየወደፊት ህልሟ ስታጫውተው ….. ሰው መሆኗን ስታሳምነው ….. አይኖቿ ውስጥ ተስፋ ሲያገኝ ….. እሷን እንደሰው ለማቀፍ …. እንደሰው ለመሳም ….. እንደሰው ለመተኛት የሚያስፈልገውን ቅድመ ሁኔታ ትዳርን ተረድቶ ለመተግበር ተጣደፈ፡፡ ሌላ ሰው እንዳገባች ሲያስታውስ ይናደዳል፡፡ በሙሉ አይኑ እንኳ በቅጡ ለማየት ያልደፈረውን ከንፈሯን ሌላ ሰው እንደገመጠው ሲረዳ ይበሳጫል ….. ግን እንደማያልቅ ያስባል ….. ‹‹የሷማ መቼም አያልቅም!›› ይላል …. ባያልቅ ቢያልቅ ለሱ ይፈይድ ይመስል በከንቱ ሀሳብ ይዋልላል፡፡

እንዳረገዘች ሲ

ልብ - ወለድ

02 Dec, 14:08


ፈገግታዋ ውስጥ ብርታት የሚሰጥ ጨረር ነበር፡፡ የክፍሉ ተማሪዎች እጃቸውን እያወጡ ተመጋጋቢ ሙገሳዎችን አዘነቡ፡፡ ክፍለጊዜው ሲገባደድ ‹‹ለፈተና እንገናኝ ፣ መልካም ፈተና!›› ብሎ ክፍሉን ለቆ ወጣ፡፡ ላፕቶፑን እና ፕሮጀክተሩን ከተሸከሙለት ተማሪዎች ኋላ ቀመር ተከተለች፡፡ ሁለቱ ተማሪዎች የተሸከሙትን አድርሰው ሲመለሱ ወደ ቢሮው ገባች፡፡
‹‹እሺ የኛ ሮሚዮ!›› ድምጧን ከፍ አድርጋ ሳቀች፡፡ ወንበሩ ላይ እየተቀመጠ ፈገገ፡፡
‹‹እሺ አንቺን ማን ልበልሽ?ኢያጎ?››
‹‹ውይ ኢያጎ እኮ ወንድ ነው፡፡ ታሪኩን በደንብ አታውቀውም ማለት ነው!››
‹‹ያው ክፋቱን ብዬ ነው፡፡ እሺ ራስሽ ምረጪ ማን ልበልሽ?››
‹‹ጁሊየት ነዋ!›› እየሳቀች ከፊትለፊቱ ያለው ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹በእጄ መሞት ፈልገሽ ነው?››
‹‹ባንተ እጅ መሞት እኮ ደስ ይላል›› የንግግሯ ትርጓሜ ገባውና ተሽኮረመመ፡፡
‹‹እሺ ጁሊየት …. ትናንት ቤት መጥተሽ ሳንገናኝ አይደል?››
‹‹እኔ ላነብ እንጂ አንተን ላገኝ አልመጣ!›› ምላሷን አውጥታ አንገቷን ወደ ግራ አዘመመች፡፡
‹‹እኔማ የሰራሽውን ወጥ ሳትነኪው ስትሄጂ ምን ጨምራበት ነው ብዬ ሳላስቀምስሽ መብላት ፈርቼ ነው፡፡››
‹‹ወረኛ ያላንቺ አልበላም አለኝ አትልም!››
‹‹እስከዛሬ እኮ ያላንቺ በልቻለሁ፡፡››
‹‹ያኔማ አታውቀኝም ነበር፡፡ አሁን ግን በማር እና በሬት መካከል ያለው ልዩነት ገብቶሀል፡፡››
‹‹በለው በለው! የሆንሽ ጉረኛ!››
‹‹እሺ ስማ ከዚህ በኋላ ቤት ከሰኞ እና እሮብ ውጪም ደስ ባለኝ ቀን እመጣለሁ፡፡ ፋይናል ደርሷል በደንብ መቸከል አለብኝ፡፡››
‹‹ወጥ ለመስራት እና ቤት ለማፅዳት እየመጣሽ ስለማጥናት ታወሪያለሽ እንዴ! አይጋጭም?››
‹‹ዝም በል ባክህ ኮተታም፡፡ በቃ ይኼን ልንገርህ ብዬ ነው፡፡ ልሂድ ቻው!›› በፈገግታዋ እንደተዋበች ቢሮውን ለቃ ወጣች፡፡ ባትሄድ ደስ ይለው ነበር፡፡ ትንሽ ቆዪ ለማለት ግን ድፍረት አጣ፡፡ እየተካሄደ ያለው ነገር ሁሉ ደስ እያለው ፣ በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ እየከፋውም ነው፡፡ ሰው ለምዶ የማጣትን ስቃይ ከዚህ ቀደም አይቶታል፡፡ ድጋሚ እንዳይሰበር ይፈራል፡፡ ከዚህ ወገን ደግሞ ከእስልምና አስተምህሮ ጋር በግልፅ የሚቃረኑትን ወንጀሎች ሳያስበው እየተዳፈራቸው ነው፡፡ ከቀመር ጋር ይህን ያህል ማውራቱ ፣ ብቻቸውን መገለላቸው ….. መዳረሻቸው የት ሊሆን እንደሚችል ሲያስብ ይፈራል፡፡ ‹‹በቃ ከዚህ በኋላ አትድረሺብኝ!›› ሊላት ይፈልግና አቅም ያጣል፡፡
.
ይቀጥላል…

