Konso News @konsonews Channel on Telegram

Konso News

@konsonews


በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ አስተያየቶቻችሁን ላኩልን፡ [email protected]

Konso News (Amharic)

ከማብሽተኛ በወጣሽ አንዋይነት እንዳለው የቼሎግሰብ ዘገባ እና አስተሳስረናል ተማሪዎችን በደሓን ኮንስወርት፡ Konso News መረጃ። ከዚህ በታች አምናም ምን ያህል ነው? እና እስኪማይከበር እስክፈከረሽ የቴሌግራም መረጃዎችን ለማግኘት እንደዚህ ያለውን አገልግሎት የሚውሉ ሰዎች ለዚህ ካንሰ ወሬ ላይ ያሉ የተለያዩ ቀናት ወጥተዋል። Konso News ከፍተኛ ውርም ከሆነ በደሓን ኮንስወርት ከላይ ማንም አይነት ተማሪዎችን ያዙ። እንዲህም ያማል እንዲመረጠ እርዳታ የሚፈፅም የቴሌይግራም መረጃዎችን በድለና እንደዚህ ካለ አድራሻ ቁጥር በችግር ስለምንከተለው እንዴት መኖሩን ማስብለዋለሁ የሚልሽ። Konso News ላይ በኢሜይሉ አድራሻ ውስጥ ከሚቀጥለው አገልግሎት የተማሪዎችን ተመልከቱ።

Konso News

21 Aug, 17:46


ወገን ምን ይበጃል?! ማለቃችን ነው እኮ!

Konso News

02 Jun, 13:29


https://www.youtube.com/watch?v=W0_PS89ufrY&t=9s

Konso News

28 May, 14:50


ፍትሕ ምንድን ነው?

Konso News

03 Sep, 04:41


Konso News pinned «3ኛው የኮንሶ ምሁራን የምክክር ጉባኤ በዞኑ መዲና በካራት ከተማ እየተካሄደ ነው ካለፉት ሦስት አመታት ጀምሮ በነሐሴ ወር የመጨረሻው ሳምንት በኮንሶ ዞን ዋና ከተማ ካራት ከተማ በየአመቱ የሚካሄደው የኮንሶ ምሁራን የምክክር ጉባኤ፣ በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ መጀመሩን የዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ይፋ አድርጓል። በምክክር መድረኩ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ፣ በዞን…»

Konso News

01 Sep, 10:49


የዕለተ ዓርብ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ሳምንታዊ አንኳር ዜናዎች፡

1) 3ኛው የኮንሶ ምሁራን የምክክር ጉባኤ በካራት ከተማ እየተካሄደ ነው

2) በቅርቡ የተመሠረተው አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የካቢኔ አባላቱን ዝርዝር ይፋ አደረገ

3) የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን በካድሬነት ሳይሆን በብቃታቸው ብቻ እንደሚመረጡ ተነገረ

Konso News

01 Sep, 10:49


https://podcasters.spotify.com/pod/show/konso-news/episodes/344------------Konso-News--Konso-News-Weekly-News-Digest-e28pred

