እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 💛
▬▬▬❁ክፍል ሰባት▬▬▬
ይቅር ብዬካለው ስለው ከወደቀበት ተነስቶ የመውጫ ከፍሎ ተያይዘን ወጣን እና ታክሲ ያዝን ምንም አላወራውም እሱም ዝም እኔም ዝም ትንሽ እንደቆየ
፨ ይቅር ያልሽኝ ግን ከምርሽ ነው አለ በመሀላችን ያለውን ፀጥታ ለመስበር
፨ ውስጤ እንደዛ ነው እንግዲ የሚለኝ
፨ አመሰግናለው በጣም። ቤቲ ልጃችንስ አለ በመሀል ትውስ ብሎት
፨ ቤት ነው አልኩት
፨ በቃ ወዳንቺ ቤት እንሂድ ማየት አለብኝ ብሎ ወደቤት ተያይዘን ሄድን ሚኪ ተኝቶ ነበር ። የሁልጊዜ ጥያቄው እንደመጣ አላወቀም። ግን እኔም ለምን ሳሚን ይቅር እንልኩት አልገባኝም ።
ያንን ቀን እኔ ቤት አደረ ጠዋት ላይ ከሚኪ ጋር አስተዋወኩት ግን አጎትክ እንጂ አባትክ ብዬ አልነበረም እሱም ደስ ብሎት ተዋወቀው ። ልጄን ሳየው ያሳዝነኛል ባላጠፋ ከኔ ከማትረባዋ ተወልዶ በልጅነቱ መከራውስጥ ሲገባ በዚች ትንሽ ጭንቅላቱ የሚመላለሱበት ጥያቄዎችን ሳስብ ሁሌም ያሳዝነዝኛል።
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,. ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ቀኑም ቅዳሜ ስለነበር ልጄ ትምርት ቤት አይሄድም ለመጀመሪያ ጊዜ ተረጋግቼ ቅዳሜን አሳለፍኩ ሳሚ የቤት ውስጥ ስራውን ጨራርሶ እኔ ከአልጋዬ ሳልነሳ ነበር የዋልኩት ዋው ጥሩ ቀን ነበር ሳሚና ሚኪም በደንብ ተግባብተዋል። ምንም ዛሬን ብደሰት ለነገም መኖር አለብኝ እና ወደ ስራ ለመሄድ ተነሳው ልብስ ለባብሼ እንደጨረስኩ ሳሚም አብሮኝ እንደሚ ሄድ ነገረኝ እና ተያይዘን ወጣን ።
፨ ዛሬ ራት ብጋብዝሽስ ቅርይልሻል አለኝ
፨ አልችልም መስራት አለብኝ...... ብዬ ሳልጨርስ
፨ ሽርሙጥናም ስራ መሆኑ ነው አለና እሱ ቶሎ ደነገጠ ሳያስበው የተናገረው መሆኑ ያስታውቃል
፨ ቢገባክ አንተ የጣልከንን እኛን የማኖርበት ስራዬ ነው እሺ ብዬ በንዴት ጥዬው ልሄስ ስል
፨ቤቲዬ ይቅርታ ለማለት የፈለኩት እንደዛ አይደለም ። ብሎ ማለቃቀስ ጀመረ
በቃ ለዚ ንግግሬ መካሻ እንዲሆን ዛሬ በኔ ወጪ አንቺ የፈለግሽበት ቦታ ልጋብዝሽ አለኝ ። ከጋበዝክ አይቀርማ ብዬ ወደ አንዲ ታዋቂ ክለብ ወሰድኩት ከዛ መጠጣት ጀመርን።
ቀወጥነው ራሴን እስክስት ድረስ ነበር የጠጣውት ቤት እየቀያየርን ይህን መጠጥ እንለው ገባን ደስ ይል ነበር የሴተኛ አዳሪ መዳኒቱ ሱሱ ነው ሁሉንም ማስረሻው ቢራን የፈጠረ ጭንቅላት እያመሰገንን ተጋትነው። ከዛ አልጋ ይዘን አብረን አደርን.......