@Lib_Weled

ልብ - ወለድ

02 Dec, 13:51


የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አስራሶስት
(ፉአድ ሙና)
.
‹‹ወይኔ ሂባዬ ተጎሳቆልሽ እኮ!›› ትንሿ የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ እንደተቀመጡ ናርዶስ በስስት አየቻት፡፡
ሂባ ከማልቀስ በቀር የምትመልሰው መልስ አልነበራትም፡፡
‹‹ሂቡዬ ምግብ አትበዪም እንዴ?››
‹‹ፍላጎቴ ወርዷል።››
‹‹እንዴ ፅንሱ እኮ ይጎዳል!››
‹‹አላህ ይሁነው ፅንሱማ! በብስጭቴም አለመጨናገፉ አልሀምዱሊላህ!››
‹‹ኧረ በስመአብ በይ! ደሞ መጨንገፍን ምን አመጣው?!››
‹‹ናርዲዬ እኔ እኮ እዚህ ቤት ስለሚከናወነው ነገር ቅንጣት ታክል እውቀት የለኝም! ሰራተኛዋ ከምታውቀው በዘለለ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ከሰራተኛዋ የምለየው አብሬው በመተኛቴ ብቻ ነው፡፡›› እንባዋ ለጉድ ይፈሳል፡፡
ሂባ ከልቧ ውስጥ ያለውን መጥፎ ስሜት በሙሉ አውጥታ አጫወተቻት፡፡ በመጨረሻም ለሶስት ቀን መኝታ ክፍል ውስጥ መታሰሯን አረዳቻት፡፡ የናርዶስ ቁጣ ጣራ ነካ!
‹‹ሂባዬ ምንም ምክንያት አልፈልግም በቃ ከዚህ ቤት እንውጣ!››
‹‹የእነናንዬ ደስታስ?››
‹‹እነሱ በልጃቸው ስቃይ አይደሰቱም!››
ናርዶስ የምትነፋረቀውን ሂባን አቅፋ አባበለቻት፡፡ በመጨረሻም ከብዙ መወላወል በኋላ ሂባ ቤቱን ለቃ ለመውጣት ተስማማች፡፡ እሱ የገዛላትን ኮተት ትታ በለበሰችው ልብስ ብቻ ለመውጣት ተዘጋጀች፡፡
ዚያድ ከጓደኞቹ ጋር እየቃመ ፣ ሶስቱም ስለሚስቶቻቸው ገላ ውበት እና ከዛም ስለከፋ የሚስቶቻቸው ግላዊ ሚስጥር እያወጉ ነበር፡፡ ሰው በሚስቱ ላይ በልኩ መቅናት ካልቻለ እጅጉን መሪር ነው፡፡ ለጓደኞቹ ስለሚስቱ የአልጋ ላይ ሁኔታ ሲዘረዝር ፣ እጅግ ሚስጥራዊ የሚባሉትን የሰውነት ክፍሎቿን ቅርፅ ሳይቀር ሲነግር ….. እነሱም የእነሱን ሚስቶች የተመለከተ ተመሳሳይ ገለፃ ሲሰጡ ሁለቱ አብሮ አደጎች የውቡን እስር ቤት ክልል ለቀው ወጡ፡፡
ሂባ ከግቢው መውጣቷን ማመን ከበዳት፡፡ በቻለችው መጠን ፈጠን ፈጠን እያለች ለመራመድ ትሞክራለች፡፡
‹‹አይዞን ሂባዬ ከዚህ በኋላ አይደርስብንም!›› ናርዶስ ተስፋ ትሰጣታለች፡፡
የውስጥ ለውስጡን መንገድ ልባቸው እንደተሰቀለ ጨርሰው ታክሲ ለመያዝ አስፓልቱ ዳር እንደቆሙ የሂባ ስልክ ጠራ፡፡
‹‹ደወለ›› ሂባ በድንጋጤ ፈዘዘች፡፡
‹‹ማነው?››
‹‹ዚያድ!››
‹‹በቃ አንሺው እና ከናርዶስ ጋ አስፓልት እቃ ለማየት ወጥተን ነው በይው!››
ስልኩን እንዳነሳችው ዚያድ ‹‹ስሚ እስኪ ከመኝታ ቤት ሹራብ አቀብዪኝ!›› አለ፡፡
‹‹እሺ›› ብላ ቶሎ ስልኩን ዘጋችው።
የእውነት ልብሱን ፈልጎ ሳይሆን በቃል የነገራቸውን በከፊል በአካል ሊያሳያቸው አስቦ ነበር አጠራሩ፡፡ የመቀመጫዋን ውበት ፣ የጡቶቿን ስድርነት …. ብዙ ጊዜ አይተው የቋመጡበትን ድጋሚ ሊያሳያቸው!
የፒያሳ ታክሲ ውስጥ ሲገቡ ድንጋጤው ትንሽ ቀለል አለላቸው፡፡ ናርዶስ በደስታ መንፈስ ሂባን አቀፈቻት፡፡
ታክሲው ስታዲየም ደርሶ ወደ ፒያሳ ሲቅጣጭ ዚያድ መልሶ ደወለ፡፡ አሁን ሂባ ከቅድሙ ተረጋግታለች፡፡ ስልኩን አንስታ ‹‹ቆይ ውጪ ስለሆንኩ ነው ስመለስ አቀብልሀለሁ!›› አለች፡፡
‹‹ውጪ?›› ደነፋ!
‹‹አዎ ውጪ! ምነው?››
‹‹እሺ አሁኑኑ ተመለሽ! አትበሳበሽ!››
‹‹እሺ›› ስልኩ ተዘጋ!፡፡
ናርዶስና ሂባ ተያይተው ተሳሳቁ፡፡ ሂባ እስካሁን ይህን ለማድረግ ባለመድፈሯ እና ስቃይዋን በገዛ እጇ በማርዘሟ አፈረች፡፡ ሳታስበው ፈገግታ ፊቷን ወረረው፡፡
‹‹አየሽ አይደል ቀላል ነው! ዝም ብለሽ ነው ያጋነንሽው!››
‹‹እኔ የነናንዬ ጉዳይ ነው እኮ በጣም ያስጨነቀኝ!››
ናርዶስ ፈገግ አለች፡፡ የጉንጯ ስርጉዶች ፊቷን በብርሀን አጠመቁት፡፡ ‹‹አይዞሽ ሂባዬ እሱም የኔ ሀላፊነት ነው ምንም አያሳስብሽ!››
ሂባ ራሷን የናርዶስ ትከሻ ላይ አሳረፈች፡፡ ናርዶስ በቀኝ እጇ ራሷን አሻሸቻት፡፡