Konso News

01 Sep, 10:46


የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን በካድሬነት ሳይሆን በብቃታቸው ብቻ እንደሚመረጡ ተነገረ
የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ከአሁን በኋላ በካድሬነት ሳይሆን፣ በብቃታቸው ብቻ እንደሚመረጡ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያለው ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 30ኛው ዓለም አቀፍ የትምህርት ጉባዔ፣ ‹‹ሁለንተናዊ ርብርብ ለትምህርት ተቋማት ደረጃ መሻሻል›› በሚል መሪ ቃል ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ከአሁን በኋላ የሚመረጡት በካድሬነት ሳይሆን፣ ባላቸው ብቃትና ችሎታቸው ላይ መሠረት ተደርጎ ይሆናል ሲሉ በመድረኩ ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሠረት በአገር አቀፍ ደረጃ በብቃታቸውና በችሎታቸው የተመዘኑ 1,600 የትምህርት አስተዳዳሪዎች ሥልጠና እንደተሰጣቸውና ይህ ዓይነቱ አሠራር ቀጣይነት እንደሚኖረው ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሳደግ ሥራ በተጨማሪ የመምህራንና ርዕሳነ መምህራን ብቃትና ችሎታ ማጎልበትም ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡
ትኩረት ካገኙ መሠረታዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤቶችን በግብዓትና በጥራት ከማሻሻል ባሻገር ክህሎት፣ ብቃትና ችሎታ ባላቸው ርዕሳነ መምህራን እንዲተዳደሩ ማድረግ ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል በተጨማሪ በዕውቀት ተማሪዎቻቸውን ተወዳዳሪ ማድረግ የሚችሉ መምህራንን ማብቃት ከተያዙ ግቦች መካከል አንዱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ባለፉት 30 ዓመታት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጥራት መውረዱን ገልጸው፣ በኑሮ ለተሻሉ ደግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩበት ሥርዓት መዘርጋቱን ተናግረዋል፡፡
ይህ ዓይነት አካሄድ በዜጎች መካከል በኑሮ ደረጃ ከተፈጠሩ ልዩነቶች አልፎ በትምህርት ዘርፍ ላይ መታየቱ ትልቅ ክስረት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ይህ አካሄድ በአገር አቀፍ ደረጃ አደገኛ ሁኔታዎች የሚፈጥር መሆኑን፣ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በገንዘብ ዕጦት ሳቢያ የትምህርት ጥራት ሊጓደልባቸው አይገባም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ትምህርት የአገር የሉዓላዊነት እሴት መለኪያ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ በዚህ ጉዳይ ለዓመታት የተቀለደበት ዘርፍ መሆኑን ጠቁመው አሁን እርስ በርስ መነጋገር የማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ የችግሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የትምህርት ዘርፍ መሠረታዊ መርሆዎች ሁለት መሆናቸውን ገልጸው፣ ዜጎች በብሔራቸውና በሃይማኖታቸው ሳይታዩ እኩል ጥራት ያለው ትምህርት የማግኘት መብታቸውን ማረጋገጥ አንደኛው መሆኑን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡
የትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች ከሁሉም እኩል ተወዳዳሪና ተፎካካሪ የሚሆኑበትን የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት፣ አሁን ያለውን የኢፍትሐዊነት ችግር በዘላቂነት መፍታት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ከአሥር ዓመታት በኋላ ትምህርት ቤቶች እንደ አሁኑ የፀብ (የረብሻ) መፍለቂያ ሳይሆኑ የመወዳደሪያና የብቃት ማጎልበቻ ይሆናሉ፡፡
ከዚህ በኋላ እንደ ከዚህ ቀደሙ ዲግሪ እንደ ከረሜላ የሚታደልበትን አሠራር አስቀርቶ፣ በብቃትና በችሎታ ብቻ ዜጎች ማዕረግ የሚያገኙበት ሥርዓት በዘላቂነት እንደሚዘረጋ ገልጸዋል፡፡
በሌላ ተያያዥ ዜና፣ የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን በሚንስትሮች ምክር ቤት የተወሰነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተሹመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመቱን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆኖ እንዲቋቋም በቁጥር 1294/23 የራስ ገዝ አዋጅ በረቀቀው መሰረትና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28፣ 2015 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ተከትሎ ነው፡፡

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ እንዲፈጽሙ እንዲሁም የሰው ሀብትና የፋይናንስ አስተዳደር ነጻነትን በማረጋገጥ በሀገሪቱ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የላቀ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ለማስቻል ነው፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ከተሾሙት ቻንስለር በተጨማሪም አዲስ የቦርድ አመራሮች የተሰየሙለት ሲሆን፣ ቦርዱም ዩኒቨርሲቲውን በሃላፊነት ሊመሩ የሚችሉ ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንቶችን በቀጣይነት ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።

Konso News

01 Sep, 10:45


በቅርቡ የተመሠረተው አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የካቢኔ አባላቱን ዝርዝር ይፋ አደረገ

በቅርቡ ለተቋቋመው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው የተሾሙት አቶ ጥላሁን ከበደ፣ ለ23 የካቢኔ አባላት ሹመት መስጠታቸው ተገለጸ።