ጥሩ ቀን ጥሩ ምሽት አሳለፍን ደስ ይል ነበር ግን ሳሚ በተደጋጋሚ የህመም ስሜት ይሰማዋል ግን ለኔ ለማሳየት አይፈልግም ደናነኝ እያለ ይሸፋፍነዋል።
ጠዋት ላይ ተነስተን ወደ ቤት ሄድን ሚኪ ት.ቤት ሊሄድ ሲል ነበር የደረስነው ከዛ አብረን ት.ቤት አድርሰነው ስንመለስ ሳሚ አንድ ያልጠበኩትን ጥያቄ ጠየቀኝ።
፨ማታ በመከላከያ ነው ወይስ እንዲው የወጣነው አለኝ
፨ማለት ከመቼ ወዲ ነው እኔ እናንተ በ... አላስጨረሰኝም.
፨ ማለት በባዶ ነው ወይኔ አለቀልክ በይኛ አለ እየጮኸ
፨ምንድነው በሽታ ፈርተክ ከሆነ አታስብ እኔ ሁሌም እመረመራ ለው ነፃ ነኝ አልኩት የድንጋጤው ምክንያት ይህ መስሎኝ
፨አደለም እኮ...... ብሎ ሊናገር ያሰበውን ሳይናገር ዝም ብሎ ሄደ
ታድያ ምንድነው ግራ አጋባኝ ግን እኔን ጠርጥሮ እንደሆነ ገምቼ ተውኩት።
ከሳሚ ጋር ከተገናኘን ሳምንታት ተቆጠሩ ጥሩ ጊዜ እያሳለፍን ነበር። ልጄም በአጎቱ መምጣት ተደስቶ ነበር ያው አባቱ እንደሆነ ስለማያቅ ነው።
ግን ችግር የማያጣው ህይወቴ ትልቅ ችግር ይዞብኝ መጣ ከቅርብ ጊዜ ወዲ ሳሚ በጣም እያመመው ነው ክብደት መቀነስ እና ጥቁርቁር እያለነው።
ከዛሬ ነገ ይሻለዋል ስል ጭራሽ ከአልጋ ወደቀ ሆስፒታል እንሂድ ስለው እንቢ ይላል አሁንማ እኔንም የህመም ስሜት እየተሰማኝ ነው ግን ጭንቀት ይሆናል ብዬ ትኩረት አልሰጠውትም።
ገንዘብ ብዙ አይቸግረንም እኔም ስራ ሰራለው ሳሚም ከየት እንዳመጣው ባላቅም በቂ የሚባል ገንዘብ አለው።
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ቀኑ ቅዳሜ ነው እንደተለመዱት ቀናት ምንም ለውጥ የለበትም ደስ ብሎኝ አልነቃውም ደስብሎኝም ነቅቼ አላቅም። በዚ ሰአት የምነቃው ማታ የሰራውበትን ለመቀበል ነው።
ዛሬም ቢሆን የማረገው ያንን ነው ገንዘቤን ተቀብዬ ወደ ቤት ተመለስኩ ሳሚ ቀን በቀን እየባሰበት ነው ሊሞት አንድ ሀሙስ የቀረው ሰው ሆኗል።
፨ በቃ ዛሬን ዝም አልልክም ሀኪም ቤት መሄድ አለብን አልኩት
፨አል..ፈል..ግም.አለኝ በተቆራረጠ ድምፅ ልሰማው አልፈለኩም።
አንድ ደንበኛዬ የሆነ ባለላዳ ልጅ ጠርቼ በግድ ሀኪም ቤት ወሰድኩት። ከዛ ለልጁ ሂሳብ ልከፍል ስል ውይ ቆንጂዬ አልቀበልም ሶሞኑን ብቅ ስለምል ታካክሽዋለሽ ብሎኝ ሄደ በቃ ወንድ በስሜቱ ምንም ይለውጣል ብሽቅ ብዬ ወደ ሳሚ ተመለስኩ ዶክተሩ ከመረመረው ቡሀላ ውጤቱን ነግረኝ ምን ውጤቱን መርዶዬንም እንጂ በድንጋጤ ደርቄ ቀረው
ይቀጥላል....
✎ ክፍል ስምንት ከ 200 Like በኋላ ይቀጥላል❤️🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።
┄┄┉┉✽»🌺✿🌺»✽┉┉┄┄