***
‹‹ዛሬ የመጨረሻ ቀናችን ነው፡፡ እንግዲህ ከዚህ በኋላ የሚቀራችሁ ፋይናል ፈተና ብቻ ነው፡፡ በእስከዛሬው ትምህርታችን ላይ ያልገባችሁ ፣ መጠየቅ የምትፈልጉት ነገር ካለ መጠየቅ ትችላላችሁ! አስተያየትም ብትሰጡኝ ደስ ይለኛል፡፡›› የክፍሉ ተማሪ በሙሉ በጥሞና እያዳመጠው ነበር፡፡ ሰላም እጇን አወጣች፡፡
‹‹እሺ ሰላም››
‹‹በመጀመሪያ በፍፁም ጀማሪ አስተማሪ አትመስልም፡፡ በጣም ተመስጠን እንድንከታተልህ አድርገኸናል፡፡ እና ለሱ ላመሰግንህ እወዳለሁ፡፡ ከሱም በተጨማሪ ይኸው ካንተ ጋር እየተማከርን የጀመርነው የሴቶች መብት እና ሴቶችን ማብቃት ላይ የሚሰራው የሴቶች ንቅናቄ እና የወንዶች አጋርነት ቢሮን የማቋቋም ጉዳይ ተሳክቶ ከሚቀጥለው ሴሚስተር ጀምሮ ከግቢው በጀት ተመድቦለት ሊከፈት ነው፡፡ የብዙዎችን ህይወት መቀየር የሚያስችለንን መንገድ ስላመላከትከን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ከግቢው አልፎ ሀገር አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንዲሆን ለማድረግ እንደምንተጋ ቃል እንገባልሀለን፡፡ አንድ ልጠይቅህ የምፈልገውና በሀቀኝነት እንደምትመልስልኝ ተስፋ የማደርገው …. ስለሴቶች መማር ፣ ማወቅ ፣ በራሳቸው እጣ ፈንታ ላይ መወሰን እንድትጨነቅ ያደረገህ ምክንያት ምንድነው?››
የአብዛኞች ልብ ውስጥ የነበረ ጥያቄ ነው፡፡ የክፍሉ ተማሪ በሙሉ አጨበጨበ፡፡ ኢምራን ፈገግ አለ ተሽኮረመመም፡፡ በአይኑ ክፍሉን ቃኘ፡፡ ቀመር አይኖቿን በልጠጥ አድርጋ ምላሷን አወጣችበት፡፡ በሷ አነሳሽነት እንደተጠየቀ ጠርጥሯል፡፡ ፈገግ አለ፡፡ ድጋሚ በትዝታ ሶስት አመታትን ተመለከተ፡፡ የጥያቄያቸው መልስ ያለው ከስድስት ወር በፊት የተፈጠረው ክስተት ላይ እንደሆነ ያውቃል።
‹‹እሺ መልካም …›› ጉሮሮውን ጠረገ፡፡ ‹‹ሂባ የምትባል እጅጉን የምወዳት ልጅ ነበረች፡፡ ….›› የክፍሉ ተማሪ ተመስጦ ይሰማዋል፡፡ ከትውውቃቸው ጀምሮ የገጠመውን ተርኮላቸው ወደ ማገባደጃው ደረሰ፡፡ ‹‹ላገባት ዝግጅት ጀምሬ ቤተሰቦቼ ሁሉ አውቀው ስለመኖሪያ ቦታ በምንጨቃጨቅበት ሰዓት ያላሰብነው ነገር ገጠመን፡፡ የሂባ ስልክ አይነሳም፡፡ ቤተሰቦቼን በጨረፍታ አስተዋውቂያት ነበርና የሷን ቤተሰቦች ልተዋወቅ ቤተሰቦቻችንንም ልናስተዋውቅ ተነጋግረን ነበር፡፡ ስልኳ ሊነሳ ስላልቻለ ቤተሰቦቼ ሳይተዋወቋት ተመለሱ፡፡ ግቢውን ለቀን እንድንወጣ የሚያሳስበው ማስታወቂያ ሲለጠፍ ምናልባት ካገኘኋት ብዬ ወደ ሴቶች ዶርም ሄድኩ፡፡ ውጪ ላይ አላገኘኋትም ነበር፡፡ የመጨረሻ እድሌን ለመሞከር ስል ትመጣለች የሚል ተስፋ ሳይኖረኝ ሰው ልኬ አስጠራኋት፡፡ ከጓደኛዋ ጋር መጣች፡፡ ሂባዬ ተጎሳቁላ ነበር፡፡ ገና አጠገቤ ከመድረሷ መንሰቅሰቅ ጀመረች፡፡ ለማንኛውም ለማሳጠር ያህል ሌላ ሰው ልታገባ እንደሆነ በጓደኛዋ አስተርጓሚነት ነገረችኝ፡፡ እሷ ማግባት የምትፈልገው እኔን እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ የቤተሰቦቿ ውሳኔ ነበር፡፡ ኋላ ላይ ሰውየው ደግሞ የነገርኳችሁን የትምህርት ጥማቷን እንደገደለው ደረስኩበት፡፡ አያችሁ ያን ጊዜ ሂባዬ እምቢ ማለት ብትችል ኖሮ…. ያን ጊዜ የራሷ እጣፈንታ ላይ የመወሰን መብት የሷ እንደሆነ ቤተሰቦቿ ቢረዱ ኖሮ …. የማህበረሰቡ እይታ ባይንሸዋረር ኖሮ …. በሰዋዊ እይታ ስንመለከተው ሂባዬን አላጣም ነበር፡፡ ሌሎች ሂባዎች የማይፈልጉት ሰው ሚስት እንዳይሆኑ …. ሌሎች ኢምራኖች የሚወዱትን እንዳይነጠቁ ….. ሌሎች ሂባዎች መድረስ ካለሙበት እንዳይጨናገፉ የማህበረሰቡ አስተሳሰብ መቀየር እንዳለበት አመንኩ፡፡ ደጋግሜ አሰብኩበት ከዛም ባገኘሁት አጋጣሚ የበኩሌን ለመወጣት ሞከርኩ፡፡ ይኸው ነው፡፡››
የከፊሎቹ ሴቶች አይን በእንባ ራሰ፡፡ ከወንድም ያለቀሱ አንድ ሁለት ተማሪዎች አልጠፉም፡፡ ቀመር ቤቱ ውስጥ የተመለከተችው ጥቅስ መቼ የተፃፈ ሊሆን እንደሚችል ተገለጠላት፡፡ እንባዋን እየጠረገች ፈገግ አለችለት።