የካቢኔ አባላቱ በርዕሰ መስተዳድሩ የተሾሙት፣ የአዲሱ ክልል ምክር ቤት ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው መሥራች ጉባኤው የካቢኔ ሹመት ኃላፊነቱን በውክልና ለርዕሰ መስተዳድሩ መስጠቱን ተከትሎ ነው ተብሏል።

ከካቢኔው አባላት መካከል 2ቱ ከኮንሶ ዞን መሆናቸውም ተመልክቷል። የቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ዶ/ር አንጋዬ ኦዳ፣ በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የእንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ በተመሳሳይ በቀድሞው ክልል ምክትል የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ገለቦ ጎልቶሞ በአዲሱ ክልል የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። የኮንሶ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ዳዊት ገበየሁ በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ረዳት የመንግሥት ተጠሪና የድርጅቱ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው፣ ከክልሉ የፊት አመራሮች አንዱ ሆነው መሾማቸው ይታወቃል።

በርዕሰ መስተዳድሩ የተሰየሙት የአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የካቢኔ አባላት የሚከተሉት ናቸው።
1) አቶ አክሊሉ ለማ የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ
2) አቶ ቢረጋ ብርሃኑ የኢንተርፕራይዝ ልማትና ሥራ ዕ/ፈ/ ቢሮ ኃላፊ
3) ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
4) ዶ/ር እንዳልካቸው ጌታቸው ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
5) ዶ/ር ቦጋለ ቦሼ የፕላን ቢሮ ኃላፊ
6) አቶ ብርሃኑ ዘውዴ የከተማና እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ
7) ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
😍 አቶ ግዛቴ ጊጄ የደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ
9) ዶ/ር ዋኖ ዋሎሌ የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
10) አቶ ሀ/ማሪያም ተስፋዬ የግብርና ቢሮ ኃላፊ
11) አቶ አብዩት ደምሴ የቴክኒካና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ
12) አቶ ተፈሪ አባተ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ
13) አቶ ታረቀኝ ሀብቴ የመስኖና ቆላማ አከባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ
14) አቶ ንጋቱ ዳንሳ የፐቢሊክ ሠርቪስ እና ሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
15) አቶ ተካልኝ ጋሎ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
16) አቶ አቤነዘር ተረፈ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
17) አቶ ገለቦ ጎልቶሞ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
18) ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
19) ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
20) አቶ አርሻሎ አርካል የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
21) ወ/ሪት ፍሬህይወት ዱባለ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
22) አቶ እንዳሻው ሽብሩ የጤና ቢሮ ኃላፊ
23) አቶ ወገኔ ብዙነህ የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

Konso News

01 Sep, 10:43


3ኛው የኮንሶ ምሁራን የምክክር ጉባኤ በዞኑ መዲና በካራት ከተማ እየተካሄደ ነው

ካለፉት ሦስት አመታት ጀምሮ በነሐሴ ወር የመጨረሻው ሳምንት በኮንሶ ዞን ዋና ከተማ ካራት ከተማ በየአመቱ የሚካሄደው የኮንሶ ምሁራን የምክክር ጉባኤ፣ በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ መጀመሩን የዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ይፋ አድርጓል።

በምክክር መድረኩ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ፣ በዞን መንግሥት የተከናወኑ ተግባራት አጭር ሪፖርትም አቅርበዋል። ምክትል አስተዳዳሪው በንግግራቸው “ለአንድነታችንና ለሰላማችን ሁላችንም ዘብ መቆም አለብን!” በማለት ለምሁራን ጉባኤው ጥሪ አቅርበዋል። “ሁላችንም ዘጠኝ ጎሳዎች ብንሆንም፣ ከአንድ አዳም የተገኘውን አንድ ዘር ነንና አንድነታችንን እናጠናክር፣ ለዚህም ፈጣሪም ይረዳናል” ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም የወረዳዎች የጽ/ቤት ህንጻ ግንባታዎችን አንስተው የካራት ዙሪያና የከና ወረዳ ግንባታዎች አሁንም በሂደት ላይ መሆናቸውን፣ ነገር ግን የኮልሜ ወረዳ የጽ/ቤት ህንጻዎች ግንባታ መጠናቀኑንም ለምሁራን ጉባኤው ገልጸዋል። ይህም አሁን ላይ ለኪራይ ወጪ የሚወጣውን ገንዘብ ወደ ልማት ለማዞር ዕድል እንደሚሰጥም ተናግዋል። አስተዳዳሪው የኮንሶ ተወላጆች ብሩህ አዕምሮ የታደሉ መሆናቸውንም በንግግራቸው ጠቅሰዋል። መድረኩም የመማማር፣ የምክክርና የአብሮነት እንዲሆን፣ እንዲሁም ጥላቻን የምንቀብርበትና ትውልድ ተሻጋሪ ሐሳቦችን የምንሸራሸሩበት እንዲሆን በመመኘት ንግግራቸውን ቋጭተዋል።

