የሐዋሳ መካነ ኢየሱስ 63ኛ አመቷን አከበረች።
ቤተ ክርስቲያኗ የምስረታ የምስጋና ክብረ በዓሏን በወንጌል ስርጭት፡ የጀማ ስብከት እና በተለያዩ ኩነቶች ነው ያከበረችው።
ማህበርው ምዕመናኗ ያለፉት 63 አመታት በሐዋሳና አካባቢዋ ለሚገኙ ሲኖዶሶች፡ አብያተ ክርስቲያናት፡ ማህበረ ምዕመናን እና የሰበካ ጣቢያዎች መመስረት ምክኒያት ናት።
በተለይ በኮሙኒስት ማርክሲስት የክርስቲያኖች ስደት ዘመን ለበርካቶች መጠለያ ሆና ማሳለፍ ችላለች።
በምስጋና መርሃግብሩ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ ጠ/ጸሃፊ ቄስ ተሾመ አመኑ፡ ከሐዋሳ ህይወት ብርሃን ቤ/ክ መጋቢ ጌቱ አያሌው፡ ከሐዋሳ መሰረተ ክርስቶስ መጋቢ አስፋው መኩሪያ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
ቄስ ዶ/ር ገመቺስ ደስታ እና መጋቢ ሄኖክ መንግስቱ በእግዚዓብሔር ቃል፡ ዘማሪ አገኘው ይደግ፡ ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ እና ሌሎችም ተጋባዥ አገልጋዮች በምስጋና መርሃግብሩ አገልግለዋል።
የቤተ ክርስቲያኗን የ63 ዓመታት ጉዞ የመታሰቢያ ድንጋይ የቤተ ክርስቲያኗ ቀሳውስትና ተጋባዥ እንግዶች አኑረዋል።
ቤተ ክርስቲያኗ ከሐዋሳ ከተማ ምስረታ ሁለት ዓመታት በኋላ በ1954 በኖርዌጂያን ሉተራን ሚሽን ነው የተተከለችው።
በጸጋይብዛህ ኢሳያስ