ልብ - ወለድ

30 Nov, 20:13


‹‹ይቺ የሆነ ቦታ ተደጋገመችሳ! ይነገረን እንጂ!›› ሀይማኖት ጣልቃ ገባች፡፡
ቀመር ዝም ስትል ሁሉም በአይናቸው ይመረምሯት ገቡ፡፡ ኢማን ከስግደት በፊት የሚደረገውን ትጥበት (ውዱዕ) አድርጋ ስትመለስ ሁሉም ቀመር ላይ አፍጥጠው ሲመለከቷት ደረሰች፡፡
‹‹እንዴ ልትበሏት ነው እንዴ?›› ኢማን ከተመስጧቸው ገታቻቸው፡፡
‹‹አንቺ ደሞ ከሁለት ሰዓት በኋላ ነው እንዴ የምትሰግጂው? ፀሀይ እኮ ከወጣች ቆየች፡፡›› ሀያት ሳታስበው የወሬውን አቅጣጫ ቀየረችው፡፡ ኢማን የንጋት ስግደትን በሰዓቱ እንደመስገድ የሚከብዳት ነገር የለም፡፡ ሁሌም ቢሆን ፀሀይዋ ካፈጠጠች በኋላ እንጂ ሰግዳ አታውቅም፡፡ ሀያት ዛሬ የወር አበባ ላይ ስለሆነች አትሰግድም እንጂ ሌላ ጊዜ ከቀመር እኩል አልያም ትንሽ ዘግይታ ተነስታ ትሰግዳለች፡፡
‹‹ከምተወው ይሻላል ብዬ ነዋ!›› እየተነጫነጨች መስገጃዋ ላይ ተመቻቸች፡፡
‹‹let us go! ቁርስ እንብላ!›› ኢማን ከሰገደች በኋላ ተያይዘው ወጡ፡፡
ቁርስ ከበሉ በኋላ ቀመር ወደ ኢምራን ቤት ሄደች፡፡ እግረ መንገዷን ከጉሊት የሚያስፈልጓትን ግብዓቶች ሸመተች፡፡ የግቢው በር ጋ ደርሳ ወደ ውስጥ ስትዘልቅ ወ/ሮ አርሴ የቤታቸው በረንዳ ላይ ተቀምጠው ቡና እየጠጡ ነበር፡፡
‹‹ኢንዴ ኢንዴ የአምረኔ ሚስት በጧት መጣች›› ሰላም ሊሏት ከመቀመጫቸው ተነሱ፡፡ ሰላም ከተባባሉ በኋላ በስስት እያዩዋት ‹‹ውይ አምረኔ እኮ በጧት ሄደ፡፡›› አሉ፡፡ ፈገግ ብላ ቁልፍ እንደያዘች ነግራቸው በሩን ከፍታ ገባች፡፡ ቤቱን ከፍታ በሩ ጋ እንደቆመች ቤቱን በአርምሞ ቃኘችው፡፡ ሁሉንም ነገር እንደ አዲስ አስተካክላ ቤቱን ለማሰማማር አስባለች፡፡ የእጅ ሰዓቷን ስትመለከተው ሶስት ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡በፌስታል የያዘችውን ሺቲ ከቀየረች በኋላ ወለል እና ፍራሹን ሳይቀር ሁሉንም ኮተት ውጪ ላይ አውጥታ ቤቱን ጠረገችው፡፡ ወለሉን በወ/ሮ አርሴ መወልወያ ከወለወለች በኋላ እቃዎችን እያራገፈች እና እየወለወለች ከነበሩበት በተለየ አኳኋን አስውባ ሰደረቻቸው፡፡ ቤቱን አስውባ ከጨረሰች በኋላ ትንሽዬ ቅርጫት ውስጥ የታጨቁትን የቆሸሹ ልብሶች አውጥታ አለቀለቀቻቸው፡፡ ልብሶቹን አጥባ ስትጨርስ ሰዓቷን ተመለከተች፡፡ አምስት ሰዓት ከሩብ ሆኗል፡፡ ስቶቩን ለኩሳ ባገኘቻት ትንሽዬ ድስት ቆንጆ ምስር ወጥ ሰራች፡፡ ስራዋን ካጠናቀቀች በኋላ ሺቲውን አውልቃ ስትመጣ የለበሰችውን ቆንጅዬ ቀሚስ ለበሰች፡፡ ድካም ያረፈበትን ፊቷን ወደ ጠዋቱ ብርሀናማ ጉልበት ለመመለስ ሞከረች፡፡
ትንሽ አረፍ እንዳለች የቤቱ አባወራ ከተፍ አለ፡፡ ግቢው ውስጥ ልብሶቹ ተሰጥተው ሲያይ ደነገጠ፡፡ በሩን ከፍቶ ሲገባ ቤቱ ውስጥ የተነፋው ሽቶ ጠረን አወደው፡፡ ግድግዳው ላይ ከለጠፈው ጥቅስ በቀር ሁሉም ነገር ቦታው ተቀያይሯል፡፡ ቀመር ፍራሹ ላይ ተቀምጣ ሲያያት ፈገግ አለ፡፡ እሷም ፈገገች፡፡
‹‹እሺ ቀውሷ አነባለሁ ያልሽው ቤቴን ነው እንዴ!›› ሳቀ፡፡
‹‹እንግዲህ እንደምታየው ከገሀነም ወደ ገነት እድገት አግኝተሀል!›› ተፍነከነከች፡፡
‹‹ባክሽ እንደውም አስተካክላለሁ ብለሽ አበላሸሽው››
‹‹መስተካከል አታውቅማ ለዛ እኮ ነው››
‹‹የምር ግን ቤት ለሴት ያሽቋልጣል ልበል?››
‹‹ወንድ አይደል እንዴ ወዶ ነው!›› ተሳሳቁ።
ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ እንጀራ ገዝቶ መጣና ምሳቸውን የሰራችውን ምስር በሉ፡፡ ከከሰዓት ትምህርት ስለነበራት ከሰገዱ በኋላ ወደ ግቢ ሸኛት፡፡ እየተካሄደ ያለው ነገር ሁሉ ከቁጥጥሩ ውጪ እየሆነ ፣ በፍፁም ይሆናሉ ብሎ ያላሰባቸው ነገሮች እየተከሰቱ ነው፡፡ ይህቺ የእሳት ዳር ጨዋታ በአግባቡ ካልሞቋት ማቃጠሏ አይቀርም፡፡ ቀመር በውሎዋ ተደስታ እየፈነጠዘች ወደ ግቢ ገባች፡፡
.
ይቀጥላል…