ከምክትል አስተዳዳሪው የመክፈቻ ንግግር በኋላ፣ ምክትል አስተዳዳሪው አቶ ገልገሎ ገልሾ፣ የኮንሶ ምሁራን የቦርድ ሰብሳቢና አቶ ጉማቸው ኩሴና የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የመንግሥት ተጠሪ ወይዘሮ ኤልሳጴጥ ተስፋዬ በጋራ በመሆን 3ኛው የምሁራን የምክክር ጉባኤው በይፋ መከፈቱን ኬክ በመቁረስ አብስረዋል።

ከዚያም በመቀጠል፣ ቀደም ሲል የተከናወኑ የምሁራን የምክክር መድረኮች፣ ዞኑ ያለፈባቸውንና አሁን የሚገኝበትን ነባራዊ ሁኔታን የሚገልጹ፣ በዞኑ ማህበረሰብና አስተዳደር ውስጥ የተስተዋሉ ችግሮች፣ ስለቀጣይ የዞኑና የአዲሱ ክልል አቅጣጫ የሚጠቁሙ፣ የምሁራን ሚናና ሌሎችም ሐሳቦች የተዳሰሱበት ሰነድ፣ በኮንሶ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ሠራዊት ዲባባ ቀርቧል።

ከዚያም በመቀጠል የኮንሶ ምሁራን ማህበር የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጉማቸው ኩሴ መድረኩን የተረከቡ ሲሆን፣ ከምክር ቤት አፈ ጉባኤ በመጀመር እስከ አጠቃላይ ምሁራን ድረስ ለሁሉም በየደረጃው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ፣ ከኮንሶ ውጭ ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ምሁራንን ተራ በተራ ለጉባኤው በማስተዋወቅ ሰላምታ አቅርበዋል።

በመቀጠልም ስለማህበሩ አመሠራረት አጭር ታሪክ ካቀረቡ፣ የማህበሩ ህጋዊ ጉዳዮችንም ከዳሰሱ በኋላ የ5 አመት ስልታዊ ዕቅድ ቀርቦ በመቀጠል የቡድን ውይይቶች እንደሚደረጉበት ገልጸዋል።

በምክክር መድረኩ የአንዳንድ የማህበሩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት፣ የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያዎች፣ የአባልነት መዋጮና ሌሎችም ጉዳዮች የሚወሰኑ ሲሆን፣የምሁራን የምክክር መድረኩ በነገውም ዕለት ይጠናቀቃል ይጠበቃል።

Konso News

24 Aug, 08:53


አስደሳች ዜና ለካራት ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ!
ኦኩማ ት/ቤት እነሆ እንደስሙ በጥበብ ልጆችን ለማነጽ የ2016 ዓ/ም ምዝገባን በይፋ ጀምሯል። በጥራቱ የተመሰከረለት ኦኩማን ምርጫዎ አድርገዉ ልጆዎን በሚመጥን ዘመናዊ ትምህርት ቤት ያስተምሩ። ከዶካቱ፣ አሮጌ ፣ካራት ከተማ በቀላሉ በትምህርት ቤቱ ተሽከርካሪ ልጆችዎን ወደ ትምህርት ቤትና ከትምህርት ቤት ተንከባክበን እንመልሳለን።
ኦኩማ የጥራት ማማ!