@Lib_Weled

ልብ - ወለድ

30 Nov, 20:13


የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አስራ ሁለት
(ፉአድ ሙና)
.
ናርዶስ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ኤርሚያስ የሰጣትን የስነ ልቦና ፊልም ተብዬ የወሲብ ፊልም ቀጣይ ክፍሎች ተመለከተቻቸው፡፡ የፈልሙን ታሪክ በጣም ወዳዋለች፡፡ ልቅነቱንም የጠላችው አይመስልም፡፡ አርብ እለት ምሽቱን ስልኳ ላይ ያሉትን ፊልሞች በሙሉ ስለተመለከተቻቸው ወደ ላፕቶፕዋ ገለበጠቻቸውና ያላየቻቸውን ሁለት አማርኛ ፊልሞች ወደ ስልኳ ላከች፡፡ ከአምስት አመት በፊት ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስትመደብ ከአጎቷ በስጦታ የተበረከተላት ላፕቶፕ ስክሪኑ መሀል ላይ በከፊል ስለፈሰሰ ፊልም ለማየት ምቹ አይደለም፡፡ ሁሌም በምሽት ፊልም ልታይ ስትል የምታደርጋቸውን ጥቁር መነፅር የማድረግ ፣ መብራት የማጥፋት ፣ የጆሮ ማዳመጫ የማጥለቅ እና ብርድልብስ ውስጥ በአግባቡ ተጠቅልሎ የመጋደም ቅድመ ሁኔታዎችን ከከወነች በኋላ ፊልሙን ከፈተችው፡፡ ፊልሙ ምርጥ ከተባሉ ሀገርኛ ፊልሞች መካከል አንዱ ነው፡፡ ፊልሙን እያየች ደቂቃዎች ተቆጠሩ ፤ ፊልሙ ግን ምንም ሊጥማት አልቻለም፡፡ የሆነ የጎደለው ነገር እንዳለ ይሰማታል፡፡ ዘጋችውና ሌላኛውን ፊልም ከፈተችው፡፡ ትንሽ ከተመለከተችው በኋላ በጭራሽ ሊጥማት ስላልቻለ ፊልሙን ዘግታ ተጠቅልላ ተኛች፡፡
ለሊቱ ተሸኝቶ ፀሀይ ብቅ ማለት ሲዳዳት ከእንቅልፏ ተነስታ ለስራ ተዘገጃጀች፡፡ ቅዳሜ ስለሆነ ታክሲ ብዙም ሳትቸገር በጊዜ ቢሮ ገባች፡፡ ዛሬ ስራ ያላት ግማሽ ቀን ብቻ ነው፡፡ ታክሲው ውስጥ ሆና ከኤርሚያስ ጋር ፌስቡክ ላይ እየተፃፃፈች ነበር፡፡ ቢሮ ስትደርስ አሳወቀችው፡፡ ሲክለፈለፍ ከቢሮዋ ከተፍ አለ፡፡ የናርዶስ ቢሮ በጣም ጠባብ ናት፡፡ እንዲሁ ለመቀመጥ እና አንዳንድ የፅሁፍ ስራዎችን ለማስተካከል ቦታ እንዳትቸገር ተብሎ ይሆናል እንጂ ዋናው ስራ የሚሰራው ቢሮ ውስጥ አይደለም፡፡
‹‹ንግስት ሆይ እንደምን አደሩ?›› ከወገቡ አጎነበሰ፡፡
‹‹ተኝቼ አደርኩ ህዝቤ ሆይ›› ብላ ራሷ ተንከተከተች፡፡ ተሳሳቁ፡፡
ጉንጯን ከሳማት በኋላ እጁን ትከሻዋ ላይ አስደግፎ ጠረጴዛዋ ላይ ተቀመጠ፡፡ የሆነ ያየችው ፊልም ላይ ያለውን ወጣት ባለሀብት እየመሰላት ነው፡፡ ጠቋሚ ጣቱን በአውራ ጣቱ አፈናጥሮ ጉንጯን ጠበሳት፡፡ ፈገግ ስትል የጉንጯ ስርጉድ ፊቷ ላይ ምትሀታዊ ውበት ረጨ፡፡ የሆነ ነገሩን እንደወደደችው መካድ አትፈልግም፡፡ ያጠራጠራት ልክ የመሆን ያለመሆኗ ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ሂባን ለማማከር ብትፈልግም ሊመቻችላት አልቻለም፡፡
‹‹ስሚ የላኩልሽን ጨረስሽው እንዴ?›› ጉንጯን እየቆነጠጠ ጠየቃት፡፡
‹‹ውይ አዎ ጨረስኩት እኮ ….. ትናንት ለካ አልተገናኘንም….. እንደውም ማታ የማየው አጥቼ ደብሮኝ ነበር፡፡››
‹‹ይላክልሻላ እድሜ ለኔ›› ፈገጉ፡፡
ከስልኩ ውስጥ ተከታታይ የወሲብ ፊልም ላከላት፡፡ እንደከዚህ ቀደሙ በከፊል ቁጥብነት ያለው ቀረፃ ያለው ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ ልቅ በሆነ መልኩ የተቀረፀ ፊልም ነበር፡፡ ኤርሚያስ ወደ የት እያንደረደራት እንደሆነ ያውቃል፡፡
‹‹ሶስት ክፍል ነው የላኩልሽ አንድ ክፍል ይቀረዋል እሱን እኔም አላየሁትም ከተመቸሽ ስቀበል እሰጥሻለሁ፡፡›› የቀረውን አንድ ክፍል ያልላከላት የላከላትን ልቅ ፊልም አይታ ቀጣዩን ላክልኝ ትላለች ወይስ ይቅርብኝ ትላለች የሚለውን ተመልክቶ ቀጣይ እርምጃውን ለመወሰን እንጂ እንዳለው የእውነት ፊልሙ ሳይኖረው ቀርቶ አይደለም፡፡
‹‹ስማ ሰውየው ዛሬ ብድሬን ልመልሳ! ልጋብዝህ?›› አንገቷን ቀና አድርጋ በስሱ ተመለከተችው፡፡
‹‹ተይ እንጂ! ካንቺ ጋር በቅዳሜ ቀን ስፕራይት ልጠጣ? አመመኝ እንዴ!››
‹‹ምን ታካብዳለህ ከፈለግክ አንተ አተላህን መጠጣት ትችላለህ እኮ!››
‹‹ገብስ ከለስላሳ አጠገብ ሲሆን ሙዱ አይመጣማ! በስራ ቀን ይሁንልኝ ግብዣው፡፡››
‹‹ቀረብሀ ኮተታም!›› በልቧ አብራው ሄዳ ትንሽ ፉት ለማለት እየወላወለች ነበር፡፡
*
ሂባ ምን መወሰን እንዳለባት ግራ ተጋብታለች፡፡ ሁለ ነገሩ አስጠልቷት ለመፋታት መንገዱን ለመጀመር ታስብና ቤተሰቦቿ ለእሱ ያላቸውን እሳቤ ስታስብ ነገሩ ሁሉ ሳትጀምረው ይደክማታል።
ከሶስት ቀን ቅጣቱ በኋላ በሩን አልቆለፈባትም፡፡ በሩ ሲከፈትላት የምትሄድበት ጠፋት፡፡ ምናልባትም ሳታስበው የሶስቱ ቀን ቅጣት ውስጧ ላይ ተፅዕኖ ፈጥሮ ሊሆን ይችላል፡፡ አሊያም ከእናቷ የሰማችው ነገር! የፎቁ ሰገነት ላይ እንደቆመች ሰራተኛዋ ከኋላዋ መጣች፡፡
‹‹እንዴ ተሻለሽ እንዴ?››
‹‹መቼ አመመኝ?››
‹‹ጋሼ እኮ ታማለች ብሎኝ ነበር፡፡ ልጠይቅሽ ፈልጌ ሰው መግባት የለበትም አለኝ፡፡››
‹‹እ እሱንማ አዎ አሁን ተሽሎኛል፡፡ መኝታ ክፍሉ በጣም ሳይቆሽሽ አይቀርም ግቢና አፅጂው፡፡››
‹‹እሺ እሺ›› እየተጣደፈች ወደ መኝታ ክፍሉ ሄደች፡፡
ሂባ ሰገነቱ ላይ እንደቆመች አካባቢዋን ቃኘች፡፡ ራመድ ብላ ወደ ሰገነቱ ጫፍ ተጠግታ ቁልቁል መሬቱን ተመለከተችው፡፡ ወደ ታች ተፈጥፈጪ ተፈጥፈጪ አላት፡፡ ‹‹አኡዙቢላህ›› ብላ ሽው ካለባት መጥፎ ሀሳብ ወደ ጌታዋ ጥበቃ ሸሸች፡፡ ስልኳን እንደያዘች ኢምራን ጋር የመደወል ሀሳብ ብልጭ አለባት፡፡ አመነታች፡፡ ድምፁን መስማት ትፈልጋለች፡፡ ምንም እንኳ እሱን ከካደች በኋላ እየተቀበለች ያለውን መከራ ልትነግረው አቅም ባይኖራትም ፣ ከጭን ገረድነት የዘለለ ሚና እንደሌላት ልታሳውቀው ባይዳዳትም ፣ ይዘኸኝ ጥፋ ለማለት የሚያስችል ወኔ ባይደግፋትም ፤ ቢያንስ እንኳ ድምፁን መስማት ትፈልጋለች፡፡ ደወለች፡፡ ጥቂት ከጠራ በኋላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ›› የኢምራን ወፍራም ድምፅ ተሰማ፡፡ እጆቿ ተንቀጠቀጡ፡፡ ‹‹ሄሎ ማን ልበል?›› ኢምራን ይጣራል፡፡ እንባዋ ከፊቷ ላይ በፍጥነት ይፈሳል፡፡ ሰውነቷ ይንዘፈዘፋል፡፡ ድምፅ ላለማውጣት ከንፈሮቿን በሀይል አሳስማ ይዛቸዋለች፡፡
‹‹ሄሎ ሄሎ›› ስልኩ ተዘጋ፡፡
የታፈነውን ድምጧን ከፍ አድርጋ እንባዋን አወረደችው፡፡ ሰባት ሰዓት ሊያልፍ ሲል የባልየው መኪና ከውጪ በኩል ቆሞ ጥሩንባውን ሲነፋ ተመለከተች፡፡ መኪናው ግቢው ውስጥ ከገባ በኋላ ሁለት ጓደኞቹ የተለመደውን ሰው የሚያክል ጫት ይዘው ወረዱ፡፡ ለጫት የሚሰጠውን ያህል ቦታ ቢሰጣት ትመኛለች፡፡ ሲመስላት ያን ያህል በውዴታ ቢቀርባት ኖሮ እሱን ለመለወጥ አትቸገርም ነበር፡፡ አሁን ግን ሁሉም ነገር ድካውን እያለፈ መስሏታል፡፡ ከሁሉም ከባዱ ነገር ቤተሰቦቿ ለሱ ያላቸውን የተሳሳተ አመለካከት ማስተካከሉ ነው፡፡
ናርዶስ የውጪውን በር አስከፍታ ስትገባ ስታይ ደስታ ወረራት፡፡ ቢያንስ የምታወራውን ሰምቶ መረዳት የሚችል አንድ ፍጡር ከውቡ እስርቤት ክልል ውስጥ ገብቷል፡፡
*
ቀመር የእሁድ ለሊት አመት ያህል ረዘመባት፡፡ የሰኞ ጠዋት ለመጀመሪያ ጊዜ የኢምራን ቤት ውስጥ ብቻዋን የምታሳልፍበት እና ለወራት ያቀደችውን መተግበር የምትጀምርበት ጠዋት ስለሆነ ናፍቋታል፡፡ ይርቃል እንጂ አይቀርምና ጎህ መቅደዱን የመስጂድ እና የቤተ ክርስቲያናት ድምፆች አበሰሩ፡፡ ከመኝታዋ ተነስታ ከስግደት በፊት የሚከወነውን ትጥበት ለመከወን ውሀ ፍለጋ ወጣች፡፡ በውስጧ የኢምራን ጠባብ ቤት ውስጥ ገብታ ስትንጎዳጎድ ይታያታል፡፡ የንጋት ስግደቷን ከከወነችና ለአንድ ሰዓት ያኽል ካጠናች በኋላ እየዞረች ጓደኞቿን መቀስቀስ ጀመረች፡፡ በጠዋቱ ተነስተው ልብስ ለማጠብ ተነጋግረው ነበር፡፡ ከረዥም ጭቅጭቅ በኋላ ሁሉም ከእንቅልፋቸው ተነሱ፡፡
ሊዲያ ቀመር ስትሽቀረቀር ስታይ እየሳቀች ‹‹hey dude እዛ ቁርስ ምንበላበት ቤት crush አለሽ እንዴ? Class እኮ አንገባም ምንድነው እንደዚህ መሽቀርቀር?›› አለች፡፡
‹‹እኔ እኮ በዛው የሆነ ቦታ ልሄድ ነው! ዛሬ ልብስ አላጥብም!››

ልብ - ወለድ

29 Nov, 04:59


‹‹ክላስ ሲኖረኝ ብቻ ነው፡፡ ከዛ ውጪ ያው መስጂድ ካልሆንኩ ቤት ነኝ፡፡››
‹‹ከኛ ክላስ ውጪ ስንት ክላስ ታስተምራለህ?››
‹‹ሁለት››
‹‹ዕሮብ እና ሰኞ ጠዋት ላይ ክላስ የለንም እና ቤት ትኖራለህ እንዴ?››
‹‹አልኖርም፡፡ በቃ ያኔ መምጣት ትችያለሽ፡፡››
ቀስ እያሉ ጎዳናው ላይ ሲጓዙ ላያቸው ባልና ሚስት ሳይመስሉት አይቀሩም፡፡ ለትንሽ ደቂቃዎች በመካከላቸው ዝምታ ነገሰ፡፡ ቀመር ዝምታውን መስበር ፈለገች፡፡
‹‹እሺ ዛሬ ስለ ሂባ አትነግረኝም?››
‹‹እሱን ብድርሽን ስትከፍዪ እነግርሻለሁ፡፡››
በየመሀሉ አንዳንድ ጥያቄዎችን እየተጠያየቁ ከኢምራን ትንሿ ቤት ደረሱ፡፡ የግቢው መግቢያ ጋ ሲደርሱ የኢምራን አከራይ ወ/ሮ አርሴ እንጨት እየፈለጡ ነበር፡፡ ከቀመር ጋር አስተዋወቃቸው፡፡ ወ/ሮ አርሴ ፈገግ ብለው ‹‹ዎይ አምረኔ አበባ ሚትመስል ሚስት አይደል እንዴ ያመጣኸው?›› አሉ፡፡ ቀመር ኢምራንን እያየች ከልቧ ፈገግ አለች፡፡ እሳቸውን አልፈው ወደ ግቢው ገቡ፡፡ ሰፋ ያለ ግቢ ነው፡፡ ወ/ሮ አርሴ የሚኖሩበት ቤት ከሚያከራዩዋቸው ቤቶች የተሻለ አይደለም፡፡ በሩን ከፍቶ ገባና መብራቱን ካበራ በኋላ እንድትገባ ጋበዛት፡፡ቤቱ ውስጥ አንድ ፍራሽ ወለሉ ላይ ከመጋደሙ በዘለለ ብዙ ኮተት የለም፡፡
‹‹ኦው አሪፍ…… ስቶቭ አለህ!›› ቀመር የቤቱ የግራ ጥግ ጋ የተቀመጠውን ስቶቭ እየጠቆመች ፈገገች፡፡ ሰዓቱ በጣም እየሄደ እንደሆነ እየተሰማው ነው፡፡ አንድ ክፍል ውስጥ ብቻቸውን መሆናቸው ሰላም ነሳው፡፡ ቀመር ፍራሹ ላይ ሄዳ ተቀመጠች፡፡
‹‹ፍራሹም አሪፍ ነው ግን አንተ ብቻ የተኛህበት አይመስልም፡፡ ማለቴ ሂባም በሀሳብ አብራህ ሳትንከባለልበት አትቀርም፡፡›› አለችና ቀና ስትል ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ፅሁፍ ተመለከተችና ጮክ ብላ አነበበችው፡፡ ‹‹ሴት ልጅ እናትህ ስትሆን አማራጭ ስለሌላት ነው ፣ እህትህም ስትሆን ተፈጥሮ አስገድዷት ነው። ሚስትህ ስትሆንም ቤተሰቧ ፈርዶባት ነው። አንድም ቀን በራሷ ላይ የመወሰን አቅም የሌላትን አካል አታፍቅር!›› አይኖቿን በምርመራ ጨረር አጅባ አይኑ ላይ ወረወረቻቸው፡፡
‹‹ይኼን አንተ ነህ የፃፍከው?››
ፅሁፉን ባታየው ደስ ይለው ነበር፡፡ አይኑን መሬት ላይ እየተከለ ‹‹አዎ›› አላት፡፡
‹‹እና ክፍል ውስጥ ከምትለው ጋር አይጋጭም?››
‹‹አይጋጭም እንደውም ተመጋጋቢ ነው፡፡››
‹‹ኦው ሂባ›› ፈገገች፡፡ በልቧ ሚስጥሩን የማወቅ ፍላጎቷ ንሯል፡፡ ግን ዛሬ ይሁን ብላ ልታስጨንቀው አልፈለገችም፡፡
‹‹በቃ ቤቱን አየሽው አይደል ነይ ልሸኝሽ!››
‹‹ኧረ እንግዳ ቤት ገብቶ በባዶ አይሸኝም፡፡››
‹‹ማነው እንግዳ? ኧረ የኔ ቤት ነው እንዳትዪኝ እየፈራሁ ነው፡፡››
‹‹ቤቱማ የአከራይህ ነው ኮተታም››
ከተቀመጠችበት ተነስታ በሩ ጋር ስትደርስ ከነበሩት ሁለት የበር ቁልፎች ውስጥ አንዱን ሰጣት፡፡ ሁለ ነገሯ ያሳሳል፡፡ አንዳንዴ ሂባን በሷ ውስጥ የሚያይ ይመስለዋል፡፡ በልቧ የዚህ ቤት ንግስት ስለመሆን አሰበች፡፡ የምትፈልገው መስመር ላይ በምን መልኩ ማስገባት አንዳለባት በደንብ ታውቃለች፡፡ ጅምሯም እየሰመረ ይመስላል፡፡ ወ/ሮ አርሴን ተሰናብታ ስትጨርስ ወደ ግቢ ሊሸኛት መንገድ ጀመሩ፡፡
ፀሀይ በዚህ መልኩ ወደ ማደሪያዋ ከገባች በኋላ ከሴት ጋር ዎክ አድርጎ አያውቅም፡፡ ልቡ እሷን ቶሎ ሸኝቶ መንገድ ላይ ያለው መስጂድ ገብቶ ለመስገድ ቸኩሏል፡፡ የግቢ በር ጋር ከመድረሳቸው ብዙም ሳይርቅ ተሰናበታትና እየተጣደፈ ወደ መስጂድ ሄደ፡፡ እሷ ልቧ በሀሴት እንደተሞላ ወደ ዶርሟ ተጣደፈች፡፡ እሱ የመቀራረባቸው ጉዳይ እያሳሰበው ነው፡፡ በዚህ መልኩ እንድትቀርበው በመፍቀዱ ይፀፀታል፡፡ ድጋሚ ሴት መቅረብ ፣ ድጋሚ መጎዳት አይፈልግም፡፡
.
ይቀጥላል…

@Lib_Weled